የበረሃ አንበጣን በምስራቅ አፍሪካ አስከወዲያኛው ለመከላከል የሚያግዘው አዲሱ ሞዴል
-----------------------------------------------
ብዙዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን በ70 አመት ውስጥ እጅግ ከባድ የተባለለትን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በመፋለም ለይ ይገኛሉ፡፡ ይህ መንጋ በአካባቢው ላይ በሚያደረገው እንቅስቃሴ በዙ ሄክታር የሚሸፍኑ የእርሻ ሰብሎችን በአንዴ ድምጥማጡን በማጥፋት የምግብ ዋስትና ፈተናን እየደቀነ ያለ እና በሃገር ኢኮኖሚ ላይም ከባድ ጥፋት እያስከተለ የሚገኝ ነው፡፡ የአለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተው የበረሃ አንበጣ እስከ 2020 መጠናቀቂያ 8.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ጥፈት ሊያስከትል እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡
እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መንጋው በተስፋፋባቸው አካባቢዎች የኬሚካል እርጭት በማድረግ እና ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም ወረርሽኙን ለማስወገድ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የመንጋው ደረጃ በከፍተኛ የመራባት አቅም ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከእርምጃው በላይ እየደረሰ ያለው ውድመት እጅግ ከባድ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ ለረዥም ጊዚያት ምርምር ሲያደርጉ የቆዩ ተመራማሪዎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የበረሃ አንበጣ ጉዳትን ከመነሻው ለመሳጠር አንዲችሉ የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም የተከተለ አዲስ ሞዴል ይፋ አድርገዋል፡፡
በአለም አቀፍ የነፍሳት ፊዚዮሎጂ እና ኢኮሎጂ ማዕከል (ICIPE) የሚሰሩ ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ይፋ እንዳደረጉት የበረሃ አንበጣ የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል በመለየት ወረርሽኙ የሚያስከትውን ከፍተኛ አደጋ ከወዲሁ ማስቀርት እንደሚቻል በጥናታቸው ይገልፃሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚያስረዱት በምስራቅ አፍሪካ አከባቢ ያለው የመረጃ አያያዝ እጅግ ደካማ በመሆኑ የበረሃ አንበጣ መራቢያ ቦታዎችን በትክክል ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም በተገበሩት የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም አማካኝነት እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን ለመገመት የሚያስችል ሞዴል አበልፅገዋል፡፡
ተመራማሪዎች የተገበሩት ይህ አዲስ ሞዴል በአለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት በተመዘገቡ 9,134 በሚጠጉ የአንበጣው መራቢያ ቦታዎች በመተንተን የተከናወነ ሲሆን እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል ለመተንበይ የሚያስችልም የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም በምርምሩ ላይ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ይህ አልጎሪዝም በምስራቅ አፍሪካ ሊኖር የሚችለውን የአንበጣ መራቢያ ቦታ በትክክል ለመገመት የሚችለው የባዮ-ክላይሜቲክ ማለትም (የሙቀት እና የዝናብ መጠን) ተፅዕኖችን በመተንተን ሲሆን ከዛ በተጨማሪም የedaphic ወይም የአሸዋ እና እርጥበት ይዘቶች የሚያስከትሉትን ትፅእኖም በጋራ ይመለከታል፡፡ እነዚህ የአየር ንብረት ተፅእኖዎች እና የአፈሩ ባህሪዎች የበረሃ አንበጣው ለሚጥለው አንቁላልቅና ከዚህ ሂደት በኋላ ለሚኖረው የእንቁላል መፈልፈል ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡
ከዚህ በፊት የተመዘገቡት አብዛኛቹ የመራቢያ ቦታዎች እንደሚያሳዩት ብዙዎች የመራቢያ አከባቢዎች ከ40 እስከ 80 ሚሊዮን የበረሃ አንበጣዎችን በአንድ ስኬር ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ይዘው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የበረሃ አንበጣ መፈልፈያ አካባቢዎች በመሆናቸው የክትትል አቅምን በማሳደግ በአጭር ጊዜ፣ በትንሽ ወጪ እና አከባቢን በማይጎዳ መልኩ የበረሃ አንበጣውን እስከወዲያኘው ማስወገድ የሚቻልበት መንገድ ነው፡፡
ተመራመሪዎች የተገበሩት አዲሱ ሞዴል የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝምን በመተግብር እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን የሚለይ እና እሱንም በካርታ መልክ የሚያስቀምጥ በመሆኑ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚከሰተውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በቀላሉ ለመከላከል እና ውድመቱ ከፍተኛ ደረጃ ሳይደረስ ከመነሻው ለማቆም በእጅጉ የሚያግዝ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩ ሙከራዎች እና የትብብር ስራዎች የበረሃ አንበጣ ወደ ምስራቅ አፍሪካ በሚገባባቸው አካባቢዎች እና በሚፈለፈልባቸው ቦታዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች የሚከናወኑ ቢሆንም የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል ተገንዝቦ መፍትሄ የሚጠቁም ባለመኖሩ፤ የማዕከሉ የምርምር ውጤት ከዚህ ቀደም ከነበሩት በተሻለ ሁኔታ ጉዳቱን ለመቀነስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
ይህ ምርምር በሞዴሉ አማካኝነት የለያቸው የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መራቢያ ቦታዎች ኬኒያ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ቢሆኑም በውስጣቸው የሚገኙ አያሌ የሰፈር ቦታዎች በካርታው ተገልፀው የሚገኙ ናቸው፡፡ እንደካርታው ማብራሪያ ከሆነ የኬኒያ እና የሱዳን ሰፊ ቦታዎች ዋና የመራቢያ አካባቢዎች ተደርገው የተቀመጡ ሲሆን ከዛ ባለፈም የኡጋንዳ ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች እና የደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ክልሎች የበረሃ አንበጣው ዋና የመራቢያ ቦታዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
በናይሮቢ መቀመጫውን ያደረገው ይህ የምርምር ማዕከል በምክረ ሃሳብ ደረጃ በሚያስቀመጣቸው ቀጣይ እርምጃዎች መሰረት እና ከማዕከሉ ጋር በሚኖር ግንኙነት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ የሚገኘውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ እስከወዲያኘው ለመከላከል በንቃት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም በዚህ የአሰራር ሞዴል በመታቀፍ በትብብር እንዲሱሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ምንጭ፡ International Centre of Insect Physiology and Ecology (icipe) እና theconversation

በበረሀ ተተክሎ የተገኘው ምስጢራዊ አንጸባራቂ አምድ
**************************
እንደ ማርስ በቀላው የዩታ በረሀ (Utah desert) ሚስጢራዊ የሆነ አንጸባራቂ የብረት ምሰሶ ተገኘ፡፡ ይህ ለስላሳና ረጅም ቅርጽ ያለው የብረት ምሰሶ የተገኘው በ ዩታ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የሒሊኮፕተር አሰሳ ሲደረግ እንደ ሆነ የግዛቷ ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡
የዩታ አካባቢ ደህንነት ክፍል አባላት አሰሳ በሚያደርጉበት ወቅት ያለፈው ህዳር 18 አንጸባራቂውን አምድ ማንም ይደርስበታል በማይባል በረሀ ውስጥ ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
የተገኘው ብረት የማይዝግ የብረት አይነት ሲሆን የሁለት ሰዎች ያክል ቁመት አለው፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ነገር ማን ለምንና እንዴት ወደዚህ በረሀ እንዳመጣው ምንም ፍንጭ አልተገኘም፡፡ የአሰሳ ቡድኑ የተገኘው የብረት አምድ ከሌላ አለም የመጣ ነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል፡፡
ብረቱ የተገኘበት ትክክለኛ አካባቢ በጣም ሩቅና በረሀ በመሆኑ ምክንያት ሰዎች ለማየት ብለው እንዳይጠፉ ሲባል ባበለስለጣናት አልተገለጸም፡፡ የአካባቢው መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች ብረቱ ለምን ያክል ጊዜ ቦታው ላይ እንደተቀመጠና ማን ወደዚህ እንዳመጣው እያጠኑ ነው፡፡
ምንጭ The Independent

በአፍሪካ ትልቁ የኮቪድ-19 ሙከራ ሊደረግ ነው
==================
ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ አጥኚዎች ጋራ በመሆን በአህጉራችን ትልቁ የሆነውን የኮቪድ-19 ህክምና ሙከራ ሊያደርጉ ነው፡፡ አንቲኮቭ የተሰኘው ጥናቱ በቤልጂየም፤ አንትወርፕ ከሚገኘው የትሮፒካል ህክምና ኢንስቲትዩት እና ሌሎች አለም አቀፍ የጥናት ኢንስቲትዩቶችንም ያካተተ ሲሆን ኮቪድ-19 ገና ያልጠናባቸውን ታማሚዎች በጊዜ በማከም ወደ በሆስፒታል አልጋ እንዳይርሱ እና ቀድሞውንም በችግር ውስጥ የሚገኘውን የአፍሪካ የጤና ስርዓትን ለባሰ ምስቅልቅል እንዳይዳርግ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
የክሊኒካል ሙከራው በ13 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ባሉ 19 ስፍራዎች የሚደረግና ከአፍሪካ በተውጣጡ ሀኪሞች የሚመራም ነው፡፡ ይህ ጥናት በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የተስማሙ የኮቪድ-19 እርምጃዎች እንዲወሰዱና ለእነዚህ ሀገራት የጤና ስርዓት የሚቀርበው በቂ ያልሆነ ድጋፍ እንዲስተካከል የሚጠይቁ ጥሪዎችን መቅረባቸውን ተከትሎ የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡ የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ የአፍሪካን ጥያቄዎች የሚመልስ አፍሪካ ተኮር የክሊኒካል ሙከራ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው አዲሱ ሙከራ በአፍሪካ የኮቪድ-19 መከልከል እና ህክምና ላይ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ አክለውም የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን በጣም ጥሩ ምላሽ ለኮቪድ-19 የሰጡ ቢሆንም አሁን ጊዜው ለቀጣይ የወረርሺኙ ማዕበሎች የምንዘጋጅበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ይህ ጥናት በኢትዮጵያ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ፣ ጋና፣ ኬኒያ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ሱዳን እና ዩጋንዳ ውስጥ ያሉ ከሁለት እስከ ሦስት ሺህ በቀላል እና መካከለኛ ህመም ደረጃ ላይ የሚገኙ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ላይ የሚከናወን ህክምናን ይገመግማል፤ በዚህም ህመሙ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይደርስ የሚያደርጉና ተላላፊነቱንም የሚገድቡ ህክምናዎችን እንደሚለይ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ በካንሰር መድሃኒቶች ላይ ተተግብሮ የነበረውን እና የተለያዩ ህክምናዎች በአንድ ጊዜ እንዲሞከሩ የሚያደርገውን የአዳፕቲቭ ክሊኒካል ሙከራ ስልት እንደሚጠቀም ታውቋል፡፡ ይህም ቆጠራ፣ እተከናወኑ ባሉ ትንተናዎች ላይ በመመስረት ህክምናውን ማቆም እና ሌሎችንም ጨምሮ ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲተላለፉ የሚያስችል ነው፡፡
የትሮፒካል ህክምና ኢንስቲትዩት ለብዙ ዓመታት በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጋሮቹ ጋራ ሲሰራ መቆቱን ያወሱት የተቋሙ ባልደረባ ፕ/ር ዮሀን ቫን ግሪንስፌን በአህጉረ አፍሪካ በቂ የህክም ቁሳቁሶች እና ባለሙያዎች ያሉባቸው የከፍተኛ ክትትል ክፍሎች ጥቂት ከመሆናቸው ጋራ ተያይዞ ይህ ጥናት የሚሰጣቸው ምላሾች የጤና ስርዓቱን ይባስ ወደ መጨናነቅ እንዳይገባ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡
በዚህ ሙከራ ላይ በመጠነኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ የቫይረሱ ታማሚዎችን በማከም ረገድ ያላቸውን አቅም ለማወቅ ይረዳ ዘንድ አዳዲስ ህክምናዎች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ በዚህም የኤች.አይ.ቪ ጸረ ቫይረስ ውህድ የሆነው ሎፒናቪር-ሪቶናቪር እና በአሁኑ ሰዓት በአፍሪካ ያሉ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ለማከብ በብዛት እየዋለ ያለውን ሀይሮክሲሎሮኩዊን የተሰኘውን የወባ መድሃኒት በመሞከር የሚጀምር ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ባትሪ መዋጥ እና የልብ ድካም ምን አገናኛቸው
==================== የህክምና ባለሙያዎች በድንገተኛ ክፍል የተገኘውን ግለሰብ በኢ.ሲ.ጅ ወይም (Electrocardiography) ሲመለከቱት ወደ ልቡ የሚዘዋወረው ደም ተቋርጦ ወይም የልብ ድካም ደርሶበት ያገኙት ቢመስልም የችግሩ መነሻ ሲጣራ ግን ግለሰቡ የባትሪ ድንጋይ በመዋጥ ከፍተኛ የልብ ችግር በራሱ ላይ እንደፈጠረ ደርሰውበታል፡፡ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ በግለሰቡ ሆድ ውስጥ ባትሪው ተቀምጦ ስለነበረ የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በሚለካው ኤሌክትሮ ካርዲዮግራም ወይም (EKG) በሚለኩት ጊዜ የልብ ምቱ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መደበኛ ሂደት ላይ እንዳልነበረ ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ይህ መሳሪያ በእያንዳንዷ የልብ ምታችን ወቅት በልባችን የሚዟዟረውን የኤሌክትሪክ ግፊት ወይም ሞገድ የሚለካ መሳሪያ ሲሆን ይህ የኤሌክትሪክ አንቅስቀሴም የልብን የደም ዝውውር ሂደት በዋናነት የሚያሳልጥ ነው፡፡ በዚህ መሳሪያ ምርመራ የተደረገለት ይህ ግለሰብ በሰውነቱ ውስጥ በነበረው የባትሪ ድንጋይ የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ ምክንያት የልብ ድካም ምልክቶች እንዳሉበት ሰው ሁሉ በኤሌክትሮ ካርዲዮግራሙ መለኪያ ላይ ይህን የልብ ድካም ምልክት ሊያሳይ ችሏል፡፡ ይሁንና የህክምና ባለሙያዎቹ ግለሰቡ የዋጠውን አንድ ባትሪ ከሰውነቱ ካወጡለት በኋላ የልቡ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ወይም (EKG) ልኬት ወደመደበኛ ሂደት መመለሱ እጅግ አስገራሚ ሆኗል፡፡
የ26 አመት ወጣት የሆነው ይህ ግለሰብ ሳንታ ማራ በተባለው የጣሊያን ሆስፐታል ከትትል ሲደረግልት የቆየ ሲሆን በማረሚያ ቤት በነበረበት ጊዜ AA የተባለውን የባትሪ ድንጋይ ሆንብሎ እንደዋጠም ተነግሯል፡፡ የግለሰቡ ኤሌክትሮ ካርዲዮግራም ውጤት የልብ ድካም መስሎ የታየበት ሁኔታ በህክምና ቃሉ "ST segment elevation" ተብሎ የሚጠራ መሆኑን የሚናገሩት የህክምና ባለሙያዎች ይህም ባትሪው በሆድ ውስጥ ከሚገኝ ጋስተሪክ አሲድ (gastric acid) ጋር በሚፈጥረው ግንኙነት ወደልብ የሚሄድ አሌክትሪክ ከረንት በሚፈጠርበት ጊዜ የሚከሰት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በኒው ዮርክ የሳንድራ አትላስ የልብ ሆስፒተል የሚሰሩት ዶ/ር ጋያ ሚንትዝ አንደሚያስረዱት ማንም ሰው አንድም ይሁን ብዙ ባትሪ በሚውጥብት ግዜ መሰል ሁኔታዎች የመፈጠር እድል እንዳላቸው ገልፀው ብዙ የህክምና ባለሙያዎች ግን ይህን ክስተት በሚገባ ያውቃሉ ብለው እንደማይገምቱ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩ ልምዶች ስድስትና ከዛ በላይ ባትሪዎችን የዋጡ ሰዎች ይህን መሰል አደጋ አጋጥሟቸው እንደነበር የሚናገሩት ዶ/ር ሚንትዝ አንድ ባትሪ የዋጠው የዚህ ግለሰብ አጋጣሚ ግን እጅግ እንዳስገረማቸው ገልፀዋል፡፡ ወጣቱ ባትሪውን ከዋጠ በኋላ በእርግጥም የልብ ጥቃት ያስከተለበት ባይሆንም የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴው ድንግት ረዘም ላለ ጊዜ ቢቆይ ከፍተኛ የልብ ችግር ይፈጠር እንደነበር እና ከዛ በላይ ደግሞ ባትሪው ተሰብሮ የኬሚካል ሊኬጅ ቢከሰት ህይወትን እስከማሳጣት ሊደረስ እንደሚችል ዶ/ር ሚንትዝ ይናገራሉ፡፡ ምንጭ፡ Live Science

የዲጂታል ላይብረሪ፤ ለምን? Why digital libraries?
=================
የዲጂታል ላይብረሪ አተገባበር የመረጃ አደረጃጀት፣ የመረጃ አስተዳደር፣ የመረጃ አመላካቾች፣ የመረጃ ማስፈንጠሪያዎችን እንዲሁም የመረጃ አጠቃቀምን በማካተት የሚከወን ተግባር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል ላይብረሪን ቢጠቀሙ ምን ያተርፋሉ፡-
• በየትኛውም ስፍራና ቦታ
• የ24 ሰዓት ያልተገደበ አገልግሎት
• ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት
• የተደራጀ ይዘት
• ያልተገደበ የመረጃ ምንጭ
• ዘላቂ ግልጋሎት
• አማራጭ ክምችት
• የተቀናጀ የመረጃ ትስስር
• ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ አገልግሎቱን ማግኘት ያስችልዎታል፡፡
እንግዲያውስ ለወዳጅ ዘመድዎ፣ ለተማሪዎችና አገልግሎቱ ለሚያሻቸው በማስተዋወቅ በጋራ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
ይህን ሊንክ በመጫን ብቻ የዲጂታል ላይበረሪያችንን በቀጥታ ሊያገኙት ይችላሉ http://library.techin.gov.et/web/dl-site/home
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት

የሞባይል ባትሪ እድሜን የሚያሳጥሩ ምክንያቶች
=====================
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) የተሰራ ሲሆን ይህንንም በአግባቡ ካለመያዛችን እና ካለመጠቀማችን የተነሳ ባትሪው መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ እንዲደክም ያደርገል፡፡ ይህም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡
የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው የሚሰሩ ቢሆንም ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ እድሜያቸውን የሚቀንስ እና ባትሪውን በተሻለ ሁኔታ እንዳንገለገል የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያች በአጠቃቀማችን ላይ ይስተዋላሉ፡፡
ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው ነጥቦች የሞባይል ባትሪን እድሜ ሊያሳጥሩ የሚችሉ ናቸው
*የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር መጠቀም (ይህ ድርጊት ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ወይም የቮልቴጅ አለመመጣጠን በመፍጠር ባትሪውን ሊጎዳብን ይችላል )
*ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ ለኢንተርኔት ለጌም እና ለተለያዩ ነገሮች መጠቀም (ይህ ድርጊት የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹም አደጋ ሊያስከትል ይችላል)
*ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ማድረግ ወይም ጃርጅ ላይ ሰክቶ ማሳደር (የሞባይል ባትሪ 100 ፐርሰንት ሞልቶ ያማይነቀል ከሆነ ከመጠን ባለፈ ሙቀት እንዲጎዳ እና የቮልቴጅ ጫና ሊፈጠርብት ይችላል)
*ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ መጠበቅ (የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ በቶሎ የሚያሳጥር ነው)
*ከእነዚህ በተጨማሪ በስልክ አጠቃቀሞ ባትሪውን የሚያወርዱ መቼቶችን አለማስተካካል (ለምሰሌ ከፍተኛ የብራይትነስ መጠን፣ የሎኬሽን (Location) መብራት፣ መተግበሪያዎችን ያለማስተዳደር (Monitor Apps) እና አልፎ አልፎ የሞባይል ስልክ አለማጥፋት ባትሪውን የሚጎዱ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ MAKE USE OF

ጉግል ቆዳን እንደ ተችፓድ (touchpad) የሚያስጠቅም ስማርት ንቅሳቶች ላይ እየሰራ ነው
********************************************
በሀገራችንም ሆነ በሌሎች የአለም ክፍሎች ንቅሳትን ለውበትና የጥበብ ስራዎች በሰውነታችን ለማስፈር መጠቀም በጣም የተለመደ ነው፡፡ ግዙፉ የጎግል ተቋም ከጀርመን የሳርላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ጊዜያዊ የሆነን ንቅሳት በመንቀስ ቆዳችንን በመንካት የሚሰራ የቴክኖሎጂ ቁስ (fully-functional touchpad) ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡
ይህ SkinMarks በመባል የሚታወቀው ፕሮጀክት ከ2017 ጀምሮ እየተሰራ ሲሆን መሰረታዊ ሀሳቡም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንደ ምልክትና መንካት ባሉ ተፈጥሯዊ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ለመጠቀም ነው፡፡
SkinMarks የንቅሳት ቴክኖሎጂ በጣም ስስ የሆነ ውፍረት ያለው ንቅሳት ሲሆን በቆዳችን ልክ መለጠጥ የሚችል ነው፡፡ ንቅሳቱ የሰውነታችንን እንቅስቃሴ የሚረዳ ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ አተገባበሩም ከ skin electronics እና epidermal electronics መሰረታዊ ሀሳብ ጋር የተዛመደ ነው፡፡ እነዚህም ቆዳን ለኮምፒውተርና ለሰው ተግባቦት የግንኙነት መስመር የሚሆኑ ናቸው፡፡
ምንጭ InceptiveMind

ዛፎችን እንትከል ወይስ በራሳቸው ይደጉ
*****************************
ከሰባት ዓመታት በፊት ሱዛን ኩክ-ፓተን ደኖችን መልሶ በማብቀል ላይ ያተኮረ የድህረ ዶክትሬት ጥናቷን በሜሪላንዱ ስሚትዞኒያን የአካባቢ ጥናት ማዕከል ውስጥ በምታከናውንበት ወቅት 20 ሺህ ያህል ችግኞች እንዲተከሉ መርዳቷን ትናገራለች፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ማስተዋል ቻለች፤ በብዛት ፀድቀው የተገኙት የተተከሉት ችግኞች ሳይሆን በራሳቸው የበቀሉት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት መትከላቸውን እንዳቆሙ እና ወዲያው ሌሎች ብዙ እፅዋት በአካባቢው መብቀል መጀመራቸውን ታወሳለች፡፡ ታድያ ይህ ምናልባትም በሌሎች አካባቢዎች ላይም እውነት ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ችግኝ መትከል እጅግ እየተዘወተረ የመጣ ተግባር ሆኗል፡፡ በቅርቡ ስዊዘርላንድ ውስጥ የተካሄደው የአለም ምጣኔ-ሐብት ጉባኤ አንድ ትሪሊዮን ዛፎች እንዲተከሉ ጥሪውን አስተላልፎ ነበር፡፡ ኢትዮጵያም ባሳለፍናቸው ሁለት ክረምቶች በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ለመትከል አቅዳ በስፋት ስትንቀሳቀስ መቆየቷ ይታወሳል፡፡ ይህ ዛፎችን የመትከል እንቅስቃሴ ታድያ እንደ አንድ ተፈጥሮ ላይ የተመረኮዘ የአየር ንብረት ለውጥን መቀልበሻ መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ሆኖም ዛፎችን በስፋት የመትከሉ እንቅስቃሴ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል፡፡ ጥያቄው የዛፎች መኖርን የሚቃወም ሳይሆን ችግኝ ተከላው የሚደረግባቸው አካባቢዎች ብዙውን ጊዜ ቶሎ በሚያድጉ ግን ደግሞ ለአካባቢው እንግዳ በሆኑ የዛፍ ዝርያዎች እየተሸፈኑ ናቸው ሲሉ ይህን ተግባር የሚተቹ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ተፈጥሮ ከማንም በላይ ለራሷ የሚስማማትን ታውቃለች እና አካባቢውን በቅርብ ለሚገኝ ደን ትተን ስፍራው ለራሱ የሚስማማውን አብቅሎ ዳግም እንዲለመልም አንተወውም በማለት ችግኝ የመትከልን አስፈላጊነት ይጠይቃሉ፡፡
ሱዛን ከ17 ትምህረት እና በከባቢ ላይ ከሚሰሩ ተቋመት ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋራ በመሆን በሰራችው ጥናት መሰረት ተ.መ.ድ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ጭምር ድጋፍ ያገኘው ይህ ደኖች በተፈጥሮ እንዲያድጉ በማድረግ ካርበንን የመሰብሰቡ እንቅስቃሴ ከሚፈለገው በታች ሆኖ አነስተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡
ጥናቱ ደኖች የት የት በራሳቸው ማደግ እና ካርቦንንም መሰብሰብ ይችላሉ የሚለውን በማጥናት ረገድ ፈር ቀዳጅ ነው፡፡ በዓለም ዙርያ ከተጠኑ 250 ጥናቶች ላይ 11 ሺህ ያህል ደኖችን ዳግም በማብቀል ካርቦንን የመሰብሰብ እርምጃዎችንንም መመልከቱ ተግጿል፡፡ እንደ ጥናት ቡድኑ ከሆነ ከከባቢ አየር ላይ ያለ ካርበንን የመሰብሰቡ ተግባር ዛፎቹ በሚተከሉበት አካባቢ አየር ንብረት፣ አፈር፣ ከባህር ጠለል በላይ ያለ ከፍታ እና የአካባቢው አቀማመጥ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ተፅዕኖ ስር ይወድወቃል፡፡ በዚህ ምክንያትም ከሀገር ሀገርም የተለያዩ ውጤቶች ታይተዋል፡፡ በመጨረሻም የዛፎች መተከል ለከባቢው ጥሩ ነገርን ይዞ መምጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ካርበንን በፍጥነት እና በመልካም ሁኔታ በመሰብሰብ ረገድ ግን ተፈጥሮ ዳግም ያበቀለቻቸው ደኖች በሰው ልጅ እጆች ከተተከሉት አንፃር የተሸሉ መሆናቸው ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ምንጭ፡ WIRED

የአለማችን ግዙፉ የነፋስ ሐይል ማመንጫ በእንግሊዝ የውሀ አካል ላይ ሊገነባ ነው
----------------------------------
SSE Plc የተባለ የኖርዌይ ድርጅት እና ASA የተባለ ሌላ ድርጅት በአለማችን በግዝፈቱ የመጀመሪያ የተባለውን የነፋስ ሐይል ማመንጫ በሰሜን ውቅያኖስ ላይ ለመገንባት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በእንግሊዝ የምስራቅ ባህር ዳርቻ የሚገነባው ይህ ግዙፍ የነፋስ ሐይል ማመንጫ ሰማይ ጠቀስ የሆኑ ምሶሶዎች ሲኖሮት ከእንግሊዝ አመታዊ የሀይል ፍላጎት ውስጥም 5 በመቶ የሚሆን ወይም ለስድስት ሚሊዮን ቤቶች የሚያገለግል ታዳሽ ሀይል እንደሚያቀርብ ታስቧል፡፡
ይህ ውሳኔም የአውሮፓ ህብረት ለዘርፉ 940 ቢሊዮን ዶላር በማጽደቁና ጠቅላይ ሚንስቴር ቦሪስ ጆንሰን የታዳሽ ሐይል ዘርፍን ለመደገፍ ካወጡት የአረንጓዴ እቅድ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በመጀመሪያዎቹ የፕሮጀክቱ ሁለት ዙሮች በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን ከስምንት ቢሊዮን ዶላር በላይ ተበጅቷል፡፡ ሀገሪቱ ከታዳሽ ምንጭ የምታገኘውን የሀይል አቅርቦቷን በ2030 ወደ 40 gigawatt-hours ለማሳደግ አቅዳለች፡፡
ይህ ሶስት የግንባታ ምእራፎች ያሉት ስራ እያንዳንዱ ምእራፍ 1,200 MW የማመንጨት አቅም እንዳለው ተነግሯል፡፡ ለግንባታውም የሚሆኑ 248 ሜትር ርዝማኔ ያላቸው 190 ምሰሶዎች እና ተርባይኖች እንዲመረቱ ታዘዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሁለት የግንባታ ምእራፎች ጎን ለጎን የሚከናወኑ ሲሆን ሶስተኛውና የመጨረሻው በሌላ ጊዜ እንደሚከናወን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ግንባታውም በ2026 ይጠናቀቃል ተብሎ የታቀደ ሲሆን ፍጻሜ ሲያገኝ በውሀ ላይ የተሰራ የአለማችን ግዙፍ የነፋስ ሀይል ማመንጫ ይሆናል ተብሏል፡፡ መረጃውን ከ Bloomberg Green አግኝተነዋል፡፡

ሰው የተራበ አዕምሮ
--------------------
ብዙ ጊዜ ረሀብ በሚጠምደን ጊዜ አዕምሮአችን ስለ ምግብ ያስባል፤ በብቸኝነት ውስጥ ስንሆንም በተመሳሳይ አዕምሮአችን ሰው ይርበዋል፡፡ ለአንድ ቀን ማንንም ሳናይ ብንቆይ የተራበ ሰው አንጎል ምግብ እንደሚታየው ሁሉ ብቸኝነቱም ማህበራዊ መሰብሰቦችን መላልሶ እንደሚታየው ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡
የኮግኒቲቭ ኒሮሳይንቲስቷ ሊቪያ ቶሞቫ እና ባልደረባዎቻቸው 40 ያህል ተሳታፊዎችን ለ10 ሰዓታት ያህል እንዲፆሙ አድርገዋቸው ነበር፡፡ በዕለቱ መጨረሻ ላይ የፋንክሽናል MRI (fMRI) ስልትን በመጠቀም የተሳታፊዎቹን ሚድብሬን የተባለ አንጎል ክፍል ውስጥ ያሉ አንዳንድ ነርቮች የፒዛ እና ቸኮሌት ኬክ ምስል ማሳት ጀመሩ፡፡ እነዚህ ኔሮኖች ከምልሰት ጋራ የተያያዘ ኬሚካላዊ መልዕክት አስተከላላፊ የሆነውን ዶፓሚንን ያመርታሉ፡፡ በሌላ ቀን እነዚሁ 40 ተሳታፊዎች ለ10 ሰዓታት ያህል ከማንም ጋራ በየትኛውም መንገድ (የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ) ሳይገናኙ እንዲቆዩ ተደረጉ፡፡ በኋላ ላይ ለማየት እንደተቻለውም ቀድሞ በተገለፀው አካባቢ ላይ ያሉ ኒሮኖች ሰዎች ቻት ሲያደርጉ እና የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሲያከናውኑ የሚያሳይ ምስለ ምልሰትን አሳይተዋል፡፡ ታድያ ረሃቡ ሲጠና ወይም ብቻቸውን ተገልለው የሚቆዩበት ጊዜ በረዘመ ቁትር የሚያሳዩት ምልሰትም በዚያው መልኩ እያየለ መጥቷል፡፡ በዕለት ተዕለት ህይወታቸው ብዙውን ጊዜ በብቸኝነት የሚያሳልፉት ተሳታፊዎች ማህበራዊ ላይ ታድያ ምላሾቹ አነስተኛ መሆናቸውን አጥኚዎቹ መመልከት ችለዋል፡፡ ይህ ከምን እንደተነሳ በሳይንሳዊ መልኩ ማብራራት ባይቻላቸውም ምናባትም በእለት ተዕለት ህይወታቸው የተላመዱት ነገር ስለሆነ ሊሆን ይችላል የሚል ግምትን ወስደዋል፡፡
የእኛ የሰው ልጆች የምግብ፣ ጓደኛ፣ ቁማር ወዘተ…. ፍላጎታችንን የሚያነሳሳው ሚድብሬን የተሰኘው የአንጎላችን ከፍል ብቸኛ ሳንሆንም ሆነ ምግብ ሳይርበን ምልሰቶችን ሊሰጥ ይችላል፡፡ እኛም ቢሆን ሁል ጊዜ ልንበላ እና ልንጫወት እንችላለን፡፡ ሆኖም ረሀብ እና ብቸኝነት ምላሹን የሚጨምረው ሲሆን እነዚህ ምላሾችም ባጣነው ነገር ዙርያ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ጥናት በተለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ተከትሎ ከቤታቸው የዋሉ ሰዎች ለአካላዊም ሆነ አዕምሮአዊ ጤና እንዲጋለጡና ከምግብ በላይ ሌሎች ነገሮችን እንዲራቡ ሊያደርግ ስለሚችል ቀውሱን ከማህበራዊ እይታ አንፃርም መመልከከት እንደሚገባ በማሳያነት ቀርቧል፡፡
ምንጭ፡ Science News

የድምጽና የብርሀን ብክለት አዕዋፋት ላይ ያለው ከባድ ተፅዕኖ
*********************
በካሊፎርኒያ ፖሊቴክኒክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የተደረገ አንድ ጥናት ሰዎች የሚፈጥሩት የድምጽና የብርሀን ብክለት በአእዋፋት የመራባት ስርዓት ላይ ክፍተኛ ተጽእኖ እንዳለው አመለከተ፡፡ የናሳን የሳተላይት መረጃ በመጠቀም የምርምር ቡድኑ በሰሜን አሜሪካ እንዴት የድምጽና የብርሀን ብክለት የአእዋፋትን የመራባት ሂደት እንደሚጎዳው አጥንተዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት የአለማችን የአእዋፋት ዝርያዎች በ30 በመቶ እየቀነሰ መምጣቱ ይነገራል፡፡ ይህ የቁትር መቀነስ በምን ምክንያት እንደሆነ ተመራማሪዎች ሲያጠኑ የቆዩ ሲሆን ከብዙ ምክንያቶች አንዱ የብርሀንና የድምጽብክለት እንደሆነ በተደረገው ምርምር ታውቋል፡፡
በምርምሩ ላይ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በሰዎች ምክንያት ከሚደርሱ ሌሎች ጉዳቶች በላቀ መልኩ የድምጽና የብርሀን ብክለት በአእዋፋት የመራባት ሂደት ላይ ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር ገልጸዋል፡፡
የምርምር ቡድኑ በሰሜን አሜሪካ ካሉ 142 የወፍ ዝርያዎች ውስጥ 58,506 እንዴት በድምጽና በብርሀን ምክንያት መራባት እንዳልቻሉ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን ተጠቅሞ ጥናቱን አካሂዷል፡፡ የወፎች እንቅስቃሴ ከንጋትና ከብርሀን ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ማለት በመጀመሪያው የንጋት ብርሀን ወፎች ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ምግብ ፍለጋ ከጎጇቸው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በጥናት እንደተረጋገጠው በሳር ምድር ወይም በርጥበታማ አካባቢ የሚኖሩ አዕዋፋትን የብርሀን ብክነት አንድ ወር ያክል ቀድመው ለምግብ ፍለጋ ከጎጇቸው እንዲወጡ ያደርጋቸዋል፡፡ እደሚታወቀው ወፎች ራሳቸውን የሚተኩት በጎጇቸው በሚቀመጡበት ወቅት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የፕላኔታችን ሙቀት በጨመረ ቁጥር የአዕዋፋት ምግብ ከመደበኛ ጊዜው ፈጥኖ ይደርሳል፡፡ ይሁን እንጂ አዕዋፋቱ የሚጠብቁት የምግብ ስብሰባ ጊዜ ስላለ ሳይታሰብ የወቅት አለመገጣጠም መጣና ምግብ ሳያገኙ ይቀራሉ፡፡ ይህም ለቁጥራቸው መቀነስ ምክንያት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ አንድ ወፍ ብርሀንን ቀድሞ ባየ ቁጥር ቀድሞ ለምግብ ስብሰባ ከጎጆው ይንቀሳቀሳል፡፡
ምንጭ፡ NASA SCIENCE