ቀኑ የከፋበት በጎ ሰው
-------------------
ለበጎ አድራጎት ስራ ወደ ህንድ ያቀና አንድ ብሪታንያዊ በወባ፣ ዳንጊ ትኩሳት፣ እና ኮቪድ-19 መጠቃቱ አልበቃ ብሎ መርዛማ በሆነ የኮብራ ዕባብ ተነድፎ ከፍተኛ የጤና እክል ውስጥ ይገኛል፡፡ እነዚህ ሁሉ አደገኛ በሽታዎች ያጋጠሙት ኢያን ጆንስ የተባለው ይህ ግለሰብ በምዕራባዊው የህንድ ክፍል በምትገኘው ራጃስታን ግዛት ውስጥ ባለች አንዲት መንደር ውስጥ ነው እጅግ አደገኛ በሚባል እባብ ለመነደፍ የበቃው፡፡ ምንም እንኳን ግለሰቡ ከተነደፈ በኋላም በህይወት መትረፍ ቢችልም አሁን ላይ ግን ማየት እንደተሳነው እና እግሮቹም ፓራላይዝድ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡
ከደቡባዊ እንግሊዝ አይል ኦፍ ዌይት ደሴት የመጣው ግለሰቡ ለሁለት ሳምንታት ያህል በከፍተኛ ክትትል ውስጥ የቆየ ሲሆን አሁን ግን በህንድ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች መብዛትን ተከትሎ ባጋጠመው የአልጋ ማነስ ሳብያ ሆስፒታሉን ሊለቅ ተገዷል፡፡ አያን ጆንስ በሁኔታው ከፍተኛ ፍርሀት ያደረበት ቢሆንም ሀኪሞቹ ሙሉ በሙሉ መዳን እንደሚችል ተስፋ አድርገዋል፡፡ “አባቴ ብርቱ ነው፤ በህንድ ቆይታው ከኮቪድ 19 በፊትም በወባ እና አደገኛ ትኩሳት ተይዞ ነበር” ሲል ልጁ ሰብ ጆንስ እነዚህ የጤና እክሎችን ተከትሎ ከሀገር እንዳይወጣ ያገደው ከፍተኛ የህክምና እዳን በመክፈል ዳግም ወደ እንግሊዝ ለመመለስ በተጀመረው የጎ ፈንድ ሚ እንቅስቃሴ ላይ ተናግሯል፡፡ እነዚህን በሽታዎች እየታገለ ሳለ ለህይወቱ አስጊ በሆነ ሁኔታ በእባብ መነደፉን ሲሰሙ ማመን እንዳቃታቸውም ጨምሮ ተናግሯል፡፡
ቀድሞ የጤና ባለሙያ የነበረው ኢያን ጆንስ በፈራጃስታን ግዛት ውስጥ ያሉ የእደ-ጥበብ ባለሙያዎች የእጅ ስራ ውጤታቸውን ወደ እንግሊዝ እንዲልኩ በማድረግ ከድህነት የማላቀቅ ስራዎችን በሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ እየሰራ ይገኛል፡፡ ወረርሺኙ በተከሰተ ጊዜ ተቋሙ በሚሰራበት አካባቢ ያለውን ማህበረሰብ እንዲረዳ ተመርጦ እዚያው በህንድ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡
ህንድ በዓለማችን ቀዳሚዋ ሰዎች በአደገኛ እባቦች የሚነደፉባት ሀገር ስትሆን በየአመቱ በአማካኝ 58 ሺህ ዜጎቿ በአደገኛ እባቦች ምክንያት እንደሚሞቱባት የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ከ9 ሚሊዮን በላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ተጠቂዎችን በማስመዝገብ ከአሜሪካ ቀጥላ በሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ህንድ 134,218 ዜጎቿን በቫይረሱ አጥታለች፡፡
ምንጭ፡ RT

የፊዚክስ ቀዳማዊት እመቤት
*****************
በሳይንስ አለም ውስጥ ጥቂት የማይባሉ ስራቸው ታውቆ እነሱ ግን ያልታወቁና ያልተዘመረላቸው እንዳሉ በዙዎች ይስማማሉ፡፡ ከእነዚህ ካልተዘመረላቸው ከሳይንስ እንቁዎች መካከል በፊዚክስ ዘርፍ ቀዳማዊት እመቤት የሚል ቅጽል ስም የተሰጣት ቺን ሺንግ ዉ አንዷ ናት፡፡ የዚህች ልዩ ሴት ሳይንሳዊ ከፍታ ጉዞ መነሻው ጃንግሱ በተባለችው የቻና የወንዝ ዳር አካባቢ ነው፡፡ በ1936 የዶግትሬት ትምህርቷን ለመማር ወደ አሜሪካ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መጣች፡፡ ዩኒቨርሲቲ በነበረችበት ወቀት ማንሃታን በመባል ለሚታወቀው ፕሮጀክት በጣም አስፈላጊ የሆነ ሙከራን በጨረር ልቀት (X-ray emissions) እና ዜኖን ጋዝ (xenon gas) ላይ ሰርታለች፡፡
ከጥቂት አመታት በኋላ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ሳለች በፊዚክስ ዘርፍ አንቱታን ስገኘላትን ስራ ሰርታለች፡፡ ይህች እንቁ እንስት የኤንሪኮ ፈርሚን በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ ቅንጣቶች (atoms) እየተረጋጉ በሚሄዱበት ቅጽበት እንዴት ጨረር እንደሚፈነጥቁ የሚገልጸውን የ radioactive beta decay እሳቤ ያረጋገጠችው ሲሆን ቆይታም አሻሽላዋለች፡፡
በ1956 ሌሎች ተመራማሪዎች እንስቷን በተመሳሳይነት ህግ (law of parity) መላምት ላ እንድታግዛቸው ጠይቀዋት ነበር፡፡ ህጉ የነገሮች የመስታዎት ምስል ቀኝና ግራ ከመለዋወጡ ውጭ ተመሳሳ መሆን አለበት የሚል ነው፡፡ ታዲያ ቺን ሺንግ ዉ መላምቱን በሙከራ በማረጋገጧ እገዛ የጠየቀው የምርምር ቡድን በ1957 በፊዚክስ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት አግኝቷል፡፡ ይሁን እንጂ ለዚህ ሽልማት ያበቃችውን ቺን ሺንግ ዉን ዘንግቷታል፡፡
በዚህ ጉዳይ የሚገባትን ክብርም ሆነ ምስጋና አለማግኘቷ እንስቷን ወደኋላ አላስቀራትም፡፡ ምርምሮችን አጠናክራ የቀጠለችው ዉ የአሜሪካ የፊዚክስ ማህበረሰብና National Medal of Science recipient ለተባለ ተቋም የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዘዳንት መሆን ችላለች፡፡ በዚህም ምክንያት “First Lady of Physics” የሚል ቅጽል ስም ተሰጥቷት ስራዋን ለረጅም ጊዜያት አከናውናለች፡፡
ምንጭ Discovery Magazine

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ ላይ እንዲሳተፍ የግል ዘርፉ ታጭቷል
========================
መንግስት ለኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያ የሆነውንና እስከ 350 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያስወጣ የሚጠበቀውን የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ከግል ዘርፉ ጋራ በትብብር ለመስራት እያጤነ ነው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋራ ቆይታ አድርገው የነበሩት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ መንግስት በመጪዎቹ ሶስት እና አራት ዓመታት ውስጥ የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ለመገንባት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ለስራው ቅድመ መደላድል የሚፈጥሩ ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ዳይሬክተሩ የገንዘብ እጥረት ግን መንግስት የግል ዝርፉን ጨምሮ ወደተለያዩ አማራጮች እንዲያማትር ማስገደዱን አመላክተዋል፡፡ አክለውም የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ማምተቁ እንደ ሀገር ያሉ ክፍተቶችን ለመሸፈን እንደሚያስችልም ተገልፀዋል፡፡
ከዚህ ዕቅድ ባሻገር ኢትዮጵያ በቅርቡ 2ኛ ሳተላይቷን ወደ ህዋ ለማምጠቅ እየሰራች ትገኛለች፡፡ አዲስ የምትመጥቀው ሪሞት ሴንሲንግ ሳተላይት በአየር ሁኔታ እና ፀባይ ጋራ የተያያዙ መረጃዎችን በማቅረብ የሀገራችንን ግብርና፣ ደን ልማት እና ተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ እንደምታግዝ ይጠበቃል፡፡ ከሳምንታት በፊትም የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በመገኘት ስለ ሳተላይት እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ፕሮግራም ዙርያ ባቀረቡት ገለፃ ታህሳስ 11 እንደምትመጥቅ በምትጠበቀው በዚህች አዲስ ሳተላይት ዙርያ ማብራራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ ማብራርያ ላይም አዲሷ ሳተላይት ከአንድ ዓመት የበለጠ የአገልግሎት ዘመን ይኖራታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የተጠቀሰ ሲሆን በ512 ኪ.ሜ ከፍታ ላይ በመሽከርከር መረጃ የምታቀብል መሆኗ በዶ/ር ይሽሩን መነገሩ ታወሳል፡፡ ET-SMART-RSS የሚል ስያሜን ያገኘችው ሳተላይቷ መጠኗ አንድ ዓመት ቀድማት ወደ ህዋ ከተጓዘችው ETRSS-1 አንፃር አነስ ያለች ስትሆን በቻይናዋ ሃይናን ግዛት ውስጥ ካለው ዌንቻንግ የማምጠቂያ ማዕከል የምትመጥቅ መሆኑ በመድረኩ ተገልፆ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት የሌላት በመሆኑ የተለያዩ ተቋማቶቿ ከውጭ ሀገራት ድርጅቶች ዘንድ የእነዚህን ሳተላይቶች ግልጋቶት እተከራዩ እንደሚጠቀሙ ይታወቃል፡፡ ኢትዮ-ቴሌኮም እንኳን ብቻውን በዓመት እስከ 12 ሚሊዮን ዶላር ድረስ ለኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ኪራይ እንደሚያወጣ ሲዘገብ የሚዲያ አካላት፣ መከላከያ እና ሌሎች የግል እና መንግስታዊ ተቋማትም በየፊናቸው እነዚህን ሳተላይቶች ለመከራት ከፍተኛ ወጪ በማውጣት ላይ ናቸው፡፡
በፋይናንስ ረገድ እንደሚሆን ከተቀመጠው ድርሻ ባሻገር የግል ዘርፉ ኢትዮጵያ ለማምጠቅ ባሰበቻት በዚህች የኮምዩኒኬሽን ሳተላይት ላይ ምን ምን አስተዋፅዖ እንደሚኖረው በዝርዝር አልተቀመጠም፡፡
ምንጭ፡ The Reporter

የበረሃ አንበጣን በምስራቅ አፍሪካ አስከወዲያኛው ለመከላከል የሚያግዘው አዲሱ ሞዴል
-----------------------------------------------
ብዙዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ደቡብ ሱዳን በ70 አመት ውስጥ እጅግ ከባድ የተባለለትን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በመፋለም ለይ ይገኛሉ፡፡ ይህ መንጋ በአካባቢው ላይ በሚያደረገው እንቅስቃሴ በዙ ሄክታር የሚሸፍኑ የእርሻ ሰብሎችን በአንዴ ድምጥማጡን በማጥፋት የምግብ ዋስትና ፈተናን እየደቀነ ያለ እና በሃገር ኢኮኖሚ ላይም ከባድ ጥፋት እያስከተለ የሚገኝ ነው፡፡ የአለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተው የበረሃ አንበጣ እስከ 2020 መጠናቀቂያ 8.5 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ጥፈት ሊያስከትል እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል፡፡
እነዚህ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መንጋው በተስፋፋባቸው አካባቢዎች የኬሚካል እርጭት በማድረግ እና ሌሎች የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም ወረርሽኙን ለማስወገድ ጥረት እያደረጉ ቢሆንም የመንጋው ደረጃ በከፍተኛ የመራባት አቅም ላይ የሚገኝ በመሆኑ ከእርምጃው በላይ እየደረሰ ያለው ውድመት እጅግ ከባድ ሊሆን ችሏል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ ለረዥም ጊዚያት ምርምር ሲያደርጉ የቆዩ ተመራማሪዎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የበረሃ አንበጣ ጉዳትን ከመነሻው ለመሳጠር አንዲችሉ የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም የተከተለ አዲስ ሞዴል ይፋ አድርገዋል፡፡
በአለም አቀፍ የነፍሳት ፊዚዮሎጂ እና ኢኮሎጂ ማዕከል (ICIPE) የሚሰሩ ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ይፋ እንዳደረጉት የበረሃ አንበጣ የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል በመለየት ወረርሽኙ የሚያስከትውን ከፍተኛ አደጋ ከወዲሁ ማስቀርት እንደሚቻል በጥናታቸው ይገልፃሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ እንደሚያስረዱት በምስራቅ አፍሪካ አከባቢ ያለው የመረጃ አያያዝ እጅግ ደካማ በመሆኑ የበረሃ አንበጣ መራቢያ ቦታዎችን በትክክል ለማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም በተገበሩት የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም አማካኝነት እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን ለመገመት የሚያስችል ሞዴል አበልፅገዋል፡፡
ተመራማሪዎች የተገበሩት ይህ አዲስ ሞዴል በአለም አቀፍ ደረጃ ከዚህ በፊት በተመዘገቡ 9,134 በሚጠጉ የአንበጣው መራቢያ ቦታዎች በመተንተን የተከናወነ ሲሆን እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል ለመተንበይ የሚያስችልም የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም በምርምሩ ላይ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ይህ አልጎሪዝም በምስራቅ አፍሪካ ሊኖር የሚችለውን የአንበጣ መራቢያ ቦታ በትክክል ለመገመት የሚችለው የባዮ-ክላይሜቲክ ማለትም (የሙቀት እና የዝናብ መጠን) ተፅዕኖችን በመተንተን ሲሆን ከዛ በተጨማሪም የedaphic ወይም የአሸዋ እና እርጥበት ይዘቶች የሚያስከትሉትን ትፅእኖም በጋራ ይመለከታል፡፡ እነዚህ የአየር ንብረት ተፅእኖዎች እና የአፈሩ ባህሪዎች የበረሃ አንበጣው ለሚጥለው አንቁላልቅና ከዚህ ሂደት በኋላ ለሚኖረው የእንቁላል መፈልፈል ትልቅ ሚና እንደሚኖራቸው ተመራማሪዎች ያስረዳሉ፡፡
ከዚህ በፊት የተመዘገቡት አብዛኛቹ የመራቢያ ቦታዎች እንደሚያሳዩት ብዙዎች የመራቢያ አከባቢዎች ከ40 እስከ 80 ሚሊዮን የበረሃ አንበጣዎችን በአንድ ስኬር ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ይዘው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ታዲያ እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የበረሃ አንበጣ መፈልፈያ አካባቢዎች በመሆናቸው የክትትል አቅምን በማሳደግ በአጭር ጊዜ፣ በትንሽ ወጪ እና አከባቢን በማይጎዳ መልኩ የበረሃ አንበጣውን እስከወዲያኘው ማስወገድ የሚቻልበት መንገድ ነው፡፡
ተመራመሪዎች የተገበሩት አዲሱ ሞዴል የማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝምን በመተግብር እምቅ አቅም ያላቸው የመራቢያ ቦታዎችን የሚለይ እና እሱንም በካርታ መልክ የሚያስቀምጥ በመሆኑ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የሚከሰተውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ በቀላሉ ለመከላከል እና ውድመቱ ከፍተኛ ደረጃ ሳይደረስ ከመነሻው ለማቆም በእጅጉ የሚያግዝ ነው፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩ ሙከራዎች እና የትብብር ስራዎች የበረሃ አንበጣ ወደ ምስራቅ አፍሪካ በሚገባባቸው አካባቢዎች እና በሚፈለፈልባቸው ቦታዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች የሚከናወኑ ቢሆንም የመራቢያ ቦታዎችን በትክክል ተገንዝቦ መፍትሄ የሚጠቁም ባለመኖሩ፤ የማዕከሉ የምርምር ውጤት ከዚህ ቀደም ከነበሩት በተሻለ ሁኔታ ጉዳቱን ለመቀነስ ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
ይህ ምርምር በሞዴሉ አማካኝነት የለያቸው የምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መራቢያ ቦታዎች ኬኒያ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ቢሆኑም በውስጣቸው የሚገኙ አያሌ የሰፈር ቦታዎች በካርታው ተገልፀው የሚገኙ ናቸው፡፡ እንደካርታው ማብራሪያ ከሆነ የኬኒያ እና የሱዳን ሰፊ ቦታዎች ዋና የመራቢያ አካባቢዎች ተደርገው የተቀመጡ ሲሆን ከዛ ባለፈም የኡጋንዳ ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች እና የደቡብ ሱዳን ሰሜናዊ ክልሎች የበረሃ አንበጣው ዋና የመራቢያ ቦታዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
በናይሮቢ መቀመጫውን ያደረገው ይህ የምርምር ማዕከል በምክረ ሃሳብ ደረጃ በሚያስቀመጣቸው ቀጣይ እርምጃዎች መሰረት እና ከማዕከሉ ጋር በሚኖር ግንኙነት ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ የሚገኘውን የበረሃ አንበጣ ወረርሽኝ እስከወዲያኘው ለመከላከል በንቃት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ እና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትም በዚህ የአሰራር ሞዴል በመታቀፍ በትብብር እንዲሱሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ምንጭ፡ International Centre of Insect Physiology and Ecology (icipe) እና theconversation

በበረሀ ተተክሎ የተገኘው ምስጢራዊ አንጸባራቂ አምድ
**************************
እንደ ማርስ በቀላው የዩታ በረሀ (Utah desert) ሚስጢራዊ የሆነ አንጸባራቂ የብረት ምሰሶ ተገኘ፡፡ ይህ ለስላሳና ረጅም ቅርጽ ያለው የብረት ምሰሶ የተገኘው በ ዩታ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ የሒሊኮፕተር አሰሳ ሲደረግ እንደ ሆነ የግዛቷ ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡
የዩታ አካባቢ ደህንነት ክፍል አባላት አሰሳ በሚያደርጉበት ወቅት ያለፈው ህዳር 18 አንጸባራቂውን አምድ ማንም ይደርስበታል በማይባል በረሀ ውስጥ ማግኘታቸው ታውቋል፡፡
የተገኘው ብረት የማይዝግ የብረት አይነት ሲሆን የሁለት ሰዎች ያክል ቁመት አለው፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ነገር ማን ለምንና እንዴት ወደዚህ በረሀ እንዳመጣው ምንም ፍንጭ አልተገኘም፡፡ የአሰሳ ቡድኑ የተገኘው የብረት አምድ ከሌላ አለም የመጣ ነው ብለው እንደማያምኑ ተናግረዋል፡፡
ብረቱ የተገኘበት ትክክለኛ አካባቢ በጣም ሩቅና በረሀ በመሆኑ ምክንያት ሰዎች ለማየት ብለው እንዳይጠፉ ሲባል ባበለስለጣናት አልተገለጸም፡፡ የአካባቢው መሬት አስተዳደር ባለሙያዎች ብረቱ ለምን ያክል ጊዜ ቦታው ላይ እንደተቀመጠና ማን ወደዚህ እንዳመጣው እያጠኑ ነው፡፡
ምንጭ The Independent

በአፍሪካ ትልቁ የኮቪድ-19 ሙከራ ሊደረግ ነው
==================
ኢትዮጵያን ጨምሮ 13 የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ አጥኚዎች ጋራ በመሆን በአህጉራችን ትልቁ የሆነውን የኮቪድ-19 ህክምና ሙከራ ሊያደርጉ ነው፡፡ አንቲኮቭ የተሰኘው ጥናቱ በቤልጂየም፤ አንትወርፕ ከሚገኘው የትሮፒካል ህክምና ኢንስቲትዩት እና ሌሎች አለም አቀፍ የጥናት ኢንስቲትዩቶችንም ያካተተ ሲሆን ኮቪድ-19 ገና ያልጠናባቸውን ታማሚዎች በጊዜ በማከም ወደ በሆስፒታል አልጋ እንዳይርሱ እና ቀድሞውንም በችግር ውስጥ የሚገኘውን የአፍሪካ የጤና ስርዓትን ለባሰ ምስቅልቅል እንዳይዳርግ ለማድረግ ያለመ ነው፡፡
የክሊኒካል ሙከራው በ13 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ባሉ 19 ስፍራዎች የሚደረግና ከአፍሪካ በተውጣጡ ሀኪሞች የሚመራም ነው፡፡ ይህ ጥናት በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የተስማሙ የኮቪድ-19 እርምጃዎች እንዲወሰዱና ለእነዚህ ሀገራት የጤና ስርዓት የሚቀርበው በቂ ያልሆነ ድጋፍ እንዲስተካከል የሚጠይቁ ጥሪዎችን መቅረባቸውን ተከትሎ የተሰጠ ምላሽ ነው፡፡ የአፍሪካ የበሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ማዕከል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ የአፍሪካን ጥያቄዎች የሚመልስ አፍሪካ ተኮር የክሊኒካል ሙከራ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው አዲሱ ሙከራ በአፍሪካ የኮቪድ-19 መከልከል እና ህክምና ላይ እጅግ ወሳኝ የሚባሉ ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚረዳም ተናግረዋል፡፡ አክለውም የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን በጣም ጥሩ ምላሽ ለኮቪድ-19 የሰጡ ቢሆንም አሁን ጊዜው ለቀጣይ የወረርሺኙ ማዕበሎች የምንዘጋጅበት መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ይህ ጥናት በኢትዮጵያ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ካሜሮን፣ አይቮሪ ኮስት፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ፣ ጋና፣ ኬኒያ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ሱዳን እና ዩጋንዳ ውስጥ ያሉ ከሁለት እስከ ሦስት ሺህ በቀላል እና መካከለኛ ህመም ደረጃ ላይ የሚገኙ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ላይ የሚከናወን ህክምናን ይገመግማል፤ በዚህም ህመሙ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይደርስ የሚያደርጉና ተላላፊነቱንም የሚገድቡ ህክምናዎችን እንደሚለይ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም ጥናቱ በካንሰር መድሃኒቶች ላይ ተተግብሮ የነበረውን እና የተለያዩ ህክምናዎች በአንድ ጊዜ እንዲሞከሩ የሚያደርገውን የአዳፕቲቭ ክሊኒካል ሙከራ ስልት እንደሚጠቀም ታውቋል፡፡ ይህም ቆጠራ፣ እተከናወኑ ባሉ ትንተናዎች ላይ በመመስረት ህክምናውን ማቆም እና ሌሎችንም ጨምሮ ውሳኔዎች በፍጥነት እንዲተላለፉ የሚያስችል ነው፡፡
የትሮፒካል ህክምና ኢንስቲትዩት ለብዙ ዓመታት በኢትዮጵያ ከሚገኙ አጋሮቹ ጋራ ሲሰራ መቆቱን ያወሱት የተቋሙ ባልደረባ ፕ/ር ዮሀን ቫን ግሪንስፌን በአህጉረ አፍሪካ በቂ የህክም ቁሳቁሶች እና ባለሙያዎች ያሉባቸው የከፍተኛ ክትትል ክፍሎች ጥቂት ከመሆናቸው ጋራ ተያይዞ ይህ ጥናት የሚሰጣቸው ምላሾች የጤና ስርዓቱን ይባስ ወደ መጨናነቅ እንዳይገባ እንደሚጠቅም ገልፀዋል፡፡
በዚህ ሙከራ ላይ በመጠነኛ እና መካከለኛ ደረጃ ላይ ያሉ የቫይረሱ ታማሚዎችን በማከም ረገድ ያላቸውን አቅም ለማወቅ ይረዳ ዘንድ አዳዲስ ህክምናዎች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ በዚህም የኤች.አይ.ቪ ጸረ ቫይረስ ውህድ የሆነው ሎፒናቪር-ሪቶናቪር እና በአሁኑ ሰዓት በአፍሪካ ያሉ የኮቪድ-19 ታማሚዎችን ለማከብ በብዛት እየዋለ ያለውን ሀይሮክሲሎሮኩዊን የተሰኘውን የወባ መድሃኒት በመሞከር የሚጀምር ይሆናል፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ባትሪ መዋጥ እና የልብ ድካም ምን አገናኛቸው
==================== የህክምና ባለሙያዎች በድንገተኛ ክፍል የተገኘውን ግለሰብ በኢ.ሲ.ጅ ወይም (Electrocardiography) ሲመለከቱት ወደ ልቡ የሚዘዋወረው ደም ተቋርጦ ወይም የልብ ድካም ደርሶበት ያገኙት ቢመስልም የችግሩ መነሻ ሲጣራ ግን ግለሰቡ የባትሪ ድንጋይ በመዋጥ ከፍተኛ የልብ ችግር በራሱ ላይ እንደፈጠረ ደርሰውበታል፡፡ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ በግለሰቡ ሆድ ውስጥ ባትሪው ተቀምጦ ስለነበረ የልብን የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ በሚለካው ኤሌክትሮ ካርዲዮግራም ወይም (EKG) በሚለኩት ጊዜ የልብ ምቱ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ መደበኛ ሂደት ላይ እንዳልነበረ ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ይህ መሳሪያ በእያንዳንዷ የልብ ምታችን ወቅት በልባችን የሚዟዟረውን የኤሌክትሪክ ግፊት ወይም ሞገድ የሚለካ መሳሪያ ሲሆን ይህ የኤሌክትሪክ አንቅስቀሴም የልብን የደም ዝውውር ሂደት በዋናነት የሚያሳልጥ ነው፡፡ በዚህ መሳሪያ ምርመራ የተደረገለት ይህ ግለሰብ በሰውነቱ ውስጥ በነበረው የባትሪ ድንጋይ የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴ ምክንያት የልብ ድካም ምልክቶች እንዳሉበት ሰው ሁሉ በኤሌክትሮ ካርዲዮግራሙ መለኪያ ላይ ይህን የልብ ድካም ምልክት ሊያሳይ ችሏል፡፡ ይሁንና የህክምና ባለሙያዎቹ ግለሰቡ የዋጠውን አንድ ባትሪ ከሰውነቱ ካወጡለት በኋላ የልቡ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ወይም (EKG) ልኬት ወደመደበኛ ሂደት መመለሱ እጅግ አስገራሚ ሆኗል፡፡
የ26 አመት ወጣት የሆነው ይህ ግለሰብ ሳንታ ማራ በተባለው የጣሊያን ሆስፐታል ከትትል ሲደረግልት የቆየ ሲሆን በማረሚያ ቤት በነበረበት ጊዜ AA የተባለውን የባትሪ ድንጋይ ሆንብሎ እንደዋጠም ተነግሯል፡፡ የግለሰቡ ኤሌክትሮ ካርዲዮግራም ውጤት የልብ ድካም መስሎ የታየበት ሁኔታ በህክምና ቃሉ "ST segment elevation" ተብሎ የሚጠራ መሆኑን የሚናገሩት የህክምና ባለሙያዎች ይህም ባትሪው በሆድ ውስጥ ከሚገኝ ጋስተሪክ አሲድ (gastric acid) ጋር በሚፈጥረው ግንኙነት ወደልብ የሚሄድ አሌክትሪክ ከረንት በሚፈጠርበት ጊዜ የሚከሰት መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
በኒው ዮርክ የሳንድራ አትላስ የልብ ሆስፒተል የሚሰሩት ዶ/ር ጋያ ሚንትዝ አንደሚያስረዱት ማንም ሰው አንድም ይሁን ብዙ ባትሪ በሚውጥብት ግዜ መሰል ሁኔታዎች የመፈጠር እድል እንዳላቸው ገልፀው ብዙ የህክምና ባለሙያዎች ግን ይህን ክስተት በሚገባ ያውቃሉ ብለው እንደማይገምቱ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በፊት በነበሩ ልምዶች ስድስትና ከዛ በላይ ባትሪዎችን የዋጡ ሰዎች ይህን መሰል አደጋ አጋጥሟቸው እንደነበር የሚናገሩት ዶ/ር ሚንትዝ አንድ ባትሪ የዋጠው የዚህ ግለሰብ አጋጣሚ ግን እጅግ እንዳስገረማቸው ገልፀዋል፡፡ ወጣቱ ባትሪውን ከዋጠ በኋላ በእርግጥም የልብ ጥቃት ያስከተለበት ባይሆንም የኤሌክትሪክ አንቅስቃሴው ድንግት ረዘም ላለ ጊዜ ቢቆይ ከፍተኛ የልብ ችግር ይፈጠር እንደነበር እና ከዛ በላይ ደግሞ ባትሪው ተሰብሮ የኬሚካል ሊኬጅ ቢከሰት ህይወትን እስከማሳጣት ሊደረስ እንደሚችል ዶ/ር ሚንትዝ ይናገራሉ፡፡ ምንጭ፡ Live Science

የዲጂታል ላይብረሪ፤ ለምን? Why digital libraries?
=================
የዲጂታል ላይብረሪ አተገባበር የመረጃ አደረጃጀት፣ የመረጃ አስተዳደር፣ የመረጃ አመላካቾች፣ የመረጃ ማስፈንጠሪያዎችን እንዲሁም የመረጃ አጠቃቀምን በማካተት የሚከወን ተግባር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል ላይብረሪን ቢጠቀሙ ምን ያተርፋሉ፡-
• በየትኛውም ስፍራና ቦታ
• የ24 ሰዓት ያልተገደበ አገልግሎት
• ዘርፈ-ብዙ አገልግሎት
• የተደራጀ ይዘት
• ያልተገደበ የመረጃ ምንጭ
• ዘላቂ ግልጋሎት
• አማራጭ ክምችት
• የተቀናጀ የመረጃ ትስስር
• ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ አገልግሎቱን ማግኘት ያስችልዎታል፡፡
እንግዲያውስ ለወዳጅ ዘመድዎ፣ ለተማሪዎችና አገልግሎቱ ለሚያሻቸው በማስተዋወቅ በጋራ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
ይህን ሊንክ በመጫን ብቻ የዲጂታል ላይበረሪያችንን በቀጥታ ሊያገኙት ይችላሉ http://library.techin.gov.et/web/dl-site/home
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት

የሞባይል ባትሪ እድሜን የሚያሳጥሩ ምክንያቶች
=====================
ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) የተሰራ ሲሆን ይህንንም በአግባቡ ካለመያዛችን እና ካለመጠቀማችን የተነሳ ባትሪው መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ እንዲደክም ያደርገል፡፡ ይህም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡
የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው የሚሰሩ ቢሆንም ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ እድሜያቸውን የሚቀንስ እና ባትሪውን በተሻለ ሁኔታ እንዳንገለገል የሚያደርጉ የተለያዩ ምክንያች በአጠቃቀማችን ላይ ይስተዋላሉ፡፡
ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው ነጥቦች የሞባይል ባትሪን እድሜ ሊያሳጥሩ የሚችሉ ናቸው
*የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር መጠቀም (ይህ ድርጊት ለሞባይል ባትሪው ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ወይም የቮልቴጅ አለመመጣጠን በመፍጠር ባትሪውን ሊጎዳብን ይችላል )
*ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ ለኢንተርኔት ለጌም እና ለተለያዩ ነገሮች መጠቀም (ይህ ድርጊት የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹም አደጋ ሊያስከትል ይችላል)
*ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ ማድረግ ወይም ጃርጅ ላይ ሰክቶ ማሳደር (የሞባይል ባትሪ 100 ፐርሰንት ሞልቶ ያማይነቀል ከሆነ ከመጠን ባለፈ ሙቀት እንዲጎዳ እና የቮልቴጅ ጫና ሊፈጠርብት ይችላል)
*ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ መጠበቅ (የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ በቶሎ የሚያሳጥር ነው)
*ከእነዚህ በተጨማሪ በስልክ አጠቃቀሞ ባትሪውን የሚያወርዱ መቼቶችን አለማስተካካል (ለምሰሌ ከፍተኛ የብራይትነስ መጠን፣ የሎኬሽን (Location) መብራት፣ መተግበሪያዎችን ያለማስተዳደር (Monitor Apps) እና አልፎ አልፎ የሞባይል ስልክ አለማጥፋት ባትሪውን የሚጎዱ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ MAKE USE OF

ጉግል ቆዳን እንደ ተችፓድ (touchpad) የሚያስጠቅም ስማርት ንቅሳቶች ላይ እየሰራ ነው
********************************************
በሀገራችንም ሆነ በሌሎች የአለም ክፍሎች ንቅሳትን ለውበትና የጥበብ ስራዎች በሰውነታችን ለማስፈር መጠቀም በጣም የተለመደ ነው፡፡ ግዙፉ የጎግል ተቋም ከጀርመን የሳርላንድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጋር በመሆን ከፍተኛ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ጊዜያዊ የሆነን ንቅሳት በመንቀስ ቆዳችንን በመንካት የሚሰራ የቴክኖሎጂ ቁስ (fully-functional touchpad) ለማድረግ እየሰራ እንደሆነ ተዘግቧል፡፡
ይህ SkinMarks በመባል የሚታወቀው ፕሮጀክት ከ2017 ጀምሮ እየተሰራ ሲሆን መሰረታዊ ሀሳቡም የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንደ ምልክትና መንካት ባሉ ተፈጥሯዊ የሰውነት እንቅስቃሴዎች ለመጠቀም ነው፡፡
SkinMarks የንቅሳት ቴክኖሎጂ በጣም ስስ የሆነ ውፍረት ያለው ንቅሳት ሲሆን በቆዳችን ልክ መለጠጥ የሚችል ነው፡፡ ንቅሳቱ የሰውነታችንን እንቅስቃሴ የሚረዳ ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ አተገባበሩም ከ skin electronics እና epidermal electronics መሰረታዊ ሀሳብ ጋር የተዛመደ ነው፡፡ እነዚህም ቆዳን ለኮምፒውተርና ለሰው ተግባቦት የግንኙነት መስመር የሚሆኑ ናቸው፡፡
ምንጭ InceptiveMind

ዛፎችን እንትከል ወይስ በራሳቸው ይደጉ
*****************************
ከሰባት ዓመታት በፊት ሱዛን ኩክ-ፓተን ደኖችን መልሶ በማብቀል ላይ ያተኮረ የድህረ ዶክትሬት ጥናቷን በሜሪላንዱ ስሚትዞኒያን የአካባቢ ጥናት ማዕከል ውስጥ በምታከናውንበት ወቅት 20 ሺህ ያህል ችግኞች እንዲተከሉ መርዳቷን ትናገራለች፡፡ እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ማስተዋል ቻለች፤ በብዛት ፀድቀው የተገኙት የተተከሉት ችግኞች ሳይሆን በራሳቸው የበቀሉት ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት መትከላቸውን እንዳቆሙ እና ወዲያው ሌሎች ብዙ እፅዋት በአካባቢው መብቀል መጀመራቸውን ታወሳለች፡፡ ታድያ ይህ ምናልባትም በሌሎች አካባቢዎች ላይም እውነት ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ችግኝ መትከል እጅግ እየተዘወተረ የመጣ ተግባር ሆኗል፡፡ በቅርቡ ስዊዘርላንድ ውስጥ የተካሄደው የአለም ምጣኔ-ሐብት ጉባኤ አንድ ትሪሊዮን ዛፎች እንዲተከሉ ጥሪውን አስተላልፎ ነበር፡፡ ኢትዮጵያም ባሳለፍናቸው ሁለት ክረምቶች በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን ለመትከል አቅዳ በስፋት ስትንቀሳቀስ መቆየቷ ይታወሳል፡፡ ይህ ዛፎችን የመትከል እንቅስቃሴ ታድያ እንደ አንድ ተፈጥሮ ላይ የተመረኮዘ የአየር ንብረት ለውጥን መቀልበሻ መንገድ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ሆኖም ዛፎችን በስፋት የመትከሉ እንቅስቃሴ የተለያዩ ጥያቄዎችን እያስነሳ ይገኛል፡፡ ጥያቄው የዛፎች መኖርን የሚቃወም ሳይሆን ችግኝ ተከላው የሚደረግባቸው አካባቢዎች ብዙውን ጊዜ ቶሎ በሚያድጉ ግን ደግሞ ለአካባቢው እንግዳ በሆኑ የዛፍ ዝርያዎች እየተሸፈኑ ናቸው ሲሉ ይህን ተግባር የሚተቹ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ ተፈጥሮ ከማንም በላይ ለራሷ የሚስማማትን ታውቃለች እና አካባቢውን በቅርብ ለሚገኝ ደን ትተን ስፍራው ለራሱ የሚስማማውን አብቅሎ ዳግም እንዲለመልም አንተወውም በማለት ችግኝ የመትከልን አስፈላጊነት ይጠይቃሉ፡፡
ሱዛን ከ17 ትምህረት እና በከባቢ ላይ ከሚሰሩ ተቋመት ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋራ በመሆን በሰራችው ጥናት መሰረት ተ.መ.ድ ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ጭምር ድጋፍ ያገኘው ይህ ደኖች በተፈጥሮ እንዲያድጉ በማድረግ ካርበንን የመሰብሰቡ እንቅስቃሴ ከሚፈለገው በታች ሆኖ አነስተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡
ጥናቱ ደኖች የት የት በራሳቸው ማደግ እና ካርቦንንም መሰብሰብ ይችላሉ የሚለውን በማጥናት ረገድ ፈር ቀዳጅ ነው፡፡ በዓለም ዙርያ ከተጠኑ 250 ጥናቶች ላይ 11 ሺህ ያህል ደኖችን ዳግም በማብቀል ካርቦንን የመሰብሰብ እርምጃዎችንንም መመልከቱ ተግጿል፡፡ እንደ ጥናት ቡድኑ ከሆነ ከከባቢ አየር ላይ ያለ ካርበንን የመሰብሰቡ ተግባር ዛፎቹ በሚተከሉበት አካባቢ አየር ንብረት፣ አፈር፣ ከባህር ጠለል በላይ ያለ ከፍታ እና የአካባቢው አቀማመጥ ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ተፅዕኖ ስር ይወድወቃል፡፡ በዚህ ምክንያትም ከሀገር ሀገርም የተለያዩ ውጤቶች ታይተዋል፡፡ በመጨረሻም የዛፎች መተከል ለከባቢው ጥሩ ነገርን ይዞ መምጣቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ካርበንን በፍጥነት እና በመልካም ሁኔታ በመሰብሰብ ረገድ ግን ተፈጥሮ ዳግም ያበቀለቻቸው ደኖች በሰው ልጅ እጆች ከተተከሉት አንፃር የተሸሉ መሆናቸው ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ምንጭ፡ WIRED