TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው፤ ከቴክኢን ቤተሰብ
====================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኛች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው” በሚል የተዘጋጀውን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊትን የማክበር ዝግጅት በተቋሙ አከናውነዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ከተቋሙ አመራር እና አብዛሀው ሰራተኞች በተጨማሪ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብር በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡
አፍሪካ እና ቴክኖሎጂ
በቁስ በፅሁፍ የተገኙ እንዲሁም ቋንቋን ባህልን ጊዜን መሰርት አድርገው የተካሄዱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አፍሪካና አፍሪካውያን ከአውሮፓ ስልጣኔ በፊት የሳይንስ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የነበሩ መሆናቸውን ያመለክታሉ፡፡
በርካታ ተመራማሪዎች አፍሪካውያን ለአለም ያበረከቱት አስተዋጽዖ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተከናወኑት ፈጠራዎች የማይተናነሱ እና ይልቁንም ከጥቁር ህዝብ የፈለቁት የጊዜ እና የወቅት መፈራረቅ ግኝት፣ የቀን አቆጣጠር፣ የሂሳብ ቀመር ግኝት፣ የእደ ጥብብ ብቃት፣ የግብርና እና የስነ ህንፃ ጥብብ ኋላ ለተፈጠሩት የሰው ልጅ የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ መሰርት ጥሏል፡፡
ቴክኖሎጂ እና የሳይንስ እውቀት የሁሉም የሰው ልጆች ንብረት እንደሆነ ሁሉ ለዚህ እውቀት እውን መሆን ሁሉም ባህሎች በአንድም ይሁን በሌላም የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዳደረጉ መዘንጋት ባይቻልም ቀደምት አፍሪካውያን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ በሚገባ መዘከር እና የወደፊቱንም አልሞ መስራት እጅግ ብልህነት ነው፡፡
ተከታዩን ዘጋባ ይከታተሉ
https://youtu.be/Sm56gb1KIsc
94.5% ውጤታማ የሆነ የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት
****************************
በሶስት ዙሮች 43,000 ታማሚዎች በተሳተፉበት የሙከራ ስራ 94.5 በመቶ ውጤታማ የሆነ ክትባት መገኘቱን Biopharmaceutical Moderna በመባል የሚታወቀው ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡ መረጃው ያለፈው እሁድ የመረጃ ደህንነት በሆነ ገለልተኛ አካል ተረጋግጦ የወጣ ነው፡፡
በተገኘው ክትባት በጣም ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በታህሳስ መገባደጃ አካባቢ ስርጭትና ክትባት እንደሚጀመር ተገልጧል፡፡ በአለማችን ሁሉም አካባቢዎች እስከ ሚያዚያ ድረስ ክትባቱ ተደራሽ እንደሚሆን በተጨማሪ የተገለጸ ሲሆን ይህ መረጃ በትክክል የሚተገበር ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ችግር እንደሚፈታ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በፊት Pfizer እና German በተባሉ የመድሀኒት አምራች ድርጅቶች ውጤታማነቱ 90 በመቶ የሆነ ክትባት መገኘቱ እንደተገለጸ የማይዘነጋ ነው፡፡ ይህ Moderna በተባለው ድርጅት የተገኘው ክትባት በፍሪጅ ውስጥ ለ30 ቀናት ያክል መቆየት የሚችል በመሆኑ ስርጭቱን በጣም ቀላል ያደርገዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
ምንጭ Futurism
የደም ስጦታ፤ ከኢንስቲትዩታችን ቤተሰቦች
-----------------------------------
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በ2013 የመጀመሪያቸው የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ 35 የተቋማችን ሰራተኞች ተገኝተው ደማቸውን የለገሱ ሲሆን በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞችም ተሳታፊ ሆነው ደማቸውን ለግሰዋል፡፡ መሰል የደም ልገሳ መርሀ ግብር ሲከናወን በተቋሙ ታሪክ የዛሬው ለአስራ ሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይ ደማቸውን የለገሱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለረጅም ጊዜያት በተከታታይ መሰል የደም ልገሳ መርሀ ግብሮችን ሲያከናውን መቆየቱን እና እርሳቸውም በእነዚህ ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ደም መስጠት ከእኛ የሚቀንሰው ነገር የሌለ ግን ደግሞ ደስ የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን የገለፁት አቶ ሙሉቀን የዛሬውን ደም ልገሳ ልዩ የሚያደርገው ለመከላከያ ሰራዊታችን እየሰጠን መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተለመዱ ከመጡ የበጎ ስራ ተግባራት ውስጥ አንዱ የደም ልገሳን ማከናወን ነው፡፡ ይህ ምግባር ብዙ በተለያዩ የጤና እክሎች አስቸኳይ የደም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ህይወት ከመታደጉም ባሻገር ለለጋሹም ጥልቅ የስሜት እርካታን የሚሰጥ ነው፡፡
ሴክሽን 230 እና ሪፐብሊካኖች
***************************
በአሜሪካ የሚገኙ ህጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሌላው የአለም ክፍል ላይ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደራቸው አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ሴክሽን 230 እየተባለ የሚጠራው የገመድ አልባ አገልግሎት መሰረት የሆነውን ህግ ማንሳት ይቻላል፡፡ የዘገባችን ምንጭ እንዳስረዳው ያለዚህ ህግ በየቀኑ የምንጎበኛቸው ተፈላጊ ድረ-ገጾች ሊኖሩ አይችሉም ነበር፡፡ የዘመናዊው ገመድ አልባ አገልግሎት ከዚህ አጭር ህግ ውጭ የተለየ መልክ ሊኖረው እንደሚችል ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ህግ በወግ አጥባቂዎቹ በኩል የይሻሻል ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡
በተደጋጋሚ የሚጎበኙ ድረገጾች በአለማቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ተጠቃሚዎች ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ፣ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ስጦታዎች እንዲለዋወጡ አለፍ ሲልም የእርቃን ምስሎችን እንዲለዋወጡ የሆነው በዚሁ በሴክሽን 230 ምክንያት ነው፡፡ ይህ ህግ ከተወሰኑ ጉዳዮች በቀር እንደ Yelp, Reddit, እና Facebook ያሉ ድረገጾችና አገልግሎቶች ተጠቃሚዎቻቸው በሚያሰራጯቸው ነገሮች ህጋዊ ተጠያቂነት እንደሌለባቸው ይደነግጋል፡፡ ለምሳሌ Wikipedia እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ድረገጽ ማንኛውም ተጠቃሚ አንድን ጽሁፍ ማስተካከል እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ክፍት ድረ-ገጽ ነው፡፡
ህጉ በገመድ አልባ አገልግሎት ዙሪያ ከወጡ ህጎች በላቀ መልኩ በጣም ወሳኝ የሆነበትን ምክንያት ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን ከወግ አጥባቂዎቹ በኩል በሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኮንግረንስ አባላት በክፉ አይን መታየቱ አልቀረም፡፡ ከዚህ ህግ አንጻር ሀለት እይታዎች አሉ፡፡ በአንድ በኩል አብዛኛዎቹ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት ህግ አውጭዎች የህጉን መሰረታዊ አላማ ችላ ብለው እንደሰሩት ሲታመን በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ነጥብ ከማስቆጠር ያለፈ ነገር የለውም ብለው የሚያምኑ አሉ፡፡ ሴክሽን 230 ድረገጾች ፖለቲካዊ አላማ ይኑራቸውም አይኑራቸውም ሁሉንም የሚጠብቅ ህግ ነው፡፡
በሪፐብሊካኑ አባል ቤን ሻፒሮ በሚንቀሳቀሰው Daily Wire በሚባለው የዜና ምንጭ በየጽሁፎቹ አንባቢዎች ከፍተኛ ስም ማጥፋት የታከለባቸውን አስተያየቶችን ይጽፋሉ፡፡ በሴክሽን 230 ህግ መሰረት አዘጋጁም ሆነ አስተያየት ሰጭዎች ምንም አይነት ህጋዊ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡

ሴክሽን 230 እየተባለ የሚጠራው ህግ
“No provider or user of an interactive computer service shall be treated as the publisher or speaker of any information provided by another information content provider.”
የሚል ሲሆን በጥቅሉ በአንድ ፕላትፎርም የሚሳተፉ ተጠቃሚዎች በሚያሰራጩት መረጃ ምክንያት የፕላትፎርሙ ባለቤት ህጋዊ ተጠያቂነት የለበትም የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በ90ዎቹ በፍርድ ቤት የተወሰነ አንድ ውሳኔ በገመድ አልባ አገልግሎት በሚኖር ህጋዊ ባልሆነ ድርጊት ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚችል ታይቷል፡፡ በዚህም ይህ አገልግሎት በህግ የተሰጠውን ሙሉ ነጻነት እንደማይጠቀም መረዳት ይቻላል፡፡
ህጉ ብዙ ችግር አለው ብለው የሚስማሙ ወግ አጥባቂዎቹ ሪፐብሊካኖች እንደ Fight Online Sex Trafficking Act (FOSTA) አይነት የተሻሻሉ ህጎችን በመጥቀስ ይህም ህግ የሶስተኛ ወገን ተጠያቂነትን በሚያመጣ መልኩ መሻሻል አለበት በማለት እየሞገቱ ነው፡፡ ከጥንስሱ ህጉን ያረቀቁት የዲሞክራቱ Ron Wyden እና የሪፐብሊካኑ Christopher Cox ግብ ያደረጉት የ pornographyን መስፋፋት መግታት ነበር፡፡
ምንጭ፡ GIZMODO (https://gizmodo.com/section-230-is-the-foundation-of-the-internet-so-why-d-1833590565)
ያለ ባትሪ የሚሰሩ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቅርቡ ልናይ እንችላለን
ምንም እንኳን እንደ ሀገር ያለንበት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደረጃ የተሸሉ ከሚባሉት ሀገራት አንፃር አነስተኛ የሚባል ቢሆንም ብዙዎቻችን ከቀን ወደ ቀን በእንቅስቃሴ ውስጥ፣ በቤት፣ ቢሮና ሌሎችም ቦታዎች ላይ የምንጠቀማቸው ስማርት ቁሳቁሶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው፡፡ እነዚሀ ቁሶች ስራቸውን ለማከናወን ያስችሏቸው ዘንድ በሆዳቸው የሚታቀፏቸው ባትሪዎች ወዲያው ወዲያው አቅማቸውን የሚሟጠጥ ሲሆኑ በውስጣቸውም በቀላሉ የማይገኙና መርዛማ የሆኑ ቁሶችን ይይዛሉ፡፡ ለዚህም ነው አጥኚዎች ሌላ እነዚህን ቁሶች አንቀሳቃሽ ኃይል ምንጭ ፍለጋ ተሰማርተው የሚገኙት፡፡
አንደኛው ለቁሶቹ ኃይል የማግኛ መንገድ ደግሞ ልክ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ፎቶቮልቴክስ ወይም PVን በመጠቀም ከቤት ውጪ እንደሚያደርጉት ሁሉ የቤት ውስጥ ብርሃንንም ለቁሶቹ የኃይል ምንጭነት መተቀም ነው፡፡ ሆኖም ከብርሃን ምንጩ ልዩነት ጋር በተያያዘ ለሶላር ፓኔሎች የሚውለው ግብዓት ተጠቅሞ የቤት ውስጥ ብርሃንን ወደ ኃይል ለመለወጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን ላይ የለንደኑ ሮያል ኮሌጅ፣ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የቻይናው ሶቾው ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች በቤት ውስጥ ያለ ብርሀንንም ወደ ኃይል ለመለወጥ የሚያስችል ሶላርፓኔል በመስራት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የጥናቱ አካል የሆኑት ዶ/ር ሮበርት ሆዬ በቤት እና ሌሎች ህንፃዎች ውስጥ ካሉ መብራቶች (አምፖል) የሚመነጭ ብርሃንን ውጤታማ በሆነ መልኩ በመሰብሰብ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መለወጥ እንደሚቻል ጥናቱ እንዳሳየ ተናግረዋል፡፡
የጥናት ቡድኑ ለቀጣዩ ዘመን የሶላር ፓኔሎች ታስበው ከተሰሩት የፔሮቭስካይት ቁሶች ተወስደው ግን ደግሞ በዚህ ቁስ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ታልመው የተሰሩትን ፔሮቭስካይትን መነሻ ያደረጉ ቁሶችን መርምሯል፡፡ ፔሮቭስካይቶች ከተለምዶአዊው ሲልከን ላይ የተመሰረተ ሶላር ፓኔል አንፃር ተመሳሳይ ኃይል የሚያመነጩና ለመስራትም ርካሽ ቢሆኑም መርዛማ የሊድ ንጥረ ነገሮችን ይይዛሉ፡፡ በዚህም ሳብያ እንደ ቢዝመዝ እና አንቲሞኒን ያሉ ግብዓቶችን የሚጠቀሙ ፔሮቭስካይትን መነሻ ያደረጉ ቁሶችን የመስራት እንቅስቃሴ እንዲያድግ ሆኗል፡፡ ታድያ እነዚህ ቁሶች ለአካባቢ ተስማሚ ሆነው ቢገኙም የፀሐይ ብርሃንን በመሰብሰብ ረገድ ግን ውጤታማነታቸው ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም እንደ ጥናት ቡድኑ ግኝት ከሆነ ቁሶቹ በአንፃራዊነት የቤት ወስጥ ብርሀንን በመሰብሰብ ረገድ እጅጉን የተሻሉ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በሙከራቸውም በእነዚህ ቁሶች አማካኝነት የሚገኘው ኃይል የኤሌክትሮኒክ ሰርኪቶችን ለማንቀሳቀስ የሚችል ሆኖ አግኝተውታል፡፡
እንደ ጥናታ ተሳታፊ ባለሙያዎች ከሆነ አዲሱ ግኝት አረንጓዴ ልማትን ይበልጥ የሚያጎለብትና በቅርቡም ባትሪ አልባ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ሊሰጠን የሚችል ነው፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore
በሩሲያ ቅልጥ እሳተ ገሞራ የተገኘው አዲሱ ምስጢራዊ ማእድን
*********************
ተመራማሪዎች በሩሲያ ቅልጥ እሳተ ገሞራ አዲስ ማእድን ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ እንደሚታወቀው በአለማችን አስጨናቂ ከሆኑና ብዙ ጥፋቶችን ከሚያስከትሉ ተፈጥሯዊ ክስተቶች መካከል እሳተ ገሞራ አንዱና ዋነናው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ገሞራ ካለው ጉዳት በተቃራኒ የተፈጥሮ ምስጢራትን በመግለጥ በኩል የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመራማሪዎች ይስማማሉ፡፡ ለዚህም ነው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያጠፋልም ያለማልም የሚባለው፡፡
አዲስ በተሰራ ጥናት የሩሲያ ተመራማሪዎች በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረን አንድ አዲስና ያልተለመደ ማእድን ማግኘታቸውን አሳውቀዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ፔትሮቫይት ሲሉ የሰየሙት አስደናቂው ደማቅ ሰማያዊና አረንጓዴ ቀለም ያለው ጠጣር ንጥረ ነገር ከዚህ በፊት በሳይንስ ተመዝግበው ካሉት ማእድናት ሁሉ የተለየ እንደሆነ ተመስክሮለታል፡፡
ንጥረ ነገሩ የተገኘው በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ በሚገኝ ካምቻትካ ከፍታ ቶልባቺክ በሚባል እሳተ ገሞራ ነው፡፡ ቶልባቺክ ገሞራ ከሺህ አመታት በላይ ታሪክ ያለው የገሞራ ፍንዳታ ሲሆን ሁለት በጣም የታወቁ ፍንዳታዎች አሉት፡፡ ከእነዚህም አንዱ ከ1975–1976 የተከሰተው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከ2012–2013 የተከሰተው ነው፡፡
በመጀመሪያው በነበረው ከፍተኛ ሀይል ያለው ፍንዳታ ብዛት ያላቸው የእሳት ፍንጥርጣሪዎች እና የትም ቦታ ታይተው የማይታወቁ ማእድናት ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ የቶለባቺክ ገሞራ 130 ዓይነት በዚህ አካባቢ ብቻ የሚገኙ ማእድናትን አስገኝቷል፡፡ ከእነዚህ ማእድናት የቅርብ ጊዜው ፔትሪቫይት ነው፡፡ ይህም ሰማያዊ ቀለም ያለው ባለ ድቦልቡል ቅርጽ ሰልፌት ማእድን ነው፡፡
በአዲሱ ማእድን የተገኘው የኮፐር ቅንጣት የልተለመደና በቀላሉ የማይገኝ ከ7 የኦክስጅን ቅንጣቶች ጋር የተጣመረ ነው፡፡ የዚህ አይነት ባህሪ የሚገኘው በውህዶች ብቻ እንደሆነ የSt Petersburg University የምርምሩ መሪ ተናግሯል፡፡ የፔተሮቫየት ሞሎኪዩላዊ ቀመሩ (molecular framework) ኦክስጅን፣ ሶዲየም፣ ሳልፈርና ኮፐር በተፈጥሮ አብረው የተሰሩ ናቸው፡፡
ምንጭ Science alert
ስለ አርዲ እና ቀደምት የሰው ቅሪተ አካላት የተጻፈው መጽሀፍ
**************
በKermit Pattison የተጻፈው ‘Fossil Men’ የተሰኘው መጽሐፍ ሳይንስንና ድራማን በማዋሀድ ስለ ጥንታዊው ስነ-ሰብ የሚተርክ ሲሆን በአለማችን እጅግ ታዋቂ የሆኑት ቅሪተ አካላት የታሪኩ ክፍል ሆነዋል፡፡ እንደ ዘገባ ምንጫችን Science News እጅግ አስገራሚዋ እና በስነ ቁፋሮ ሳይንስ እስካሁን ከተገኙ ጥንታዊ የሰው ዘር ቅሪተ አካት መካከል ልዩ የሆነችው አርዲ እና ተመራማሪዎቿ በመጽሀፉ ውስጥ ተካትተዋል፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ ጋዜጠኛው Kermit Pattison በአርዲ ፍለጋ ላይ የተሳተፉ ተመራማሪዎች በሰው ዘር ዝግመተ ለውጥ ታሪክ ውስጥ የታወቀውን እሳቤ ለመሞገት የሄዱበትን መንገድ ማራኪ ታሪኮችን በመጠቀም ያስነብባል፡፡ በተጨማሪም የአርዲ ቅሬተ አካል ከሌሎች ቅሬተ አካላት የተለየ የሆነበትን ምክንያትም መጽሀፉ ያስረዳል፡፡
የቁፋሮ ምርምር ቡድኑ በምርምር ሂደቱ የያዛቸውን ፎቶዎች ቪዲዮዎችና ልዩ ልዩ ማስታዎሻዎች ያካተተው መጽሐፉ አርዲ የተገኘችበትን የመጀመሪያ ቅጽበት የገለጸበት መንገድ ሳቢ ነው፡፡ ጋዜጠኛው ሁኔታውን ሲያስረዳ የምርምር ቡድኑ ብቸኛ ጥበቃ የሆነው የአፋሩ ጋዲ ከምርምር ቡድኑ ጋር አብሮ ይንቀሳቀስ በነበረበት ወቅት ከቁፋሮው ስፍራ አንድ ጥርስ እንዳገኘ ይናገራል፡፡ ይህ ጋዲ ያገኘው ጥርስ በቁፋሮ ከተገኙት የአርዲ አስር ጥርሶች መካከል አንዱ ነበር፡፡
ምንጭ Science News Magazine
ሲንጋፖር የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ሰዎች አዲስ ቪዛ አዘጋጀች
*********************
ለባለ ተሰጥኦዎች የተዘረጋ ቀይ ምንጣፍ ያላት ሲንጋፖር 500 ሰዎች የሚሳተፉበት ልዩ የተሰጥኦ ማሳያ ዝግጅት አቅዳለች፡፡ ለዝግጅቱም በቴክኖሎጂው አለም ተሞክሮ ያለፈ አስተዋጽኦ ያላቸው ሰዎች እንደሚሳተፉ ተገልጧል፡፡ Tech.Pass program በተሰኘው እቅድ አዲስ ቪዛ የተዘጋጀላቸው ሰዎች ብቃታቸው የተረጋገጠ እና ወደ ከተማዋ መጥተው ከአንድ በላይ ተቋም ገንብተው አልሚዎች እንዲሆኑ ወይም ለጀማሪ ተቋማት አማካሪ እና አሰልጣኝ እንዲሆኑ የታሰበ ነው፡፡ይህም ድርጅቶች የሚፈልጉትን ሰው ስፖንሰር በማድረግ ብቻ ወደከተማዋ እንዲያስገቡ የሚፈቅደው የመንግስት መመሪያ እየተሸሻለ መሄዱን የሚያሳይ ነው፡፡
የሁለት አመታት የጊዜ ርዝማኔ ያለው ቪዛ የተፈቀደው መካከለኛ ክህሎት ላላቸውና የአካባቢውን ገበያ ለሚሻሙ የፈጠራ ሙያተኞች ሳይሆን ከተማዋ የቀጠናው የቴክኖሎጂ ማእከል ለመሆን የምታደርገውን ጉዞ ሊያቀላትፉ የሚችሉ ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን የቴክኖሎጂ ሰዎች ለማምጣት ያለመ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ስራ ለውጭ ዜጎች የሚሰጥበትን መመሪያ እንዲጠብቅ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጫና ስላደረበትም እንደሆነ የዘገባችን ምንጭ ገልጧል፡፡
የከተማዋ የገበያና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሆኑት Chan Chun Sing ፕሮግራሙ በቀጠናው የምንፈልገውን ቴክኖሎጂ የበላይነት እንድናመጣ ከፍተኛ ሚና ያለውና መንገዱንም ቀላል የሚያደርግልን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የፊታችን ጥር በሚጀምረው ምልመላ ተወዳዳሪዎች ለውድድር ከማመልከታቸው በፊት ካሉት ሶስት መስፈርቶች መካከል ቢያንስ ሁለቱን ማሟላት እንዳለባቸው ተነግሯል፡፡
ለማመልከትም ቢያንስ አምስት አመት የስራ ልምድ የቴክኖሎጆ ተቋምን በመምራት ወይም በቴክኖሎጂ ተቋም በመስራት ተቋሙ ቢያን 500 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ እንዲያገኝ ያደረገ/ች ወይም በባለሙያነት በተሰራ ስራ ቢያንስ 100,000 ተጠቃሚዎች ያሉት ፈጠራን የሰራ/ች እና በስራ ዘመን ከ14,800 ዶላር ያላነሰ ተከፋይ የሆነ/ች መሆን እንዳለበት ተገልጧል፡፡
ምንጭ Bloomberg Technology
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM