TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
እንቅልፍ እና እንስሳት
*******************
እስከ አሁን ባለው መረጃ መሰረት ሁሉም እንስሳት እረፍት ያደርጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ በእንቅልፍ ባህሪያቸው እና በቀን ውስጥ በሚተኙት ሰዓት መጠን የተለያየ ባህሪ ያላቸው የእንስሳት ዝርያዎች አሉ፡፡ አንዳንድ እንስሳቶች እጅግ ለረዘመ ሰዓት በእንቅልፍ የሚወድቁ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ከነአካቴው እንቅልፍ የማይተኙም አሉ፡፡
እንቅልፍ ከድካም ለማረፍ ካለው ጥቅም ባለፈ ያለው መሰረታዊ ምክንያት በሳይንስ እስካሁን አልተረጋገጠም፡፡ ባለፈው አመት በተፈጥሮ ጥናት በተሰራ ምርምር ሰዎችና እንስሳት እንቅልፍ የሚተኙት የጭንቅላት DNAን እንደገና ለማደስ ይሆናል የሚል መላምት የተመታ ቢሆንም ከዚህ በተቃራኒው በ2017 በተሰራ ተመሳሳይ ጥናት jellyfish እየተባለ የሚጠራው ጭንቅላትና ማዕከላዊ ስርዓተ ነርቭ የሌለው የባህር ውስጥ እንስሳ እንቅልፍ እንደሚተኛ ተረጋግጧል፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ጥናቶች የተሰሩት በአእዋፋትና በአጥቢ እንስሳቶች ላይ ቢሆንም አብዛኞቹ እንስሳት እረፍት ሲሹ ይታያሉ፡፡
የአለማችን ረጅሙ እንስሳ ቀጭኔ ከአጥቢ እንስሳቶች መካከል እንቅልፍ አልባ ወይም በጣም ለጥቂት ጊዜ የሚተኛ እንስሳ ነው፡፡ ይህ እንስሳ እስከ 3000 ፓውንድ የሚደርስ ግዝፈት ሲኖረው በአብዛኛው በቀን ውስጥ ለ30 ደቂቃ ያክል ብቻ ያሸልባል፡፡ እንስሳው የ30 ደቂቃ ጥልቅ እንቅልፍ ለመተኛት 4 ሰዓት ከግማሽ ያክል አይኑን ይከድናል፡፡
ሌላው እንደቀጭኔ ሀሉ በቁሙ የሚተኛው አጭር የእንቅልፍ ጊዜ ያለው እንስሳ ዝሆን ነው፡፡ በ2017 በወጣ አንድ ዘገባ ዝሆኖች በቀን ለሁለት ሰዓታት ያክል ብቻ ይተኛሉ፡፡ ሁለቱ እንስሳት በግዙፍነታቸው ምክንያት የሚተኙት እንደቆሙ ወይም ክብደታቸውን የሚችል ትልቅ ዛፍ ወይም ሌላ ነገር ላይ ተደግፈው ብቻ ነው፡፡
ከነዚህ እንሰሳት በተቃራኒው ወንድ አንበሳ በቀን ውስጥ ለ20 ሰዓታት ያክል ሲተኛ ሴቷ ደግሞ እስከ 15 ሰዓታት ድረስ ትተኛለች፡፡ በአብዛኛው ስጋ በል የሆኑ እንስሳት ከሳርና ቅጠላቅጠል በል እንሰሳት በተለየ ለረጅም ሰዓታት የመተኛት ልምድ አላቸው፡፡ በአውስትራሊያ ብቻ የሚገኘው ኮዋላ እየተባለ የሚጠራው የድብ ዝርያ ከ18 እስከ 22 ሰዓታት ያክል በመተኛት የአለማችን እንቅልፋሙ እንስሳ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ እንስሳ በብዛት የሚመገበው የባህርዛፍ ቅጠል ነው፡፡
በጣም አስደናቂ የሚባለው ደግሞ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ሁለ በል የሆኑት ጥቁርና ቡናማ የሆኑት ድቦች በተከታታይ ለስምንት ወራት ያክል ይተኛሉ፡፡
ከደረቅ መሬት ወጥተን ወደ ውሀ አካላት ስንሄድ ያልተለመደ የአተኛኝ ልምድ ያላቸው አሳዎችን እናገኛለን፡፡ አንዳንድ አሳዎች በሚተኙበት ጊዜ አይናቸውን አይከድኑም፤ ምን እንኩዋን ይሄ የአይን ሽፋል የሌላችው በመሆኑ ምክንያት ቢሆንም፡፡ እንዲሁም በከፊል ንቃት በከፊል እንቅልፍ ውስጥ ሆነው የሚተኙ የአሳ ዝርያዎችም አሉ፡፡
ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ ከነጭራሹ የማተኛው የእንቁራሪት ዝርያ ነው፡፡ ይህም bullfrog እየተባለ የሚጠራው ዝርያ ነው፡፡ የመረጃ ምንጫችን የሆነው Discover Magazine መረጃውን ሲያጠናቅቅ በሰዎችና በእንስሳት እንቅልፍ ዙሪያ ገና ያልተጠኑ ብዙ ምስጢሮች እንዳሉ በመናገር ነው፡፡
በህይወት አድን ግስጋሴ ላይ የሚገኙት የኮቪድ-19 ክትባቶች፤ ተስፋ እና ስጋት
===============
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ54 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን አጥቅቶ 1.3 ሚሊዮን የተሻገሩትን ህይወት የነጠቀው ኮቪድ-19 ወረርሺኝን ለመግታት ያለሙ ክትባቶችን የመስራቱ ሩጫ የወረርሺኙ መነሳት ከተሰማባቸው ጥቂት ሳምንታት አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በፍጥነት እየተከናወነ ነው፡፡ ከነዚህ መካከልም የሰው ልጆች ላይ የተሞከሩ እና በተጓዳኝ ሙከራ ላይ ያሉት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቶ በአሁኑ ሰዓት 54 ክትባቶች የክሊኒካል ሙከራ መከወን ላይ ደርሰዋል፤ 87ቱ ደግሞ በእንሳት ላይ ሙከራቸው እየተከናወነ ነው፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካን ፋይዘር የተሰኘው ክትባት እያደረገ የነበረው የሰዎች ላይ ሙከራም 90 በመቶ ስኬታማ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ ከ43 ሺህ በላይ ሰዎችን ተሳታፊ አድርጎ የነበረው ጥናቱ ገና በባለሙያዎች ሳይገመገም ይፋ የተደረገ ቢሆነም ለብዙ ሰዎች ተስፋ የሰጠ ውጤት ነበር፡፡
አሁን ደግሞ በኢቦላ ላይ ተመስርቶ የተሰራ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በስድስት ሺህ የእንግሊዝ ነዋሪዎች ላይ ሙከራ ማድረግ እንደሚጀምር ይፋ ተደርጓል፡፡ መቀመጫውን ሀገረ ቤልጅየም ባደረገው ጃንሰን ዓለም አቀፍ የመድሃኒት አምራች አማካኝነት የተሰራው ክትባቱ ለንደን፣ ማንቼስተር፣ ሳውዛምፕተን እና ሌስተርን ጨምሮ በ17 የተለያዩ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ ሙከራውን የሚያከናውን ሲሆን በቀጣይም 24 ሺህ ተጨማሪ በጎ ፈቃደኛ ተሳታፊዎችን በዓለም ዙርያ አካቶ ሙከራውን እንደሚቀጥል ታውቋል፡፡ ሙከራው በእንግሊዝ ብቻ የሚደረግ ሦስተኛው ወሳኝ የኮቪድ-19 ክትባት ሙከራ ያደርገዋል፡፡ ይህ ክትባት አቅሙ እንዲደክም የተደረገ አዴኖቫይረስ የተሰኘ የጉንፋን ቫይረስን የሚጠቀም ሲሆን ህዋሶችን በዚህ በማጥቃት የበሽታ መከላከል ስርዓታችንን የሚቀሰቅስ ነው፡፡ ታድያ ተመሳሳይ ክትባቱ ከዚህ ቀደም ለኢቦላ ወረርሺኝ ታስቦ ተስርቶ የነበረና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎም ቫይረሱን እንዲመክት ከዓመት በፊት ጥቅም ላይ የዋለ ነበር፡፡
ፋይዘር የተሰኘውን ክትባት የሰራው ባዮኤንቴክ ኩባንያ መስራቹ ፕ/ር ኡሁር ሳሂን በተቋማቸው በተሰራው ክትባት ዙርያ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሰፊ መረጃዎችን የሚሰጡ ትንተናዎች ይፋ ይሆናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ገልፀው ነገሮች በጥሩ ሁኔታ የሚሄዱ ከሆነም ክትቶቹ ባለንበት የፈረንጆች ዓመት መባቻ ላይ ለተጠቃሚዎች መድረስ እንደሚጀምርና እስከሚያዝያ ድረስም 300 ሚሊዮን የክትባት ፍሬዎች እንደሚመረቱ አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ መጪዎቹ የኮቪድ 19 ክትባቶች በጊዜ ከመድረስ ጋራ ብቻ አይደለም ግብግባቸው፤ የህብረተሰብን እምነት ከማግኘት ጋራ ጭምር እንጂ፡፡ በቅርብ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአሜሪካን ከሚኖረው ህዝብ መካከል የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ፍቃደኛ ሆኖ የተገኘው 51 በመቶው ብቻ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 21 በመቶው ብቻ ለመውሰድ እርግጠኛ ሲሆኑ የተቀረው 30 በመቶ ግን እርግጠኛ ያልሆነ ፍቃደኝነትን ያሳየ ነው፡፡ ለነዚህ ክትባቶቹ ላይ ላሉት አሉታዊ አመለካከለቶች በዋና ምክንያትነት የተቀመጡት ክትባቶቹን እውን የማድረግ ሂደቶችን ከመጠራጠር እና ከጎንዮሽ ጉዳት ከመስጋት ጋራ የተቆራኙት ናቸው፡፡ ለምሳሌ 78 በመቶው የሀገሪቱ ነዋሪ ሂደቶቹ ክትባቶቹ መድረስ ከሚገባቸው ጊዜ በላይ ባልተገባ ፍጥነት እየሄዱ እንዳይሆን የሚል ጥርጣሬ ሲያድርባቸው ፈፅሞ ክትባቶቹን ለመውሰድ ፈቃደኛ ካልሆኑት ውስጥ ደግሞ 76 በመቶው ዋናው ስጋታቸው ክትባቶቹ ሊያደርሱት ከሚችሉት የጎንዮሽ ጉዳት ጋራ የተያየዘ ነው፡፡
ይህ ግን በአሜሪካን ብቻ የሚታይ ችግር አይደለም፤ ለምሳሌ በሰኔ ወር 19 ሀገራትን አካሎ በተሰራ ጥናት 71.5 በመቶው ሰው ክትባቶቹን ለመውሰድ ያለውን ፈቃደኝነት አሳይቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ቻይና 90 በመቶው ህዝቧ ክትባት ለመውሰድ ፍቃዱን ሲያሳይ በአንፃሩ ይህ ቁጥር በሩስያውያን ዘንድ ወደ 55 በመቶ ይወርዳል፡፡ ይህ ግን ቀድሞ የነበረው ፈቃደኝነት ወይም እንቢተኝነት አሁንም በቦታው ነው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያሳለፍነው ግንቦት ላይ በአሜሪካን የተሰራው ጥናት 72 በመቶ ያህሉ የሀገሩ ህዝብ ለክትባቶቹ ፍቃደኛ መሆኑን ያሳዩ ነበር፡፡
እንደ ፕ/ር ሳሂን ከሆነ የፋይዘር ክትባት ያሳው ጎንዮሽ ጉዳት ክትባቱ በተወጋበት አካል አካባቢ ላይ በመጣ መጠነኛ ህመም ስሜት ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ ይህ በራሱ ጥሩ ዜና ይመስላል፤ የፋይዘር እና ሌሎች አዳዲሶቹ ሙከራዎች ስኬት ህዝቡ በክትባቶቹ ላይ ያለውን አመለካከት እንደሚያጠሩና ፍቃደኝነትንም እንደሚጨምሩ እየተጠቀሰ ይገኛልና፡፡
ምንጭ፡ Science News፣ The Guardian፣ BBC እና ሌሎችም
ዘመናዊው የእጅ ጓንት
*******************
በኮርኔል ዩኒቭርሲቲ የሚገኝ አንድ የምርምር ቡድን ተለጣጭ የሆነ እና VR (virtual reality) እንድንነካና ስሜቱን እንድንረዳ የሚያስችል የእጅ ጓንትን ሰርቷል፡፡ ይህ ዘመናዊ የእጅ ጓንት በጣቶቻችን የምናደርጋቸውን ተግባራት መረዳት የሚችል ሲሆን ከቨርቹዋል አለም ጋር ያለንን ግንኙነት በትልቁ ይለውጠዋል ተብሎ ይታሰባል፡፡
በጓንት ስራው ላይ የተሳተፈው የዩኒቨርሲቲው ኢንጅነሪንግ ፐሮፌሰር የሆነው ሮብ ሺፓርድ በቨርቹዋል ስርዓት ውስጥ የሁነቶች እንቅስቃሴ ከፍተኛ በመሆኑ ንክኪ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ በ Science today መጽሔት ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው የጓንቱ የመጀመሪያ ስሪት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወን የሚችል እንደሚችል ተገልጧል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአንድን ቁስ የጉዳት መጠን፣ ግፊትና እጥፋትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ይህ ሴንሰር ያለው ጓንት የተሰራው በሽቦው የብርሀን መስመር እያንዳንዱ እጣት ያለውን እንቅስቃሴ መግለጽ በሚችሉ ቀጫጭን ሽቦዎች (fiber optic) ነው፡፡ ጓንቱን ተጠቅመን አንድን ስራ በምንሰራበት ወቅት በጓንቱ ላይ የተገጠመው ኮምፒውተር ስለእጃችን እንቅስቃሴ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ይሰጠናል፡፡
ጓንቱ መሰረታዊ የሚባሉ እና ውድ ያልሆኑ እንደ ብሉቱዝ፣ ባትሪ (lithium ion) እና የተለያዩ LEDዎች ተገጥመውለታል፡፡ ተመራማሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ግኝቱ ለአካል ብቃትና ለስፖርት (physical therapy) የጤና ክትትሎች ሊውል የሚችልበትን መንገድ እያጠኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ግኝቱ ትልቅ ተስፋ ከሰጣቸው ነገሮች ዋነኛው የቨርቹዋል እንቅስቃሴ ተጠቃሚዎች አሳማኝ የሆነ ምልከታ እንዲኖራቸው ማድረጉ ነው፡፡
እንደሚታወቀው Virtual reality የሚባለው ቴክኖሎጂ ከገሀዱ እውነታ ጋር የመመሳሰል ችግር አለበት፡፡ ይህ ተለጣጭ የሆነው የቆዳችንን ስሜት የሚረዳ (skin sensor)የእጅ ጓንት ይህንን ችግር ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ምንጭ፡ www.engadget.com
ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው፤ ከቴክኢን ቤተሰብ
====================
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኛች “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለው” በሚል የተዘጋጀውን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊትን የማክበር ዝግጅት በተቋሙ አከናውነዋል፡፡ በስነ ስርዓቱ ከተቋሙ አመራር እና አብዛሀው ሰራተኞች በተጨማሪ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ለሰራዊቱ ያላቸውን ክብር በጭብጨባ ገልፀዋል፡፡
አፍሪካ እና ቴክኖሎጂ
በቁስ በፅሁፍ የተገኙ እንዲሁም ቋንቋን ባህልን ጊዜን መሰርት አድርገው የተካሄዱ መረጃዎች እንደሚያሳዩት አፍሪካና አፍሪካውያን ከአውሮፓ ስልጣኔ በፊት የሳይንስ እውቀት እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለቤቶች የነበሩ መሆናቸውን ያመለክታሉ፡፡
በርካታ ተመራማሪዎች አፍሪካውያን ለአለም ያበረከቱት አስተዋጽዖ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተከናወኑት ፈጠራዎች የማይተናነሱ እና ይልቁንም ከጥቁር ህዝብ የፈለቁት የጊዜ እና የወቅት መፈራረቅ ግኝት፣ የቀን አቆጣጠር፣ የሂሳብ ቀመር ግኝት፣ የእደ ጥብብ ብቃት፣ የግብርና እና የስነ ህንፃ ጥብብ ኋላ ለተፈጠሩት የሰው ልጅ የፈጠራ ስራዎች ወሳኝ መሰርት ጥሏል፡፡
ቴክኖሎጂ እና የሳይንስ እውቀት የሁሉም የሰው ልጆች ንብረት እንደሆነ ሁሉ ለዚህ እውቀት እውን መሆን ሁሉም ባህሎች በአንድም ይሁን በሌላም የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዳደረጉ መዘንጋት ባይቻልም ቀደምት አፍሪካውያን በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋፅኦ በሚገባ መዘከር እና የወደፊቱንም አልሞ መስራት እጅግ ብልህነት ነው፡፡
ተከታዩን ዘጋባ ይከታተሉ
https://youtu.be/Sm56gb1KIsc
94.5% ውጤታማ የሆነ የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት
****************************
በሶስት ዙሮች 43,000 ታማሚዎች በተሳተፉበት የሙከራ ስራ 94.5 በመቶ ውጤታማ የሆነ ክትባት መገኘቱን Biopharmaceutical Moderna በመባል የሚታወቀው ድርጅት ይፋ አደረገ፡፡ መረጃው ያለፈው እሁድ የመረጃ ደህንነት በሆነ ገለልተኛ አካል ተረጋግጦ የወጣ ነው፡፡
በተገኘው ክትባት በጣም ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በታህሳስ መገባደጃ አካባቢ ስርጭትና ክትባት እንደሚጀመር ተገልጧል፡፡ በአለማችን ሁሉም አካባቢዎች እስከ ሚያዚያ ድረስ ክትባቱ ተደራሽ እንደሚሆን በተጨማሪ የተገለጸ ሲሆን ይህ መረጃ በትክክል የሚተገበር ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊ ችግር እንደሚፈታ ይጠበቃል፡፡
ከዚህ በፊት Pfizer እና German በተባሉ የመድሀኒት አምራች ድርጅቶች ውጤታማነቱ 90 በመቶ የሆነ ክትባት መገኘቱ እንደተገለጸ የማይዘነጋ ነው፡፡ ይህ Moderna በተባለው ድርጅት የተገኘው ክትባት በፍሪጅ ውስጥ ለ30 ቀናት ያክል መቆየት የሚችል በመሆኑ ስርጭቱን በጣም ቀላል ያደርገዋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡
ምንጭ Futurism
የደም ስጦታ፤ ከኢንስቲትዩታችን ቤተሰቦች
-----------------------------------
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ሰራተኞች በ2013 የመጀመሪያቸው የሆነውን የደም ልገሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት አከናውነዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ 35 የተቋማችን ሰራተኞች ተገኝተው ደማቸውን የለገሱ ሲሆን በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰራተኞችም ተሳታፊ ሆነው ደማቸውን ለግሰዋል፡፡ መሰል የደም ልገሳ መርሀ ግብር ሲከናወን በተቋሙ ታሪክ የዛሬው ለአስራ ሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡
በዝግጅቱ ላይ ደማቸውን የለገሱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለረጅም ጊዜያት በተከታታይ መሰል የደም ልገሳ መርሀ ግብሮችን ሲያከናውን መቆየቱን እና እርሳቸውም በእነዚህ ላይ ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ደም መስጠት ከእኛ የሚቀንሰው ነገር የሌለ ግን ደግሞ ደስ የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን የገለፁት አቶ ሙሉቀን የዛሬውን ደም ልገሳ ልዩ የሚያደርገው ለመከላከያ ሰራዊታችን እየሰጠን መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ እየተለመዱ ከመጡ የበጎ ስራ ተግባራት ውስጥ አንዱ የደም ልገሳን ማከናወን ነው፡፡ ይህ ምግባር ብዙ በተለያዩ የጤና እክሎች አስቸኳይ የደም እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ህይወት ከመታደጉም ባሻገር ለለጋሹም ጥልቅ የስሜት እርካታን የሚሰጥ ነው፡፡
ሴክሽን 230 እና ሪፐብሊካኖች
***************************
በአሜሪካ የሚገኙ ህጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በሌላው የአለም ክፍል ላይ አወንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደራቸው አይቀርም፡፡ ለምሳሌ ሴክሽን 230 እየተባለ የሚጠራው የገመድ አልባ አገልግሎት መሰረት የሆነውን ህግ ማንሳት ይቻላል፡፡ የዘገባችን ምንጭ እንዳስረዳው ያለዚህ ህግ በየቀኑ የምንጎበኛቸው ተፈላጊ ድረ-ገጾች ሊኖሩ አይችሉም ነበር፡፡ የዘመናዊው ገመድ አልባ አገልግሎት ከዚህ አጭር ህግ ውጭ የተለየ መልክ ሊኖረው እንደሚችል ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ህግ በወግ አጥባቂዎቹ በኩል የይሻሻል ጥያቄ ተነስቶበታል፡፡
በተደጋጋሚ የሚጎበኙ ድረገጾች በአለማቀፍ ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ተጠቃሚዎች ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ፣ ፎቶዎችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ስጦታዎች እንዲለዋወጡ አለፍ ሲልም የእርቃን ምስሎችን እንዲለዋወጡ የሆነው በዚሁ በሴክሽን 230 ምክንያት ነው፡፡ ይህ ህግ ከተወሰኑ ጉዳዮች በቀር እንደ Yelp, Reddit, እና Facebook ያሉ ድረገጾችና አገልግሎቶች ተጠቃሚዎቻቸው በሚያሰራጯቸው ነገሮች ህጋዊ ተጠያቂነት እንደሌለባቸው ይደነግጋል፡፡ ለምሳሌ Wikipedia እየተባለ የሚጠራው የመረጃ ድረገጽ ማንኛውም ተጠቃሚ አንድን ጽሁፍ ማስተካከል እንዲችል ተደርጎ የተሰራ ክፍት ድረ-ገጽ ነው፡፡
ህጉ በገመድ አልባ አገልግሎት ዙሪያ ከወጡ ህጎች በላቀ መልኩ በጣም ወሳኝ የሆነበትን ምክንያት ጥያቄ የሚያስነሳ ሲሆን ከወግ አጥባቂዎቹ በኩል በሆኑ ተጽዕኖ ፈጣሪ የኮንግረንስ አባላት በክፉ አይን መታየቱ አልቀረም፡፡ ከዚህ ህግ አንጻር ሀለት እይታዎች አሉ፡፡ በአንድ በኩል አብዛኛዎቹ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት ህግ አውጭዎች የህጉን መሰረታዊ አላማ ችላ ብለው እንደሰሩት ሲታመን በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ነጥብ ከማስቆጠር ያለፈ ነገር የለውም ብለው የሚያምኑ አሉ፡፡ ሴክሽን 230 ድረገጾች ፖለቲካዊ አላማ ይኑራቸውም አይኑራቸውም ሁሉንም የሚጠብቅ ህግ ነው፡፡
በሪፐብሊካኑ አባል ቤን ሻፒሮ በሚንቀሳቀሰው Daily Wire በሚባለው የዜና ምንጭ በየጽሁፎቹ አንባቢዎች ከፍተኛ ስም ማጥፋት የታከለባቸውን አስተያየቶችን ይጽፋሉ፡፡ በሴክሽን 230 ህግ መሰረት አዘጋጁም ሆነ አስተያየት ሰጭዎች ምንም አይነት ህጋዊ ተጠያቂነት የለባቸውም፡፡

ሴክሽን 230 እየተባለ የሚጠራው ህግ
“No provider or user of an interactive computer service shall be treated as the publisher or speaker of any information provided by another information content provider.”
የሚል ሲሆን በጥቅሉ በአንድ ፕላትፎርም የሚሳተፉ ተጠቃሚዎች በሚያሰራጩት መረጃ ምክንያት የፕላትፎርሙ ባለቤት ህጋዊ ተጠያቂነት የለበትም የሚል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በ90ዎቹ በፍርድ ቤት የተወሰነ አንድ ውሳኔ በገመድ አልባ አገልግሎት በሚኖር ህጋዊ ባልሆነ ድርጊት ተጠያቂነት ሊኖር እንደሚችል ታይቷል፡፡ በዚህም ይህ አገልግሎት በህግ የተሰጠውን ሙሉ ነጻነት እንደማይጠቀም መረዳት ይቻላል፡፡
ህጉ ብዙ ችግር አለው ብለው የሚስማሙ ወግ አጥባቂዎቹ ሪፐብሊካኖች እንደ Fight Online Sex Trafficking Act (FOSTA) አይነት የተሻሻሉ ህጎችን በመጥቀስ ይህም ህግ የሶስተኛ ወገን ተጠያቂነትን በሚያመጣ መልኩ መሻሻል አለበት በማለት እየሞገቱ ነው፡፡ ከጥንስሱ ህጉን ያረቀቁት የዲሞክራቱ Ron Wyden እና የሪፐብሊካኑ Christopher Cox ግብ ያደረጉት የ pornographyን መስፋፋት መግታት ነበር፡፡
ምንጭ፡ GIZMODO (https://gizmodo.com/section-230-is-the-foundation-of-the-internet-so-why-d-1833590565)
ያለ ባትሪ የሚሰሩ የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን በቅርቡ ልናይ እንችላለን
ምንም እንኳን እንደ ሀገር ያለንበት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደረጃ የተሸሉ ከሚባሉት ሀገራት አንፃር አነስተኛ የሚባል ቢሆንም ብዙዎቻችን ከቀን ወደ ቀን በእንቅስቃሴ ውስጥ፣ በቤት፣ ቢሮና ሌሎችም ቦታዎች ላይ የምንጠቀማቸው ስማርት ቁሳቁሶች መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነው፡፡ እነዚሀ ቁሶች ስራቸውን ለማከናወን ያስችሏቸው ዘንድ በሆዳቸው የሚታቀፏቸው ባትሪዎች ወዲያው ወዲያው አቅማቸውን የሚሟጠጥ ሲሆኑ በውስጣቸውም በቀላሉ የማይገኙና መርዛማ የሆኑ ቁሶችን ይይዛሉ፡፡ ለዚህም ነው አጥኚዎች ሌላ እነዚህን ቁሶች አንቀሳቃሽ ኃይል ምንጭ ፍለጋ ተሰማርተው የሚገኙት፡፡
አንደኛው ለቁሶቹ ኃይል የማግኛ መንገድ ደግሞ ልክ የፀሐይ ኃይል ማመንጫዎች ፎቶቮልቴክስ ወይም PVን በመጠቀም ከቤት ውጪ እንደሚያደርጉት ሁሉ የቤት ውስጥ ብርሃንንም ለቁሶቹ የኃይል ምንጭነት መተቀም ነው፡፡ ሆኖም ከብርሃን ምንጩ ልዩነት ጋር በተያያዘ ለሶላር ፓኔሎች የሚውለው ግብዓት ተጠቅሞ የቤት ውስጥ ብርሃንን ወደ ኃይል ለመለወጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ አሁን ላይ የለንደኑ ሮያል ኮሌጅ፣ ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ እና የቻይናው ሶቾው ዩኒቨርሲቲ አጥኚዎች በቤት ውስጥ ያለ ብርሀንንም ወደ ኃይል ለመለወጥ የሚያስችል ሶላርፓኔል በመስራት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የጥናቱ አካል የሆኑት ዶ/ር ሮበርት ሆዬ በቤት እና ሌሎች ህንፃዎች ውስጥ ካሉ መብራቶች (አምፖል) የሚመነጭ ብርሃንን ውጤታማ በሆነ መልኩ በመሰብሰብ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መለወጥ እንደሚቻል ጥናቱ እንዳሳየ ተናግረዋል፡፡
የጥናት ቡድኑ ለቀጣዩ ዘመን የሶላር ፓኔሎች ታስበው ከተሰሩት የፔሮቭስካይት ቁሶች ተወስደው ግን ደግሞ በዚህ ቁስ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ታልመው የተሰሩትን ፔሮቭስካይትን መነሻ ያደረጉ ቁሶችን መርምሯል፡፡ ፔሮቭስካይቶች ከተለምዶአዊው ሲልከን ላይ የተመሰረተ ሶላር ፓኔል አንፃር ተመሳሳይ ኃይል የሚያመነጩና ለመስራትም ርካሽ ቢሆኑም መርዛማ የሊድ ንጥረ ነገሮችን ይይዛሉ፡፡ በዚህም ሳብያ እንደ ቢዝመዝ እና አንቲሞኒን ያሉ ግብዓቶችን የሚጠቀሙ ፔሮቭስካይትን መነሻ ያደረጉ ቁሶችን የመስራት እንቅስቃሴ እንዲያድግ ሆኗል፡፡ ታድያ እነዚህ ቁሶች ለአካባቢ ተስማሚ ሆነው ቢገኙም የፀሐይ ብርሃንን በመሰብሰብ ረገድ ግን ውጤታማነታቸው ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም እንደ ጥናት ቡድኑ ግኝት ከሆነ ቁሶቹ በአንፃራዊነት የቤት ወስጥ ብርሀንን በመሰብሰብ ረገድ እጅጉን የተሻሉ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በሙከራቸውም በእነዚህ ቁሶች አማካኝነት የሚገኘው ኃይል የኤሌክትሮኒክ ሰርኪቶችን ለማንቀሳቀስ የሚችል ሆኖ አግኝተውታል፡፡
እንደ ጥናታ ተሳታፊ ባለሙያዎች ከሆነ አዲሱ ግኝት አረንጓዴ ልማትን ይበልጥ የሚያጎለብትና በቅርቡም ባትሪ አልባ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን ሊሰጠን የሚችል ነው፡፡
ምንጭ፡ Tech Xplore
በሩሲያ ቅልጥ እሳተ ገሞራ የተገኘው አዲሱ ምስጢራዊ ማእድን
*********************
ተመራማሪዎች በሩሲያ ቅልጥ እሳተ ገሞራ አዲስ ማእድን ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ እንደሚታወቀው በአለማችን አስጨናቂ ከሆኑና ብዙ ጥፋቶችን ከሚያስከትሉ ተፈጥሯዊ ክስተቶች መካከል እሳተ ገሞራ አንዱና ዋነናው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ገሞራ ካለው ጉዳት በተቃራኒ የተፈጥሮ ምስጢራትን በመግለጥ በኩል የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው ተመራማሪዎች ይስማማሉ፡፡ ለዚህም ነው የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያጠፋልም ያለማልም የሚባለው፡፡
አዲስ በተሰራ ጥናት የሩሲያ ተመራማሪዎች በገሞራ ፍንዳታ ምክንያት የተፈጠረን አንድ አዲስና ያልተለመደ ማእድን ማግኘታቸውን አሳውቀዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ ፔትሮቫይት ሲሉ የሰየሙት አስደናቂው ደማቅ ሰማያዊና አረንጓዴ ቀለም ያለው ጠጣር ንጥረ ነገር ከዚህ በፊት በሳይንስ ተመዝግበው ካሉት ማእድናት ሁሉ የተለየ እንደሆነ ተመስክሮለታል፡፡
ንጥረ ነገሩ የተገኘው በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ በሚገኝ ካምቻትካ ከፍታ ቶልባቺክ በሚባል እሳተ ገሞራ ነው፡፡ ቶልባቺክ ገሞራ ከሺህ አመታት በላይ ታሪክ ያለው የገሞራ ፍንዳታ ሲሆን ሁለት በጣም የታወቁ ፍንዳታዎች አሉት፡፡ ከእነዚህም አንዱ ከ1975–1976 የተከሰተው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከ2012–2013 የተከሰተው ነው፡፡
በመጀመሪያው በነበረው ከፍተኛ ሀይል ያለው ፍንዳታ ብዛት ያላቸው የእሳት ፍንጥርጣሪዎች እና የትም ቦታ ታይተው የማይታወቁ ማእድናት ተገኝተዋል፡፡ በአጠቃላይ የቶለባቺክ ገሞራ 130 ዓይነት በዚህ አካባቢ ብቻ የሚገኙ ማእድናትን አስገኝቷል፡፡ ከእነዚህ ማእድናት የቅርብ ጊዜው ፔትሪቫይት ነው፡፡ ይህም ሰማያዊ ቀለም ያለው ባለ ድቦልቡል ቅርጽ ሰልፌት ማእድን ነው፡፡
በአዲሱ ማእድን የተገኘው የኮፐር ቅንጣት የልተለመደና በቀላሉ የማይገኝ ከ7 የኦክስጅን ቅንጣቶች ጋር የተጣመረ ነው፡፡ የዚህ አይነት ባህሪ የሚገኘው በውህዶች ብቻ እንደሆነ የSt Petersburg University የምርምሩ መሪ ተናግሯል፡፡ የፔተሮቫየት ሞሎኪዩላዊ ቀመሩ (molecular framework) ኦክስጅን፣ ሶዲየም፣ ሳልፈርና ኮፐር በተፈጥሮ አብረው የተሰሩ ናቸው፡፡
ምንጭ Science alert