ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ መሰጠት ተጀመረ
--------------------
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሚገኙ ስታርትአፖችን በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመ ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል፡፡ የሁለት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ይህ ስልጠና በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሚሆኑበት ነው፡፡ በፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ውስጥ የICT ዳይሬክተሩ አቶ ተክሊት በርሄ በስልጠናው ጅማሮ ላይ ለተሳታፊዎች ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ኢንስቲትዩቱ ስታርታፖችን በማገዝ ረገድ እያከናወነ ላለው ተግባር አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡ ዲጂታል ማርኬቲንግ ቀድሞ ይሰራበት የነበረውን የገበያ አካሄድ በመቀየር ከICT ጋራ የተሳሰረ እንዲሆን ማድረጉን የተናገሩር አቶ ተክሊት ይህ ስልጠናም ተሳታፊዎችን በጠቃሚ እውቀት፣ ክህሎት እና ደጋፊ የሆኑ መንገዶች ላይ ግንዛቤን የሚሰጥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዛሬው መርሀ ግብር ጅማሮ ላይ ስለ በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት ልዩ ልዩ ግንዛቤዎችን የሚያስጨብጥ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ባልደረባ አቶ ገብሬ ኩንታኖ የተሰጠ ሲሆን ይህም በይነ መረብ ምንድነው፣ እንዴት ይሰራል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየው እድገት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ተነስተው ማብራርያ ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ በተጨማሪም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን አቶ ገብሬም ሙያዊ ምላሻቸውን ሰጥተውባቸው አልፈዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ዛሬን ጨምሮ ስልጠናው በሚካሄድባቸው በሁለቱም ቀናት ውስጥ ሌሎችም ከዲጂታል ማርኬቲንግ እና አጠቃቀሙ ጋራ የተያያዙ ልዩ ልዩ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እንዲሁም የስልጠናው ተሳታፊዎች አማካኝነት ዳሰሳ የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡ ከነዚህ አብይ ጉዳዮች መካከል ድረ-ገፅ፣ መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀቶች፣ ብራንዲንግ፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ እና ሌሎች የማህበራ ሚዲያ ብሎም የበይነ መረብ አማራጮችን ተጠቅሞ ማከናወን በሚቻል የማርኬቲንግ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡
በስልጠናው ላይ ከቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግንባታ፣ ባልትና እና ሌሎችም ዘርፎች ተውጣጡ 37 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን እነዚህ ከፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ጋራ በመተባበር የተመረጡ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፤ ዘመን ተሻጋሪ መገለጫ
========
መዲናችን አዲስ አበባ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የከተማነት ቅርጿን በእጅጉ የለወጡ ብዙ ግንባታዎችን አስተናግዳለች፡፡ በተለይም ከ1940ዎቹ እና 50ዎቹ የተከናወኑት ግንባታዎች እሳካሁንም ድረስ የከተማችን ዋና መገለጫ ተብለው ከሚወሰዱት ቋሚ ሀብቶች መካከል ናቸው፡፡ ከነዚህ ስመ ጥር ህንፃዎች መካከል ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ወይም በቀድሞ ስያሜው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት ይገኝበታል፡፡ ቴአትር ቤቱ በተለይም ከውጭ በኩል በቀረበው ዝነኛ የአንበሳ ሐውልትም ተለይቶ ይታወቃል፡፡
የዛሬ 40 ዓመት ገደማ በ1973 ዓ.ም በራሱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አማካኝነት ታትሞ በወጣው “ከሙያችን” መፅሔት ውስጥ ከገፅ ሦስት አንስቶ ከሰፈረው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አጭር ታሪክ” ፅሑፍ ውስጥ ስለ ግንባታው የሚያትተውን ክፍል መርጠን አቅርበንላችኋል፡፡
“ከ፷፮ አብዮት ፍንዳታ ወዲህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተብሎ የተሰየመው አዳራሽ ትክክለኛውን ባናውቅም ፋሽስት ሀገራችንን በወረረበት ዘመን ተደላድሎ የመኖር ሕልሙን ለመተርጎም በርዕሰ ከተማችን ቺኒማ ማርኮኒ በሚል ስያሜ ሊያሠራው የጀመረው አዳራሽ መሆኑን በጊዜው የነበሩት አባቶች ይናገሩታል።
እኛም የታሪክ ማስታወሻ መያዝ ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ለብዙ ዓመታት የሕንፃው ውጭና ውስጥ የአላፊው አግዳሚው መንገደኛ መጸዳጃ እንደነበር በገሃድ አይተናል።
በዚህ ወቅት ከ፲፱፻፵፯ ዓ/ም በፊት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የቴአትርና ሙዚቃ ማስፋፊያ ክፍል ነበረው። ከ፲፭ እስከ ፲፰ ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ፷ ያህል የሙዚቃና ቴአትር ተማሪዎችም ነበሩት። ወጣቶች ሙዚቃ ተጫዋቾች በየክብረ በዓሉ በየአዳባባዩ በመገኘት የአማርኛ ዜማዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል ይችላል በዘመናዊ ሙዚቃ መሣሪያ በሰልፍ እየተዘዋወሩ በማሰማት ተወዳጅነታቸውን በይፋ አስመስከሩ። በቴአትሩም በኩል በስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ዮፍታሄ ንጉሤ፤ አፈወርቅ አዳፍሬና በሌሎችም ደራሲያን የቀረቡ ድርሰቶችን በማሳየት ክፍሉ ዝና እያተረፈ ሄደ። ሕዝብም በብዛት ወደ ቀድሞው ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ እየመጣ በቦታ ጥበት የተነሣ መመለስ ጀመረ።
ይኸም የሕዝቡን የቴአትርና ሙዚቃ ፍላጎት እያጎላው ሄደ። ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ አንድ ዘመናዊ አዳራሽ እንዲሠራ ዕቅድ ወጣ። የታወቁ ፕላን ሠራተኞች የነደፉት የኣዳራሽ ሞዴል ቀርቦ ሥፍራው ተመረጠ። ይኸውም ኣቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ፊት ለፊት የአሁኑ ማዘጋጃ ቤት ከተሠራበት ግቢ ነበር።
ሥራው ሊጀመር እንደተቃረበ የቀድሞው ንጉሥ የብር ኢዮቤልዩ ስለደረሰ በአጣዳፊ አንድ ዘመናዊ የቴአትር አዳራሽ እንዲሠራ ትእዛዝ ተላለፈ። ጉዳዩን ጀምሮት ስለነበር ከማዘጋጃ ቤት የማይገነጠል ሆነ። ለዚህም በፈረንሳዩ አርቺቴክት በሄንሪ ሾሜት የቀረበው ሃሳብ ጸድቆ ይኸው አሁን ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተብሎ የተሰየመው ጅምር ሲኒማ ቤት ፍጻሜ እንዲያገኝ ተወሰነ።የማዘጋጃ ቤት ሙዚቃና ቴአትር ሲያስተምራቸው የነበሩት ባለሙያዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ ለሚሠራውም ዘመናዊ ቴአትር ቤት ብቁ ሆነው እንዲገኙ አንድ አሰልጣኝ ከቪየና እንዲመጣ ተደረገ የሙዚቃና ቴአትር ኣሰልጣኙም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እንግዳ ያልነበረና ቀድሞ በሌላ ክፍል ሲሠራ ቆይቶ ኮንትራቱን ፈጽሞ ወደሀገሩ የተመለሰ ስለነበረ ሥራውን ያለችግር ሊጀምር ችሏል
የመሠልጠኑ ሥራ በአንድ ክፍል ፡ የቴአትርና የሙዚቃ ዝግጅት በሌላ ክፍል እንደዚሁም የአዳራሹ ሥራ በየፊናው ይከናወን ጀመር።
በጅምር የቀረውን ሕንፃ በተሻለና በቀለጠፈ መንገድ ፍጻሜ ለማድረስ ኃላፊነቱ የተሰጣቸው አርክቴክት ሐንሪ ሾሜት የሚስማሙትን የሥራ ረዳቶች እንዲመርጡ መፍቀዱ ቀና መንገድ ስለሆነ ታዘዘላቸው።
በዚህ ወቅት በሰኔ ወር ፲፱፻፵፯ ዓ ም ሙሴ ሾሜት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት መሐንዲስ ክፍል በኃላፊነት የሚሠሩ ነበሩ።
በዚሁ አኳኋን ሙሴ ኣላዤ ለዴኮራሲዮን'ሙሴ ካልካ በሙሴ ፈልቶኒና በሙሴ ሞዜ እየተረዱ ለውቅር ሥራ ! ሙሴ ሞሲያን ለፖሊክሮሚ ለሞዛይክና ለመስተዋት ሥራ ደግሞ ሙሴ ፔሬዝና ሙሴ ፒኞ ለመጋረጃዎችና ለንድፍ ሥራ ተመደቡ።
ሙሴ ሾሜት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትርን ሕንፃ ለማስፈጸም በመመረጣቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤታቸውን የሥራ ልምድና ችሎታ አስተባብረው ደስ በሚያሰኝ አኳኋን ሥራውን እንደሚመሩ ቃል ገቡ።
በጊዜው የቀረቡት ዕቃዎችና መሣሪያዎች ለሥራቸውም ውጤት ማስረጃ የቴአትር ቤቱ ሕንፃ እንዴት ተጀምሮ እንዳለቀ መገምገሙ ያረጋግጣል ። የጊዜው ማጠር ይህን ከፍተኛ ሥራ ወደ ፍጻሜ ለማድረስ የሚፈቅድ ኣደለም የሚል ግምት በቀድሞው አስተዳደር ከፍተኛ ባለጣኖች ዘንድ ነበር። ሌሎችም የቴክኒክ ሰዎች የሕንፃወ ሥራ ብቻ የውስጡ ድርጅት ሳይጨመር ከሁለት ዓመት የበለጠ ጊዜ ይጠይቃል የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር። ነገር ግን እስከ ኢዮቤልዩ በዓል የነበረው ጊዜ አራት ወር ብቻ ሲሆን ለሥራው የሚያስፈልጉት አብዛኞቹ ዕቃዎች የሚመጡት ከውጭ ሀገር ነበር።
ከዚህም በላይ ወቅቱ የክረምት መግቢያና እንዲሁም በአውሮፓ ያሉት የሚበዙት የንግድ አካባቢዎች በያመቱ በበጋ ወራት ለዕረፍት የሚዘጉ በመሆናቸው በሁለቱ ተቃራኒዎች የተፈጠረው ችግር እጅግ ከፍ ያለ ነበር።
ሶስት ሳምንታት ያህል ያለማቋረጥ በተደረገው ጥናት የመጀመሪያው ክፍል በአስተማማኝ ወደ ፍጻሜ ደረሰ። ይህም የሆነው በፓሪስ ከተማ በሚገኘው በሐንሪ ሾሜት ዋና መሥሪያ ቤት ፡ በአዲስ አበባው ጽሕፈት ቤትና እንደዚሁም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተጨማሪ በመደባቸው መሐንዲሶች ሕብረትና መረዳዳት ነበር።
ስለሥራው ጨረታ ተካሂዶ ለሁለት ተቋራጮች ተሰጠ። ኣንደኛው ተቋራጭ የጣና ማህበር የሚባለው ሲሆን የተመደበለትም በተለይ የቴአትሩ የውስጥ ድርጅት ስለነበር በሰባት መቶ ሃምሳ ሞያተኞች ሥራውን ጀመረ። ሁለተኛው ተቋራጭ “ጄ ሳልሞን” የሚባለው ነበር። እሱም በሁለት መቶ ሞያተኞች የአደባባዩንና የሕንፃውን ሥራ ጀመረ። በዝናቡ ምክንያት እጅግ በጣም አስቸጋሪና የሕንፃው ሥራ ፍጻሜም አጠራጣሪ ሆኖ እንደነበረ አይዘ ነጋም። በዚህና በመሳሰለው ሁኔታ ሥራው ሲካሄድ የሾ ሜት ጽሕፈት ቤት ሌሎቹን ጉዳዮች የውስጥ ሥራ ዝግጅት ማጣደፍ ቀጠለ። እነሱም ማለት የውስጥ መጋረጃዎችን ቅርጻቅርጾችን ፡ ልዩ ልዩ ዕቃዎችንና ፡ ሥዕሎችን ምን ጣፎችን ፡ የትርዒት ማሳያ ፡ መድረክ የሲኒማ መሣሪያ ዎች ፡ መስታወቶች : ሞዛይክ የቡና ቤት ዕቃዎችና ሌሎችንም ነበር። በተጨማሪ ከቴአትር ቤቱ ሥራ ተነጥሎ የማይታይ ሐውልቶች እንዲሠሩ ሃሳብ ቀረበ። በቴአትር ቤቱ አደባባይ ለሚታየው ሐውልትና በአዳራሹ መግቢያ ለቆሙት ስድስት ቅርጾች ሥራ ጉዳይ ኣንድ ውድድር ተዘጋጀ። በዚህም ውድድር ሞሪስ ኮልካ የተባለው ተወ ዳዳሪ አሸነፈ። ይኸ ተቋራጭ ማሸነፉ ለንጉሡ ቀርቦ ንድ ፉን ካሳየ በኋላ ተፈቀደ። በአዳራሹ መግቢያ ላይ በፕ ሎሞብ የተሠሩት አራት ቅርጾች ኣራቱን የኪነጥበብ ባሕ ርያት የሚያስረዱ በመሆናቸው ወደቴአትሩ አዳራሽ የሚ ገቡ ሁሉ የመጀመሪያ አትኩሮታቸው የሚያርፈው እነሱ ላይ ነው።
እነዚህ ባሕርያት ተራዠዲ ፡ ኮሜዲ ' ሙዚቃና ዳንስ ሲሆኑ ቀድሞ በአተረጓጐሙ የተስማሙ ሊቃውንት መግለጫ ሰጥተውበት ነበር።
በዚሁ መግቢያ በደረጃው ግራና ቀኝ የሁለት እንስሳት ቅርፅ እንዳለ ግልጽ ነው። በውጭ በኩል በቴአትሩ አደባባይ ላይ በዚሁ ጠራቢ የተሠሩ ከውኃ ፋፋቴ ውስጥ የሚወጡ የሶስት ዓሣዎች ምስል ተሠሩ።

የአዳራሹን መስ ታዎቶች ለማዘጋጀት ሲ ሞሲዮን የተባለ ሠዓሊ ተመረጠ። በልዩ ልዩ ሕብረ ቀለም የደመቀው መስተዋት የተለየ ውበት ቴአትር ቤቱ እንዲያጎናጽፍ በጥናት የተሠራ በመ ሆኑ የተመልካች ዓይን የሚስብና ምርምር ውስጥ የሚከት ሆነ። በአዳራሹ ውስጥ ያሉት ወንበሮች የእንጨት ልባሶች መጋረጃዎች የአዳራሹ ዙሪያ ፕላስቲኮች : ምንጣፎች በሙሴ ጃኮብሰንና በሙሴ ቢኒ መሪነት በቴል አቪቭ የተሠሩ ናቸው። በአጭር ጊዜ ውስጥ እነዚህን የተጠቀሱትን ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከሥፍራወ በማምጣትና በማገጣጠም ቅልጥፍናውና በቴክኒክኦ በኩል ያለውን ሙሉ ችሉታ ተቋራጩ ክፍል አስመስክሮ ከፍተኛ ዝና በጊዜው አግኝቷል።
ለፋፋቴዎች የሚያስፈልጉትን የውኃና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ያቀረበ የረሪኔክ የንግድ ቤት ነበር። እስከ ፲፭ ሜትር ከፍታ የሚደርሰው የውኃ ፋፋቴ በ፯ ዘውድ የሚመሳሰሉ ሌሎች ፏፏቴዎች የተከበበ ሆኖ ነበር የተሠራው። በምሽት ጊዜ በመብራት ኃይል ደምቆ ሲታይ የሚማርክ ገጽታ ነበረው።
የቀድሞው ንጉሥና ንግሥት የተለዩ መመልከቻዎች ሥፍራ ለእግር መርገጫ የዋለውን ምንጣፍ ያዘጋጀው በፈረንሳይ እጅግ የታወቀው ምንጣፍ ሠሪ ዣን ሉርሳ ነው። ሥራውም በሙሉ የተከናወነው በእርሱ ኢንዱስትሪ ውስጥ ነው።
ለመድረክ የትርኢት ብርሃን ሥራ የዋለውን የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ያቀረቡ ሬይሽ ቦጅልና ስቴይነር የተባሉት የአውስትሪያ ነጋዴዎች ነበሩ። በዚህ አኳኋን ማንኛውም ተሟልቶ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ ም ከእኩለ ቀን በኋላ በቴአትሩ አደባባይ ያለው የአንበሳ ሐውልት ቴአትር ቤቱ ተመርቆ ተከፈተ ።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆንም ከፈረንሳይ ሀገር በመጡ የባሌት አርቲስቶችና ከማዘጋጃ ቤት ወደ ቴአትር ቤቱ በተዛወሩ አክተሮችና ሙዚቀኞች “ዳዊት ኦሪዮን” ተውኔት የመጀመሪያው ትርኢት ፩ሺ፪፻፲፬ ተመልካች በተገኙበት የመጀመሪያው የብሔራዊ ቴአትር የትርኢት ምዕራፍ ፡ ተከፈተ ። ቴአትር ቤቱን የልዩ ልዩ ክፍል ዓለም ጋዜጠኞች መጥተው ጎብኝተው በኣፍሪቃ አህገር አሉ ከሚባሉት ታላላቅ ኦፔራዎች አንዱ መሆኑን እየመሰከሩ ሲጽፉ ብዙ የውጭ ሀገሮች አርቲስቶች እየመጡ ትርኢታቸውን ለማቅረብ ጥያቄ እያቀረቡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የፈረንሳይ የፕራግ ፤የፔኪንግ ኦፔራ ፡ የፍራንሱዋዝ ሉዱስዴ የፒያኖ ጨዋታ፤የዓይነ ስውሩ የጆርጅ ቴማሊ የፒያኖ ጨዋታ፤በስመ ጥሩው ባሪ ቶን ተጫዋች ዊሊያም ዎርፊልድ ከአሜሪካ ፤ የቶኒክ ጊርጊዮ የፒያኖ ጨዋታ ፡የኣሌክሳንደር ቦን ስዊድንና የፈዛስክቤል የክላሲክ ዳንስ ትርኢት ፤ የሞስኮ ናሽናል ቴአትር ተጨዋቾች : የኒው ኦርሊአንስ የጃዝ ተጫዋቾች ዊልበር ደ ፓሪና ረዳቶቹ ፡ በተከታታይ መጥተው በቴአትር ቤቱ ትርኢታቸውን አቀረቡ።
የቴአትር ቤቱ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት ሥር ነበር። የቴኣትር አዘጋጅና የዘመናዊ ኦርኬስትራ መሪ ፍራንዝ ዜልዌከር የሚባል ሲሆን የመድረኩን ሥራ ኃላፊ ሪቻርድ ሄትማኒክ ፤ የመብራቱ ሥራ ኃላፊ ፍራንዝ ኒል ሁሉም ከአውስትሪያ የመጡ የኪነት ሰዎች ነበሩ። የዴኮሬሽን አዘጋጁም ሲኞር ፉም ነበሩ።”

የአዕምሮ ህመም እያስከተለ ላለው ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ ምን ይሁን ? ክፍል ሁለት
https://www.youtube.com/watch?v=LwcniVU8VpM
ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይከታተሉን
(Nilesat 12520/v/27500)
(በተጨማሪም Ethiosat ላይ እንገኛለን)

YouTube
የአዕምሮ ህመም እያስከተለ ላለው ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ ምን ይሁን ? ክፍል ሁለት
ከአያቷ የተወለደችው ልጅ
*****************
የ51 ዓመቷ ጁሊ ላቪንግ የሴት ልጇን በማህጸኗ አሳድጋ በመውለድ የልጅ ልጇን የወለደች አያት ለመባል በቅታለች፡፡ ብሪና ሎክዉድ እና አሮርን የህጻኗ ስነ-ህይወታዊ ወላጆች ሲሆኑ አዲሷ ህጻን ለሁለቱ ጥንዶች የመጀመሪያ ልጅ ናት፡፡
ህጻኗ ብሪያር ጁሌት ተብላ የተጠራች ሲሆን ስለሁኔታው እናቷ (ያልጸነሰቻት) እንዲህ ትላለች "ሁኔታውን እንዲህ ነው ብሎ ማስረዳት በጣም ከባድ ነው እውነት አይመስልም እናቴ ለኔ ስትል በዚህ ሁሉ ነገር ላይ እንዳለፈች ሳስብ በጣም ከባድ ነገር ነው" ፡፡ ወይዘሮ ላቪንግ ትወልዳለች ተብሎ ከተጠበቀው ከ10 ቀን በፊት ህጻኗን ለመውለድ ተገድዳለች፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በእትብት አካባቢ በተፈጠረ ችግር ምክንያት እንደሆነ ሎክውድ ተናግራለች፡፡
የእርግዝናውን ወቅት በተመለከተ እናቴ ሀሉንም ነገር በብቃት ተወትታዋለች ነገር ግን በጥቂቱም ቢሆን ጉዳት አጋጥሟታል ስትል ሎክውድ ተናግራለች፡፡ በሆስፒታል ውስጥ ነበረው ሁኔታ ስሜታዊነት የበዛበት ነበር፡፡ በወቅቱ ፍርሀትም ደስታም ይፈራረቁብን ነበር የሀኪሞች ቡድን የሚገርም ስራ ሰርተዋል ስትል አክላለች፡፡
ሁለቱ ጥንዶች በ2016 ተጋብተው ወዲያው ልጅ መውለድ ቢፈልጉም አልተሳካላቸውም፡፡ ከአንድ አመት ሙከራ በኋላ ሎክውድ የስነ-ተዋልዶ ስፔሻሊስት መፈለግ ጀመረች፡፡ ለሁለት ዓመታት ያክል በሀኪም ምክር የተለያዩ ሙከራዎችን ስታደርግ የቆየችው ሎክውድ ማህፀኗ ምንም አይነት ለውጥ ሊያመጣ ባለመቻሉ ሌላ ማህጸን መፈለግ እንዳለባት መከራት፡፡
መውለድ አለመቻሌ የህይወት ህልሜን ሁሉ አጨልሞብኛል የምትለው ሎክውድ መካንነት በህይወቷ ውስጥ ካጋጠሟት ችግሮች ሁሉ ወደር የሌለው እንደሆነ ትናገራለች፡፡
ከዚያም ሀኪሟ ከቤተሰብ ወይም ከቅርብ ጓደኞቿ መካከል ማህጸን የሚያውሳት ሰው እንድትፈልግ ነገራት፡፡ ምንም እንኳን ይህንን ሀሳብ ደግፋ እንድትቀጥልበት ያበረታታቻት ቢሆንም ተፈላጊዋ ባለማህጸን የ51 ዓመት እናቷ ልትሆን እንደምትችል በፍጹም አልገመተችም ነበር፡፡
19 የማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፈችው ወይዘሮ ላቪንግ ሁለቱን ልጆቼን ስወልድ እንደነበረው አሁንም ሙሉ ጤንነት የሚሰማኝ በመሆኑ በቀላሉ ልወጣው እችላለሁ ብላ ታስባለች፡፡
ይህ ሀሳብ የእውነት ሊሆን የቻለውም ከአዋዋይ ተቋም ጋር በነበራቸው የመጀመሪያ ቀጠሮ ነበር፡፡ ከዚያ ቀጠሮ ቀን በኋላ ወይዘሮ ላቪንግ በአምስት የተለያዩ ስፔሻሊስቶች የተለያዩ ምርመራዎችን አድርጋለች፡፡ ከዚም የሽል (embryo) ማዘዋወር ስራ ተሰራ፡፡ በቀጣዩ ወር ለወይዘሮ ላቪንግ የእርግዝና ምርመራ ተደርጎላት የሽል ማዘዋወሩ ስኬታማ እንደነበር እና የአንድ ወር ነብሰ-ጡር እንደሆነች ተረጋገጠ፡፡
ከዚህ በፊት በልጅ ዙሪያ ብዙ አለመሳካቶች ገጥመውን ስለነበር በተፈጠረው ነገር ለመደሰት አልቸኮልንም የምትለው ሎክውድ ለሚወለደው ልጅ እንኳን ማቀድ የጀመርነው የእርግዝናው ግማሽ ከተጠናቀቀ መኋላ ነበር ስትል ታስረዳለች፡፡ እርግዝናው የተረጋገጠው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከቤት አትውጡ ከመታወጁ ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር፡፡
ሎክውድ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ድረስ ከእናቷ እና ከልጇ እናት ክይዘሮ ላቪንግ ጎን አልተለየችም ነበር፡፡
ምንጭ abc News

ቻይና የኮቪድ ክትባትን ለአፍሪካ ሀገራት ለማድረስ እንደምትሰራ አስታወቀች
===================
የቻይና ውጩ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዪ ሀገራቸው የኮቪድ ክትባቶች በዓለም ገበያ ላይ እንደሚኖሩ ለማድረግ አሁንም ፍቃደኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ክትባቶቹ ለግልጋሎት ዝግጁ በሚሆኑበት ሰዓት ለአፍሪካ ሀገራት የማከፋፈልን ጉዳይ ቻይና እያሰበችበት ነው ሲሉም መናገራቸውንም ግዙፉ የቻይና ሚዲያ ተቋም CGTN ዘግቦታል፡፡
ዋንግ ይህን ያሉት የቻይና አፍሪካ ትብብር ጉባኤን (FOCAC) 20ኛ ዓመትን አስመልክቶ በተደረገው የአቀባበል ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡ ሀገራቸው በህብረተሰብ ጤና፣ ምጣኔ-ሐብቱን ዳግም በመክፈት እና የሰዎችን ህይወት በማሻሻል ላይ በቀዳሚነት በማተኮር ከቻይና አፍሪካ የትብብር ጉባኤ የሚወጡ ውሳኔዎችን ከተግባር ለማዋል እንዲሁም በኮቪድ-19 ዙርያ ከአፍሪካ ጋራ በጥብቅ መስራቷን ትቀጥላለች ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቻይናና አፍሪካ አሁን ያጋጠሙ አለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በመሻገር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ጋራ መፃዕይ ሊገነቡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ብቅ ብቅ እያሉ ያሉ የክትባት እምርታዎችን ተከትሎ ብዙዎቹ ሐብታም ሀገራት አብዛኛው ክትባቶቹን በመቀራመት ውስጥ እንደገቡ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ አዲስ ሪፖርት እንደሚያሳውም እነዚህ ሐብታም ሀገራት ቀድመው ወደ ምርት ይገባሉ ከሚባሉት የኮቪድ-19 ከትባት ፍሬዎች ውስጥ 8.8 ቢሊዮን የሚሆኑትን ለመግዛት የሚያስችላቸውን ስምምነት አድርጓል፡፡ እንደ አውስትራልያ ያሉት ጥቂት ሀገራት ከሚፈፅሙት ግዢ ውስጥ የተወሰነውን ለደሀ ሀገራት ለመለገስ ቃል የገቡ ቢሆንም ይህ ግን የሚያመጣው ተጨባጭ ለውጥ እብዛም ነው፡፡ ታድያ ምንም እንኳን የክትባቶቹ መጠን እና ከዚኅ ቀደም ለክትባቶቹ ባይተዋር ሆኖ የተቀመጠውን አፍሪካዊ በምን ደረጃ ከወረርሺኙ መጠበቅ እንደሚችሉ ከወዲሁ ማወቅ ባይቻልም ቻይና ክትባቶቹን ለአፍሪካ ሀገራት ለመለገስ የሳየችው ፈቃደኝነት ተስፋ ሰጪና ምናልባትም ሌሎች ታላላቅ ሀገራትም ተመሳሳዩን እንዲያደርጉ የሚገፋፋ ሊሆን ይችላል፡፡
ምንጭ፡ CGTN

የስድስተኛ ትውልድ (6G) ገመድ አልባ አገልግሎት ማበልጸጊያ ማእከል ተከፈተ
************************************
የእንግሊዙ ሰሬይ ዩኒቨርሲቲ የከፈተው ማዕከል ፈጣን ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አጋጣሚዎች ሲፈጠሩ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ እንዲያግዝ የስድስተኛ ትውልድ የገመድ አልባ አገልግሎትን ለማበልጸግ የታለመ ነው፡፡ ለምሳሌ በየትኛውም የአለም ክፍል የሚያስፈልግ የህይወት አድን ስራን ሀኪሞች ሮቦቶችን እንዲጠቀሙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
ምንም እንኳን በእንግሊዝ የአምስተኛ ትውልድ (5G) የገመድ አልባ አገልግሎት ጥቅም ላይ ለመዋል ጥቂት አመታት የሚያስፈልጉት ቢሆንም በስድስተኛ ትውልድ ላይ የተለያዩ ጥናቶች እየተተገበሩ እንደሆነ የዘገበው sky news ነው፡፡ የ4G አገልግሎት የተለያዩ የምስልና ድምጽ ቅንብሮችን (ቪዲዮ) እና ሙዚቃ ለመከታተል ያስቻለ ሲሆን የ5G አገልግሎት ደግሞ ካለው የተሸለ ከፍያለ አግልግሎትን በግዙፋን ኢንዱስትሪዎች ሳይቀር ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዩኒቭርሲቲው እየተዘጋጀበት ያለው የስድስተኛ ትውልድ ገመድ አልባው አገልግሎት ፈጣን የሆነ የቀጥታ ግንኙነት ወይም ተግባቦት እንዲኖር ያስችላል፡፡ ለዘ ታይምስ መጽሔት ሀሳባቸውን ያጋሩት ፕሮፌሰር አለን ዉድዋርድ አዲሱ ትውልግ ከመድሀኒት ጋር የተያያዘው ስራ ዋናው ተጠባቂ ነገር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ይህንንም ሀኪሞች በአለም ከአንዱ ጥግ ሆነው በሌላኛው የአለም ጥግ ያለን አንድ ታካሚ በሮቦት በመታገዝ ማከም ያስችላል ብለው ገልጸውታል፡፡ አክለውም ምንም እንኳን ምርምሩ አሁን በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ ቢሆንም ተስፋ የተታለባቸው ግኝቶች እንዳሉ ፕሮፌሰሩ ገልጸዋል፡፡
የ5G አገልግሎት ከፍተኛ የሆነ ኤሌክትሮ መግነጢስ በመጠቀም ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን ማስተላለፍ የሚያስችል ሲሆን ይህ ግን ሁልጊዜ ላይሰራ እንደሚችል ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡ የስድስተኛ ትውልድ ማበልጸጊያ ማዕከሉ ዳይሬክተር የሆኑት ፐሮፌሰር ራሂም ታፋዞሊ በዚህ ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የተለየ አካሄድ መከተል አለማቀፍ ችግሮችን ለመፍታት ያስችለናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው "ambient information" እና "ubiquitous coverage" የተባሉ የጥናት ጭብጦችን እንደሚከተል አሳውቋል፡፡
የመጀመሪያው ሀረግ አካላዊውን እና ምናባዊውን አለም የሚገልጽ ጥምር ሲሆን ከፍ ባለ የዲጂታል አገልግሎት ደረጃ የሰዎችን ስሜት ከሩቅ በሌሎች መሳሪያዎች ላይ ለማጋባት የታለመ ነው፡፡
ሁለተኛው ደግሞ በቦታ ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት ገደብ እንዳኖር ለማስቻል የታለመ እሳቤ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ይህንን ስራውን ያለውን ገመድ አልባ አገልግሎት ለማሻሻልና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም በማለም እየሰራ እንደሆነና አገልግሎቱን በየትኛውም የአለማችን ክፍል ለማቅረብ እንዳሰበ ተናግሯል፡፡
ይህንን አገልግሎት አሁን ላይ ማሰብ ያስፈለገበትን ምክንያት ዩኒቨርሲቲው ሲገልጽ የአምስተኛ ትውልድ አገልግሎትን እየተቆጣጠሩ ያሉ ሀገራትና ድርጅቶች ከ10 እና 15 አመታት በፊት ማሰብ እንደጀመሩ ስለሚታወቅና በዚህ ዘርፍ እንግሊዝ ቀዳሚ እንድትሆን በማሰብ እንደሆነ መረጃ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ sky news

እውነት ግን ግመሎች በሻኛቸው ውሃ ያጠራቅማሉ?
=========================
ግመሎች በዚያ አስከፊ በረሃ ውስጥ ያለ ብዙ ችግር ለመኖር ውሃን በሻኛቸው ያጠራቅማሉ የሚለው ሀሳብ በብዙ ሰዎች ውስጥ የሰረፀ ነው፡፡ ዕውነታው ግን ይህ አይደለም፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ድንቅ እንስሳት ያገኙትን ውሃ በቁጠባ የመጠቀምያ ብዙ መንገዶች ቢኖሯቸውም ሻኛቸው ግን ከነዚህ አንዱ አይደለም፡፡
ታድያ ሻኛው ምን ይሰራላቸዋል?
ለዚህ መልሱ ስብ ለማከማቸት ነው፡፡ ግመሎች ምግብ በሚያገኙበት ሰዓት በቂ ካሎሪን በመመገብ ሻኛቸውን ያደላድላሉ፤ በዚህም ምግብ ችግር በሚሆንባቸው ጊዜያት ብዙም ሳይቸገሩ ለብዙ ጊዜ መቆየት ይችላሉ፡፡ ሻኛውን ጠብሰቅ አድርጎ የሞላ አንድ ግመል ከ4 እስከ 5 ወራት ድረስ ያለ ምግብ የመቆየት አቅም አለው፡፡ ታድያ በነዚህ ምግብ አልባ ወራት ውስጥ የግመሉ ሻኛ ልክ በትንሹ እንደተከፈተ ፊኛ ቀስ በቀስ መሟሸሽ ይጀምራል፤ ፊኛውን መልሰን ስንነፋው እንደሚወጠር ሁሉ ሻኛውም ምግብ ሲያገኝ እንደቀድሞው መሙላት መደላደል ይጀምራል፡፡
ሌላው ምናልባት ለነዚህ እንስሳት ቅርበት ለሌለን ሰዎች አዲስ የሚሆንብን እውነታ ሻኛው ሲወለዱ አብሯቸው የማይወለድ መሆኑ ነው፡፡ እንደውም ጡት በሚጠቡበት ዕድሜያቸውም ሆነ ከዚያ ወድያ ባሉት ጥቂት ወራት ሁሉ ጀርባቸው ባዶ ሜዳ ሆኖ ይቆያል፡፡ ሻኛው ማደግ የሚጀምረው በተወለዱ በአስረኛው ወር ጀምሮ ነው፡፡
ምድራችን ሁለት አይነት ግመሎችን ታኖራለች፡፡ የመጀመሪያዎቹ የአረብ ግመል (Camelus dromedarius) ሲሆኑ በሀገራችን ጭምር ተስፋፍተው ያሉ ባለአንድ ሻኛ ግመሎች ናቸው፡፡ ሁለተኛው የግመል አይነት ግን ባክትሪያን ግመል (Camelus bactrianus) ተብለው የሚታወቁት ሲሆኑ በምዕራባዊ ቻይና እና ማዕከላዊው የእሲያ ክፍል ያሉና ባላቸው ሁለት ሻኛ ተለይተው የሚታወቁ ግመሎች ናቸው፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው፤ የሻኛው መብዛት ከባለ አንድ ሻኛ ግመሎች ለበለጠ ጊዜ ምግብ ሳይመገቡ ሊያቆያቸው አይችልም፡፡
ብዙዎች እንስሳት ስብ የሚያጠራቅሙት በሆዳቸው በኩል ነው፡፡ ይህ ግን ለግመሎች አይሰራም፤ ስቡን የሚያጠራቅሙት ጀርባቸው ላይ ነውና፡፡ ለዚህ ከሚሰጡት ማብራርያዎች ውስጥ አንደኛው ግመሎች በዚያ በረሃ እረፍት የሚያደርጉት በሆዳቸው በመተኛት ስለሆነ ይህ ስብን በሆዳቸው በኩል ለማከማቸት ከባድ ማድረጉ ነው፡፡ ሁለተኛው ማብራርያ ደግሞ ግመሎቹ በበረሃ ውስጥ ስለሚኖሩ ወደጎን አለመስፋታቸው እና ቁመተ ለግላጋነታቸው ስቡ ከጎን ይልቅ ወደላይ ከመቀመጡ ጋራ ተዳምሮ ለፀሐይ እና ከፍተኛ ሙቀት ያላቸውን ተጋላጭነት ይቀንሰዋል የሚለው ነው፡፡
እስካሁን እንደተብራራው ግመሎች ሻኛቸውን ለውሃ ሳይሆን ለምግብ ማከማቻነት ይጠቀሙታል፡፡ በዚህም ምክንያት አስከፊውን በረሃ ይቋቋሙ ዘንድ ሌላ የውሃ እጥረትን መቋቋምያ መንገድ ተበጅቶላቸዋል፡፡ ለምሳሌ በአንድ ጊዜ ብቻ ግመሎቹ ሰላሳ ጋሎን አልያም 114 ሊትር ውሃ የሚጠጡ ሲሆን ይህን ውሃ ለማስቀመጥ ሲሉ ሰገራቸውን የሚያስወግዱ፤ ኩላሊታቸውም መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከውሃ ውስጥ በማስወገድ በተቻለው መጠን ውሃ እንዲይዙ ያደርጋል፡፡ ሌላም ብዙ ውሃን በአስገሚ አኳሀን የመጠቀሚያ መንገድ አላቸው፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ በአፍንጫቸው ከሚስቡት አየር ውስጥ እርጥበትን ይሰበስባሉ፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ጠጣር (crystal) ኤሌክትሮን ከ86 ዓመታት ሙከራ በኋላ
*******************************************
በ1934 የነበረው የፊዚክስ ሊቅ ዩግኔ ዊግነር ለየት ያለ የክሪስታል እሳቤን በሀሳብ ደረጃን አስቀምጦ ነበር፡፡ አንድ ኔጌቲቭ ቻርጅ የተሞላ ኤሌክትሮን እፍግታው በተወሰነ ደረጃ ከቀነሰ ንኡስ ቅንታቶቹ (subatomic particles) በመደራረብ ክሪስታል ኤሌክትሮን ይፈጥራሉ ይህ ሀሳብ ነው የዊግነር ክሪስታል በመባል የሚታዎቀው፡፡
የኤሌክትሮኖች እረፍት አልባ ባህሪ በአንድ ቦታ ተወስነውና ረግተው እንዲቀመጡ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በጣም አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡ ነገርግን የፊዚክስ ተመራማሪዎች ቡድን የማይቻል የሚመስለውን ታንግስተን በሚባለው ንጥረ ነገር ማሳካት ችሏል፡፡
እንደ ዳይመንድና ኳርትዝ ያሉ ክሪስታሎች በታወቀ ልኬት ተስተካክለው በተቀመጡ ባለሶስት ጎን እይታ ተደራራቢና የተያያዙ ቅንጣቶች የተሰሩ ናቸው፡፡ እንደ ዊግነር ሀሳብ ኤሌክትሮኖች በተመሳሳይ አኳኋን በመሰደር ጠታር ክሪስታል መፍጠር ይቻላል ነገርግን ይህ የሚሆነው ኤሌክተሮኖቹ የረጉ ወይም የማይንቀሳቀሱ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
የኤሌክትሮኖች እፍግታ በበቂ ሁኔታ ከቀነሰ የእንቅስቃሴ ሀይላቸውን በመቀነስ በአንድ አካባቢ ረግተው እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ኤሌክትሮኖች በጣም ጥቃቅን ነገሮች ናቸው ምንም እንኳን እኛ የምናደርገው ነገር ባይኖርም እነሱ ግን ያለእረፍት እንቅስቃሴ ላያ ይሆናሉ፡፡
ኤሌክትሮኖች ካላቸው የእንቅስቃሴ ባህሪ የተነሳ ጠጣርነታቸው ሁሌም ለመቅለጥ የተጋለጠ ነው፡፡
በ2018 የ MIT ተመራማሪዎች በዊግነር ክሪስታል እሳቤ ኢንሱሌተር ለመስራት ያልተሳካ ሙከራ በግራፌን አድርገው ነበር፡፡ የአሁኑ ምርምር ቡድን tungsten disulfide (WS2) እና tungsten diselenide (WSe2) የሚባሉ በልዩ ሁኔታ በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የበለጸጉ ሁለት ንጥረ ነገሮች ላይ ሙከራውን አድርጓል፡፡
ምንጭ ScienceAlert