ከ20 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የአልዛይምር መድሃኒት ፍቃድ ሊያገኝ ነው
በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ትልቅ ዝናን ካተረፉ የመድሃኒት አምራቾች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ባዮጂን (Biogen) ከጃፓን አቻው ኢዛይ (Eisai) ጋር በመተባበር ያበለፀገው የአልዛይምር መድሃኒት ከሁለት አስርት አመታት በኋላ አገልግሎት ላይ ለመዋል የሚያስችለውን ፈቃድ ሊያገኝ እንደሚችል ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስታውቋል፡፡
የማዕከላዊ እና የከባቢያዊ የነርቭ ሥርዓት መድኃኒቶች አማካሪ ኮሚቴ አርብ እለት በነበረው ስብሰባ አዲሱ የአልዛይምር መድሃኒት ፍቃድ የሚገኝበት ሁኔታ እንዲመቻች ለአሜሪካ የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር ምክረ ሃሳብ ማቅረቡን እና በዚህ ውሳኔ መሰረትም ከረዥም ጊዜያት በኋላ በሽታውን የሚከላከል መድሃኒት ጥቅም ላይ የመዋል እድል እንዳለው የአማካሪ ኮሚቴው አባል ፕሮፌሰር ሩዶልፍ ታንዚ ተናግረዋል፡፡ እንደሳቸው ገለፃ የአማካሪ ቡድኑ ፍቃድ የማግኘት ውሳኔው ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚኖረው በማንሳት የምግብና የመድሃኒት አስተዳደር (FDA) ምክረ ሃሳቡን ከግምት ውስጥ እንደሚያስገባ ያላቸውን እምነት ይገልፃሉ፡፡
Aducanumab የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የአልዛይምር ማከሚያ መድሃኒት እስካሁን ባለፈበት የኪሊኒካል ሙከራ ብዙ ታማሚዎች ላይ መልካም ተስፋ እንዳሳየ የሚናገሩት የአልዛይምር መቆጣጠሪያ ክሊኒክ ዋና ዳይሬክትር ዶ/ር ሪቻርድ ኣይዛክሰን መድሃኒቱ በአግባቡ ከመስራቱ ውጭ ግን የደህንነቱ ጉዳይ፣ ከወጪ ምጣኔው አንፃር እንዲሁም ከሌሎች ህጋዊ እሳቤዎች አኳያ ጥብቅ ምርመራ እንደሚደረግበት አንስተዋል፡፡ መድሃኒቱ ለረዥም ጊዜያት በተለያዩ ሂደቶች ሙከራ ሲደረግበት የቆየ ቢሆንም ከሃምሌ 2020 እነስቶ ውጤታማነቱ እየተረጋገጠ በምጣቱ ፍቃድ የሚያገኝብት ሁኔታ እንዲመቻች መደረጉንም የመድሃኒት አምራቹ ባዮጂን አስታውቋል፡፡
እንደአውሮፓውያኑ ከ2004 አንስቶ በሽታውን የሚከላከል ኖቬል መድሃኒት ፍቃድ አለማግኘቱን የሚያወሳው ዘገባው፤ አዲሱ መድሃኒት ግን አሁን ባለው ሁኔታ ፍቃድ የሚያገኝ ከሆነ በአልዛይምር በሽታ ምክንያት በአንጎል ውስጥ የሚፈጠረውን amyloid beta ለማስወገድ እና በሽታ የመከላክለ አቅምን ለማጎልብት በእጅጉ አንደሚረዳ ገልጿል፡፡ CNN

መግነጢሳዊ ክልልን ለማጥፋት ባለ 178 ዓመት እድሜ ጠገብ እሳቤ
*****************************************
መግነጢሳዊ ክልልን (magnetic field) ማጥፋት እንደ ኳንተም ቴክኖሎጂ፣ ባዮሜዲሲንና ስነ-አእምሮ ላሉ ዘርፎች እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ሁለት የሰሴክስ ዩኒቭርሲቲ የፊዚክስ ምሁራንን ያካተተው የተመራማሪዎች ቡድን ከርቀት በመሆን መግነጢሳዊ ክልልን በትክክል ማጥፋት የሚችሉበትን መንገድ ማግኘታቸውን SciTechDaily የተሰኘ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ የመረጃ ተቋም በድረ-ገጹአስነብቧል፡፡ በዚህም እነዚህ ተመራማሪዎች በዘርፉ ረብ ያለው ነገር በመስራት የመጀመሪያ እንደሆኑ የወጣው መረጃ ያሳያል፡፡
ስራው በተለያዩ መስኮች ጥቅም ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ለምሳሌ ያክል እንደ አልዛይመርና ፓርኪንሰን ያሉ የስነ-አእምሮ ጤና ችግር ያለባቸው ህመምተኞች ለወደፊት አስተማማኝ ህክምና ሊያገኙ ይችላሉ የሚል ተስፋ ተጥሏል፡፡ ለህክምና ስራ አዋኪ የሆነው መግነጢሳዊ ክልልን ለማስወገድ መላ ከተገኘ ሀኮሞች በበሽተኞች ጭንቅላት ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ትክክለኛ ነገር አጥርተው መመልከት ይችላሉ ሲል መረጃው አክሎ አስነብቧል፡፡
“Earnshaw’s Theorem” በመባል የሚታወቀው እሳቤ በ1842 የመግነጢሳዊ ክልልን መወሰን ወይም መከለለል እንደማይቻል አሳውቆ ነበር፡፡ የምርምር ቡድኑም ይህን እሳቤ ፈጠራ በታከለበት ስልት እሳቤውን ይቻላል ወደሚል መለወጥ ችሏል፡፡ ይህንንም በጣም በትንቃቄ የተደረደሩ የኤሌክትሪክ ሽቦወች ያሉበት መሳሪያ በመስራት እንዳሳኩት መረጃው ጠቁሟል፡፡
ግኝቱ ለቴክኖሎጂው አለም እድገት ካለው አስተዋጽኦ በይበልጥ በስነ- አእምሮ ህክምና ላይ ያለው አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡ SciTech Daily

እናት ወይስ አባት? ማንን መስለን እንወለዳለን?
-------------------------------------
“አንተ እኮ ቁርጥ እናትህን ትመስላለህ”፤ “የአባትሽን መልክ ይዘሽ ነው የተወለድሽው”፤ “አፍንጫሽ የእናትሽን ይመስላል”፤ “እዩት እስቲ በአባቱ ቤተሰቦች ነው የወጣው”… እነዚህ አስተያየቶች በተለይ በልጅነት ጊዜያቶቻችን ደጋግመን መስማታችን በብዙዎቻችን ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ ግን ማንን መስለን እንወዳለን? በዚህ ጉዳይ ላይ ሳይንስ ተከታዩን ማብራሪያ ይሰጠናል፡፡
የዚህ ጥያቄ መልስ በዋናነት ከእናት ወይ አባት የወሰድነው በራሂ (ጂን) ይበዛል? ወይስ የማን ጂን ተፅዕኖው የጎላ ነው? በሚለው ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ ነው፡፡ ታድያ የሳይንስ ጠበብት ሁለቱ ወላጆቻችን የሚያበረክቱት ድርሻ እኩል እኩል እንደማይሆን ያምናሉ፡፡ ለምሳሌ በራሂዎች 23 X ወይም የY ቅርፅ ባላቸው ክሮሞሶሞች ውስጥ ባሉት የዲ.ኤን.ኤ ስንስሎች ላይ ይቀመጣሉ፡፡ እነዚህ ኦቶሶሞች (ፆታዊ ያልሆኑ ክሮሞሶሞች) በህዋሶቻችን ኒውክሊየሶች ውስጥ ያሉ ሲሆን የያዙት DNAም ከሁለቱም ወላጆቻችን በእኩል መጠን የተወሰደ ነው፡፡ ሆኖም ሕዋሶቻችን ማይቶኮንድሪያ ውስጥ የተደበቀ ሌላ ክሮሞሶም ይዘዋል፡፡ ማይቶኮንድሪያ የሕዋሶች የኃይል ምንጭ ሲሆን በእንቅስቃሴ እና እርጅና ላይም ትልቅ ተፅዕንዖ አለው፡፡ ታድያ ማይቶኮንድሪያ የራሱ የሆነ የDNA አኳሀን ሲኖረው ከእናታችን ብቻ የምንወርሰው ነው፡፡ ይህ ታድያ ከአባት ይልቅ እናታችንን ለመምሰላችን ማሳያ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል፡፡
አንዳንድ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የማይቶኮንድሪያ DNAያችን (በዚህ ምክንያትም እናታችን) በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ችሎታችን ላይ የጎላውን ሚና ይጫወታል፡፡ የእስራኤል እና ስፔን ተመራማሪዎች በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ከሚኖረን የኦክስጅን አጠቃቀም ልኬት ጋራ በሚያያዘው የማይቶኮንድሪያ ሕዋስ ላይ ያተኮረ ጥናት ሰርተው ነበር፡፡ ከ15 ዓመታት በፊት ተሰርቶ ይፋ ሆኖ የነበረው ይህ ጥናታቸው እንደሚያሳየው ከሆነ ከዝቅተኛ የአካላዊ እንቅስቃሴ ብቃት ጋራ የተያያዙ በራሒዎች ከሌላው ህዝብ በተለየ በብስክሌት ግልቢያ ተወዳዳሪዎች እና ሯጮች ላይ አነስ ብለው መገኘታቸውን ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ሌሎች የተለያዩ ጥናቶችም እነዚህ እና ሌሎች በራሒዎችን በማውረስ ረገድ እናቶቻችን የሚወስዱትን ላቅ ያለ ሚና አሳይተዋል፡፡ ጥናቶቹ ከአባቶች ይልቅ እናቶች ያላቸው አካላዊ ብቃት ብቻውን የልጆችን የወደፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ችሎታ ሊተነብይ እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡
ሆኖም ግን ከየትኛው ወላጅ የሚመጣው በራሂ ይበዛል? ከሚለው ይልቅ የትኛው ከፍ ያለ ተፅዕንዖን ያሳድራል? የሚለው ጥያቄ ጎልቶ ሊነሳ ይችል ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን በፊት አልያም ሌላ ውጫዊ ገፅታችን ላይ የሚታየው ልዩነት በበራሂዎች መሰረታዊ መነሻነት የሚመነጭ ሳይሆን በDNA ጫፍ ላይ ተቀምጠው ባሉት የኬሚካል መቀያየሪያዎች (switches) አማካኝነት ለሰውነታችን በሚተላለፈው ንባብ እና ይህን ተከትሎ በሚመጣው የየትኛው ፕሮቲን አይነት ይመረት እና የተኛው ይተው ትርጓሜ ነው፡፡ ኢምፕሪንቲንግ ተብሎ በሚጠራ ሁነት አማካኝነት እነዚህ መቀያየሪያዎች አንዳንድ ከአንደኛው ወላጅ ብቻ የመጡ በራሂዎችን ሙሉ ለሙሉ ፊት ሊነሱ ይችላሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በትውልዶች ውስጥ ሊቀጥል ይችላል፡፡ ለምሳሌ አንድ በራሂ በአባት በኩል ኢምፕሪንት ከሆነ ምንጊዜም የሚሰራው ከእናት በኩል ሲመጣ ብቻ ነው፡፡ ምንም እንኳን በዚህ ላይ ልዩነቶች ቢኖሩም ብዙዎቹ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የሰው ልጆች ከ100 እስከ 200 የሚደርሱ ኢምፐሪንት የተደረጉ በራሂዎችን በሰውነታችን እንይዛለን፡፡
ኢምፕሪንቲንግን ተከትሎ በሚመጣው ወደ አንደኛው ወይም ሌላኛው ወላጅ የሚደረግ ማዘንበል መኖሩ ላይ ግን ሁሉን አቀፍ ስምምነት የለም፡፡ “ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙን ከሆነ ከእናት እና አባት የሚወረሱት ኢምፕሪንት የሆኑ በራሂዎች ሰውነት ውስጥ በእኩል መጠን ይገኛሉ” ሲሉ የጀነቲክ ባለሙያው አንድሪው ዋርድ ያስረዳሉ፡፡ ታድያ ኢንፕሪንት በሆኑ በራሒዎች አማካኝነት በሚመጡ አካላዊ መገለጫዎች ላይ ወደ አንዱ ወላጅ ልናደላ እንደምንችልም አክለው ይገልፃሉ፡፡ በሌላ አነጋገር ኢምፕሪንቲንግ እንደ ሰውነት መጠን፣ እንቅልፍ እና ማስታወስ ባሉ ልዩ ገፅታዎቻችንም ላይ ተፅዕንዖ ሊኖረው ይችላል ማለት ነው፡፡ ሆኖም ኢምፕሪንቲንግ የሚደረግባቸው በራሂዎች በአንፃሩ አነስተኛ በመሆናቸው እና እነርሱም ቢሆን ከሁለቱም ወላጆቻችን በተመጣጣኝ መጠን የሚወሰዱ በመሆናቸው ሳብያ ከእናት አልያም አባት በጣም የተለየ መመሳሰል እንዳይኖር የማድረግ እድል አለው፡፡
ሆኖም አይጦች ላይ የተደረገ አንድ ጥናት የሚያመላክተው ግን ምናልባትም ወደ አባቶቻችን የቀረብን መሆናችንን የሚያሳይ አድሎ ሊኖር መቻሉን ነው፡፡ እ.አ.አ በ2015 ኔቸር ጀነቲክስ ጆርናል ላይ ታትሞ የወጣው ጥናቱ እንደሚያሳየው ከሆነ በእናት በኩል ያሉት ኢንፕሪንት የሆኑ በራሒዎች ከአባት በኩል ከሚመጡት አንፃር ተቀባይነት የማጣት እድላቸው (በተቃራኒው የአባቶች ተቀባይንነት የማግኘታቸው እድል) በ1.5 እጥፍ የላቀ ነው፡፡ ቀድሞ በ2008 (እ.አ.አ) የወጣ ሌላ ጥናትም ተመሳሳይ ውጤት አሳይቶ ነበር፡፡ በአንጎል ውስጥ ያሉት ኢምፕሪንት ከሆኑ በራሂዎች ውስጥ ከአባት የመጡ ሲሆኑ ይበልጥ ንቁ ናቸው፤ በእንግዴ ልጅ ላይ ደግሞ በተቃራኒው ይሆናል፡፡ ሆኖም ይህ አለመመጣጠን ለሰው ልጆችም ይስራ አይስራ የሚያሳይ መረጃ እስካሁን አልተገኘም፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በተለይ በበራሂ ላይ ከአንደኛው ወላጃችን የወሰድነው ኢምፕሪንት የሆነ በራሂ ቢበልጥ እንኳን ከሌላኛው ወላጅ በበለጠ ወደ እርሱ/እርሷ እንቀርባለን ማለት አይደለም፡፡ ምናልባትም በእኛ ውስጥ ንቁ ሆኖ ያለው አንድ የበራሂ አይነት እናትም ይሁን አባት ባወረሰን ወላጅ ላይ ንቁ ሆኖ ላይገኝ ይችላልና፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ሚትዮሮች ምንድን ናቸው?
አካባቢያችንን አግልቶ የሚያሳይ ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማለትም እንደቴሌስኮፕ ያሉ ኢኖቬሽኖችን ሳንጠቀም በአይናችን ብሌን ብቻ የምንታዘባቸው አስገራሚ የተፈጥሮ ውበቶች አሉ፡፡ አልፎ አልፎ ጥርት ባለ ጨለማ ሰማይ ላይ አተኩረን በምንመለከትበት ሰአት አብዛኛውን ጊዜ በጣም በፍጥነት የሚያልፉ ደማቅ ብርሀን ያላቸው ነገሮችን ልንመለከት እንችላለን። በተለምዶም ተወርዋሪ ኮከብ ብለን እንጠራቸዋለን (meteors) ወይም ሚትዮሮችን። ተወርዋሪ ኮከቦች በህዋ ውስጥ የሚንሳፈፉ አለቶች ናቸው። ይህ አለት በብዛት የያዘው የብረት መአድን ሲሆን የአለቱ ስፋት ከ 1 ሳ.ሜ (ማይክሮ ሚትዮራይድ) እስከ 1 ሜትር ሊደርስ ይችላል።
ሚትዮሮች ከዋክብት እድሜያቸውን ጨርሰው በሚፈነዱበት ሰአት የፍንዳታቸው ቅሪተ አካል በህዋ ውስጥ ለብዙ ሚሊዮን አመታት ይንሳፈፋል። ተወርዋሪ ኮከቦችም እነዚህ ቅሪተ አካላት ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ ይታሰባል። ከዚህ ባለፈ ደግሞ በተለያዩ የህዋ አካላት መካከል በሚከሰት የእርስ በእርስ ግጭት የሚፈጠሩ ፍንጣሪዎች እንደሚሆኑም ይገለፃል።
ተወርዋሪ ኮዋክብት በህዋ ላይ በመንሳፈፍ ላይ ሳሉ ወደምድር ከባቢ አየር መጠጋታቸው አይቀርም። በዚን ግዜ በምድር የስበት ሀይል ይሳባሉ፤ በዚህም ከአየር ጋር በሚያደርጉት ሰበቃ ይቃጠላሉ። ሲንሳፈፍ የነበረውን የህዋ አካል ሚትዮሮይድ የሚል ስያሜ ሲኖረው በሰበቃ ሀይል የተቃጠለውን ሚትዮር ሳይተን ምድር ከደረሰ ሚትዮራይት ተብሎ ይጠራል። ተወርዋሪ ከዋክብት በሰኮንድ 20 ኪሎሜትር ይጓዛሉ። አንዳንድ ጊዜ በጅምላ ሲከሰቱ የሚትዮራይት ሻወር ተብሎ ይጠራል።
Airtable Universe

ዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ መሰጠት ተጀመረ
--------------------
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት በሀገራችን የሚገኙ ስታርትአፖችን በዲጂታል ማርኬቲንግ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ያለመ ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀምሯል፡፡ የሁለት ቀናት ቆይታ የሚኖረው ይህ ስልጠና በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሚሆኑበት ነው፡፡ በፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ውስጥ የICT ዳይሬክተሩ አቶ ተክሊት በርሄ በስልጠናው ጅማሮ ላይ ለተሳታፊዎች ባሰሙት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ኢንስቲትዩቱ ስታርታፖችን በማገዝ ረገድ እያከናወነ ላለው ተግባር አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡ ዲጂታል ማርኬቲንግ ቀድሞ ይሰራበት የነበረውን የገበያ አካሄድ በመቀየር ከICT ጋራ የተሳሰረ እንዲሆን ማድረጉን የተናገሩር አቶ ተክሊት ይህ ስልጠናም ተሳታፊዎችን በጠቃሚ እውቀት፣ ክህሎት እና ደጋፊ የሆኑ መንገዶች ላይ ግንዛቤን የሚሰጥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በዛሬው መርሀ ግብር ጅማሮ ላይ ስለ በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት ልዩ ልዩ ግንዛቤዎችን የሚያስጨብጥ ስልጠና በኢንስቲትዩቱ ባልደረባ አቶ ገብሬ ኩንታኖ የተሰጠ ሲሆን ይህም በይነ መረብ ምንድነው፣ እንዴት ይሰራል፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያሳየው እድገት እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ተነስተው ማብራርያ ተሰጥቶባቸው ነበር፡፡ በተጨማሪም ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን አቶ ገብሬም ሙያዊ ምላሻቸውን ሰጥተውባቸው አልፈዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን ዛሬን ጨምሮ ስልጠናው በሚካሄድባቸው በሁለቱም ቀናት ውስጥ ሌሎችም ከዲጂታል ማርኬቲንግ እና አጠቃቀሙ ጋራ የተያያዙ ልዩ ልዩ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ በኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎች እንዲሁም የስልጠናው ተሳታፊዎች አማካኝነት ዳሰሳ የሚደረግባቸው ይሆናል፡፡ ከነዚህ አብይ ጉዳዮች መካከል ድረ-ገፅ፣ መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀቶች፣ ብራንዲንግ፣ ፌስቡክ፣ ዩትዩብ እና ሌሎች የማህበራ ሚዲያ ብሎም የበይነ መረብ አማራጮችን ተጠቅሞ ማከናወን በሚቻል የማርኬቲንግ እንቅስቃሴ ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡
በስልጠናው ላይ ከቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ግንባታ፣ ባልትና እና ሌሎችም ዘርፎች ተውጣጡ 37 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ የሆኑበት ሲሆን እነዚህ ከፌደራል የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ጋራ በመተባበር የተመረጡ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር፤ ዘመን ተሻጋሪ መገለጫ
========
መዲናችን አዲስ አበባ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የከተማነት ቅርጿን በእጅጉ የለወጡ ብዙ ግንባታዎችን አስተናግዳለች፡፡ በተለይም ከ1940ዎቹ እና 50ዎቹ የተከናወኑት ግንባታዎች እሳካሁንም ድረስ የከተማችን ዋና መገለጫ ተብለው ከሚወሰዱት ቋሚ ሀብቶች መካከል ናቸው፡፡ ከነዚህ ስመ ጥር ህንፃዎች መካከል ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ወይም በቀድሞ ስያሜው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴአትር ቤት ይገኝበታል፡፡ ቴአትር ቤቱ በተለይም ከውጭ በኩል በቀረበው ዝነኛ የአንበሳ ሐውልትም ተለይቶ ይታወቃል፡፡
የዛሬ 40 ዓመት ገደማ በ1973 ዓ.ም በራሱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አማካኝነት ታትሞ በወጣው “ከሙያችን” መፅሔት ውስጥ ከገፅ ሦስት አንስቶ ከሰፈረው “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር አጭር ታሪክ” ፅሑፍ ውስጥ ስለ ግንባታው የሚያትተውን ክፍል መርጠን አቅርበንላችኋል፡፡
“ከ፷፮ አብዮት ፍንዳታ ወዲህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተብሎ የተሰየመው አዳራሽ ትክክለኛውን ባናውቅም ፋሽስት ሀገራችንን በወረረበት ዘመን ተደላድሎ የመኖር ሕልሙን ለመተርጎም በርዕሰ ከተማችን ቺኒማ ማርኮኒ በሚል ስያሜ ሊያሠራው የጀመረው አዳራሽ መሆኑን በጊዜው የነበሩት አባቶች ይናገሩታል።
እኛም የታሪክ ማስታወሻ መያዝ ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ለብዙ ዓመታት የሕንፃው ውጭና ውስጥ የአላፊው አግዳሚው መንገደኛ መጸዳጃ እንደነበር በገሃድ አይተናል።
በዚህ ወቅት ከ፲፱፻፵፯ ዓ/ም በፊት የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የቴአትርና ሙዚቃ ማስፋፊያ ክፍል ነበረው። ከ፲፭ እስከ ፲፰ ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ፷ ያህል የሙዚቃና ቴአትር ተማሪዎችም ነበሩት። ወጣቶች ሙዚቃ ተጫዋቾች በየክብረ በዓሉ በየአዳባባዩ በመገኘት የአማርኛ ዜማዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል ይችላል በዘመናዊ ሙዚቃ መሣሪያ በሰልፍ እየተዘዋወሩ በማሰማት ተወዳጅነታቸውን በይፋ አስመስከሩ። በቴአትሩም በኩል በስመ ጥሩው ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ዮፍታሄ ንጉሤ፤ አፈወርቅ አዳፍሬና በሌሎችም ደራሲያን የቀረቡ ድርሰቶችን በማሳየት ክፍሉ ዝና እያተረፈ ሄደ። ሕዝብም በብዛት ወደ ቀድሞው ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ እየመጣ በቦታ ጥበት የተነሣ መመለስ ጀመረ።
ይኸም የሕዝቡን የቴአትርና ሙዚቃ ፍላጎት እያጎላው ሄደ። ለዚህም መፍትሔ ይሆን ዘንድ አንድ ዘመናዊ አዳራሽ እንዲሠራ ዕቅድ ወጣ። የታወቁ ፕላን ሠራተኞች የነደፉት የኣዳራሽ ሞዴል ቀርቦ ሥፍራው ተመረጠ። ይኸውም ኣቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ፊት ለፊት የአሁኑ ማዘጋጃ ቤት ከተሠራበት ግቢ ነበር።
ሥራው ሊጀመር እንደተቃረበ የቀድሞው ንጉሥ የብር ኢዮቤልዩ ስለደረሰ በአጣዳፊ አንድ ዘመናዊ የቴአትር አዳራሽ እንዲሠራ ትእዛዝ ተላለፈ። ጉዳዩን ጀምሮት ስለነበር ከማዘጋጃ ቤት የማይገነጠል ሆነ። ለዚህም በፈረንሳዩ አርቺቴክት በሄንሪ ሾሜት የቀረበው ሃሳብ ጸድቆ ይኸው አሁን ያለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ተብሎ የተሰየመው ጅምር ሲኒማ ቤት ፍጻሜ እንዲያገኝ ተወሰነ።የማዘጋጃ ቤት ሙዚቃና ቴአትር ሲያስተምራቸው የነበሩት ባለሙያዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ ለሚሠራውም ዘመናዊ ቴአትር ቤት ብቁ ሆነው እንዲገኙ አንድ አሰልጣኝ ከቪየና እንዲመጣ ተደረገ የሙዚቃና ቴአትር ኣሰልጣኙም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን እንግዳ ያልነበረና ቀድሞ በሌላ ክፍል ሲሠራ ቆይቶ ኮንትራቱን ፈጽሞ ወደሀገሩ የተመለሰ ስለነበረ ሥራውን ያለችግር ሊጀምር ችሏል
የመሠልጠኑ ሥራ በአንድ ክፍል ፡ የቴአትርና የሙዚቃ ዝግጅት በሌላ ክፍል እንደዚሁም የአዳራሹ ሥራ በየፊናው ይከናወን ጀመር።
በጅምር የቀረውን ሕንፃ በተሻለና በቀለጠፈ መንገድ ፍጻሜ ለማድረስ ኃላፊነቱ የተሰጣቸው አርክቴክት ሐንሪ ሾሜት የሚስማሙትን የሥራ ረዳቶች እንዲመርጡ መፍቀዱ ቀና መንገድ ስለሆነ ታዘዘላቸው።
በዚህ ወቅት በሰኔ ወር ፲፱፻፵፯ ዓ ም ሙሴ ሾሜት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት መሐንዲስ ክፍል በኃላፊነት የሚሠሩ ነበሩ።
በዚሁ አኳኋን ሙሴ ኣላዤ ለዴኮራሲዮን'ሙሴ ካልካ በሙሴ ፈልቶኒና በሙሴ ሞዜ እየተረዱ ለውቅር ሥራ ! ሙሴ ሞሲያን ለፖሊክሮሚ ለሞዛይክና ለመስተዋት ሥራ ደግሞ ሙሴ ፔሬዝና ሙሴ ፒኞ ለመጋረጃዎችና ለንድፍ ሥራ ተመደቡ።
ሙሴ ሾሜት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትርን ሕንፃ ለማስፈጸም በመመረጣቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውን ጽሕፈት ቤታቸውን የሥራ ልምድና ችሎታ አስተባብረው ደስ በሚያሰኝ አኳኋን ሥራውን እንደሚመሩ ቃል ገቡ።
በጊዜው የቀረቡት ዕቃዎችና መሣሪያዎች ለሥራቸውም ውጤት ማስረጃ የቴአትር ቤቱ ሕንፃ እንዴት ተጀምሮ እንዳለቀ መገምገሙ ያረጋግጣል ። የጊዜው ማጠር ይህን ከፍተኛ ሥራ ወደ ፍጻሜ ለማድረስ የሚፈቅድ ኣደለም የሚል ግምት በቀድሞው አስተዳደር ከፍተኛ ባለጣኖች ዘንድ ነበር። ሌሎችም የቴክኒክ ሰዎች የሕንፃወ ሥራ ብቻ የውስጡ ድርጅት ሳይጨመር ከሁለት ዓመት የበለጠ ጊዜ ይጠይቃል የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር። ነገር ግን እስከ ኢዮቤልዩ በዓል የነበረው ጊዜ አራት ወር ብቻ ሲሆን ለሥራው የሚያስፈልጉት አብዛኞቹ ዕቃዎች የሚመጡት ከውጭ ሀገር ነበር።
ከዚህም በላይ ወቅቱ የክረምት መግቢያና እንዲሁም በአውሮፓ ያሉት የሚበዙት የንግድ አካባቢዎች በያመቱ በበጋ ወራት ለዕረፍት የሚዘጉ በመሆናቸው በሁለቱ ተቃራኒዎች የተፈጠረው ችግር እጅግ ከፍ ያለ ነበር።
ሶስት ሳምንታት ያህል ያለማቋረጥ በተደረገው ጥናት የመጀመሪያው ክፍል በአስተማማኝ ወደ ፍጻሜ ደረሰ። ይህም የሆነው በፓሪስ ከተማ በሚገኘው በሐንሪ ሾሜት ዋና መሥሪያ ቤት ፡ በአዲስ አበባው ጽሕፈት ቤትና እንደዚሁም የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተጨማሪ በመደባቸው መሐንዲሶች ሕብረትና መረዳዳት ነበር።
ስለሥራው ጨረታ ተካሂዶ ለሁለት ተቋራጮች ተሰጠ። ኣንደኛው ተቋራጭ የጣና ማህበር የሚባለው ሲሆን የተመደበለትም በተለይ የቴአትሩ የውስጥ ድርጅት ስለነበር በሰባት መቶ ሃምሳ ሞያተኞች ሥራውን ጀመረ። ሁለተኛው ተቋራጭ “ጄ ሳልሞን” የሚባለው ነበር። እሱም በሁለት መቶ ሞያተኞች የአደባባዩንና የሕንፃውን ሥራ ጀመረ። በዝናቡ ምክንያት እጅግ በጣም አስቸጋሪና የሕንፃው ሥራ ፍጻሜም አጠራጣሪ ሆኖ እንደነበረ አይዘ ነጋም። በዚህና በመሳሰለው ሁኔታ ሥራው ሲካሄድ የሾ ሜት ጽሕፈት ቤት ሌሎቹን ጉዳዮች የውስጥ ሥራ ዝግጅት ማጣደፍ ቀጠለ። እነሱም ማለት የውስጥ መጋረጃዎችን ቅርጻቅርጾችን ፡ ልዩ ልዩ ዕቃዎችንና ፡ ሥዕሎችን ምን ጣፎችን ፡ የትርዒት ማሳያ ፡ መድረክ የሲኒማ መሣሪያ ዎች ፡ መስታወቶች : ሞዛይክ የቡና ቤት ዕቃዎችና ሌሎችንም ነበር። በተጨማሪ ከቴአትር ቤቱ ሥራ ተነጥሎ የማይታይ ሐውልቶች እንዲሠሩ ሃሳብ ቀረበ። በቴአትር ቤቱ አደባባይ ለሚታየው ሐውልትና በአዳራሹ መግቢያ ለቆሙት ስድስት ቅርጾች ሥራ ጉዳይ ኣንድ ውድድር ተዘጋጀ። በዚህም ውድድር ሞሪስ ኮልካ የተባለው ተወ ዳዳሪ አሸነፈ። ይኸ ተቋራጭ ማሸነፉ ለንጉሡ ቀርቦ ንድ ፉን ካሳየ በኋላ ተፈቀደ። በአዳራሹ መግቢያ ላይ በፕ ሎሞብ የተሠሩት አራት ቅርጾች ኣራቱን የኪነጥበብ ባሕ ርያት የሚያስረዱ በመሆናቸው ወደቴአትሩ አዳራሽ የሚ ገቡ ሁሉ የመጀመሪያ አትኩሮታቸው የሚያርፈው እነሱ ላይ ነው።
እነዚህ ባሕርያት ተራዠዲ ፡ ኮሜዲ ' ሙዚቃና ዳንስ ሲሆኑ ቀድሞ በአተረጓጐሙ የተስማሙ ሊቃውንት መግለጫ ሰጥተውበት ነበር።
በዚሁ መግቢያ በደረጃው ግራና ቀኝ የሁለት እንስሳት ቅርፅ እንዳለ ግልጽ ነው። በውጭ በኩል በቴአትሩ አደባባይ ላይ በዚሁ ጠራቢ የተሠሩ ከውኃ ፋፋቴ ውስጥ የሚወጡ የሶስት ዓሣዎች ምስል ተሠሩ።

የአዳራሹን መስ ታዎቶች ለማዘጋጀት ሲ ሞሲዮን የተባለ ሠዓሊ ተመረጠ። በልዩ ልዩ ሕብረ ቀለም የደመቀው መስተዋት የተለየ ውበት ቴአትር ቤቱ እንዲያጎናጽፍ በጥናት የተሠራ በመ ሆኑ የተመልካች ዓይን የሚስብና ምርምር ውስጥ የሚከት ሆነ። በአዳራሹ ውስጥ ያሉት ወንበሮች የእንጨት ልባሶች መጋረጃዎች የአዳራሹ ዙሪያ ፕላስቲኮች : ምንጣፎች በሙሴ ጃኮብሰንና በሙሴ ቢኒ መሪነት በቴል አቪቭ የተሠሩ ናቸው። በአጭር ጊዜ ውስጥ እነዚህን የተጠቀሱትን ልዩ ልዩ ዕቃዎች ከሥፍራወ በማምጣትና በማገጣጠም ቅልጥፍናውና በቴክኒክኦ በኩል ያለውን ሙሉ ችሉታ ተቋራጩ ክፍል አስመስክሮ ከፍተኛ ዝና በጊዜው አግኝቷል።
ለፋፋቴዎች የሚያስፈልጉትን የውኃና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ያቀረበ የረሪኔክ የንግድ ቤት ነበር። እስከ ፲፭ ሜትር ከፍታ የሚደርሰው የውኃ ፋፋቴ በ፯ ዘውድ የሚመሳሰሉ ሌሎች ፏፏቴዎች የተከበበ ሆኖ ነበር የተሠራው። በምሽት ጊዜ በመብራት ኃይል ደምቆ ሲታይ የሚማርክ ገጽታ ነበረው።
የቀድሞው ንጉሥና ንግሥት የተለዩ መመልከቻዎች ሥፍራ ለእግር መርገጫ የዋለውን ምንጣፍ ያዘጋጀው በፈረንሳይ እጅግ የታወቀው ምንጣፍ ሠሪ ዣን ሉርሳ ነው። ሥራውም በሙሉ የተከናወነው በእርሱ ኢንዱስትሪ ውስጥ ነው።
ለመድረክ የትርኢት ብርሃን ሥራ የዋለውን የኤሌክትሪክ መሣሪያዎች ያቀረቡ ሬይሽ ቦጅልና ስቴይነር የተባሉት የአውስትሪያ ነጋዴዎች ነበሩ። በዚህ አኳኋን ማንኛውም ተሟልቶ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፵፰ ዓ ም ከእኩለ ቀን በኋላ በቴአትሩ አደባባይ ያለው የአንበሳ ሐውልት ቴአትር ቤቱ ተመርቆ ተከፈተ ።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆንም ከፈረንሳይ ሀገር በመጡ የባሌት አርቲስቶችና ከማዘጋጃ ቤት ወደ ቴአትር ቤቱ በተዛወሩ አክተሮችና ሙዚቀኞች “ዳዊት ኦሪዮን” ተውኔት የመጀመሪያው ትርኢት ፩ሺ፪፻፲፬ ተመልካች በተገኙበት የመጀመሪያው የብሔራዊ ቴአትር የትርኢት ምዕራፍ ፡ ተከፈተ ። ቴአትር ቤቱን የልዩ ልዩ ክፍል ዓለም ጋዜጠኞች መጥተው ጎብኝተው በኣፍሪቃ አህገር አሉ ከሚባሉት ታላላቅ ኦፔራዎች አንዱ መሆኑን እየመሰከሩ ሲጽፉ ብዙ የውጭ ሀገሮች አርቲስቶች እየመጡ ትርኢታቸውን ለማቅረብ ጥያቄ እያቀረቡ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የፈረንሳይ የፕራግ ፤የፔኪንግ ኦፔራ ፡ የፍራንሱዋዝ ሉዱስዴ የፒያኖ ጨዋታ፤የዓይነ ስውሩ የጆርጅ ቴማሊ የፒያኖ ጨዋታ፤በስመ ጥሩው ባሪ ቶን ተጫዋች ዊሊያም ዎርፊልድ ከአሜሪካ ፤ የቶኒክ ጊርጊዮ የፒያኖ ጨዋታ ፡የኣሌክሳንደር ቦን ስዊድንና የፈዛስክቤል የክላሲክ ዳንስ ትርኢት ፤ የሞስኮ ናሽናል ቴአትር ተጨዋቾች : የኒው ኦርሊአንስ የጃዝ ተጫዋቾች ዊልበር ደ ፓሪና ረዳቶቹ ፡ በተከታታይ መጥተው በቴአትር ቤቱ ትርኢታቸውን አቀረቡ።
የቴአትር ቤቱ አስተዳደር በማዘጋጃ ቤት ሥር ነበር። የቴኣትር አዘጋጅና የዘመናዊ ኦርኬስትራ መሪ ፍራንዝ ዜልዌከር የሚባል ሲሆን የመድረኩን ሥራ ኃላፊ ሪቻርድ ሄትማኒክ ፤ የመብራቱ ሥራ ኃላፊ ፍራንዝ ኒል ሁሉም ከአውስትሪያ የመጡ የኪነት ሰዎች ነበሩ። የዴኮሬሽን አዘጋጁም ሲኞር ፉም ነበሩ።”

የአዕምሮ ህመም እያስከተለ ላለው ውስብስብ ችግሮች መፍትሄ ምን ይሁን ? ክፍል ሁለት
https://www.youtube.com/watch?v=LwcniVU8VpM
ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይከታተሉን
(Nilesat 12520/v/27500)
(በተጨማሪም Ethiosat ላይ እንገኛለን)

YouTube