TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ሁለት ጾታ ያለው ወፍ
*****************
ተመራማሪዎች ግማሽ ጎኑ ሴት ግማሽ ጎኑ ደግሞ ወንድ የሆነ ወፍ ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ CNN ባወጣው ዘገባ ባለሁለት ጾታው ወፍ አዘውትሮ በመዘመር የሚታወቅ ድምጸ መረዋ ነው፡፡ ይህንም ግኝት ተመራማሪዎቹ የመከሰት እድሉ በጣም ጠባብ ነው ብለዋል፡፡
ከ15 ዓመታት በፊት የተፈጥሮና ታሪክ ሙዚየም የሆነው ካርኔጅ ሙዚየም ተመሳሳይ የወፍ አይነት ማግኘቱን ገልጾ ነበር፡፡ ይህም ተቋሙ ካያቸው 800,000 ከሚደርሱ ወፎች መካከል አምስተኛው እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የዚህ አይነት ወፎች የራሳቸው መለያ ቀለም ያላቸው ሲሆን ወንዶቹ ሮዝ ነጠብጣብ ላባ ሲኖራቸው ሴቶቹ ደግሞ ቢጫና ቡናማ ቅልቅል ላባ አላቸው፡፡ አሁን ተገኘ የተባለውም ወፍ በአንዱ ክንፉ የወንድ ቀለም ሲኖረው በሌላ ክንፉ ደግሞ የሴት ቀለም አለው፡፡ በሳይንሳዊ (በዘረመል) መጠሪያው ጂናንድሮሞረፊዝም የሚባል ክስተት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ለCNN ተናግረዋል፡፡ ጂን`- በግሪክ ቋንቋ ለሴት የሚነገር ሲሆን `አንድሮ ደግሞ ወንድ ማለት ነው፡፡ ሞርፍ የሚለው ቃል ስብጥርን የሚያመለክት ነው፡፡
ይህ አይነቱ ክስተት በሌሎች እንደ ሸረሪት፣ አሳዎችና በዶሮዎችም ሊከሰት እንደሚችል ተመራማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡ CNN
አስደናቂ ተፈጥሯዊ ብቃት ያላቸው እንስሳት
******************************************
የእንስሳት ዝርያዎችን የበለጠ እያጠናናቸው በሔድን ቁጥር አስደናቂ የሆኑ ተፈጥሯቸውን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ የእፍኝት ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ እይታ፣ ንቦች ያላቸው ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ብርሀንን የመለየት ችሎታ እና የአማዞን ውሃ ውስጥ እባብ መሰል ዓሳዎች ብርሃን በሌለበት የአማዞን ውሃ የማየት አቅምን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አሳ ነባሪ፡ ይህ በውሃ ውስጥ የሚኖር መለስተኛ መጠን ያለው የአሳ ዝርያ ሲሆን አስደናቂ ተፈጥሮ ካላቸው እንስሳት መካከል አንዱ ነው፡፡ በአለማችን ከ40 በላይ የአሳ ነባሪ ዝርያዎች አሉ፡፡ አሳ ነባሪዎች ከእናታቸው ጋር ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ፡፡
ምግብ ለማከማቸትና ምግብ ለመፍጨት የሚጠቀሙባቸው ሁለት ሆድ አላቸው፡፡ እስከ 1000 ጫማ ድረስ ጠልቀው መዋኘት የሚችሉ ሲሆን እስከ 50 ዓመት እድሜ መኖር ይችላሉ፡፡ መጠናቸውም ከ3 እስከ 30 ጫማ ድረስ ይረዝማሉ፡፡
ሌላው አሳ ነባሪዎች የሚታወቁበት ባህሪያቸው ለሌሎች ፍጥረታትና ለራሳቸው ዝርዎች ወዳጆች መሆናቸው ነው፡፡ ከመካከላቸው በዕድሜ የገፉትንና የተጎዱትን በመርዳት ይታወቃሉ፡፡
ከሰዎች ያነሰ ቢሆንም ከሌሎች ፍትረታት የተሻለ የማሰብ ችሎታ አላቸው፡፡ በአካልና ጭንቅላት መጠን ንጽጽር ከሰዎች ቀጥሎ አሳ ነባሪዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በሚተኙበት ጊዜ ግማሽ የአእምሯቸው ክፍል ንቁ ይሆናል፡፡ ይህም በእንቅልፍ ጊዜ ሊያጋጥማቸው ከሚችል አደጋ ለመጠበቅና ለመተንፈስ ይረዳቸዋል፡፡
አሳ ነባሪዎች ጥርሳቸውን የሚጠቀሙበት ለመያዝ ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ምግብ ሲያገኙ ሳያላምጡ ይውጡታል፡፡
የሌሊት ወፍ፡ ይህች በአጥቢነቷ የምትታዎቀው ብቸኛዋ በራሪ እንስሳ የደም ስርን ማየት የሚያስችል ብቃት አላት፡፡ ወፍራምና ብዙ ደም ያለባቸው የደም ስሮች ሙቀት መለያቸው በመሆኑ ይህንን ሙቀት ከእንስሳት ላይ በቀላሉ መለየት ትችላለች፡፡
በዚህም ምግቧን ማደን ተክናበታለች፡፡ ከእንስሳት ደም ስትመጥ እንስሳው ሳይነቃ ለ30 ደቂቃ ያክል ልትመጥ ትችላለች፡፡ ይህ ሲሆን ግን እንስሳውን ለሞት የሚዳርግ ያክል መጠን ደም አትመገብም፡፡
ምንጭ www.aquaworld.com እና www.onekindplanet.com
በታዳጊው የተሰራው የውሃ ተርባይን
ከአፋር የተገኘው ካሚል አብዱ የወንዝ ግፊትን ተጠቅሞ ያለምንም ነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ሃይል ውሃ የሚያሰራጭ ተርባይን መስራት የቻለ ታዳጊ ነው፡፡ ይህ የፈጠራ ስራው የወንዝ ተፋሰስን በመጠቀም ለተለያዩ የመስኖ ስራዎች ውሃን ለማደራስ የሚያገለግል ከመሆኑም በላይ፤ የእርሻ ልማትን ለማፋጠንም በእጅጉ የሚያግዝ ነው፡፡
ውድ የፔጃችን ተከታታዮች የብዙ ታዳጊዎችን የፈጠራ ተሰጥኦ የሚመለከቱበት ብላቴናት ፕሮግራምን ጨምሮ ሌሎች ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ተኮር መሰናዶዎችን በቀጥታ ለማግኘት ዘወትር ቅዳሜ በ10 በ MOE ቴሌቪዥን ይጠብቁ፤ ከዚያ ባለፈም በተከታዩ የዩትዩብ ቻናላችን ይከታተሉን!!! youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg
ጭስ እንዴት ይፈጠራል
********************
በሀገራችን በልማድ አንድ ነገር ያለ ምክንያት እንደማይፈጠር ለማመልከት "እሳት በሌለበት ጭስ አይኖርም" ይባላል፡፡ ለመሆኑ ሳይንስ ስለ እሳትና ጭስ ምን ይላል፡፡
በማንኛውም አይነት እንጨት አራት ነገሮችን እናገኛለን፡፡ እነዚህም ውሃ፣ ሊተን የሚችል ተፈጥሯዊ ውህድ፣ ካርቦንና አመድ ናቸው፡፡ አንድ አዲስ የተቆረጠ ዛፍ በአብዛኛው ከግማሽ የሚበልጥ ክብደቱ በውስጡ ባለው ውሃ ምክንያት የመጣ ነው፡፡ ለአመት ለሁለት አመት ተቆርጦ የተቀመጠ እንጨት መጠኑ ይነስ እንጂ በውስጡ ውሃ አለው፡፡
አንድ ዛፍ ከመቆረጡ በፊት በህይወት እያለ በህዋሱ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ትነትን የሚፈጥሩ የሀይድሮጅንና የካርቦን ውህዶች አሉት፡፡ እነዚህ ውህዶች ተቀጣጣይ በመሆናቸው እሳት በሚነካቸው ጊዜ ከእንጨቱ ጭስ ይወጣል፡፡
አንድን ያልደረቀ እንጨት እሳት ውስጥ ስንጥለውና ሙቀቱ 149º ሲደርስ መጨስ ይጀምራል፡፡ ሙቀቱ ከዚህ የሚበልጥ ከሆነ እነዚህ ውህዶች ወደ ነበልባልነት ይለወጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንጨቱ ምንም ጭስ አይወጣም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በእንጨቱ ውስት ያለው የሀይድሮጅንና የካርቦን ውህድ ወደ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድና ወደ ውሃ ስለሚቀየር ነው፡፡ ሁለቱም ሲነዱ አይታዩም፡፡
ከዛፉ ውስጥ ሊቃጠሉ የማይችሉ ማዕድናት እንደ ካልሺየም፣ ፖታሺየምና ማግኒዥየም ያሉት ደግሙ መጨረሻ ላይ አመድ ሆነው ይቀራሉ፡፡ የምድጃ ክሰል የሚያዘጋጅ አንድ ሰው ምንም ኦክስጅን በሌለበት ከፍተኛ ሙቀት ውስጥ እንጨቱን ሲከተው ከእንጨቱ የሚጨሰው ክፍል ብቻ ይጠፋና ካርቦን ከሌሎች ማዕድናት ጋር ይቀራል፡፡ ለዚህም ነው የወጣለት ክሰል የማይጨሰው፡፡
ምንጭ፡ Howstuffworks
የጠፉ ቋንቋዎችን የመተርጎም ስራ
*****************************
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአለማችን እስከዛሬ ድረስ ካሉት ቋንቋዎች አብዛኛዎቹ ተናጋሪ የላቸውም፡፡ ከእነዚህ ተናጋሪ ከሌላቸው ቋንቋዎች መካከል ጥቂት የማይባሉት ደግሞ የጠፉ በሚል የተፈረጁ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ስለ ቋንቋዎቹ ሰዋሰው፣ ቃላት እና አጠቃቀም የሚታወቅ ነገር የለም ማለት ነው፡፡

የጠፉ ቋንቋዎች ጉዳይ የቋንቋ ጥናት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ያለ እነዚህ ቋንቋዎች ስለ ተናጋሪዎቻቸው ያለው አጠቃላይ መረጃ ሊታወቅ አይችልም፡፡ ያለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቹ የጠፉ ቋንቋዎች በሳይንሳዊ መንገድ ሊጠኑ የሚችሉበት ፍንጭ እንኳን የላቸውም፡፡ ይሁን እንጂ በአንድ CSAIL (Computer Science and Artificial Intelligence Laboratory) በተባለ ቤተ ሙከራ ተመራማሪዎች አንድ የጠፋ ቋንቋን መረዳትና ማንበብ የሚችል ፈጠራን አበልጽገዋል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ፈጠራው የጠፋውን ቋንቋ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይቀር ለማጥናት የሚያስችል ነው፡፡

የተመራማሪዎቹ ቡድን ዋና አላማ አንድን ከጠፋ ብዙ ጊዜ ያስቆጠረን ቋንቋ በሺዎች በሚቆጠሩ ቃላት ለመረዳት ነው፡፡ በምርምሩ በቋንቋ የመጥፋትና የመለወጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ የቃላት፣ የሆሄያትና የድምጾች ለውጥና መወራረስ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ ያበለጸጉት ቋንቋን የመረዳት ስልት decipherment algorithm ብዙ አማራጭ ቃላትንና ድምጾችን ወይም ስልተ ንባቦችን የሚጠቀም ነው፡፡ ቋንቋን የመረዳት ሂደቱ የጠፋውን ቋንቋ በጣም መሰረታዊ የሚባሉ የቋንቋ ውቅሮችን እና ለውጦችን በሌላ ቋንቋ ይገልጻል፡፡ ውጤቱንም በተጠኝው ቋንቋና በተነጻጻሪ ቋንቋ ያሰፍራል፡፡

በዚህ ጥናት አንድ ኡጋሪቲክ (Ugaritic) ቋንቋ የተጠና ሲሆን ቋንቋው ከጥንታውያን የእብራውያንና የግሪክ ቋንቋዎች ጋር ዝምድና እንዳለው ማዎቅ ችለዋል፡፡ የተሰራው ቀመር በቋንቋዎች መካከል ያለውን ዝምድና በማጥናት የጠፉ ቋንቋዎችን መሰረታዊ ጭብጥና ስነ-ልሳናዊ ይዘት ለመረዳት ያስችላል፡፡ የጥናት ስልቱ ባልጠፉ ቋንቋዎች ላይ ተሞክሮ የቋንቋውን ቤተሰብ ሳይቀር መለየት አስችሏል፡፡

የጥናት ቡድኑ ለወደፊት የጠፋውን ቋንቋ ጽሁፍ ከሚታወቅ ጋር በማዛመድ ብቻ እየተሰራ ያላውን ጥናት በማሳደግ ምንም እንኳን የቋንቋው ድምጸትና አነባበብ ቢጠፋም የአንድን ቃል ስነ-ፍቻዊ መንገድ በመከተል ቋንቋውን ለማጥናት አቅደዋል፡፡
ምንጭ፡ Massachusetts Institute of Technology እና www.technology.org
የተማሪዎችን የሂሳብ ክህሎት ለማሳደግ የሚረዱ ጠቃሚ መተግበሪያዎች

አሁን ባለንበት የዲጂታል ዓለም በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ ተመስርተው የሚሰሩ መተግበሪያዎች ለቁጥር አዳጋች እየሆኑ መተዋል፡፡ በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተመስርተው የሚሰሩት የተለያዩ መተግበሪያዎች ብዙ ሰዎችን ውጤታማ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች መሰል የስልክ መተግበሪያዎችን በትምህርታቸው ላይ ቢጠቀሙ የሂሳብ ክህሎታቸውን በቀላሉ ለማሳደግ እና እራሳቸውንም ለማብቃት በእጅጉ ሊረዳቸው ይችላል፡፡

Photomath
ይህ መተግበሪያ በአንድሮይድ ስማርትፎን እና በiOS ዲቫይዞች ላይ በቀላሉ የሚጫን አፕሊኬሽን ሲሆን በዓለማችን ላይ ብዙ ተጠቃሚዎችም የሚተገብሩት ነው፡፡ አፕሊኬሽኑ በተለይም የስልክ ካሜራን በመጠቀም ማንኛውንም የሂሳብ ጥያቄዎች ከወረቀት ላይ በማንሳት፤ መልሶቹን ደረጃ በደረጃ ወይም (step-by-step) የሚያሳይ በመሆኑ ለተማሪዎች የሂሳብ ክህሎት መዳበር ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡

MalMath
ይህ መተግበሪያ እንደ Photomath ሁሉ በዓለማችን ላይ ብዙ ተጠቃሚ ያለው እና በአጠቃቀም ቅለቱም ብዙዎች የሚመርጡት የአፕሊኬሽን አይነት ሲሆን የ Integral፣ Logarithm፣ Algebra እና ሌሎች የሂሳብ መሰረታዊ አሰራሮችን ባማረና በቀለለ መልኩ የሚያቀርብ ነው፡፡

Mathway

Mathway እንዲሁ ብዙ ገጽታዎች የተጨመሩለት እና ማንኛውንም የሂሳብ ጥያቄዎች በካሜራ በማንሳት የመልሱን አሰራር በቀላሉ ለማሳየት የሚያስችል መተግበሪያ ሲሆን በዓለም ላይ ካሉ የተለያዩ የሂሳብ ባለሙያዎች ጋር በማገናኘት ስልጠናዎችን እና ትምህረቶችን በቀላሉ ለማቅረብ በመቻሉ የተለየ ያደርገዋል፡፡

WolframAlpha
ይህ መተግበሪያ እንደሌሎቹ ሁሉ ተማሪዎችን በሂሳብ ትምህርት ለማገዝ የቀረበ ሲሆን በተለያዩ አሰራሮች ዙሪያ የጠለቀ ትንታኔን እና ምሳሌዎችንም አካቶ የያዘ ነው፡፡ WolframAlpha በተለይም የarithmetic እና calculus አሰራሮችን ባማረና ሁሉም ሰው ሊረዳው በሚችለው መልኩ የሚያቀርብ መተግበሪያ ሲሆን አንድሮይድ ስልክን ጨምሮ በiOS ዲቫይዞች ላይም በቀላሉ የሚጫን ነው፡፡
መረጃው የ Tech Viral ነው
ለመድሀኒት አምራቾች አዲስ የኬሚስትሪ ሶፍትዌር
*************************************************
ግላስጎው የተባለ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የኬሚስትሪን ቃላትና ፎርሙላዎች አንድ ሮቦት እንዲረዳው የሚያስችለው የኮምፒውተር ሶፍትዌርን አበልጽገዋል፡፡ ይህም ኬሚስትሪን ወደ ዲጂታል ዘመን ሊያሸጋግረው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የምርምር ስራውን ለአመታት ሲያከናውኑ የነበሩ ኮኒን እና ጓደኖቹ እንዳሉት ፈጠራው አንድን መድሀኒት በፋብሪካዎች ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ ዝርዝር ግብዓቶችን ለይቶ የሚሰጥ ነው፡፡ ይህም የተለያዩ ሞሎኪዩሎችን በጥራት ለመስራትና ለማምረት የሚያስችል የኬሚስትሪ ebook reader ነው፡፡
በኬሚስትሪ ዙሪያ ያሉ አብዛኛዎቹ ሳይንሶች ላለፉት 200 ዓመታት ያልተለወጡ መሆናቸውን የገለጹት ተመራማሪዎቹ አሁን ግን ተግባሩን ከማኑዋል (በወረቀት ካለ) ወደ አውቶሜትድ (በኮምፒውተር) ለመቀየር ችለዋል፡፡ አዲሱን ግኝት እነ ክሮኒን XDL ብለው የሰየሙት ሲሆን የኬሚስተሪ ኮምፒውተራዊ ቋንቋ ተብሎ ሊወሰድ ይችላል (chemical description language)፡፡ የመጀመሪያው X በግሪክ ድምፀት “kai” ተብሎ የሚነበብ ሲሆን ይህም ከግሪክ የኬሚስትሪ ቃላት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ XDL አንድ ማሽን ምን መስራት እንዳለበት የሚያዝ ፕሮግራም ነው ልክ እንደ HTML::
ሌላው ግኝቱ ያለው ጥቅም ኬሚስቶች ኬሚካዊ ህጉን (chemical protocol) በቀላል ቋንቋ ማስተካከል መቻላቸው ነው፡፡ ይህም ተመራማሪዎቹ ማሽኑን በቀላል ስልጠና መጠቀም እንዲችሉ ያስችላቸዋል፡፡ በሙከራ ወቅትም ለ12 ትግበራዎች የሚያገለግሉ ፎርሙላዎችን በጽሁፍ ማቅረብ ተችሏል፡፡ ስራውም ውጤታማ እንደነበር ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል፡፡
ከተመራማሪዎቹ አንዱ የሆነው ክሮኒን የኬሚስትሪ ሮቦቶችንና የXDL ፕሮግራሙን ለመሸጥ Chemify የተሰኘ ድርጅትን አቋቁሟል፡፡ በግንቦት 2019 GlaxoSmithKline የተባለ የመድሀኒት አምራች ኩባንያ የምርምሩን የመጀመሪያ ምርት (prototype) ጥቅም ላይ አውሎታል፡፡ በዚህም ለአንድ መድሀኒት የሚያስፈልገውን የሞሎኪዩሎች ጥንቅር (molecular recipe) በቀላሉ በኮምፒውተር በመታገዝ ማዎቅ ተችሏል፡፡
ምንጭ CNBC Technology
የእጅ ጽሁፍ ለአእምሮ ንቃት
***************************
ኮምፒውተር የአብዛኛውን የአለማችን እንቅስቃሴ እየተቆጣጠረ ባለበት በአሁኑ ዘመን የጽሁፍ ስራ ከወረቀት ይልቅ ወደ ኮምፒውተር ኪቦርድ እየተለወጠ መሄዱ እሙን ነው፡፡ በእጅ ጽሁፍ ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በተለይ ቅጥልጥል ጽሁፍን አለመለማመድ ወይም አለመማር አዕምሯችን ያለውን አቅም በመጠቀም መማርና ማስታወስ እንዳንችል ያደርገናል፡፡ በ NTNU (Norwegian University of Science and Technology) የተሰራው ጥናት ዘመን አልፎበታል ተብሎ የሚታሰበው ቅጥልጥል የእጅ ጽሁፍ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ሊታደስ እንደሚገባው አትቷል፡፡
በተለይ የተሸሻለ የትምህርት ግብአት አቅርቦት ባላቸው ያደጉ ሀገራት ህጻናት የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚማሩ ቢሆንም በወረቀት ላይ የሚጻፍ ቅጥልጥል ጽሁፍ ግን የአእምሮን የመማርና የማስታወስ ችሎታ ለማዳበር ወደር አይገኝለትም፡፡ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ያደጉ ሀገራት ትምህርት ቤቶች የእጅ ጽሁፍ ልምምድ ሙሉ ለሙሉ እየተቋረጠ ይገኛል፡፡
በጥናቱ የተተፉ Audrey van der Meer የተባሉ ፕሮፍሰር በኖሮይ ከ1 በላይ የሆነ ትውልድ የእጅ ጽሁፍ ችሎታውን ያላዳበረ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል አጥኝዎች MRI የተባለ መሳሪያን በመጠቀም በእጅ ጽሁፍ ጊዜ እና ኮምፒውተር በመጠቀም ጊዜ ያለውን የአእምሮ ምላሽ ለ10 ዓመታት ያክል አጥንተዋል፡፡ በጥናቱም የእጅ ጽሁፍ የበለጠ የአእምሮ ስራን የሚያቀላጥፍና የሚያነቃቃ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ በተጨማሪም የእጅ ጽሁፍ ልምድ የልጆችን የንባብ ልምድ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድግ ጥናቱ አመልክቷል፡፡
በሀገራችን እንደሚታወቀው አብዛኛዎቻችን የእጅ ጽሁፍ ትምህርት የጀመርነው የመጨነቋቆር ልምምድ በሚል ርዕስ በሚሰጥ ትምህርት ነው፡፡
ምንጭ፡ psychology today
ውሳኔዎችን እንዴት እናሳልፋለን
******************************
ብዙዎቻችን የህይወት መስመራችንን ለማስተካከል፣ የምንሰማራበትን የስራ መስክ ለመምረጥና ሌሎች በህይወታችን ትልልቅ የምንላቸውን ውሳኔዎች ለማሳለፍ እንቸገር ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በነገሮች ላይ ለመወሰን ተቸግረን ቀናት፣ ሳምንታት ወይም ወራት ሊያልፉ ይችላሉ፡፡ ምም እንኳን በአንድ ነገር ላይ ውሳኔ ማሳለፍ ቀላል ባይሆንም አብዛናውን ጊዜ ውሳኔዎች የሚጋሯቸው ተመሳሳይ መሰረታዊ ነጥቦች አሉ፡፡ በዚህ ጽሁፍ በነገሮች ላይ ውሳኔ ከማሳለፋችን በፊት ልናደርጋቸው የሚገቡንን መሰረታዊ ነጥቦች ልናጋራችሁ ወደናል፡፡ ተጋበዙልን፡፡
የውሳኔያችን ግብ፡ አንድን ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት የውሳኔያችን ግብ ምን እንደሆነ በደንብ መለየት ይኖርብናል፡፡ እዚህ ላይ ግብ የምንለው የአንድ ውሳኔ ተግባራዊ ሂደቶች ካለቁ በኋላ የምንጠብቀው ውጤት ነው፡፡ ለምሳሌ ልንሰማራ በፈለግነው የስራ መስክ ዙሪያ ውሳኔ ለማሳለፍ በቅድሚያ ያንን የስራ መስክ ለምን እንደመረጥነው እና በስራው ምን ለማደረግ እንዳሰብን መለየት ይኖርብናል፡፡ ይህ በስራችን ውጤታማ እንድንሆንና የምንፈልገውን ግብ እየሰብን በመካከል ሊገጥመን የሚችልን ማንኛውንም ዓይነት ፈተና መሻገር እንድንችል ያደርገናል፡፡ ግብን መረዳት ውሳኔን ለማሳለፍ እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡
አንድ ሰው የት እንደሚሄድ ሳያውቅ ከቤት የሚወጣ ከሆነ እያንዳንዱ እንቅስቃሴው ያልታቀደ እና አላማ የሌለው ይሆናል፡፡ የዚህ አይነት ሰው ለምሳሌ የታክሲ ተራ ሂዶ ሶስት ያልሞሉ ታክሲዎች ቢያገኝ ሊሳፈር የሚችለው አብዝቶ በጠየቀው ረዳት ታክሲ ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ ምንም ሰው ባልገባበት ታክሲ ይገባና ቢያንስ ታክሲው እስኪሞላ ጊዜው ይሔዳል ብሎ ሊያስብ ይችላል፡፡ ስለዚህ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት አላማችን ወይም ግባችን ምን እንደሆነ መለየት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡
ሌሎች አማራጮች፡ አማራጭ ባለበት ቦታ ሁሉ እያንዳንዱን አማራጭ መፈተሸና ቢያንስ ከፍላጎታችን አብዛኛውን ይዟል ብለን የምናስበውን አማራጭ መርጠን መወሰን ይኖርብናል፡፡ አማራጮችን በደንብ ማየት ውሳኔያችን በእውቀት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ የዚህ ዓይነት ውሳኔ ደግሞ በስራ ሂደት ውቴታማ እንድንሆን የሚያስችለን ቁልፍ ነገር ነው፡፡ ሁሉም ሰው ዓረፍተ ዘመን ሳይገድበው አከናውነዋለሁ፣ እደርስበታለሁ ወይም እሆነዋለሁ ብሎ የሚያልመው ነገር መኖሩ አይቀርም፡፡ በውሳኔ ጊዜ ከፊታችን ከቀረቡት አማራጮች ያለምነውን ለመሆን ወይም ለመስራት የሚያስችለን አማራጭ የቱ ነው ብሎ ውሳኔን ማሳለፍ በውሳኔያችን መጸጸት እንዳይኖር ያደርገናል፡፡
የውሳኔያችን ውጤት፡ አንድን ውሳኔ መወሰን በምንወስነው በእኛ እና በሌሎች ላይ የሚኖረው አወንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ አለ፡፡ ታዲያ ውሳኔያችን ከሚያስገኘው ጥቅምና ከሚኖረው ጉዳት በማነጻጸር መወሰን አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ ብዙዎቹ መጥፎ የሚባሉ ውሳኔዎች መጥፎ ዓላማን አንግቦ በመነሳት የተወሰኑ ናቸው፡፡ ስለዚህ ከአንድ ውሳኔ በፊት ውሳኔን የሚያሳልፍ ሰው በትክክል ምን ማድረግ እንደፈለገ መረዳት አለበት፡፡
በአጠቃላይ በህይወታችን አንድን ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት የውሳኔያችን ግብ፣ በውሳኔያችን ውስጥ ያሉ አማራጮች እና ውሳኔያችን የሚያስከትለውን ውጤት መለየት የውሳኔያችን ወሳኝ ጉዳዮች መሆን አለባቸው፡፡
ምንጭ፡ www.howstuffworks.com
ውድ የገፃችን ተከታታዮች “BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በኢንስቲትዩታችን የዩትዩብ ቻናል ላይ ስልጠና አዘጋጅተን ለእናንተው ያቀረብን መሆኑ ይታወሳል፡፡
በስልጠናው ማብቂያ ላይ ጥያቄዎችን አቅርበን እንድትመልሱና የምስክር ወረቀት እንድታገኙ በጠየቅነው መሰረት ጥያቄዎቹን ሞልታችሁ ለላካችሁልን ከ50 በላይ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት አድርሰናል፡፡ የተቀራችሁ ሰልጣኞችን በተመለከተም የምስክር ወረቀቶቹ እየተዘጋጁ ሲሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ የምንልክላችሁ ይሆናል፡፡
በተያያዘም በልዩ ልዩ ምክንያች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ጥያቄዎቹን ሞልታችሁ መላክ ላልቻላችሁ የስልጠናው ተካፋዮች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ አርብ ጥቅምት 22 ድረስ በኢ-ሜይል አድራሻችን (stic.ethiopia@gmail.com) መላክ የምትችሉ ይሆናል፡፡
መሬት ስበት ህግ በቅንጣቶች (atoms)
**********************************
በፊዚክስ ታሪክ ውስጥ ከሚነገሩ የምርምር ስራዎች የጣሊያናዊው ጋሊሊዮ ጋሊሊ የመሬት ስበት ሙከራ አንዱ ነው፡፡ እነደሚታወቀው ጋሊሊዮ ከተወሰነ ከፍታ ላይ የተለያየ ክብደት ያላቸውን ነገሮች ወደታች እኩል በመልቀቅ ሁለቱም በእኩል ሰዓት መሬት ላይ በመድረሳቸው የመሬት ስበት ሀይል ተመሳሳይ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ተመራማሪዎች ይህ የጋሊሊዮ የምርምር ውጤት የሆነው የመሬት ስበት ህግ በቅንጣቶች (atoms) መስራትና አለመስራቱን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሙከራዎችን ሲደርጉ ቆይተዋል፡፡
አዲስ በተሰራው ጥናት በጣም አስቸጋሪ የሆነው ቅንጣቶችን ከእኩል ከፍታ ወደ መሬት የመልቀቅ ሙከራ ከጋሊሊዮ ሙከራ ጋር ተመሳሳይ ውጤት አሳይቷል፡፡ የተለያዩ ቅንጣቶች በመሬት ስበት ምክንያት ከላይ ወደ ታች በተመሳሳይ ፍጥነት (acceleration) ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ተመራማሪዎች የሩቢዲየም (rubidium) ቅንጣትን ሁለት የተለያዩ ክፍሎች (isotopes) አወዳድረዋል፡፡ እነዚህ ክፍሎች በማዕከላዊ ክፍላቸው (nuclei) የተለያየ የኒውትሮን ቁጥር ያላቸው ናቸው፡፡ ሙከራውን 8.6 ሜትር ከፍታ ካለው ቱቦ ውስጥ የተሰራ ሲሆን ሁለቱ ክፍሎች (isotopes) ከመነሻቸው እስከ መድረሻቸው ተመሳሳይ እንቅስቃሴ አሳይተዋል፡፡
ይህ ግንኝት ከአልበርት አንስታይን general relativity እሳቤ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ በስበት ህግ የአንድ ነገር የእንቅስቃሴ ፍጥነት በነገሩ መጠነቁስ ወይም ውቅር (composition) አይወሰንም፡፡
ምንጭ Sciences News Magazine
ለውድ ተከታታይ ቤተሰቦቻችን በሙሉ፤ እንኳን 1 ሺህ 495ኛው የነብዩ ሙሐመድ መውሊድ በዓል አደረሳችሁ፡፡
መልካም በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ ምኞታችን ነው!!!