ሌሎች የፕላስቲክ አማራጮች ተፈጥሮን ለመታደግ
-------------------------------
በዓለማችን ያሉ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን ለማስወገድ እና ተያይዘው የሚመጡ የአካባቢ ብክለት ችግሮችን ለማስቀረት የረዥም ጊዜ እቅዶችን ቀርፀው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡ ኒውላይት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ይህን መርህ በሚገባ ከሚከተሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው ፕላስቲከ መሰል የባዮዲግሬደብል ቁስ ደግሞ ከብዙዎች ተቀባይነት ያስገኘለት ነው፡፡
በካሊፎርኒያ መቀመጫወን ያደረገው ኒውላይት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከአስር አመት በላይ ምርምር ሲያደርግብት የቆየው (AirCarbon) የተሰኘው ይህ ቁስ የፕላስቲክ መልክ፣ ይዘት እና ግልጋሎት ኖሮት የተሰራ ቁስ ቢሆንም አጠቃላይ ስሪቱ ግን በተለያዩ ደቂቅ አካለትና ባካቴሪያዎች መበስበስ እንዲችል የተደረገ እና ምንም አይነት ብክለት እንዳይኖረው የተቀመረ ነው፡፡
ኩባንያው ይህን መሰል ፈጠራ ለማከናወን እንደመነሻ የተጠቀመው በውቅያኖስ ውስጥ መኖሪያቸውን ባደረጉ እና ለአለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ምክንያት የሆኑትን የሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳድ ጋዛችን በሚመገቡ ደቂቅ አካላት አማካኝነት ነው፡፡ አነዚህ አካላት የሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳድ ጋዞችን ወደተፈጥሮ ፖሊመር በመቀየር ልክ እንደፕላስቲክ የሚተጣጠፉ እና የሚቀረፁ ቁሶችን ማውጣት የቻሉ ሲሆን ተመራማሪዎችም ከዚህ የተፈጥሮ ሂደት በመነሳት ፕላስቲኮችን በዚህ አምሳያ ለመስራት ሞክረዋል፡፡
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ሀርማ በምርምሩ ዙሪያ እንደተናገሩትም በዚህ ሂደት ለወጤት የበቃውን ፈጠራ (AirCarbon) ብለን የሰየምንበት ምክንያት አየርም ይሁን ካርቦን በውሃ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሊሟሙ እና ወደፈሳሽነት ሊቀየሩ መቻላቸውን ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡ የምርምር ውጤቱ የከባቢ አየር ጋዞችን እንደግብዓት መጠቀም ዋና አላማ አድርጎ የተነሳ በመሆኑ የተፈጥሮ ስነምህዳርን በተለያየ መልኩ የሚታደግ ይሆናል፡፡
ኒውላይት ለዚህ አስገራሚ የፈጠራ ስራው በእንግሊዝ መቀመጫቸውን ባደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣነት ሙገሳን ያስገኘለት ሲሆን፤ የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳዳር (FDA) እና የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ (EPA) ከተፈጥሮ ጋር ወዳጀነት ለመሰረተው አስገራሚ ፈጠራ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል፡፡
ምንጭ፡ CNN Business

የፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክን በረከሰ ዋጋ በማቅረብ ታሪካዊ ሆኗል
--------------------------------------
ዓለም አቀፉ የኃይል ኤጀንሲ (IEA) በየዓመቱ በሚያወጣው ሪፖርት አባል ሃገራት በኢነርጂ አጠቃቀማቸው እና አካባቢ ጥበቃ ላይ ሊኖራቸው ስለሚችለው አተገባበር ሰፊ መረጃዎችን እና ቅድመ ትንታኔዎችን የሚያቀርብ ነው፡፡ ድርጅቱ በዚህ አመት ሪፖርቱ ከፀሃይ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል ቀድሞ ሲታሰብ ከነበረው አንጻር የዋጋ ምጣኔ በእጅጉ ያነሰ እና በቀላሉ ሰዎች ጋር በመድረስ በቀዳሚነት የሚቀመጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከፀሃይ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል በአለማችን እስካሁን ከታዩት የሃይል አማራጮች ቀዳሚነቱን የያዘበት ዋና ምክንያት በታዳሽ ሃይል ኢንቨስትመንት ዘሪያ የሚኖረውን ከፍተኛ ስጋት የሚቀንሱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመበልፀጋቸው እና ወሳኝ የመንግስታት ፖሊሲዎች በመኖራቸው መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡
በኤሌክትሪክ ሃይል ገበያው የፀሃይ የሃይል ምንጭነት ያለጥርጥር መንገሱን የሚናገሩት የድርጅቱ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክትር ዶ/ር ፋቲ ቢሮል ከዚሀ የፖሊሲ መነሻ ተነስተን ከ2022 በኋላ የሚኖረንን የኤሌክትሪክ ሃይል አጠቃቀም መለካት እና መተንተን እንችላለን ይላሉ፡፡ የዓለም አቀፉ የኃይል ኤጀንሲ የ2020 ሪፖርት እንዳስቀመጠው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአለማችን ላይ መከሰት ኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎትን ለመተንበይ አስቸጋሪ ቢያደርገውም ከተለያዩ ሴናሪዮች በመነሳት በየዓመቱ ሊኖር የሚችለውን ውጤቱ መገመት እንደሚቻል የድርጅቱ ሪፖርት ያሳያል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ መጠነ ሰፊ የፀሃይ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የኤሌክትሪክ ሃይልን በረከሰ ዋጋ በማቅረብ በኩል ትልቅ ለውጥ ማምጣታቸውን የሚያወሳው ሪፖርቱ በተለይም ባለፉት 10 አመታት አስገራሚ መሻሻሎች እንደነበሩ ያስቀምጣል፡፡ ለአብነት በአውሮፓውያኑ 2010 አንድ ኪሎዋት በሰዓት የኤሌክትሪክ ሃይል ለማቅረብ 38 ሳንቲም ያስወጣ የነበረ ሲሆን በ2019 ይህ ዋጋ በእጅጉ ቀንሶ 6.8 ሳንቲም ሆኗል፡፡
ይህ የዋጋ ምጣኔ በቀጣዮቹ አስር አመታት የበለጠ ተሻሽሎ የአለማችን የኤሌክትሪክ ሃይል ፍላጎት 80 በመቶው በታዳሽ የሀይል አማራጮች እንዲያዝ የሚያነሳሳ ቢሆንም አሁን ያለው አጠቃላይ ከታዳሽ ሃይል የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል ከ40 % የሚሻገር ባለመሆኑ በቀጣዮቹ አመታት የሚሰሩት ስራዎች እጅግ ወሳኝ እንደሚያደርጋቸው ድርጅቱ በሪፖርቱ ያነሳል፡፡
በዚህ የሃይል አማራጭ መዋቅር ውስጥ የሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶች ትልልቆቹ የሃይል ማመንጫ መንገዶች ቢሆኑም፤ ከፀሃይ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል አለማችን እስከዛሬ አይታ ከምታውቀው የሃይል አማራጮች በተደራሽነቱም ይሁን በኢኮኖሚ ጥቅሙ ወደር የማይገኝለት መሆኑ የ2020 የIEA ሪፖርት በሚገባ ያረጋግጣል፡፡ ምንጭ Big Think

ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ፤ የኢትዮጵያ ፈር ቀዳጅ ሳይንቲስት
አለማችን በበርካታ ውስብስብ ችግሮች የተሞላች ነች፡፡ ይህንን ውስብስብ ችግር እራሱ የሰው ልጅም ሲፈጥረውና ማጣፍያው አጥሮት ሲቸገርም አስተውለናል፡፡ በተፈጥሮም ይሁን በሰው ሰራሽ ምክንያት ታዲያ ለተፈጠሩ ችግሮች የሰው ልጅ ጥልቅ አዕምሮ በተለያዩ ወቀቶች መፍትሄዎችን ለአለም ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ በረዥሙ የሰው ልጅ ህይወትም አለም ላይ የተከሰቱ ችግሮችን በጥልቅ ምርምራቸው እና አሳቢነታቸው መፍትሄ የወለዱ እንቁ ባለሙያዎች በየሃገሩ ተፈጥረዋል፡፡ ታዲያ አትዮጵያችን ለአለም ካበረከተቻቸው ውድ ምሁራኖች መካከል ብዙዎችን መጥቀስ ብንችልም ለዛሬ ግን ስለፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ በጥቂቱ ልናስታውቹ ወደናል፡፡
መስከረም 7.1928 ዓ/ም በጅጅጋ ወረዳ ከእናታቸው ወ/ሮ አየለች ለማ እና ከአባታቸው በቀለ ወልደየስ ተወለዱ የያኔው ህጻን አክሊሉ፡፡ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ያኔው ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በ1960 ከዊንስከንሲን ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በሚያጠኑበት ወቅት በብላሀርዝያ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ነበራቸው፡፡ እኚህ ወጣት ተመራማሪ በየቀኑ ሴቶች በወንዝ ዳር ልብስ በሚያጥቡበት ወቅት በትኩረት ይከታተሉ ነበር፡፡ ሴቶቹ ልብሱን እንዶድ በሚባል ተክል ነበር የሚያጥቡት፤ በወቅቱ እንዶድ በርካታ የብላሀርዝያ ትሎችን መግደል የሚችል ተክል በመሆኑ ፕሮፌሰሩ ከፍተኛ ትኩረት ሰተውት ነበር፡፡ በ1966ም በቤተ ሙከራ ውስጥ ከተሞከረ በኋላ ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ በሳይንስ ፎረም ላይ አቀረቡት፡፡ በወቅቱ በአፍሪካ ውስጥ የሺስቶስሚያሲስ በሽታ ይከሰት ስለነበር እና የፕሮፌሰሩ ግኝት በዝቅተኛ ዋጋ በሽታ አምጪ የሆነውን ትል የሚገድል በመሆኑ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት ነበር፡፡
በዚያን ወቅት ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ በሜዲካል ኮሌጅ የፓራሳይቶሎጂ ፕሮግራም ጀምረው ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ታሪካ በሳይንስ ፋካሊቲ ውስጥ የመጀመሪያው ዲን ሆነውም አገልግለዋል፡፡ በዚያን ወቅት ፕሮፌሰር አክሊሉ ወደ ስታምፎርድ ዩኒቨርሲቲ በማቅናት ትኩሳትና ሌሎች የጥገኛ በሽታ አምጪ ህዋስያን ለመዋጋት የሚያስችል የእንዶድን ኬሚካላዊ ባህሪያቶች ላይ ጥናት ለማድረግ ለሁለት አመት ቆይተዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የሚያስፈልገው ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ የእንዶድ ተክል ቀንድ አውጣውን ለመግደል ስለሚችል እና በሂደትም በሽታውን ለመቆጣጠር እንደሚረዳ ስለደረሱበት ዕውቅና እንዲሰጣቸው ተደርጓል።ቴክ-ሳይንስ 92
ስለ እንዶድ ጥቅምና የውኃ ትላትል ገዳይነት በማግኘታቸው የዩናይትድ ስቴትስ የፈጠራ ባለቤትነት ወይም ፓተንቶች ኣግኝተዋል። እንዶድ ሳይንሳዊ መጠሪያ ስሙ (Phy¬tolacca dodecandra) ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በወንዝ ዳርቻዎች ይበቅላል፡፡ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ልክ እንደሳሙና በሰፊው ለልብስ ማጠቢያነት የሚያገለግለው እንዶድ፣ ከተክሉ የሚገኘው ጭማቂ ወይም ፍሬው ደግሞ ለብላሀርዝያ በሽታ የሚዳርገውን ተውሳክ የሚያስጠልለውን ቀንድ አውጣ ስለሚገድል ለመድኃኒትነት ያገለግላል፡፡ ከተክሉ የሚገኝ ጭማቂ አልቅትንም ስለሚገድል በውኃ ውስጥ የአልቅቶችን ቁጥር ለመቆጣጠር ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ተክሉ ለከብቶች የማይስማማ በመሆኑ እንስሳት ለምግብነት አይመርጡትም፡፡
ሺስቶሶሚያሲስ (ብላሀርዝያ ወይም ካታያማ ትኩሳት) በመባል ይታወቃል፡፡ ፕሮፌሰር አክሊሉ ስለዚህ በሽታ ባደረጉት ሰፊ ምርምር የመተላለፊያውን መንገድ፣ ምልክቶቹን እና ህክምናውን ከሌሎች ጉዳዮች ጋር አብራርተው ሊያሳትሙ ችለዋል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር አክሊሉ ጥናት በሽታው የሚተላለፈው ጥገኛ ትል በሆነው የሺስቶሶማ ህዋስ ዓይነት ሲሆን የሽንት መተላለፊያን ወይም አንጀትን ሊያጠቃ ይችላል፡፡ የሕመሙ ምልክት የሆድ ህመም፣ ተቅማጥ፣ ደም የተቀላቀለበት ሰገራ ወይም በሽንት ላይ ደም መታየትን ያጠቃልላል፡፡ ለረጅም ጊዜ ህመሙ የቆየበት ሰው የጉበት ህመም፣ የኩላሊት ስራ ማቆም፣ መሃንነት ፣ ወይም የፊኛ ካንሰር ሊያስከትልበት ይችላል፡፡ በልጆች ላይ ደግሞ ዝቅተኛ እድገትና የመማር ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡
በሽታው የሚሰራጨው ትላትሎቹ በሚገኙበት ውኃ ስፍራ በሚፈጠር የቆዳ ንክኪ ነው፡፡ እነዚህ ትላትሎች የሚመነጩት ከተበከሉ ቀንድ አውጣዎች ነው፡፡ ይህ በሽታ በደሃ አገራት በሚገኙ ታዳጊዎች ላይ የተለመደ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ልጆቹ በተበከለ ውኃ የመጫወታቸው አጋጣሚ ሰፊ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም በእለት ተእለት ስራ አማካኝነት ማለትም ገበሬዎች፣ አሳ አጥማጆችና ሌሎች የተበከለ ውኃ የሚጠቀሙ ሰዎች የበሽታው ስጋት የሚያጠላባቸው የህበረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
ህክምናውን በተመለከተ ምርመመራው የሚደረገው የትሉን እንቁላሎች ሽንት ወይም ሰገራ ላይ መኖራቸውን በመመርመር ሲሆን፤ በደም ላይ ፀረ እንግዳ አካል በመፈለግ በሽታው መኖሩን ማረጋገጥም ይቻላል፡፡ የብላሀርዝያን በሽታ ለመከላከል ንፁህ የውኃ አቅርቦትን ማሻሻል እና የቀንድ ኣውጣ ቁጥርን መቀነስ ዋነኞቹ ቢሆንም በሽታው በተስፋፋበት አካባቢ በአንድ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ፕራዚኩዋንትል በተባለ መድኃኒት በየዓመቱ ማከም በሽታውን ለማጥፋት ሌላኛው መንገድ ነው፡፡ ይህ እርምጃ በበሽታው የሚያዙ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስና የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ያስችላል፡ ፡ ፕራዚኩዋንትል በበሽታው የተጠቁትን ለማከም በ(World Health Organization) የሚመከር የሕክምና ዘዴ ነው፡፡ የበሽታው መስፋፊያ ዘዴ የትሉ እንቁላሎች በሽንትና ሰገራ አማካኘነት ከሰው አካል ወጥተው ቀንድ ኣውጣ ውስጥ በመግባት የሚባዙ በመሆኑ በሽታውን ለመከላከል ሕዝቡ ሽንቱንና ሰገራውን ከሚጠጣው ውኃ እንዲያርቅ ማስተማር ያስፈልጋል፤ እንዲሁም የሚጠቀመው የኩሬ ወይም የወንዝ ውኃ ከሆነ ውኃውን ማከም እንደሚገባው ማስተማር ያስፈልጋል።
ሲስቶሶሚያሲስ በዓለም ላይ ወደ 210 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ የሚያጠቃ ሲሆን፤ ከ12,000 እስከ 200,000 የሚሆነ ሕዝብ በዓመት ውስጥ በዚህ በሽታ ይሞታል ተብሎ ይገመታል፡፡ በሽታው በስፋት የሚታየው በአፍሪካ፣ በእስያና ደቡም አሜሪካ ነው፡፡ እንዲሁም ወደ 700 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ፣ ከ70 በላይ አገራት፣ በሽታው በስፋት በተሰራጨበት አካባቢ ይኖራል፡፡ ሲስቶሶሚያሲስ ከወባ ወይም ማላሪያ ቀጥሎ በሁለተኛነት የሚቀመጥና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ተፅእኖ ያለው በሽታ ነው፡ ፡
እ.ኤ.አ. በ1993 እስከ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ በነበረው ጊዜያቸው በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ትስስር በመፍጠር ለአገሬው ተወላጅ የአቅም ግንባታ ያደረጉት ፕሮፌሰር አክሊሉ፤ የሳይንሳዊ ምርምሮችን በማስተዋወቅም ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል፡ ፡ ፕሮፌሰር አክሊሉ ለማ ሶስት ፓተንቶችን፤ አምስት መጽሐፍቶችን እና 60 ሳይንሳዊ የጥናት ጽሁፎችን በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡ በ1969 በንጉስ ቀዳማዊ ሓይለ ስላሴ የወርቅ ሜዳሊያ እና ሌሎች በርካታ ሽልማቶችን ያገኙት እኝህ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ምሁር ከብዙ ትሩፋቶቻቸው በኋላ ይህችን አለም በ62 አመታቸው ተሰናብተዋል፡፡
ከቴክ ሳይንስ ቅፅ 17 የተወሰደ

ስለ GMO (ልውጠ ህያዋን) የተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም፡፡ GMO (ልውጠ ህያዋን) አሉታዊ ወይስ አወንታዊ ጎኑ ያመዝናል? ሙሉ ዝግጅቱን በዩትዩብ ቻናላችን ይዘንልዎ ቀርበናል፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=Eka5wceAA1A
ያስታውሱ!!! ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ይከታተሉን
(Nilesat 12520/v/27500)
(በተጨማሪም Ethiosat ላይ እንገኛለን)

YouTube
ስለ GMO (ልውጠ ህያዋን) የተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም፡፡ GMO (ልውጠ ህያዋን) አሉታዊ ወይስ አወንታዊ ጎኑ ያመዝናል?A special program on GMO.
የጤና ባለሙያዎች እና ተጋላጭ ማህበረሰቦች በጥር ወር ማለቂያ ክትባት ሊያገኙ ይችላሉ
የኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን አደጋ ውስጥ ለከተተው ግለሰቦች እና ቫይረሱን ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ለሚገኙት የጤና ባለሙያዎች በፈረንጆቹ ጥር ወር ማለቂያ ላይ ክትባት ሊደርሳቸው እንደሚችል የአሜሪካ የጤና እና ሰብዓዊ አገልግሎቶች (HHS) ተቋም ዋና ፀሃፊ አሌክስ አዛር በትላንትናው ዕለት ገልፀዋል፡፡
ዋና ፀሃፊው በዕለቱ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ የኮሮናቫይስ ክትባቶች አስተማማኝ እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ሰዎች ጋር የመድረሳቸው ሁኔታ በመጨረሻዎቹ የክትባቶቹ የሙከራ ሂደት ላይ ሊወሰን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ጥቅም ላይ ለመዋል ከጫፍ የደረሱ ክትባቶች ፍፁም ደህንነታቸው ተረጋግጦ ሰዎች ጋር መድረስ እንዲችሉ በሶስተኛው የክሊኒካል ሙከራ አማካኘነት ብዙ ሺ ሰዎች ላይ ሊሞከሩ እንደሚገባም ዋና ጸሃፊው አስረድተዋል፡፡
በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ እጅግ የገዘፈ ስም ያለው ፋይዘር (Pfizer) የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያዘጋጀው ክትባት አስተማማኝነቱን እና ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ የሚስችል መረጃ በቀጣዩ ህዳር ወር መጠናቀቂያ የሚጠበቅ ሲሆን ክትባቱ መልካም ውጤቱ ከታየበትም የድንገተኛ ጊዜ አጠቃቀም ባለስልጣን (EUA) በሚፈቅው መሰረት ጥቅም ላይ የሚውልበት እድል አለ፡፡
በዓመቱ መጠናቀቂያ የምግብ እና መድሃኒት አስተዳደር (FDA) በሚፈቅደው መሰረት ክትባቶችን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ፀሃፊው በቅድሚያም በበሽታው እጅግ ለተጎዱ እና ለተጋለጡ ሰዎች የሚቀርብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በማስከተልም በጥ ወር መጠናቀቂያ ላይ በሁለም ዘርፍ የሚገኙ ሲኒየር ሃኪሞች የጤና ባለሙያዎች እና ተንከባካቢዎች ክትባቱን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ሚስተር አዛር ተናግረዋል፡፡
ዋና ጸሃፊው ከዚህ ውጭ ያለው የማህበረሰብ ክፍል በመጋቢት እና ሚያዚያ ወር ላይ ክትባቱን የማግኘት እድል እንዳለው ቢገልፁም ክትባቱን ብስፋት የመምረት ሁኔታ የስርጭቱ አካሄድ ገና ያልተረጋገጠ ጉዳይ መሆኑን አልሸሸጉም፡፡ አንዳንድ የጤና ኤክስፐርቶች እንደሚገልፁት ክትባት ከማግኘት እኩል በአስተማማኝ ሁኔታ ሰዎች ጋር የማሳራጨት ስራ እጅግ ከባድ ሲሆን፤ ከዚህም በላይ ክትባቱ ሰዎች ጋር ደርሶም ውጤታማነቱ እና ድህንነቱ 100% ማረጋገጥ አስቸጋሪ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡ ምንጭ፡ Livescience

ሁለት ጾታ ያለው ወፍ
*****************
ተመራማሪዎች ግማሽ ጎኑ ሴት ግማሽ ጎኑ ደግሞ ወንድ የሆነ ወፍ ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ CNN ባወጣው ዘገባ ባለሁለት ጾታው ወፍ አዘውትሮ በመዘመር የሚታወቅ ድምጸ መረዋ ነው፡፡ ይህንም ግኝት ተመራማሪዎቹ የመከሰት እድሉ በጣም ጠባብ ነው ብለዋል፡፡
ከ15 ዓመታት በፊት የተፈጥሮና ታሪክ ሙዚየም የሆነው ካርኔጅ ሙዚየም ተመሳሳይ የወፍ አይነት ማግኘቱን ገልጾ ነበር፡፡ ይህም ተቋሙ ካያቸው 800,000 ከሚደርሱ ወፎች መካከል አምስተኛው እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የዚህ አይነት ወፎች የራሳቸው መለያ ቀለም ያላቸው ሲሆን ወንዶቹ ሮዝ ነጠብጣብ ላባ ሲኖራቸው ሴቶቹ ደግሞ ቢጫና ቡናማ ቅልቅል ላባ አላቸው፡፡ አሁን ተገኘ የተባለውም ወፍ በአንዱ ክንፉ የወንድ ቀለም ሲኖረው በሌላ ክንፉ ደግሞ የሴት ቀለም አለው፡፡ በሳይንሳዊ (በዘረመል) መጠሪያው ጂናንድሮሞረፊዝም የሚባል ክስተት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ለCNN ተናግረዋል፡፡
ይህ አይነቱ ክስተት በሌሎች እንደ ሸረሪት፣ አሳዎችና በዶሮዎችም ሊከሰት እንደሚችል ተመራማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡ CNN
*****************
ተመራማሪዎች ግማሽ ጎኑ ሴት ግማሽ ጎኑ ደግሞ ወንድ የሆነ ወፍ ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ CNN ባወጣው ዘገባ ባለሁለት ጾታው ወፍ አዘውትሮ በመዘመር የሚታወቅ ድምጸ መረዋ ነው፡፡ ይህንም ግኝት ተመራማሪዎቹ የመከሰት እድሉ በጣም ጠባብ ነው ብለዋል፡፡
ከ15 ዓመታት በፊት የተፈጥሮና ታሪክ ሙዚየም የሆነው ካርኔጅ ሙዚየም ተመሳሳይ የወፍ አይነት ማግኘቱን ገልጾ ነበር፡፡ ይህም ተቋሙ ካያቸው 800,000 ከሚደርሱ ወፎች መካከል አምስተኛው እንደሆነ ተገልጧል፡፡
የዚህ አይነት ወፎች የራሳቸው መለያ ቀለም ያላቸው ሲሆን ወንዶቹ ሮዝ ነጠብጣብ ላባ ሲኖራቸው ሴቶቹ ደግሞ ቢጫና ቡናማ ቅልቅል ላባ አላቸው፡፡ አሁን ተገኘ የተባለውም ወፍ በአንዱ ክንፉ የወንድ ቀለም ሲኖረው በሌላ ክንፉ ደግሞ የሴት ቀለም አለው፡፡ በሳይንሳዊ (በዘረመል) መጠሪያው ጂናንድሮሞረፊዝም የሚባል ክስተት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ለCNN ተናግረዋል፡፡
ጂን`- በግሪክ ቋንቋ ለሴት የሚነገር ሲሆን `አንድሮ ደግሞ ወንድ ማለት ነው፡፡ ሞርፍ የሚለው ቃል ስብጥርን የሚያመለክት ነው፡፡ይህ አይነቱ ክስተት በሌሎች እንደ ሸረሪት፣ አሳዎችና በዶሮዎችም ሊከሰት እንደሚችል ተመራማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡
ምንጭ፡ CNN
አስደናቂ ተፈጥሯዊ ብቃት ያላቸው እንስሳት
******************************************
የእንስሳት ዝርያዎችን የበለጠ እያጠናናቸው በሔድን ቁጥር አስደናቂ የሆኑ ተፈጥሯቸውን እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ የእፍኝት ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ እይታ፣ ንቦች ያላቸው ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ብርሀንን የመለየት ችሎታ እና የአማዞን ውሃ ውስጥ እባብ መሰል ዓሳዎች ብርሃን በሌለበት የአማዞን ውሃ የማየት አቅምን መጥቀስ ይቻላል፡፡
አሳ ነባሪ፡ ይህ በውሃ ውስጥ የሚኖር መለስተኛ መጠን ያለው የአሳ ዝርያ ሲሆን አስደናቂ ተፈጥሮ ካላቸው እንስሳት መካከል አንዱ ነው፡፡ በአለማችን ከ40 በላይ የአሳ ነባሪ ዝርያዎች አሉ፡፡ አሳ ነባሪዎች ከእናታቸው ጋር ለረጅም ጊዜ ይቆያሉ፡፡
ምግብ ለማከማቸትና ምግብ ለመፍጨት የሚጠቀሙባቸው ሁለት ሆድ አላቸው፡፡ እስከ 1000 ጫማ ድረስ ጠልቀው መዋኘት የሚችሉ ሲሆን እስከ 50 ዓመት እድሜ መኖር ይችላሉ፡፡ መጠናቸውም ከ3 እስከ 30 ጫማ ድረስ ይረዝማሉ፡፡
ሌላው አሳ ነባሪዎች የሚታወቁበት ባህሪያቸው ለሌሎች ፍጥረታትና ለራሳቸው ዝርዎች ወዳጆች መሆናቸው ነው፡፡ ከመካከላቸው በዕድሜ የገፉትንና የተጎዱትን በመርዳት ይታወቃሉ፡፡
ከሰዎች ያነሰ ቢሆንም ከሌሎች ፍትረታት የተሻለ የማሰብ ችሎታ አላቸው፡፡ በአካልና ጭንቅላት መጠን ንጽጽር ከሰዎች ቀጥሎ አሳ ነባሪዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በሚተኙበት ጊዜ ግማሽ የአእምሯቸው ክፍል ንቁ ይሆናል፡፡ ይህም በእንቅልፍ ጊዜ ሊያጋጥማቸው ከሚችል አደጋ ለመጠበቅና ለመተንፈስ ይረዳቸዋል፡፡
አሳ ነባሪዎች ጥርሳቸውን የሚጠቀሙበት ለመያዝ ብቻ ሲሆን ምንም አይነት ምግብ ሲያገኙ ሳያላምጡ ይውጡታል፡፡
የሌሊት ወፍ፡ ይህች በአጥቢነቷ የምትታዎቀው ብቸኛዋ በራሪ እንስሳ የደም ስርን ማየት የሚያስችል ብቃት አላት፡፡ ወፍራምና ብዙ ደም ያለባቸው የደም ስሮች ሙቀት መለያቸው በመሆኑ ይህንን ሙቀት ከእንስሳት ላይ በቀላሉ መለየት ትችላለች፡፡
በዚህም ምግቧን ማደን ተክናበታለች፡፡ ከእንስሳት ደም ስትመጥ እንስሳው ሳይነቃ ለ30 ደቂቃ ያክል ልትመጥ ትችላለች፡፡ ይህ ሲሆን ግን እንስሳውን ለሞት የሚዳርግ ያክል መጠን ደም አትመገብም፡፡
ምንጭ www.aquaworld.com እና www.onekindplanet.com

በታዳጊው የተሰራው የውሃ ተርባይን
ከአፋር የተገኘው ካሚል አብዱ የወንዝ ግፊትን ተጠቅሞ ያለምንም ነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ሃይል ውሃ የሚያሰራጭ ተርባይን መስራት የቻለ ታዳጊ ነው፡፡ ይህ የፈጠራ ስራው የወንዝ ተፋሰስን በመጠቀም ለተለያዩ የመስኖ ስራዎች ውሃን ለማደራስ የሚያገለግል ከመሆኑም በላይ፤ የእርሻ ልማትን ለማፋጠንም በእጅጉ የሚያግዝ ነው፡፡
ውድ የፔጃችን ተከታታዮች የብዙ ታዳጊዎችን የፈጠራ ተሰጥኦ የሚመለከቱበት ብላቴናት ፕሮግራምን ጨምሮ ሌሎች ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ተኮር መሰናዶዎችን በቀጥታ ለማግኘት ዘወትር ቅዳሜ በ10 በ MOE ቴሌቪዥን ይጠብቁ፤ ከዚያ ባለፈም በተከታዩ የዩትዩብ ቻናላችን ይከታተሉን!!! youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg

EthioTunes
Share your videos with friends, family, and the world
ጭስ እንዴት ይፈጠራል
********************
በሀገራችን በልማድ አንድ ነገር ያለ ምክንያት እንደማይፈጠር ለማመልከት "እሳት በሌለበት ጭስ አይኖርም" ይባላል፡፡ ለመሆኑ ሳይንስ ስለ እሳትና ጭስ ምን ይላል፡፡
በማንኛውም አይነት እንጨት አራት ነገሮችን እናገኛለን፡፡ እነዚህም ውሃ፣ ሊተን የሚችል ተፈጥሯዊ ውህድ፣ ካርቦንና አመድ ናቸው፡፡ አንድ አዲስ የተቆረጠ ዛፍ በአብዛኛው ከግማሽ የሚበልጥ ክብደቱ በውስጡ ባለው ውሃ ምክንያት የመጣ ነው፡፡ ለአመት ለሁለት አመት ተቆርጦ የተቀመጠ እንጨት መጠኑ ይነስ እንጂ በውስጡ ውሃ አለው፡፡
አንድ ዛፍ ከመቆረጡ በፊት በህይወት እያለ በህዋሱ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ትነትን የሚፈጥሩ የሀይድሮጅንና የካርቦን ውህዶች አሉት፡፡ እነዚህ ውህዶች ተቀጣጣይ በመሆናቸው እሳት በሚነካቸው ጊዜ ከእንጨቱ ጭስ ይወጣል፡፡
አንድን ያልደረቀ እንጨት እሳት ውስጥ ስንጥለውና ሙቀቱ 149º ሲደርስ መጨስ ይጀምራል፡፡ ሙቀቱ ከዚህ የሚበልጥ ከሆነ እነዚህ ውህዶች ወደ ነበልባልነት ይለወጣሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ከእንጨቱ ምንም ጭስ አይወጣም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በእንጨቱ ውስት ያለው የሀይድሮጅንና የካርቦን ውህድ ወደ ካርቦን ዳይ ኦክሳይድና ወደ ውሃ ስለሚቀየር ነው፡፡ ሁለቱም ሲነዱ አይታዩም፡፡
ከዛፉ ውስጥ ሊቃጠሉ የማይችሉ ማዕድናት እንደ ካልሺየም፣ ፖታሺየምና ማግኒዥየም ያሉት ደግሙ መጨረሻ ላይ አመድ ሆነው ይቀራሉ፡፡ የምድጃ ክሰል የሚያዘጋጅ አንድ ሰው ምንም ኦክስጅን በሌለበት ከፍተኛ ሙቀት ውስጥ እንጨቱን ሲከተው ከእንጨቱ የሚጨሰው ክፍል ብቻ ይጠፋና ካርቦን ከሌሎች ማዕድናት ጋር ይቀራል፡፡ ለዚህም ነው የወጣለት ክሰል የማይጨሰው፡፡
ምንጭ፡ Howstuffworks

የጠፉ ቋንቋዎችን የመተርጎም ስራ
*****************************
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በአለማችን እስከዛሬ ድረስ ካሉት ቋንቋዎች አብዛኛዎቹ ተናጋሪ የላቸውም፡፡ ከእነዚህ ተናጋሪ ከሌላቸው ቋንቋዎች መካከል ጥቂት የማይባሉት ደግሞ የጠፉ በሚል የተፈረጁ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ስለ ቋንቋዎቹ ሰዋሰው፣ ቃላት እና አጠቃቀም የሚታወቅ ነገር የለም ማለት ነው፡፡
የጠፉ ቋንቋዎች ጉዳይ የቋንቋ ጥናት ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ ያለ እነዚህ ቋንቋዎች ስለ ተናጋሪዎቻቸው ያለው አጠቃላይ መረጃ ሊታወቅ አይችልም፡፡ ያለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቹ የጠፉ ቋንቋዎች በሳይንሳዊ መንገድ ሊጠኑ የሚችሉበት ፍንጭ እንኳን የላቸውም፡፡ ይሁን እንጂ በአንድ CSAIL (Computer Science and Artificial Intelligence Laboratory) በተባለ ቤተ ሙከራ ተመራማሪዎች አንድ የጠፋ ቋንቋን መረዳትና ማንበብ የሚችል ፈጠራን አበልጽገዋል፡፡ እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከሆነ ፈጠራው የጠፋውን ቋንቋ ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ሳይቀር ለማጥናት የሚያስችል ነው፡፡
የተመራማሪዎቹ ቡድን ዋና አላማ አንድን ከጠፋ ብዙ ጊዜ ያስቆጠረን ቋንቋ በሺዎች በሚቆጠሩ ቃላት ለመረዳት ነው፡፡ በምርምሩ በቋንቋ የመጥፋትና የመለወጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ የቃላት፣ የሆሄያትና የድምጾች ለውጥና መወራረስ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ተመራማሪዎቹ ያበለጸጉት ቋንቋን የመረዳት ስልት decipherment algorithm ብዙ አማራጭ ቃላትንና ድምጾችን ወይም ስልተ ንባቦችን የሚጠቀም ነው፡፡ ቋንቋን የመረዳት ሂደቱ የጠፋውን ቋንቋ በጣም መሰረታዊ የሚባሉ የቋንቋ ውቅሮችን እና ለውጦችን በሌላ ቋንቋ ይገልጻል፡፡ ውጤቱንም በተጠኝው ቋንቋና በተነጻጻሪ ቋንቋ ያሰፍራል፡፡
በዚህ ጥናት አንድ ኡጋሪቲክ (Ugaritic) ቋንቋ የተጠና ሲሆን ቋንቋው ከጥንታውያን የእብራውያንና የግሪክ ቋንቋዎች ጋር ዝምድና እንዳለው ማዎቅ ችለዋል፡፡ የተሰራው ቀመር በቋንቋዎች መካከል ያለውን ዝምድና በማጥናት የጠፉ ቋንቋዎችን መሰረታዊ ጭብጥና ስነ-ልሳናዊ ይዘት ለመረዳት ያስችላል፡፡ የጥናት ስልቱ ባልጠፉ ቋንቋዎች ላይ ተሞክሮ የቋንቋውን ቤተሰብ ሳይቀር መለየት አስችሏል፡፡
የጥናት ቡድኑ ለወደፊት የጠፋውን ቋንቋ ጽሁፍ ከሚታወቅ ጋር በማዛመድ ብቻ እየተሰራ ያላውን ጥናት በማሳደግ ምንም እንኳን የቋንቋው ድምጸትና አነባበብ ቢጠፋም የአንድን ቃል ስነ-ፍቻዊ መንገድ በመከተል ቋንቋውን ለማጥናት አቅደዋል፡፡
ምንጭ፡ Massachusetts Institute of Technology እና www.technology.org

የተማሪዎችን የሂሳብ ክህሎት ለማሳደግ የሚረዱ ጠቃሚ መተግበሪያዎች
አሁን ባለንበት የዲጂታል ዓለም በእያንዳንዱ ጉዳዮች ላይ ተመስርተው የሚሰሩ መተግበሪያዎች ለቁጥር አዳጋች እየሆኑ መተዋል፡፡ በተለይም በትምህርት፣ በጤና እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተመስርተው የሚሰሩት የተለያዩ መተግበሪያዎች ብዙ ሰዎችን ውጤታማ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች መሰል የስልክ መተግበሪያዎችን በትምህርታቸው ላይ ቢጠቀሙ የሂሳብ ክህሎታቸውን በቀላሉ ለማሳደግ እና እራሳቸውንም ለማብቃት በእጅጉ ሊረዳቸው ይችላል፡፡
Photomath
ይህ መተግበሪያ በአንድሮይድ ስማርትፎን እና በiOS ዲቫይዞች ላይ በቀላሉ የሚጫን አፕሊኬሽን ሲሆን በዓለማችን ላይ ብዙ ተጠቃሚዎችም የሚተገብሩት ነው፡፡ አፕሊኬሽኑ በተለይም የስልክ ካሜራን በመጠቀም ማንኛውንም የሂሳብ ጥያቄዎች ከወረቀት ላይ በማንሳት፤ መልሶቹን ደረጃ በደረጃ ወይም (step-by-step) የሚያሳይ በመሆኑ ለተማሪዎች የሂሳብ ክህሎት መዳበር ትልቅ እገዛ ያደርጋል፡፡
MalMath
ይህ መተግበሪያ እንደ Photomath ሁሉ በዓለማችን ላይ ብዙ ተጠቃሚ ያለው እና በአጠቃቀም ቅለቱም ብዙዎች የሚመርጡት የአፕሊኬሽን አይነት ሲሆን የ Integral፣ Logarithm፣ Algebra እና ሌሎች የሂሳብ መሰረታዊ አሰራሮችን ባማረና በቀለለ መልኩ የሚያቀርብ ነው፡፡
Mathway
Mathway እንዲሁ ብዙ ገጽታዎች የተጨመሩለት እና ማንኛውንም የሂሳብ ጥያቄዎች በካሜራ በማንሳት የመልሱን አሰራር በቀላሉ ለማሳየት የሚያስችል መተግበሪያ ሲሆን በዓለም ላይ ካሉ የተለያዩ የሂሳብ ባለሙያዎች ጋር በማገናኘት ስልጠናዎችን እና ትምህረቶችን በቀላሉ ለማቅረብ በመቻሉ የተለየ ያደርገዋል፡፡
WolframAlpha
ይህ መተግበሪያ እንደሌሎቹ ሁሉ ተማሪዎችን በሂሳብ ትምህርት ለማገዝ የቀረበ ሲሆን በተለያዩ አሰራሮች ዙሪያ የጠለቀ ትንታኔን እና ምሳሌዎችንም አካቶ የያዘ ነው፡፡ WolframAlpha በተለይም የarithmetic እና calculus አሰራሮችን ባማረና ሁሉም ሰው ሊረዳው በሚችለው መልኩ የሚያቀርብ መተግበሪያ ሲሆን አንድሮይድ ስልክን ጨምሮ በiOS ዲቫይዞች ላይም በቀላሉ የሚጫን ነው፡፡
መረጃው የ Tech Viral ነው