የምንጊዜውም አጭሩ የጊዜ ርዝማኔ
====================
አንድን ድርጊት አከናውነን ለመፈጸም ርዝማኔው ወይም ቆይታው ይለያይ እንጂ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ታዲያ አንድን ድርጊት ሰርተን የጨረስንበትን ቆይታ የተለያዩ አሀዶችን በመጠቀም እንለካለን፡፡ ይኸውም በአመታት፣ በወራት፣ በሳምንታት፣ ወይም ደግሞ በቀናት፣ በሰዓታት፣ በደቂቃዎችና በሴኮንዶች ሊሆን ይችላል፡፡
ከጊዜ መለኪያ ምድቦች አንጻር ከሴኮንድ በታች ያሉ ለመደበኛ ጊዜ መለኪያ የማንጠቀማቸው ነገር ግን ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ጥቃቅን ምድቦች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክልም ዴሲ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ አስረኛ)፣ ሴንቲ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ መቶኛ)፣ ሚሊ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሺኛ)፣ ማይክሮ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሚሊዮንኛ)፣ ናኖ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ቢሊዮንኛ)፣ ፒኮ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ትሪሊዮንኛ)፣ ፌምቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ኳድሪሊዮንኛ)፣ አቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ኳንቲሊዮንኛ)፣ ዜፕቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሲክስቲሊዮንኛ)፣ ዮክቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሴፕቲሊዮንኛ) እና ፐላንክ (Planck time) የሚታወቁት ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ምድቦች በጊዜ ምድብነት ይታወቁ እንጂ በቅርብ በወጣ ዘገባ ተመራማሪዎች የብርሃን ቅንጣቶች የሃይድሮጅን ሞሎኪዩልን ለመቋረጥ የሚወስድባቸውን የጊዜ ርዝማኔ መለካት ችለዋል፡፡ ይህም ልኬት እስካሁን ከተመዘገቡት ርዝማኔዎች የመጨረሻ ትንሹ የጊዜ ርዝማኔ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የብርሃን ቅንጣቶቹ የሃይድሮጅን ሞሎኪዩልን ለማቋረጥ የወሰደባቸው ጊዜም 247 ዜፕቶ ሴኮንድ (zeptoseconds) ሆኗል፡፡
ከዚህ በፊት በ1999 የኖቤል ሽልማት ማግኘት የቻለ በፌማቶ ሴኮንድ የተለካ የኬሚካል ቦንድ ለመሰራትና ለመከፈል (break and form) የሚወስደው ጊዜ ታውቆ ነበር፡፡
የዚህ ግኝት ተጨማሪ ማብራሪያዎች በጥቅምት 16 የሳይንስ ጆርናል ላይ ታትሟል፡፡
ምንጭ Science alert

መልካም ዜና
=======
ውድ ተከታታዮቻችን “BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በኢንስቲትዩታችን ዩትዩብ ቻናል ላይ ያዘጋጀነውን ተከታታይ ስልጠና እየተከታተላችሁ ነው ?
ስልጠናውን ከተከታተላችሁ በኋላ በሰባተኛው (7ኛ) ክፍል ዲስክርፕሽን ላይ የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን የተዘጋጀውን ጥያቄ በወረቀት ላይ (A4 ወይም A3) በመስራት በኢሜይል አድራሻችን (stic.ethiopia@gmail.com) የምታደርሱን ይሆናል፡፡ ታድያ እስካሁን ጥያቄዎቹን ሞልታችሁ ለላካችሁልን ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀቱ የተዘጋጀላችሁ ሲሆን በቅርቡም ከእጃችሁ እንደምናደርስ መግለፅ እንወዳለን፡፡
ታድያ አሁንም ጊዜው አላለቀምና ስልጠናውን ከተከታተላችሁ በኋላ በስልጠናው ላይ የተዘጋጀውን ጥያቄ መልስ እስከ ዓርብ ጥቅምት 13 2013 ዓ/ም ድረስ ብቻ በመላክ ሰርተፊኬት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ያሎት ጊዜ አጭር በመሆኑ ተከታታይ ስልጠናውን በሚገባ ተከታትለው የተዘጋጀውን ጥያቄ ሰርተው ይላኩልን ፡፡
ስለተከታተሉን እናመሰግናለን፡፡

እንጀራን ለ24 ቀናት ሳይሻግት የሚያቆየው ምርምር ማብራርያ ተሰሠጠበት
===================
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር እዮቤል ሙሉጌታ በትብብር የተሰራውንና እንጀራ ሳይሻግት እስከ 24 ቀናት ድረስ ማቆየት በሚችለው የምርምር ውጤት ዙርያ ዛሬ ጠዋት በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተገኝተው ገለፃ አቅርበዋል፡፡
ዶ/ር እዮቤል በገለፃቸው በአሁኑ ወቅት አንጀራ ከሦስት ወይም አራት ቀናት በኋላ እንደሚበላሽና ለዚህም በዋነኝነት ፔኔሲሊየም ጨምሮ ሶስት የፈንገስ አይነቶች ዋነኛ ምክንያት መሆናቸውን ጠቅሰው እንጀራውን ሳይበላሽ ለማቆየት በሚደረገው የማሞቅ እና ሌሎች ተግባራት ወቅት የሚደርሰውን የኃይል ብክነትንና በተለይ ስራውን በዋናነት በሚያከናውኑት እናቶቻችን ላይ የሚያስከትለውን ቀላል የማይባል የስራ ጫና ገልፀዋል፡፡ ሶስት አራተኛው ኢትዮጵያውያን የእንጀራ ተመጋቢ መሆናችንን ያወሱት ዶ/ር እዩቤል የዚህ ምርምር ግኝት ወደ ተግባር መለወጥ በማህበራዊ፣ ምጣኔ ሀብት፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ኃይል ቁጠባ ብሎም የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አውንታዊ ሚናን እንደሚጫወትም አብራርተዋል፡፡
ምርምሩ ሲልቨር እና ዚንክ ኦክሳይድን በናኖ ፓርቲክል ደረጃ በመጠቀም የሚሰራ ሲሆን ውህዱን በእንጀራ ማስቀመጫው ላይ በማኖር ብቻ ነው ለዚህ ያህል ጊዜ እንዲቆይ ማድረግ የተቻለው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በምርምሩ ላይ የተገኙ ዝርዝር የቤተ ሙከራ ውጤቶችን ለታዳሚያኑ አብራርተዋል፡፡
በገለፃው ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢንስቲትዩቱ ተመራማሪዎችም በቀረበው ምርምር ዙርያ ጥያቄ እና አስተያየታቸውን ሰንዝረዋል፡፡ በመድረኩ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል የፓርቲክል መጠኑ ሁኔታ፣ የጤና ተፅዕኖው፣ በዋጋ ደረጃ ያለው ተደራሽነት፣ ከሌሎች ምርምሮች ጋራ እንዴት በተመጋጋቢነት መሄድ እንደሚችል እና በጥናቱ ላይ በዋለው የጤፍ አይነት ላይ ያውጠነጠኑት ይገኙበታል፡፡
ጥያቄዎቹ ተገቢ መሆናቸውን በምላሻቸው ያነሱት ዶ/ር እዮቤል ምርምሩ በሁለተኛ ዲግሪ ማሟያነት የቀረበና ቀሪ ስራዎች መኖራቸው ከግምት ይገባ ዘንድ አሳስበዋል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይም ዝርዝር ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከሌሎች የፈጠራ ባለሙያና ምርምሮች ጋራም ወደፊት በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ምርምሩ ወደ ህብረተሰቡ ከመድረሱ በፊት በጤና ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተፅዕንዖ፣ የፓርቲከሎቹ መጠን ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮችም በቂ ምርምር እንደሚደረግባቸው ዶ/ር እዮቤል አስረድተዋል፡፡
ከዚህ በፊት እንጀራን ሳይሻግት ለ12 ቀናት ያህል ለማቆየት የሚያስችል ምርምር የተሰራ ቢሆንም የእንጀራውን ጣዕም እንዲቀይር የያደረገ ነበር፡፡ በአንፃሩ አዲሱ መርምር የዚህ አይነት ለውጥ የማያስከትል መሆኑን ዶ/ር እዮቤል ገልፀዋል፡፡
ምርምሩ በቀጣይ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ሲሆን እኛም በምርምሩ ዙርያ ዝርዝር ዘገባን ይዘንልዎ የምንመጣ ይሆናል፡፡

የኮቪድ-19 ገጸ-በረከቶች
=============
በኮቪድ 19 ምክንያት የተጣሉ ገደቦችና የኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዝ በአለማችን ጉዳት ብቻ ሳይሆን ጥቅምንም ይዘው መጥተዋል፡፡ በተለይ ከአየር ንብረት ብክለት አንጻር የታየው ለውጥ አለማችን ያላትን የኃይል አጠቃቀምና ልቀት ልምድ እንደገና መከለስ እንዳለባት በሰፊው ያመላከተ ነው፡፡ ናሽናል ጆግራፊክ መጽሔት በያዝነው ወር እትሙ ወረርሽኙ ከአየር ንብረት አንጻር ያበረከተውን አስተዋጽኦ በሶስት ከፍሎ አቅርቦታል፡፡ እኛም በዚህ መልክ በአጭሩ አዘጋጅተንላችኋል፡፡
1ኛ. በካርበን ልቀት በአንድ አመት ብቻ ትልቅ የሚባል ቅናሽ ኮቪድ 19 አምጥቷል፡፡ መጽሔቱ ይህን ለካርበን ልቀት መቆም መባቻ ይሆናል የሚል ሀሳብ አስፍሯል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የካርቦን ልቀት አስከ 2024 የተጠበቀ ቢሆንም ኮቪድ 19 ሁኔታውን ሳያፋጥነው አልቀረም፡፡ በወረርሽኙ ምክንያት የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብና የግዙፋን ፋብሪካዎች ስራ መቀነስ የነበረውን የካርበን ልቀት በሚገርም ሁኔታ ቀንሶታል፡፡ ይህ ግን ለጊዜው መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ የአለም መንግስታት ከዚህ በመነሳት ለካርበን ልቀት መቀነስ ምክንያት የነበሩ ነገሮችን መጣኔ ሐብት እና ማህበራዊ እንቅስቃሴውን በማይጎዳ መልኩ ስራቸውን ከብክለት ነጻ የሚደርጉበትን መንገድ በአፋጣኝ መፈለግ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ለተከታታይ አመታት ያክል የካርቦን ጥቅል ልቀቱ ዜሮ እስኪሆን ድረስ መሰራት አለበት፡፡
2ኛ. ኮቪድ 19 የተናጥል እርምጃ የአለም ሙቀትን ለመቀነስ በቂ እንደማይሆን አስተምሯል፡፡ ኮቪድ 19 በኃይል አጠቃቀም ዙሪያ የሚሮረውን ተጽዕኖ በሚያመለክት ትንተናው በአሁኑ ወቅት አማራጭ ኃይል መፈለግ፣ የኃይል አጠቃቀምን ማሻሻልና የትራንስፖርት ኃይል አቅርቦት አማራጭ መጠቀም ተገቢ እንደሆነ አመላክቷል፡፡ በያዝነው አመት የነዳጅ ዘይት ፍላጎት በአየርና ሌሎች ትራንስፖርት እንቅስቃሴ መቆም ምክንያት 60 በመቶ የሚሆነው ፍላጎት ቀንሷል፡፡ ይህም ከካርበን ልቀት መቀነስ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ በ2040 የነፋስና የፀሐይ ኃይል አማራጮች ፍላጎት ከአጠቃላይ የድፍድፍ ነዳጅ ፍላጎት 34 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናሉ ተብሎ ተገምቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት እየመጡ ያሉ ቴክኖሎጂዎች እና በትኩረት የሚሰሩ ፖሊሲዎች የአለም አቀፍ የኃይል አማራጭ ሽግግሩን ያፋጥኑታል፡፡ በኮቪድ ምክንያት የታየውን የካርበን ልቀት መቀነስ ካሉን የፖሊሲ ግቦች ጋር ማስተሳሰር የመነሻ ትግባር ሊሆን ይገባል፡፡
3ኛ. የዛሬ የምጣኔ-ሐብት ማገገሚያ እቅዶች የወደፊት የአየር ንብረት ሁኔታን ይወስናሉ፡፡ ከኃይል ጋር የተያያዘ ኢንቨስትመንት በ2020 ያድጋል ተብሎ የታለመ ቢሆንም በኮቪድ ምክንት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የነዳጅ ዘይት ዋጋ እና የገበያ ተፈላጊነት በዚያው ልክ ወርዷል፡፡ መንግስታት በአሁኑ ወቀት የነበረውን የምጣኔ-ሐብት መቀዛቀዝ ሊያነቃቁ የሚችሉ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ላይ ናቸው፡፡ በመሆኑም አለማችን አሁን ካለው የካርበን ልቀት በላይ ላታስተናግድ ስለምትችል የሚሰሩት የምጣኔ ሐብት ማነቃቂያ ተግባራት ከተፈጥሮ ጋር የተስማሙ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
ምንጭ National Geographic

በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የተዘጋጀው አዲስ የፖሊሲ ጥናት
=====================
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ጥናት ዳይሬክቶሬት “Data Privacy Policy for Ethiopia and the need for Compliance with International Standards” በሚል ርዕስ የፖሊሲ ጥናት አውጥቷል፡፡ ጥናቱ በኢትዮጵያ የተደራጀና ሁሉን አለም አቀፍ ስታንዳርዶችን ያሟላ የመረጃ/ጥሬ ሀቅ ጥበቃ ፖሊሲ አልያም ሕግ መኖር አስፈላጊነት ላይ የተለያዩ አመክንዮዎችን በመንተራስ ምክረ ሀሳብ የሚያቀርብ ነው፡፡
ያደጉት ሀገራት የዛሬ 40 እና 50 ዓመታት ገደማ ግለሰባዊ መረጃን የሚጠብቁ ሕጎችን ሲተገብሩ መኖራቸውን ያወሳው ጥናቱ በአንፃሩ ሀገራችን ላይ አሁንም ድረስ ይህን ሁኔታ ባልተደራጁና በቂ ባልሆኑ ሕጎች ለመቆጣጠር እየዳከርን መሆኑን ይጠቁማል፡፡
የፖሊሲ ጥናቱ በኢትዮጵያ የመረጃ ጥበቃ ፖሊሲ አልያም ሕግ መኖር አስፈላጊነት ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በሌሎች ሀገራት ደረጃ ካለው የፖሊሲ እና ህግጋት ጋራ አለመጣጠም በተለይም ሀገራችንን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ወይም ኢ-ኮሜርስ ስርዓቱን በሚፈለገው ልክ እንዳታሳድግ እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ብሎም ሀገራት ከእኛ ጋራ እንዲሰሩ የማያስችል ሁኔታ እንደሚፈጥር የአውሮፓ ህብረት እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሕግጋትን በተግባራዊ ምሳሌነት አስደግፎ አትቷል፡፡
በሌላ መልኩ ኢትዮጵያ በቅርብ መረጃ እና ግንኙነት ቴክሎጂዎችን (ICT) ጨምሮ ስድስት አባይት ዘርፎች ዋና የትኩረት ማዕከል አድርጎ የያዘ አዲስ የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡ ይህ መሪ ዕቅድ ቴክኖሎጂን ማዕከል ያደረገና ለስኬቱም ያለው ወሳኝነት የማያጠራጥር መሆኑ ዘርፉን የዲጂታል ጥሬ ሀቅን (Data) በሚቆጣጠሩ ሕግጋቶች ለመደገፍ እንደሚገደድ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም ከሚከፍተው አዲስ የዕድል በር እና አሁን ያለንበት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሁኔታ ያለ ሕግ እና ፖሊሲ ብዙም የማያራምድ መሆኑ በረቂቁ ላይ ተቀምጧል፡፡
ጥናቱ ግለሰባዊ መረጃን ከሚጠብቁ ፖሊሲ እና ሕግጋት አስፈላጊነት ባሻገርም በሀገራችን በአሁኑ ሰዓት ያለውን የግለሰባዊ መረጃ አጠባበቅ ሁኔታ እንዲሁም የICT ፖሊሲ እና ሌሎች ከጉዳዩ ጋራ ግንኙነት ያላቸው ወሳኝ ሕግጋቶችንም የቃኘ ነው፡፡
ሙሉ ጥናቱን ቀጥሎ የተቀመጠውን pdf ፋይል በመክፈት ያገኙታል፡፡

ሀሰተኛ መረጃ እና የአዕምሮ ጫና
================
በአለማችን የማህበራዊ ሚዲያ እየተስፋፋ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የሀሰተኛ መረጃ መጠንና የዝውውር ፍጥነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል፡፡ ሀሰተኛ መረጃ መሰራጨት ከመጀመሩ በፊት አዘጋጆቹ በቅድሚያ ሰዎች መስማት የሚፈልጉትን ወቅታዊ እና ትኩረት ሳቢ የሆነውን ጉዳይ ይለያሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው በጣም ቀላል ነው፤ ማህበራዊ ሚዲያዎች ከመሰረታቸው መረጃን ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላ ጫፍ በፍጥነት በማዘዋወር የታዎቁ በመሆናቸው በደቂቃዎች ውስጥ ሰፊ ተመልካች ያገኛል፡፡ በይዘት ደረጃ ይዘቱ ምንም ዓይነት ይሁን ወቅታዊና ሰዎች መስማት የሚፈልጉት ከሆነ ሀሰተኛው መረጃ ተመርቶ ይቀርባል፡፡
የደቡብ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የኮምፒውተር ተመራማሪዎች በሰሩት ትንተና በ2016 የአሜሪካ ምርጫ ወቅት 20 በመቶ የሚሆኑ የትዊተር መረጃዎች ሀሰተኛ ነበሩ፡፡
በኢቫንስቶን ሰሜን ምዕራብ ዩኒቨርሲቲ የስነ-አዕምሮ እድገት ተመራማሪ የሆነው ዴቪድ ራፕ ሰዎች በብዛት ወቅታዊ የፖለቲካ አቋማቸውን የሚደግፍ ማንኛውንም መረጃ ይቀበላሉ ሲል ልዩ ልዩ ምርምሮችን ዋቢ አድርጎ ይናገራል፡፡ ተመራማሪው በተጨማሪም አንድ ጽሁፍ ሀሰት እንደሆነ እያወቅን እንኳን እውነት እንዲሆን ካለን ፍላጎት የተነሳ እንቀበለዋለን ይላል፡፡ የዚህ አይነቱ የተሳሳተ መረጃ በልዩ ልዩ ውሳኔዎቻችን ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳረፉ አይቀርም፡፡
ብዛት ያላቸው ሀሰተኛ መረጃዎችን ባነበብን ቁጥር አዕምሯችን በዚሁ የተሞላ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ የተለያዩ ሙከራዎችን ያደረጉት የተመራማሪዎች ቡድን አንድን ሀሰተኛ መረጃ በተደጋጋሚ የምንሰማው ከሆነ ለአዕምሯችን እውነት እየሆነ ይመጣል፡፡ ለምሳሌ "ዛፎች ከመኪና ይልቅ ለአየር ብክለት መንስኤ ናቸው" የሚል ሀሰተኛ መረጃን በተደጋጋሚ ብንሰማውና እኛ የምናውቃቸው እና የምንደግፋቸው ጥቂት ሰዎች ሀሳቡን ቢቀበሉት ሀሳቡን መርህ አድርገን ተፈጥሮን ከዛፎች እንታደግ ማለታችን የማይቀር ነው፡፡ ይህ ምሳሌ የሀሰተኛ መረጃን አደገኝነትና በአዕምሯችን ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ በቀላሉ የሚያሳይ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪም ልቦለዶቸ ላይ የምናነባቸው መረጃዎችን እንደ እውነተኛ መረጃዎች በመውሰድ አቋም ልንይዝባቸው እንችላለን፡፡ ይህም ከነባራዊው እውነታ ይልቅ ለማስታዎስ ከልቦለድ ጽሁፍ ያገኘነው መረጃ ለአእምሯችን ስለሚቀል ነው፡፡
ምንጭ Science news magazine

አስደናቂው የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ
*******************************
አንድ ብርጭቆ ያልተቀመመ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ መጠጣት በጣም አስደናቂ የሆነ የጤና ጥቅም አለው፡፡ እንዲሁም ሰውነታችን የሚፈልጋቸውን ጠቃሚ ንጥረ ምግቦች የያዘ ነው፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የደም ግፊትን ይቀንሳል፣ አጥንትን ያጠነክራል፣ የኮሊስትሮል መጠንን ይቀንሳል፣ ክብደት ለመቀነስ ያግዛል እንዲሁም ትኩሳትንና ልዩ ልዩ የጤና መታወክን በማጥፋት ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡ ጭማቂው በተጨማሪም ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት፣ የሰውነት ሐይልን ለመጨመር፣ የኩላሊትን ጤና ለመጠበቅ፣ቆዳን ለመንከባከብ፣ ስርዓተ እንሽርስሪትን (የምግብ መፈጨትን) ለማስተካከልና የበሽታ መከላከል አቅምን ለማሳደግ ይረዳል፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ምንድን ነው?
ይህ ጭማቂ በጣእሙ ከሚታወቀው እና ለገበታ ስኳር ማምረቻ ዋና ግባት ከሆነው የሸንኮራ አገዳ ተክል የሚሰራ ነው፡፡ የዚህ ተክል በሳይንሳዊ መጠሪያው ሳቻረም ኦፊሲናረም (Saccharum officinarum) በመባል ይታወቃል፡፡ ሳቻረም የሚለው የጥፍጥናውን መጠን የሚያሳይ ነው፡፡ ጭማቂው በሸንኮራ አገዳ ምርታቸው በሚታወቁት እንደ ብራዚል፣ ህንድ እና ታይላንድ ባሉ ሀገራት የታወቀ ነው፡፡ በአብዛኛው ጭማቂው የብረት መጭመቂያ በመጠቀም ከሸንኮራ አገዳ በፍጥነት የሚዘጋጅ ነው፡፡ በብዛት ከበረዶና ከሎሚ ካር ተቀላቅሎ በቀዝቃዛ መጠጥነት የሚቀርብ ሲሆን አንኳር ጨውና ዝንጅብልም እንደመቀመሚያነት ሊያገለግሉ ይችላሉ፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለሌሎች ምርቶችም ዋና ግብአት በመሆን ያገለግላል፡፡ ለምሳሌ ያክልም ሞላሰስ፣ ኢታኖልና ባዮፊውል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የምግብ ይዘት
አንድ ብርጭቆ ያልተቀመመ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ መጠጣት በጣም አስደናቂ የሆነ የጤና ጥቅም አለው፡፡ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ከፍተኛ መጠን ያለው ፖታሺየም፣ ካልሺየም፣ ማግኒዥየም፣ ብረት፣ ማንጋኔዝ፣ የተለያዩ አሚኖ አሲዶች፣ ዚንክ፣ ቲያሚን እና ሪቦፍላቢን የያዘ ነው፡፡ ከ224 ግራም ጭማቂ 180 ካሎሪ እና 30 ግራም ስኳር ማግኘት እንችላለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ለሰውነታችን ጤንነት በጣም አስፈላጊ የሆኑ ውህዶችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ጥቅሞች
ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ዋና ዋና ጥቅሞች መካከል የሚከተሉትን ማየት ይቻላል፡፡
የሰውነት ሀይልን ከፍ ደርጋል፡ በፋብሪካዎች ተቀምመው ከሚመጡ ምግብና መጠጦች በተለየ መልኩ ለሰውነታችን ከፍተኛ ሀይል የሚሰጥ የተመጣጠነ ስኳር ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ማግኘት እንችላለን፡፡
የቆዳችንን ጤንነት ይጠብቃል፡ ከሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ይዘቶች አንዱ አልፋ ሀይድሮ ኦክሳይድ አሲዶች መካከል የሆነው ግላይኮሊክ አሲድ ነው፡፡ ይህ አሲድ የቆዳ ላይ ሽፍታንና ቁስለትን በማስወገድ ጥራት ያለው ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ እንዲሁም አዘውትረን የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የምንጠጣ ከሆነ በእድሜ ምክንያት የሚመጣን የቆዳ መሸብሸብ ያስወግዳል፡፡
ምቹ ለሆነ የእርግዝና ወቅት፡ በእርግዝና ወቅት የሚወሰድ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ የምግብ መፈጨትን በአግባቡ እንዲከናዎን በማድረግ ጥዋት ጥዋት የሚስተዋልን የሆድ ቁርጠት ያስወግዳል፡፡ እንዲሁም በእርግዝና ወቅት የሐይል እጥረት እንዳያጋጥም ያደርጋል፡፡ ተፈጥሯዊ የሆነ የበሽታ መከላከል አቅምን ከፍ ያደርጋል፡፡
መጥፎ የአፍ ጠረንን ያስወግዳል፡ የጥርስ መበስበስን ለማስወገድ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ፍቱን መድሀኒት ነው፡፡ ሸንኮራ በተፈጥሮ ካልሺየምና ፎስፈረስ የተባሉ ማዕድናት ያለው በመሆኑ የጥርስ መበስበስ ችግርን በማስወገድ ለጥርሳችን ጥንካሬን ይሰጣል፡፡ በጭማቂው ውስጥ ያለው ከፍተኛ መጠን ማዕድን በእጥረት ምክንያት የሚመጣን የአፍ ጠረን ያስወግዳል፡፡
አጥንትን ያጠነክራል፡ ጭማቂው በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ካልሺየም፣ ብረት፣ ፖታሺየም፣ ማግኒዢየምና የማንጋኔዝ መጠንን በማመጣጠን አጥንታችንን ያጠነክራል፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ከመጠን በላይ የምንጠጣ ከሆነ ተጓዳኝ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የራስ ምታት፣ የሆድ ህመም፣ ትውኪያና የእንቅልፍ ማጣት ሊያስከትል ይችላል፡፡ ይህ እንዳይሆን በቀን ውስጥ አንድ ብርችጭቆ ብቻ መጠቀም ተገቢ ነው፡፡
ምንጭ፡ www.organicfacts www.indianrecips

አዲስ የሰውነት አካል ተገኘ
=============== በጉሮሮዋችን የላይኛው ክፍል ውስጥ የሳሊቫሪ እጢ ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡ ከዚህ ቀደም ኔይዞፋሪንክስ ተብሎ በሚጠራው ከአፍንጫችን ጀርባ ያለው ክፍል በጣም ጥቃቅን እና ተበታትነው የተቀመጡ ሳሊቫሪ እጢዎች ብቻ እንዳሉበት ይታሰብ ነበር፡፡ ሆኖም አዲስ የተገኘው እጢ በአማካኝ የ3.9 ሴ.ሜ ርዝማኔ ያለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እጢው ቶረስ ተባሪየስ በተባለው የአጥንቶች ማገናኛ (Cartilage) ውስጥ በመገኘቱ ምክንያትም የተባሪየስ ሳሊቫሪ እጢ የሚል ስያሜ ባገኙት ተመራማሪዎች ተሰጥቶታል፡፡ እጢው ምናልባትም ከአፍንጫና አፍ ጀርባ የሚገኘውን የጉሮሮዋችንን የላይኛውን ክፍል የሚያለሰልሱ እና የሚያረጥቡ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተመራማሪዎቹ የራዲዮቴራፒ እና ኦንኮሎጂ ጆርናል ላይ ባወጡት ጥናታዊ ፅሁፍ አስታውቀዋል፡፡
ታድያ ግኝቱ ድንገተኛ ግኝት ነበረ፡፡ በኔዘርላንድ የካንሰር ኢንስቲትዩት የሚገኙ ተመራማሪዎች የፕሮስቴት ካንሰርን ለማጥናት በማሰብ ሲቲ ስካን እና PSMA PET-CT ተብለው የሚታወቁትን የፖዚትሮን ኢሚሽን ቲሞግሮፊ (PET) ስካኖች በመጠቀም እየሰሩ ነበር፡፡ በPSMA PET-CT ስካን በሚደረግበት ጊዜ ሀኪሞች የራዲዮአክቲቭ መከታተያን ወደ ታማሚው ይከታሉ፡፡ ይህ መከታተያ በፕሮስቴት ካንሰር ህዋሶች ውስጥ ከፍ ብለው በሚገኙት የPSMA ፕሮቲኖች ላይ በጥሩ ሁኔታ መጣበቅ ይችላል፡፡ የህክምና ሙከራዎች እንዳሳዩት ከሆነ በPSMA PET-CT የሚደረግ ስካን ከተለምዶው ምስል የመውሰድ ስልት አንፃር የፕሮስቴትካንሰርንበተሻለ የማግኘት ብቃት አለው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በPSMA PET-CT ስካን ማድረግ PSMA ከፍ ብሎ የሚገኝበትን የሳሊቫሪ እጢ ሕብረ ሕዋስን ለይቶ በማግኘት ረገድም ጥሩ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
እስከ አሁን ድረስ ሶስት ትላልቅ የሳሊቫሪ እጢዎች በሰው ልጆች ውስጥ እንዳሉ ይታወቁ ነበሩ፤ ከምላስ በታች፣ ከመንገጭላ በታች እና ከመንገጭላ ጀርባ፡፡ ከነዚህ ባሻገር ግን በሺዎች የሚቆጠሩ እጅግ ጥቃቅን የሳሊቫሪ እጢዎች በአፍ እና ጉሮሮ የውስጥ ቆዳ (Mucosal) ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ ተበትነው ይገኛሉ፡፡
ግኝታቸውን ለማረጋገጥ የጥናት ቡድኑ አባላት የ100 ታማሚዎችን የውስጥ ምስል የወሰዱ ሲሆን በውጤቱም ሁሉም አዲስ የታወቀው እጢ እንዳላቸው ለማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በተጨማሪም የኔይዞፋሪንክስ አካባቢን ከተለገሰ የሙት ሰው አካል ላይ ለይተው በማውጣት ምልከታ ካደረጉበት በኋላ አዲስ የተገኘው ክፍል ፈሳሽን ወደ ኔይዞፋሪንክስ በሚያደርሱ የሚኮሳል እጢ ሕብረ ሕዋሳት እና ማስተላለፊያዎች የተሞላ መሆኑን ማወቅ ችለዋል፡፡
ታድያ አዲሱ ግኝት ለካንሰር ህክምና በጎ አስተዋፅዖ ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል፡፡ ካንሰርን ለማከም በጭንቅላታች እና አንገታችን ላይ ጨረርን የሚጠቀሙ ሀኪሞች የሳሊቫሪ እጢዎችን በጨረሩ ላለመንካት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ለዚህም የነዚህ አካላት በጨረር መጎዳት የህይወት ዘይቤያችን ላይ መስተጓጎልን ሊፈጥር መቻሉ በምክንያትነት ይቀመጣል፡፡ ለምሳሌ ለመመገብ፣ ለመዋጥ እና ለማውራት ልንቸገር እንችላለን፡፡ ሆኖም ከዚህ በፊት ማንም ስለ ተባሪየስ ሳሊቫሪ እጢዎች በቦታው መኖር ስለማያውቅ እነርሱን ከጨረሩ ለመጠበቅ ጥረት የሚያደርግ አልነበረም፡፡
ተመራማሪዎቹ በግሮኒንገን ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናቸውን የተከታተሉ 700 የካንሰር ታማሚዎችን መዝገብ በመመልከት አዲስ በተገኘው እጢ አካበቢ ላይ የሚያርፈው ጨረር በበዛ ቁጥር ከህክምናው የሚገኘው የጎንዮሽ ጉዳትም ማሻቀቡን ለመረዳት ችለዋል፡፡ አዲሱ ግኝትም ይህን በማሻሻል ታማሚዎች ከካንሰር ህክምናቸው በኋላ የሚደርስባቸው የጎንዮሽ ጉዳት ያነሰ እንዲሆን ያስችላል ሲሉ የጥናት ቡድኑ አባል ያስረዳሉ፡፡
ምንጭ፡ Live Science

ሌሎች የፕላስቲክ አማራጮች ተፈጥሮን ለመታደግ
-------------------------------
በዓለማችን ያሉ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አንድ ጊዜ ጥቅም ላይ ውለው የሚጣሉ ፕላስቲኮችን ለማስወገድ እና ተያይዘው የሚመጡ የአካባቢ ብክለት ችግሮችን ለማስቀረት የረዥም ጊዜ እቅዶችን ቀርፀው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል፡፡ ኒውላይት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ይህን መርህ በሚገባ ከሚከተሉ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን ከሰሞኑ ይፋ ያደረገው ፕላስቲከ መሰል የባዮዲግሬደብል ቁስ ደግሞ ከብዙዎች ተቀባይነት ያስገኘለት ነው፡፡
በካሊፎርኒያ መቀመጫወን ያደረገው ኒውላይት ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከአስር አመት በላይ ምርምር ሲያደርግብት የቆየው (AirCarbon) የተሰኘው ይህ ቁስ የፕላስቲክ መልክ፣ ይዘት እና ግልጋሎት ኖሮት የተሰራ ቁስ ቢሆንም አጠቃላይ ስሪቱ ግን በተለያዩ ደቂቅ አካለትና ባካቴሪያዎች መበስበስ እንዲችል የተደረገ እና ምንም አይነት ብክለት እንዳይኖረው የተቀመረ ነው፡፡
ኩባንያው ይህን መሰል ፈጠራ ለማከናወን እንደመነሻ የተጠቀመው በውቅያኖስ ውስጥ መኖሪያቸውን ባደረጉ እና ለአለማችን የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ምክንያት የሆኑትን የሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳድ ጋዛችን በሚመገቡ ደቂቅ አካላት አማካኝነት ነው፡፡ አነዚህ አካላት የሚቴን እና ካርቦን ዳይኦክሳድ ጋዞችን ወደተፈጥሮ ፖሊመር በመቀየር ልክ እንደፕላስቲክ የሚተጣጠፉ እና የሚቀረፁ ቁሶችን ማውጣት የቻሉ ሲሆን ተመራማሪዎችም ከዚህ የተፈጥሮ ሂደት በመነሳት ፕላስቲኮችን በዚህ አምሳያ ለመስራት ሞክረዋል፡፡
የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ማርክ ሀርማ በምርምሩ ዙሪያ እንደተናገሩትም በዚህ ሂደት ለወጤት የበቃውን ፈጠራ (AirCarbon) ብለን የሰየምንበት ምክንያት አየርም ይሁን ካርቦን በውሃ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ ሊሟሙ እና ወደፈሳሽነት ሊቀየሩ መቻላቸውን ለማሳየት ነው ብለዋል፡፡ የምርምር ውጤቱ የከባቢ አየር ጋዞችን እንደግብዓት መጠቀም ዋና አላማ አድርጎ የተነሳ በመሆኑ የተፈጥሮ ስነምህዳርን በተለያየ መልኩ የሚታደግ ይሆናል፡፡
ኒውላይት ለዚህ አስገራሚ የፈጠራ ስራው በእንግሊዝ መቀመጫቸውን ባደረጉ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣነት ሙገሳን ያስገኘለት ሲሆን፤ የአሜሪካ ምግብና መድሃኒት አስተዳዳር (FDA) እና የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ (EPA) ከተፈጥሮ ጋር ወዳጀነት ለመሰረተው አስገራሚ ፈጠራ የእውቅና ሽልማት አበርክቷል፡፡
ምንጭ፡ CNN Business