TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ስፓርክ ሜከር 3ዲ ማተሚያ ማሽን
====
3ዲ ማተሚያ ማሽን የሰው ልጅ ህይወቱን ለማቅለል በሚያደርገው ረዥም ጉዞ ውስጥ ትልቅ እርምጃን ያራምዳል የተባለለት ወሳኝ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ይህ ማሽን በታሪክ ለመጀመሪ ጊዜ እ.ኤ.ኣ በ 1984 ዓ.ም የተዋወቀ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እተሻሻለ እና እያደገ መምጣቱም ይታወቃል፡፡
መሳሪያው በ ዲዛይን ደረጃ ወረቀት ላይ የነበሩ ስዕሎችን ሊዳሰስ ወደሚችል ግዑዝ አካልነት መቀየር የሚችል ነው፡፡ ወደ መሳሪያው የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ካስገባን በኋላ በዲዛይኑ መሰረት 3ዲ ቁሶችን ይወልድልናል፡፡ ይህ አብዛኃኛውን ጊዜ ትልልቅ ፋበሪካዎችን የሚያገለግል የማሽን ዓይነት ነው፡፡
ይሁንና ስፓርክ ሜከር (spark maker) ተብሎ የሚጠራው ይህ የ 3ዲ ማተሚያ ማሽን ዋና ዓላማው በዝቅተኛ ስኬል ህትመቶችን በማውጣት የ3ዲ ማተሚያ መሳሪያ የእያንዳንዳችንን ደጃፍ እንዲያንኳኳ ማድረግ ነው፡፡ ስፓርክ ሜከር በ መጠን አነስተኛ ሲሆን በካንፓኒው ከተሰራው ስፓርክ ሰቱዲዮ ከተሰኘው ሶፍት ዌር ውስጥ ማንኛውንም ዲዛይን መመምረጥ አሊያም የራሳችንን ዲዛይን በሶፍት ዌሩ ላይ መስራት የሚያስችለን ነው፡፡
በዚህ ማሽን አማካኝንት ፋይሉን ከኮምፒውተራችን በሚሞሪ በመውሰድ እና እርሱ ላይ በመሰካት ያሻንን ቅርፅ በግል ጥረታችን እንድናመርት የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ማሽን ለግብዓትነት የሚውሉ 5 የተለያዩ ፈሳሾችን የያዘ ሲሆን በርከት ያሉ የቀለም ምርጫዎችም አሉት፡፡ በተለይ ለህፃናት ጥሩ መማሪያ እና መዝናኛ ሊሆን ይችላል ተብሎም ይገመታል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ልዩ እና ዘመናዊ ቢሆንም ምናልባት የግለሰቦችን የፈጠራ ችሎታን ይገድብ ይሆን የሚለው ጥያቄ ለመጪው ጊዜ የሚተው ይሆናል፡፡
ምንጭ: Tech Virial
አንድ ሰው በኮቪድ 2ኛ ጊዜ ሊጠቃ ይችላል?
****************************
በአሁኑ ሰዓት በአለማችን የኮቪድ ተጠቂዎች ቁጥር ከ37.6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሔድም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከህመሙ እያገገሙ ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተ ከወራት በኋላ ተመራማሪዎችንና መንግስታትን ሲያስጨንቅ የነበረው የወረርሽኙ ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር መከሰት ነበር፡፡ ይህም ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር የመዋል አዝማሚያ ካሳየ በኋላ ዳግም እንደገና መስፋፋት ነው፡፡ እንደተፈራውም በአንዳንድ የአለማችን ከተሞች ይህ ችግር መከሰቱ አልቀረም፡፡ ከዳግም ወረርሽኝ በተጨማሪ ሌላው ጥናት ሲደረግበት የነበረው ነገር አንድ ሰው በበሽታው ተይዞ ካገገመ በኋላ ዳግመኛ በቫረሱ ይጠቃል ወይስ አይጠቃም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
በቅርብ ጊዜ የወጡ ዘገባዎች ደግሞ በሆንግ ኮንግ፣ ቤልጀም፣ ኔዘርላንድና ኢኳዶር ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆንም ከባድ የሚባል ህመም ግን አልታየባቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች በሽታ የመከላከል ብቃታቸው በመጀመሪያው ዙር ስለተነቃቃ ሁለተኛውን ዙር ህመም በቀላሉ መቋቋም ችለዋል፡፡
ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተጠቃ አንድ የ25 ዓመት ጎልማሳ የታየበት ከፍተኛ ህመም ተመራማሪዎችን እያከራከረ ይገኛል፡፡
ታማሚውን የሚከታተለው የናቫዳ ዩኒቨርስቲ ስለ ሁኔው የተለያዩ ማብራሪያዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ማብራሪያ ታማሚው በሁለተኛው ዙር ከፍተኛ መጠን ያለው የቫይረስ ቁጥር ወደ ሰውነቱ ገብቷል የሚል ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ታማሚው antibody dependent enhancement (ADE) የሚባለው ያልተለመደ የበሽታ መከላከል አቅም በሽታን የማባባስ ክስተት ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ችግር በ2003 በሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳርስ ጊዜ አጋጥሞ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር መካከል ያለው ጊዜ ተቀራራቢ መሆን አንዱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የያሌ ዩኒቨርሲቲ ኢሚዩኖባዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆነችው Akiko Iwasaki ክስተቱ (reinfection) በወረርሽኞች ዙሪያ የሚሰሩ ጥናቶችን የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰሯ አክለውም በሁኔታው ወረርሽኞችን ለመከላከል በሰዎች ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል ብቃት ላይ ብቻ መደገፍ እንደሌለብን ተረድተናል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ Financial Times
የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ ስንል ምን ማለታችን ነው?
አብዛኛውን ጊዜ እንደምንሰማው የአዕምሮ ጤና ሲነሳ ሰዎች ላይ ተደጋግሞ የሚታየው የድብርት እና የጭንቀት ሁኔታዎች አልያም ደግሞ ራስን የመሳትና የማጠት ሁኔታዎች ቀድመው ወደሃሳባችን ይመጣሉ፡፡ ይሁንና የአዕምሮን ጤና በትክክል ለመግለፅ ከሞከርን የሰዎችን ስሜታዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነትን በአንድነት ማንሳት ግድ ይለናል፡፡ የአዕምሮ ጤና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የሚሰማንን የድብርት እና የጭንቀት ስሜቶች ብቻ የምንገልፅበት ተራ ፅንሰ-ሃሳብ ሳይሆን እንዴት ማሰብና ማድረግ እንዳለብን፣ ዓለምን በምን መነፅር መመልከት እንደሚኖርብን እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የትኞቹን ውሳኔዎች ማሳለፍ እንደሚገባን የሚያመላክት እና በሁሉም ነገሮች ላይ እኛነታችን የሚገለፅበት የማንነታችን ቁልፍ ነው፡፡
የአዕምሯችን ደህንነት በእያንዳንዷ የህይወታችን እንቅስቃሴ፣ በሚኖረን ማህበራዊ ግንኙነት፣ በአካለዊ ጤንነታችን እና መሰረታዊ ፍላጎታችንን በማሟላት ውስጥ የሚገነባና የሚቀረፅ ቢሆንም ከቤተሰብ በምንወርሳቸው ጄኔቲካዊ ባህርያቶች እና በስነህዝብ አወቃቀር ውስጥ በሚጠቃለሉት የዘር፣ ቀለም እና ጾታዊ ምክንያቶች ተፅዕኖ ሊደረግበት ይችላል፡፡
በአለማችን ከስድስት ሰዎች በአንዱ የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ችግር የሚታይ ሲሆን አብዛኞቹ አጋጣሚዎችም በተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚያስቀምጡት የአዕምሮ ጤና ችግሮች ኒውሮቲክ እና ሳይኮቲክ በሚል የሚከፈሉ ሲሆን ሁለቱም ምደባዎች የያራሳቸው መገለጫዎች ያሏቸው ናቸው፡፡ እንደተመራማሪዎች ከሆነ ኒውሮቲክ (Neurotic) የሚባለው የተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የመሸበር፣ የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ሳይኮቲክ (psychotic) የሚባለው ደግሞ ሌሎች ሰዎች የማያዩትን፣ የማይሰሙትን እና የማያሸቱትን እውነታዊ ያልሆነ አለም ሞኖርና እና በሱ ውስጥም መገኘት ማለት ነው፡፡
እዚህ ለይ እኛ የተነሳንበት የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ሂደት እና የሚያጋጥሙት ችግሮች ከላይ ባነሳናቸው ምክንያቶች ተፅዕኖ የሚደረግበት ቢሆንም አሁን በምንኖረው ህይወት ውስጥ የአዕምሮ ጤናችንን ለማስጠበቅና ወደዛ ቸግር የሚስገቡንን ክፍተቶች ለመሙላት ከእኛ የሚጠበቀውን የህይወት ልምምድ በጥንቃቄ መከወን ይገባናል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በትኩረት ባይመለከቱትም እየኖሩት ያለው የየእለት እንቅስቃሴ የአዕምሮን ጤና ከማስጠበቅ ይልቅ የአዕምሮን ጤና ችግር ውስጥ የሚከት መጥፎ የህይወት ልምምድ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ብዙዎቻችንም በትኩረት ሳንመለከተው ቀርተን ይሆናል እንጂ የአዕምሯችንን ጤና ወደከፋ ደረጃ እየሄደ መሆኑን የሚመለክቱን የማስጠንቀቂያ ምልክቶች በራሳችን ላይ ታዝበን ይሆናል፡፡
ለምሳሌ ከሰዎች የመለየት አባዜ አብዝቶ ሲፀናወተን፣ ሁሌም ተስፋ ያማጣትና ረዳት አልባነት ሲሰማን፣ ከቤተሰብና ከጓደኛ ጋር በተደጋጋሚ መግባባት ሲያቅተን እንዲሁም ሌሎች ያልተለመዱ አድራጎቶችን በተከታታይነት ስንመለከት ቆም ብሎ በማሰብ ራሳችን መመርመር እና እርዳታ የምናገኘበት ሁኔታም መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችል፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ከአእምሯችን ጤና የሚቀዱት እነዚህ አድራጎቶች አስተሳሰባችንን፣ ባህሪያችንን እና ስሜቶቻችንን የሚቀርፁ በመሆናቸው ሁልግዜም የአዕምሯችን ደህንነት የሚጠበቅበትን ሁኔታ ማከናወን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የአዕምሮን ጤና በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ሁላችንም ልብ ልንላቸው ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጠው ሙያዊ እርዳታ የምናገኘበትን ሁኔታ መፈለግ ሲሆን፤ ከዚያ ባለፈ ግን ከሌሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አካለዊ እንቅስቀሴዎችን በማዘውተር፣ በቂ እንቅልፍ በመተኛት፣ አወንታዊ አስተሳሰብ በማበልፀግ እና ሌሎችን በመርዳት የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ እና ይበልጥ ማሻሻል እንችላለን፡፡
ምንጭ፡ Livescience እና Mental Health
5G እና የጤና ስጋት
*******************
የአምስተኛ ትውልድ የገመድ አልባ አገልግሎትን ለመጀመር ፉክክር አየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት የጤና ችግር ያስከትላል ብለው ስጋት የደረባቸው መንግስታትም ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶች እንዳሉ ሆኖ በሰዎች ላይ የጤና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚለው ስጋት ግን ሳያይል አይቀርም፡፡ ለመሆኑ የ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት የጤና ስጋት ይኖረው ይሆን?
ከዚህ በፊት በነበሩት የገመድ አልባ ትውልዶች የጤና ስጋት አሳስቧችሁ የማያውቅ ከሆነ አሁንም ምንም የሚያጨንቅ ጉዳይ የለም ለናል ዘገባውን ያወጣው www.WIRED.com . ቴክኖሎጂው ወደ ስራ ሲገባ የተወሰኑ አገልግሎቶች ብቻ ከፍተኛውን መጠን የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ውስን አገልግሎት ሰጭዎች የሚኖረው ሞገድ በሌሎች ከምናገኘው ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር የከፋ ጉዳት የሚያደርስ አይሆንም፡፡
በ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት ያለው የሬድዮ ሞገድ ፍጥነትን ለመጨመር ብቻ የሚሆን ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ የሚጠቀመው millimeter-wave ቴክኖሎጂ ከመደበኛው በተለየ ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል ቢሆንም የስምና የፍሪኩየንሲ ለውጡ መደበኛ የሆነውን ስነ-ህይዎታዊ የጤና መገለጫ ሐይል አይለውጠውም፡፡
ከሙቀት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቀነስ ተቆጣጣሪ አካላት የገመድ አልባ መገልገያዎች ሊያመነጩ የሚችሉትን ሙቀት ገደብ አበጅተውለታል፡፡ ጥናቶች አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው፡፡
ምንጭ www.WIRED.com
የኢንተርንሺፕ ጥሪ
===========
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለተሳታፊ ባለሙያዎች ጠቃሚ ክህሎት እና ዕውቀት ያስገኝ ዘንድ በኢንስቲትዩቱ የሚዘጋጀው የ TECH-TALENT HUNT ፕሮግራም አካል የሆነ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ኢንተርንሺፑ በህዝብ አገልግሎት ዘርፍ እና ማህበረሰብ ላይ ላሉ ተግዳሮቶች በፈጠራ የተሞላ መፍትሄ የሚሰጡ ባለሙያዎችን ለማውጣት ያለመ ነው፡፡
ከጥቅምት 16 አንስቶ ለስድስት ወራት በሚቆየው ዝግጅት ተሳታፊዎች እንደ ሴስተም ሶፍትዌር፣ የስልክ መተግበሪያ፣ በዌብ ፕሮዳክቶች ዲዛይን እና ማበልጸግ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
ከአውሮፓውያኑ 2018 በኋላ ከታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ አልያም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ መሆን አለባቸው፡-
computer science, information technology, information science, software engineering, computer engineering, data science, architecture, interior designer, educational planning and management (or Educational Policy and Strategic Management or Curriculum and Instruction), Multimedia Developer (audio visual).
ምዝገባ፡- አመልካቾች ከዛሬ ጥቅምት 4 2013 አንስቶ እስከ እሁድ ጥቅምት 8 ድረስ በድረ ገፃችን www.techin.gov.et/announcement ላይ ብቻ በመሄድ ፎርሙን መሙላት እና ከ2 ገፅ ያልበነለጠ ሲቪ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የተመረጡ አመልካቾች ብቻ በኢሜል አድራሻቸው መልዕክት እና ሌሎች ስራዎች የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት በዚህ ሊንክ ( http://techin.gov.et/post/345/ ) አማካኝነት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ያልዎትን ማንኛውም አይነት ጥያቄ በኢ-ሜይል አድራሻችን internship@techin.gov.et ተጠቅመው ሊያደርሱን ይችላሉ፡፡
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
የእይታ ትኩረትን (focus) ማስተካከል የሚችለው መነጽር
******************************
የሰው ልጅ እድሜ እየጨመረ በሔደ ቁጥር መደበኛ ስራቸውን መስራት እየተሳናቸው የሚሔዱ የሰውነት ክፍሎች መኖራቸው ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ከእነዚህ የሰውነት ክፍሎች መካከል አይናችን በቅርበትም ሆነ በርቀት የማየት ችግር በብዛት ያጋጥመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ሐኪም ሔደን ለአይናችን ችግር መፍትሔ ሊሆን የሚችል የአይን መነጽር ይታዘዝልናል፡፡ እዚህ ላይ ያለው ችግር በትእዛዝ የምንገዛቸው መነጽሮች ለአንድ ተግባር ብቻ የሚውሉና ዋጋቸውም በጣም ውድ መሆኑ ነው፡፡ በሐኪም ያልታዘዘ ወይም በህክምና ያልተረጋገጠ መነጽር መጠቀም ከሚሰጠው ጥቅም የሚያስከትለው ጉዳት ይበልጣል፡፡
በአይን ህክምና ረገድ በአለማችን ብዙ አዳዲስ ነገሮች ያሉ ሲሆን የተጠቃሚውን የማየት ፍላጎት ተከትሎ የእይታ ትኩረት (focus) የሚያስተካክል መነጽር አንደኛው ነው፡፡ በእስራኤሉ Deep Optics የቴክኖሎጂ ተቋም የተመረተው ይህ የአይን መነጽር ምንም አይነት ብዥታ እንዳኖር ማድረግ የሚችል ነው፡፡
መነጽሩ የተገጠመለት ሙሉ እይታ "liquid crystal" lens በኤሌክትሪካዊ መንገድ ከሴንሰሩ ወደ ፕሮሰሰሩ በሚላክ መረጃ የእታን ትኩረት (view focus) ወዲያውኑ ያስተካክላል፡፡ በዚህም ምክንያት ተጠቃሚው ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ማየት የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር በግልጽ መመልከት እንዲችል ያደርገዋል፡፡ 'omnifocals' የተባለው የካምፓኒው ምርት በቅርብ ያሉ ነገሮችን የማየት ችግር (presbyopia) ለመቅረፍ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡

ምንጭ: www.howstuffworks.com
TECHIN seminar
==========
TECHIN seminar will be back next week, at TECHIN hall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School). For this session Dr. Eyobel Mulugeta will discuss improvement of Enjera shelf life through the use of Ag and ZnO nano particles.
Starting time: 9:30 AM
ትምህርትና ቅድመ ጥንቃቄ
***********************
ባለፈው ዓመት መጋቢት የሆነ ቀን ህጻናት ትምህርት ቤት ክፍላቸው ውስጥ ነበሩ፡፡ በሌላኛው ቀን ግን ያልተጠበቀ ዱብእዳ መጣና ትምህር ቤቶች ተዘጉ፡፡ ያ ተማሪዎች እንደዋዛ ጥለውት የወጡት ክፍል አሁን ምንም እንኳን ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባይቻልም ህይወት መቀጠል አለበትና ዳግም ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በክፍል ውስጥ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም በመማሪያ ክፍል ውስጥ አየር በብዛት እንዳይንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡ ይህም የተማሪዎቹን በቫይረሱ የመያዝ እድል በተወሰነ መልኩ ይቀንሰዋል፡፡ አካላዊ ርቀትን መጠበቅና ጭንብል መልበስ እንዳለ ሆኖ ሊደረጉ የሚገባቸውን ወሳኝ ጥንቃቄዎች ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡
1ኛ. በቂ አየር (ventilation)
አሁን ባለው ሁኔታ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20-25 ተማሪዎችን 2 ሜትር ያክል አራርቆ ማስቀመጥ እና ማስተማር የሚያስችል የመማሪያ ክፍል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በመሆኑም በክፍል ውስጥ በቂ አየር እንዲዎጣ እና እንዲገባ አስፈላጊው ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡ ይህም ሲባል የመማሪ ክፍሉ በርና መስኮቶች አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን ማረጋገጥና ጥብቅ በሆነ መመሪያ መከፈት ያለባቸው ተከፍተው ክፍሉ ንጹህ አየር የሚንቀሳቀስበት መሆን አለበት፡፡ ተማሪዎቹ የለበሱትን ጭንብል በየጊዜው እያወለቁ እንዳይቸገሩ ያደርጋቸዋል፡፡
2ኛ. የግቢና የክፍል ውስጥ ጥብቅ ዲሲፕሊን
በተለይ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና ጭምብል በአግባቡ በመልበስ በኩል ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ አንጻር መጀመሪያ ሊነሳ የሚችለው በእረፍት ላይ በነበሩበት ወቅት በቤት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ጭምብል የመልበስ ልምድ ስለማይኖራቸው በአግባቡ ላይጠቀሙት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም አካል ራሱ መመሪውን በአግባቡ ተግብሮ ተማሪዎች እንዲተገብሩት ማድረግ የህይወትና የሞት ጉዳይ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ በተቻለ መጠን በአመቱ ውስጥ ትልቁ የትምህርት ቤቶች ስራ ተማሪዎችና መምህራን ጤናቸው እንደተጠበቀ የመማር ማስተማር ስራውን ማስቀጠል ሊሆን ይገባዋል፡፡
3ኛ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት
በዚህ ወቅት በተማሪዎች አእምሮ ውስጥ ከሚርመሰመሱ ሀሳቦች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የወረርሽኙ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም በቀጥታ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ወላጆችና መምህራን ተማሪዎች ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ መጨነቅ እንደማይገባቸው እና ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ የምክር አገልግሎት በየጊዜው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከላይ የተዘረዘሩ ጥንቃቄዎች በትኩረት ሁላችንም መተግበር ከቻልን ወረርሽኙ ተስፋፍቶ ዳግም ትምህርት ቤቶች እንዳይዘጉና ተማሪዎቻችን ለሌላ ጭንቀት እንዳዳረጉ መጠበቅ እንችላለን፡፡
የደም ዓይነትና ኮቪድ 19
***********************
የሰዎች የደም ዓይነት በኮሮናቫይረስ ከመያዝና በጸና ህመም ከመሰቃየት ጋር ግንኙነት እንዳለው NBC news የተባለ የዜና ማሰራጫ ተቋም በዘገባው አስነብቧል፡፡ እንደማብራሪያው ይህ ሁኔታ ከደም አይነቶች መካከል አንዱ ለወረርሽኙ በጣም ተጋላጭ ያደርጋል የሚል መደምደሚያ ባይኖረውም የሚወጡት ግኝቶች ግን ከመልስ ይልቅ ብዙ ጥያቄዎችን ያስከተሉ ናቸው ተብሏል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የአሜሪካ ሄማቶሎጂ ሶሳይቲ ጆርናል ላይ የወጡት ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን በሰዎች የደም ዓይነት እና በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚነሱ ነጥቦችን በሚከተለው መልኩ ቃኝተዋቸዋል፡፡
በመጀመሪያው ጥናት በዴንማርክ 473,654 ሰዎች የኮቪድ ምርመራ ተደርጎላቸው አብዛኞቹ ነጻ ሲሆኑ ቫይረሱ የተገኘባቸው 7,422 ብቻ ነበሩ ይህም ከየካቲት እስከ ሐምሌ ድረስ ያለው መረጃ ነው፡፡ ከደም ዓይነቶች መካከል O በመባል የሚታዎቀው ያላቸው ሰዎች ለSARS-CoV-2 የተጋላጭነት እድላቸው አነስተኛ እንደሆነ ጥናቶች አመልክተዋል፡፡ SARS-CoV-2 ለኮቪድ 19 መነሻ የሆነ ቫይረስ እንደሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ የጥናቱ ውጤት ከተመረመሩ ሰዎች መካከል 62 በመቶ ያክሉ ብቻ የደም አይነት መረጃ ያላቸው በመሆኑ እጥረት አለበት፡፡ መጠኑ ይነስ እንጂ O የደም ዓይነት ያላቸው ሰዎች የተጋላጭነት እድላቸው የቀነሰ ነው፡፡
ሌላኛው ጥናት በካናዳ የተደረገ ሲሆን ለሆስፒታል የሚያበቃ ህመም በገጠማቸው 95 የኮቪድ ታማሚዎች ላይ የተሰራ ነው፡፡ በጥናቱም ከታማሚዎች A ወይም AB የደም ዓነት ያላቸው ሰዎች የመተንፈሻ መሳሪያ ሲስፈልጋቸው ተስተውሏል፡፡ እንዲሁም በከፍተኛ ክትትል ክፍል (ICU) ውስጥ ረጅም ቆይታ አድርገዋል፡፡ ይህም O ወይም B የደም ዓይነት ካላቸው ሰዎች ጋር ሲነጻጸር ነው፡፡ A ወይም AB የደም ዓይነት ያላቸው ሰዎች ኩላሊታቸው የበለጠ ደም ማጣራት እንዲችል የዲያለሲስ እገዛም ተደርጎላቸዋል፡፡ በሁለቱም ጥናቶች ግን ይህ የደም አይነት የተጋላጭነት መጠኑ ዜሮ ነው የሚል ግኝት የለም፡፡
የማህበረሰብ ጤና ባለሙያዎች የትኛውም የደም ዓይነት ቢኖረንም ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችሉ መከላከያ መንገዶችን በአግባቡ መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ስለ ጥናቱ የWisconsin ሜዲካል ኮሌጅ ሀላፊ የሆኑት Dr. Roy Silverstein ለተጨማሪ ጥናቶች መነሻ የሚሆን ጥናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ NBC NEWS
ቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ተሸላሚ ሆነ
====================
በቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶ ለአየር የሚበቃው የቴክ-ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራም የ2020 OFAB Ethiopia chapter annual award ውድድር ላይ የአንደኝነት ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡ ሽልማቱ የተበረከተው ፕሮግራሙ በቴሌቪዥን ስርጭት ዘርፍ በዓመቱ የግብርና ባዮ ቴክኖሎጂ ላይ በሰራቸው የሳይንስ ጋዜጠኝነት ስራዎች ነው፡፡
ውድድሩ ሲዘጋጅ ይህ ለአራተኛ ጊዜው ሲሆን ከቴሌቪዥን በተጨማሪም በህትመት እና ራድዮን ዘርፎች በየዓመቱ አወዳድሮ ሲሸልም ቆይቷል፡፡ ከዚህ በመቀጠልም ቴክ-ሳይንስን ጨምሮ በኢትዮጵያ ያሸነፉት ሦስት ተወዳዳሪዎች በአፍሪካ ደረጃ በሚደረገው መሰል ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል፡፡
ሽልማቱን ያበረከተው OFAB ወይም በሙሉ መጠሪያው Open Forum on Agricultural Biotechnology in Africa በዓለም አቀፉ የግብርና ከብቶች ጥናት ኢንስቲትዩት (ILRI) አማካኝነት የሚዘጋጅ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሚንቀሳቀሰው ፎረሙ በባዮ ቴክኖሎጂ ዙርያ ያሉ ባለ ድርሻ አካላትን በእውቀት እና ልምድ በማስተሳሰር የባዮ ቴክኖሎጂን ትሩፋቶች ለአፍሪካውያን ገበሬ ብሎም ባለሀብቶች ለማቋደስ የሚሰራ ነው፡፡
ቴክ ሳይንስ የቴሌቪዥን ፕሮግራምን ዘውትር ቅዳሜ በ10 ሰዓት በድጋሚ ደግሞ ማክሰኞ በ10 ሰዓት በ MOE TV ያገኙታል
በተጨማሪም የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ያመለጥዎትን ፕሮግራም እና ሌሎች የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዝግጅቶች ያግኙ>>> https://www.youtube.com/channel/UC6jvUOLRSkVEQtc5Annfwvg