TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
የድምጽ ፍጥነት ከፍተኛው ልኬት (The Upper Limit of speed of sound)
********************************
Special Relativity እየተባለ የሚጠራው የአልበርት አንስታይን መላምት ብርሀን በወና ውስጥ ሲያልፍ የሚኖረውን የፍጥነት ጥግ speed limit እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ ነገር ግን በማንኛውም አካል ላይ ያለ ትክክለኛውን ከፍተኛ የብርሀን ፍጥነት ማዎቅ አልተቻለም፡፡ በእያንዳንዱ ነገር ላይ ያለውን የድምጽን ፍጥነት መለካት እጅግ አስቸጋሪ ነገር ቢሆንም የፊዚክስ ተመራማሪዎች ከፍተኛውን የድምጽ ፍጥነት ልኬት ማግኘት ችለዋል፡፡
በአዲሱ ቀመር መሰረት የፍጥነት ጥጉ በሴኮንድ 36 ኪሎ ሜትሮች ያክል ሆኗል፡፡ ይህም ድምጽ በዳይመንድ ሲያልፍ ካለው ፍጥነት ሁለት እጥፍ ማለት ነው፡፡ ድምጽና ብርሀን እንቅስቃሴያቸው በሞገድ መልኩ ቢሆንም የተወሰነ ልዩነት አላቸው፡፡ ክሱት የሆነው ብርሀን (Visible light) በኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር መልክ ይጓዛል፡፡ እነዚህ ኤሌክትሪካዊና መግነጢሳዊ መንገዶች ብርሀንን በወና ውስጥ በሴኮንድ 300,000 ኪሎ ሜትር እንዲጓዝ ያደርጉታል፡፡ ብርሀን በውሃና በከባቢ አየር ውስጥ ሲጓዝ ፍጥነቱ ይቀንሳል፡፡
ድምጽ በርግብግቦሽ የሚፈጠር ሜካኒካዊ ሞገድ ነው፡፡ የድምጽ ማስተላለፊያው ቅንታቶች ጥግግት በጨመረ ቁጥር የድምጽ ሞገድ ፍጥነትም ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ፍጥነት ከጋዝ በውሃ ሲጨምር ከውሃ ደግሞ በጠጣር ይጨምራል፡፡
ይህንን ጥናት የእንግሊዞቹ ኩይን ሜሪ ዩኒቨርስቲ እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በጋራ የሰሩት ሲሆን በሩሲያ የሚገኘው ሃይ ፕሬዠር ፊዚክስ ኢኒስቲትዩትም እንዲሁ ታሳትፎበታል፡፡
ምንጭ፡ Science Alert
ጥርስ እና አጥንት፤ ምን ለያቸው?
============
ጥርስም ሆነ አጥንት የተላበሱት ጥንካሬ እና ንጣት ብሎም በካልሺየም መበፀጋቸው የጋራ የሚያደርጉ መገለጫዎቻቸው ቢሆኑም አንድ ግን አያደርጓቸውም፡፡ ከገፅታቸው አንስቶ እራሳቸውን ማከሚያ መንገዳቸው አጥንቶቻችን ሰውነታችንን ከተሸከሙት አጥንቶች ይለያሉ፡፡
ጥርሶቻችን ካልሺየም፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን አቅፎው የያዙ ናቸው፡፡ አጥንቶቻችን ግን በዋናነት የተገነቡት በኮላጅን ፕሮቲን ነው፡፡ ኮላጅን ህይወት ያለውና እድገት የሚያሳይ ህብረ-ህዋስ ሲሆን ለአጥንቶቻችንም ግፊትን ለመቋቋም የሚያስችላቸውን ተለማጭነት የሚያጎናጽፍ ነው፡፡ ካልሺየም በበኩሉ በዚህ በተፈጠረ መዋቅር ዙርያ በሚገኘው ስፍራ በመሄድ አጥንቶታችን ጠንካራ እና የሰውነት ክብደታችንን መቋቋም እንዲችሉ የማድረግ ድርሻውን ይወጣል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አጥንቶቻችን ከጥርሶቻችን የሚስተካከል ጥንካሬ የላቸውም፡፡ በሰውነታችን ከሚገኙ ማንኛውም ክፍሎች በላቀ ጠንካራ የሆነው ጥርሳችን በዋናነት ዴንታይን የተባለውን በካልሺየም ጨው የበለፀገ ህብረ-ህዋስ የተሞላ ነው፡፡ የጥርሳችንን ዴንታይል ህብረ-ህዋስ ኤናሜል በተባለው ጠንካራ እና አብለጭላጭ ምንጣፍ ከላይ ተሸፍኗል፡፡
አብዛኛው የአጥንቶቻችን የውጭ ክፍል ፔሪዎሴየም በተባለ ጠንካር ግን ለስላሳና አንሸራታች በሆነ በሆነ ሜምብሬን የተሞላ ነው፤ በበአሙለጭላጩ ሃይላይን ካርትሌጅ ከተሞሉት የረጃጅም አጥንቶች መገጣጠሚያ ውጪ፡፡ ፔሪዎሴየም አዲስ አጥንትን በሚጠግኑ እና እንደ አዲስ በሚፈጥሩት የኦሲዮብላስት ህዋሳት የተሞላ ነው፡፡
ከአጥንት በተለየ ጥርሶቻችን እራሳቸውን ዳግም የመተካት ብቃት የላቸውም፡፡ ጥርሶቻችን እራሳቸውን ማከም እና ከተሰበሩም ዳግም አድገው ወደነበሩበት መመለስ አይችሉም፡፡ አንድ አጥንት በሚሰነጠቅበት ሰዓት አዳዲስ የአጥንት ህዋሳት ክፍተቱን ለመሙላት እና ለመጠገን ፈጥነው ወደስፍራው ይነጉዳሉ፡፡ ሆኖም የተሰበረ ወይም የተሰነጠቀ ጥርስ ግን ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡
ሌላኛው በሁለቱ የሰውነት አካላቻችን መካከል ያለው ልዩነት፤ አጥንቶቻችን በውስጣቸው ባሉ አካላት አማካኝነት ቀይ እና ነጭ የደም ህዋሳትን ሲያመርቱ ጥርሶቻችን ግን ይህን ለማድረግ አለመታደላቸው ነው፡፡ አጥንቶቻችን የደም ፍላጎታቸውን ከውስጥ እስከ ፔሪዎሴየማቸው ከሚያልፉት በርካታ የደም ቧንቧዎች ያሟላሉ፡፡
ወደ ጥርሶቻችን ስንመለስ የወለቀ ጥርስ ቦታ ላይ ምናገኘው አካል አነስተኛ መስሎ ሊታየን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ክፍል ዴንታል ፐልፕ ተብሎ የሚጠራው ህይወት ያለው የእያንዳንዱ ጥርሶቻችን ክፍል ሲሆን፤ በአገጭ አጥንቶቻችን ውስጥ የተዘረጉትን ነርቭ እና የደም ቧንቧዎች የያዘ ነው፡፡ በተቦረቦሩ ጊዜ ወይም ቀዝቃዛም ሆነ ሙቅ ነገሮችን ስንመገብ ህመምን የሚፈጥሩብንም እነዚህ ነርቮቻችን ናቸው፡፡
ምንጭ፡ Live Science
የኮሮናቫይረስ ለ28 ቀናት በስልኮቻችን መስታዎት ላይ ሊቆይ ይችላል
የብሄራዊ ሳይንስ ኤጄንሲ (CSIRO) በአውስታራሊያ የበሽታ ዝግጁነት ማዕከል (ACDP) አደረኩት ባላው ጥናት ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት የሆነው SARS-CoV-2 ቫይረስ በአንዳንድ የቁሶች ገፅ (surfaces) ላይ ለ28 ቀናት መቆየት እና መትረፍ እንደሚችል በጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ተመራማሪዎች በዚህ ጥናት እንደጠቆሙት የኮሮናቫይረስ በስልካችን የመስታዎት እስክሪኖች፣ በማይዝጉ ብረቶች (stainless steel)፣ በሸክላ ዲስኮች እና በወረቀት የባንክ ኖቶች ላይ ለ28 ቀናት በህይወት የመቆየት አቅም እንዳለው ይፋ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎች በዚህ ጥናት ላይ ለመረዳት እንደቻሉት SARS-CoV-2 ቫይረስ በፕላስቲክ ከሚሰሩ የገንዘብ ኖቶች በላይ በወረቀት የባንክ ኖቶች ላይ ለረዥም ጊዜ የመቆየት አቅም ሲኖረው ፈሳሽ ከሚያሳልፉ እንደጥጥ ካሉ ቁሶች በላይ ደግሞ በደረቅ ለስላሳ ቁሶች ላይ ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ምርምሩ የአልትራቫዮሌት ወይም (UV light) ብርሃኖችን ውጤታማነት ለመቀነስ ሲባል በጨለማ ቦታ ላይ መከናወኑን የሚያስረዱት የአውስታራሊያ ብሄራዊ ዩኒቨርስቲ ተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰር ፒተር ኮሊኒዮን ይህ ድርጊት ቫይረሱ በወለሎች ላይ የመቆየት አቅሙን ይቀንሰዋል ይላሉ፡፡
ቫይረሱ ሰፊ የወለል መዳረሻ ባላቸው ቁሶች እና ስፍራዎች ላይ በንክኪ የመተላለፍ ሁኔታው ምን ያህል ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ቢሆንም ከዚህ ጥናት ለመረዳት እንደተቻለው SARS-CoV-2 ቫይረስ ሞቃታማ ከሆኑ አካባቢዎች ይልቅ ዝቅተኛ የሙቀት ሁኔታዎች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ ይበልጥ የመቆየት አቅም እንዳለው ለማየት ተችሏል፡፡
ተመራማሪዎች በጥናት እንደጠቆሙት የኮሮናቫይረስ ለዚንያህል ቀናት በቁሶች ላይ የመቆየት አቅም ቢኖረውም ሰዎች ቫይረሱን በንክኪ የማግኘታቸው ሁኔታ በሌሎች ከሚተላለፍባቸው አንፃር ሲታይ እጅግ የሰፋ ልዩነት ይታይበታል፡፡ ፕሮፌሰር ኮሊኒዮን እንደሚያስረዱትም 90 በመቶው የኮቪድ 19 መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚኖራቸው የቀረበ ንክኪ እና ከአፋቸው በሚወጡ ጥቃቅን የትንፋሽ ብናኞች ሊሆን እንደሚችልም በጥናቱ ላይ አስረድተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ እጃችን የተለያዩ ቁሶችን በመንካት የሚኖረው የቫይረስ የመተላለፍ ሁኔታ ከአስር በመቶ የሚሻገር አለመሆኑን በልበ ሙሉነት ይገልፃሉ፡፡
ቫይረሱ በእጅ ንክኪ ሊተላለፍ ከመቻሉ አንጻር ፊታችንን ከመንካታችን በፊት ሁልግዜም እጆቻችንን በሳሙና መታጠብ ከቻልን በሽታውን ሙሉ ለሙሉ ወደ እኛ እንዳይደርስ ማድረግ እንደሚቻልም ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ፡፡
ጥናቱ በትክክል እንዳስቀመጠው 20 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት ልኬት ባለባቸው አካባቢዎች የቫይረሱ መትረፍ አቅም እጅግ ከፍተኛ ሆኖ የተገኘ ሲሆን ለስላሳ ገፅ ባለቻው እንደ ስልክ ስክሪን ያሉ ቁሶች ላይ ደግሞ ለ28 ቀናት በሚገባ ሊቆይ ይችላል፡፡ ከዚህ ባለፈ የሙቀት ልኬታቸው 30 እና 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚገመት አካባቢዎች የቫይረሱ የመትረፉ ሁኔታ እጅግ እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ያለባቸው አካባቢዎች ግን ለቫይረሱ የተመቹ ቦታዎች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ The Guardian
ስፓርክ ሜከር 3ዲ ማተሚያ ማሽን
====
3ዲ ማተሚያ ማሽን የሰው ልጅ ህይወቱን ለማቅለል በሚያደርገው ረዥም ጉዞ ውስጥ ትልቅ እርምጃን ያራምዳል የተባለለት ወሳኝ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ይህ ማሽን በታሪክ ለመጀመሪ ጊዜ እ.ኤ.ኣ በ 1984 ዓ.ም የተዋወቀ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እተሻሻለ እና እያደገ መምጣቱም ይታወቃል፡፡
መሳሪያው በ ዲዛይን ደረጃ ወረቀት ላይ የነበሩ ስዕሎችን ሊዳሰስ ወደሚችል ግዑዝ አካልነት መቀየር የሚችል ነው፡፡ ወደ መሳሪያው የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ካስገባን በኋላ በዲዛይኑ መሰረት 3ዲ ቁሶችን ይወልድልናል፡፡ ይህ አብዛኃኛውን ጊዜ ትልልቅ ፋበሪካዎችን የሚያገለግል የማሽን ዓይነት ነው፡፡
ይሁንና ስፓርክ ሜከር (spark maker) ተብሎ የሚጠራው ይህ የ 3ዲ ማተሚያ ማሽን ዋና ዓላማው በዝቅተኛ ስኬል ህትመቶችን በማውጣት የ3ዲ ማተሚያ መሳሪያ የእያንዳንዳችንን ደጃፍ እንዲያንኳኳ ማድረግ ነው፡፡ ስፓርክ ሜከር በ መጠን አነስተኛ ሲሆን በካንፓኒው ከተሰራው ስፓርክ ሰቱዲዮ ከተሰኘው ሶፍት ዌር ውስጥ ማንኛውንም ዲዛይን መመምረጥ አሊያም የራሳችንን ዲዛይን በሶፍት ዌሩ ላይ መስራት የሚያስችለን ነው፡፡
በዚህ ማሽን አማካኝንት ፋይሉን ከኮምፒውተራችን በሚሞሪ በመውሰድ እና እርሱ ላይ በመሰካት ያሻንን ቅርፅ በግል ጥረታችን እንድናመርት የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ማሽን ለግብዓትነት የሚውሉ 5 የተለያዩ ፈሳሾችን የያዘ ሲሆን በርከት ያሉ የቀለም ምርጫዎችም አሉት፡፡ በተለይ ለህፃናት ጥሩ መማሪያ እና መዝናኛ ሊሆን ይችላል ተብሎም ይገመታል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ልዩ እና ዘመናዊ ቢሆንም ምናልባት የግለሰቦችን የፈጠራ ችሎታን ይገድብ ይሆን የሚለው ጥያቄ ለመጪው ጊዜ የሚተው ይሆናል፡፡
ምንጭ: Tech Virial
አንድ ሰው በኮቪድ 2ኛ ጊዜ ሊጠቃ ይችላል?
****************************
በአሁኑ ሰዓት በአለማችን የኮቪድ ተጠቂዎች ቁጥር ከ37.6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሔድም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከህመሙ እያገገሙ ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተ ከወራት በኋላ ተመራማሪዎችንና መንግስታትን ሲያስጨንቅ የነበረው የወረርሽኙ ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር መከሰት ነበር፡፡ ይህም ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር የመዋል አዝማሚያ ካሳየ በኋላ ዳግም እንደገና መስፋፋት ነው፡፡ እንደተፈራውም በአንዳንድ የአለማችን ከተሞች ይህ ችግር መከሰቱ አልቀረም፡፡ ከዳግም ወረርሽኝ በተጨማሪ ሌላው ጥናት ሲደረግበት የነበረው ነገር አንድ ሰው በበሽታው ተይዞ ካገገመ በኋላ ዳግመኛ በቫረሱ ይጠቃል ወይስ አይጠቃም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
በቅርብ ጊዜ የወጡ ዘገባዎች ደግሞ በሆንግ ኮንግ፣ ቤልጀም፣ ኔዘርላንድና ኢኳዶር ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆንም ከባድ የሚባል ህመም ግን አልታየባቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች በሽታ የመከላከል ብቃታቸው በመጀመሪያው ዙር ስለተነቃቃ ሁለተኛውን ዙር ህመም በቀላሉ መቋቋም ችለዋል፡፡
ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተጠቃ አንድ የ25 ዓመት ጎልማሳ የታየበት ከፍተኛ ህመም ተመራማሪዎችን እያከራከረ ይገኛል፡፡
ታማሚውን የሚከታተለው የናቫዳ ዩኒቨርስቲ ስለ ሁኔው የተለያዩ ማብራሪያዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ማብራሪያ ታማሚው በሁለተኛው ዙር ከፍተኛ መጠን ያለው የቫይረስ ቁጥር ወደ ሰውነቱ ገብቷል የሚል ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ታማሚው antibody dependent enhancement (ADE) የሚባለው ያልተለመደ የበሽታ መከላከል አቅም በሽታን የማባባስ ክስተት ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ችግር በ2003 በሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳርስ ጊዜ አጋጥሞ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር መካከል ያለው ጊዜ ተቀራራቢ መሆን አንዱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የያሌ ዩኒቨርሲቲ ኢሚዩኖባዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆነችው Akiko Iwasaki ክስተቱ (reinfection) በወረርሽኞች ዙሪያ የሚሰሩ ጥናቶችን የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰሯ አክለውም በሁኔታው ወረርሽኞችን ለመከላከል በሰዎች ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል ብቃት ላይ ብቻ መደገፍ እንደሌለብን ተረድተናል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ Financial Times
የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ ስንል ምን ማለታችን ነው?
አብዛኛውን ጊዜ እንደምንሰማው የአዕምሮ ጤና ሲነሳ ሰዎች ላይ ተደጋግሞ የሚታየው የድብርት እና የጭንቀት ሁኔታዎች አልያም ደግሞ ራስን የመሳትና የማጠት ሁኔታዎች ቀድመው ወደሃሳባችን ይመጣሉ፡፡ ይሁንና የአዕምሮን ጤና በትክክል ለመግለፅ ከሞከርን የሰዎችን ስሜታዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነትን በአንድነት ማንሳት ግድ ይለናል፡፡ የአዕምሮ ጤና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የሚሰማንን የድብርት እና የጭንቀት ስሜቶች ብቻ የምንገልፅበት ተራ ፅንሰ-ሃሳብ ሳይሆን እንዴት ማሰብና ማድረግ እንዳለብን፣ ዓለምን በምን መነፅር መመልከት እንደሚኖርብን እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የትኞቹን ውሳኔዎች ማሳለፍ እንደሚገባን የሚያመላክት እና በሁሉም ነገሮች ላይ እኛነታችን የሚገለፅበት የማንነታችን ቁልፍ ነው፡፡
የአዕምሯችን ደህንነት በእያንዳንዷ የህይወታችን እንቅስቃሴ፣ በሚኖረን ማህበራዊ ግንኙነት፣ በአካለዊ ጤንነታችን እና መሰረታዊ ፍላጎታችንን በማሟላት ውስጥ የሚገነባና የሚቀረፅ ቢሆንም ከቤተሰብ በምንወርሳቸው ጄኔቲካዊ ባህርያቶች እና በስነህዝብ አወቃቀር ውስጥ በሚጠቃለሉት የዘር፣ ቀለም እና ጾታዊ ምክንያቶች ተፅዕኖ ሊደረግበት ይችላል፡፡
በአለማችን ከስድስት ሰዎች በአንዱ የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ችግር የሚታይ ሲሆን አብዛኞቹ አጋጣሚዎችም በተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚያስቀምጡት የአዕምሮ ጤና ችግሮች ኒውሮቲክ እና ሳይኮቲክ በሚል የሚከፈሉ ሲሆን ሁለቱም ምደባዎች የያራሳቸው መገለጫዎች ያሏቸው ናቸው፡፡ እንደተመራማሪዎች ከሆነ ኒውሮቲክ (Neurotic) የሚባለው የተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የመሸበር፣ የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ሳይኮቲክ (psychotic) የሚባለው ደግሞ ሌሎች ሰዎች የማያዩትን፣ የማይሰሙትን እና የማያሸቱትን እውነታዊ ያልሆነ አለም ሞኖርና እና በሱ ውስጥም መገኘት ማለት ነው፡፡
እዚህ ለይ እኛ የተነሳንበት የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ሂደት እና የሚያጋጥሙት ችግሮች ከላይ ባነሳናቸው ምክንያቶች ተፅዕኖ የሚደረግበት ቢሆንም አሁን በምንኖረው ህይወት ውስጥ የአዕምሮ ጤናችንን ለማስጠበቅና ወደዛ ቸግር የሚስገቡንን ክፍተቶች ለመሙላት ከእኛ የሚጠበቀውን የህይወት ልምምድ በጥንቃቄ መከወን ይገባናል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በትኩረት ባይመለከቱትም እየኖሩት ያለው የየእለት እንቅስቃሴ የአዕምሮን ጤና ከማስጠበቅ ይልቅ የአዕምሮን ጤና ችግር ውስጥ የሚከት መጥፎ የህይወት ልምምድ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ብዙዎቻችንም በትኩረት ሳንመለከተው ቀርተን ይሆናል እንጂ የአዕምሯችንን ጤና ወደከፋ ደረጃ እየሄደ መሆኑን የሚመለክቱን የማስጠንቀቂያ ምልክቶች በራሳችን ላይ ታዝበን ይሆናል፡፡
ለምሳሌ ከሰዎች የመለየት አባዜ አብዝቶ ሲፀናወተን፣ ሁሌም ተስፋ ያማጣትና ረዳት አልባነት ሲሰማን፣ ከቤተሰብና ከጓደኛ ጋር በተደጋጋሚ መግባባት ሲያቅተን እንዲሁም ሌሎች ያልተለመዱ አድራጎቶችን በተከታታይነት ስንመለከት ቆም ብሎ በማሰብ ራሳችን መመርመር እና እርዳታ የምናገኘበት ሁኔታም መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችል፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ከአእምሯችን ጤና የሚቀዱት እነዚህ አድራጎቶች አስተሳሰባችንን፣ ባህሪያችንን እና ስሜቶቻችንን የሚቀርፁ በመሆናቸው ሁልግዜም የአዕምሯችን ደህንነት የሚጠበቅበትን ሁኔታ ማከናወን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የአዕምሮን ጤና በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ሁላችንም ልብ ልንላቸው ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጠው ሙያዊ እርዳታ የምናገኘበትን ሁኔታ መፈለግ ሲሆን፤ ከዚያ ባለፈ ግን ከሌሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አካለዊ እንቅስቀሴዎችን በማዘውተር፣ በቂ እንቅልፍ በመተኛት፣ አወንታዊ አስተሳሰብ በማበልፀግ እና ሌሎችን በመርዳት የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ እና ይበልጥ ማሻሻል እንችላለን፡፡
ምንጭ፡ Livescience እና Mental Health
5G እና የጤና ስጋት
*******************
የአምስተኛ ትውልድ የገመድ አልባ አገልግሎትን ለመጀመር ፉክክር አየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት የጤና ችግር ያስከትላል ብለው ስጋት የደረባቸው መንግስታትም ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶች እንዳሉ ሆኖ በሰዎች ላይ የጤና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚለው ስጋት ግን ሳያይል አይቀርም፡፡ ለመሆኑ የ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት የጤና ስጋት ይኖረው ይሆን?
ከዚህ በፊት በነበሩት የገመድ አልባ ትውልዶች የጤና ስጋት አሳስቧችሁ የማያውቅ ከሆነ አሁንም ምንም የሚያጨንቅ ጉዳይ የለም ለናል ዘገባውን ያወጣው www.WIRED.com . ቴክኖሎጂው ወደ ስራ ሲገባ የተወሰኑ አገልግሎቶች ብቻ ከፍተኛውን መጠን የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ውስን አገልግሎት ሰጭዎች የሚኖረው ሞገድ በሌሎች ከምናገኘው ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር የከፋ ጉዳት የሚያደርስ አይሆንም፡፡
በ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት ያለው የሬድዮ ሞገድ ፍጥነትን ለመጨመር ብቻ የሚሆን ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ የሚጠቀመው millimeter-wave ቴክኖሎጂ ከመደበኛው በተለየ ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል ቢሆንም የስምና የፍሪኩየንሲ ለውጡ መደበኛ የሆነውን ስነ-ህይዎታዊ የጤና መገለጫ ሐይል አይለውጠውም፡፡
ከሙቀት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቀነስ ተቆጣጣሪ አካላት የገመድ አልባ መገልገያዎች ሊያመነጩ የሚችሉትን ሙቀት ገደብ አበጅተውለታል፡፡ ጥናቶች አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው፡፡
ምንጭ www.WIRED.com
የኢንተርንሺፕ ጥሪ
===========
የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ለተሳታፊ ባለሙያዎች ጠቃሚ ክህሎት እና ዕውቀት ያስገኝ ዘንድ በኢንስቲትዩቱ የሚዘጋጀው የ TECH-TALENT HUNT ፕሮግራም አካል የሆነ የኢንተርንሺፕ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ ኢንተርንሺፑ በህዝብ አገልግሎት ዘርፍ እና ማህበረሰብ ላይ ላሉ ተግዳሮቶች በፈጠራ የተሞላ መፍትሄ የሚሰጡ ባለሙያዎችን ለማውጣት ያለመ ነው፡፡
ከጥቅምት 16 አንስቶ ለስድስት ወራት በሚቆየው ዝግጅት ተሳታፊዎች እንደ ሴስተም ሶፍትዌር፣ የስልክ መተግበሪያ፣ በዌብ ፕሮዳክቶች ዲዛይን እና ማበልጸግ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡
ከአውሮፓውያኑ 2018 በኋላ ከታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ አልያም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ መሆን አለባቸው፡-
computer science, information technology, information science, software engineering, computer engineering, data science, architecture, interior designer, educational planning and management (or Educational Policy and Strategic Management or Curriculum and Instruction), Multimedia Developer (audio visual).
ምዝገባ፡- አመልካቾች ከዛሬ ጥቅምት 4 2013 አንስቶ እስከ እሁድ ጥቅምት 8 ድረስ በድረ ገፃችን www.techin.gov.et/announcement ላይ ብቻ በመሄድ ፎርሙን መሙላት እና ከ2 ገፅ ያልበነለጠ ሲቪ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የተመረጡ አመልካቾች ብቻ በኢሜል አድራሻቸው መልዕክት እና ሌሎች ስራዎች የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት በዚህ ሊንክ ( http://techin.gov.et/post/345/ ) አማካኝነት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ያልዎትን ማንኛውም አይነት ጥያቄ በኢ-ሜይል አድራሻችን internship@techin.gov.et ተጠቅመው ሊያደርሱን ይችላሉ፡፡
ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
የእይታ ትኩረትን (focus) ማስተካከል የሚችለው መነጽር
******************************
የሰው ልጅ እድሜ እየጨመረ በሔደ ቁጥር መደበኛ ስራቸውን መስራት እየተሳናቸው የሚሔዱ የሰውነት ክፍሎች መኖራቸው ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ከእነዚህ የሰውነት ክፍሎች መካከል አይናችን በቅርበትም ሆነ በርቀት የማየት ችግር በብዛት ያጋጥመዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ወደ ሐኪም ሔደን ለአይናችን ችግር መፍትሔ ሊሆን የሚችል የአይን መነጽር ይታዘዝልናል፡፡ እዚህ ላይ ያለው ችግር በትእዛዝ የምንገዛቸው መነጽሮች ለአንድ ተግባር ብቻ የሚውሉና ዋጋቸውም በጣም ውድ መሆኑ ነው፡፡ በሐኪም ያልታዘዘ ወይም በህክምና ያልተረጋገጠ መነጽር መጠቀም ከሚሰጠው ጥቅም የሚያስከትለው ጉዳት ይበልጣል፡፡
በአይን ህክምና ረገድ በአለማችን ብዙ አዳዲስ ነገሮች ያሉ ሲሆን የተጠቃሚውን የማየት ፍላጎት ተከትሎ የእይታ ትኩረት (focus) የሚያስተካክል መነጽር አንደኛው ነው፡፡ በእስራኤሉ Deep Optics የቴክኖሎጂ ተቋም የተመረተው ይህ የአይን መነጽር ምንም አይነት ብዥታ እንዳኖር ማድረግ የሚችል ነው፡፡
መነጽሩ የተገጠመለት ሙሉ እይታ "liquid crystal" lens በኤሌክትሪካዊ መንገድ ከሴንሰሩ ወደ ፕሮሰሰሩ በሚላክ መረጃ የእታን ትኩረት (view focus) ወዲያውኑ ያስተካክላል፡፡ በዚህም ምክንያት ተጠቃሚው ከቅርብም ሆነ ከሩቅ ማየት የሚፈልገውን ማንኛውንም ነገር በግልጽ መመልከት እንዲችል ያደርገዋል፡፡ 'omnifocals' የተባለው የካምፓኒው ምርት በቅርብ ያሉ ነገሮችን የማየት ችግር (presbyopia) ለመቅረፍ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡

ምንጭ: www.howstuffworks.com
TECHIN seminar
==========
TECHIN seminar will be back next week, at TECHIN hall (Located in our head office behind Lycée Guebre-Mariam School). For this session Dr. Eyobel Mulugeta will discuss improvement of Enjera shelf life through the use of Ag and ZnO nano particles.
Starting time: 9:30 AM
ትምህርትና ቅድመ ጥንቃቄ
***********************
ባለፈው ዓመት መጋቢት የሆነ ቀን ህጻናት ትምህርት ቤት ክፍላቸው ውስጥ ነበሩ፡፡ በሌላኛው ቀን ግን ያልተጠበቀ ዱብእዳ መጣና ትምህር ቤቶች ተዘጉ፡፡ ያ ተማሪዎች እንደዋዛ ጥለውት የወጡት ክፍል አሁን ምንም እንኳን ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ባይቻልም ህይወት መቀጠል አለበትና ዳግም ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡
በክፍል ውስጥ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል መጠቀም በመማሪያ ክፍል ውስጥ አየር በብዛት እንዳይንቀሳቀስ ያደርገዋል፡፡ ይህም የተማሪዎቹን በቫይረሱ የመያዝ እድል በተወሰነ መልኩ ይቀንሰዋል፡፡ አካላዊ ርቀትን መጠበቅና ጭንብል መልበስ እንዳለ ሆኖ ሊደረጉ የሚገባቸውን ወሳኝ ጥንቃቄዎች ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡
1ኛ. በቂ አየር (ventilation)
አሁን ባለው ሁኔታ በአንድ ክፍል ውስጥ ከ20-25 ተማሪዎችን 2 ሜትር ያክል አራርቆ ማስቀመጥ እና ማስተማር የሚያስችል የመማሪያ ክፍል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በመሆኑም በክፍል ውስጥ በቂ አየር እንዲዎጣ እና እንዲገባ አስፈላጊው ዝግጅት መደረግ አለበት፡፡ ይህም ሲባል የመማሪ ክፍሉ በርና መስኮቶች አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸውን ማረጋገጥና ጥብቅ በሆነ መመሪያ መከፈት ያለባቸው ተከፍተው ክፍሉ ንጹህ አየር የሚንቀሳቀስበት መሆን አለበት፡፡ ተማሪዎቹ የለበሱትን ጭንብል በየጊዜው እያወለቁ እንዳይቸገሩ ያደርጋቸዋል፡፡
2ኛ. የግቢና የክፍል ውስጥ ጥብቅ ዲሲፕሊን
በተለይ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች አካላዊ ርቀትን በመጠበቅና ጭምብል በአግባቡ በመልበስ በኩል ሊቸገሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ አንጻር መጀመሪያ ሊነሳ የሚችለው በእረፍት ላይ በነበሩበት ወቅት በቤት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ጭምብል የመልበስ ልምድ ስለማይኖራቸው በአግባቡ ላይጠቀሙት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም አካል ራሱ መመሪውን በአግባቡ ተግብሮ ተማሪዎች እንዲተገብሩት ማድረግ የህይወትና የሞት ጉዳይ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ በተቻለ መጠን በአመቱ ውስጥ ትልቁ የትምህርት ቤቶች ስራ ተማሪዎችና መምህራን ጤናቸው እንደተጠበቀ የመማር ማስተማር ስራውን ማስቀጠል ሊሆን ይገባዋል፡፡
3ኛ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት
በዚህ ወቅት በተማሪዎች አእምሮ ውስጥ ከሚርመሰመሱ ሀሳቦች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የወረርሽኙ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም በቀጥታ በተማሪዎቹ ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ስለዚህ ወላጆችና መምህራን ተማሪዎች ጥንቃቄ ከማድረግ ባለፈ መጨነቅ እንደማይገባቸው እና ሙሉ ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ እንዲያደርጉ የምክር አገልግሎት በየጊዜው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ውስጥ ከላይ የተዘረዘሩ ጥንቃቄዎች በትኩረት ሁላችንም መተግበር ከቻልን ወረርሽኙ ተስፋፍቶ ዳግም ትምህርት ቤቶች እንዳይዘጉና ተማሪዎቻችን ለሌላ ጭንቀት እንዳዳረጉ መጠበቅ እንችላለን፡፡