አዳዲስና ጠቃሚ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዱ ድረገጾች
*****************************************
እነዚህ ድረ-ገጾች በአለማችን በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡
1. TechCrunch
2. Gizmodo
3. TechHive
4. CB Insights
5. Cord Cutters News
6. MakeUseOf
7. Life Hacker
8. Computerworld
9. How to Geek
10. Pymnts.com

ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ግለሰቦች የተለያዩ ጥቅሞች ለማግኘት ሲሉ የሃሰት አካውንት በመክፈት ድብቅ አጀንዳቸውን ሲያራምዱ ማስተዋል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ተከታይ በሚኖራቸው የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ላይ እጅግ ጎልቶ ይታያል፡፡አብዛኞቹ እነዚህ ያልተረጋገጡ የሚዲያ ምንጮች ለገቢያቸው መደለብ ሲሉ ብቻ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ ብዙዎችን ለአደጋ ማጋለጣቸው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል፡፡
ያልተረጋገጡ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች የኮሮናቫይረስን የመከላከል ስራ ካባድ እድርገውታል
==============
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም እነዚህ የተሳሳቱ የመረጃ ቅብብሎች ከመቼውም ጊዜ ባላይ እየጨመሩ የመጡ ሲሆን በዚህ ጉዳይ የተሰሩ አብዛኞቹ ጥናቶችም ከወረርሽኙ እኩል ህዝቡን እያሸበሩት የሚገኙት ጉዳዮች እነዚሁ ያልተረጋገጡ የመረጃ ምንጮች እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ ከሰሞኑ በእንግሊዝ የተደረገው ተመሳሳይ ጥናት እንዳመለከተውካልተረጋገጡ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚገኙ ዘገባዎችን ዋና የመረጃ ምንጫቸው ያደረጉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሴራ ትንተና (conspiracy) የበዛባቸውን መረጃዎች በይበልጥ እያመኑ መምጣታቸውንና በዚህም የተለያዩ የመንግስታትን የጤና መመሪያዎች እየጣሱ እንደሚገኝ በጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡
በእንግሊዝ መቀመጫቸውን ባደረጉ ኪንግ ኮሌጅ እና Ipsos Mori የምርምር ማዕከል የተሰራው ይህ የዳሰሳ ጥናት በጥቅሉ 2,000 ሰዎችን በጥናቱ አሳትፎ የተለያዩ መጠይቆችን ለተሳታፊዎቹ አቅርቦ ነበር፡፡ይህ የምርምር ቡድን ካቀረባቸው መጠይቆች መካከል የኮሮናቫይረስ በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረ ነው የሚለው እንደኛው ጥያቄ ሲሆን ከተሳታፊዎቹ 30 በመቶ የሚሆኑት በዚህ የሴራ ትንተና የሚያምኑ እና በዚህም የተነሳ እርምጃዎችን እየጣሱ እንደሚገኝ በጥናቱ ታይቷል፡፡ ከዚህ ባለፈ በጥናቱ እንደተገለፀው ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው የጥናቱ ተሳታፊዎች በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥራቸው እንዳይታወቅ መንግስታት ይደብቃሉ የሚለውን መጠይቅ በስፋት እንደሚያምኑ በጥናቱ ተዳሷል፡፡
13 በመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ወረርሽኙ የአለም ሰዎችን በክትባት ለመቆጣጠር የተዘየደ ሴራ ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን፤ 8 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ደግሞ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች በአንድም ይሁን በሌላ ከ5G ራዲዬሽን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ በዚህ የዳሰሳ ጥናቱ ለመታዘብ እንደተቻለው ብዙ ሰዎች መሰል የኮኒስፓይሪሲ ዘገባዎችን በስፋት እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ይፋዊ የጤና ምክሮችን የሚያገኙበት የመረጃ ምንጭ ከመፈለግ ይልቅ ብዙ ያልታመኑ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ዋና የመረጃ ምንጭ በማድረጋቸው ነው፡፡ በተለይም ከፌስቡክ እና ከዩቲዩብ የሚገኙ ያልታመኑ የመረጃ ምንጮች ለእነዚሁ የተዛቡ የኮኒስፓይሪሲ ዘገባዎች ዋና መደላድል ናቸው፡፡
ወረርሽኙን ከመከላከል እኩል መረጃዎች የሚሰራጩበትን ሁኔታ በሚገባ መከታተል ያስፈልጋል የሚሉት የጥናቱ ዋና መሪ ዶ/ር ዳንኤል አሊንግቶን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎችን እና ሌሎች እርምጃዎችን በምናስተላልፍበት መጠን ግልፅና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን ለሰዎች እንዲደርስ ማድረግ ቀዳሚ ስራ ሊሆን ይገባል ይላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እንደ ቲቪ እና ራዲዮ ያሉ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ትልቅ ሚና የሚኖራቸው ቢሆንም ወጣቱ የሚመርጣቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለአደጋው መባባበስ ትልቅ እድል እንደሚፈጥሩ በጥናቱ ተዳሷል፡፡ ለምሳሌ በዚህ እይታ በጥናቱ ከተሳተፉ አጠቃላይ ሰዎች 45 በመቶ (ብዙዎቹ ከ16 እስከ 24 እድሜ) የሚሆኑት ዋና የመረጃ ምንጫቸው ያልታመኑ ዩቲዩብ ቻናሎች ሲሆን፤ ሌሎች 40 በመቶውን የሚሸፍኑት ደግሞ (ብዙዎቹ ከ30 በታች) ዋና የመረጃ ምንጫቸው ከፌስቡክ እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

የኮሮናቫይረስ ለ9 ሰዓታት በሰዎች ቆዳ ላይ ይቆያል
==========================
ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት የሆነው SARS-CoV-2 ቫይረስ በሰዎች ቆዳ ላይ ካረፈ በኋላ ለዘጠኝ ሰዓታት በህይወት የመቆየት አቅም እንዳለው በጃፓን የተሰራ አንድ ጥናት ጠቁሟል፡፡ ጥናቱ የኮሮናቫይረስ ቆይታን ከጉንፋን (IAV) ቫይረስ ጋር ለማነፃፅር የሞከረ ሲሆን፤ በውጤቱም ኢንፍሉዌዛ ቫይረስ በሰባት ሰዓታት በማነስ በቆዳችን ላይ ለሁሉት ሰዓት እንደሚቆይ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡
ይህ ጥናት ለማሳየት እንደሞከረው SARS-CoV-2 ቫይረስ በቆዳ ላይ ለረዥም ሰዓት መቆየት በመቻሉ ከ (IAV) ቫይረስ በላይ በቀጥታ በንክኪ የመተላለፍ አቅሙ እጅግ ከፍተኛ እንዲሆን እና የመዛመት አቅሙም እጅግ የሰፋ አንዲሆን ትልቅ ምክንያት ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም በወረርሽኙ መከሰቻ ሰሞን በተደረጉ ተያያዥ ጥናቶች የኮሮናቫይረስ በተለያዩ እቃዎች ላይ በሚያርፍብት ጊዜ እንደእቃዎቹ አይነት የቫይረሱም የመቆየት አቅም እጅግ እንደሚለያይ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ በአሜሪካ በተደረጉ ጥናቶች ቫይረሱ እንደመዳብ ባሉ ቁሶች ላይ ለአራት ሰዓት የመቆየት አቅም ሲኖረው እንደካርቶን እና ፕላስቲክ ባሉ ቁሶች ላይ ደግሞ ከ24 ሰዓት እስከ 72 ሰዓት የመቆየት አቅም እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡ እነዚህ ጥናቶች የቫይረሱ ቆይታ በቁሶች ላይ ምን እንደሚመስል የሚያሳዩ ቢሆንም በስነ ምግባር ምክንያቶች የተነሳ ቫይረሱ በሰዎች ቆዳ ላይ ለምንያህ ጊዜ እንደሚቆይ የሚያሳዩ ጥናቶች ሊከናወኑ አልቻሉም ነበር፡፡
ይሁንና በዚህ አዲስ ጥናት ተመራማሪዎች ከሬሳ ምርመራ የተገኘ የሰው ቆዳ እንደናሙና በመጠቀም አዲስ የቆዳ ሞዴል መፍጠር የቻሉ ሲሆን፤ በዚሁ ሞዴል አማካኝነትም ቫይረሱን በቆዳው ላይ በማድረግ SARS-CoV-2 ለምን ያህል ጊዜ በህይወት መቆየት ወይም መትረፍ እንደሚችል ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ በዚህም የኮሮናቫይረስ በሰው ቆዳ ላይ ለ9.04 ሰዓታት መቆየት ወይም መትረፍ እንደሚችል የተረጋገጠ ሲሆን ኢንፍሉዌዛ ኤ ቫይረስ ደግሞ ለ1.82 ሰዓት በህይወት መቆየት እንደሚችል ታውቋል፡፡
ተመራማሪዎች ከጥናቱ እንደተረዱት ሰዎች በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ ከእነሱ የሚወጣው mucus ወይም ንፋጭ ከኮሮናቫይረስ ጋር በሚቀላቀልበት ጊዜ የቫይረሱ የሞቆያ ጊዜ ወደ 11 ሰዓት ሊጨምር እንደሚችል አረጋግጠዋል፡፡ በዚህ ጥናት እንደታየው ሰዎች ለ15 ሰኮንድ እጆቻቸውን በሳሙና በሚገባ ከታጠቡ እና 80% ኢታኖል የታከለበት የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘር ከተጠቀሙ ቫይረሱን ከመቅፅበት ማጥፋት እንደሚችሉም በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡
ምንጭ፡ Live Science

Create
Technology and Innovation Institute, Ethiopia
20m ·
ነዳጅን በፀሐይ ሐይል መተካት
***************************
በምድራችን ብዙ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮች ቢኖሩም የከባቢ አየር ለውጥ ግን እጅግ በጣም አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ እና ከተፈጥሮ ጋር ለመታረቅ በሌላ ጽሁፋችን በግለሰብ ደረጃ ማድረግ የምንችላቸውን ነገሮች አስነብበናችሁ ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በአለማችን በቴክኖሎጂ ዘርፍ ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነና የነዳጅ ወጪን ሊቀንስ የሚችል ፈጠራን እናስተዋውቃችኋለን፡፡
ከተፈጥሮ ጋር ተስማሚ ከሆኑ የሀይል ምንጮች መካከል ኤሌክትሪክ፣ የፀሐይ ሐይልና የነፋስ ሐይልን መጥቀስ ይቻላል፡፡ የከባድ ተሸከርካሪዎች አምራች የሆነው ስካኒያ በፀሐይ ሐይል የሚታገዙ ባለ ረጅም ሽንጥ ተሸከርካሪዎችን ለማምረት በሙከራ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት ይህን ቴክኖሎጂ በHyundai’s Sonata Hybrid መኪና ላይ የተሞከረ ቢሆንም መኪናው መጠኑ ትንሽ በመሆኑ የተነሳ በቂ ሐይል ማመንጨት አልተቻለም ነበር፡፡ የስካኒያ ከባድ መኪኖችም ተመራጭ የሆኑት ሰፋፊ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፎችን (Solar panels) መያዝ ስለሚችሉ ነው፡፡
የቮልስ ዋገን አካል የሆነው ስካኒያ የተባለው የመኪና አምራች ድርጅትም 1507 ስኩየር ጫማ የሚሆን የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፍ (Solar panel) በአንዱ ምርቱ ላይ ገጥሟል፡፡ የዚህ ስራ አላማ የፀሐይ ሐይልን በመጠቀም ምን ያክል ነዳጅ መቆጠብ እንደሚቻል ለመፈተሸ ነው፡፡ ሙከራው የሚሳካ ከሆነ በመኪና ቴክኖሎጂ ላይ አንድ ሌላ ተጨማሪ እድገት ይሆናል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኤሌክትሪክ ሐይል የሚሰሩ መኪኖችን ማየት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሌላው አማራጭ ነፋስ ነው እሱንም የማየት እድላችን እሩቅ አይሆንም፡፡
ምንጭ፡ Engadget

የድምጽ ፍጥነት ከፍተኛው ልኬት (The Upper Limit of speed of sound)
********************************
Special Relativity እየተባለ የሚጠራው የአልበርት አንስታይን መላምት ብርሀን በወና ውስጥ ሲያልፍ የሚኖረውን የፍጥነት ጥግ speed limit እንድናውቅ አድርጎናል፡፡ ነገር ግን በማንኛውም አካል ላይ ያለ ትክክለኛውን ከፍተኛ የብርሀን ፍጥነት ማዎቅ አልተቻለም፡፡ በእያንዳንዱ ነገር ላይ ያለውን የድምጽን ፍጥነት መለካት እጅግ አስቸጋሪ ነገር ቢሆንም የፊዚክስ ተመራማሪዎች ከፍተኛውን የድምጽ ፍጥነት ልኬት ማግኘት ችለዋል፡፡
በአዲሱ ቀመር መሰረት የፍጥነት ጥጉ በሴኮንድ 36 ኪሎ ሜትሮች ያክል ሆኗል፡፡ ይህም ድምጽ በዳይመንድ ሲያልፍ ካለው ፍጥነት ሁለት እጥፍ ማለት ነው፡፡ ድምጽና ብርሀን እንቅስቃሴያቸው በሞገድ መልኩ ቢሆንም የተወሰነ ልዩነት አላቸው፡፡ ክሱት የሆነው ብርሀን (Visible light) በኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር መልክ ይጓዛል፡፡ እነዚህ ኤሌክትሪካዊና መግነጢሳዊ መንገዶች ብርሀንን በወና ውስጥ በሴኮንድ 300,000 ኪሎ ሜትር እንዲጓዝ ያደርጉታል፡፡ ብርሀን በውሃና በከባቢ አየር ውስጥ ሲጓዝ ፍጥነቱ ይቀንሳል፡፡
ድምጽ በርግብግቦሽ የሚፈጠር ሜካኒካዊ ሞገድ ነው፡፡ የድምጽ ማስተላለፊያው ቅንታቶች ጥግግት በጨመረ ቁጥር የድምጽ ሞገድ ፍጥነትም ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ፍጥነት ከጋዝ በውሃ ሲጨምር ከውሃ ደግሞ በጠጣር ይጨምራል፡፡
ይህንን ጥናት የእንግሊዞቹ ኩይን ሜሪ ዩኒቨርስቲ እና ካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ በጋራ የሰሩት ሲሆን በሩሲያ የሚገኘው ሃይ ፕሬዠር ፊዚክስ ኢኒስቲትዩትም እንዲሁ ታሳትፎበታል፡፡
ምንጭ፡ Science Alert

ጥርስ እና አጥንት፤ ምን ለያቸው?
============
ጥርስም ሆነ አጥንት የተላበሱት ጥንካሬ እና ንጣት ብሎም በካልሺየም መበፀጋቸው የጋራ የሚያደርጉ መገለጫዎቻቸው ቢሆኑም አንድ ግን አያደርጓቸውም፡፡ ከገፅታቸው አንስቶ እራሳቸውን ማከሚያ መንገዳቸው አጥንቶቻችን ሰውነታችንን ከተሸከሙት አጥንቶች ይለያሉ፡፡
ጥርሶቻችን ካልሺየም፣ ፎስፈረስ፣ ሶዲየም እና ሌሎች ንጥረ ነገሮችን አቅፎው የያዙ ናቸው፡፡ አጥንቶቻችን ግን በዋናነት የተገነቡት በኮላጅን ፕሮቲን ነው፡፡ ኮላጅን ህይወት ያለውና እድገት የሚያሳይ ህብረ-ህዋስ ሲሆን ለአጥንቶቻችንም ግፊትን ለመቋቋም የሚያስችላቸውን ተለማጭነት የሚያጎናጽፍ ነው፡፡ ካልሺየም በበኩሉ በዚህ በተፈጠረ መዋቅር ዙርያ በሚገኘው ስፍራ በመሄድ አጥንቶታችን ጠንካራ እና የሰውነት ክብደታችንን መቋቋም እንዲችሉ የማድረግ ድርሻውን ይወጣል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን አጥንቶቻችን ከጥርሶቻችን የሚስተካከል ጥንካሬ የላቸውም፡፡ በሰውነታችን ከሚገኙ ማንኛውም ክፍሎች በላቀ ጠንካራ የሆነው ጥርሳችን በዋናነት ዴንታይን የተባለውን በካልሺየም ጨው የበለፀገ ህብረ-ህዋስ የተሞላ ነው፡፡ የጥርሳችንን ዴንታይል ህብረ-ህዋስ ኤናሜል በተባለው ጠንካራ እና አብለጭላጭ ምንጣፍ ከላይ ተሸፍኗል፡፡
አብዛኛው የአጥንቶቻችን የውጭ ክፍል ፔሪዎሴየም በተባለ ጠንካር ግን ለስላሳና አንሸራታች በሆነ በሆነ ሜምብሬን የተሞላ ነው፤ በበአሙለጭላጩ ሃይላይን ካርትሌጅ ከተሞሉት የረጃጅም አጥንቶች መገጣጠሚያ ውጪ፡፡ ፔሪዎሴየም አዲስ አጥንትን በሚጠግኑ እና እንደ አዲስ በሚፈጥሩት የኦሲዮብላስት ህዋሳት የተሞላ ነው፡፡
ከአጥንት በተለየ ጥርሶቻችን እራሳቸውን ዳግም የመተካት ብቃት የላቸውም፡፡ ጥርሶቻችን እራሳቸውን ማከም እና ከተሰበሩም ዳግም አድገው ወደነበሩበት መመለስ አይችሉም፡፡ አንድ አጥንት በሚሰነጠቅበት ሰዓት አዳዲስ የአጥንት ህዋሳት ክፍተቱን ለመሙላት እና ለመጠገን ፈጥነው ወደስፍራው ይነጉዳሉ፡፡ ሆኖም የተሰበረ ወይም የተሰነጠቀ ጥርስ ግን ህክምና ሊያስፈልገው ይችላል፡፡
ሌላኛው በሁለቱ የሰውነት አካላቻችን መካከል ያለው ልዩነት፤ አጥንቶቻችን በውስጣቸው ባሉ አካላት አማካኝነት ቀይ እና ነጭ የደም ህዋሳትን ሲያመርቱ ጥርሶቻችን ግን ይህን ለማድረግ አለመታደላቸው ነው፡፡ አጥንቶቻችን የደም ፍላጎታቸውን ከውስጥ እስከ ፔሪዎሴየማቸው ከሚያልፉት በርካታ የደም ቧንቧዎች ያሟላሉ፡፡
ወደ ጥርሶቻችን ስንመለስ የወለቀ ጥርስ ቦታ ላይ ምናገኘው አካል አነስተኛ መስሎ ሊታየን ይችላል፡፡ ሆኖም ይህ ክፍል ዴንታል ፐልፕ ተብሎ የሚጠራው ህይወት ያለው የእያንዳንዱ ጥርሶቻችን ክፍል ሲሆን፤ በአገጭ አጥንቶቻችን ውስጥ የተዘረጉትን ነርቭ እና የደም ቧንቧዎች የያዘ ነው፡፡ በተቦረቦሩ ጊዜ ወይም ቀዝቃዛም ሆነ ሙቅ ነገሮችን ስንመገብ ህመምን የሚፈጥሩብንም እነዚህ ነርቮቻችን ናቸው፡፡

የኮሮናቫይረስ ለ28 ቀናት በስልኮቻችን መስታዎት ላይ ሊቆይ ይችላል
የብሄራዊ ሳይንስ ኤጄንሲ (CSIRO) በአውስታራሊያ የበሽታ ዝግጁነት ማዕከል (ACDP) አደረኩት ባላው ጥናት ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ምክንያት የሆነው SARS-CoV-2 ቫይረስ በአንዳንድ የቁሶች ገፅ (surfaces) ላይ ለ28 ቀናት መቆየት እና መትረፍ እንደሚችል በጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡ ተመራማሪዎች በዚህ ጥናት እንደጠቆሙት የኮሮናቫይረስ በስልካችን የመስታዎት እስክሪኖች፣ በማይዝጉ ብረቶች (stainless steel)፣ በሸክላ ዲስኮች እና በወረቀት የባንክ ኖቶች ላይ ለ28 ቀናት በህይወት የመቆየት አቅም እንዳለው ይፋ አድርገዋል፡፡
ተመራማሪዎች በዚህ ጥናት ላይ ለመረዳት እንደቻሉት SARS-CoV-2 ቫይረስ በፕላስቲክ ከሚሰሩ የገንዘብ ኖቶች በላይ በወረቀት የባንክ ኖቶች ላይ ለረዥም ጊዜ የመቆየት አቅም ሲኖረው ፈሳሽ ከሚያሳልፉ እንደጥጥ ካሉ ቁሶች በላይ ደግሞ በደረቅ ለስላሳ ቁሶች ላይ ለረዥም ጊዜ መቆየት እንደሚችል አስረድተዋል፡፡ ምርምሩ የአልትራቫዮሌት ወይም (UV light) ብርሃኖችን ውጤታማነት ለመቀነስ ሲባል በጨለማ ቦታ ላይ መከናወኑን የሚያስረዱት የአውስታራሊያ ብሄራዊ ዩኒቨርስቲ ተላላፊ በሽታዎች ፕሮፌሰር ፒተር ኮሊኒዮን ይህ ድርጊት ቫይረሱ በወለሎች ላይ የመቆየት አቅሙን ይቀንሰዋል ይላሉ፡፡
ቫይረሱ ሰፊ የወለል መዳረሻ ባላቸው ቁሶች እና ስፍራዎች ላይ በንክኪ የመተላለፍ ሁኔታው ምን ያህል ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ቢሆንም ከዚህ ጥናት ለመረዳት እንደተቻለው SARS-CoV-2 ቫይረስ ሞቃታማ ከሆኑ አካባቢዎች ይልቅ ዝቅተኛ የሙቀት ሁኔታዎች ባሉባቸው ቦታዎች ላይ ይበልጥ የመቆየት አቅም እንዳለው ለማየት ተችሏል፡፡
ተመራማሪዎች በጥናት እንደጠቆሙት የኮሮናቫይረስ ለዚንያህል ቀናት በቁሶች ላይ የመቆየት አቅም ቢኖረውም ሰዎች ቫይረሱን በንክኪ የማግኘታቸው ሁኔታ በሌሎች ከሚተላለፍባቸው አንፃር ሲታይ እጅግ የሰፋ ልዩነት ይታይበታል፡፡ ፕሮፌሰር ኮሊኒዮን እንደሚያስረዱትም 90 በመቶው የኮቪድ 19 መተላለፊያ መንገድ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በሚኖራቸው የቀረበ ንክኪ እና ከአፋቸው በሚወጡ ጥቃቅን የትንፋሽ ብናኞች ሊሆን እንደሚችልም በጥናቱ ላይ አስረድተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ እጃችን የተለያዩ ቁሶችን በመንካት የሚኖረው የቫይረስ የመተላለፍ ሁኔታ ከአስር በመቶ የሚሻገር አለመሆኑን በልበ ሙሉነት ይገልፃሉ፡፡
ቫይረሱ በእጅ ንክኪ ሊተላለፍ ከመቻሉ አንጻር ፊታችንን ከመንካታችን በፊት ሁልግዜም እጆቻችንን በሳሙና መታጠብ ከቻልን በሽታውን ሙሉ ለሙሉ ወደ እኛ እንዳይደርስ ማድረግ እንደሚቻልም ፕሮፌሰሩ ይናገራሉ፡፡
ጥናቱ በትክክል እንዳስቀመጠው 20 ዲግሪ ሴልሺየስ የሙቀት ልኬት ባለባቸው አካባቢዎች የቫይረሱ መትረፍ አቅም እጅግ ከፍተኛ ሆኖ የተገኘ ሲሆን ለስላሳ ገፅ ባለቻው እንደ ስልክ ስክሪን ያሉ ቁሶች ላይ ደግሞ ለ28 ቀናት በሚገባ ሊቆይ ይችላል፡፡ ከዚህ ባለፈ የሙቀት ልኬታቸው 30 እና 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚገመት አካባቢዎች የቫይረሱ የመትረፉ ሁኔታ እጅግ እየቀነሰ የሚመጣ ሲሆን ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ያለባቸው አካባቢዎች ግን ለቫይረሱ የተመቹ ቦታዎች ናቸው፡፡
ምንጭ፡ The Guardian

ስፓርክ ሜከር 3ዲ ማተሚያ ማሽን
====
3ዲ ማተሚያ ማሽን የሰው ልጅ ህይወቱን ለማቅለል በሚያደርገው ረዥም ጉዞ ውስጥ ትልቅ እርምጃን ያራምዳል የተባለለት ወሳኝ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው፡፡ ይህ ማሽን በታሪክ ለመጀመሪ ጊዜ እ.ኤ.ኣ በ 1984 ዓ.ም የተዋወቀ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እተሻሻለ እና እያደገ መምጣቱም ይታወቃል፡፡
መሳሪያው በ ዲዛይን ደረጃ ወረቀት ላይ የነበሩ ስዕሎችን ሊዳሰስ ወደሚችል ግዑዝ አካልነት መቀየር የሚችል ነው፡፡ ወደ መሳሪያው የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ካስገባን በኋላ በዲዛይኑ መሰረት 3ዲ ቁሶችን ይወልድልናል፡፡ ይህ አብዛኃኛውን ጊዜ ትልልቅ ፋበሪካዎችን የሚያገለግል የማሽን ዓይነት ነው፡፡
ይሁንና ስፓርክ ሜከር (spark maker) ተብሎ የሚጠራው ይህ የ 3ዲ ማተሚያ ማሽን ዋና ዓላማው በዝቅተኛ ስኬል ህትመቶችን በማውጣት የ3ዲ ማተሚያ መሳሪያ የእያንዳንዳችንን ደጃፍ እንዲያንኳኳ ማድረግ ነው፡፡ ስፓርክ ሜከር በ መጠን አነስተኛ ሲሆን በካንፓኒው ከተሰራው ስፓርክ ሰቱዲዮ ከተሰኘው ሶፍት ዌር ውስጥ ማንኛውንም ዲዛይን መመምረጥ አሊያም የራሳችንን ዲዛይን በሶፍት ዌሩ ላይ መስራት የሚያስችለን ነው፡፡
በዚህ ማሽን አማካኝንት ፋይሉን ከኮምፒውተራችን በሚሞሪ በመውሰድ እና እርሱ ላይ በመሰካት ያሻንን ቅርፅ በግል ጥረታችን እንድናመርት የሚያስችል መሳሪያ ነው፡፡ ይህ ማሽን ለግብዓትነት የሚውሉ 5 የተለያዩ ፈሳሾችን የያዘ ሲሆን በርከት ያሉ የቀለም ምርጫዎችም አሉት፡፡ በተለይ ለህፃናት ጥሩ መማሪያ እና መዝናኛ ሊሆን ይችላል ተብሎም ይገመታል፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ ልዩ እና ዘመናዊ ቢሆንም ምናልባት የግለሰቦችን የፈጠራ ችሎታን ይገድብ ይሆን የሚለው ጥያቄ ለመጪው ጊዜ የሚተው ይሆናል፡፡
ምንጭ: Tech Virial

አንድ ሰው በኮቪድ 2ኛ ጊዜ ሊጠቃ ይችላል?
****************************
በአሁኑ ሰዓት በአለማችን የኮቪድ ተጠቂዎች ቁጥር ከ37.6 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡ ምንም እንኳን የተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ ቢሔድም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከህመሙ እያገገሙ ነው፡፡ ወረርሽኙ ከተከሰተ ከወራት በኋላ ተመራማሪዎችንና መንግስታትን ሲያስጨንቅ የነበረው የወረርሽኙ ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር መከሰት ነበር፡፡ ይህም ወረርሽኙ በቁጥጥር ስር የመዋል አዝማሚያ ካሳየ በኋላ ዳግም እንደገና መስፋፋት ነው፡፡ እንደተፈራውም በአንዳንድ የአለማችን ከተሞች ይህ ችግር መከሰቱ አልቀረም፡፡ ከዳግም ወረርሽኝ በተጨማሪ ሌላው ጥናት ሲደረግበት የነበረው ነገር አንድ ሰው በበሽታው ተይዞ ካገገመ በኋላ ዳግመኛ በቫረሱ ይጠቃል ወይስ አይጠቃም የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
በቅርብ ጊዜ የወጡ ዘገባዎች ደግሞ በሆንግ ኮንግ፣ ቤልጀም፣ ኔዘርላንድና ኢኳዶር ሰዎች ለሁለተኛ ጊዜ በቫይረሱ የተጠቁ ቢሆንም ከባድ የሚባል ህመም ግን አልታየባቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች በሽታ የመከላከል ብቃታቸው በመጀመሪያው ዙር ስለተነቃቃ ሁለተኛውን ዙር ህመም በቀላሉ መቋቋም ችለዋል፡፡
ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ በአሜሪካ ለሁለተኛ ጊዜ በበሽታው የተጠቃ አንድ የ25 ዓመት ጎልማሳ የታየበት ከፍተኛ ህመም ተመራማሪዎችን እያከራከረ ይገኛል፡፡
ታማሚውን የሚከታተለው የናቫዳ ዩኒቨርስቲ ስለ ሁኔው የተለያዩ ማብራሪያዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡ የመጀመሪያው ማብራሪያ ታማሚው በሁለተኛው ዙር ከፍተኛ መጠን ያለው የቫይረስ ቁጥር ወደ ሰውነቱ ገብቷል የሚል ነው፡፡ ሌላው ደግሞ ታማሚው antibody dependent enhancement (ADE) የሚባለው ያልተለመደ የበሽታ መከላከል አቅም በሽታን የማባባስ ክስተት ነው፡፡ የዚህ አይነቱ ችግር በ2003 በሌላኛው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳርስ ጊዜ አጋጥሞ እንደነበር ተመራማሪዎቹ አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር መካከል ያለው ጊዜ ተቀራራቢ መሆን አንዱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የያሌ ዩኒቨርሲቲ ኢሚዩኖባዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆነችው Akiko Iwasaki ክስተቱ (reinfection) በወረርሽኞች ዙሪያ የሚሰሩ ጥናቶችን የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሰሯ አክለውም በሁኔታው ወረርሽኞችን ለመከላከል በሰዎች ተፈጥሯዊ በሽታ የመከላከል ብቃት ላይ ብቻ መደገፍ እንደሌለብን ተረድተናል ብለዋል፡፡
ምንጭ፡ Financial Times

የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ ስንል ምን ማለታችን ነው?
አብዛኛውን ጊዜ እንደምንሰማው የአዕምሮ ጤና ሲነሳ ሰዎች ላይ ተደጋግሞ የሚታየው የድብርት እና የጭንቀት ሁኔታዎች አልያም ደግሞ ራስን የመሳትና የማጠት ሁኔታዎች ቀድመው ወደሃሳባችን ይመጣሉ፡፡ ይሁንና የአዕምሮን ጤና በትክክል ለመግለፅ ከሞከርን የሰዎችን ስሜታዊ፣ ስነልቦናዊ እና ማህበራዊ ደህንነትን በአንድነት ማንሳት ግድ ይለናል፡፡ የአዕምሮ ጤና በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የሚሰማንን የድብርት እና የጭንቀት ስሜቶች ብቻ የምንገልፅበት ተራ ፅንሰ-ሃሳብ ሳይሆን እንዴት ማሰብና ማድረግ እንዳለብን፣ ዓለምን በምን መነፅር መመልከት እንደሚኖርብን እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ስናልፍ የትኞቹን ውሳኔዎች ማሳለፍ እንደሚገባን የሚያመላክት እና በሁሉም ነገሮች ላይ እኛነታችን የሚገለፅበት የማንነታችን ቁልፍ ነው፡፡
የአዕምሯችን ደህንነት በእያንዳንዷ የህይወታችን እንቅስቃሴ፣ በሚኖረን ማህበራዊ ግንኙነት፣ በአካለዊ ጤንነታችን እና መሰረታዊ ፍላጎታችንን በማሟላት ውስጥ የሚገነባና የሚቀረፅ ቢሆንም ከቤተሰብ በምንወርሳቸው ጄኔቲካዊ ባህርያቶች እና በስነህዝብ አወቃቀር ውስጥ በሚጠቃለሉት የዘር፣ ቀለም እና ጾታዊ ምክንያቶች ተፅዕኖ ሊደረግበት ይችላል፡፡
በአለማችን ከስድስት ሰዎች በአንዱ የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ችግር የሚታይ ሲሆን አብዛኞቹ አጋጣሚዎችም በተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶች ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የዘርፉ ተመራማሪዎች እንደሚያስቀምጡት የአዕምሮ ጤና ችግሮች ኒውሮቲክ እና ሳይኮቲክ በሚል የሚከፈሉ ሲሆን ሁለቱም ምደባዎች የያራሳቸው መገለጫዎች ያሏቸው ናቸው፡፡ እንደተመራማሪዎች ከሆነ ኒውሮቲክ (Neurotic) የሚባለው የተለመዱ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ውስጥ የሚካተቱት የመሸበር፣ የድባቴ እና የጭንቀት ባህሪያቶችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ሳይኮቲክ (psychotic) የሚባለው ደግሞ ሌሎች ሰዎች የማያዩትን፣ የማይሰሙትን እና የማያሸቱትን እውነታዊ ያልሆነ አለም ሞኖርና እና በሱ ውስጥም መገኘት ማለት ነው፡፡
እዚህ ለይ እኛ የተነሳንበት የአዕምሮን ጤና የማስጠበቅ ሂደት እና የሚያጋጥሙት ችግሮች ከላይ ባነሳናቸው ምክንያቶች ተፅዕኖ የሚደረግበት ቢሆንም አሁን በምንኖረው ህይወት ውስጥ የአዕምሮ ጤናችንን ለማስጠበቅና ወደዛ ቸግር የሚስገቡንን ክፍተቶች ለመሙላት ከእኛ የሚጠበቀውን የህይወት ልምምድ በጥንቃቄ መከወን ይገባናል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች በትኩረት ባይመለከቱትም እየኖሩት ያለው የየእለት እንቅስቃሴ የአዕምሮን ጤና ከማስጠበቅ ይልቅ የአዕምሮን ጤና ችግር ውስጥ የሚከት መጥፎ የህይወት ልምምድ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ብዙዎቻችንም በትኩረት ሳንመለከተው ቀርተን ይሆናል እንጂ የአዕምሯችንን ጤና ወደከፋ ደረጃ እየሄደ መሆኑን የሚመለክቱን የማስጠንቀቂያ ምልክቶች በራሳችን ላይ ታዝበን ይሆናል፡፡
ለምሳሌ ከሰዎች የመለየት አባዜ አብዝቶ ሲፀናወተን፣ ሁሌም ተስፋ ያማጣትና ረዳት አልባነት ሲሰማን፣ ከቤተሰብና ከጓደኛ ጋር በተደጋጋሚ መግባባት ሲያቅተን እንዲሁም ሌሎች ያልተለመዱ አድራጎቶችን በተከታታይነት ስንመለከት ቆም ብሎ በማሰብ ራሳችን መመርመር እና እርዳታ የምናገኘበት ሁኔታም መጀመር አስፈላጊ ሊሆን ይችል፡፡ ምንጊዜም ቢሆን ከአእምሯችን ጤና የሚቀዱት እነዚህ አድራጎቶች አስተሳሰባችንን፣ ባህሪያችንን እና ስሜቶቻችንን የሚቀርፁ በመሆናቸው ሁልግዜም የአዕምሯችን ደህንነት የሚጠበቅበትን ሁኔታ ማከናወን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
የአዕምሮን ጤና በማስጠበቅ ሂደት ውስጥ ሁላችንም ልብ ልንላቸው ከሚገቡ ጉዳዮች ውስጥ በቀዳሚነት የሚቀመጠው ሙያዊ እርዳታ የምናገኘበትን ሁኔታ መፈለግ ሲሆን፤ ከዚያ ባለፈ ግን ከሌሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ አካለዊ እንቅስቀሴዎችን በማዘውተር፣ በቂ እንቅልፍ በመተኛት፣ አወንታዊ አስተሳሰብ በማበልፀግ እና ሌሎችን በመርዳት የአዕምሮን ጤና ማስጠበቅ እና ይበልጥ ማሻሻል እንችላለን፡፡
ምንጭ፡ Livescience እና Mental Health

5G እና የጤና ስጋት
*******************
የአምስተኛ ትውልድ የገመድ አልባ አገልግሎትን ለመጀመር ፉክክር አየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት የጤና ችግር ያስከትላል ብለው ስጋት የደረባቸው መንግስታትም ድምጻቸውን ማሰማት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ቴክኖሎጂ ዙሪያ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶች እንዳሉ ሆኖ በሰዎች ላይ የጤና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚለው ስጋት ግን ሳያይል አይቀርም፡፡ ለመሆኑ የ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት የጤና ስጋት ይኖረው ይሆን?
ከዚህ በፊት በነበሩት የገመድ አልባ ትውልዶች የጤና ስጋት አሳስቧችሁ የማያውቅ ከሆነ አሁንም ምንም የሚያጨንቅ ጉዳይ የለም ለናል ዘገባውን ያወጣው www.WIRED.com . ቴክኖሎጂው ወደ ስራ ሲገባ የተወሰኑ አገልግሎቶች ብቻ ከፍተኛውን መጠን የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡ ከነዚህ ውስን አገልግሎት ሰጭዎች የሚኖረው ሞገድ በሌሎች ከምናገኘው ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ ጨረር የከፋ ጉዳት የሚያደርስ አይሆንም፡፡
በ5ኛ ትውልድ ገመድ አልባ አገልግሎት ያለው የሬድዮ ሞገድ ፍጥነትን ለመጨመር ብቻ የሚሆን ነው፡፡ ይህ ቴክኖሎጂ የሚጠቀመው millimeter-wave ቴክኖሎጂ ከመደበኛው በተለየ ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል ቢሆንም የስምና የፍሪኩየንሲ ለውጡ መደበኛ የሆነውን ስነ-ህይዎታዊ የጤና መገለጫ ሐይል አይለውጠውም፡፡
ከሙቀት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመቀነስ ተቆጣጣሪ አካላት የገመድ አልባ መገልገያዎች ሊያመነጩ የሚችሉትን ሙቀት ገደብ አበጅተውለታል፡፡ ጥናቶች አሁንም እንደ ቀጠሉ ነው፡፡
ምንጭ www.WIRED.com