TechIn2
1.22K subscribers
1.47K photos
1 video
120 files
500 links
Technology & Innovation Institute (TechIn2), Ethiopia

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢኒስቲትዩት

ጠቃሚና ወቅታዊ የሆኑ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ፈጠራ፣ ጤና እና ሰብአዊ-ኣቅም ግንባታ(Human Development)መረጃዎችንና ምክሮችን በየእለቱ እናደርሶታለን።
Download Telegram
ወረርሽኞችን እንዴት ማስቆም ይቻላል
*************************************
አለማችን በልዩ ልዩ ወረርሽኞች ተጠቅታለች፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ተስፋችንን በክትባቶች ላይ ብንጥልም እውነቱ ግን አብዘኞቹ ወረርሽኞች እስከ መጨረሻው አብረውን የሚዘልቁ መሆኑ ነው፡፡ የጥንት ሰዎች ልክ እንዳሁኑ በተለያዩ ወረርሽኞች ተጠቅተዋል፡፡
ለምሳሌ The Black Death እየተባለ የሚጠራው ከ1346-1353 የተከሰተው ከሁሉም በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተከሰተው በልዩ ልዩ ጥናቶች እንደተመለከተው ለ2000 ዓመታት ያክል ወረርሽኝ ሆኖ የተከሰተው ምንጩ ባክቴሪያ የሆነው yersinia pestis ሌላው በገዳይነቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እዚህ ላይ የህዝብ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የወረርሽኞች የመስፋፋትና የገዳይነት አቅምም እየጨመረ መምጣቱን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
የሆንግ ኮንግ ጉንፋን እየተባለ የሚጠራው ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት እስከ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ቢሆንም አሁንም ግን ስርጭቱ አላቆመም፡፡ እንዲሁም ከጥቂት አስርት አመታት በፊት የተከሰተው ኤች አይ ቪ ቫይረስ መፍትሔ ሳይገኝለት አሁንም ስርጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ እንደ WHO የቁጥር መረጃ ከሆነ በ2019 ብቻ በአለም ዙሪያ 690 ሺህ ሰዎች በዚሁ በሽታ ህይዎታቸው አልፏል፡፡
ሌላም ሳርስ የተባለ ከ2002-2003 ብቻ 800 ሺህ የሚደርሱ ሰዎችን የቀጠፈ በሽታ በአለማችን መከሰቱ የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁን ደግሞ የሞት መጠኑ ያልታዎቀ በግማሽ አመት ብቻ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ ኮቪድ 19 ተከሰተ፡፡
በአጠቃላይ በአለማችን የተከሰቱ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ስንመለከት በቁጥጥር ስር ለመዋል ረጅም አመታትና ብዙ ትውልዶች ስፈልጓቸዋል፡፡ በመሆኑም ስለ ወረርሽኞች ያለን እውቀት መዳበር፣ የማህበረሰብ አጠቃላይ ጤና መሻሻል፣ አዳዲስ ክትባቶች መገኘታቸው የየራሳቸው የሆነ ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር የሚያግዝ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ የተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታት ዘርፈ ብዙ ጥናቶች የተደረጉ ቢሆንም እንዲሁም ስልጣኔ እየጨመረ ሲሄድ የክትባት ፍለጋው እየተሳካ ቢመጣም የውሸባን (ቀሳ) (quarantine) ያክል ግን ውጤታማ የሆነ መፍትሔ አልተገኘም፡፡ አሁን እያለፍንበት ያለውም ወረርሽኝ ማብቂያ ሊገኝ የሚችለው ከላይ የተዘረዘሩት መፍትሔዎች በጥምረት በተግባር ሲውሉ ብቻ ነው፡፡ ምንጭ BBC news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
CDC ኮሮናቫይረስ በህፃናት እና በአዋቂዎች ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው ከባድ የጤና ቀውስ እያስጠነቀቀ ነው
=====================
የአሜሪካው የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ መዕከል (CDC) ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ህፃናት ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያየ የበሽታ ምልክቶች ወይም (syndromes) በአዋቂዎች ላይም የመከሰት እድላቸው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ በዚህ ሲንድረም ዙሪያ የሚወጡ መረጃዎች በሚገባ እንዲጤኑ እና በትኩረት እንዲታዩ ጥሪ አስተላልፏል፡፡http://www.techin.gov.et/post/318/
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 6
Basic Geometry / Basic forms
====================
In this tutorial we will be going over Basic forms for complex drawing.
https://www.youtube.com/watch?v=kw7TdZ7jkXQ
For more science and technology information’s, please subscribe to our cannel.
የእይታ ችግር ላለባቸው ትልቅ መላ
**********************************
ቺይኮ አሳካዋ ትባላለች፡፡ አይነ ስውር ናት፡፡ የኮምፒውተር ሳይንቲስት ስትሆን በስራ ምክንያት በየወሩ ከአሜሪካ ጃፓን ከጃፓን አሜሪካ የአውሮፕላን ጉዞ ታደርጋለች፡፡ በረራ ያደረገችው ብቻዋን ከሆነ ከአየር መንገዱ ሰራተኞች አንዱ ወደምትፈልገው ቦታ ያደርሳታል፡፡ ካልሆነም የምትፈልገውን ሰው እስክታገኝ ለረጅም ሰዓት ትጠብቃለች፡፡
ችግር ብልሀትን ይወልዳል እንዲባል በዚህ ነገር የተማረረችው ቺይኮ ባለ ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ሻንጣን ሰርታ አቅርባለች፡፡ ይህም ፈጠራዋ ከአውሮፕላን ከወረደች በኋላ በፍጥነትና ደህንነቷ እንደተጠበቀ ወደ መዳረሻዋ የሚመራት ነው፡፡ ሻንጣው የጉዞ ሻንጣ ሲሆን ካሜራና ሴንሰር የተገጠመለት ነው፡፡ ካሜራና ሴንሰሩ በአብዛኞቹ ራስ ነድ መኪኖች (autonomous car) እንደተገጠሙት ያለ ነው፡፡ ሻንጠው አካባቢውን እንዲያውቅ ሰው ሰራሽ ክህሎትን (artificial intelligence) ይጠቀማል፡፡ ሻንጣውን ለማዘዝ የሞባይል መተግበሪያ እንዲጠቀም ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሻንጣው የሰው ፊት መለየት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ ተገጥሞለታል፡፡ ይህም ተጠቃሚውንና በቅርብ ያለ ሰውን እንዲለይ ያስችለዋል፡፡
ይህች ድንቅ እንስት ሌሎች ብዙ ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን ለአለም ያስተዋወቀች ሲሆን ከእነዚህም መካከል "aDesigner," ለዲዛይነሮች የሚያግዝና ዌብሳቶችን ለተጠቃሚዎች ቀላል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ፣ በድምጽ ኢንተርኔት መክፈት የሚያስችል በተለይ ለአይነ ስውራን ምቹ የሆነ ፈጠራ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
ባለድንቅ ቴክኖሎጂውን ሻንጣ ለመስራት ያነሳሳትን ነገር ስትናገር " ብቻየን ስራመድ ምንም ምቾት አይሰማኝም፡፡ ሁልጊዜ በጉዞ ብቸኝነቴን ሊቀርፍልኝ የሚችል ቴክኖሎጂ ምን ሊሆን ይችላል እያልኩ አስባለሁ፡፡ እንዲሁም ስጓዝ የደህንነት ስሜት እንዲሰማኝና በፍጥነት እንዲሆን እፈልጋለሁ ይህም ነው ይህን ሻንጣ እንድሰራ መነሻ የሆነኝ" ትላለች፡፡ ሻንጣው ሌሎች አይነ ስውራንን ሊያግዙ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ተገጥመውለታል፡፡
ምንጫ CNN Travel
በህክምና ዘርፍ የዚህ ዓመት ኖቬል ሽልማት አሸናፊዎች
===================
በዓለም ዙርያ ለብዙ የሄፒታይተስ እና ጉበት በሽታዎች መነሻ የሆነውን የሄፒታይተስ ሲ ቫይረስን ያገኙትና መረጃዎችን የገለጡት ሦስት የስነ ቫይረስ (Virology) ተራማሪዎች የዚህ ዓመት የህክምና ዘርፍ የኖቬል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ አሸናፊዎቹ ሃርቪ አልተር በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካን ብሄራዊ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያ ሲሆኑ፤ ማይክል ሆውተን እና ቻርልስ ሪይስ ደግሞ የካናዳው የአልበርታ ዩኒቨርሲቲ እና አሜሪካን የሚገኘው የሮክፌለር ዩኒቨርሲቲ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ሦስቱ ተመራማሪዎች በሄፒታይተስ ሲ ላይ የሰሩት ስራ በአሁኑ ሰዓት በበሽታው ላይ ለሚደረገው ስኬታማ ህክምና መንገዱን የጠረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የእነዚህ ተመራማሪዎች ጥናት ጅማሮ ከአራት አስርት ዓመታት በፊት አንስቶ ነው፤ እ.አ.አ ከ1970ዎቹ ሃርቪ አልተር ደም በመስጠት በሚደረገው ህክምና አማካኝነት የሚከሰት የጉበት ህመም መተላለፍን ሲያጠና ቆይቷል፡፡ ቀደም ያለ ስራ ሄፒታይተስ ኤ እና ቢ ቫይረሶችን ቢያገኝም ሃርቪ አልተር ሶስተኛና የደም ውስጥ በሽታ አምጪ ተህዋሲ የሆነው ቫይረስ በሽታውን ወደ ቺምፓንዚዎች ሊያስተላልፍ እንደሚችል አሳየ፡፡ ከዚህ በመቀጠል ማይክል ሆውተን ከስራ አጋሮቹ ጋራ በመሆን በበሽታው ከተጠቁ ቺንፓንዚዎች በተወሰደ ዘረ መል አማካኝነት ቫይረሱን መበየን ችለዋል፡፡ ይህም ከፋቫቪራዴ ቤተሰብ የሚመደብ አዲስ የRNA ቫይረስ አይነት መሆኑን ማሳየት የቻለ ውጤት ነበር፤ ስሙንም ሄፒታይተስ ሲ ብለው ጠሩት፡፡ ቻርለስ ሪይስ በሚመራው የጥናት ቡድን አማካኝነት የተደረገ ምርምር ደግሞ የዘረ-መል ምህንድስና ስልቶችን በመጠቀም ቫይረሱ ያጠቃቸው ህዋሶች ላይ ለሚደረገው የቫይረሱ መባዛት ምክንያት የሆነውን የሄፒታይተስ ሲ ክፍል መለየትና በጉበት በሽታ ውስጥ ያለውን ድርሻ ማሳየት ችሏል፡፡
በአለም የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት 71 ሚሊዮን ሰዎች በየዓመቱ በሄፒታይተስ ሲ ሲጠቁ 400 ሺህ ያህሉ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ ሰፊውን ድርሻ የሚወስዱት የሲሮሲስ እና ጉበት ካንሰር በሽታዎች ናቸው፡፡ የኖቬል ሽልማቱ አሸናፊ ተመራማሪዎቹ ስራ ከሌሎች ባለሙያዎች አበርክቶት ጋራ በመሆን በሄፒታይተስ ምርመራ እና ህክምና ላይ ትልቅ መሻሻል እንዲመጣ መንስኤ ሆኗል፡፡ ቀድሞ በበሽታው ላይ ይተገበሩ የነበሩት ከባድ ግን ብዙም ውጤታማ ያልሆኑ የህክምና ስልቶች ምስጋና ለተመራማሪዎቹ ጥረት ይሁንና ቫይረሱን በቀጥታ ወደሚገቱ መድሃኒቶች ዞረዋል፡፡ መድሃኒቶቹ አብዛኛውን የሄፒታይተስ ሲ አመጣሽ በሽታዎችን ማከመም የሚችሉ ሆነው ሳለ ግን ዋጋቸው ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ለሚኖሩ ዜጎች የሚቀመስ አለመሆኑ ተደራሽነታቸውን ቀንሶታል፡፡
የአለም የጤና ድርጅት ከ10 ዓመት በኋላ ሄፒታይተስ ሲን ጨርሶ ከምድራችን ለማስወገድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ከሆነ ግን ይህን ማድረግ ክትባትን ያሻል፡፡ ይህ ግን በተለይም ለበሽታው ክትባት ለማግኘት ካለው መዘናጋት እና ዝቅተኛ ርብርብ አንፃር አስቸጋሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም ባሻገር ምንም እንኳን አሁን የደረስንበት ቴክኖሎጂ ደረጃ ሊፈታው የሚችለው ቢመስልም ቫይረሱ ከሌሎች የቫይረስ አይነቶችም አንፃር ያለው የላቀ ውስብስብነት ሌላው ፈተና ነው፡፡ ታድያ የኖቤል ሽልማቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ትልቁን እርምጃ ለተራመዱት ተመራማሪዎች መበርከቱ በሽታው የሚገባውን ትኩረት ለመሳብ ሊረዳው ይችል ይሆን የሚል ተስፋን ፈጥሯል፡፡
ምንጭ፡ Nature
“BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” online training፡- Part 7 (final)
Simple Drawing Exercises on Basic geometry
In this tutorial we will be going over exercise on basic forms, the seven element of art, Which are building block for Artist and designer.
https://www.youtube.com/watch?v=tUK2By1ig_I&t=71s
Answer the questions in Plain paper (A4/A3) and get participation certificate. Email us your captured answer with your full name.
Check out our email and PDF file in the description.
Thank you.
ውድ ተከታታዮቻችን “BASIC PRODUCT SKETCHING TECHNIQUE” በሚል ርዕስ በኢንስቲትዩቱ ዩቲዩብ ቻናል ላይ ሲተላለፍ የቆየውን ስልጠና አስመልክቶ የሚቀርቡላችሁን የመለማመጃ ጥያቄዎች በመወረቀት ላይ (A4 ወይም A3) ሞልታችሁ ከነስማችሁ በኢሜይል አድራሻችን (stic.ethiopia@gmail.com) የምታደርሱን ይሆናል፡፡
//ስልጠናውን በአግባቡ ለተከታተሉና የሚቀርቡትን የመለማመጃ ጥያቄዎች ሞልተው ከላይ በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻችን ለሚልኩልን ሰልጣኞች ሰርተፊኬት አዘጋጅተን የምናደርስ መሆኑን በድጋሚ እንገልፃለን፡፡//
የመለማመጃ ጥያቄዎችን በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://drive.google.com/file/d/1uVzucK89r8dvHm3jyMOTTsxh4eNykbhk/view
የአፍንጫ መድማትን ለማቆም የሚያስችል መንገድ
********************************
ምንም እንኳን የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር አስደንጋጭ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ የተለመደ ነው፡፡ በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ወደ 60 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የአፍንጫ መድማት ይታይባቸዋል፡፡ በተለይ ከ2-10 ዕድሜ ክልል ያሉ ህፃናትና ከ50-80 ዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች ከፍተኛውን የቁጥር ድርሻ ይወስዳሉ፡፡
አፍንጫችን የምንስበውን አየር የሚያረጥቡ ብዙ የደም ስሮች አሉት፡፡ በአፍንጫችን በኩል የሚገባው አየርም ወደ አፍንጫችን ግድግዳ ተጠግቶ በሚያልፍበት ወቅት ለዚህ የመድማት ችግር ልንጋለጥ እንችላለን፡፡ ይህም የሚሆነው ከፍተኛ ግፊት ያለው ነፋስ ሲኖርና በእጃች አላስፈላጊ መነካካት ስናዘወትር ነው፡፡ እዚህ አካባቢ የሚከሰት መድማት anterior nosebleeds በመባል ይታወቃል፡፡
ብዙ ጊዜ ያልተለመደውና የከፋ ጉዳት ሊያደርስ የሚችለው ከውስጠኛው የአፍንጫ ስር የሚመነጨው posterior nosebleeds የሚባለው ነው፡፡ ልዩ ህክምናም የሚስፈልገው የአፍንጫ መድማትም ይህኛው ነው፡፡ የዚህ አይነቱ የአፍንጫ መድማት በአደጋ የአፍንጫ መሰበር ሲያጋጥም፣ የቅርብ ጊዜ የአፍንጫ ቀዶ ህክምና ሲኖር፣ ደምን ሊያቀጥኑ የሚችሉ መድሀኒቶችን ስንጠቀም፣ የደም ስሮችን የሚጎዳ ተፈጥሯዊ ችግር ሲኖርና የሉኪሚያ ተጠቂ ስንሆን የሚከሰት ነው፡፡
ይሁንና የአፍንጫ መድማትን በቀላሉ በቤት ውስጥ ማሰቆም ይቻላል፡፡ ችግሩን ለማስቆም ብዙ መንገዶች ቢኖሩም በአሜሪካ የሚገኘው Yale Medicine ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቅደም ተከተሎች መከተል ተገቢ ነው ይላል፡፡
ተስተካክሎ በመቀመጥ የአፍንጫን ለስላሳውን ክፍል በለስላሳ ጨርቅ ወይም በሶፍት ለ10 ደቂቃ ያክል መያዝ
እጅን ፊት ለፊት አድርጎ አፍንጫን መያዝና በአፍ ብቻ መተንፈስ
በጨርቅ የተጠቀለለ በረዶ ከግንባራችን ስር በማድረግ የአፍንቻችን የደም ቧንቧዎች እንዲጠቡ ማድረግ
መተኛት ወይም መንጋለል ልባችንን ወደ አፍንጫችን ስለሚያቀርበው በተቻለ መጠን ተስተካክሎ መቀመጥ
ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በአግባቡ ከተገበርን መድማቱ የመቆም እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ህክምና ተቋም መሔድ የሚጠበቅብን ጊዜ ሊኖር እንደሚችል ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ Revere Health የተባለ የምርምር ተቋም ወደ ህክምና ሊያስኬዱን የሚችሉ ምልክቶችን እንዲህ ሲል ዘርዝሯል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅመን የአፍንጫ መድማቱ ካልቆመ
የአፍንጫ መድማቱ የተከሰተው በአደጋ ከሆነ
አፍንጫችን የደማው የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶችን ከወሰድን በኋላ ከሆነ
ምንጭ:- www.howstuffworks.com
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኮቪድ 19 አንዳንድ ሰዎች ላይ ከባድ የሆነበት ሚስጥር ምንድነው
ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ብዙዎች የሚጠይቁት ጉዳይ ቢኖር በሽታው አንዳንድ ሰዎች ላይ እጅግ ከባድ ሆኖ ሌሎች ላይ ደግሞ ቀላል የሚሆንበት ምክንያት ምን እንደሆነ ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች በቫይረሱ ከተያዙ በኋላ ጤናቸው እጅግ ወደካፋ ሁኔታ የሚለወጥባቸው ሲሆን ሌሎች ደግሞ እንደጉንፋን እና ሌሎች ቀላል በሽታዎች የሚሆንባቸው አሉ፡፡ ይህ ሁኔታ እድሜያቸው በገፋ ሰዎች ላይ እና ሌሎች ተያያዥ በሽታዎች ባለባቸው ሰዎች ላይ የሚጠበቅ ቢሆንም በወጣቶች እና አደገኛ የሚባል በሽታ በሌለባቸው ሰዎች ላይ ተደጋግሞ መታየቱ ግን ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
በዚህ ጉዳዩ ዙሪያ የተሰሩ ተደጋጋሚ ጥናቶች የተለያየ ግኝት የተንፀባረቀባቸው ቢሆኑም አብዛኞቹ የሚስማመቡት ጉዳይ ግን የቫይረሱ ባህሪ እጅግ ተለዋዋጭ ከመሆኑ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ በዚህ አውድ መሰረት ከተሰሩት አያሌ ጥናቶች መካከል በቅርቡ ይፋ የተደረገው አዲሱ ጥናት የሚገኝ ሲሆን ይህም ስለኮሮናቫይረስ ተለዋዋጭነት እና ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለደረሰበት ግኝትም የሚከተለውን መልስ ይሰጣል፡፡
ከሰሞኑ በዚሁ ጉዳይ ላይ አተኩሮ የተሰራው አዲስ ጥናት እንደሚለው ለዚህ ሁኔታ መከሰት ጄኔቲክ ሚውቴሽን (genetic mutation) እና የአውቶ አንቲቦዲስ (Autoantibodies) በብዛት መመረት ዋና ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ያስቀምጣል፡፡ ይህ ሁኔታ በሽታ የመከላከል ስርዓታችን የሚያመርተው ፕሮቲን (immune proteins) በተሳሰተ ሁኔታ የራሳችን የሆነውን አካል ወይም ቲሹ ኢላማ በማድረግ ምላሽ ሲሰጥ የሚከሰት ሲሆን፤ አብዛኛውን ጊዜ ለከፋ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ይህን ጥናት ያከናወነው ሃዋርድ ሂዩዝ ሜዲካል ኢኒስቲትዩት ይፋ እንዳደረገው ይህን ውጤት ለማግኘት 3,000 የሚጠጉ ሰዎች ላይ ጥልቅ ምርምር የተደረገ ሲሆን የተሳታፊዎቹን በቫይረሱ የመጠቃት ሁኔታ እና በሌሎች ተያያዥ በሽታዎች የመጋለጥ ሁኔታቸውም በምርመራው ሂደት ተጠንቷል፡፡ ታዲያ ተመራማሪዎች ቀድመው በለዩት የጄኔቲክ ሚውቴሽን እና የአውቶ አንቲቦዲስ ብያኔ መሰረት እንደተረዱት ከ10 በመቶ በላይ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች የአውቶ አንቲቦዲስ ፕሮቲኖችን አምርተው የተገኙ ሲሆን 3.5 በመቶ የሚሺፍኑት ደግሞ ቫይረሱን በሚዋጋው ስርዓት ላይ የጄኔቲክ ሚውቴሽን ችግር ታይቶባቸዋል፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ተመሳሳይ ቫይረስ ያጠቃቸው ሰዎች በሽታ በመከላከል ስርዓታቸው ላይ በሚፈጠር የጄኔቲክ ሚውቴሽን ችግር ምክንያት አንዳንዶቹ በቫይረሱ ክፉኛ እንዲጎዱ ሌሎች ደግሞ የበሽታ ምልክት እንኳን ሳይታይባቸው ከበሽታው እንዲድኑ ያደርጋቸዋል፡፡
ተመራማሪዎች እንደሚሉት በጄኔቲክ ሚውቴሽን ችግሩ ምክንያት በቫይረሱ የተያዙ ታካሚዎች ወደሰውነታቸው የገባውን በሽታ አምጪ ተህዋሲ (pathogen) በሚገባ ስለማይለዩ በሽታው በቀላሉ እንዲያጠቃቸው እና የመከላከል አቅማቸው እንዲዳከም አስተዋፅዖ ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በዚህ ጥናት ላይ ምርምር ከተደረገባቸው 659 ተካሚዎች መካከል 23 የሚሆኑት በሽታ የመከላከል ስርዓታቸው የሚያመርተው ፕሮቲን (immune proteins) በመረጃ ቅደም ተከተሉ ላይ የጂን ስህተት (gene errors) በመፈጠሩ ቫይረሱን የሚከላከል ፕሮቲን በሚገባ እንዳይመረት እክል ፈጥሯል፡፡
በዚሁ የጥናት ሂደት ሌላ ምርመራ ከተደረገባቸው 987 ታከሚዎች መካከል 101 የሚሆኑት የአውቶ አንቲቦዲስ ፕሮቲኖችን አምርተው የተገኙ ሲሆን ይህም በሽታ የመከላከል ስርዓታቸው በስህተት የራሳችውን አካል ኢላማ በማድረግ በሽታ የመከላከል አቅማቸው እንዲወርድ ያስቻለበት ምክንያት ነው፡፡
ተመራማሪዎች በእነዚህ ጥናቶች ላይ የተረዱት ነገር ቢኖር መሰል አንቲቦዲዎችን አበልጽገው ከተገኙ ታካሚዎች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች መሆናቸው እስካሁን በቫይረሱ ምክንያት ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ህይወታቸው ያጡበት ምከንያት ከዚህ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው እንዲባል አስችሏል፡፡
እነዚህ የምርምር ውጤቶች እንዳሳዩት የጄኔቲክ ሚውቴሽን ችግሩ ያለባቸው ሰዎች እንደኮሮና ባሉ የቫይረስ በሽታዎች ይበልጥ የመጠቃታቸው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ስለሚጨምር አስፈላጊውን የጤና ምርመራ እና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያስፈልጋል፡፡ ከክትባቶች ጋር በተያያዘም በሽታ የመከላከል ስርዓታቸው አውቶ አንቲቦዲ የሚያመርትባቸው የቫይረሱ ተጠቂዎች፤ ስጋት ያለባቸው የማህበረሰቦች ክፍሎች ተደርገው ተወስደው ክትባቶችን ቀድመው እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡
ይህ ችግር ቀጣይ በሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች ይበልጥ እየዳበረ መምጣት ቢገባውም እስካሁን ከታዩት ናሙናዎች ለማየት እንደተቻለው የችግሩ ሁኔታ ተፈጥሮአዊ ባህሪ ያለው ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ የጄኔቲክ ሚውቴሽን እና ኮሮናቫይረስ ዙሪያ የሚደረጉ ምርምሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መደረጋቸው የበሽታውን የወደፊት መፍትሄ በመጠኑም ቢሆን ሊያመለክት ይችላል፡፡
ምንጭ፡ Big think እና medical news today
ምድርን ከአደጋ መጠበቅ ይፈልጋሉ
**********************************
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሁን ያለንበትን የአየር ጠባይ ለውጥ እንደዋዛ መመልከት እንደማገባ በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ የአየር ጠባይ ለውጡ በአለማችን ታይተው የማይታወቁ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ከማስከተሉም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የምግብ ምርት ማነስን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የውሀ አካላት ከልካቸው በማለፍ በየአካባቢው የጎርፍ አደጋን እያስከተሉ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ሀገራት ይህ የተፈጥሮ መናጋት ወደማይመለስበት ደረጃ ከመድረሱ በፊት አስቸኳይ እርምጃን መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ መንግስታት መስራት ያለባቸውን እስኪሰሩ ድረስ እያንዳንዱ ሰው በግለሰብ ደረጃ የሚኖርባትን ምድር መንከባከብ የሚችልበትን መንገድ ከዚህ እንደሚከተለው ልናስነብባችሁ ወደድን፡፡ መልካም ንባብ
1ኛ. ውሃን በአግባቡ መጠቀም
ስናያቸው ትንሽ ናቸው ብለን የምናስባቸው ነገሮች በትኩረት መሰራት ከቻሉ ትልቅ ለውጥ ማምታት ይችላሉ፡፡ በማንናውም ሰዓት ለምሳሌ ምሳ ለመብላት እጅ ስንታጠብ ወዲያው የመታጠቢያውን ውሀ መዝጋት ከቻልን እና ሌሎችም ይህን እንዲያደርጉ ከገፋፋን በቀላሉ የውሀ ብክነትን መቀነስ እንችላለን፡፡ በእርግጥ ውሃ የሚባክንበት ምክንያት ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን አንድን ነገር ለመስራት የሚያስፈልገንን ውሃ ብቻ መጠቀም ይኖርብናል፡፡ በተቻለ መጠን ውሀን ከቤታችን እያጣራን እንጠቀም፡፡ በዚህ ምክንያት ምድራችንን ከፕላስቲክ ኮዳዎች መታደግ እንችላለን፡፡
2ኛ. መኪና የመጠቀም ልምዳችንን እንቀንስ
በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መኪና ይዞ መውጣት ጊዜያዊ የጤና ችግር ከማስከተሉ በተጨማሪ የካርቦን ልቀትን በማስፋፋት የተፈጥሮን ሚዛን ያዛባል፡፡ ከተቻለ ለ2 ቀን ከመኪና መንገድ ራቁ፡፡ መኪና መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ በአንድ ጉዞ ብዙ ተጋባራትን በመከወን ምልልሳችንን እንቀንስ፡፡



3ኛ. መራመድ፣ ብስክሌት መጠቀም፣ የህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም
በእግር መራመድና ብስክሌት መጠቀም ከተፈጥሮ ጋር ወደር የሌለው ስምምነት አላቸው፡፡ ካልሆነ ደግሞ የህዝብ ትራንስፖርን በመጠቀም በመንገድ ላይ የሚታዩ መኪኖችን ቁጥር በመቀነስ ሀላፍነትን መወጣት አስፈላጊ ነው፡፡
4ኛ. መቀነስ፣ በድጋሚ መጠቀምና ለሌላ አገልግሎት ማዋል
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ብክለትን በከፍተኛ መጠን መቀነስ ያቻላል፡፡ የተጠቀምናቸውን ነገሮች ከማስወገዳችን በፊት በድጋሚ መጠቀም መቻልና አለመቻላችንን ማረጋገጥ፡፡ በድጋሚ መጠቀም ከቻልን እናድርገው፡፡ ካልሆነ ደግሞ ወደሌላ አገልግሎት ለመቀየር ጥረት እናድርግ፡፡ ይህን በማድረግ የሚጣሉና በካይ የሆኑ ነገሮችን መቀነስ እንችላለን፡፡
5ኛ. ቆሻሻን ወደ ተፈጥሮ ማዳበሪያ መቀየር
መበስበስ የሚችሉ ውጋጆችን ጉድጓድ ቆፍሮ በመቅበር ወደተፈጥሮ ማዳበሪያነት መቀየር ይቻላል፡፡ ይህንም ማድረግ በሁለት መልኩ ይጠቅማል፡፡ የመጀመሪያው በአካባቢ የሚታይን ቆሻሻ ይቀንሳል፡፡ ሌላው ደግሙ ለሰብል ልማት የተፈጥሮ ማዳበሪያ የመጠቀም ልምድ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
6ኛ. የሐይል አጠቃቀምን ማስተካከል
የምንጠቀመው የቤት ውስጥ አምፖል የሀይል ፍላጎታችንን ይወስነዋል፡፡ በመሆኑም የቤት ውስጥ መገልገያዎቻችንን በሙሉ ሀይል ቆጣቢ በሆኑ መገልገያዎች በመተካት የሀይል ፍጆታችንን እንቀንስ፡፡ የሀይል ፍጆታን መቀነስ ለሀይል የምናወጣውን ወጭ ይቀንስልናል፡፡
7ኛ. ቤታችንን ማስተካከል
ቤታችን በቂ የሆነ ብርሀን የማያስገባ ከሆነ የሀይል ፍላጎታችን ሊጨምር ይችላል፡፡ ስለዚህ ቤትን በቂ ብርሀን እንዲያገኝ ማድረግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡


8ኛ. ለተፈጥሮ ምቹ የሆነ አመጋገብ
በተቻለ መጠን በምርት ሂደት መሬትን የማይጎዱ የግብርና ምርቶችን ለምግብነት መጠቀም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ከዚህ በበለጠ ደግሞ የጓሮ አትክልትን በራስ አምረቶ መጠቀም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
9ኛ. ዛፎችን መትከልና መንከባከብ
በ2018 የተባበሩት መንግስታት በአየር ንብረት ዙሪያ የሚሰራ የመንግስታት ጥምረት ባወጣው ሪፖርት በ2050 የተለያ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የዛፍ ዝርያዎች መተከል አለባቸው ብሎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በሀገራችንም በዚሁ ረገድ አበረታች ስራ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ እንደ ግለሰብ ግን በአመት ቢያንስ ሁለት ዛፎችን ተክለን ተንከባክበን ብናጸድቅ የሚመጣውን ለውጥ መገመት ቀላል ነው፡፡
10ኛ. ፕላስቲክን አለመጠቀም
ይህ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም በተፈጥሮ ላይ የሚያመጣው ቀውስ ግን በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ፕላስቲክን ለመገልገያነት ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ለአንድና ሁለት ጊዜ አገልግሎት ብቻ የሚውሉ ፕላስቲኮችን ባለመጠቀም ብድራችንን ከፕላስቲክ ቆሻሻ ማላቀቅ ይኖርብናል፡፡
እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን 10 ነገሮች ሁሉም የአለም ህዝብ መተግበር ቢችል ምድራችን እንዴት ጤናማ ትሆን ይለናል ከwww.howstuffworks ያገኘነው መረጃ፡፡
የናኖ ቴክኖሎጂ
***********
ይህ አስገራሚ ዘርፍ የኢንጅነሪንግ፣ የሳንስና ቴክኖሎጂ ጥምረት ሲሆን መጣም ጥቃቅን ስለሆኑ ነገሮችም የሚያጠና ነው፡፡ ከ1-100 ናኖሜትር የሚደርስ መጠን ያላቸውን ትኩረት ያደርጋል፡፡ የዚህ ቴክኖሎጂ አባት እየተባለ የሚጠራው Richard Feynman ነው፡፡ የዚህ ሀሳብ ጥንስስ የተጀመረው በታህሳስ ወር 1959 የአሜሪካ የፊዚክስ ምሁራን ውይይት ጊዜ Richard Feynman ባነሳው “There’s Plenty of Room at the Bottom” በሚል ሀሳብ ነው፡፡ በውይቱ ፌይንማን እያንዳንዱን ሞሎኪዩልና አቶም እንዴት ነጣጥሎ ማጥናት እንደሚቻል አስረድቷል፡፡
ናኖ ቴክኖሎጂ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለማሰብ እጅግ በጣም ይከብዳል፡፡ አንድ ናኖ ሜትር አንድ ቢሊዮንኛ ሜትር ነው፡፡ በአንድ ኢንች ውስጥ 25,400,000 ያክል ናኖ ሜትሮች አሉ፡፡ በሌላ አገላለጽ የጋዜጣ ወረቀት 100,000 ናኖ ምትር ውፍረት አለው፡፡
ተመራማሪዎች STM (scanning tunneling microscope) እና AFM (atomic force microscope) የሚባሉ ማይክሮስኮፖችን ከፈጠሩ በኋላ የናኖ ስኬል በሰፊው ስራ ላይ መዋል ጀምሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ይህ ቴክኖሎጂ በተለዩ መስኮች ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የፀሐይ መከላከያ ሎሽኖች (sunscreens) የተለያዩ የአይን መነጽሮች (Self-cleaning glass) አልባሳት እና ጸረ-ባክቴሪያ መጠቅለያዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ምንጭ፡ National Nanotechnology Initiative
አዳዲስና ጠቃሚ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት የሚረዱ ድረገጾች
*****************************************
እነዚህ ድረ-ገጾች በአለማችን በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሰሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡
1. TechCrunch
2. Gizmodo
3. TechHive
4. CB Insights
5. Cord Cutters News
6. MakeUseOf
7. Life Hacker
8. Computerworld
9. How to Geek
10. Pymnts.com
ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ግለሰቦች የተለያዩ ጥቅሞች ለማግኘት ሲሉ የሃሰት አካውንት በመክፈት ድብቅ አጀንዳቸውን ሲያራምዱ ማስተዋል እየተለመደ መጥቷል፡፡ ይህ ደግሞ ከፍተኛ ተከታይ በሚኖራቸው የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ላይ እጅግ ጎልቶ ይታያል፡፡አብዛኞቹ እነዚህ ያልተረጋገጡ የሚዲያ ምንጮች ለገቢያቸው መደለብ ሲሉ ብቻ የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ ብዙዎችን ለአደጋ ማጋለጣቸው የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ቆይቷል፡፡






ያልተረጋገጡ የማህበራዊ ሚዲያ መረጃዎች የኮሮናቫይረስን የመከላከል ስራ ካባድ እድርገውታል
==============
ኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞም እነዚህ የተሳሳቱ የመረጃ ቅብብሎች ከመቼውም ጊዜ ባላይ እየጨመሩ የመጡ ሲሆን በዚህ ጉዳይ የተሰሩ አብዛኞቹ ጥናቶችም ከወረርሽኙ እኩል ህዝቡን እያሸበሩት የሚገኙት ጉዳዮች እነዚሁ ያልተረጋገጡ የመረጃ ምንጮች እንደሆኑ አሳይተዋል፡፡ ከሰሞኑ በእንግሊዝ የተደረገው ተመሳሳይ ጥናት እንዳመለከተውካልተረጋገጡ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የሚገኙ ዘገባዎችን ዋና የመረጃ ምንጫቸው ያደረጉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሴራ ትንተና (conspiracy) የበዛባቸውን መረጃዎች በይበልጥ እያመኑ መምጣታቸውንና በዚህም የተለያዩ የመንግስታትን የጤና መመሪያዎች እየጣሱ እንደሚገኝ በጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡

በእንግሊዝ መቀመጫቸውን ባደረጉ ኪንግ ኮሌጅ እና Ipsos Mori የምርምር ማዕከል የተሰራው ይህ የዳሰሳ ጥናት በጥቅሉ 2,000 ሰዎችን በጥናቱ አሳትፎ የተለያዩ መጠይቆችን ለተሳታፊዎቹ አቅርቦ ነበር፡፡ይህ የምርምር ቡድን ካቀረባቸው መጠይቆች መካከል የኮሮናቫይረስ በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረ ነው የሚለው እንደኛው ጥያቄ ሲሆን ከተሳታፊዎቹ 30 በመቶ የሚሆኑት በዚህ የሴራ ትንተና የሚያምኑ እና በዚህም የተነሳ እርምጃዎችን እየጣሱ እንደሚገኝ በጥናቱ ታይቷል፡፡ ከዚህ ባለፈ በጥናቱ እንደተገለፀው ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው የጥናቱ ተሳታፊዎች በኮሮናቫይረስ ህይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች ትክክለኛ ቁጥራቸው እንዳይታወቅ መንግስታት ይደብቃሉ የሚለውን መጠይቅ በስፋት እንደሚያምኑ በጥናቱ ተዳሷል፡፡

13 በመቶ የሚሆኑ የጥናቱ ተሳታፊዎች ወረርሽኙ የአለም ሰዎችን በክትባት ለመቆጣጠር የተዘየደ ሴራ ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን፤ 8 በመቶ የሚሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ደግሞ የኮሮናቫይረስ ምልክቶች በአንድም ይሁን በሌላ ከ5G ራዲዬሽን ጋር የጠበቀ ግንኙነት አላቸው ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ በዚህ የዳሰሳ ጥናቱ ለመታዘብ እንደተቻለው ብዙ ሰዎች መሰል የኮኒስፓይሪሲ ዘገባዎችን በስፋት እንዲቀበሉ ያደረጋቸው ይፋዊ የጤና ምክሮችን የሚያገኙበት የመረጃ ምንጭ ከመፈለግ ይልቅ ብዙ ያልታመኑ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ዋና የመረጃ ምንጭ በማድረጋቸው ነው፡፡ በተለይም ከፌስቡክ እና ከዩቲዩብ የሚገኙ ያልታመኑ የመረጃ ምንጮች ለእነዚሁ የተዛቡ የኮኒስፓይሪሲ ዘገባዎች ዋና መደላድል ናቸው፡፡

ወረርሽኙን ከመከላከል እኩል መረጃዎች የሚሰራጩበትን ሁኔታ በሚገባ መከታተል ያስፈልጋል የሚሉት የጥናቱ ዋና መሪ ዶ/ር ዳንኤል አሊንግቶን ቤት የመቀመጥ መመሪያዎችን እና ሌሎች እርምጃዎችን በምናስተላልፍበት መጠን ግልፅና ጥራት ያላቸው መረጃዎችን ለሰዎች እንዲደርስ ማድረግ ቀዳሚ ስራ ሊሆን ይገባል ይላሉ፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ እንደ ቲቪ እና ራዲዮ ያሉ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገዶች ትልቅ ሚና የሚኖራቸው ቢሆንም ወጣቱ የሚመርጣቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለአደጋው መባባበስ ትልቅ እድል እንደሚፈጥሩ በጥናቱ ተዳሷል፡፡ ለምሳሌ በዚህ እይታ በጥናቱ ከተሳተፉ አጠቃላይ ሰዎች 45 በመቶ (ብዙዎቹ ከ16 እስከ 24 እድሜ) የሚሆኑት ዋና የመረጃ ምንጫቸው ያልታመኑ ዩቲዩብ ቻናሎች ሲሆን፤ ሌሎች 40 በመቶውን የሚሸፍኑት ደግሞ (ብዙዎቹ ከ30 በታች) ዋና የመረጃ ምንጫቸው ከፌስቡክ እንደሆነ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡