ስጦታ ለልጆች…..የቀጠለ (2)
ልጅ አስተዳደግ እጅግ ከባድ ነገር ነው ፡፡ ከበድ ያለ ልጅ ማሳደግ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ያከብደዋል፡፡ journal Psychological Bulletin ላይ የወጣው ጥናት እንደጠቆመው ከሆነ እንደመንቀዥቀዥ እና እንደ የስሜት አሉታዊነት ያሉ ነገሮች ተፈጥሯዊ የሚሆኑበት ሁኔታ የጎላ ነው፡፡
ይሁንና የወላጆች የተስተካከለ የልጀ አስተዳደግ መኖር ከልጆቹ ተፈጥሯዊ በሃሪ በበለጠ የልጆቹ እጣ ፈንታ ላይ የመወሰን አቅሙ የጎላ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ በሃሪያቸው አስቸጋሪ የሆኑ ልጆች ፤ የተስተካከለ የአስተዳደግ ስልት ይበልጡኑ የሚያስፈልጋቸው እንደሆነ ጥናቱ አክሎ ጠቅሷል፡፡
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ መንገድ የሚከተሉ ወላጆች አሉታዊ የአስተዳደግ አካሄድ ከሚከተሉ ወላጆች በበለጠ ስኬታማ እና ፍሬያማ ልጆች ማሳደግ ችለዋል፡፡
አሉታዊ አስተዳደግ ስልት
• ውይይት አልባ፡- በዚህኛው የአስተዳደግ ስልት ውስጥ ነግግር የሚኖረው ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ነው፤ እሱም ከወላጅ ወደ ልጅ፡፡
• የተዘጋ ስርዓት ነው፡- በዚህ የአስተዳደግ ስልት ውስጥ ልጆች አማራጭ እንዲኖራቸው አይደረግም፡፡ ማለትም በልጆች እና በወላጆች መሃል ምንም ዓይነት ድርድር የለም፡፡
• ፈፃሚዎች ናቸው፡- በዚህ ቤት ውስጥ ልጆች ፈፃሚዎች ናቸው፡፡ ወላጆች የልጆቹን ያልተገራ በሀሪ የሚገሩት ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፍ ይመስላቸዋል፡፡
• ህግ ይበዛዋል፡- በዚህ ቤት ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ህግ ይበዛል፡፡ ያ ደግሞ ልጆቹን ይበልጥ እያራቀ እና ወላጆች እራሳቸውን ከልጆቻቸው እነዲነጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡
እንዲህ ያለው የአስተዳደግ ዓይነት የልጆቹን የተፈጥሮ አስቸጋሪ በሃሪ ለማስተካከል የማይረዳ ከመሆኑም እና ህፃናቱ ያለባቸውን የበሃሪ ችግር በራሳቸው እንደያዩት ካለማረጉ በተጨማሪ ለ ሁለት ዋና ዋና ችገሮች ያጋልጣቸዋል፡፡ እሱም
1ኛው፡- ለውስጣዊ ችግር ሲሆን በራስ መተማመናቸውንና ራስን የማወቅ ደረጃቸውን ይጎዳዋል፡
2ኛው፡- ለውጫዊ ችግር የሚያጋልጣቸው ሲሆን ከአከባቢያቸው እና ከሰዎች ጋር ጥሩ ተግባቦት እንዳይኖራቸው ያደርጋል፡፡
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ
አዎንታዊ የልጅ አስተዳደግ ሚከተሉ ወላጆች የተሳካ ደስተኛ እና ህይወት ያላቸውን ልጆች የማፍራት እድላቸው የሰፋ መሆኑን ጥናቱ ገልጧል፡፡ እኚህ ወላጆች ጠንካራ ህጎች ያሏቸው ቢሆኑም ፍቅር አይለያቸውም ይህም፡-
• ስለልጆቻቸው ህይወት ግድ እንሚሰጣቸው በተግባር ያሳያሉ
• ለልጆቹ ስኬት እና መልካም ስራ ሁሉ ሙገሳ እና አድናቆትን ይለግሳሉ
• ከልጆቻቸው የሚጠብቁት ነገር ግልፅ እና ተጨባጭ ጉዳይ ነው
• ልጆቻቸውን ያዳምጣሉ
• ቋሚ ስሜቶች አሏቸው
• የልጆቻቸውን አስተያየት ከግምት ያስገባሉ
• ፍቅራቸውን በቃላት ይገልጻሉ፡፡
• ልጆች የራሳቸውን እንዲመርጡ እድል ያመቻቻሉ
• የምርጫዎቻቸውን ውጤት ቀድመው ያስረዳሉ
እውቀት ከሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ውስጥ የልጅ አስተዳደግ የቁንጮውን ቦታ ይይዛል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ትንሽ ስህተት ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፡፡
አሉታዊ የሆነ በሀሪ የሚበዛባቸውን ልጆች ማስተካከል የሚቻለው በአሉታዊ መንገድ አይደለም፡፡ ይህ በልጡን ጥፋተኝነት እንዳሰማቸው ያደርጋል፡፡

አዎንታዊ ስነልቦና…..ክፍል ሁለት
ቀደም ብለን ባቀረብነው ፅሁፍ ውስጥ ለማሳይት እንደሞከርነው የዘመናዊ የስነልቦና ሳይንስ ትኩረት የተበላሸን መጠገን ላይ እና ችግርን ማወቅ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡
ለሳንቲስቶች እንደ ደስታ፣ ተስፋ እና ማገገም ያሉ እድሜ ጠገብ ፍልስፍናዎች ላይ አዲስ አሊያም ደግሞ ተጨማሪ እይታ እና አቅጣጫን ለመጠቆም መቻል ቀላል የቤት ስራ አይደለም፡፡ ምክኒያቱም እንደ እነዚህ ያሉ አጀንዳዎች ባለ ብዙ አቀጣጫ እውነታዎች ናቸውና፡፡
የአዎንታዊ ስነልቦና ታሪካዊ አውድ
ይህ ሳይንስ ለመጀመሪያ ጊዜ በማርቲን ሴሊግማን በ1998 የተዋወቀ አንደሆነ ይነገራል፡፡ ይሁንና በርካታ ጥናቶች ሊያረጋግጡ እንደቻሉት ከሆነ ሳይንሱ ቀደም ብሎ የታወቀና ብዙ የተባለለት እንደሆነ ነው፡፡
አዎንታዊ ስነልቦና በዊሊያም ጄምስ እና ከዛም ቀጥሎ በ1950 አከባቢ በአብራሃም ማስሎው በሰፊው ተቃኝቷል፡፡ ይሁንና በ1998 አከባቢ የተጀመረው የዳግማዊ አዎንታዊ ስነልቦና አብዮት ለእነዚህ ቀደምት ሳይንቲስቶች እውቅና አልሰጠም፡፡ ምክኒያቱ ደግሞ ሳንቲፊክ የሆኑ ማስረጃዎች ይጎሏቸዋል የሚል ነበር፡፡
ይሁንና ሁሉም ተመሳሳይ ሃሳብ እና ዘውግ ላይ የሚያጠነጥኑ በመሆናቸው ጉዳዩ ያን ያህል አሳሳቢ ሳይሆን ቀጥሏል፡፡
የዚህ ሳይንስ መነሸ ሃሳብ የስነልቦና ሳይንስ አጠቃላይ አንድምታ አሉታዊ ስሜትን ይፈጥራል የሚል ነበር፡፡
ያም የሚሆንበት ምክኒያት ሳይንሱ ማለትም የስነልቦና ሳይንስ ሰዎች ስለጎደላቸው ነገር ብቻ የሚያወራ በመሆኑ ነው የሚሉት እነዚህ የአዎንታዊ ስነልቦና ሳይንስ አቀንቃኞች የስነልቦና ሳይንስ ቅኝት ወደ አዎንታዊነት ሊዞር ይገባዋል ብለዋል፡፡
የሰው ልጅ የጎደለውን ከማወቁ ይልቅ ያለውን ቢያውቅ የተሸለ የስነልቦና ደረጃ ላይ ይደርሳልም ብለዋል፡፡
በአዎንታዊ ስነልቦና ሳይንስ ውስጥ የተለያዩ የእርዳታ መንገዶች ተቀምጠዋል እነርሱም “positive psychology interventions.” (ppi) በመባል የሚጠሩ ሲሆኑ እነርሱም አስራ ሁለት ናቸው፡፡
እነዚህን የአዎንታዊ የስነልቦና የእርዳታ መንገዶች ሁሉም የስነልቦና ባለሞያዎች ቢጠቀሙበት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላልም ብለዋል፡፡
1- ምስጋና መለማመድ፡- በዚህ ልምመድ ውስጥ ሰዎች ቢያንስ ስላላቸው እና ደስ ስለሚሰኙበት የህይወታቸው አካል ቢያንስ 3 ነገር እንዲፅፉ ይደረጋል፡፡ ይህ መንገድ የማመስገን ባህላቸውን እና የደስታ መጠናቸውን ከፍ የሚያደርገው እንደሆነ ሊረጋገጥ ችሏል፡፡ ሰዎች ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ፀጋ በሚቆጥሩበት ጊዜ የሚፈጠርባቸው የስሜት ከፍታ ስነልቦናቸውን ረዘም ላለ ጊዜ ማደስ እንደቻለ ጥናቶቹ አሳይተዋል፡፡
እንደዚህ ያሉ ሰዋዊ የሆኑ ሳይንሶች እያደጉ እና እየበለፀጉ በመጡ ቁጥር መንፈሳዊነትን እና ኃይማኖተኝነትን እያረጋገጡ እና እያጎለበቱ እንደሚሄዱ ግልፅ ነው፡፡ ምስጋና የስነልቦናን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ እና ማመስገን የዕለታዊ ስንቃችን እንደሆነ የሚናገሩ ብዙ የቅዱሳን መፃህፍት አናቅፆች ያሉ ሲሆን ለምሳሌ ያህል በመፅሀፍ ቅዱስ ቆሮ 9፤15 እና በቅዱስ ቁርአን 14፤34 የተጠቀሱት ለዚህ እንደማስረጃነት መቀመጥ ይችላሉ፡፡
በቀጣይ ክፍላችን የቀሩትን የ “positive psychology interventions.” አንድ በአንድ ለማይት ምንሞክር እንደሆነ ቃል እየገባን መልካም ቀን ተምኝተናል፡፡
ሼር
ምንጭ፡- psycologytoday, he History of Positive Psychology እና ሌሎችም

የ 'Black Panther' ፊልም ቴክኖሎጂዎች ከልብ ወለድነት ከፍ ያሉ ናቸው
ይህ ፊልም ዓለምን ያነጋገረ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገቢን ለፊልም ኢንደስትሪው ያስገባም ጭምር ነው፡፡ በ 'Black Panther' ፈልም ውስጥ ያለችው የዋካንዳ ግዛት እጅግ አስደናቂ ቴክኖሎጂዎች የሚታዩባት እና ፍፁም ስልጡን ከተማ ነች፡፡ ፊልሙ ውስጥ የታዩት ቴክኖሎጂዎችም እጅቅ ምጡቅ እና የተጋነኑም ይመስሉ ነበር፡፡
ከነሱም ውስጥ በራሳቸው የሚበሩ አውሮፕላኖች፣ በ virtual reality (VR) ቴክኖሎጂ በቀላሉ ሊንቀሳቀሱ የሚችሉ መኪናዎች ፣ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥራት ያላቸው ስክሪኖች እና ማግኔታማ የባቡር ሃዲዶች በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡
ከዛም በተጨማሪ ንጉሱ የሚለብሳቸው የተለየ አቅም እና ጉልበት የሚሰጡ እንዲሁም የሰበቃ ቅስቃሴውን (kinetic energy)የሚቆጣጠሩ እና ሃይል የሚሰበስቡ አልባሳቶች በፊልሙ ላይ ተስተውለዋል፡፡
እነዚህ አስደናቂ ቴክኖሎጂዎች ምናባዊ ብቻ አይደሉም፡፡ በ ማርች 30 በፊልሙ ውስጥ ስላሉት የሳይንስ ውጤቶች እና ሃሳቦች የሚተነተኑበት የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን በውይይቱ ወቅትም ከተለያየ አቅጣጫ የመጡ የቴክኖሎጂ ባለሞያዎች የነበሩ ሲሆን ፊልሙ ውስጥ ስላሉት ቴክኖሎጂዎች እውነተኝነትም ተናግረዋል፡፡
ከዛም በተጨማሪ ቴክኖሎጂዎቹ የሚዋቀሩበት ንጥረ ነገሮች በአፍሪካ ብቻ በተረፍ የሚገኙ አንጡር ሃብቶች መሆናቸውም ሌላው አስደናቂ እውነት ነው ብለዋል ፡፡
የ Smithsonian National Museum ዳይሬክተር የሆኑት Gus Casely-Hayfor በውይይቱ ወቅት አሁን አሁን የአፍሪካ አገራት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ከ ምዕራባዊያኑ በላይ እንደሆነ ገልፀው የነበረ ሲሆን ባለፈው ዓመት በወጣው የአፍሪካ ታይም መፅሄት ላይም የስማርት ስልክ እና ኮምፑተርን በመጠቀም አፍሪካ አንደኛ ናት ያለ ሲሆን ከዛም ውስጥ ናይጄሪያ፣ጋና ፣ ኮንጎ እና ኮትዲቯር በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ ሲልም አስነብቧል፡፡
ይህ ፊልም ለጥቁር ህዝቦች የተለየ ስሜትን ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ለኢትዮጲያዊያን ደግሞ ልዩ ትርጉም ነበረው፡፡ ፊልሙ ውስጥ የታዩት ገፅታዎች ለኢትዮጲያ እና ለኢትዮጲያዊያን የሚቀርብ እንደነበር ከተለያየ አቅጣጫ በተሰጡ አስተያየቶች ማወቅ ተችሏል፡፡
ያልተነካ ኃይል፣ እውቀት እና መሬት ያላት አፍሪካ ዋካንዳን መሆን የምትችልበት ብዙ ምክኒያቶች አሏት እያልን 'Black Panther ፊልምን ተጋበዙልን ብለናል፡፡ ሼር
ምንጭ፡- Live Science

ብቸኝነት፡- ለህብረተሰብ ጤና ዋነኘው ተጠያቂ ሆነ
ዓለም አቀፋዊነት የዓለማችን እጣ ፈንታ ሁኗል፡፡ ዓለም እንደ አንድ ቤት የዓለም ህዝቦች ደግሞ እንደ አንድ ቤተሰብ ከሆኑ ቆይቷል፡፡ በአንድ ጥላ ስር ለሚኖር ቤተሰብ ደግሞ ተነጣጥሎ የሚመጣ ችግርም ሆነ በረከት አይኖርም የአንዱ ቃስታ ለአንዱ ይሰማል በአንዱ ሙዚቃም ሌላው ይዝናናል፡፡
ይህ ዓይነቱ ትስስር ተመሳሳይ የአኗኗር ዘይቤ ፣ ተመሳሳይ የአመለካካት ውቅር እና ተመሳሳይ እጣ ፈንታ እንዲኖር ያስገድዳል፡፡
ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ አሁን አሁን በከፍተኛ ሁኔታ የህብረተሰብ ጤና አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንዲደርስ አድርጓል፡፡ የበዛ የአልኮል አወሳሰድ ፣ የታዳጊዎች በአደገኛ ሁኔታ በሱስ መጠመድ እና ረዘም ላለ ሰዓት መቀመጥ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠቀሱ ሲሆን በቅርቡ የብሪገሃም ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰር በሆኑት በፕሮፌሰር ጁሊያን ሆልት ለንስታንድ የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን ብቸኝነት አሁን ላይ ከፍተኛውን የህብረተሰብ ጤና ስጋትን በበላይነት ይመራል ብለዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ እናዳሉት "የሰው ለሰው ግንኙነቶች ለሰው ልጅ ለመኖር እና በህይወት ለመቆየት የሚያስፈልግ መሰረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ የጨቅላ ህጻናት ማቆያን በተመለከተ የተደረገው ጥናት እንዳሳየው ከሆነም አጠገባቸው ሰው ከነበራቸው ጨቅላ ህፃናት ይልቅ ለብቻቸው ተነጥለው ተቀምጠው የነበሩት ለሞት የመጋለጥ እድላቸው የሰፋ ነበር፡፡ ከዛም በላይ ሰዎችን ከህብረተሰባቸው ተነጥለው እንዲቆዩ ማድረግ የሰው ልጆች ለዘመናት ሲጠቀሙበት የነበረ የቅጣት ዓይነት እና ፍርድም ጭምር ነው፡፡ይሁንና አሜሪካዊያን በአሁኑ ሰዓት ይህን የቅጣት ፍርድ በራሳቸው ላይ እየፈረዱ ይገኛሉ፡፡"
ይህንኑ የብቸኝነት ጣጣን በተመለከተ AARP ያወጣው ጥናት እንሚያሳየው ከሆነ በአሜሪካ እድሜያቸው ከ45 ዓመት በላይ የሆኑ ወደ 42ሚሊዮን የሚጠጉ ጎልማሶች በአሰቃቂ የብቸኝነት ህይወትን እየገፉ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡
በቅርቡ የወጣው የህዝብ ቆጠራ ውጤት ደግሞ እጅግ አስፈሪ የሆነን ዜና ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ እሱም ግማሹ የአሜሪካን ህዝብ ያላገባ እንደሆነና ሩቡ ደግሞ በፍፁም ብቸኝነት እየኖረ እንደሚገኝ አሳይቷል፤ ይህም የማግባት እና የመውለድ ምጣኔ እጅጉን እንዲያሽቆለቁል ምክኒያት ሆኖታል ተብሏል፡፡
ሚሊዮኖችን ላይ የተሰራው የፕሮፌሰሩ ጥናት አሜሪካዊያንን ፣ አውሮፓዊያንን እና አሲያዊያንን ያሳተፈ የነበረ ሲሆን የጥናቱ ውጤት እንዳሳየው ከሆነ ብቸኝነት ያለእድሜ ሞትን ያስከትላል፡፡ በተጨማሪም ማህበረሳዊ ግንኙነቶች ያላቸው ሰዎች 50 በመቶ ያህል ያለእድሜ ከመሞት የማምለጥ እድል አላቸው ብሏል፡፡
በስተመጨረሻም ፕሮፌሰሩ እንደዚህ ካለው አሳሳቢ ቀውስ ለመውጣት ለተማሪዎች፣ ለህጻናት እና ለህብረተሰቡ የተለያዩ ስልጠናዎች እና ትምህርቶች መሰጠት አለበት ያሉ ሲሆን አክለውም ሀኪሞች ከበሽተኞቻቸው ጋር ቅርበት ሊኖራቸው እና ህብረተሰቡም አንዱ ከአንዱ የሚተሳሰርበት የገንዘብ ፍሰት ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡
ጉዳዩ አሳሳቢ ነው በተለይም ዘመናዊነትን በፈርቀዳጅነት እየመሩ የሚገኙት ምዕራባዊያን የገቡበት ጉርጓድ ውስጥ ተከትሎ የማይገባ አንድ ህብረተሰብ በጠፋበት በዚህ ዘመን ውስጥ ይህ በሽታ ወደ ሌላው አይዛመትም ለማለት ይከብዳል፡፡
ስለዚህ ብቸኝነት የሚባል ገደል ከፊታችን እየጠበቀን እንደሆነ ልብ እንበል፡፡ ኢትዮጲያዊነት ገደሉ ላይ የሚዘረጋ አስተማማኝ ድልድይ ነው ባህላችንን እንታጠቅ እያልን ከዚህ ልናመልጥ ያስችልናል የምንለውን መንገድ በኮሜንት መስጫ ሳጥን ውስጥ በማስቀምጥ እንድንማማር በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ለኮሜንት መንደርደሪያ፡- ምናልባት ፕሮፌሰሩ ያቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ በኛ ሲተረጎም እድራችንን እና እቁባችንን እናጠናክር የሚል አንድምታ ይኖረው ይሆን?..... ሼር
ምንጭ፡-RedOrbit

ጭንቀት ተላላፊ በሽታ እንደሆነ ተረጋገጠ
ከ ወደ nature neuroscience መንደር አእምሮንና ጭንቀትን በተመለከተ ፕሮፌሰር ጄዲፕ ቤን እና ቡድናቸው ባደረጉት ጥናት መሰረት ጭንቀት እንደሚተላለፍ ተረጋገጠ።
ጥናቱ ሁለት ወንድና ሴት ጥንድ አይጦች ላይ የተደረገ ሲሆን፡ በሂደቱ ውስጥ እንደታየው ከሆነ ወንዱ አይጥ ውስጥ የተፈጠረው ጭንቀት ወደ ሴቷ አይጥ በተመሳሳይ ሁኔታ ሊተላለፍ ችሏል።
“ጭንቀትና ውጥረት ተዛማጅ በሽታዎች እንደሆኑ ጥናታችን ሊያረጋግጥ ችሏል” ያሉት ፕሮፌሰሩ “ስለሁኔታው ዘላቂነት ግን እስካሁን ያወቅነው ነገር የለም” ብለዋል።
አጥኚዎቹ ጥንዶቹን አይጦች በመነጣጠልና አንደኛውን አይጥ ብቻዉን ለጭንቀት እንዲጋለጥና ወደ አጋሩ ሳይመለስ ለብቻው እንቂቆይ ቢያደርጉም እንኳ አእምሮ ለጭንቀት ሲጋለጥ የሚመነጨው የCRH ኒውሮን በተመሳሳይ መልኩ የሴት አጋሩ አእምሮ ውስጥ ሊመነጭ ችሏል።
“ይህ በአይጦቹ ላይ የታየው ሁኔታ በሰው ልጆችም ላይ ሊሰራ የሚችልበት እድል ሰፊ ነው” ያሉት የጥናት ቡድኑ መሪ ፕሮፌሰር ቤን “አስበነውም ይሁን ሳናስበው ጭንቀታችንን ለሌላ ሰው እናስተላልፋለን” ያሉ ሲሆን አክለውም “በተለይ በሚፋቀሩና ቤተሰብ በሆኑ ሰዎች ላይ ሁኔታው ይበረታል“ ብለዋል።
ተመራራማሪዎቹ ስለጥናታቸው አጠቃላይ አንድምታ ሲናገሩ እንዳሉት ከሆነ ከዚህ ምርምር የምንረዳው ትልቁ ቁም ነገር ማህበራዊ ህይወትና ስሜት ቀጥተኛ ዝምድና ያላቸው መሆኑንና ስለ አንዱ ጉዳት መጎዳት ያለንን ማህበራዊ ትስስር ማሳያም ጭምር እንደሆነ ነው ብለዋል።
ምንጭ፡ ScienceDaily

ጾም ከመንፍሳዊ ጥቅም ባሻገር
ጾምን የሚጾሙት መንፍሳዊ ጥቅምን ለማግኘት ነው። ነገር ግን ጾም ከመንፍሳዊ ጥቅም ባሻገር የጤና ጥቅሞችም እንዳሉት ያውቁ ኖሯል? እንግዲያውስ ፆም ከሜስገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ የተወሰኑቱን እንንገራችሁ፡-
• የኢንሱሊን መጠንን በመቆጣጠር ከዓይነት ሁለት ስኳር በሽታ ይታደጋል
ፃም በተለያዩ ጥናቶች እንደተረጋገጠው ሰውነት ውስጥ የሚኖርን የስኳር መጠንን የመቀነስ በሀሪ ታይቶበታል፡፡
በተደረገው ጥናት ላይም እንታየው ከሆነ ትናንት ፆሞ የነበረ ሰው በነጋታው ጠዋት በፆም ሆዱ የስኳር መጠኑ በሚመረመርበት ጊዜ በደም ውስጥ የሚገኘው የስኳር መጠን ከ 3-6 በመቶ መቀነስን ያሳየ ሲሆን የኢንሱሊን መጠኑ ደግሞ ከ20-31 በመቶ መቀነስን አሳይቷል፡፡
ከዛም በተጨማሪ በጥናቱ ውስጥ እንደተረጋገጠው የስኳር በሽታ መጥፎ ውጤት በመሆኑ ከሚታወቀው ከኩላሊት ውድመት ይታደጋል ተብሏል፡፡
በስተመጨረሻም ተመራማሪዎቹ ዓይነት ሁለት የስኳር በሽታ ሊኖርባቸው ላሉ በሽተኞች (ድንበር ላይ ያሉ በሽተኞች) ፆምን እንደመከላከያ ቢጠቀሙት ውጤቱ ፍሬያማ ይሆናል ሲሉ መክረዋል፡፡
• ከልብ በሽታ ለመታደግ
ተመራማሪዎቹ እንዳሉት ከሆነ ፆም እንደ ደም ግፊት ፣ መጥፎ ኮሌስትሮል፣ የደም የስኳር መጠን እና ሌሎችንም ለልብ በሽታ መንስዔ ሊሆኑ የሚችሉትን (risk factors) ሁሉ ከሰውነት የማስወገድ በሀሪ ስላለው በልብ በሽታ የመጠቃት እድልን ያጣብባል ብለዋል፡፡
ሆኖም ጉዳዩ ሰፊ ጥናት የሚስፈልገው በመሆኑ ከዚህ በላይ በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ነገር የለም ብለዋል፡፡
• ክብድት መቀነስ
በጾም ወቅት ሰውንታችን ከምግብ ሀይል ስለማያግኝ ሀይልን ፍለጋ ጉበት እና ጡንቻዎች ላይ ወደ ተጠራቀሙ ጉሉኮሶች ይጠጋል። ይህም ምግብ ከተበላ ከ8 ሰዓት በኋላ ይጀምራል።
የተከማቸዉን ግሉኮስ ከተጠቀመ በኋላ ሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ማቃጠል ይጀምራል ይህ ደግሞ በተራው ክብድት መቀነስን ያስክትላል። በተለይም ደግሞ ሆድ አከባቢ ያሉ አላስፈላጊ ስቦችን የማስወገድ አቅሙ ከፍተኛ ነው ብለወል፡፡
• የኮሌስትሮል መጠን (cholesterol levels) መቀነስ
የሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ማቃጠል ጡንቻን ለማቆየት እና የኮሌስትሮል መጠን ለመቀነስ ይረዳል።
• ሰውንት ማጥራት
ሰውነታችን ስብን(fat) በሚያቃጠል ጊዜ በሰውነታችን መርዝ የማስወገድ (detoxification) ሂድትም ይፈጠራል ።
ምክንያቱም ሰውነታችን ስብን (fat) እንደ ሃይል ምንጭ አድርጎ ሲያቃጠል በሰውነት ስብ ውስጥ ተከማችተው የነበሩ ማንኛውም መርዛማ ነገሮች ይሟሟሉ እንዲሁም ከሰውነታችን ይወገዳሉ።
• አእምሮ ጤና
ከትንሽ ጊዜ ጾም በኋላ ከፍ ያለ መጠን ያላቸው ኢንዶርፊኖች (endorphins) (የጥሩ ስሜት ሆርሞኖች) በደማችን ውስጥ ይመረታል ይህም አእምሮ ጤና ላይ መልካም ለውጥ ያመጣል። ሼር
ረመዳን ከሪም
ምንጭ፦ Medical News Today and healthline

የጥርስ ህምም እያሰቃይዎ ነው?
እንግዲያውስ ጥንታዊያን ህንዶች በቤት ውስጥ የጥርስ ህምምን ለማስታገስ ይጠቀሙዋቸው የነበሩትን መድሃኒቶች እንንገርዎ፡-
1- የተወሰነ የተፈጨ ቀንዶ በርበሬ እና በመጠን ከቆንዶ በርበሬው እኩል የሆነ የተፈጨ ጨው አንድ ላይ በመጠነኛ ውሃ በመለወስ ልክ እንደ ጭቃ ያለ ቅርፅ ሲኖረው አንስቶ የተጎዳው ጥርስ ላይ በመቀባት ፋታ ከሚያሳጣው የጥርስ ህምም እፎይታ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
2- አንድ ወይንም ሁለት ፍሬ ነጭ ሽንኩርት ቀጥ ቀጥ አድርጎ እና ላዩ ላይ የተወሰነ ጨው ነስንሶ የታመመው ጥርስ ላይ መቀባት፡፡
3- የተፈጨ ቁሩንፉድን በዘይት ለውሶ የታመመው ጥርስ ላይ መቀባት
በተጨማሪም ከህመሙ በተጨማሪ እብጠት ያለ እንደሆነ ጥንታዊ ህንዳዊያን ጥሬ ቀይ ሽንኩርት እንዲያኝኩ የሚመክሩ ሲሆን ሳያኝኩ እዛው ቦታ ላይ ይዞ ማቆየትም አከባቢው ላይ ያሉ ጎጂ ህዋሳትን የሚገል በመሆኑ እብጠቱ እንዲጠፋ ይረዳል ይላሉ፡፡ ሼር
ምንጭ፡- TOP 10 HOME REMEDIES

እንቅልፍ እጦት ፕሮቲኖችን ይጎዳል
በኮሎራዶ ቡልደር ዩኒቨርስቲ የተከናወነው አዲሱ የሳይንቲስቶች ምርምር ሰዎች በ24 ሰዓት ውስጥ በሚተኙበትና በሚመገቡበት ወቅት በደማቸው ውስጥ የሚገኘው የፕሮቲን መጠን እንዴት እንደሚቀያየር ለማየት ያስቻለ አዲስ ምርምር ነው፡፡
በዚህም መነሻነት ተመራማሪዎቹ በጥናቱ ለማሳየት እንደሞከሩት ሰዎች ሌሊቱን ሙሉ ያለእንቅልፍ በሚያድሩበት ጊዜ ከመቶ በላይ ለሚሆኑ የፕሮቲን አይነቶች በደም ውስጥ ለሚኖራቸው ቅርፅ ወይም ፓተርን የመፋለስ ምክንየት ይሆናል፡፡
በምርምሩ ላይ ስድስት የሚሆኑ ፍቃደኛ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን በዩኒቨርስቲው በሚገኝ የምርምር ማዕከል ለስድስት ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ የአመጋገብ ሁኔታቸው፣ የሚተኙበት ሰዓት እና በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሲደረግ ነበር፡፡
በተጨማሪም የሰዎቹን 1,129 የሚሆን የተለያየ የፕሮቲን አይነት የእንቅስቃሴ ሁኔታ ለመረዳት ሲባል የደም ናሙናቸውን በየአራት ሰዓት ለመውሰድ ተሞክሯል፡፡ በዚህም ሂደት ለሁለት ቀን ከቆዩ በኋላ በሶስተኛው ቀን አሰራራቸውን በመቀየር ቀን ለስምንት ሰዓታት እየተኙ ሌሊቱን ያለእንቅልፍ እንዲያድሩና እንዲመገቡ ተደርጓል፡፡ በውጤቱም 129 የሚሆኑ የፕሮቲን አይነቶች በማታው ሺፍት የተነሳ በቅርፃቸው ላይ የመነጠል ወይም የመፋለስ ነገር ታይቶባቸዋል፡፡
ምርምሩን በቀዳሚነት ሲመሩት ከነበሩት መካከል አንዱ የሆኑት ክርስቶፎር ዴፕነር ስለሁኔታው ሲገልፁ በቀንና ማታ በሚኖረው የእንቅልፍ ወይም የአመጋገብ ለውጥ፤ ወሳኝ የሆኑ የፕሮቲን አይነቶች በመፋለስ (disruption) ምክንያት ለችግር እንደሚጋለጡ ተናግረዋል፡፡
እንደምሳሌም ሲገልፁ ግሉኮን (glucagon) የተሰኘውን የፕሮቲን አይነት የጠቀሱ ሲሆን ይህም በደም ዝውውር ላይ ጉበት የሚረጨውን ከፍተኛ መጠን ያለው ስኳር የሚያስገኝ ወሳኝ ፕሮቲን ነው፡፡ በመሆኑም ማታ በሺፍት የሚሰሩና ሌሊቱን ያለእንቅልፍ በማደር የሚያሳልፉ ሰዎች ከሌሎች በተለየ የስኳር መጠናቸው ዝቅ የማለትና እና መሰል ተያያዥ ችግሮች ሊየጋጥሟቸው እንደሚችል ተጠቅሷል፡፡ ሼር
ምንጭ፡ newatlas እና Tech Explorist

ሻይ ቅጠል የካንሰር ሴልን ይገላል
ከወደ ህንድ አቅጣጫ ያፈተለከው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ የስዋንሲያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች በሻሂ ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ቅንጣቶች በማደግ ላይ የሚገኙ የሳንባ ካንሰሮችን 80 በመቶ ያህል ሊያጠፉ እንደቻሉ አረጋግጠዋል፡፡
ተመራማሪዎቹ ይህንን ግኝት እንዲያገኙ ምክኒያት የሆናቸው መነሻ የተጠነሰሰው የናኖ ቴክኖሎጂ አዲስ ግኝት የሆነውን የኳንተም ዶት ቴክኖሎጂን ለማጥናት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ነበር፡፡
ኳንተም ዶት ቴክኖሎጂ ማለት ከ10 ናኖ ሜትር በታች የሆነ መጠን ያላቸውን ረቂቅ ቅንጣቶችን ለመለካት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ዓይነት ነው፡፡ (አንድ የፀጉር ዘለላ ውፍረት 40ሺህ ናኖ ሜትር ነው)፡፡
ይህ የናኖ ቴክኖሎጂ አብዮት ዓለምን ወደ ፊት ብዙ እርምጃ ያራመደ ሲሆን ከኢንስትሪው መንደር አንስቶ ለግብርናውም ሆነ ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ እርደታን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በጤናው ዘርፍ ናኖ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ የካንሰር ሴሎችን ከእንጭጫቸው በመቅጨት እንዳይራቡ እና እንያዳያጉ ለማድረግ እየተሞከረ እንሆነ የተናገሩት ተመራማሪዎቹ ይህ ኳንተም ዶት የተሰኘውን ቴክኖሎጂ መጠቀም ከተቻለ ደግሞ በእርግጠኝነት የካንሰር ሴል ርቢን ማስቆም ይቻለናል ብለዋል፡፡
ይሁንና እስካሁን በተደረገው ጥናት መሰረት በኳንተም ዶት የሚዘጋጁ መድሀኒቶች ወደ ሰውነታችን የሚገቡት በኬሚካል እገዛ በመሆኑ የኬሚካሉን የጎንዮሽ ጉዳት ማስቀረት የምንችልበት ሌላ አማራጭ መንገድ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
ከወደ ህንድ የሚገኙ የስዋንሱያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ኳንተም ዶትን ወደ ሰውነታችን በምናስገባበት ወቅት የምንወስደው የኬሚካል ዓይነት ለሰውነታችን ተስማሚ ሊሆን የሚችልበትን መንገድ አጊኝተናል ያሉ ሲሆን እሱም መድሃኒቱን በሻሂ ቅጠል ውስጥ አድርጎ መስራት ነው ብለዋል፡፡
የምርምር ቡድን መሪ የሆኑት ዶክተር ሱዳጋር እንዳሉት ከሆነ የሻሂ ቅጠል በውስጡ የተለያዩ አሚኖ አሲዶች፣ ቫይታሚኖች እና ፀረ-መርዛም ውህዶችን የያዘ በመሆኑ ኳንተም ዶትን ለመስራት ዓይነተኛ አማራጭ ሁኖ አጊኝተነዋል ያሉ ሲሆን በቀላሉ የሚገኝ እና ከዋጋ አንጻርም ያን ያህል የማይጎዳ በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል ብለዋል ፡፡
አክለውም የኳንተም ዶት ቴክኖሎጂን እውን ለመድረግ ባደረግነው ሙከራ ውስጥ ያላሰብነውን ውጤት አጊኝተናል ያሉ ሲሆን እሱም የሳንባ ካንሰር ሴል እድገትን ይገታል ብለን በኳንተም ዶት ቴክኖሎጂ ወደ ሰውነት ውስጥ ከላክነው መድሀኒት ይልቅ በሻሂ ቅጠል ውስጥ የሚገኙ ረቂቅ ቅንጣቶች የሳንባ ሴል እድገትን 80 በመቶ ያህል በተሳካ ሁኔታ ከትተውታል ብለዋል፡፡ ሼር
ምንጭ፡- ScienceDaily

ለእሳት አደጋ የሚደረግ የመጀመሪያ ዕርዳታና ህክምና
የቆዳ ቃጠሎ በሙቀት፣ ኤሌክትሪክ፣ ኬሚካል፣ ፀሃይ ወይም ጨረርና ሌሎች አደጋዎች አማካይነት የሰውነት ህዋሶቻችን ላይ የሚደርስ ጉዳት ሲሆን በደረሰው የጉዳት መጠን ላይ ተመርኩዘን በደረጃ ልንከፋፍለው እንችላለን፡፡
ቀዳሚው የመጀመሪያ ደረጃ ቃጠሎ ሲሆን፤ ኤፒደርሚስ (Epidermis) በመባል የሚጠራው የላይኛው የቆዳችን አካል ላይ የሚደርስ መጠነኛ ቃጠሎ ነው፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ ኤፒደርሚስ እንዲሁም ከስሩ የሚገኘውን ደርሚስ (Dermis) የተባለ ሽፋን የሚያቃጥል ነው፡፡
የቆዳን ሽፋኖች ሙሉ በሙሉ አልፎ ከስራቸው የሚገኘው የስብ ሽፋንና አጥንት ላይ ያረፈ ቃጠሎ የሶስተኛ ደረጃ ቃጠሎ ተብሎ ሲጠራ፤ የደምና ደም ስር ጥፋትን በማስከተል ወደ ሞት መንደር ሊያደርሰን ይቻለዋል፡፡ ታድያ የሚደረጉት ህክምናዎችም በነዚህ የቃጠሎ ደረጃዎችና በሚሸፍነው የቆዳ አካል ላይ በመንተራስ ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ቃጠሎ ላይ እብጠት፣ ውሃ መቋጠር፣ ማቃጠል፣ የማቃጠል ስሜትና መቅላት ሲያጋጥመን፣ በዚህ ጊዜ፡-
• ማቃጠሉ እስኪቀንስ ድረስ ቀዝቃዛ ውሃን (በረዶ ደረጃ ያልደረሰ) በተቃጠለው የሰውነት አካል ላይ ማፍሰስ
• ማቃጠሉ ከቀነሰ ወዲያው ከተቻለ የኢንፌክሽን መከላከያ (Wound Gel) መጠቀም፤ ካልሆነ በፋሻ ወይም ንፁህ ጨርቅ መሸፈን
• እብጠት ከመከሰቱ አስቀድሞ በተጎዳው ሰውነት ላይ የሚገኙ ማንኛውም ዓይነት ጌጣጌጥና ቁሳቁሶችን ማስወገድ
• የቃጠሎው ቦታ ውሃ ከቋጠረ አለማፈንዳት
• የህመም ስሜት ከቀጠለ የህመም መከላከያ መድሃኒትን መውሰድ
• የቃጠሎው ቦታ ከታከመ በኋላ የጉዳት ቦታውን በልብስና ሌሎች መከላከያዎች አማካይነት በመሸፈን ከፀሃይ መከላከል
• በሁለተኛ ደረጃ ቃጠሎ ወቅት ጥልቅ ህመም ከመሰማቱም በተጨማሪ እጅ፣ ፊት፣ ጭን እና ዙሪያው፣ መቀመጫ፣ እንዲሁም ውስጥ እግርና ሌሎች ዋና ዋና ቦታዎች ላይ አደጋው ሲደርስ አስቸኳይ የህክምና ባለሙያ እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ቃጠሎ ሲያጋጥመን፡-
• በአስቸኳይ ወደ ለህክምና ባለሙያ ጥሪ ማድረግ
• ከባሰ ጉዳት ለመዳን ከቃጠሎው ቦታ በአስቸኳይ መራቅ
• የንፁህ አየር አቅርቦትን እንዲሁም የአተነፋፈስ ስርዓትና የደም ዝውውር አለመታወኩን ማረጋገጥ
• ቃጠሎ የደረሰበትን የሰውነት ክፍል ንፁህ፣ እርጥብና ቀዝቃዛ በሆነ ፋሻ መሸፈን
• ቃጠሎ የደረሰበት የሰውነት አካል እጅግ ሰፊ ከሆነ ተጎጂውን ከሰውነት ሙቀት ማነስ ወይም ከፍተኛ የቅዝቃዜ መጠን ለመጠበቅ ቀዝቃዛ ውሃን ከማፍሰስ መቆጠብ
• ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ ማንኛውንም ቁስ ከተቃጠለው የሰውነት ክፍል ላይ ማንሳት
• በሶስተኛ ደረጃ ቃጠሎ ወቅት የሚተገበሩ የህክምና ስራዎች (በህክምና ባለሙያ ብቻ) ተከታዮቹን ያጠቃልላሉ፡-
• የጉዳት ጠጋኝ መድሃኒቶችን፣ ሎሽን እና የቁስል ቅባት (Ointments) መጠቀም
• ህመምና ፍርሃትን የሚቀንሱ መድሃኒቶችን መጠቀም
• የደም ግፊትንና ድርቀትን ለመከላከል የሰውነት ፈሳሽ መጠንን መቆጣጠር
• ያመረቀዙና የሞቱ ህዋሳትን ከሰውነት ላይ እንዲያነሳ የቁስል መሸፈኛን (Wound Dressing) መጠቀም
• ከኢንፌክሽን እንዲጠብቅ ፀረ-ባክቴሪያን (Antibiotics) መጠቀም
• ቲታኖስ መውጋት
• እንደአስፈላጊነቱ የፊዚዮቴራፒ ህክምና መከወን
• እንደአስፈላጊነቱ የመተንፈሻ መሳሪያ መጠቀም
• ቁስልን አንሺ ቀዶ ህክምና
• የቆዳ ንቅለ ተከላ ቀዶ ህክምና
• ጠባሳን አካሚ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምና
• ሼር
ምንጭ፡- News Medical

በ2018ቱ የሩሲያ ዓለም ዋንጫ የሚተገበሩ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች
ሐሙስ የሚጀመረው የ2018ቱ ፊፋ የአለም ዋንጫ ከእግር ኳሳዊ ገፅታው በተጨማሪ በውድድሩ ታሪክ አዲስ የሆኑና ዘመን አፈራሽ ቴክኖሎጂዎችንም የያዘ ነው፡፡ ታድያ እነዚህ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ገፅታዎች በውድድሩ ላይ በሚደረጉት 64 ጨዋታዎች ላይ ለቡድኖችም ሆነ ለዳኞች ከቀድሞው ጊዜ እጅግ የተሻለና ለውሳኔ አሰጣጥ የሚረዳ መረጃን ያቀርባሉ፡፡ እነዚህም እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡፡
የግብ መስመር ቴክኖሎጂ (Goal-Line Technology)
የግብ መስመር ቴክኖሎጂን የተገበረው የመጀመሪያ አለም ዋንጫ ያለፈው የብራዚል አለም ዋንጫ ነው፡፡ ሆኖም ዳኞች ይህን ቴክኖሎጂ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚያውሉት ይሆናል፡፡ አስራ አራት ፈጣን ካሜራዎችን የሚጠቀመው ይህ ቴክኖሎጂ ኳስ የግብ መስመርን ባለፈበት ቅፅበት ከአንድ ሴኮንድ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለዳኛው ምልክት የሚሰጥ ነው፡፡
በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዘ ዳኝነት (Video Assistant Referee)
የአለም አቀፉ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን ወይም ፊፋ ቦርድ የዚህን ቴክኖሎጂ ትግበራ ባለፈው መጋቢት ላይ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ የአለም ዋንጫ ቴክኖሎጂውን በመተግበት የመጀመሪያው ይሆናል፡፡
ሆኖም የሚተገበረው ግልፅና የማያሻሙ እንዲሁም ውጤት ቀያሪ በሆኑ ስህተቶች ላይ ብቻ ብያኔ ለማሳለፍ ይሆናል፡፡ ዳኞች ውሳኔ ከማሳለፋቸው አስቀድመው ከተንቀሳቃሽ ምስል ዳኛው ስለ ሁናቴው እይታዊ ንግግርን በቃል ሊያገኙ አሊያም እራሳቸው ሄደው ምስሉን ለማየት ይችላሉ፡፡
ቴክኖሎጂው አነስተኛ ጣልቃ ገብነት፤ ከፍተኛ ጥቅም (minimum interference, maximum benefit) ላይ ካተኮረው የቴክኖሎጂው ፍልስፍና ጋር እንዲጣጣም ያለፉትን ሁለት አመታትን ያስከፈሉ የተለያዩ ማሻሺያዎች ተደርጎበታል፡፡
የኤሌክትሮኒክስ ብቃትና ክትትል ስርዓቶች (Electronic
Performance and Tracking Systems)
ይህ ቴክኖሎጂ የተለያዩ ግብዓቶችን አጠቃሎ የያዘ ነው፡፡ የየብሄራዊ ቡድኑ ቴክኒክና ህክምና ስታፎች ሜዳ ላይ ካሉ አሰልጣኞችና የህክምና ባለሙያዎች መረጃን ለመለዋጠጥ የሚያስችላቸው የግንኙነት መስመር የተዘረጋለት የስራ ቦታ ይኖራቸዋል፡፡ ይህም ውሳኔዎች አዳዲስና የተደራጁ መረጃዎች ላይ ተመስርተው እንዲከወኑ ያደርጋል፡፡
እንደ ፊፋ አገላለፅ የጨዋታው ተንናኞች ከተመረጡ ታክቲካል ካሜራዎች ከሚያገኙት በተጨማሪ ተጫዋቾቹን በሚከታተሉ ሁለት ኦፕቲካል ተራኪንግ ካሜራዎች አማካኝነት የአሰላለፍ መረጃን ያገኛሉ፡፡
ቴልስታር 18 የመጫወቻ ኳስ
በተሰናበትነው የፈረንጆች ዓመት መገባደጃ ላይ ይፋ የተደረገችው አዲዳስ ሰሪሿ ቴልስታር 18፣ 1970 ላይ በተሰደረገው የሜክሲኮ አለም ዋነጫ ላይ መጫወቻ በነበረችው ቴልስታር የመጫወቻ ኳስ ላይ ተመስርታ የተሰራች ናት፡፡ ስሟም የምስለ-መስኮት (ቴሌቪዥን)፣ ኮከብ እና በጥቁር እና ነጭ ቀለም ምስለ መስኮቶች ላይ ያሉትን ጥቁርና ነጭ ፓኔሎች አቀናብሮ የያዘ ነው፡፡ ይህ የ2018ቱ ኳስ አዲስ ውስጣዊ ሽፋን (carcass)፣ ዳግም ጥቅም ላይ የሚውል ማሸጊያና ከፍተኛ ቴክኖሎጂን ያቀፈ ሲሆን ስማርት ስልኮችን ጨምሮ ሜዳው ዙሪያ ላይ ካሉት ጋር ግንኙነት ማድረጊያ (Near-Field Communication/
NFC) መሳሪያ የተገጠመላት ናት፡፡ ሼር