Suicide is not a solution, solution is the mixture of solute and solvent😟🤷♂
ከእለታት ግማሽ ቀን. .
ማኅበረሰቡ አንዲትን ሴት "የብረት መዝጊያ" የሚሆን አማች የምታመጣ እንጂ፣ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም! ስለዚህ የነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት፣ አንዲት ሴት ዓይኗንም አእምሮዋንም ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል።
እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ በሥነፅሁፉ፣ በፊልሙ አእምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኑሯል። ከመራመዷ በላይ የአረማመዷንና የእግሯን ውበት እንድታስብ ስትሰበክ ኑራለች።
ለዚያም ነው ከፊታቸው የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ረግጠውና ዋጋ ከፍለው ወዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው፣ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት። እግራቸው ከለሰለሰ በኋላ፣ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ። ...
ለብዙኃኑ ወንዶች ጠንካራ የሴት እጅ አገርን ያቆመ ሳይሆን፣ ሴትነትን የገፋ መስሎ ነው የሚታያቸው። ለዚያ ነው በሥራ ስለደደረ የሴት መዳፍ፣ ዘፋኙም መዝፈን፣ ገጣሚውም መግጠም የማይወደው። ድንጋይ ፈልፍሎና እምነበረድ ጠርቦ ውብ የእጅ ጣት ያላት ሴት ሐውልት የሚያቆመውን ቀራጺ እጅ ግን ተመልከተው፣ በሥራ የጎለደፈ ሆኖ ታገኘዋለህ።
ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሕዝብ ሴት በሆነበት አገር፣ ሴቶች እጃቸውን አስውበው መደርደሪያ ላይ እንዲያስቀምጡት በማድረግ፣ ለውጥ ጠብ አይልም፤ እንዲሠሩ ማደፋፈር፣ እጅ ወደተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማ እንዲመለስ መሰበክ አለበት!!» ...
ከአሌክስ አብርሃም
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
@Teamvips @Teamvips @Teamvips

ቀና...
ባለፈው አልጋ ላይ የነገርሽኝ ነገር
ቀናተኛ አርጎኝ ቀና ስል ልናገር
አቅንተሽ የያዝሽው ገደበኝ ስሜቴ
እያስጮውኩ ለቀቀኝ ጥብቆ ቅናቴ
✍ሳምሶን ጌቱ
ባለፈው አልጋ ላይ የነገርሽኝ ነገር
ቀናተኛ አርጎኝ ቀና ስል ልናገር
አቅንተሽ የያዝሽው ገደበኝ ስሜቴ
እያስጮውኩ ለቀቀኝ ጥብቆ ቅናቴ
✍ሳምሶን ጌቱ
በመንታ ፏፏቴዎች ታጅበን የደመቅንበት ድንቅ ጊዜ እንካቹ
የመሐል ከተማ ግርግር ለሰለቸው
የስራና የኑሮ ውጣ ውረድ ላደከመው
ከከተማ ወጣ ብሎ መዝናናት ላሰበ
ሮሐ ትላንትም ዛሬም ነገም ከጎኖ ሆኖ ኢትዮጵያን በራሶ ቀለም ያስመለክቶታል
@Roha_Roha @Roha_Roha

አለሌ ነበርኩ ። ከህንድ እስከ እብድ የቀረኝ የለም የምል አለሌ። የተኛኋቸው ሴቶች ጠቢቡ ሰለሞን ከተኛቸው የሚያንስ አይደለም አልቆጠርኳቸውም እንጂ።
ጀንጅኜ መዳረሻዬ ማራኪ ሆቴል ነው ።ሆቴሏ ሸጎጥ ያለች ሰዋራ ስፍራ ነች ፤ ከመኖርያዬም እሩቅ ነች ።
አስተናጋጆቹም ምቹ ናቸው። በእርግጥ ጉርሻ ምቹ የማያደርገው የለም ። ፈረንጁ እና መስኪ የሚባሉ አስተናጋጆችን የበለጠ አውቃቸዋለሁ ።
ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኛል ፤ በእርግጥ መስኪ የምትባለው ትንሽ ተለቅ ትላለች ።
ፊት ከሰጠሁት ይጎነትለኛል ብላ ይሆን ፣ ተፈጥሮዋ ሆኖ ይሆን ፣ ነፍፍ ቺክ ስለማመላልስ ይሆን ፣ ስለማጨስ ወይም ስለምጠጣ ይሆን እኔ'ንጃ ብቻ
አትስቅልኝም አትኮሳተርብኝም ።
ፊቷ ወጣትነትን ቢሸኝም ውበቷ ግን እንዳለ ነው። መስኪ ምንም ያህል ቲፕ ብሰጣት አመሰጋገኗ ሆነ አስተያየቷ አይለይም ተመሳሳይ ነው ።
ክላሴ ውስጥ አጭሼ ፣ ጠጥቼ ፣ ባልጌ ሹልክ ብለን በጓሮ እንሄዳለን ። በሌላ ቀን ሌላ ቺክ ይዤ እመጣለሁ ፣ ካልጠረረብኝ ቺክ አልገርብም ።
ሁሉንም እንደሙዳቸው እና እንደፍላጎታቸው እሰክሳቸዋለሁ ።
ላጤነቴ በነፃነት ታየው አልታየው ብዬ ሳልሳቀቅ ለመባለግ አግዞኛል።
ጓደኞቼ ሁሉ ሲያገቡ ፤ ቤተሰቦቼ የአታገባም ውትወታ የበረታ ወቅት ሶልያና የምትባል ልጅ ተዋወቅኩ ።
ባገኘኋት በሁለተኛ ቀን ለመቾመስ በት በት አልኩ አልተሳካልኝም ።
በውስጤ ስንቷ እንደ አንቺ አካብዳ ጭኗን ሳትከፍት የቀረች የለችም ብዬ ፈገግ ስል ምነው አለቺኝ
እርጋታሽ ደስ ይላል አልኳት
ውስጤ እንደላዬ የተረጋጋ እንዳይመስልህ አለቺኝ ። ይሆናል ግን ውስጥም ላይም አንድ ላይ ከመንቀዥቀዥ ይሻላል አልኳት ከንፈሯን ገለጥ አድርጋ ሳቅኩኝ አይነት አለቺኝ
በነገራችን ላይ
አንተም ረጋ ያልክ ነክ አለቺኝ... ስስቅ ። ውስጥህ ወዲ ወዲያ ስለሚል ነው እርጋታህ ያልታወቀህ አለችኝ ።
ይሆናል አልኳት
ሶልያና የበዛ እርጋታ አላት ፥ እርጋታዋ ይረብሸኛል ከደስታ ይልቅ ለድብርት አጋልጦ ነው የሚሰጠኝ።
አብሪያት የምሆነው እስከምደክላት ብቻ ነበር።
ትፈልጋለች ብዬ የማስበውን እነግራታለሁ ። ሲኒማ እጋብዛታለሁ ፤ ትያትር ትጋብዘኛለች ከንፈሯ ጋ ሳልደርስ ቀናቶች ነጎዱ
በጭራሽ የወሲብ ወሬ ለማውራት አታመችም ። ወሲብ ነክ ከተወራ ለመቀጠል ፊቷ አይጋብዝም።ወሲብ ነክ ወሬ ካወራሁ ለይሉኝታ እንኳን ፈገግ አትልም።
መንፈሳዊ ጉባኤ ትጋብዘኛለች። ለእሷ ደስ እንዲላት አንዳንድ አሰልቺ ፣ አንዳንድ ማራኪ ስብከቶችን እሰማለሁ ።
ቀልቧን ለመግዛት መንፈሳዊ መፅሃፍ እያነበብኩ ፤ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እውቀት አለኝ ወሬ ሳወራት ቀልቧ ሲሳብ ወሬው ሲጥማት አያለው።
ሳይታወቀኝ የኔን መንገድ እየተውኩ በእሷ መንገድ መመላለስ ቀጠልኩ ።
ከሌሎች ስለተለየች ይሆን ፣ እንደምፈልገው
አለመሆኗ ይሆን ፣ የምፈልገውን ስላልሰጠቺኝ ይሆን ብቻ ቀልቤን ገዝታዋለች።
ውሎዋን ስራዬ ብዬ እከታተላለሁ ። ካልተደዋወልን ይታወቀኛል ። እንቅስቃሴዋ እየገቡኝ መጡ ። ሳላገኛት የት እና ምን እያረገች እንደሆነ መገመት ቻልኩ ።
ከደወለችልኝ ስግብግብ ብዬ አነሳለሁ ። በሂደት መንገዷ ምቾት ሰጠኝ ። ከተመላለስኩበት መንገድ በተሻለ ይሄኛው መንገድ ጣፈጠኝ
የድሮ አመሌ ውል ሲለኝ የምቀመጭላቸው ቺኮች ውልብ ብዬባቸው ሲደውሉ ሳላቅማማ የድሮ ስልክ ቁጥሬን ቀየርኩ ።
የትላንት የውድቀት መንገዳችንን ካልቀየርነው ለለውጣችን ሳንካ ይሆናል ።
አሁን ፈልጌ መፅሃፍ ቅዱስ አነባለሁ፤ እፆማለሁ ጉባኤ እከታተላለሁ ።መንፈሳዊ ጉዞ እሄዳለሁ ። ከሶሊያና ጋ እንፋቀራለን። የትላንት መንገዴን አልተረኩላትም ለዛሬው ማንነቴ ግን ማሃንዲሷ እሷው ናት ።
ለአምላኬ ስንቴ በእሷ ምክንያት ምስጋና እንዳቀረብኩለት። የትላንት ህይወቴን እንዴት አሁን እንደማልወደው ። ስለ ሴት አውልነት ሲነሳ ምንም ሃሳብ አልሰጥም ያ ዘመን ያሳፍረኛል።
ሶልያና አንድ እለት ስትፍነቀነቅ መጣች ምነው ስላት እቴቴ ስራ አገኘች አለቺኝ የት ስላት ባንክ
በቀላሉ ፍንክንክ የምትል አይደለችም የእናቷ ጉዳይ ግን ስስ ጎኗ ነው። ብቻዋን ስላሳደገቻት ይሆን ሁሉ ነገሯ ስለሆነች ይሆን ብቻ ስፍስፍ ትልላታለች።
ምን እንደምትሰራ አላውቅም ። በትምህርት ብዙ ያልገፋች ስለሆነች የት እና ምን ትሰራለች ብዬ አልጠየኩም ፤ እሷም ስራ ነች አልመጣችም ፣ ስራ ቀረች ነው እንጂ የት እና ምን እንደምትሰራ ነግራኝ አታውቅም ።
በጥንጡም በግዙፉም ወሬዎቾ መሃል እቴት ሳትል አትውልም ።
የድሮ ስራዋስ ስላት ። ውይ የድሮ ስራዋን እኮ አትወደውም ግድ ሆኖባት እንጂ አለቺኝ።
ስለ እኔ እንደነገራቻት እና እንደወደደቺኝ የነገረቺኝ እለት እንዴት ደስ እንዳለኝ ።
ባሻዬ ብላ ቴክስት አደረገችልኝ ። ደስ ስላት እና ስትቀልድ ባሻዬ ነው የምትለኝ ። ከእቴት ጋ እንደምንመሳሰል ነግሬህ አውቃለሁ ኣ ስትለኝ ሁሌ ብዬ የሳቅ ስቲከር ላኩላት ።
እንደ እሷ ቆንጀ ነኝ ግን ብላ ፎቶዋን ላከችልኝ ።
ማመን አልቻልኩም
ክው
ድርቅ አልኩ
የላከችልኝ ፎቶውን አገላብጬ አየሁት ፤ አልቀየር አለ ። የማራኪ ሆቴል አስተናጋጅ መስኪ የሶሊያና እናት ናት ፤ ሁለት አብረው ሆነው እና አንድ የመስኪን ማራኪ እንግዳ መቀበያ ጋ የተነሳችውን ፎቶ ላከችልኝ ።
ውስጤ ታወከ ።
ያ ሴት አውል አብርሃም ፤ ያ በየጊዜው ለቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሴቶችን የሚያጋድመው ፣ የሚያጨሰው አብራሃም ፤ ያ በጥሩ አይን አይታው የማታውቀው አብራሃም ፤ የአንድ ልጇ ሶሊያና እጮኛ ነኝ ብሎ ፊቷ እንዴት ይቆማል??
ትላንቴ ተከተለኝ። እግዜር በተፀፀትንበት ትላንታችን ይቀጣናል እንዴ? ስንቴ ያመሰገንኩበት ጉዳይ መጨረሻው እንዴት እንደዚህ ሆነ ??
የማደርገው ጠፋኝ ። ጠፋሁ ። አንዳንድ ትላንት ትላንት ላይ ብቻ አይቆምም።

:::::::::::::::::::የቸገራት:::::::::::::::::::::
አንዳንድ ጠዋት አለ
ውበት ደፍቶብኝ ምንቃበት
እንደ ፀሀይዋ ማበራበት
እንደ ጤዛዋቹ ምጠራበት።
ደግሞ በሌላ ቀን በሌላ ጠዋት
ቀጠሮ ኖሮኝ ፈልጌ ለመውጣት
ተቀብቼ ማልወዛበት
ተሽቀርቅሬ ማልደምቅበት
አለኝ የቀን ክፉ የቀን ልክፍት።
ኩሽና ስውል አሳምሮኝ
ልታይ ስል ሚደብቀኝ
የቀንማ ምቀኛ አለኝ።
ብሄድ እንኳን ችላ ብዬ
"ምንው ጠቆርሽ ተጎሳቆልሽ"
...........................ጎሽ!
ከቀኑ ማሽቃበጥ የነሱ ተዳምሮ
በዚጋ ወሬያቸው በዚያ የመልኬ ጉዳይ ናላዬን አዙሮ።
መበሳጨት ጀምራለው
መስታወት ፊት እቆማለው
ኩሌን ሊፒስቲኬን ሁሉንም ጠርጋለው
ልብሴን እጥላለው
የኩሽና ልብሴን መልሼ ለብሳለው
በድጋሚ ሄጄ መስታወት አያለው።
.............. አቤት ሳምር!
ለውበት አይደል ወይ ይህ ሁሉ መዳከር
በቃ ይቅር አልቀባ አልሽቀርቀር
ኩሽና ልቅጠርህ እባክህ እንዳትቀር።
✍hami
@Dear_hami
@Teamvips @Teamvips @Teamvips
አንዳንድ ጠዋት አለ
ውበት ደፍቶብኝ ምንቃበት
እንደ ፀሀይዋ ማበራበት
እንደ ጤዛዋቹ ምጠራበት።
ደግሞ በሌላ ቀን በሌላ ጠዋት
ቀጠሮ ኖሮኝ ፈልጌ ለመውጣት
ተቀብቼ ማልወዛበት
ተሽቀርቅሬ ማልደምቅበት
አለኝ የቀን ክፉ የቀን ልክፍት።
ኩሽና ስውል አሳምሮኝ
ልታይ ስል ሚደብቀኝ
የቀንማ ምቀኛ አለኝ።
ብሄድ እንኳን ችላ ብዬ
"ምንው ጠቆርሽ ተጎሳቆልሽ"
...........................ጎሽ!
ከቀኑ ማሽቃበጥ የነሱ ተዳምሮ
በዚጋ ወሬያቸው በዚያ የመልኬ ጉዳይ ናላዬን አዙሮ።
መበሳጨት ጀምራለው
መስታወት ፊት እቆማለው
ኩሌን ሊፒስቲኬን ሁሉንም ጠርጋለው
ልብሴን እጥላለው
የኩሽና ልብሴን መልሼ ለብሳለው
በድጋሚ ሄጄ መስታወት አያለው።
.............. አቤት ሳምር!
ለውበት አይደል ወይ ይህ ሁሉ መዳከር
በቃ ይቅር አልቀባ አልሽቀርቀር
ኩሽና ልቅጠርህ እባክህ እንዳትቀር።
✍hami
@Dear_hami
@Teamvips @Teamvips @Teamvips
አንድ ባለስልጣን አማኑኤል ሆስፒታልን እየጎበኙ አንድ በሽተኛ ያጋጥማቸውና ጠጋ ብለው
ወደዚህ እንዴት ልትመጣ ቻልክ ማለቴ የህመምህ መንስኤ ምንድነው?' ብለው ይጠይቁታል ።
በሽተኛውም መለሰ...
' ጌታዬ ይሄ ሁሉ መዓት የወረደብኝ አንዲት መናጢ ሴት ሳገባነው።
ይሀውሎት አንዲት አግብታ የፈታችና ቆንጆ ሴት ልጅ ያለቻት ወይዘሮ አገባለው።
እናም ይህቺ ቆንጆ ልጅ የእንጀራ ልጄ ሆነች ማለት ነው።
ከዛ አባቴ አንድ ቀን ሊጎበኘን ይመጣል። በዚህች ቆንጆ ልጅ ፍቅር ይከንፍና በግድ ያገባታል።
ስለዚህ የእንጀራ ልጄ የእንጀራ እናቴ ሆነች ማለት ነው። ባለቤቴም ለኔ አንድ ወንድ ልጅ ትወልድልኛለች።
በመሆኑም የኔ ልጅ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ ለአባቴ ደግሞ ዋርሳ ሆነ ማለት ነው ምክንያቱም አባቴ የእንጀራ ልጄን አግብቷልና።
እና እንደነገርኩህ የእንጀራ ልጄ አባቴን ስታገባ እሷ በመጀመሪያ የእንጀራ እናቴ ሆነች በኋላ ላይ ደግሞ ወንዱ ልጄ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ እርሱ ደግሞ በተዘዋዋሪ አጎቴ ሆኖ እርፍ!
ሚስቴ ደግሞ የእንጀራ እናቴ እናት ስለሆነች የእንጀራ አያቴ ሆና እርፍ!
የእንጀራ እናቴ የእንጀራ ልጄ መሆኗን አትርሳ። እንዲሁም የራሴ የገዛ ሚስቴም የእንጀራ ልጅ ልጅ መሆኔንም አትዘንጋ። ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔን የገረመኝ የእንጀራ አያቴን ስላገባሁ ለሚስቴ የእንጀራ የልጅ ልጇ እና ባሏ ብቻ ሳልሆን የራሴም አያት መሆኔ ነው።
ወደዚህ ወደ አማኑኤል ሆስፒታል አብጄ የመጣሁበት ምክንያቴም ይሄው ነው!!'😭
# Fro Eticha እንደፃፈው ።

Only for VIP'S
https://drojob.com/?r=Samget
Register and clam $10 and $2 per day
Withdrew in paypal, western union and other enjoy and work in home

https://t.me/hamster_komBat_bot/start?startapp=kentId1073506431
Play with me, become cryptoexchange CEO and get a token airdrop!
💸 +2k Coins as a first-time gift
🔥 +25k Coins if you have Telegram Premium

Telegram
Hamster Kombat
Just for you, we have developed an unrealistically cool application in the clicker genre, and no hamster was harmed! Perform simple tasks that take very little time and get the opportunity to earn money!