ተአምኖ ሚዲያ teamno media
515 subscribers
184 photos
2 videos
111 links
እንኳን ወደ ተአምኖ ሚዲያ የቴሌግራም ቻናል በሰላም መጡ። በቻናላችን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን የተመለከቱ ዜናዎችን የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችና አጫጫር ቪዲዮዎች ይለቀቁበታል።
ለአስተያየትና ጥያቄዎ
☎️+251903149262 ተአምኖ ሚዲያ ብለው ይጻፉልን
Download Telegram
የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ 14 ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ተከበረ።


የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንትና የዓለም የሰላም አምባሳደር የነበሩ 14ኛ ዓመት በዓለ ዕረፍት መታሰቢያ በዓል ዛሬ እሑድ ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ.,ም በመላው ኢትዮጵያ ገዳማትና አድባራት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ በካህናትና በምእመናን በተገኙበት በጸሎት ታስቦ ውሏል።

የቅዱስነታቸው ክቡር ሥጋቸው ባረፈበት ቦታ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመምሪያ ኃላፊዎችና አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በጸሎተ ፍትሐትና በዝማሬ ተከብሯል።
👏3
ወንድም እኅቶቻችን ቻናሎቻችን ችግር ስለገጠማቸው አገልግሎታችን ለማስቀጠል አማራጭ ቻናል ከፍተናል እባክዎን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👉https://youtube.com/@senaykidase?si=wTDTXpQ-gTvejPuD
🙏3👍1
🌹🌹🌹 የ2019 ዓ/ም በዓላትና አጽዋማት🌹🌹🌹
➡️ ጾመ ነነዌ የካቲት 15 ቀን ሰኞ፣
➡️ዐቢይ ጾም የካቲት 29  ቀን ሰኞ፣
➡️ደብረ ዘይት መጋቢት 26 ቀን እሑድ፣
➡️ሆሣዕና ሚያዚያ 17 ቀን እሑድ፣
➡️ስቅለት ሚያዚያ  22  ቀን ዐርብ፣
➡️ትንሣኤ ሚያዚያ  24  ቀን እሑድ፣
➡️ርክበ ካህናት ግንቦት 18 ርክበ ካህናት ይሆናል።
➡️ዕርገት ሰኔ 3 ቀን ሐሙስ የሚውሉ ይሆናል
➡️ጰራቅሊጦስ ሰኔ 13 ቀን እሑድ፣
➡️ጾመ ሐዋርያት ሰኔ 14
➡️ጾመ ድኅነት ሰኔ  16

©አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም
እንኳን ለ2019 ዓ.ም ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ።
❤3