TEMARI-NET
3.97K subscribers
707 photos
14 videos
150 files
233 links
This Channel is created to disseminate proper, timely information and news for Students
Download Telegram
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። (የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

@TEMARI_Net1
1👍1
#ደመወዝ

የደመወዝ ማሻሻያ ሊደረግ ነው።

ከመስከረም 2018 ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት እንደወሰነ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በዚህ ማሻሻያ፦

1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ እንደሚደረግ፤

2. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲያድግ እንደሚደረግ፤

3. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11, 500 እንደሚሻሻል፤

4. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም ማሻሻያ እንደሚደረግበት አሳውቋል።

ይህ የደመወዝ ማስተካከያ ከ160 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እንደጠየቀ ገልጿል።

ለደመወዝ የሚወጣው ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ አመልክቷል።

መረጃው የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነው።

@TEMARI_Net1
🥰2👏1
የትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥሉት ዓመታት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደ ተመደቡበት የተልዕኮ መስክ ይገባሉ አለ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ (ዶ/ር) እንዳሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በተመደቡባቸው የአጠቃላይ የተግባር እና የምርምር መስኮች ገብተዋል፡፡

በተለያየ ደረጃ ቢሆንም ሁሉም የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወደ ተልዕኮ መስካቸው መግባታቸውን ገልጸው÷ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ ለሙሉ ወደ ተልዕኮ መስካቸው እንዲገቡ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ መስክ መለየት ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት ይሰራል ነው ያሉት።

ኢንዱስትሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በመምጣት ለተማሪዎች ስልጠና እንዲሰጡ እና ስታርትአፖች እንዲፈጠሩ የሚደረግ መሆኑንም አመልክተዋል።

በምርምር ዘርፍ የተለየው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)÷ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በመምህራን ትምህርት፣ በጤናና እና በግብርና ዘርፎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

የሚታጠፉ ወይም አዲስ የሚጀመሩ የትምህርት ፕሮግራሞች ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል፡፡

በ2021 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ራስ ገዝ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለመሆን ህጎች እና የሰነድ ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የትምህርት ፕሮግራሞች ክለሳ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸው፤ ከንድፈ ሀሳብ በዘለለ ተግባር ተኮር ትምህርቶች ላይ ሰፊ ትኩረት መሰጠቱን ጠቅሰዋል፡፡

ተማሪዎች በኢንተርንሽፕ እና በኤክስተርንሽፕ በኢንዱስትሪዎች እንዲለማመዱ ከ44 ኢንዱስትሪዎች ጋር ስምምነት ተደርጓል ብለዋል።


@TEMARI_Net1
1
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት የ6000 አለም አቀፍ ተማሪዎችን ቪዛ መሻሩን አስታወቀ።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ከቪዛ ጊዜያቸው በላይ በአሜሪካ ቆይተዋል እንደዚሁም የአሜሪካን ህግ ጥሰዋል ያላቸውን ከ6000 በላይ የአለም አቀፍ ተማሪዎች ቪዛ መሰረዙን አስታውቋል።

ቪዛቸው ከተሰረዘባቸው 6000 ተማሪዎች መካከል 4000 ያህሉ አልኮል እና አደንዛዥ ዕፅ ወስዶ ከማሽከርከር እና እንደ ድብድብ ባሉ የህግ ጥሰቶች የተሰረዘባቸው ነው ሲባል ከ200-300 የሚሆኑት ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ ተሰርዞባቸዋል ተብሏል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ ማርክ ሩቢዮ ባለፈው ግንቦት ወር ወደ አሜሪካ መጥተው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የሚረብሹ ሰዎች ቪዛ መሰረዝ ይቀጥላል ብለው ማስጠንቀቃቸውም ይታወሳል።

በአሜሪካ በ2023-2024 የትምህርት ዘመን ከ210 ሃገራት የተውጣጡ ከ1.1 ሚሊየን በላይ አለም አቀፍ ተማሪዎች እንዳሉ ቁጥሮች ሲያሳዩ ከዚህ በኋላ ወደ አሜሪካ የሚያመሩ ተማሪዎችም የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴያቸውን ጨምሮ ተጨማሪ የደህንነት ፍተሻ እንደሚደረግባቸው ከወራት በፊት መገለፁ ይታወሳል።

Source: BBC

@TEMARI_Net1
2
UG Application Announcement 2018_Reg and Ext.docx
24 KB
#AAU
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2018 ዓ.ም ለቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ.ም ለቅድመ-ምረቃ ትምህርት በቀን በመደበኛ መርሃ ግብር በመንግስት ስኮላርሽፕ እና በግል ከፍለዉ ለሚማሩ እንዲሁም በማታ በተከታታይ መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት መስኮች መማር ለሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡
በዚህም መሠረት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጾች (www.aau.edu.et ወይም https://portal.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን ዝርዝር የማመልከቻ መስፈርቶች በማሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
• የመመዝገቢያ ቀናት ከነሐሴ 15 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን
• የዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት ቀናት ወደፊት በዩኒቨርሲቲዉ ድረ ገጽ (www.aau.edu.et፣ https://portal.aau.edu.et) እና በኦፊሻል የቴሌግራም ገጾች (t.me/aauGAT, t.me/aau_official) ላይ ይገለጻል::
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር

Share
@TEMARI_NET1
1
Forwarded from AAU MEREJA
Call_for_applications_for_admission_to_graduate_programs_PADM.pdf
879.9 KB
🎓 Graduate Program Opportunities at Addis Ababa University
Department of Public Administration and Development Management (PADM)

📚 Now accepting applications for the 2025/26 academic year:

MA in Public Policy & Development Management(Regular & Extension Programs)
PhD in Public Management & Policy(Regular Program)

🗓 Important Dates:

GAT Registration:July 7 – August 17, 2025
GAT Examination Period: August 18 – 25, 2025

🌐 Apply Now:[https://portal.aau.edu.et](https://portal.aau.edu.et)

📍 Location:
Eshetu Chole Building, Offices 507 & 407, College of Business and Economics (CoBE), AAU

📞 Contact Us:
Tel: +251 111 229 602 / 0910 081 200


📄 For More Information:Please refer to the official PDF announcement.


The Department

@AAUMEREJA
1
💻 Ethio Coders – Learn. Build. Grow. 🚀

Are you passionate about coding or dreaming of becoming a web developer?
At Ethio Coders, we share free daily tips & tricks on:
Frontend (HTML, CSS, JavaScript, React, etc.)
Backend (Node.js, PHP, Databases, APIs, etc.)
Web development best practices & career advice

Stay updated with the latest in web technologies
Learn faster with bite-sized tips
Get motivated & connect with like-minded techies

@Ethio_Coders_channel
"በቀጣይ ዓመት ከ100 እስከ 150 ሺህ የሚሆኑ አዳዲስ መምህራን የብቃት ምዘና ወስደው ወደ ዘርፉ ይሰማራሉ፡፡" - የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሔደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፤ በቀጣይ ዓመት ሁሉንም በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት አሠራርን ዲጂታላይዝ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ

በሀገር አቀፍ ፈተናዎች ላይ ተማሪዎችን በማሳለፍ ምጣኔ ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ 700 ትምህርት ቤቶችን በመለየት በ2018 ዓ.ም ልዩ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡

26 ሚሊዮን አዳዲስ መፅሐፍት ህትመት እየተከናወነ እንደሚገኝ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመምህራንን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና አቅማቸውን የማጎልበት ሥራ በትኩረት እንደሚሠራበት ጠቅሰዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው የምክክር መድረክ፤ የክልል ትምህርት ቢሮዎች ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ ላይ ውይይት ይደረጋል።

@TEMARI_Net1
What comes to mind when you think of the Hult Prize?

Is it innovation?
Is it young changemakers with bold ideas?
Or is it the chance to transform a simple idea into a global movement?

The Hult Prize AAU Chapter is proud to carry forward this spirit as we prepare for the 2025/26 Cohort kickoff events. Just like in previous years, we are creating a platform where creativity meets opportunity, and where ambitious thinkers can turn their visions into real, lasting impact.

This is a call to all startups, entrepreneurs, and dreamers with big ideas if you believe your idea can change the world, this is YOUR moment.

Stay tuned for updates, announcements, and opportunities to join us on this transformative journey. Together, let’s build solutions that matter and shape the future we want to see.

And exciting news! Registration for the 2025/26 Cohort Organizing Committee (OC) will open soon. If you’re passionate about leadership, teamwork, and impact this is YOUR chance to be part of something global!
2
🌞 Good Morning, Changemakers! 🌍

The Hult Prize is more than a competition—it’s a movement of youth, innovation, and impact. 💡🚀

For students, it’s a stage to turn ideas into action. For the youth, it’s a chance to lead with purpose. And for our country, it’s a moment to shine globally. 🇪🇹🌎

Your idea could be the one to change the world—don’t hold back. Show up, participate, and make it happen! 💪🔥
Learn more at 👉 www.hultprize.org
#HultPrize #YouthForImpact #Innovation
What comes to mind when you think of the Hult Prize?

Is it innovation?
Is it young changemakers with bold ideas?
Or is it the chance to transform a simple idea into a global movement?

The Hult Prize AAU Chapter is proud to carry forward this spirit as we prepare for the 2025/26 Cohort kickoff events. Just like in previous years, we are creating a platform where creativity meets opportunity, and where ambitious thinkers can turn their visions into real, lasting impact.

This is a call to all startups, entrepreneurs, and dreamers with big ideas if you believe your idea can change the world, this is YOUR moment.

Stay tuned for updates, announcements, and opportunities to join us on this transformative journey. Together, let’s build solutions that matter and shape the future we want to see.

And exciting news! Registration for the 2025/26 Cohort Organizing Committee (OC) will open soon. If you’re passionate about leadership, teamwork, and impact this is YOUR chance to be part of something global!
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካቾች (KPIs) የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለሁለት ቀናት በሀዋሳ ሲያካሒደው የቆየው የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተጠናቋል።

በመድረኩ በአጠቃላይ የትምህርት ልማት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ከመግባባት የተደረሰ ሲሆን፤ የ2018 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት ውጤት አመላካች መለኪያዎች ላይ የጋራ ስምምነት ተፈርሟል።

የትምህርት ለትውልድ፣ የትምህርት ቤት ምገባ፣ የቅድመ አንደኛ ትምህርት፣ የስርዓተ ትምህርት ትግበራ፣ የመምህራን አቅም ግንባታ፣ ዲጂታይዜሽን እና ሌሎች የሪፎርም ሥራዎች ላይ ሁሉም የክልል እና የከተማ አስተዳድር ትምህርት ቢሮዎች በትኩረት እንዲሠሩ የአጠቃላይ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ አሳስበዋል።

@TEMARI_Net1
1
#ግዕዝ‼️
በ2018 የትምህርት ዘመን #የግዕዝ ትምህርት በአማራ ክልል ባሉ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ መወሰኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለዞን እና ከተማ አስተዳደሮች ከላከው ደብዳቤ ተመልክተናል።
@TEMARI_Net1
11
በደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ የመውጫ ፈተና አጭበርብሮ ለሴት ጓደኛ  ሲፈተን የነበረው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

ተከሳሽ መለሰ ያረጋል የተባለ ግለሰብ በዳንግላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያ ሲሆን ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00  በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በተድላ ጓሉ ክፍለከተማ ቀበሌ 02 በደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ድርጊቱን መፈጸሙ ተገልጿል ።

ተከሳሹ ወይንሸት ገነት ለተባለች ግለሰብ በፐብሊክ ሄልዝ የመውጫ ፈተና በመፈተን ላይ እንዳለ እጅ ከፍንጅ መያዙን የ2ኛ ፖሊስ ጣቢያ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ለብስራት ሬዲዮ የላከው መረጃ ያመላክታል።ተከሳሹ ስሙን በመቀየር ወንደሰን ገነት የሚል ሀሰተኛ ሰነድ መታወቂያ በመያዝ ፈተናውን ሲወስድ እጅ ከፈንጅ ሊያዝ መቻሉ ተገልጿል።

ፖሊስ የተፈጸመውን ወንጀል በተፋጠነ መልኩ ምርመራውን በማጣራት መዝገቡን ለሚመለከተው ለምስራቅ ጎጃም ዞን አቃቢ ህግ መምሪያ በመላክ የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነሃሴ 16 ቀን 2017  ዓ .ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ መለሰ ያረጋል በተከሰሰበት የማጭበርበር እና ሀሰተኛ ሰነድ አዘጋጅቶ በመገልገል ወንጀል ጥፋተኛ መሆኑ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በመረጋገጡ በሁለት አመት ከሶስት ወር ጽኑ እስራት መቀጣቱ ተገልጿል።

የዩንቨርሲቲም ሆኑ ሌሎች መሰል የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና እና ምዘና በሚያካሂዱበት ግዜ ተገቢውን የማጣራት ስራ እንዲሰሩ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተነግሯል ።

@TEMARI_Net1
4
Forwarded from AAU MEREJA
Call_for_applications_for_admission_to_graduate_programs_PADM.pdf
879.9 KB
🎓 Study Public Policy & Development Management at Addis Ababa University

📚 Now accepting applications for the 2025/26 academic year:

MA in Public Policy & Development Management(Regular & Extension Programs)
PhD in Public Management & Policy(Regular Program)


🌐 Apply Now:[https://portal.aau.edu.et](https://portal.aau.edu.et)

📍 Location:
Eshetu Chole Building, Offices 507 & 407, College of Business and Economics (CoBE), AAU

📞 Contact Us:
Tel: +251 111 229 602 / 0910 081 200


📄 For More Information:Please refer to the official PDF announcement.


The Department

@AAUMEREJA