The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የኢትዮጵያን የቤተ ክርስቲያን ቅርስ የደበቀው የብሪታንያ ሙዚየም ላይ ምርመራ ተጀመረ

የብሪታንያ ሙዚየም ከኢትዮጵያ የተዘረፉ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶችን ለዕይታ ባለማቅረቡ ምርመራ እየተካሄደበት ነው።

ሙዚየሙ ከኢትዮጵያ የተዘረፉና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆኑ ቅርሶችን ለ150 ዓመታት ለዕይታ አቅርቧቸው አያውቅም በሚል በብሪታንያ የማስታወቂያ ኮሚሽነር ቢሮ አማካኝነት ነው ክስ የቀረበበት።

ቢሮው ከግለሰቦች የደረሱትን ጥቆማዎች መሰረት በማድረግ ነው ሙዚየሙ ላይ ክሱን የጀመረው።

እነዚህ ቅርሶች ከእንጨትና ከጥርብ ድንጋይ የተሰሩ ጥንታዊ 11 ታቦታት መሆናቸውንም አር ቲ በዘገባው አመላክቷል።

ከዚህ ቀደም ሙዚየሙ ከታቦታቱ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ቢቀርብለትም የተድበሰበሰ ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱንም ዘገባው አስታውሷል።

ጉዳዩን በተመለከተ የሚከታተለው የተቆርቋሪዎች ቡድን ታቦታቱ ለህዝብ ዕይታ የሚቀርቡ ባለመሆናቸው ወደ መጡበት ሊመለሱ ይገባል በሚል እየጠየቀ ነው።

ታቦታቱ በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ወታደሮች የተረዘፉ መሆናቸው ታውቋል።

እነዚህ ታቦታት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ብቻ የሚታዩ ናቸው።

ታቦታቱ በለንደን ምዕራባዊ ዳርቻ በሚገኘው ብሉምስበሪ ከመሬት በታች በሚገኝ የተዘጋበት አዳራሽ ውስጥ እንደሚገኙም ዘገባው ጠቅሷል።
በበጎ ፍቃድ ተግባር የታደሱ የአረጋዉያን #ቤት ረክክብ ተፈፀመ።

#Ethiopia :- የWSG (የዊንሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የወገኖቻችንን ቤት እድሳት አስጀምሮ በማስጨረስ የሰብዓዊ ግዴታዉን እንደተወጣ ገለፀ።

የዊንሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ አገልግሎት መሪ የተከበሩ ዶክተር ግዛቸው አይካ፣ የብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን የድርጅት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ አለማየው ፍቃዱ፣ አቶ እንዳልካቸው አስራት የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አደጃጀት ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ አዲሱ አንጃ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ጽ/ቤት ኃላፊ እና ወ/ሮ ሔለን አሰፍ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈፃሚ በጋራ በመሆን ያደሱትን ቤት ተረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት የደብሊው ኤስ ጂ (WSG) ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ የአቅመ ደካሞች ቤትን ማደስ ትልቅ ተግባርና የህሊና እርካታ የሚሰጥ ተግባር በመሆ በቀጣይም ይህንን መሰል የበጎ ፍቃድ ተግባራትን በመደገፍ በማስተባበር የሚጠበቅብንን ኃላፊነት እንወጣለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው አስራት በበኩላቸው በጎነት ለራስ በመሆኑ ሁላችንም የድርሻችንን ካደረግንና ከተባበርን ብዙ እንሰራለን ከሰራን ደግሞ ሀገርን እንገነባለን ሀገርን ከፍ እናደርጋለን ለቀጣይ የሚመጣ ትውልድ አሻራ እናሳርፋለንብለዋል።

ይህ የበጎ ስራ የተከናወነዉ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባባር መሆኑን (WSG) በላከልን መረጃ ተገልጿል።
መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ ይቅርታ ጠየቀ ..

አብና መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ በሚለው ስም ውስጥ ይጠቃለላሉ ብዬ ያስተማርኩት ንግግሬ የአገላለፅ ስህተት ፈጥሮ በርካቶችን ስላስቆጣ መላውን የወንጌል አማኝ እህት ወንድሞቼን በግልፅ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ !

እኔ በ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የማምን አዲስ ፍጥረት ነኝ!
"፩ ምዕራፍ" የመዝሙር ድግስ

ዘማሪ ቴዲ ታደሰ "፩ ምዕራፍ" የመዝሙር ድግስ መጋቢት 28 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል።

በእለቱ ኦፕን ሄቨን ሚኒስትሪ ጅማሬውን ያደርጋል።


ድግሱን አስመልክቶ ዘማሪ ቴዲ ዛሬ ለክርስቲያን ሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው "፩ ምዕራፍ" አዲስ የምህረት ጊዜ ሊሆንልን እግዚዓብሔር ከህዝቡ ጋር ቀጠሮ ይዞበታል ተብሏል።


ድግሱን ኦፕን ሄቨን ሚኒስትሪ ያዘጋጀው ሲሆን፡ ዘማሪ ቴዲ ያለፉትን 3 ወራት ከባንድ ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።

በእለቱ የኤግዚቢሽን ማዕከል በሮች ከ 4 ሰዓት ጀምረው ክፍት የሚሆኑ ይሆናል።


ዘማሪው ከጋዜጠኞች ለቀረበ ጥያቄ መልስ እና ማብራሪያ ሰጥቷል። ኦፕን ሄቨን ሚኒስትሪ በዋናነት ወንጌልን የመስበክ ራዕይ ያለው ሲሆን፡ የዝማሬ፡ ማማከር፡ እና ሌሎችም መንፈሳዊ አገልግሎት ይሰጣል ብሏል።

ራዕይ ከእኔ ሃሳብ የሚመነጭ አይደለም፡ ከላይ የሚሰጥ ነው፡ ምንም እንኳን ጊዜው እንደ ሃገር ፈታኝ ቢሆንም፡ ሁል ጊዜም ለአምላካችን ይዘመራል ብሏል።
#"ጉዞው"_የመጽሃፍ_ምረቃ
የኤልሻዳይ ቲቪ ኔትወርክ የ17 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ መጽሃፍ ተመረቀ።

ጁላይ 2007 (እ.አ.አ) ለአውሮፓ ክርስቲያኖች በጄኔሲስ ቲቪ፡ ከሰሃራ በታች ላሉ ክርስቲያኖች በወንደርፉል ቲቪ ነው ስርጭቱን የጀመረው።

"ራዕይውን ገና በጌታ ቤት ልጅ እያለው ነው ከ31 ዓመታት በፊት ከጌታ የተቀበልኩት። በወቅቱ በርካቶች እብድ ቢሉኝም 15 አመታትን ጠብቆ በ30 ደቂቃ የቴሌቭዥን ስርጭት ኤልሻዳይ ቲቪ ተወለደ።" ፓስተር አበራ ሃብቴ

"እኛ ኤልሻዳይን ስንጀምር በሃገሪቱ ርሃብ እና ብርቱ ችግር ነበረ። እግዚዓብሔር ግን በኤልሻዳይ እጁ ኤልሻዳይን 17 አመታትን በድል ሲመራው አይቻለው" ፓስተር በለጡ ሃብቴ

ለረጅም አመታት ከኤልሻዳይ ጋር ሲያገለግሉ የቆዩት ቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና፡ ዛሬ የተገናኘነው መጽሃፍ ለመመረቅ ሳይሆን፡ እግዚዓብሔር በኤልሻዳይ አልፎ ለሰራው ነገር ልናመሰግነው ነው ብለዋል።

"ጉዞው" የኤልሻዳይ ቴሌቭዥን ኔትዎርክ የ17 ዓመታት አግልግሎት የሚያስቃኝ መጽሃፍ ነው።
መጽሃፉ አገልጋዮች፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተመርቋል።
"ጉዞው" ኤልሻዳይ በሃገርኛ ቋንቋ ብቸኛ የወንጌል አገልግሎት ከመሆን ጀምሮ ዛሬ ላሉን በርካታ መንፈሳዊ የመገናኛ ብዙሃን በር ከፋች መሆኑን እና በነዚህ አመታት ያለፈበትን ጉዞ ያስቃኛል።

ሰሜንን ለወንጌል፡ ሌት አፍሪካ ጎ (Let Africa Go)፡ የተማሪዎች ምገባን ቆየት ላለ ጊዜ እና ለልዩ ፍላጎት ቤተሰብ ልጆች ቋሚ ድጋፍ ማድረግ ኔትዎርኩ እየሰራባቸው የሚገኙ ሌሎች አገልግሎቶች ናቸው።

ከኤልሻዳይ ቲቪ የተጠቀማችሁ ምስክርነት ያላችሁ፡ ኮሜንት ስር አስቀማጡልን።
#ዘማሪ ቴዎድሮስ ታደሰ (ቴዲ) #ፓስተር ተደርጎ ተሾመ።

ዘማሪ ቴዲ በአሁኑ ሰዓት "አንድ ምዕራፍ" በሚል የዝማሬ ኮንሰርት እያከናወነ ሲሆን በኮንሰርቱ ላይ በመጋቢነት ሲሾም የቀረውን ጊዜ በተሰጠው ጸጋ #እግዚአብሔርን እና የእግዚአብሔን ሕዝብ በታማኝነት እና በቅንነት በተሰጠው ጸጋ ልክ ለማገልገል ቃል ገብቷል።

ቃል የማስገባቱን ስነ-ስረዓት የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን መሪ የሆኑት ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ አስፈጽመዋል።
"ክቡር #ልጆች " ተመረቀ።

ክቡር ልጆች ትኩረቱን ልጆች ላይ ያደረገ በተለይ ለቤተሰብ ግንባታ መሰረታዊያንን ያካተተ ነው።

መጽሃፉ የልጆችን ስነ ልቦና መገንባትና የስሜት ስብራት ለመጠገን የሚረዱ ቁልፍ መንገዶችን በስፋት የሚዳስስ ነው።

በትላንትናው እለት በኢንተርናሽናል ኢቫንጀሊካል ቸርች በተካሄደው ምረቃ መጋቢ በቀለ ወ/ኪዳን፡ አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን፡ ማስተር በላቸው ግርማ (የሳቅ ንጉስ)፡ የእስራኤል አምባሳደር በኢትዮጵያ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ታድመዋል።

የመጽሃፉ ጸሃፊ ብርሃኑ በላቸው፡ በቤቶቻችን ምንም #እንኳን ወንበር ባንለቅላቸውም የከበሩ ልጆች እንዳሉን ስናስብ፡ በስነ ልቦና የጠነከሩ ልጆች እንፈጥራለን ሲል The Christian News - የክርስቲያን ዜና አስተያየቱን ሰጥቷል። ክቡር ልጆችን ለማንበብ ማንም ሰው መውለድ አይጠበቅበትም፡ ቢያንስ ታናናሽ ወንድም ልና እህቶቻችን ክቡር ናቸው ብሏል።

ዛሬ ልጆችን የሚሰማ ሃገር፡ ቤ/ክ፡ ቤተሰብ ከሌለ ነገ ትውልድ አይኖርም። ስለዚህ በዚህ መጽሃፍ ውስጥ ለልጆች ትኩረት መሰጠቱ ልጆችን የሚሰማ መኖሩን ያሳያል ተብሏል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዘገባውን አሰናዳንላችሁ።

የዕለቱን ፕሮግራም የሚገልፅ ተጨማሪ ፎቶዎችኝ ማየት ከፈለጉ የፌስቡክ ገፃችን ላይ ያገኛሉ።
#ክርስቶስ እንኳን #ወደ ምድር ቢወርድ #አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም

#ክርስቲያኖች ላይ ስደት በዝቷል።

በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ በምትገኘው ኮሶቮ፣ ክርስቲያኖች #ላይ ስደት በርትቷል ተባለ።

በሃገሪቱ ክርስቲያኖች #ምንም አይነት የመሰብሰብ መብት እንደሌላቸው #እና ፈቃድ ለማግኘትም ሁኔታዎች እንደሚወሳሰቡባቸው ገልጸዋል።

የአርሜ #ቋንቋ ተናጋሪዎች የሚበዙባት ኮሶቮ፣ 93 በመቶ ዜጎቿ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።

ምንም #እንኳን የሃገሪቱ ህገ መንግስት የሃይማኖት ነጻነትን የሚፈቅድ ቢሆንም፣ ክርስቲያኖች ላይ ግን መድሎና አመጽ ይበረታባቸዋል።

#ይህ ስደት በግል ደረጃም፣ የቀብር ስፍራ መከልከል፣ ንብረት የማፍራት መብት አለማግኘትና ሌሎችም በደሎች እየደረሱባቸው እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በተለይ #ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች፣ የባንክ ሂሳብ መክፈት፣ ንብረት ማፍራት እና ሰራተኞችን ቀጥሮ የመንቀሳቀስ ዴሞክራሲያዊ መብቶች የላቸውም።

በቅርቡ የወጣ #አንድ ህግ ደግሞ የሰርቢያ ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊኮችን እና ሌሎችንም ታሪካዊ አብያተ ክርስቲያናትን ኢላማ ያደረገ ነው ይባልለታል።

በሃገሪቱ ያለፉትን 25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ ቄስ ሲናገሩ፣ ያለው ስቃይ በግልጽ ስላልሆነ ይበልጥ ከባድ ያደርገዋል ብለዋል።

ለቀብር እንኳን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ፣ በኢማሞች የተመራ ቀብር ስነ ስርዓት እያደርግን ነው የምንገኘው ብለዋል። ምንም ቢሆን #ግን ለሃገራችን የወንጌል ተስፋ አለን ሲሉም እኚሁ ቄስ ይናገራሉ።

በኮሶቮ በ1980ዎቹ ወንጌላዊያን፣ ክርስቶስ እንኳን ወደ ምድር ቢወርድ አንድ አዳራሽ መስሪያ ቦታ አይሰጣችሁም የሚል ተደጋጋሚ ዛቻ ከወቅቱ ኮሚኒስት መንግስት ሲደርስባቸው እንደ ነበረ ዘገባዉ አስታዉሷል።
#ቤተክርስቲያን እዉቅና ሰጠች።

ወንጌላዊ ጋሽ ቦጋለ ለማ ለረጅም አመታት በቀጠና #ሁለት #ሙሉ #ወንጌል ያገለገሉ #እና አጋሽ ቦጋለ ለማ ለረጅም አመታት በቀጠና ሁለት ሙሉወንጌል ያገለገሉ እና አሁን ደግሞ በአዲስ ከተማ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ውስጥ እያገለገሉ ይገኛሉ ይህንንም በማስመልከት ቤተክርስቲያን እውቅና ሰጥታለች።

ቤተክርስቲያን እንደዚህ ላሉ አገልጋዮች እውቅናና ክብር መስጠቷ እጅግ የሚያበረታታ እና ሊቀጥል የሚገባ ተግባር ነው።

Christian ዜማ Tube ገፅ የተወሰደ...
ጠቢባን እንደኖህ ቤታቸውንና ትውልዳቸውን ከዘመናችን የጥፋት ውሃ የሚያስመልጥ መርከብ በእግዚአብሔር ቃል ንድፍ መሰረት እየሰሩ ነው። 

ፈጥኖ መቀላቀል ከጠቢባን መካከል መሰለፍ ነው።
"አርቤን ለትዳሬ" ምን ማለት ነው?

ለሥራ ፣ ለትምህርት ወይም ለተለያየ ተግባሮቻችን እና የህይወታችን ክፍል ጊዜ እንሰጣለን።

ትዳራችን ግን በህይወት ሩጫ መካከል ሲሸፈን ይታያል። ስለዚህ ይህ እንዳይሆን በሳምንት አንድ ቀን ማለትም "አርብን" ትዳራችንን ፣ ራሳችንን (ከትዳር አንፃር) ፣ የትዳር አጋሪችንን እና ልጆቻችንን በአስተውሎት ልናጤን ይገባናል። "አርቤን ለትዳሬ" ማለት ይህ ነው።

ዓላማው ምንድነው?
👉ባለትዳሮች ትዳራቸውን በእውቀት ፣ በማስተዋልና በጥበብ እንዲመሩ ማገዝ፤
👉ስለጋብቻና ልጆች አስተዳደግ ቁጭ ብሎ የመማርን ልምድ ማስረፅ፤
👉"አርብን" የቤተሰብ ቀን የማድረግ ባህልን ማስተዋወቅ ፤

ይህንን ሊንክ ተጭነው ይቀላቀሉ።
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
#ጤናማ_ቤተሰብ_ጤናማ_ሀገር
#የቤተሰብ_ቅጥር_አዳሽ
#ወደ ሚወደዉ ጌታ ሄዷል። #ዜና 😭😭

ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደሚወደው ጌታ ሄዷል።

የሄደው ወደጌታ ቢሆንም የሚወዱት ሲለይ ያሳዝናልና The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን.... 🙏🙏🙏
#የኢየሱስ ወታደር ነኝ ... #ወደ አምላኩ ሄደ 😭
ከ40ዓመት በላይ በጌታ ቤት ቆይቷል...

#ሄደ #ወደ አምላኩ ሄደ ...
ኢየሱስን ብሎ አለምን የካደ ሄደ ..😭

ከ1945 - 2016 ...

ሙሉቀን በ1960ና 70ዎቹ ብዙዎች በኢትዮጵያ ወርቃማ በሚባለው የሙዚቃ ዘመን፣ ቁንጮ ከነበሩት መካከል ነዉ ይሉታል። ኋላ ላይም ወደ ጌታ #ኢየሱስ መጥቷል።

ሙሉቀን በ1945 ዓ.ም በጎጃም ክፍለ ሃገር ተወለደ። በልዩ ተሰጦው ምክንያት በ12 አመቱ ሙዚቃን የጀመረው ሙሉቀን፣ በለጋ እድሜው ነበረ በመሸታ ቤቶች ውስጥ “እናቴ ስትወልደኝ መች አማከረችኝ” በሚለው ሙዚቃ የጀመረው።

ሙሉቀን የዘፈኑ አለም በቃኝ ብሎ ወደ ጌታ ከመጣበት 1970ዎቹ ማገባደጃ አካባቢ ጀምሮ በዝማሬ ማገልገሉን ቀጥሏል። በየጊዜው የቀድሞ የዘፈን ወዳጆቹ የእንዝፈን ግብዣ ቢቀርብለትም፣ አሻፈረኝ ብሎ ቀጥሎበታል።

ህመሙ በጠናበት ጊዜም እነ ታማኝ በየነ ልህክምና ወጪ የዘፈን ድግስ እናዘጋጅ ሲሉትም በኔ ስም አይዘፈንም ብሎ በቅድስና የኖረ ጀግና ክርስቲያን ነው።

ሙሉቀን ወደ ክርስቲያኖች ካደረሳቸው መዝሙሮች መካከል “ስለ ውለታህ”፣ አድራሻ ቢስ ሆኜ በዓለም ውስጥ ስጨነቅ”፣ “ሃሌሉያ”፣ “አቤኔዜር” እና ሌሎችንም መዝሙሮችን ከሃሌሉያ አልበሙ አስመቶናል።

በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ መታሰቢያ በEBS Tv ላይ "ከኢትዮጵያ ከወጣህ 38 ዓመት ሆኖሃል አትናፍቅህም?" የሚል ጥያቄ ብትሰነዝርለትም ሙሉቀን መለሠ ግን አትናፍቀኝም! ... ኢየሱስን ማየት ነው የናፈቀኝ ማለቱ የቅርብ ዓመች ትዝታ ነዉ።

#ዘማሪ #ሙሉ #ቀን ኑሮውን በአሜሪካን ሃገር ዋሽንግተን ዲሲ ከባለቤቱ ጋር አድርጎ በኖረበት በ71 ዓመቱ ወደ ሚወደውና ወዳገለገለው #ጌታ ሄዷል።

በነገራችን #ላይ ሙሉቀን መለሰ በዓለም የሙዚቃ ስራ ዉስጥ ለ14ዓመት ብቻ ከ13 ዓመቱ እስከ 27ዓመቱ ብቻ ነዉ የቆየው ዘፈን አቁሞ ወደ ጌታ ከመጣ ደግሞ 43 አመታትን አስቆጥሯል።

ከበርካታ ዝማሬዎቹ መካከል
አለም ተስፋ ቁረጭ አልተገናኘንም
አምላክ ከእኔ ጋር ነው አታሸንፊኝም

እንዲሁም
ከኢየሱስ ጋራ ሲሄዱ
ከጌታ ጋራ ሲሄዱ
እንዴት ያምራል ጎዳናዉ
እንዴት ያምራል መንገዱ

በብዙዎች ዘንድ የሚታወቀዉ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
የኢየሱስ ወታደር ነኝ
እዋጋለሁኝ አልሽነፍም
ለጠላት እጅን አልስጥም

የሚሉት ተጠቃሽ ናቸዉ ...

ለሙሉቀን መለሰ ቤተሰብና ወዳጅ ዘመዶች The Christian News - የክርስቲያን ዜና በድጋሜ መጽናናትን ይመኛል።
ለ3 እናቶች #እዉቅና ተሰጣቸዉ።

ላለፋት 12 ዓመታት ለቀደምት የወንጌል አርበኞችን በግምባር ቀደምነት እውቅና በመስጠት የሚታወቀው የምርጦቹ 7000 #ቤተክርስቲያን ለሦስት እናቶች እውቅና ሰጥቷል።

መረሃ ግብሩ ለትውልድ ወንጌልን ስላደረሱ ማመስገን የሚል ዓላማ ያለዉ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ቀጣዩን ትውልድ እንዲባርኩ ነው።

የበረከቱ ትሩፋት ምን እንደሆነ የቤተክርስቲያኒቷ ዋና መጋቢ አቢ እምሻው "የእናቶች በረከት የሚስጥር መዝገብ በሙላት ሲፈታ ብዙ ዘመን አሻጋሪ አቅሞች ይለቀቃሉ ፣ኃያላንም ይንቀሳቀሳሉ የትውልድን እስራት እየፈቱ ፣ "የዘመንን ስብራት እየፈወሱ ፣ ለቤተክርስቲያን መታደስና ለአገር መፈወስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በመረሀግብሩ እውቅና የተሰጣቸው እናቶች፦

👉 የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ መስራች የነበረው የተማሪዎች ህብረት እና የሴሎ መጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት የመጀመሪያ ዳይሬክተር እትዬ እናጉ ደሴ፣

👉የኢትዮጵያ ገነት ቤ/ክ አገልጋይ እና የዴቦራ የሴቶች አገልግሎት መስራች ወ/ዊ መዓዛ በቀለ፣

👉የኒው ላይፍ የሱስ ማገገሚያ ማዕከል መስራች ሲ/ር ይርገዱ ሀብቴ ናቸው።
#ሙሉቀን_መለሰን_ወደጌታ_ያመጡት_ሰው....

እኝህ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ሐዋሪያው ዳንኤል መኮነን ይባላሉ፡፡

በ1960ዎቹ እና በ70ዎቹ እጅግ አስገራሚ ነገር ጌታ ገልጦባቸዋል፡፡

ሽባ ሲተረተር፣ እብዶች ሲፈወሱ፣ አይድንም የተባለ በሽታ ሲድን፣ የሚታዮ የሚጨበጡ የሚዳሰሱ ተአምራቶች ሲሆኑ ብዙ ሰዎችም ጌታን ሲቀበሉ ነበር፡፡

ካሜራ ያልነበረበት ዘመን ሆኖ እንጅ እውነተኛው ሪቫይቫል በምድራችን የተገለጠበት ጊዜ ነበር፡፡

በጊዜው ፍላሚንጎ አካባቢ የነበረችውን መሰረተክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሚያስታውሳት ሁሉ ይሄንን እውነት ያውቀዋል፡፡

ጊዜው የደርግ መንግስት ቤተክርስቲያን ላይ ስደት ያወጀበት ፣ የወንጌላውያን ቸርቾች እየተዘጉ ያሉበት አስጨናቂ ጊዜ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን ታማኙ እግዚአብሔር በልጆቹ እያለፈ ብዙዎቹን ያሳርፍ፣ ብዙዎችን ይፈታ ነበር፡፡

በዛን ዘመን በእሳቸው እጅ ወደጌታ ከመጡ ብዙ ሰዎች መሀል በትናንትናው ዕለት ወደጌታ የሄደው የቀድሞው ታዋቂ ዘፋኝ የአሁኑ ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ይገኛል።

ዳንኤል መኮነን መድረክ ላይ እየሰበኩ እኔ ኢየሱስን አገኘሁት እስከመጨረሻው አለቀውም ብዬ ወሰንኩ ይላል።

ሙሉቀን....

ክርስቲያን ቲዩን እንደከተበዉ .. 🙏🙏🙏
#እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏

ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
ሮሜ 12:9

#FBI #church (ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል #ቤተክርስቲያን) በአንድ #አመት ውስጥ #በአዲስ አበባ በሁለት ክፍለ ከተሞች የአምስት አቅም የሌላቸውን ቤተሰቦች #ቤት ሰርተን አስረክበናል።

የረዳን #እግዚአብሔር የተመሰገነ ነው::