The Christian News
5.46K subscribers
3.21K photos
29 videos
760 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ብራቮ አብነት!

ማንም ይስታል ፤ ይሳሳታል ፤ይወድቃል ፤ የትኛውም ሰው የራሱ የሆነ ድክመት አለበት።

የዘማሪ አብነት ነገር ተገለጠ እንጂ ሁላችንም የራሳችን ድካም አለብን።

አስቀድሞ በስሜት ከሰራው ጥሩ ካልሆነው ቪዲዮ ይልቅ እግዚአብሔርን ይቅርታ ማለቱ ጥሩ ነው።

ህዝቡንም ማሳሳቱን ማመኑ እጅግ ጥሩ ነው። ይህ ለወደፊት አገልግሎቱ የመንገድ ጥርጊያ ነው። እኔም በግሌ አድንቄሀለው።

በግል የወሰደውንም እርምጃ ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት አቁሞ እራሱን እና አገልግሎቱን ፈትሾ በክብር ወደ ቀድሞው የዝማሬ አገልግሎት ለመምጣት መወሰኑን ከምንም በላይ አድንቄአለሁኝ ወዳጄ በርታልኝ።

በድካምህ እንደተገለጥንብህ ሁሉ በብርታትህም ደግሞ አብረንህ እንቆማለን። መልካም እድል በርታ!

Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
#አንድ ቀን #ብቻ ቀረዉ..

#አሁኑኑ ይመዝገቡ !!!

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር።

#እያደገ #ሄደ ...ምዝገባ ሊጠናቀቅ የቀረን #1 #ቀን ብቻ ነው።

#ማሳሰቢያ :- ያለ ምዝገባ መግባት አይቻልም።

ስለዚህ ፈጥነዉ በቀሩን #ጥቂት ቦታዎች በተቀመጡት የስልክ እና link አድራሻዎች በመጠቀም ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ ሊንኩን ይጫኑ

https://docs.google.com/forms/d/1XBwJuLL8hCAO1SA3E8aTmmg2y32G9jwY1PnG-BS8XXQ/edit?usp=drivesdk

#ወይም  ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
#ኑ #የእግዚአብሔርን #ቤት በጋራ እንስራ!!!

ለብዙዎች መጠለያ የሆነችው እና ለአርሲ ዩንቨርስቲ አሰላ ካምፓስ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ማምለኪያ የሆነችው የአሰላ አርዱ ቁጥር 2 #ሙሉ #ወንጌል ቤተክርስትያን #ዛሬ የሁላችንን እገዛ ትፈልጋለች።

#አሁን የምትገኝበት የማምለኪያ አዳራሽ የአምልኮ ፕሮግራም ለመካፈል የሚመጡትን አማኞች መያዝ ስላልቻለ እና እንዲሁም የአሁኑ አዳራሽ እየፈረሠ ስለሚገኝ ከአጥቢያዋ በረከት የተካፈላችሁ በዓለም ዙሪያ እንዲሁም በሃገር ውስጥ የምትገኙ የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቤተሰቦች ወዳጆች እንዲሁም #የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ለዚህ ስራ እጆቻቸሁን እንድታበረቱ ስንል በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ከመጋቢት 6 እስከ 8/2016 ዓ.ም በአጥቢያዋ የተዘጋጀ #ልዩ ኮንፍራንስ ስላለ በቦታው በመገኘት በዚህ የወንጌል ስራ እንድትሳተፉ #በጌታ #ፍቅር እንጠይቃለን።

በተጨማሪም በቦታው መገኘት የማትችሉ ከታች በመተቀመጠው የቤተክርስቲያኒቷ አካውንት እጆቻችሁን ትዘረጉ ዘንድ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን።

1000515969962 ንግድ ባንክ
1600860054837 ብርሃን ባንክ

የአሰላ አርዱ ሙሉ ወንጌል #ቤተክርስቲያን
#ማሳሰቢያ

አንዳንዶች የ VIP እና የVVIP ካርዶችን የዘማሪ ይድነቃቸውን አገልግሎት ለመደገፍ እያሉ እየሸጡ መሆኑን እየሰማን እንገኛለን ።

ነገር ግን ቀዳሜ ለሚደረገው መንፈሳዋ የአምልኮ ፕሮግራም ምንም አይነት የመግቢያ ክፍያም ሆነ የሚሸጥ ካርድ ስለሌለ ቅዱሳን ከእንደዚህ አይነት አጭበርባሪዎች ራሳችሁን እንድትጠብቁ እናሳስባለን....
#ዛሬ አልቋል።
ምዝገባ ተጠናቋል።

#ልጆችን በእግዚአብሔርም በሰዉም ፊት የማሳደግን #ጥበብ አብረን እንማር። #እያደገ #ሄደ ...ምዝገባ አጠናቀናል።

#ወደ ስልጠና ሲመጡ #አቅጣጫ እንዳይሳሳቱ ይደውሉ

0911136520/0988353423

#ለልጆቾ ማቆያ አያስቡ በቂ #ቦታ እና ባለሞያዎች አሉን።

ቀን:- መጋቢት 7/2016ዓ.ም
ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:30-10:30
ቦታ :- በወንጌል አማኞች የምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ደንበል አከባቢ)
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት ከኢትዮጰያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና ከአባል አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጉ።

ዉይይቱ ባለፉት ሳምንታት ከተደረጉ ውይይቶች የቀጠለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መሪዎች ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።

በዉይይታቸዉ የተነሱ ዝርዝር ነጥቦች ምን ይመስላል የሚለዉን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#መንገድ #ዝግ #ነዉ

#የኢትዮጲያ #ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመስቀል አደባባይ የሚያከናውኑት የፀሎት ፕሮግራም ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶችን ለተሸከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ

አሽከርካሪዎች እንደ ተለመደው ለትራፊክ ፖሊሶች ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ተጠይቋል፡፡

#ነገ ዕሁድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሽከርካሪዎች መረጃው አስቀድሞ ኖሯቸው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ ተባባሪ እንዲሆኑ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ #ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

• ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

.የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

• ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ ዕሁድ መጋቢት 8/16 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

በድል ተጠናቋል...

#ኢየሱስ ላውድልህ ሃገሩን በሚል በዘማሪ ይድነቃቸው ተካ የተዘጋጀ የመዝሙር ኮንሰርት #ዛሬ ከቀኑ 7 ሰዓት #ጀምሮ በሚሊኒየም #አዳራሽ ተካሂዷል።

ተወዳጁ #ዘማሪ ይድነቃቸዉ ተካ ከዳዊት ለሚ ባንድ ጋር በመሆን በ2003ዓ.ም የተለቀቀዉን ቁጥር አንድ #ቸኮለብኝ እና ከ5 ወራት በፊት የተለቀቀውን #ኢየሱስ አልበም አቅርቧል።

ነብይ ጥላሁን ጸጋዬ #በእግዚአብሔር ቃል በማካፈል አገልግሏል።

ዘማሪ ይድነቃቸው የአገልግሎት እና የህይወት ወጣ ዉረዱን በተመለከተ አጭር ዘጋቢ የቀረበ ሲሆን የመዝሙር ኮንሰርቱ በድል ተጠናቋል።
#በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተዘጋጀ የፀሎት መርሃ ግብር በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው።

ለሀገር ሰላምና አንድነት እየተካሄደ በሚገኘው የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።
#እንኳን ደስ አለን. .

#ክርስቲያን ፖድካስት #በክርስቲያን ቲዩብ በቅርብ ቀን..

ወንጌላዉያን ዘንድ ፈር ቀዳጅ እና ለብዙዎቻችን ምሳሌ የሆነዉ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ #አሁን ደግሞ በአዲስ አቀራርብ ብዙዎችን ተደራሽ ለማድረግ መጥቷል።

በጌታ የሆንን ክርስቲያኖች ወንጌልን ለብዙዎች የምንደርስበት ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የምንወያይበት፣ በወቅታዊ የቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ ሀሳባችንን የምናካፍልበት፣ የህይወት ተሞክሯችንን ለሌሎች የምናጋራበት፣ እግዚአብሔር ያደረገለንን የምንመሰክርበት የክርስቲያኖች መድረክ ክርስቲያን ፖድካስት በክርስቲያን ቲዩብ የዩቲዩብ ቻናል ተጀምሯል።

https://youtube.com/@christiantube4198?si=yUCsLdTyUAFh8VJz

ማንኛውንም በዚህ ፕሮግራም መነገር አለበት የምትሉትን ነገር ልታጋሩን የምትወዱ በስልክ ቁጥር +251777418556 ይደውሉልን

#ወንጌል በተለያየ መንገድ ያልተደረሱትን ለመድረስ ፣ የተደረሱትን ለማጠንከር ይቀጥላል...
#ደረሰ ደረሰ ደረሰ ...

የመጽሃፍ #ቅዱስ ሳምንት

#በኢትዮጵያ የመጽሃፍ ቅዱስ ማህበር አዘጋጅነት የሚካሄደዉ የመፅሐፍ ቅዱስ ሳምንት #እና የቅዱሳት መጻህፍት አውደ ርዕይ ከመጋቢት 16-21 በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል።

ክርስቲያኑን #ስለ መጽሃፍ ቅዱስ ንባብ ማነቃቃት፣ በመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ላይ የሚሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን በተዛማጅ ስራዎች ላይ ማስተባበር፣ የወንጌል ስብከትን ማበረታት፣ ለአሁኑ ትውልድ የመጽሃፍ ቅዱስን አደራና ሃላፊነት ማስተላለፍ እና መጽሃፍ ቅዱስን ከአደጋዎች መጠበቅ በሳምንቱ ከሚኖሩ ክንውኖች መካከል ናቸው።

ትውልዱን ስለ ቅዱሳት መጻህፍት እንዲያውቅ ማድረግ፣ የህትመት ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህዝብ ማድረስ እና ማህበሩን ከህዝብ ጋር ማስተዋወቅ በአውደ ርዕይው የሚከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች ናቸው።

#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

መግቢያ #በነፃ ...
... “ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።” ...

— ማቴዎስ 25፥43

የመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት የኤጄሬ ማረሚያ ቤትን ጎበኙ።

በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ የተመራ የልዑካን ቡድን #ዛሬ ጠዋት በምዕራብ ሸዋ የኤጄሬ ወረዳ ማረሚያ ቤትን ተጎብኝቷል ።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሕግ ታራሚዎች አገልግሎት መምሪያ ላለፉት 14 ዓመታት የእንጨት መሰንጠቂያ መሣሪያ ፣የብሎኬት ማምረቻ ማሽን እንዲሁም ለመስኖ ሥራ የሚሆን የውሃ ፓምፕ ማሽኖችን በመግዛት እና በማሰልጠን የሕግ ታራሚዎች የሞያ ባለቤት እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ይገኛል ።

ከሁለት ዓመት ወዲህ #ደግሞ #የሰላም ግንባታ እና የእርቅ አገልግሎት ሥልጠና በመስጠት ሰዎች በሠላም አብሮ እንዲኖሩ ታራሚዎች ከባላኔጣዎቻቸው ጋር ጠባቸውን በእርቅ እንዲጨርሱ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

የዛሬው ጉብኝት እስከ ዛሬ እየተሰሩ ያሉትን ማህበራዊና መንፈሳዊ ሥራዎችን በማየት ለቀጣይነት ለማበረታታት የተሰበ ቢሆንም እግረመንገዳቸውን 250 ለሚሆኑ ታራሚዎች መጽሐፍ ቅዱሳትን በነጻ አከፋፍለዋል።

በተጨማሪም የማረሚያ ጊዜያቸውን ጨርሰው በወጡ የቀድሞ የሕግ ታራሚዎች አማካኝነት የተተከለችውን የሆራ ቆታ የወንጌል ሥርጭት ጣቢያ ተጎብኝቷል ።
Follow the The Christian News channel on WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029VaSL4K8BadmdUHPWQW3m
#መጽሐፍ #ቅዱስ የማያነብ #ክርስቲያን የተበደለ ነው”

ይህንን ያሉት የኢትዮጵያ የመጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው ናቸው።

“መጽሀፍ ቅዱሳዊ እሴቶችን በሕዝባችን ሕይወት እናስርጽ!” በሚል መሪ ቃል የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የማህበሩ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ተስፋጽዮን ደለለው “መጽሐፍ ቅዱስ ያነበቡት ሁሉ ሕይወታቸው ተለውጧል ስለዚህ አሁን ያለው ትውልድ እንዲነብ ልናበረታታው ይገባል ብለዋል።” ብለዋል።

አክለውም መጽሐፍ ቅዱስን የማያነብ እና የማይገልጥ ክርስቲያን የተበደለ ነው። ማህበሩ ከማሳተም እና ከማሰራጨት ውጪ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልም በመሆኑም ህዝበ ምዕመኑ መጽሐፍ ቅዱስን አጠንክሮ እንዲያነብ ስለሚያስፈልግ ይህንን መድረክ አዘጋጅተናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር አዘጋጅነት የመጽሀፍ ቅዱስ ሳምንት በዓል እና የቅዱሳት መጻሕፍት ዐውደ ርዕይ መክፈቻ መረሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

መረሃ ግብሩ የቀጠለ ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#ሩስያ ወሰነች... የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴ የሽብር ድርጊት ነዉ።

ሩሲያ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን የአክራሪነት #እና የሽብር ድርጊት ዝርዝር #ውስጥ አካተተች

የሩሲያ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ተቆጣጣሪው ሮስፊንሞኒቶሪንግ አለምአቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን የሩሲያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ውሳኔው የተደረሰው ሩሲያ ከሞስኮ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች አክራሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው ተብሏል።

የሩሲያ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት አክራሪ ወይም አሸባሪ ተብለው የተፈረጁና በዝርዝሩ የሚካተቱ የግብረሰዶም አቀንቃኞችን ወይም ቡድኖችን የባንክ ሂሳቦች የማገድ ስልጣን ያለው መሆኑም ተጠቁሟል።

#tikvahethmagazine
#አስደሳች #ዜና

በአሁኑ ወቅት #ብቻ በኢንዶኔዥያ ከ35 በሚበልጡ ቋንቋዎች መጽሃፍ #ቅዱስ ትርጉም እየተካሄደ ይገኛል።

ኢንዶኔዥያን ለየት የሚያደርጋት ነገር፣ በአለማችን #ላይ ብዙ የእስልምና #እምነት ተከታዮች ያሉባት ሃገር መሆኗ ነው። ዋይክሊፍ አሶሴሽን የትርጉም ስራዎቹን የሚያከናውነው፣፣ በአካባቢው ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና #አዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው።

#አዲሱ የትርጉም ቴክኖሎጂ፣ በየአካባቢው የሚገኙ ክርስቲያኖች የትርጉም ስራውን ከፊት ሆነው ይመሩ ዘንድ ይረዳል ነው የተባለው። ይሄም መጽሃፍ ቅዱስ ባለቤትነታቸውን ይበልጥ ያረጋግጥላቸዋል። ግምገማ፣ ስልጠና፣ ህትመትና ስርጭቱንም ቢሆን እራሳቸው የየአካባቢው #ሰዎች እንዲሳተፉበት ይረዳቸዋል ነው የተባለው።

በአሁኑ ወቅት ብቻ ከዋይክሊፍ ተጨማሪ ሌሎች የመጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ድርጅቶች #አንድ ላይ በመሆን ከ60 በማያንሱ የኢንዶኔዥያ ሃገር ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ።

በኢንዶኔዥያ ብቻ ለሚሰራው የመጽሃፍ ቅዱስ ስራ፣ ከ400 እስከ 500 ሺህ ዶላር በጀት ተይዞለታል። #ይሄ ወጪ ከበጎ ፈቃደኞች የተሰበሰበ ሲሆን ሌሎችም በጸሎት የዚህ #ታላቅ ስራ አካል ይሁኑ ሲል ዋይክሊፍ ጥሪ አቅርቧል።

ኢንዶኔዥያ ውስጥ ከ700 በላይ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ይሄም ሃገሪቱን በአለም ላይ ካሉ ቋንቋዎች 10 በመቶ በሃገሪቱ ብቻ መኖሩን ያሳያል።
43ኛ ሲኖዶስ ተመሰረተ

#የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ #ኢየሱስ 43ኛ ሲኖዶስ የሆነው የጆርጎ ብርብር ሲኖዶስ ምስረታ በትናትናው ዕለት መጋቢት 16, 2016 ዓ.ም በታላቅ ክብረ በዓል እና ቁጥራቸው በሺዎች በሚቆጠሩ ምዕመናን በከተማ ጎዳኖች ላይ በተንፀባረቀ #ደስታ በደበሶ ከተማ፣ ምዕራብ ወለጋ ተካሄደ።
" 2 አገልጋዮች ከነ #ሙሉ ቤተሰቦቻቸው በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል " - የአካባቢው ምዕመናን

የደብረ ቅዱሳን #ቅዱስ ገ/ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን #ሁለት አገልጋዮች #ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው መገደላቸውን የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ገለጸ።

በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 2 አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለጊዜው " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት መገደላቸው ተነግሯል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ ግድያው የተፈፀመው ትናንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ገደማ መሆኑን የአካባቢው ምዕመናን እንደነገሩት ገልጿል።

በተፈጸመው በዚህ ግድያ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት አንድ መሪጌታና ዲያቆንን ጨምሮ 5 የቤተሰብ አባሎቻቸው በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተገልጿል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፥ በዶዶላ ከተማ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም በርካታ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን አስታውሷል። ሲል ቲክቫህ #ኢትዮጵያ አስነብቧል።
የቀድሞው የ #አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መጽሃፍ #ቅዱስ መሸጥ ጀመሩ።

ትራምፕ በራሳቸው ማህበራዊ ትስስር ገጽ (ትሩዝ ሶሻል) ደጋፊዎቻቸው “ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” የሚል ስያሜ ያለውን መጽሃፍ ቅዱስ እንዲገዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#ወደ ፋሲካ በዓል እየተቃረብን ነው፤ ‘ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ’ መጽሃፍ ቅዱስን በመግዛት አሜሪካ ዳግም እንድትጸልይ እናድርጋት” ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

#ሁሉም አሜሪካውያን በቤታቸው መጽሃፍ ቅዱስ ሊኖራቸው እንደሚገባም ነው ያነሱት።

ትራምፕ ዝርዝር #ውስጥ መግባት ባልፈልግም መጽሃፍ ቅዱስ በህይወቴ ውስጥ ልዩ ቦታ አለው ብለዋል።

“ፈጣሪ አሜሪካን ይባርክ” መጽሃፍ ቅዱስ God Bless The USA Bible.com በተሰኘ ድረገጽ በ59.9 ዶላር ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ድረገጹ መጽሃፍ ቅዱስ በትራምፕ መተዋወቁ “ምንም አይነት ፖለቲካዊም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ” አላማ የለውም ማለቱንም አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

#አዲሱ የመጽሃፍ ቅዱስ ግዙ ቅስቀሳም በወንጌላውያን አማኞች ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ትራምፕ በቀጣዩ ምርጫ ክርስቲያን ደጋፊዎቻቸውን ለማብዛት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ተገልጿል።