The Christian News
5.43K subscribers
3.23K photos
30 videos
767 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አዲስ_መረጃ
#የአዲስ_አበባ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉብኝት
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባላት በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ግጥር ግቢ ውስጥ በመገኘት በጎርፍ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦችን ጎበኙ።

ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ/ም ከሰዓት በጣለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በመከሰቱ በመካነ ኢየሱስ ሴሚነሪ ግቢ በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ የህይወትና የንብረት አደጋ በመከሰቱ ህይወታቸውን ላጡት እንዲሁም ንብረት ለወደመባቸው ወገኖቻችን ተቋማችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል። ሲል ባስተላለፉት መልዕክት

በደረሰው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡት ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲያበዛላቸው እየተመኘ ለሞቱት ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ምኞታችንን እንገልፃለን። ሲሉም ሀዘናቸውን ገልጸዋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
#አዲስ_መረጃ
#ካውንስሉ
#ህብረቱ
#መሰረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን

#እግዚአብሔር_መፅናናትን_እንዲያበዛላችሁ_ፀሎታችን_ነዉ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በመካኒሳ መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ እና በአከባቢዉ ማህበረሰብ ላይ በደረሰዉ የጎርፍ አደጋ በህይወት እና በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት እጅግ ማዘናችንን እንገልጻለን።
በትላንትናው እለት በጣለው ከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ህይወታቸውን ላጡ እና ንብረቶቻቸው ለወደመባቸው አካላት ካውንስሉ መጽናናትን ይመኛል።

ስለሆነም ሁላችሁም የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አባላት ቤተእምነቶች፤ ሚኒስትሪዎች እና አገልጋዮች በሙሉ ከሴሚናሪው እና ጉዳት ከደረሰባቸው አካላት ጉን በጸሎታችሁ እና ልዩ ልዩ ድጋፍ በማድረግ አብራችሁ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና ለተጎጂ ቤተሰቦች እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲያበዛላችሁ ፀሎታችን ነዉ።
1 ተሰ. 4፥13-18
ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ጠቅላይ_ፀሐፊ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት፣ በመካነ የሱስ ሰሚናርየም ግቢ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማውን ኀዘን እየገለ፣ የመጽናናት አምላክ ለቤተሰቦቻቸውና ለቤተክርስቲያኒቱ ብርታቱን ይሰጥ ዘንድ ይመኛል።

#የኢትዮጵያ_ወንጌላውያን_አብያተክርስቲያናት_ህብረት

በትናንትናው ዕለት በአዲስ በአዲስ አበባ መካኒሳ አከባቢ በደረሰው የጎርፍ አደጋ በደረሰው የወገኖቻችን ሕልፈት ሕይወት ከፍተኛ ሐዘን ተሰምቶናል። ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን ።

#የመሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን
#አዲስ_መረጃ
#የክርስቲያን_መጽሐፍ_ቅዱስ_ካምፕ_በሰደድ_እሳት_ወደመ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በካሊፎርኒያ ሰደድ እሳት ምክንያት የክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ካምፕ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

በካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኝው እና በየአመቱ እስከ 2200 ጎብኚዎች ያሉት አንድ ታዋቂ የክርስቲያን ካምፕ ሙሉ በሙሉ በሰደድ እሳቱ አማካኝኘት ወድሟል።
ከሰሞኑን የነበረው የሰደድ እሳትም በክልሉ ታሪክ ውስጥ ከታዩት የከፋ የእሳት አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።

በ1952 የተመሰረተው እና በአልማኖር ሐይቅ ዳርቻ ላይ በክልሉ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍል የሚገኘው የሴራ መጽሐፍ ቅዱስ ካምፕ በውስጡ 23 ቤቶች የነበሩ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ወደ አመድነት ተቀይረዋል።

የሴራ መጽሐፍ ቅዱስ ካምፕ የቦርድ አባል የሆኑት ማይክ ቬንሲሊ ለክርስቲያን ፖስት እንደተናገሩት ይህ ልብን የሚሰብር ነው ሲሉ ገልጸውታል።

በርካታ ሰዎች እና ህጻናት ክርስቶስን እዚህ አግኝተዋል በየአመቱ ከ1500-2200 የሚሆኑ ሰዎች እና ህጻናት ይጎበኙት ነበር አሁን ይሄ ሁሉ ጠፍቷል። ሁላችንም በጣም አዝነናል ልባችንም ተሰብሯል ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ቬንሲሊ አክለው አሁን ተቋሙ መልሶ እራሱን ለማቋቋም በኢንሹራንስ እና የገቢ ማሰባሰቢያዎች ያደርጋል ግን ይሄ ሁሉንም አይሸፍንም ስለዚህም ምናልባት ተጨማሪ የሳምንታት ማስታወቂያ ስራ እንሰራለን ብለዋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ
#አዲስ_መረጃ
#በሀገራዊ_ጉዳይ_አስቸኳይ_ጾም_ጸሎት_ታወጀ
#ካውንስሉ
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት አውጀ።

የጾም እና የጸሎት መረሃ ግብሩን አስመልክቶ በዛሬው እለት ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ በጽ/ቤቱ ሰጥቷል።

ካውንስሉ በመግለጫው የኢትዮጵያ ወንጌል አማኖች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የሰላም ምንጭ በኢትዮጵያ አገራችን ላይ እንዲታይ ሕዝቦች ሁሉ እንዲያርፉ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ፤ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ዘማሪያንና በተለያዩ የጸሎት ቡዱኖች ወስጥ የማናገለግል በአጠቃላይ ሁላችን አገልጋዮች ነሃሴ 25/2013ዓ.ም አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው በመማጸኛ ከተማ ቤተክርስቲያን (ዩጎ ሲቲ) ከማለዳው 01:00 ሰዓት ጀምሮ የጾምና የጸሎት ፕሮግራም አዘጋጅተናል። ሲል አሳውቋል።

መግለጫውን የሰጡት የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ እና የካውንልሱ ጽ/ቤት ሀላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ እንዳሳወቁት መሪዎች በየቤተእምነታቸው የሚጸልዩት እንደተጠበቀ ሆኖ በዚህ በጋራ በተዘጋጀው መረሀ ግብርም ሁሉም በመገኘት በጋራ እንዲጸልዩ ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!