The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የአርጀንቲና ወንጌል አማኞች ህጋዊ እውቅና አገኙ

በሃገሪቱ ህግ መሰረት ከካቶሊክ በስተቀር ለማንኛውም ሃይማኖት እውቅና አይሰጥም። የሃቪየር ሚሌ መንግስት ካቶሊክ ያልሆነ ምንግስትን ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ሰጥቷል።

በማህበርነት ስም ሲመዘገብ ለቆየ የወንጌላዊያን እምነት ተከታይ ዛሬ ህጋዊ ሰውነት ማግኘት ትልቅ የምስራች ነው። ላለፉት 30 አመታት ይህግ ባለሙያዎች፡ የወንጌላዊያን ማህበራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያቀርቡ ነበረ።

እውቅናውን የሃገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር ፈርሞ አጽድቆታል። የአርጀንቲና ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጥምረት ውሳኔው የእምነት እኩልነትን ያረጋገጠ፡ የሃይማኖት ነጻነትን ያረጋገጠ እና የወንጌላዊያንን ጥንካሬ ያረጋገጠ ነው ብሎታል።

የህጋዊ እውቅና ጉዳዩ ከልታወቅ ባለፈ ክርስቲያኖች ወንጌልን በነጻነት መስበክ የሚያስችል እርምጃ ነው። የወንጌላዊያን ቁጥር በ2008 ከነበረበት የ8% በ2018 ወደ 15% አድጓል። ይሄ ወንጌል በአካባቢው ምን ያክል እየተስፋፋ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው።

በኦቦሌሳ አዶላ

Evangelical Focus እንዳስነበበው።
👍1410🔥3🥰1👏1
የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎችን ለማገዝ 250 ሺህ ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን እና ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ ከአዲስ አበባ ሴቶች እና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ 10 የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚ ለነበሩ ሴቶች ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፉ ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺህ የብር ግምት ያለው የመስሪያ እቃዎችና ግብአት (የአንጀራ መጋገሪያ ምጣድ እና የችብስ መጥበሻ) እንዲሁም ስራ ማስጀመሪያ መቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያካተተ በአጠቃላይ ግምቱ 250 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ አቋቁሟል።

በዚህ መርኃ ግብር የብራይት ስታር ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ፣ የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላን ጨምሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

የድጋፍ ርክክቡ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ተጠቃሚዎች በፍላጎታቸው መሠረት የተደረገላቸው መነሻ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፍን ተጠቅመው ጠንክረው በመስራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከተረጂነት በማላቀቅ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማሳሰብ ቢሮውም በመዋቅሩ አማካኝነት ክትትልና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በመጨረሻም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን አሁንም በጊዜያዊ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ሆነው መቋቋም የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ለማገዝ አቅሙ ያላቸው ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ቢሮው በጋራ ለመስራት ዝግጁ ስለመሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
👍31
በፕሪሚየር ሊጉ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ምልክት/አርማ በተጨዋቾች የጫማ ክር እና የአምበሎች አርማ ላይ መደረግ ይቆማል።

በቀጣዩ አመት #የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በብዙዎች የሚወገዘዉ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ምልክት/አርማ በተጨዋቾች የጫማ ክር እና የአምበሎች አርማ ላይ መደረግ እንደሚቆም ተሰምቷል።

ፕሪሚየር ሊግ ለ 13 አመታት በዚህ ተግባር ላይ ከሚሰራ ተቋም ጋር የነበረዉ የስፖንሰርሺፕ ዉል ጊዜዉን ጨርሷል ተብሏል። የሁሉም ቡድን አምበሎች በተገኙበት በተደረገ ስብሰባ አርማዉ መደረጉ ከድጋፍ ይልቅ ተቃዉሞ እየታየበት ነዉ ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የእግር ኳስ ተመልካቾች የሚያዉቁትን አርማ ተጨዋቾች የማይጠቀሙት ይሆናል። ሆኖም ፕሪሚየር ሊጉ በራሱ የሊጉ አርማ ላይ ምልክቱን እንደሚጠቀም ተዘግቧል። ሊጉ የራሱን "የግንዛቤ ማስጨበጫ" ሲል የጠራዉን ዘመቻ እንደሚሰራም ገልጿል።

በባለፈዉ አመት የክሪስታል ፓላሱ አምበል ማርክ ጌሂ በአርማዉ ላይ "ኢየሱስን እወዳለሁ። ኢየሱስም ይወዳችኋል" ሲል በመጻፍ ተጨዋቹ የእምነቱን ህግጋት እንደሚያከብር ተናግሯል።

በተጨማሪም የኢፕስዊች ታዉን አምበሉ እና የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሙሪ አርማዉን አልጠቀምም ማለቱ አይዘነጋም። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አርማ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ መጠቀም ሲጀመር የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን የሚያቋርጡ ሀገራት እንዳሉም ይታወቃል።

ይህ ተግባር ለአመታት ተቃዉሞ ሲቀርብበት የነበረ ነዉ።
በረከት ሞገስ ለዳጉ ጆርናል እንደዘገበው።
15👍3👏3👌1
“በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል” መጽሐፍ በሀዋሳ ከተማ በይፋ ተመረቀ።

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ “በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል” በሚል ርዕስ የተጻፈው መጽሐፍ #ዛሬ ነሐሴ 4/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን በይፋ ተመረቀ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በመፅሐፍ ምረቃው ላይ ተገኝተው መጋቢ ፃዲቁ አብዶ ትውልድን ሊያስተምር የሚችል መፅሐፍ መፃፋቸውን በመጥቀስ በቀል በቀለኛን የሚያጠፋ በመሆኑ ትውልድ ከበቀል በመውጣት በይቅርታና በፍቅር መኖር እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ በበኩላቸው ከባለቤታቸው ሰላማዊት ቡርቂቱ ጋር በመሆን መፅሐፉን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

በመጽሐፍ ምረቃው ፕሮግራም ላይ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ሰንበቶ በሼን ጨምሮ የሲዳማ ክልል እና የሀዋሳ ከተማ ወንጌውያን አማኞች ካውንስልና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ በዝማሬና በእግዚአብሔር ቃል ያገለገሉ ሲሆን የሲዳማ ክልል የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስያናት ካውንስል እና የወንጌላውያን አብያተክርስትያናት ህብረት የቦርድ ሰብሳቢዎች፤ የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን መጋቢዎች በአንድነት በመሆን የመፅሐፍ ሪቫን በመቁረጥ የመፅሐፉን መመረቅ በይፋ አብስረዋል።

ምንጭ @የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
5👍2👏1
ተመዝግበሻል?

እኛ ሚስቶች እንደብልኋ ሴት ቤታችንን በእጆቻችን የምንሰራበትን ጥበቦች ልንሸምት፣ ማስተዋሎችን ልንካፈልና እውቀቶችን ልንገበይ ቀናቶችን ቀጥረናል።

2ኛው ዙር  ዕንቁ ልብ የሚስቶች ት/ቤት ምዝገባ ተጀምሯል ‼️

📍በሰሊሆም የተላከ ትውልድ ቤተ-ክርስቲያን

🗓ከነሐሴ 12-23 አስር የሥራ ቀናት

⌚️ከጠዋቱ 2:30-6:30

አሰልጣኞች ፦
1. ዘለቃ በቀለ (ቃቁ)
2. ወንጌላዊት መዓዛ በቀለ
3. መጋቢ ምዕልተፀጋ ገ/መድህን (ዶ/ር)
4. እህት ዘነበች እርዳ
5. እህት ሳሮን ውድነህ

👉አድራሻ ፦ ከስታድየም ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጠመንጃ ያዥ ኖክ ማደያ ሳይደርስ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት 3ኛ ፎቅ

🖊ለመመዝገብ ፦ በ0911136520/0946693468 ይደውሉ!

💯 ለውጥ ይሆንልሻል‼️


ከ1ኛ ዙር ተሳታፊዎች የተሰጠ ምስክርነት 👇
https://youtu.be/R0xrbvtxH58?si=mxOUGROh3VPDgzGB

ለበለጠ መረጃ ይህን ግሩፕ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
4👍2🔥1🙏1
#እንደ ሃገር ምን ያክል የምንጸልይ እንሆን?

ሰሞኑን የትኛዎቹ ሃገራት ምን ያክል ይጸልያሉ የሚል ጥናታዊ ግኝት ይፋ ተደርጓል።

ቪዥዋል ካፒታሊስት የተሰኘ ድህረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በፈረንጆቹ 2025 የ35 ሃገራትን የጸሎት መረጃ ይፋ አድርጓል። ኢንዶኔዥያ ከ269 ሚሊዮን ህዝቧ 95% ቢያንስ በየቀኑ እንደሚጸልዩ ይፋ አድርጓል።

በተለይ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት ደረጃውን የሚመሩት ሲሆን፣ ምዕራባዊያን እና ባለ ትልቅ ኢኮኖሚ ሃገራት ደግሞ በሰንጠረዡ እግርጌ ይገኛሉ።

• ኢንዶኔዥያ ከ269 ሚሊዮን ህዝቧ 95 ሚሊዮን ህዝቧ በየእለቱ ይጸልያል።
• ኬኒያ ከ47.4 እና ናይጄሪያ ከ195.5 ሚሊዮን ህዝቧ 84 በመቶ በመጸለይ ሁለተኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
• ሃንጋሪ ከ1.1 ሚሊዮን ህዝቧ 11 በመቶ እና ስዊድን ከ8 መቶ ሺህ ህዝቧ 8 በመቶ ብቻ በመጸለይ በደረጃው እግርጌ ይገኛል።
• በህንድ ከ1 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ወይም 71% ህዝብ ይጸልያል።
• ከአሜሪካ ህዝብ 149 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ወይም 44 በመቶ ህዝብ በየቀኑ ይጸልያል።

ፒው ሪሰርች ማዕከል ከአለም ባንክ ባገኘው መረጃ ባደረገው ምርመራ አማካኝነት ባደረገው ጥናት ነው ይሄንን ውጤት ይፋ ያደረገው። 35ቱ ሃገራት የአለምን ግማሽ ህዝብ ያክላሉ ይበል እንጂ እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ ቁጥር ያላቸው ሃገራት መረጃ ማግኘት አለመቻሉን ይፋ ተደርጓል።

የክርስትና እና እስልምና እምነት የሚበዛባቸው ሃገራት በሰንጠረዡ ከላይ ሲቀመጡ፣ ሴኩላር እና በኢኮኖሚ የበለጸጉ የሚባሉት ሃገራት ደግሞ ከታች ተቀምጠዋል። ግኝቱ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ይፋ ያደረገው መረጃ የለም።

እናንተስ ከ132 ሚሊዮን ህዝባችን ምን ያክል % በየቀኑ ይጸልያል ትላላችሁ? ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

በኦቦሌሳ አዶላ
6🤔3👏1🙏1
የአዋሽ አርባ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከከተማው አብያተ ክርስቲያናት እና ከወረዳው ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የደም ልገሳ ፕሮግራም አከናወነች።

በአፋር ክልል ዞን 3 አሚባራ ወረዳ በአዋሽ አርባ ከተማ የምትገኘው የአዋሽ አርባ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከከተማው አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ጋር በመተባበር በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተዉን የእናቶች ሞት ለመቀነስ የደም ልገሳ አከናዉነዋል።

በመርሀ ግብሩ ደም ለሚለግሱ ወገኖችም የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠም ሲሆን በግሬት ኮምሽን ኢትዮጵያ የተማሪዎች የሚሽን አገልግሎት ህብረት በጋራ የፕሮግራሙ አካል በመሆን ደም ለግሰዋል።

በእለቱም በተደረገ ልገሳ 43 ዩኒት የተሰበሰበ ሲሆን በወረዳውም የመጀመሪያ ሪከርድ ሆኖ ተመዝግቧል።

በእለቱ በአዋሽ አርባ ከተማ የሚገኙ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አባላት ከዚህ ቀደም በከተማዋ በሚከናወን የማሕበራዊ በጎ ስራዎች ላይ ሲሳተፉ እንደነበር የተጠቀሰ ሲሆን ማህበረሰብን በሁለንተናዊ መልክ በማገልገል ረገድ አሁንሕ የተጠናከረ ስራ እንደሚሰራ መሪዎቹ ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያንም በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ የነበሩ ተቋማትንና ደም የለገሱ ቅዱሳንን አመስግነዋል።

አልዓዘር ማቴዎስ
6👍1
ለሲኖዶሶች የመንፈሳዊ መጽሐፍት ድጋፍ ተደረገ።

የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ለመማር ማስተማር ህደት እና ለአገልጋዮች የሚረዱ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤጊ ግዳሚ ሲኖዶስ (ቤጊ): ለቦረናና አካባቢው ሲኖዶስ (ያቤሎ): ለአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ (አዶላ ወዩ) የመጽሐፍት ድጋፍ አበርክቷል።

መጽሐፍቶቹም በየሲኖዶሶቹ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት እና ምዕመናን አገልግሎት የሚውሉ እንደሆነም ተገልጿል።

የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሳ የተለያዩ መንፈሳዊ መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያኒቱ ድጋፍ ያደረጉትን ተቋማት 'Rafiki Foundation' fi 'Lutheran Heritage Foundation' እና ሌሎችንም በማመስገን : መጽሐፍቶቹን ለቤተክርስቲያኒቱ ሴሚናሪዎች: መጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጆች እና ት/ቤቶች እና ማ/ምዕመናን ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን ድጋፍ የማድረጉ ስራ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
👍32
5 ቀን ቀረው‼️

ተመዝግበሻል?

#እኛ ሚስቶች እንደብልኋ ሴት ቤታችንን በእጆቻችን የምንሰራበትን ጥበቦች ልንሸምት፣ ማስተዋሎችን ልንካፈልና እውቀቶችን ልንገበይ ቀናቶችን ቀጥረናል።

2ኛው ዙር  ዕንቁ ልብ የሚስቶች ት/ቤት ምዝገባ ተጀምሯል ‼️

📍በሰሊሆም የተላከ ትውልድ ቤተ-ክርስቲያን

🗓 ከነሐሴ 12-23 አስር የሥራ ቀናት

ከጠዋቱ 2:30-6:30

አሰልጣኞች ፦
1. ዘለቃ በቀለ (ቃቁ)
2. ወንጌላዊት መዓዛ በቀለ
3. መጋቢ ምዕልተፀጋ ገ/መድህን (ዶ/ር)
4. እህት ዘነበች እርዳ
5. እህት ሳሮን ውድነህ

👉አድራሻ ፦ ከስታድየም ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጠመንጃ ያዥ ኖክ ማደያ ሳይደርስ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት 3ኛ ፎቅ

🖊ለመመዝገብ ፦ በ0911136520/0946693468 ይደውሉ!

💯 ለውጥ ይሆንልሻል‼️

ከ1ኛ ዙር ተሳታፊዎች የተሰጠ ምስክርነት 👇
https://youtu.be/R0xrbvtxH58?si=mxOUGROh3VPDgzGB

ለበለጠ መረጃ ይህን ግሩፕ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
3👍2🔥2👏1
#የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን ታሪክ የሚመዘግብ  ስምምነት ተፈረመ

ዋይክሊፍ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር ነው የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረመው። ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ የወንጌላዊያንን ታሪክ መሰነድ እና አትሞ ይፋ ማድረግ ላይ በጋራ ይሰራሉ ተብሏል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝደንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እና የዋይክሊፍ ኢትዮጵያ መጽሃፍ ቅዱስ ትርጉም ማህበር አመራሮች ናቸው። በዚህ ስራ የረጅም አመታት የወንጌላዊያን ታሪክን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ ያስችላል ተብሏል።

ምንጭ፡ ዋይክሊፍ ኢትዮጵያ
👏12🔥4🙏3👍1
የጉዲና ቱምሳ ሌጋሲ ቀን በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ።

“Reading the Signs of the Times ወይም የጊዜውን ምልክቶች ማንበብ የሚል መሪ ቃል የተሰጠው የዘንድሮው አመት ጉባኤ በአድዋ ድል መታዘቢያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ። መድረኩ ቄስ ጉዲና ቱምሳ የነበራቸውን ሁለንተናዊ አገልግሎት ራዕይ ዛሬ ድረስ በተግባር የሚያሳይ ነው ተብሏል።

መድረኩን ቄስ ሃረገወይን በጸሎት ያስጀመሩ ሲሆን፣ የፋውንዴሽኑ ዳሬክተር ወ/ሮ ሌንሳ ጉዲና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አቅርበዋል። ከ1ሺህ በላይ ምሁራን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የማህበርሰብ ልማት ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዶ/ር ለማ ደገፋ፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ ዶ/ር ሳሙኤል ዮናስ እና ቄስ ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ በመድረኩ ጥናታዊ ጽሁፎችን አቅርበዋል። ወንድም አሳየኸኝ ለገሰ፣ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በዲጂታል ሚድያ ዘመን የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ከማስፈጸም እና ጥአንካራ የማህበረሰብ ግንኙነትን ከመፍጠር አንጻር ንግግር አድርጓል።

ሌላው በመድረኩ የተነሳው ጉዳይ ቄስ ጉዲና የነበራቸው ባለራዕይ የስነ መለኮት አረዳድ በዛሬ ጊዜ አተገባበር ላይ የፓነል ውይይት ተካሂዷል።

ቄስ ጉዲና ቱምሳ የቀድሞ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ጠቅላይ ጸሃፊ ሲሆኑ በ1971 ዓ.ም በደርግ መንግስት ነው የተገደሉት። ጉዲና ቱምሳ ፋውንዴሽን በሳቸው ስም የተሰየመ እና ከ1984 ጀምሮ በኢትዮጵያ የግብረ ሰናይ ስራዎችን የሚሰራ ተቋም ነው።
8👍2🙏1👌1
ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር በተያያዘ እየተሠራጨ ያለውን ስም የማጥፋት ዘመቻ የተሳሳተ እና ቤተክርስቲያንን የማይወክል ነው ስትል የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የዐቋም መግለጫ አወጣች።

መግለጫው ቤተክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ አስተምህሮን ሳይነጣጠል፣ ሳይጣስና ሳይሸራረፍ አማኞች በሕይወታቸው ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጽኑ አቋሟን በትጋት የምታስተምር ቤተከርስቲያን መሆኗን በመጥቀስ በቅርቡ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነትና ተቃራኒ እንዲሁም ከኢትዮጵያዊው ባሕል ተጻራሪ ከሆነው ከግብረ ሰዶማዊነት ጋር በተያያዘ የቤተ ከርስቲያናችን ስም ሲነሣ መታዘቧን ጠቅሳለች።

በመግለጫው ቤተክርስቲያን ይህ ተግባር መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ለሌለው እስከዛሬ እየተቃወመችው ያለ አሁንም አጠናክራ የምትቀጥለው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ የምታምነውን እና በመሰረተ እምነቷ የተቀመጡ እየተገበረች ያለችውን 6 ነጥቦች በግልጽ አስቀምጣለች።

በሌላ በኩል የግል ፍላጎቶቻቸውን ለማሳካት የቤተከርስቲያናችንን መልካም ስም በማጥፋት የተጠመዱ ወገኖች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡም ማሳሰቢያ ሰጥታለች።

ሙሉ መግለጫውን እንድታነቡት እናሳስባለን!!!
👍96🙏1👌1
የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ዘላቂ #ሰላም ማምጣት እንዲቻል የሁሉም ባለድርሻ ካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ አስታወቀች።

ቤተክርስቲያኗ GRAND project ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ የምክክር መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩም ከጋምቤላ ከተማ ከአምስቱም ቀበሌ ከአኝዋሃ ዞን እና ጎግ ወረዳ የተወጣጡ የሀይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የምስራቅ ጋምቤላ ቤቴል ሲኖዶስ መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ቄስ ኝጎዎ ኡሞድ በመድረኩ እንደተናገሩት ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የሰላም ግንባታ ማዳበር እንዲቻል የሀይማኖት ተቋማት የሀገር ሽማግሌዎች ጨምሮ ሁሉም አካላት ለሰላም ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሰላም ለሰዉ ልጅ ከሚያስፈልጉት እጅግ መሰረታዊ ነገሮች ዉስጥ አንዱና ግንባር ቀደም መሆኑን ገልፀዉ የክልሉን ማህበረሰብ ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ዋነኛ ተግባር አድርጋ ቤተክርስቲያኗ እየሰራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

የሰላም እጦት በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በተፈጠሩ አለመግባባቶች ብዙ የልማት ስራዎች ሳንሰራ የቀረን ሲሆን የሰላምን ዋጋ በመገንዘብ የሰላም ግንባታዉ እንዲዳብር ብዙ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የእምነት ተቋማቱ በጋራ በመሆን ያለዉን ሰላም ለማስቀጠል የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ልንሰራ ይገባልም ብለዋል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው።

ተጨማሪ ዝርዝር በፌስቡክ ገጻችን መመልከት ትችላላችሁ
4👍2👏1🙏1
ክፍለ ዘመን የዘለቀው አገልግሎት ወደ ጌታ በመሄድ ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

የከፍተኛ ትምህርትን ማጠናቀቅና የሥራ እድል ማግኘት እንደ ትልቅ ስኬት በሚወሰድበት በ1950ዎቹ መጨረሻ መጋቢ ፍቃዱ የኮሌጅ ትምህርታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ በሚገኘው አደይ አበባ ብርድ ልብስ ፋብሪካ የተቀጠሩ ቢሆንም እሳቸው ግን የወንጌል አገልጋይነትን መለኮታዊ ጥሪ ተቀብለው ሥራቸውን በመሠዋት ሁለት አመት አዲስ አበባ ውስጥ ራሳቸውን ለወንጌል አገልጋይነት ሲያዘጋጁ በጸሎትና በሕያው ቃሉ ሲታጠቁ ከቆዩ በኋላ ወደ ነቀምት አቅንተው በብዙ ዋጋ መክፈል ለ5 ዓመታት ወንጌልን ሰብከዋል።

ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ በመለኮታዊ ምሪት አቅንተውም ወንጌልን የሰበኩ ቢሆንም እስርና ስደት በርትቶባቸው ወደ ነቀምት ቢመለሱ ወንጌልን በዚያ ስፍራ ድጋሚ ማገልገል አይገባቸውም በሚል በተነሳባቸው ስደትና ተቃውሞ ወደ ወኅኒ ተወረወሩ። ከወኅኒ እንደ ወጡም አዲስ አበባ በመምጣት በቀድሞ አጠራሩ አዲስ አበባ ሙሉ ወንጌል አሁን ቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ የሚባለው አጥቢያ አገልጋይ በመሆን በጡረታ እስከወጡበት ዕለት ድረስ በጽናትና በታማኘት ለሌሎች አርአያ በመሆን አገልግለዋል።

መጋቢ ፍቃዱ ግማሽ ከፍለ ዘመን የዘለቀው አገልግሎታቸው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ ከምሥረታዋ ጀምሮ አስከ ዛሬ ድረስ በጸሎት ፤ በወንጌል ሰባኪነት ፤ በመጋቢነት በማግልገል ከብዙዎች ጋር ስለወንጌል ዋጋ የከፈሉ የወንጌል አርበኛ ነበሩ።

በ2014 ቀጠና 2 ሙሉ ወንጌል ቤ/ክን "ለወንጌል እና ለቤ/ክን ብዙ መከራ የተቀበሉ አባቶችን ምስጋና እና እውቅና በሰጠችበት ወቅት ዛሬ ከዚህ አለም ድካም ያረፉት መጋቢ ፍቃዱ ኦፍጋ አንዱ ነበሩ።

የክርስቲያን ዜና በመጋቢ ፍቃዱ ዜና እረፍት የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን መጽናናትን እንመኛለን።
13😭13🕊6💔1
#በኢትዮጵያ የመንፈሳዊ ቴሌቪዥን ሲነሳ የኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ኔትወርክ ተቀዳሚ እና ለብዙዎች ምሳሌ ነዉ።

በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን አንጋፋ እና ወጣት የወንጌል አገልጋዮች እንዲሁም አብያተክርስቲያናት ወንጌልን በዚህ የቴሌቪዥን መስኮት መልክታቸውን ለብዙ ሚሊዮኖች አድርሰዋል።

አብያተክርስቲያናት ወንጌል በብዙ መንገድ በአራቱም አቅጣጫ ሲሰሩ ቆይተዋል በብዙ ሺህ የሚደርሱ ነፍሳት ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ሲጨመሩ በመንፈሳዊ ቴሌቪዥን ወንጌል በማድረግ ግንባር ቀደም ሚና ተጫዉቷል ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን።

የቴሌቪዥኑ መስራች እና መሪዎች ፖ/ር አበራ ሀብቴ እና ፖ/ር በለጡ ሀብቴ ለወንጌል አማኙ ፣ ለታዳጊ ወጣቶች ፣ ለመሪዎች እና ለአብያክርስቲያናት ባለውለታዎች ናቸው።

እነዚህ አገልጋዬች ዛሬ የተጋቡበት 32ኛ አመት እያሰቡ ነዉ።

ወደ ጌታ መንግስት ከተጨመሩ 36 አመት ያስቆጠሩ ሲሆን፣ 3 አመት ተኩል በእጮኛምነት፣ 19 አመት በመሉ ጊዜ አብሮ በማገልገል ቆይተዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና #እንኳን አደረሳችሁ እያልን ቀሪ የአገልግሎት ዘመናችሁ #መልካም እንዲሆን እንመኛለን።
19👍8👏3🔥1
ኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ 10ኛውን አመታዊ ስብሰባና የወዳጅነት ቀን አካሄደ፡፡

በናዛሪን ኢንተርናሽናል ቤ/ክ በተካሄደው በዚህ አመታዊ የሴሚናሪው ስብሰባ ላይም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የመጡ ተሳታፊዎችም ተገኝተዋል።

በመድረኩም የኪንግደም ፓሽን ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዘካሪያስ እና የሴሚናሪው የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፓ/ር ሰለሞን በንቲ ለታዳሚያ የእንኳን ደህና መጣችው ንግግርም አድርገዋል።

ሚሽን ተኮር የሆነውና በስነ መለኮት ትምህር በርካታ ቦታዎችን ተደራሽ ማድረግ ራዕዩ ያደረገው ሴሚናሪው በአሁኑ ሰዓትም በአማርኛ ፣ እንግሊዝኛ ና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን ጨምሮ በሌሎችም ቋንቋዎች ወንጌልን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም በዕለቱ ተወስቷል።

በዝግጅቱም ቄስ ትዕግስቱ ሞገስ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አማኞች ትኩረታቸውን በወንጌል ስራ ላይ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዶ/ር ዘካሪያስ አዱኛ ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ በሴሚናሪው በተካሄደው አመታዊ ጉባኤ በተቋሙ እየተሰሩ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎች እና በቀጣይ ሊሰሩ የታሰቡ እቅዶች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑንም የገለፁት የሴሚናሪው የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ፓ/ር ሰለሞን በንቲ ናቸው።

በተጨማሪም የናዛሪን ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት መልካሙ እንደተናገሩትም ሴሚናሪው እየሰራ ያለውን በጎ ተግባር በማንሳት ከኪንግደም ፓሽን ሴሚናሪ ጎን እንደሚቆሙም አስታውቀዋል።

ሴሚናሪው በአሁኑ ሰዓት ወንጌል ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ወንጌልን በማድረስ እና የቤ/ክን ተልዕኮ ለማድረስ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተነግሯል።

በመጨረሻም በቦርድ አባልነት ሲያገለግሉ ለነበሩ የስልጣን ሽግግርና በተለያዩ ዘርፎች አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማትም የእውቅና መርሀ ግብርም ተካሄዷል።
4👍3👌1
ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በኤርትራ የታሰሩት 7 የሀይማኖት አባቶች እንዲፈቱ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ክርስቲያን ዴይሊ እንደዘገበው እነዚህ የሀይማኖት አባቶች ከእስር እንዲለቀቁ የሚጠይቅ አለም አቀፍ ዘመቻ ተጀምሯል፡፡

እንደዘገባው ከታሰሩት ውስጥ ሶስቱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ሲሆኑ ከታሰሩ 21 አመት ሆኗቸዋል፡፡

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች የሆኑት ቄስ ገብረመድህን ገብረጊዮርጊስ፣ ዶክተር ፍፁም ገብረንጉስና ቄስ ተክለአብ መንግስትአብ ከተያዙበት ኖቬምበር 19 ቀን 2004 አንስቶ ምንም ክስ እንዳልቀረበባቸው የጠቀሰው ዘገባው እንዲሁም ቄስ ሀይሌ ናይግዚ፣ ፓስተር ሚሊዮን ገብረስላሴ፣ ፓስተር መንግስትአብና ፓስተር ኪዳኔ ከ20 አመታት በላይ በወንጀል ምርመራ ቢሮ ያለምንም ክስ በእስር እየማቀቁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

እነዚህ የሀይማኖት አባቶች እንዲፈቱ በሚጠይቀው አዲስ ዘመቻ መሰረት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም በለንደን በሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲም ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደሚደረግ ያስታወቁት አስተባባሪዎቹ እንዲሁም በፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ዴንማርክ፣ ካናዳና ስዊድን የተለያዩ የተቃውሞና የፀሎት እንቅስቃሴዎች እንደሚከናወኑ ገልፀዋል፡፡

እንደ ኦፕን ዶርስ ጥናት መሰረት 1.6 ሚሊዮን አከባቢ ክርስቲያኖች እንዳሏት የሚገመተው ኤርትራ ለክርስታን አስቸጋሪ ከሆኑ 50 ሀገራት መካከል ባለፉት 5 አመታት ከ4-6ኛ በመሆን እጅግ አስቸጋሪ ከሚባሉት መካከል ተቀምጣለች።
👍65👏4🙏1👌1
በመጋቢ አመሉ ጌታ የተፃፈው "መንፈሳዊ ተዋጊ" የተሰኘው መፅሐፍ ተመረቀ።

መፅሐፉ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አባቶች፣ የአብያተክርስቲያናት መሪዎች፣ አገልጋዮች እንዲሁም የፅሐፊዉ ወዳጆች በተገኙበት በኢቫንጀሊካል ቲዌሎጂካል ኮሌጅ ተመርቋል።

በመረሃግብሩ አርቲስት ቴዎድሮስ በዛብህ እና የቀድሞ የደራሲያን ማሕበር ፕሬዚዳንት ጋሽ ጌታቸው በለጠ የፅሐፊዉን የህይወት ታሪክ በአጭሩ ያቀረቡ ሲሆን ቄስ ሳሙኤል ሀይሉም የመፅሃፉን ዳሰሳ ለታዳሚያን አቅርበዋል።

የመጽሐፋ አርታኢ ወንድም ግርማቸው ሀብቴም የመፅሐፉ አበርክቶት የተደረገላቸውን ባለታሪክ ግለታሪካቸውን ለታዳሚያን አውስቷል።

ይህን ራዕይ ለመደገፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ሁሉ በማመስገን በቀጣይም በህትመት ዙርያ ላይ ያላቸውን ራዕይ ለታዳሚያን ያካፈሉት ደግሞ የመፅሀፊ ፀሀፊ መጋቢ አመሉ ጌታ ናቸዉ።

ለፅሐፊዉ ይህ መፅሀፍ 12ኛ መፅሐፋቸው ሲሆን ከዚህ በፊት እናትና አባታችሁን አክብሩ ፣ አስራት ፣ ቅድመ ጋብቻና ድህረ ጋብቻ ጥበብ ፣ ማስተዋል ፣ ሌጋሲ ፣ መንፈሳዊ ባለስልጣን ፣ ታዳጊ ወጣቶች ጋብቻ ፣ ከብዙ ሞት አዳነኝና ቡራኬ የተሰኙ መፅሀፎችን በተለያዩ ቋንቋዎች ለአንባቢያን ማቅረባቸው ይታወሳል።
7👍1
#በአቡ ዳቢ አቅራቢያ ጥንታዊ የክርስቲያን ቅሪቶች ተገኙ

ሲር ባኒ ያስ በተባለ አቡ ዳቢ አቅራቢያ በምትገኝ ደሴት ላይ የተገኘው ይህ ቅሪት፣ በጭቃ ቡኪት የተሰራ የመስቀል ቅርጽ ነው። ቅርሱ የ1400 ዓመታት ታሪክ እንዳለው ተነግሯል። ግኝቱ ወንጌል ወደ ምስራቅ የአለም ክፍል እንዴት እንደተስፋፋ ፍንጭ ይሰጣል ተብሏል።

ቅሪቱ የተገኘበት አካባቢ ጥንታዊ የአብያተ ክርስቲያን እና ገዳማት ፍርስራሽ ይገኛል። ግኝቱ በአካባቢ እስልምና ከመስፋፋቱ በፊት በአካባቢው ተስፋፍቶ የነበረውን ክርስትና ያሳያል ተብሏል።

ቅሪቱን ያገኙ አርኪዮሎጂስቶች ክርስትና በአካባቢውመኖሩን ብቻ ሳይሆን በስፋት እንደነበረ ያሳያል ብለዋል። ቅርሱ 27 ሳንቲም በ17 ሳንቲም የሆነ እና 2 ሳንቲም ስፋት ያለው እና ይንጠለጠል የነበረ መሆኑን ያሳያል።

በአቡ ዳቢ አካባቢ የነበሩ ክርስቲያኖች ከእየሩሳሌም እስከ ህንድ እና ቻይና የተዘረጋው ክርስትና መሸጋገሪያ ነጥብ መሆናቸውን ያሳያል ተብሏል። የገዳማቱ ሁኔታ በአካባቢው ክርስቲያኖች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች በሰላም ይኖሩ እንደነበረም ያሳያል ተብሏል። ስፍራው ወንጌል ከአረብ ባህረ ሰላጤ በኩል አድርጎ ወደ እስያ ለመስፋፋቱ መነሻ ስፍራ ነበረ ተብሏል።

በአካባቢው በ1990ዎቹ የክርስትና እምነት ቅሪቶች መገኘት የጀመሩ ሲሆን፣ በ2022 በዚያው አቡ ዳቢ አካባቢ፣ ኡም አል ቁዋይን በተባለ አካባቢ ጥንታዊ ገዳማት መገኘታቸው ይታወሳል። ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ገዳማት በኩዌት፣ ኢራን እና ሳውዲ አረቢያ ተገኝተዋል። Christianity today እና The National እንዳስነበቡት

በኦቦሌሳ አዶላ
🔥6👍21👏1