The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ነፃ የዓይን ህክምና

በፕሮፌሰር ሞሪስ ሃሽታን የሚመራው የእስራኤል የዓይን ህክምና ቡድን ከ#1600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነፃ የዓይን ህክምና ሰጠ።

የህክምና ቡድኑ በመቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ፣ በማዘር ቴሬሳ፣ በህይወት ማዕከል፣ በደብረብርሃን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለአይሁድ ማህበረሰብ ህፃናት ፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን ህክምናውን ሰጥቷል።

ከዓይን ምርመራ እስከ ዓይን ቀዶጥገና ያካተተው ህክምና የዓይን ጠብታዎች፣ መነፅሮችና ለዓይነ ስውራን ደግሞ ነጭ በትሮች ለግሰዋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል  አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ይህ በጎ ስራ የእስራኤል እና የኢትዮጵያ ሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር አንዱ ማሳያ ነው።

በተለያዮ ዘርፎች የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
👍41🔥1🙏1👌1
የሰሜን ምስራቅ የቃለ #እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በደሴ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ከአንፆኪያ - ኬሚሴ ጀምሮ እስከ አላማጣ — ኮረም ድረስ ከሚገኙ 25 ከተሞች የመጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት ጉባኤ ዋና ትኩረት የሆነው የዘፍጥረት መጽሐፍ አሳታፊ በሆነ መንገድ የተጠና ሲሆን በቆይታችን፣ ፌሎሽፕ (school fellowship) መመስረት እና ማጠናከር ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የጉባኤው ተሣታፊ ተማሪዎች፣ የቤተሰብ ቡድን አገልግሎት ስልት እና አገልጋይ መሪነት በሚሉ አርእስቶች ላይ ጠቃሚ ሴሚናር ወስደዋል።

ተማሪዎች የመጡባቸው ከተሞች በወንጌል ያልተደረሱ ሲሆኑ በአንድ 2ደረጃ ትምህርት ቤት 1 ክርስቲያን ተማሪ ብቻ ያለባቸው ከተሞች ጭምር እንደሚገኙ በመድረኩ ተጠቅሷል። ተሣታፊ አካባቢያዊ ሁኔታቸውን ያገናዘበ ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር መንገድ (መፀለይ-መንከባከብ-ማካፈል) እና አለም አቀፍ የእግዚአብሔር ራዕይ የሚሉ ስልጠናዎችንም ወስደዋል።

በአራት ቀን ቆይታችን፣ ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች እና ከየቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር አሶሼት ስታፎች ጋር የውይይትና የአብሮነት ጊዜ አሳልፈናል።

ሰሜን ምስራቅ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልል ብዙ ፀሎት የሚያስፈልገው እንደሆነ እና አማኞች እንዲበረቱ ፤ በአካባቢው እያገለገሉ ለሚገኙ ቅዱሳን የወንጌል እሣት በተማሪዎች መካከል እንዲቀጣጠል እንዲጸለይ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
7👍2👌1
እሁድ በማዕከላዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ 38 ክርስቲያኖች ተገደሉ

እሁድ ማለዳ በአምልኮ ላይ የነበሩ ክርስቲያኖች የካቶሊክ ቤ/ክ ውስጥ ነው በISIS የሚደገፈው የተባበሩት ዴሞክራቲክ ሃይል (Allied Democratic Forces) አማካኝነት የተገደሉት። የቫቲካን ዜና እንዳሳወቀው፣ ቤተ ክርስቲያኗ በሃገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ኮማንዳ አካባቢ፣ የተባረከች አኗሪቴ ትባላለች።

ADF በ1990 በዩጋንዳ የተመሰረተ ሲሆን አሁን በዋናነት በማዕከላዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚንቀሳቀስና በISIS የሚደገፍ ነው። ከISIS ጋር አብሮ መስራቱን በ2019 ይፋ ያደረገ ስሲሆን፣ የእሁዱን ጥቃት ISIS ሃላፊነት ወስዷል።

የቫቲካን ዜና እንዳስነበበው አዲሱ የካቶሊክ ቤ/ክ ጳጳስ አባ ሊዮ 14ኛ በጥቃቱ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ADF በየካቲት ወር 70 ክርስቲያኖችን በሰሜን ኪቩ ግዛት መግደሉ ይታወሳል።
ክርስቲያን ፖስት እንዳስነበበው

በኦቦሌሳ አዶላ
3🔥2👍1🙏1
በሀገራዊ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ሁሉም የወንጌል አማኞች ምዕመናን በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ።

#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ባስተላለፉት መልዕክት እግዚአብሔር ሰውን በኤደን ገነት ያስቀመጠው አንድም እንዲያበጅ አንድም እንዲጠብቅ ነው ብለዋል።

የወንጌል አማኞች ከ100 አመታት በላይ በሃገራችን ማህበራዊ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ያስታወሱት ቄስ ደረጀ አንድ ተክል መትከል ማለት ለመጪው ትውልድ አሻራችንን ማስቀመጣችን መሆኑን በማሰብ መላው የወንጌል አማኞች ካውንስል አባላት እና ምዕመናን በሙሉ ወጥተን አሻራችንን እንድናሳርፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ 📸 ፋይል
18👍4🔥1
#አፋልጉን!

የWSG ንብረት የሆነው AA ኮድ- 5-01526
#ነጭ_ሚኒባስ_መኪና ቤሌር (ሕንድ ኤምባሲ) መግቢያ አካባቢ ከቆመበት እሁድ ሐምሌ 27 ምሽት ላይ #ተሰርቆብናል

እባክዎ
#በፀሎት ይደግፋን
#በፍለጋ ይተባበሩን
#በማህበራዊ_ገፅዎ_ያጋሩልን

+251913307297
+251929917573
+251911617261
+251910078659

ይደውሉልን
👍63🙏1
"#እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ" ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ ከደቡብ አፍሪካ

የደቡብ አፍሪካ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ጥሪ አቅርቧል።

የወንጌል አብሳሪዎች አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በጁሃንስበርግ መሪ እና የካውንስሉ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ እንደገለጹት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን #እና ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ ቡድኖች ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጸው ነገሮች እንዲስተካከሉ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ ብለዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ በመልዕክታቸው በአሁኑ ሰዓት ዱዱላ የተባለ ቡድን ስደተኞችን የማይገቡ ዶክመንቶችን በመጠየቅ እያሰቸገረ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም እዛው የተወለዱ እና ያደጉ #ልጆች ሲማሩም ይሁን ትምህርት ተምረውም ከጨረሱ በኋላ ስራ ለማግኘት በመቸገር ከፍተኛ ስንለቦናዊ ጫና እያደረባቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እግዚአብሔርን አምነን ፊታችንን ወደ እርሱ በማድረግ ያለውን ችግር በእርሱ ፊት እንቅረብ በማለት በፈረንጆቹ ኦገስት 5-7 / 2025 ወይም ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም ድረስ በጾም እና ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጸሎት እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሐንስ ግርማ
👍108🙏3🕊1
የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቀረበ።

ከሰሞኑ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ
በተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች ቤት ውስጥ ጎርፍ በመግባት ንብረቶች መበላሽት እና ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

ሁኔታውን አስመልክቶ የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቅርቧል።

ጥሪዉን ያቀረቡት የሕብረቱ ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ብሩክ ከበደ በከተማዋ በጣለው ንፈስ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ላይ እና በህብረታችን በታቀፋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ በደረሰው የንብረት ውድመት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እገልፃለሁ ብለዋል።

መጋቢ ብሩክ አክለዉ ቅዱሳን የወንድም የእህት መኖርያ ቤቶችን እንዲሁም የአጥቢያ ቤተክርስቲያናትን መሰብሰቢያ አዳራሾች መልሶ ለመስራት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ሁሉ በማድረግ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ እርስ በእርስ በመተጋገዝ አብረን እንቁም የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

እስካሁን ከአከባቢዉ በወጣዉ ዘገባ አንድ የቤተሰባችን አባል በዝናቡ ምክንያት የቤታቸው ጣራ መነሳቱን ፤ ሌላኛው አባል ደግሞ ቤታቸው በጎርፍ መጥለቅለቁን ቲክቫ ኢትዮጵያ መዘገቡ ይታወሳል።

Photo - Bayew Atiye & Social Media
10👍5👌1😭1
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ያወጀችው የጽዕም ጸሎት #ነገ ይጀምራል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም ባወጣችው የጽሁፍ መግለጫ መሠረት ሀገራችን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሰላምና ጸሎት ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል።

በመግለጫው መሠረትም ለቤተክርስቲያኒቱ አባላት፣ አገልጋዮችና መሪዎች ከነሃሴ 1 እስከ 11/2017 ዓ.ም ድረስ ስለምድራችን #ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ፊት በጾምና በጸሎት እንድንፈልግ ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።

“እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገስታትና ለባለስልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው”። 1ኛ ጢሞ. 2፥1-2 (አ.መ.ት)
11👍2🕊1
የሆሳዕና እናት ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ወጣቶች በለምቡዳ ተራራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዷል።

‎የሆሳዕና እናት ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት መሪ አቶ ናትናኤል አበራ እንደገለፁት ችግኝ መትከል የመንግስት ዓላማን ከመደገፍ በተጨማሪም የልማት ተግባራትን መከናወን ከሀይማኖት ተቋማት ተልዕኮ አንዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎ቤተክርስቲያኒቱ ከዚህ ቀደም በርካታ የልማት ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ጠቁመው ይህም የችግኝ ተከላ ለ7ኛ ዙር መሆኑን አንስተዋል።

‎በዛሬው ዕለትም የቤተክርስቲያን ወጣቶችን በማሳተፍ ከ2 ሺህ 500 በላይ የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን ተናግረው የተተከሉ ችግኞችን እንክብካቤ እንደሚያደርጉም አቶ ናትናኤል ተናግረዋል።

‎የሌሞ ወረዳ ደንና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት የደን ልማት ብድን መሪ አቶ ተፈራ ኤረንጎ ምድርን መጠበቀና መንከባከብ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መሆኑና በጎ ተግባር እንደሆነም ተናግረዋል።

የተተከሉ ችግኞች ለውበት፣ ለጥላ፣ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ የሚውሉ መሆናቸው ጠቁመው ይህንን የመንግስት ራዕይ ወጣቱ በቀጣይነት ማስቀጠል ይገባል ብለዋል ።

‎የቤተክርስቲያኑ የወጣቶች መሪ አቶ ዳዊት ወልደ ዮሐንስ በበኩላቸው ‎ከመንፈሳዊ አገልግሎት ጎን ለጎን ምድርን መጠበቅና መንከባከብ ከአባቶች የተረከብነው አደራ ነው ብለዋል።

‎ቀደሚ ሲል ‎ቤተክርስቲያኒቱ አቅመ ደካሞችን በመርዳት፣ በከተማ ጽዳትና ሌሎች የልማት ስራዎችን መከናወኑን ጠቁመው ሌሎች ሀይማኖት ተቋማት በዚህ የልማት ስራ ላይ እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

‎የለሙቡዳ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሰብሳቢ አቶ ሰላሙ በቀለ በበኩላቸው ችግኝ መትከል የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረው የተተከሉ ችግኞችን አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
4👍4🔥2👏1
የአርጀንቲና ወንጌል አማኞች ህጋዊ እውቅና አገኙ

በሃገሪቱ ህግ መሰረት ከካቶሊክ በስተቀር ለማንኛውም ሃይማኖት እውቅና አይሰጥም። የሃቪየር ሚሌ መንግስት ካቶሊክ ያልሆነ ምንግስትን ለመጀመሪያ ጊዜ እውቅና ሰጥቷል።

በማህበርነት ስም ሲመዘገብ ለቆየ የወንጌላዊያን እምነት ተከታይ ዛሬ ህጋዊ ሰውነት ማግኘት ትልቅ የምስራች ነው። ላለፉት 30 አመታት ይህግ ባለሙያዎች፡ የወንጌላዊያን ማህበራት እና አብያተ ክርስቲያናት በተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያቀርቡ ነበረ።

እውቅናውን የሃገሪቱ ፍትህ ሚኒስቴር ፈርሞ አጽድቆታል። የአርጀንቲና ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ጥምረት ውሳኔው የእምነት እኩልነትን ያረጋገጠ፡ የሃይማኖት ነጻነትን ያረጋገጠ እና የወንጌላዊያንን ጥንካሬ ያረጋገጠ ነው ብሎታል።

የህጋዊ እውቅና ጉዳዩ ከልታወቅ ባለፈ ክርስቲያኖች ወንጌልን በነጻነት መስበክ የሚያስችል እርምጃ ነው። የወንጌላዊያን ቁጥር በ2008 ከነበረበት የ8% በ2018 ወደ 15% አድጓል። ይሄ ወንጌል በአካባቢው ምን ያክል እየተስፋፋ እንደሚገኝ የሚያሳይ ነው።

በኦቦሌሳ አዶላ

Evangelical Focus እንዳስነበበው።
👍1410🔥3🥰1👏1
የተስፋ ብርሀን ምገባ ማዕከላት ተጠቃሚዎችን ለማገዝ 250 ሺህ ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

ብራይት ስታር ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን እና ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ ከአዲስ አበባ ሴቶች እና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ 10 የተስፋ ብርሀን የምገባ ማዕከላት ተጠቃሚ ለነበሩ ሴቶች ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፉ ለእያንዳንዳቸው የ25 ሺህ የብር ግምት ያለው የመስሪያ እቃዎችና ግብአት (የአንጀራ መጋገሪያ ምጣድ እና የችብስ መጥበሻ) እንዲሁም ስራ ማስጀመሪያ መቋቋሚያ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ያካተተ በአጠቃላይ ግምቱ 250 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ አቋቁሟል።

በዚህ መርኃ ግብር የብራይት ስታር ድርጅት ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ግዛቸው አይካ፣ የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ሶፊያ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላን ጨምሮ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

የድጋፍ ርክክቡ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ ተጠቃሚዎች በፍላጎታቸው መሠረት የተደረገላቸው መነሻ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ድጋፍን ተጠቅመው ጠንክረው በመስራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ከተረጂነት በማላቀቅ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ በማሳሰብ ቢሮውም በመዋቅሩ አማካኝነት ክትትልና ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

በመጨረሻም ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በማመስገን አሁንም በጊዜያዊ ማህበራዊ ችግር ውስጥ ሆነው መቋቋም የሚፈልጉ ነዋሪዎችን ለማገዝ አቅሙ ያላቸው ድርጅቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ቢሮው በጋራ ለመስራት ዝግጁ ስለመሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
👍31
በፕሪሚየር ሊጉ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ምልክት/አርማ በተጨዋቾች የጫማ ክር እና የአምበሎች አርማ ላይ መደረግ ይቆማል።

በቀጣዩ አመት #የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በብዙዎች የሚወገዘዉ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ምልክት/አርማ በተጨዋቾች የጫማ ክር እና የአምበሎች አርማ ላይ መደረግ እንደሚቆም ተሰምቷል።

ፕሪሚየር ሊግ ለ 13 አመታት በዚህ ተግባር ላይ ከሚሰራ ተቋም ጋር የነበረዉ የስፖንሰርሺፕ ዉል ጊዜዉን ጨርሷል ተብሏል። የሁሉም ቡድን አምበሎች በተገኙበት በተደረገ ስብሰባ አርማዉ መደረጉ ከድጋፍ ይልቅ ተቃዉሞ እየታየበት ነዉ ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የእግር ኳስ ተመልካቾች የሚያዉቁትን አርማ ተጨዋቾች የማይጠቀሙት ይሆናል። ሆኖም ፕሪሚየር ሊጉ በራሱ የሊጉ አርማ ላይ ምልክቱን እንደሚጠቀም ተዘግቧል። ሊጉ የራሱን "የግንዛቤ ማስጨበጫ" ሲል የጠራዉን ዘመቻ እንደሚሰራም ገልጿል።

በባለፈዉ አመት የክሪስታል ፓላሱ አምበል ማርክ ጌሂ በአርማዉ ላይ "ኢየሱስን እወዳለሁ። ኢየሱስም ይወዳችኋል" ሲል በመጻፍ ተጨዋቹ የእምነቱን ህግጋት እንደሚያከብር ተናግሯል።

በተጨማሪም የኢፕስዊች ታዉን አምበሉ እና የእስልምና እምነት ተከታዩ ሳም ሙሪ አርማዉን አልጠቀምም ማለቱ አይዘነጋም። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አርማ በፕሪሚየር ሊጉ ላይ መጠቀም ሲጀመር የቴሌቪዥን ስርጭታቸውን የሚያቋርጡ ሀገራት እንዳሉም ይታወቃል።

ይህ ተግባር ለአመታት ተቃዉሞ ሲቀርብበት የነበረ ነዉ።
በረከት ሞገስ ለዳጉ ጆርናል እንደዘገበው።
15👍3👏3👌1
“በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል” መጽሐፍ በሀዋሳ ከተማ በይፋ ተመረቀ።

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ “በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል” በሚል ርዕስ የተጻፈው መጽሐፍ #ዛሬ ነሐሴ 4/2017 ዓ.ም በሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን በይፋ ተመረቀ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ በመፅሐፍ ምረቃው ላይ ተገኝተው መጋቢ ፃዲቁ አብዶ ትውልድን ሊያስተምር የሚችል መፅሐፍ መፃፋቸውን በመጥቀስ በቀል በቀለኛን የሚያጠፋ በመሆኑ ትውልድ ከበቀል በመውጣት በይቅርታና በፍቅር መኖር እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ በበኩላቸው ከባለቤታቸው ሰላማዊት ቡርቂቱ ጋር በመሆን መፅሐፉን በተመለከተ ንግግር አድርገዋል።

በመጽሐፍ ምረቃው ፕሮግራም ላይ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ ማርሻዬ፤ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ሰንበቶ በሼን ጨምሮ የሲዳማ ክልል እና የሀዋሳ ከተማ ወንጌውያን አማኞች ካውንስልና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

መጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ በዝማሬና በእግዚአብሔር ቃል ያገለገሉ ሲሆን የሲዳማ ክልል የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስያናት ካውንስል እና የወንጌላውያን አብያተክርስትያናት ህብረት የቦርድ ሰብሳቢዎች፤ የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን መጋቢዎች በአንድነት በመሆን የመፅሐፍ ሪቫን በመቁረጥ የመፅሐፉን መመረቅ በይፋ አብስረዋል።

ምንጭ @የሀዋሳ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚዲያ አገልግሎት
5👍2👏1
ተመዝግበሻል?

እኛ ሚስቶች እንደብልኋ ሴት ቤታችንን በእጆቻችን የምንሰራበትን ጥበቦች ልንሸምት፣ ማስተዋሎችን ልንካፈልና እውቀቶችን ልንገበይ ቀናቶችን ቀጥረናል።

2ኛው ዙር  ዕንቁ ልብ የሚስቶች ት/ቤት ምዝገባ ተጀምሯል ‼️

📍በሰሊሆም የተላከ ትውልድ ቤተ-ክርስቲያን

🗓ከነሐሴ 12-23 አስር የሥራ ቀናት

⌚️ከጠዋቱ 2:30-6:30

አሰልጣኞች ፦
1. ዘለቃ በቀለ (ቃቁ)
2. ወንጌላዊት መዓዛ በቀለ
3. መጋቢ ምዕልተፀጋ ገ/መድህን (ዶ/ር)
4. እህት ዘነበች እርዳ
5. እህት ሳሮን ውድነህ

👉አድራሻ ፦ ከስታድየም ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ጠመንጃ ያዥ ኖክ ማደያ ሳይደርስ ኦሮሚያ ባንክ ያለበት 3ኛ ፎቅ

🖊ለመመዝገብ ፦ በ0911136520/0946693468 ይደውሉ!

💯 ለውጥ ይሆንልሻል‼️


ከ1ኛ ዙር ተሳታፊዎች የተሰጠ ምስክርነት 👇
https://youtu.be/R0xrbvtxH58?si=mxOUGROh3VPDgzGB

ለበለጠ መረጃ ይህን ግሩፕ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
4👍2🔥1🙏1
#እንደ ሃገር ምን ያክል የምንጸልይ እንሆን?

ሰሞኑን የትኛዎቹ ሃገራት ምን ያክል ይጸልያሉ የሚል ጥናታዊ ግኝት ይፋ ተደርጓል።

ቪዥዋል ካፒታሊስት የተሰኘ ድህረ ገጽ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በፈረንጆቹ 2025 የ35 ሃገራትን የጸሎት መረጃ ይፋ አድርጓል። ኢንዶኔዥያ ከ269 ሚሊዮን ህዝቧ 95% ቢያንስ በየቀኑ እንደሚጸልዩ ይፋ አድርጓል።

በተለይ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢኮኖሚ ያላቸው ሃገራት ደረጃውን የሚመሩት ሲሆን፣ ምዕራባዊያን እና ባለ ትልቅ ኢኮኖሚ ሃገራት ደግሞ በሰንጠረዡ እግርጌ ይገኛሉ።

• ኢንዶኔዥያ ከ269 ሚሊዮን ህዝቧ 95 ሚሊዮን ህዝቧ በየእለቱ ይጸልያል።
• ኬኒያ ከ47.4 እና ናይጄሪያ ከ195.5 ሚሊዮን ህዝቧ 84 በመቶ በመጸለይ ሁለተኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
• ሃንጋሪ ከ1.1 ሚሊዮን ህዝቧ 11 በመቶ እና ስዊድን ከ8 መቶ ሺህ ህዝቧ 8 በመቶ ብቻ በመጸለይ በደረጃው እግርጌ ይገኛል።
• በህንድ ከ1 ቢሊዮን በላይ ህዝብ ወይም 71% ህዝብ ይጸልያል።
• ከአሜሪካ ህዝብ 149 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ወይም 44 በመቶ ህዝብ በየቀኑ ይጸልያል።

ፒው ሪሰርች ማዕከል ከአለም ባንክ ባገኘው መረጃ ባደረገው ምርመራ አማካኝነት ባደረገው ጥናት ነው ይሄንን ውጤት ይፋ ያደረገው። 35ቱ ሃገራት የአለምን ግማሽ ህዝብ ያክላሉ ይበል እንጂ እንደ ቻይና ያሉ ግዙፍ ቁጥር ያላቸው ሃገራት መረጃ ማግኘት አለመቻሉን ይፋ ተደርጓል።

የክርስትና እና እስልምና እምነት የሚበዛባቸው ሃገራት በሰንጠረዡ ከላይ ሲቀመጡ፣ ሴኩላር እና በኢኮኖሚ የበለጸጉ የሚባሉት ሃገራት ደግሞ ከታች ተቀምጠዋል። ግኝቱ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ ይፋ ያደረገው መረጃ የለም።

እናንተስ ከ132 ሚሊዮን ህዝባችን ምን ያክል % በየቀኑ ይጸልያል ትላላችሁ? ኮሜንት ላይ አስቀምጡልን

በኦቦሌሳ አዶላ
6🤔3👏1🙏1