The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
እዩ ጩፋ ካውንስሉን ይቅርታ ጠየቀ

የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በቅርቡ በሚዲያ ላይ እንደሰማችሁት ለተፈጠሩት ክፍተቶች ከካውንስሉ የስነ መለኮት ኮሚሽን እና የህግ ኮሚሽን ጋር ዉይይት ካደረገን በኋላ ቤተክርስቲያናችን በጉዳዩ ላይ ስንፀልይና ስንመካከር ቆይተን የደረስንበትን ስምምነት እንደሚከተለው እናቀርባለን።

ካውንስሉን እና የካውንስል አመራሮች በተመለከተ በቴሌቭዥን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ለተጠቀምናቸው ያልተገባ ቃላት ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ከዚህ ቀን ጀምሮ ካውንስሉን ከሚመሩ መሪዎቻችን ጋር በቅርበት እየተነጋገርን እንደ አባት እና ልጅ ተቀራርበን የክርስቶስን ወንጌል መንፈሳዊ ጨዋነት ተከትለን ቀዳሚዎቻችንን አክብረን ለማገልገል የተስማማን መሆኑን እየገለፅን ካውንስሉም ይቅርታችንን ተቀብሎ አባታዊ በሆነ መንገድ እየመከረን እና እያስተማረን እንዲመራን በመተማመን ይህንን መግለጫ እንደ ቤተክርስቲያን አውጥተናል።
👍34👏12🤣106🔥2👌1
አታዋሌ - “Let Jesus Reign”

#ኢየሱስ #ይንገስ ወይም #“Let Jesus Reign” በሚል መሪ ቃል በሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤ/ክ የወጣቶች ኮንፈራንስ ተካሄደ። ፕሮግራሙ በአታዋሌ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ እና ፒስ ጌት ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ በጋራ የተዘጋጀ ነው።

ፕሮግራሙ በተለይ ወጣት አገልጋዮችን ማስታጠቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ ሜንቶሪንግ፣ ተተኪ መሪዎች ማፍራት፣ አውዳዊ የወንጌል ስርጭት እና ድንበር ዘለል የወንጌል ስርጭት በኮንፈረንሱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።

የኮንፈራንሱ መሪ ቃል “Let Jesus Reign” ወይም ኢየሱስ ይንገስ በሁሉም ነገር ላይ ኢየሱስ ብቻ መንገስት አለበት የሚለውን ሃሳብ ከፍ አድርጎ ለማሳየት የታሰበ መሆኑን የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም #ሳሙኤል በላይነህ ለክርስቲያን ዜና ተናግረዋል።

በፕሮግራም እንዲያስተምሩ የተጋበዙት የአታዋሌ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ መሪ ፓስተር #ራምጃኒ ጆሽዋ እና በአለም አቀፍ የተማሪዎች አገልግሎት ሪጅናል ዳሬክተር ወንድም #ዘላለም አበበ ናቸው። ተናጋሪዎቹ በትምህርቱ ነገ ወጥቶ ከድንበሩ ያለፈ ወንጌል ሰባኪ እና ከፊቱ ሰው ያለ እና ከኋላውም የሚረከበው እንዲሁም የሚያማክረው ሰው መኖር አገልግሎት አስፈላጊነት ዙሪያ አስተምረዋል።

የፒስ ጌት ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ ዳይሬክተር ወንድም ሳሙኤል በላይነህ፣ የኮንፈራንሱ ተሳታፊዎች የተፈጠሩበትን አላማ ማወቅ እና ለአላማቸው መኖርን ከዚህ ሰንቀው መውጣትን እና አላማቸውን ደግሞ በሚገባ መኖርን ከእነርሱ እንጠብቃለን ብለዋል።

#“አታዋሌ” የስዋህሊ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ኢየሱስ ይንገስ ማለት ነው።
9👍1🔥1👌1
#የአደባባይ ስብከት እግድ

የለንደን ከተማ ምክር ቤት የአደባባይ ላይ የጣለው ስብከት እግድን አነሳ።

በለንደን ከተማ መሃል ላይ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ የአደባባይ ላይ ስብከት እና ሃይማኖታዊ ህትመቶችን መበተን ተከልክሎ ነበረ። በሰሜን ምዕራብ ለንደን የምትገኝ አንዲት #ቤተ ክርስቲያን የከተማውን ምክር ቤት በወርሃ ነሃሴ 2023 አውጥቶ የነበረው እግድ እንዲያነሳ አድርጋለች።

እግዱ በአደባባይ ወንጌል ሲሰብክ የተገኘ ሰው እስከ 100 ፓውንድ ይቀጣል የሚል ውሳኔ ነበረው። ክርስቲያኖች በፖሊስ እርምጃ ይወሰድባችኋል የሚል ማስፈራራት ቀርቦባቸው እንደነበረ ተዘግቧል።

ቤተ ክርስቲያኗን የወከለው የክርስቲያን ህግ ማዕከል (Christian Legal Centre) ነው። ሂሊንግዶን የተባለው ምክር ቤት ውሳኔውን መቀልበሱን እና ቤተ ክርስቲያኗ ለህግ ጉዳዮች ያወጣችውን ወጪዎች እንደሚሸፍን ገልጿል።

ህጉ የመናገር ነጻነት ላይ አደጋ ደቅኖ የነበረ መሆኑን በማንሳት አሁን የተወሰነው ውሳኔ እፎይታን እንዳመታ የክርስቲያን ህግ ማዕከል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። #በአደባባይ ወንጌል መስበክ ጸረ - ማህበራዊ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ በ2009 ነጻ የምገባ ማዕከል ከፍታ የነበረ ሲሆን፣ የአርሰናሉ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ የሚያመልክባት ናት። የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ፓስተር ቱንዴ ባሎጉን፣ ክርክሩን ስንጀምር በእግዚአብሔር ላይ እርግጠኞች ነበርን ብለዋል።

ኢንግሊዝ እነ ጆን ዌስሊ እና ቻርለስ ስፐርጅንን የመሳሰሉ ሃያል ወንጌላዊያን የወጡባት ሃገር መሆኗ ይታወሳል።

ፕሪሚየም ክርስቲያን ኒውስ እንዳስነበበው
በኦቦሌሳ አዶላ
🔥1813👍4👏1🙏1
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጋምቤላ ወረዳ ፑኮንግ ቀበሌ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉን ያበረከቱት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ላኮ በዳሶ እንደገለፁት በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች መደገፍና መንከባከብ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የድርሻዋን እየተወጣች እንደምትገኝም ፕሬዝደንቱ አክለው ገልፀዋል።

በአከባቢው ያለውን ለም መሬትና የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ከተረጅነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ያነሱት ፓስተር ላኮ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የእርሻ መሳሪያ ቁሳቁስ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የጋምቤላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡማን ኡሞድ በበኩላቸው ቤ/ክ ያለውን ችግር በመመልከት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ከድህነት ለመላቀቅ ብቸኛ አማራጭ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅመን ማልማት ስንችል ነው" ለዚህም ለተግባራዊነቱ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በጋምቤላ ቁጥር 3 ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ መጋቢ የሆኑት ፓ/ር ወንድወሰን መሀመድ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኗን አንስተዋል።

የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት የአንድ አካል ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም በችግር ላይ ያሉ ዜጎችን በመርዳትና በመንከባከብ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅበት አንስተዋል።

በዕለቱ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ባልዲ፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ሳሙናና የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።
10👍3👏2🙏2🔥1
#ወንድማገኝ ኡዴሳ ቄስ ሆነው ተሾሙ

መካነኢየሱስ 31 አገልጋዮችን በቅስና አገልግሎት ሾመች።

በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ የአዶላ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ በነበረው የቅስና አገልግሎት ምደባ ስነ ስርዓት፣ ቀሳውስቱ በቃል እና ቅዱሳት ሚስጥራት እንዲያገለግሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር #ዮናስ ይገዙ ሃላፊነቱን ሰጥተዋል።

የቤተክርስቲያኒቱም የወንጌል እና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ለእጩ ቀሳውስቱና ለምዕመናን የማበረታቻ ቃል አስተላልፈዋል።

በቤተ ክርስቲያኗ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ሃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ወንድማገኝ ኡዴሳ በቅስና አግልግሎት ከተሾሙት መካከልናቸው። #ቄስ ወንድማገኝ የክርስቲያን ዜና መልካም የአገልግሎት ዘመን ይመኛል።

ምንጭ፡
Facebook EECMY
3👍1
የኢትዮጵያ የስነ መለኮት ድህረ ምረቃ ት/ቤት (EGST) ለ25ተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ት/ቤቱ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን 80 ተማሪዎች የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኣብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዘዳንት መጋቢ ፃድቁ አብዶን ጨምሮ ጥሩ የተደረገላቸው መሪዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በተቋሙ አዳራሽ አስመርቋል።

ኤገስት የድህረ ምረቃ የስነ መለኮት ትምህርት ቤት በተለያዩ ዘርፎች ተማሪዎችን በማስተማር ብቁ እና ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ እያፈራ ያለ ተቋም መሆኑንም በዕለቱ ተወስቷል።

በምረቃ መረሃ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት የት/ቤቱ ፕሬዘዳንት ዶክተር ወርቁ ሀይለማሪያም እና በክብር እንግዶች አማካኝነት ለተመራቂዎቹ ተበርክቷል።

ምንጭ GMM TV
3👍2👌1
#መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የሰላም ጥሪ

ቤተ ክርስቲያኗ ለፌደራል መንግስት እና ትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ነው የሰላም ጥሪ ያስተላለፈችው።

አመሻሹን ይፋ ባደረገችው ፕሬስ ሪሊዝ፡
ሁለቱም አካላት የጦር ወሬ እንዲተዉ፡ ለአለም አቀፍ ማህበር ሰብ፡ ሃላፊነት የሚሰማው ሚድያ እና ቤተ ክርስቲያኗ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት በፕሬሱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።

አሁን የመከፋፈል ጊዜ፡ ሳይሆን የቆራጥ መሪነት፡ ትህትና የተሞላበት ንግግር እና ለሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላም በጋራ የምንሰራበት ይሁን ይላል።

ምንጭ፡ ቴሌግራም MKC Official
👏64🕊1💯1
#ነፃ የዓይን ህክምና

በፕሮፌሰር ሞሪስ ሃሽታን የሚመራው የእስራኤል የዓይን ህክምና ቡድን ከ#1600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነፃ የዓይን ህክምና ሰጠ።

የህክምና ቡድኑ በመቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ፣ በማዘር ቴሬሳ፣ በህይወት ማዕከል፣ በደብረብርሃን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለአይሁድ ማህበረሰብ ህፃናት ፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን ህክምናውን ሰጥቷል።

ከዓይን ምርመራ እስከ ዓይን ቀዶጥገና ያካተተው ህክምና የዓይን ጠብታዎች፣ መነፅሮችና ለዓይነ ስውራን ደግሞ ነጭ በትሮች ለግሰዋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል  አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ይህ በጎ ስራ የእስራኤል እና የኢትዮጵያ ሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር አንዱ ማሳያ ነው።

በተለያዮ ዘርፎች የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
👍41🔥1🙏1👌1
የሰሜን ምስራቅ የቃለ #እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በደሴ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ከአንፆኪያ - ኬሚሴ ጀምሮ እስከ አላማጣ — ኮረም ድረስ ከሚገኙ 25 ከተሞች የመጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት ጉባኤ ዋና ትኩረት የሆነው የዘፍጥረት መጽሐፍ አሳታፊ በሆነ መንገድ የተጠና ሲሆን በቆይታችን፣ ፌሎሽፕ (school fellowship) መመስረት እና ማጠናከር ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የጉባኤው ተሣታፊ ተማሪዎች፣ የቤተሰብ ቡድን አገልግሎት ስልት እና አገልጋይ መሪነት በሚሉ አርእስቶች ላይ ጠቃሚ ሴሚናር ወስደዋል።

ተማሪዎች የመጡባቸው ከተሞች በወንጌል ያልተደረሱ ሲሆኑ በአንድ 2ደረጃ ትምህርት ቤት 1 ክርስቲያን ተማሪ ብቻ ያለባቸው ከተሞች ጭምር እንደሚገኙ በመድረኩ ተጠቅሷል። ተሣታፊ አካባቢያዊ ሁኔታቸውን ያገናዘበ ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር መንገድ (መፀለይ-መንከባከብ-ማካፈል) እና አለም አቀፍ የእግዚአብሔር ራዕይ የሚሉ ስልጠናዎችንም ወስደዋል።

በአራት ቀን ቆይታችን፣ ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች እና ከየቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር አሶሼት ስታፎች ጋር የውይይትና የአብሮነት ጊዜ አሳልፈናል።

ሰሜን ምስራቅ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልል ብዙ ፀሎት የሚያስፈልገው እንደሆነ እና አማኞች እንዲበረቱ ፤ በአካባቢው እያገለገሉ ለሚገኙ ቅዱሳን የወንጌል እሣት በተማሪዎች መካከል እንዲቀጣጠል እንዲጸለይ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
7👍2👌1
እሁድ በማዕከላዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ 38 ክርስቲያኖች ተገደሉ

እሁድ ማለዳ በአምልኮ ላይ የነበሩ ክርስቲያኖች የካቶሊክ ቤ/ክ ውስጥ ነው በISIS የሚደገፈው የተባበሩት ዴሞክራቲክ ሃይል (Allied Democratic Forces) አማካኝነት የተገደሉት። የቫቲካን ዜና እንዳሳወቀው፣ ቤተ ክርስቲያኗ በሃገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ኮማንዳ አካባቢ፣ የተባረከች አኗሪቴ ትባላለች።

ADF በ1990 በዩጋንዳ የተመሰረተ ሲሆን አሁን በዋናነት በማዕከላዊ ዴሞክራቲክ ኮንጎ የሚንቀሳቀስና በISIS የሚደገፍ ነው። ከISIS ጋር አብሮ መስራቱን በ2019 ይፋ ያደረገ ስሲሆን፣ የእሁዱን ጥቃት ISIS ሃላፊነት ወስዷል።

የቫቲካን ዜና እንዳስነበበው አዲሱ የካቶሊክ ቤ/ክ ጳጳስ አባ ሊዮ 14ኛ በጥቃቱ ማዘናቸውን ገልጸዋል። ADF በየካቲት ወር 70 ክርስቲያኖችን በሰሜን ኪቩ ግዛት መግደሉ ይታወሳል።
ክርስቲያን ፖስት እንዳስነበበው

በኦቦሌሳ አዶላ
3🔥2👍1🙏1
በሀገራዊ ችግኝ ተከላ መረሃ ግብር ሁሉም የወንጌል አማኞች ምዕመናን በነቂስ ወጥተው እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ።

#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ባስተላለፉት መልዕክት እግዚአብሔር ሰውን በኤደን ገነት ያስቀመጠው አንድም እንዲያበጅ አንድም እንዲጠብቅ ነው ብለዋል።

የወንጌል አማኞች ከ100 አመታት በላይ በሃገራችን ማህበራዊ አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ያስታወሱት ቄስ ደረጀ አንድ ተክል መትከል ማለት ለመጪው ትውልድ አሻራችንን ማስቀመጣችን መሆኑን በማሰብ መላው የወንጌል አማኞች ካውንስል አባላት እና ምዕመናን በሙሉ ወጥተን አሻራችንን እንድናሳርፍ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ 📸 ፋይል
18👍4🔥1
#አፋልጉን!

የWSG ንብረት የሆነው AA ኮድ- 5-01526
#ነጭ_ሚኒባስ_መኪና ቤሌር (ሕንድ ኤምባሲ) መግቢያ አካባቢ ከቆመበት እሁድ ሐምሌ 27 ምሽት ላይ #ተሰርቆብናል

እባክዎ
#በፀሎት ይደግፋን
#በፍለጋ ይተባበሩን
#በማህበራዊ_ገፅዎ_ያጋሩልን

+251913307297
+251929917573
+251911617261
+251910078659

ይደውሉልን
👍63🙏1
"#እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ" ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ ከደቡብ አፍሪካ

የደቡብ አፍሪካ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ጥሪ አቅርቧል።

የወንጌል አብሳሪዎች አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን በጁሃንስበርግ መሪ እና የካውንስሉ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ እንደገለጹት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን #እና ኤርትራውያን ስደተኞች በተለያዩ ቡድኖች ችግር እየደረሰባቸው እንደሆነ ገልጸው ነገሮች እንዲስተካከሉ እግዚአብሔር ጣልቃ እንዲገባ እንጸልይ ብለዋል።

ዶ/ር ብርሃኑ በመልዕክታቸው በአሁኑ ሰዓት ዱዱላ የተባለ ቡድን ስደተኞችን የማይገቡ ዶክመንቶችን በመጠየቅ እያሰቸገረ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም እዛው የተወለዱ እና ያደጉ #ልጆች ሲማሩም ይሁን ትምህርት ተምረውም ከጨረሱ በኋላ ስራ ለማግኘት በመቸገር ከፍተኛ ስንለቦናዊ ጫና እያደረባቸው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

እግዚአብሔርን አምነን ፊታችንን ወደ እርሱ በማድረግ ያለውን ችግር በእርሱ ፊት እንቅረብ በማለት በፈረንጆቹ ኦገስት 5-7 / 2025 ወይም ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም ድረስ በጾም እና ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ጸሎት እንዲቀርብ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሐንስ ግርማ
👍108🙏3🕊1
የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቀረበ።

ከሰሞኑ በቢሾፍቱ ከተማ ከፍተኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለዉ ዝናብ
በተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች ቤት ውስጥ ጎርፍ በመግባት ንብረቶች መበላሽት እና ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።

ሁኔታውን አስመልክቶ የቢሾፍቱ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ አቅርቧል።

ጥሪዉን ያቀረቡት የሕብረቱ ዋና ሰብሳቢ መጋቢ ብሩክ ከበደ በከተማዋ በጣለው ንፈስ እና በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በርካታ የከተማው ነዋሪዎች ላይ እና በህብረታችን በታቀፋ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ላይ በደረሰው የንብረት ውድመት የተሰማኝን ጥልቅ ሃዘን እገልፃለሁ ብለዋል።

መጋቢ ብሩክ አክለዉ ቅዱሳን የወንድም የእህት መኖርያ ቤቶችን እንዲሁም የአጥቢያ ቤተክርስቲያናትን መሰብሰቢያ አዳራሾች መልሶ ለመስራት በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ሁሉ በማድረግ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ እርስ በእርስ በመተጋገዝ አብረን እንቁም የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

እስካሁን ከአከባቢዉ በወጣዉ ዘገባ አንድ የቤተሰባችን አባል በዝናቡ ምክንያት የቤታቸው ጣራ መነሳቱን ፤ ሌላኛው አባል ደግሞ ቤታቸው በጎርፍ መጥለቅለቁን ቲክቫ ኢትዮጵያ መዘገቡ ይታወሳል።

Photo - Bayew Atiye & Social Media
10👍5👌1😭1
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ያወጀችው የጽዕም ጸሎት #ነገ ይጀምራል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም ባወጣችው የጽሁፍ መግለጫ መሠረት ሀገራችን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሰላምና ጸሎት ጥሪ ማቅረቧ ይታወሳል።

በመግለጫው መሠረትም ለቤተክርስቲያኒቱ አባላት፣ አገልጋዮችና መሪዎች ከነሃሴ 1 እስከ 11/2017 ዓ.ም ድረስ ስለምድራችን #ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ፊት በጾምና በጸሎት እንድንፈልግ ጥሪ መተላለፉ ይታወቃል።

“እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ልመናና ጸሎት፣ ምልጃና ምስጋና ለሰዎች ሁሉ፣ ለነገስታትና ለባለስልጣናት ሁሉ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤ ይህም በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ፣ በሰላምና በጸጥታ እንድንኖር ነው”። 1ኛ ጢሞ. 2፥1-2 (አ.መ.ት)
11👍2🕊1