The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ፓስተር ጆን ማከርተር አረፉ

በከሜሪካን ሃገር ግሬስ ኮሚኒቲ ቤ/ክ ለ56 አመታት ሲያገለገሉ የነበሩት ፓስተር ጆን ዛሬ ማለዳ ማረፋቸውን 'Grace to You" የተሰኘው ሚኒስትሪያቸው አስታውቋል።

በአገልግሎት ዘመናቸው ለህትመት የበቁ እና አርትኦት የሰሩባቸው ከ150 በላይ መጽሃፍት ለአንባቢያን አድርሰዋል። በቤተ ቤተርስቲያን አገልግሎት፡ በሴሚናሮች በማስተማር እና ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ "Grace to you" በተሰኘ ሚድያ ወንጌል ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ጆን ማከርተር በገጠማቸው የሳምባ ምች (Pneumonia) በሽታ ታመው ሆስፒታል በገቡበት በ86 አመታቸው ማረፋቸውን ሚኒስትሪያቸው አሳውቋል።

በኦቦሌሳ አዶላ
22🔥4😭1
50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዬቤልዩ

በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ የደቡብ ምስራቅ ክልል የባሌ ጎባ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ 50ኛ የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

በክብረ በዓሉ መረሃ ግብር ላይ በ1966 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌልን የሰበኩት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዱን ጨምሮ ከመጋቢ ጻዲቁ አብዱ ጋር ከጅማሬው አንስቶ በጋራ ወንጌልን ያገለገሉ እና አሁን የአይ ኤል አይ መስራችና መሪ የሆነት ፕሮፌሰር ባደግ በቀለ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አገልግለዋል፡፡

የጎባ ክ/ከተማ ም/አስተዳዳሪ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለአባላቱ በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

"ዘመን ተሻጋሪ የወንጌል የማዳን ሃይል” በሚል መሪ ቃል የቤተክርስቲያኒቱ ምስረታ 50ኛ የወርቅ ኢዩቤልዩ ሲከበር የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻውን ጨምሮ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማ፣ ከሀዋሳ ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ቀደምት የቤተክርስቲያኒቱ አባላትና አገልጋዮች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው በበኩላቸው የጎባ ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ ከራሷ አልፋ በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑ አገልጋዮችን አፍርታ ሰጥታናለች በማለት ካመሰገኑ በኋላ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ላይም የጎባ ሙሉ ወንጌል "ሀ" መዘምራን የመዝሙር አልበማቸዉን ከማስመረቅ በተጨማሪ በበዓሉ ላይ በዝማሬ አገልግለዋል፡፡

በመጨረሻም የቤ/ክ የመሪዎች ጉባዔ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሀይሉ ንባቢ በተለያየ መንገድ ለበዓሉ መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው በዓሉ በታላቅ ደስታና መጽናናት እንደሚሆን #መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
9👍2🔥1👏1
#በሱዳን አንድ አብያተ ክርስቲያን በወታደር እገዛ መፍረሱ ተነግረ።

የሱዳን ጴንጤቆስጤ ቤተ ክርስቲያን መካከል አንዷ በካርቱም ምስራቅ ናይል በሚባልበት አካባቢ ያለችው ቤ/ክ ናት የፈረሰችው። ቤተ ክርስቲያን ህንጻ ፈረሳው ሲካሄድ፣ የፖሊስ እና ወታደራዊ አካላት በስፍራው የነበሩ ሲሆን ህንጻውን ያፈረሱት ደግሞ ከ20 የማያንሱ ግለሰቦች ናቸው።

የቤተ ክርስቲያን ህንጻ የተገነባው በ1990 ሲሆን፣ የአምልኮ አገልግሎት እና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። ፖሊሶች በስፍራው ግለሰቦች ሲያፈርሱ ማንም ሰው እንዳይቀርጽ ሲከለክሉ ነበር።

የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ቤተ ክርስቲያኗ መልሳ እንድትገነባ እና ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ስደት እንዲቆም ጸሎት ይደረግልን ሲሉ ጠይቀዋል። ክርስቲያኖችን ከሱዳን የማውጣት እንቅስቃሴ በሰፊው እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል።

የተለያየ አይነት አመጽ፣ አስገድዶ ጋብቻ፣ ጾታዊ ጥቃት፣ ልጆችን መነጠቅ፣ ርስት መነጠቅ እና ሃሰተኛ ክሶች በሱዳን ያሉ ክርስቲያኖች በየ እለቱ የሚያልፉባቸው መከራዎች ናቸው። ከዚህ ባለፈ፣ በጦርነት ወቅት በሚያጋጥም፣ ርሃብ ወቅት ክርስቲያኖች ተለይተው ምግብ አይደርሳቸውም።

ከሙሉ ህዝቧ 2 ሚሊዮን የሚሆነው ወይም 4.1 % የሚሆነው ክርስቲያን ቢሆንም የክርስቲያኖች ግድያ እና ጠለፋ በተደጋጋሚ ይስተዋላል። ሱዳን በኦፕን ዶርስ አመታዊ መረጃ መሰረት 5ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አሁንም የሱዳን ክርስቲያኖች ጥያቄያቸው ግን “ጸሎት” ብቻ ነው ሲል ያስነበበው ዎርዚ ኒውስ ነው።

በኦቦሌሳ አዶላ
😭176🙏6🕊2💔1
በአሮሬሳ መጆ #ሙሉ #ወንጌል አማኞች #ቤተክርስቲያን በቡቤ-ቦሬ ቀበሌ ሐዳ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከስድስት ወራት በፊት የተተከለችው ሐዳ አዳጊ ቤተክርስቲያን የአምልኮ አዳራሿን መስራት ጀምራለች።

ከሰሞኑ ቤተክርስቲያኒቷ የአምልኮ አዳራሿን ለመሥራት መሠረት የጣለች ሲሆን የአሮሬሳ መጆ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤ/ክ አባላት በነፍስ ወከፍ በመውጣት ለግንባታው ሥራ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለግሰዋል።

በሂደቱም የአሮሬሳ መጆ ሙሉ ወንጌል አማኞች አጥቢያ ቤተክርስቲያን፣ የአሮሬሳ መጆ ስታዲየም ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን እና የሶዶ አዳጊ ቤተክርስቲያን አባላት ተሳትፈዋል።

በቀጣይነት ሁላችንም ወደ ሶዶ አዳጊ ቤተክርስቲያን እንደምንዘምት ፓ/ር በቀለ ሐዴሶ ገልጸዋል።

ክብር ሁሉ ለሥራው ባለቤት ለእግዚአብሔር ይሁን !!!
9🔥3👍2🥰1🙏1👌1
ታላቅ የአምልኮ ኮንሰርት እና የወንጌል ድግስ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።

በመጋቢ ትዝታው ሳሙኤል የምትመራው የዘላለም ሕይወት ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አዘጋጅነት ሐምሌ 26 ከቀኑ 7:00 ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን የወንጌል ኮንሰርቱን አስመልክቶ በዛሬው እለት ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው ከ13 ዓመታት በኋላ ወደ ሀገር የተመለሰው መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል “ዛሬ ለኢየሱስ” በሚል ርዕስ #እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋ በዝማሬ እንደሚያገለግል ተገልጿል።

ኮንሰርቱ 3 ዓላማዎች እንዳሉት የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያው አምላካችንን በዝማሬ ማክበር ሲሆን ፤ በሁለተኛ ደረጃ ወንጌል በማወጅ አዳዲስ ነብሳትን ለክርስቶስ መማረክ እንዲሁም ለምድራችን እና ለሕዝባችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ማድረግ እንደሆነ መግለጫውን የሰጡት መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል ተናግረዋል።

ለበርካታ አመታት ከምወዳቸው ሕዝቦች ጋር በጋራ ለማገልገል ብዙ ሲመኝ እንደነበር እና ይህ ከ13 ዓመት በኋላ መሳካቱን በመጥቀስ ነጭ ለብሳችሁ በመምጣት አብረን እንድናመልክ መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል ጥሪ አቅርበዋል።

መግለጫውን መጋቢ በጋሻው ደሳለኝ ፤ መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ የሰጡ ሲሆን በእነዚህ ወንድሞች እና እህታችን አገልግሎት የተባረኩ በሙሉ በአዲስ አበባ እና አከባቢው የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ተገኝተው አብረውን እንዲያመልኩ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ትዝታው ሳሙኤል ዘማሪ፤መጋቢ እና የዝማሬ ግጥሞችን የሚጽፍ ሲሆን “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” “መርከቤ” “ስመሰክር” እና “ማን ቀረ ከሜዳን” ጨምሮ ከ15 በላይ ዝማሬዎችን ለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያበረከተ መጋቢ ሲሆን በተለይ በ90 ዎቹ እጅግ ተወዳጅ ከነበሩ ዘማሪዎች መካከል አንዱ እንደነበር ይታወሳል።

በዮሐንስ ግርማ
35❤‍🔥2🔥2👍1👌1
እዩ ጩፋ ካውንስሉን ይቅርታ ጠየቀ

የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በቅርቡ በሚዲያ ላይ እንደሰማችሁት ለተፈጠሩት ክፍተቶች ከካውንስሉ የስነ መለኮት ኮሚሽን እና የህግ ኮሚሽን ጋር ዉይይት ካደረገን በኋላ ቤተክርስቲያናችን በጉዳዩ ላይ ስንፀልይና ስንመካከር ቆይተን የደረስንበትን ስምምነት እንደሚከተለው እናቀርባለን።

ካውንስሉን እና የካውንስል አመራሮች በተመለከተ በቴሌቭዥን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ለተጠቀምናቸው ያልተገባ ቃላት ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን።

ከዚህ ቀን ጀምሮ ካውንስሉን ከሚመሩ መሪዎቻችን ጋር በቅርበት እየተነጋገርን እንደ አባት እና ልጅ ተቀራርበን የክርስቶስን ወንጌል መንፈሳዊ ጨዋነት ተከትለን ቀዳሚዎቻችንን አክብረን ለማገልገል የተስማማን መሆኑን እየገለፅን ካውንስሉም ይቅርታችንን ተቀብሎ አባታዊ በሆነ መንገድ እየመከረን እና እያስተማረን እንዲመራን በመተማመን ይህንን መግለጫ እንደ ቤተክርስቲያን አውጥተናል።
👍34👏12🤣106🔥2👌1
አታዋሌ - “Let Jesus Reign”

#ኢየሱስ #ይንገስ ወይም #“Let Jesus Reign” በሚል መሪ ቃል በሐልዎት አማኑኤል ህብረት ቤ/ክ የወጣቶች ኮንፈራንስ ተካሄደ። ፕሮግራሙ በአታዋሌ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ እና ፒስ ጌት ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ በጋራ የተዘጋጀ ነው።

ፕሮግራሙ በተለይ ወጣት አገልጋዮችን ማስታጠቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ ሜንቶሪንግ፣ ተተኪ መሪዎች ማፍራት፣ አውዳዊ የወንጌል ስርጭት እና ድንበር ዘለል የወንጌል ስርጭት በኮንፈረንሱ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው።

የኮንፈራንሱ መሪ ቃል “Let Jesus Reign” ወይም ኢየሱስ ይንገስ በሁሉም ነገር ላይ ኢየሱስ ብቻ መንገስት አለበት የሚለውን ሃሳብ ከፍ አድርጎ ለማሳየት የታሰበ መሆኑን የፕሮግራሙ አስተባባሪ ወንድም #ሳሙኤል በላይነህ ለክርስቲያን ዜና ተናግረዋል።

በፕሮግራም እንዲያስተምሩ የተጋበዙት የአታዋሌ ኢንተርናሽናል ሚኒስትሪ መሪ ፓስተር #ራምጃኒ ጆሽዋ እና በአለም አቀፍ የተማሪዎች አገልግሎት ሪጅናል ዳሬክተር ወንድም #ዘላለም አበበ ናቸው። ተናጋሪዎቹ በትምህርቱ ነገ ወጥቶ ከድንበሩ ያለፈ ወንጌል ሰባኪ እና ከፊቱ ሰው ያለ እና ከኋላውም የሚረከበው እንዲሁም የሚያማክረው ሰው መኖር አገልግሎት አስፈላጊነት ዙሪያ አስተምረዋል።

የፒስ ጌት ሆሊስቲክ ሚኒስትሪ ዳይሬክተር ወንድም ሳሙኤል በላይነህ፣ የኮንፈራንሱ ተሳታፊዎች የተፈጠሩበትን አላማ ማወቅ እና ለአላማቸው መኖርን ከዚህ ሰንቀው መውጣትን እና አላማቸውን ደግሞ በሚገባ መኖርን ከእነርሱ እንጠብቃለን ብለዋል።

#“አታዋሌ” የስዋህሊ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ኢየሱስ ይንገስ ማለት ነው።
9👍1🔥1👌1
#የአደባባይ ስብከት እግድ

የለንደን ከተማ ምክር ቤት የአደባባይ ላይ የጣለው ስብከት እግድን አነሳ።

በለንደን ከተማ መሃል ላይ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ የአደባባይ ላይ ስብከት እና ሃይማኖታዊ ህትመቶችን መበተን ተከልክሎ ነበረ። በሰሜን ምዕራብ ለንደን የምትገኝ አንዲት #ቤተ ክርስቲያን የከተማውን ምክር ቤት በወርሃ ነሃሴ 2023 አውጥቶ የነበረው እግድ እንዲያነሳ አድርጋለች።

እግዱ በአደባባይ ወንጌል ሲሰብክ የተገኘ ሰው እስከ 100 ፓውንድ ይቀጣል የሚል ውሳኔ ነበረው። ክርስቲያኖች በፖሊስ እርምጃ ይወሰድባችኋል የሚል ማስፈራራት ቀርቦባቸው እንደነበረ ተዘግቧል።

ቤተ ክርስቲያኗን የወከለው የክርስቲያን ህግ ማዕከል (Christian Legal Centre) ነው። ሂሊንግዶን የተባለው ምክር ቤት ውሳኔውን መቀልበሱን እና ቤተ ክርስቲያኗ ለህግ ጉዳዮች ያወጣችውን ወጪዎች እንደሚሸፍን ገልጿል።

ህጉ የመናገር ነጻነት ላይ አደጋ ደቅኖ የነበረ መሆኑን በማንሳት አሁን የተወሰነው ውሳኔ እፎይታን እንዳመታ የክርስቲያን ህግ ማዕከል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል። #በአደባባይ ወንጌል መስበክ ጸረ - ማህበራዊ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ በ2009 ነጻ የምገባ ማዕከል ከፍታ የነበረ ሲሆን፣ የአርሰናሉ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ የሚያመልክባት ናት። የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ፓስተር ቱንዴ ባሎጉን፣ ክርክሩን ስንጀምር በእግዚአብሔር ላይ እርግጠኞች ነበርን ብለዋል።

ኢንግሊዝ እነ ጆን ዌስሊ እና ቻርለስ ስፐርጅንን የመሳሰሉ ሃያል ወንጌላዊያን የወጡባት ሃገር መሆኗ ይታወሳል።

ፕሪሚየም ክርስቲያን ኒውስ እንዳስነበበው
በኦቦሌሳ አዶላ
🔥1813👍4👏1🙏1
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በጋምቤላ ወረዳ ፑኮንግ ቀበሌ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጋለች።

ድጋፉን ያበረከቱት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝዳንት ፓስተር ላኮ በዳሶ እንደገለፁት በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖች መደገፍና መንከባከብ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ቤተክርስቲያኗ ከመንፈሳዊ አገልግሎት በተጨማሪ በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የድርሻዋን እየተወጣች እንደምትገኝም ፕሬዝደንቱ አክለው ገልፀዋል።

በአከባቢው ያለውን ለም መሬትና የተለያዩ የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም ከተረጅነት መላቀቅ እንደሚያስፈልግ ያነሱት ፓስተር ላኮ ይህንን ታሳቢ በማድረግ የእርሻ መሳሪያ ቁሳቁስ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የጋምቤላ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡማን ኡሞድ በበኩላቸው ቤ/ክ ያለውን ችግር በመመልከት ላደረገችው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ከድህነት ለመላቀቅ ብቸኛ አማራጭ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ተጠቅመን ማልማት ስንችል ነው" ለዚህም ለተግባራዊነቱ ሁሉም ሊረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በጋምቤላ ቁጥር 3 ሙሉ ወንጌል ቤ/ክ መጋቢ የሆኑት ፓ/ር ወንድወሰን መሀመድ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች መሆኗን አንስተዋል።

የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት የአንድ አካል ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን ሁሉም በችግር ላይ ያሉ ዜጎችን በመርዳትና በመንከባከብ የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅበት አንስተዋል።

በዕለቱ ዘይት፣ ዱቄት፣ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ባልዲ፣ የእርሻ መሳሪያዎች፣ ሳሙናና የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።
10👍3👏2🙏2🔥1
#ወንድማገኝ ኡዴሳ ቄስ ሆነው ተሾሙ

መካነኢየሱስ 31 አገልጋዮችን በቅስና አገልግሎት ሾመች።

በአዶላ ገናሌ ሲኖዶስ የአዶላ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ በነበረው የቅስና አገልግሎት ምደባ ስነ ስርዓት፣ ቀሳውስቱ በቃል እና ቅዱሳት ሚስጥራት እንዲያገለግሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር #ዮናስ ይገዙ ሃላፊነቱን ሰጥተዋል።

የቤተክርስቲያኒቱም የወንጌል እና ቲኦሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል የእግዚአብሔርን ቃል በማስተማር ለእጩ ቀሳውስቱና ለምዕመናን የማበረታቻ ቃል አስተላልፈዋል።

በቤተ ክርስቲያኗ የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት ሃላፊ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ወንድማገኝ ኡዴሳ በቅስና አግልግሎት ከተሾሙት መካከልናቸው። #ቄስ ወንድማገኝ የክርስቲያን ዜና መልካም የአገልግሎት ዘመን ይመኛል።

ምንጭ፡
Facebook EECMY
3👍1
የኢትዮጵያ የስነ መለኮት ድህረ ምረቃ ት/ቤት (EGST) ለ25ተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ት/ቤቱ በተለያዩ መስኮች ያስተማራቸውን 80 ተማሪዎች የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ኣብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዘዳንት መጋቢ ፃድቁ አብዶን ጨምሮ ጥሩ የተደረገላቸው መሪዎች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት በተቋሙ አዳራሽ አስመርቋል።

ኤገስት የድህረ ምረቃ የስነ መለኮት ትምህርት ቤት በተለያዩ ዘርፎች ተማሪዎችን በማስተማር ብቁ እና ለቤተክርስቲያንም ሆነ ለሀገር ጠቃሚ ዜጋ እያፈራ ያለ ተቋም መሆኑንም በዕለቱ ተወስቷል።

በምረቃ መረሃ ግብሩ ላይ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት የት/ቤቱ ፕሬዘዳንት ዶክተር ወርቁ ሀይለማሪያም እና በክብር እንግዶች አማካኝነት ለተመራቂዎቹ ተበርክቷል።

ምንጭ GMM TV
3👍2👌1
#መሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የሰላም ጥሪ

ቤተ ክርስቲያኗ ለፌደራል መንግስት እና ትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ነው የሰላም ጥሪ ያስተላለፈችው።

አመሻሹን ይፋ ባደረገችው ፕሬስ ሪሊዝ፡
ሁለቱም አካላት የጦር ወሬ እንዲተዉ፡ ለአለም አቀፍ ማህበር ሰብ፡ ሃላፊነት የሚሰማው ሚድያ እና ቤተ ክርስቲያኗ ለሰላም ያላትን ቁርጠኝነት በፕሬሱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።

አሁን የመከፋፈል ጊዜ፡ ሳይሆን የቆራጥ መሪነት፡ ትህትና የተሞላበት ንግግር እና ለሃገራችን ኢትዮጵያ ሰላም በጋራ የምንሰራበት ይሁን ይላል።

ምንጭ፡ ቴሌግራም MKC Official
👏64🕊1💯1
#ነፃ የዓይን ህክምና

በፕሮፌሰር ሞሪስ ሃሽታን የሚመራው የእስራኤል የዓይን ህክምና ቡድን ከ#1600 በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ነፃ የዓይን ህክምና ሰጠ።

የህክምና ቡድኑ በመቄዶንያ የአረጋውያንና አእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል ፣ በማዘር ቴሬሳ፣ በህይወት ማዕከል፣ በደብረብርሃን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና ለአይሁድ ማህበረሰብ ህፃናት ፣ አቅመ ደካሞች እና አረጋዊያን ህክምናውን ሰጥቷል።

ከዓይን ምርመራ እስከ ዓይን ቀዶጥገና ያካተተው ህክምና የዓይን ጠብታዎች፣ መነፅሮችና ለዓይነ ስውራን ደግሞ ነጭ በትሮች ለግሰዋል።

በኢትዮጵያ የእስራኤል  አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሴ ይህ በጎ ስራ የእስራኤል እና የኢትዮጵያ ሁለትዮሽ ግንኙነት መጠናከር አንዱ ማሳያ ነው።

በተለያዮ ዘርፎች የምናደርጋቸውን ግንኙነቶች አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
👍41🔥1🙏1👌1
የሰሜን ምስራቅ የቃለ #እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልላዊ የተማሪ መሪዎች ጉባኤ በደሴ ከተማ ሲካሄድ ቆይቶ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ከአንፆኪያ - ኬሚሴ ጀምሮ እስከ አላማጣ — ኮረም ድረስ ከሚገኙ 25 ከተሞች የመጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት ጉባኤ ዋና ትኩረት የሆነው የዘፍጥረት መጽሐፍ አሳታፊ በሆነ መንገድ የተጠና ሲሆን በቆይታችን፣ ፌሎሽፕ (school fellowship) መመስረት እና ማጠናከር ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የጉባኤው ተሣታፊ ተማሪዎች፣ የቤተሰብ ቡድን አገልግሎት ስልት እና አገልጋይ መሪነት በሚሉ አርእስቶች ላይ ጠቃሚ ሴሚናር ወስደዋል።

ተማሪዎች የመጡባቸው ከተሞች በወንጌል ያልተደረሱ ሲሆኑ በአንድ 2ደረጃ ትምህርት ቤት 1 ክርስቲያን ተማሪ ብቻ ያለባቸው ከተሞች ጭምር እንደሚገኙ በመድረኩ ተጠቅሷል። ተሣታፊ አካባቢያዊ ሁኔታቸውን ያገናዘበ ወዳጃዊ ወንጌልን የመመስከር መንገድ (መፀለይ-መንከባከብ-ማካፈል) እና አለም አቀፍ የእግዚአብሔር ራዕይ የሚሉ ስልጠናዎችንም ወስደዋል።

በአራት ቀን ቆይታችን፣ ከወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ካውንስል መሪዎች እና ከየቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር አሶሼት ስታፎች ጋር የውይይትና የአብሮነት ጊዜ አሳልፈናል።

ሰሜን ምስራቅ የቃለ እግዚአብሔር አንባቢዎች ማኅበር ክልል ብዙ ፀሎት የሚያስፈልገው እንደሆነ እና አማኞች እንዲበረቱ ፤ በአካባቢው እያገለገሉ ለሚገኙ ቅዱሳን የወንጌል እሣት በተማሪዎች መካከል እንዲቀጣጠል እንዲጸለይ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።
7👍2👌1