The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
51 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
እውቁ የወንጌል አገልጋይ ጂሚ ስዋጋርት በ90 ዓመታቸው አረፉ።

ጂሚ ስዋጋርት ሚኒስትሪ በፌስቡክ ገጹ ይፋ እንዳደረገው ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት አገልጋዩ ጂሚ ስዋጋርት ወዳገለገለው ጌታ ተሰብስቧል ሲል ገልጿል።

ባለፈው ወር ጁን 15 በልብ ህመም ሆስፒታል የገባ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ወዳገለገለው ጌታ መሄዱን ሚኒስትሪው አስታውቋል።

ጂሚ ከ8 ዓመቱ ጀምሮ ህይወቱ እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በታማኝነት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያገለግል መቆየቱን ሚኒስትሪው በፌስቡክ ገጹ አሳውቋል።

ከ1969 ዓ.ም በራድዮ፡ በ1970 በመጽሄት ህትመት እና በ1973 ጀምሮ ደግሞ በቴሌቭዥን የወንጌል አገልግሎት ይታወቃል።

ጂሚ በተለይ በ1987 ዓ.ም በብራዚል ሪዮ ዲ ጃኔሮ በነበረው የወንጌል ክሩሴድ ከ127 ሺህ ሰዎች ወንጌል ሰምተዋል።

ጂሚ ስዋጋርት በተደጋጋሚ የወሲብ ቅሌት ስሙ የሚነሳ የነበረ ቢሆንም በንስሃ ተመልሶ ሲያገለግል ነበረ።
ተሶሼትድ ፕሬስ እና ክርስቲያን ፖስት ናቸው ያስነበቡት።
🕊12🙏61😭1
#እግዚአብሔር ቀን አለዉ ለሁሉ የተሰኘዉ ቁጥር 1 የዝማሬ አልበሙን ጨምር

#ቃል ያለዉ አይወድቅም" የሚል መጠርያ ባለዉ በቁጥር 2 አልበሙ ዛሬም ድረስ ብዙዎች ይፅናኑበታል።

ለቅሶ ማታ ቢሆንም ጠዋት ደስታ ይሆናል
ሁሉን ቻዩ ጌታ እግዚአብሔር ቀን ያዛል ዛሬም ድረስ ለብዙዎች በእለፍኛቸዉ ከጌታ ጋር የሚወያዩበት እና ምላሽ የሚጠይቁበት ዝማሬያቸዉ ነዉ።

ላለፉት 2 አስርት አመታት በተሻገረ በዝማሬዎቹ ተባርከንበታል። #ጌታ በሰጠዉ ፀጋ ምዕመናንን ቃሉን በመመገብ ወደ ኋላ አላለም።

ፖስተር ካሳሁን ለማ #አሁን ደግሞ የልቀት ሚስጥር በሚል #አዲስ መፅሐፍ ይዞልን መጥቷል።

ሰኔ 29 እሑድ ከ 08:00 ጀምሮ

ይህንን #ድንቅ ቀን በአንድነት ጌታን እናከብር ዘንድ በአክብሮት ጥሪ እናቀርባለን ።

👉 አድራሻ ቦሌ ኤርፖርት አዲሱ VIP መንገድ ጫፍ ላይ ።
7👍5👌1
#ደረሰ #ደረሰ

በክረምት መረሃ ግብር ለጋዜጠኝነት ስልጠና ፈላጊዎች (ክርስቲያኖች)

መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል።

ስልጠናውን የሚያተኩርባቸው

1. ተግባቦት (Communication)
2. ጋዜጠኝነት ( Journalism )
3. ዜና (NEWS)
4. መጣጥፍ እና ስነ ጽሁፍ (Feature Article & Literature)
5. የሚድያ ስነ ምግባር (Media Ethics)
6. ዲጂታል ሚድያ (Digital Media)
7. ፕሮዳክሽን (Production)
8. ዘጋቢ ፊልምና ቃለ መጠይቅ (Documentary and Interview)

ከሃምሌ 5 - ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም

ቦታ፡ #አዲስ አበባ #እና ሀዋሳ

(5ኪሎ መ/ኢየሱስ) (ሞቢል ሕይወት ብርሃን ቤ/ክ)

አዘጋጆች;- የደስ ደስ መልቲ ሚዲያ ፤ ቲኪቆስ ሚዲያ እና የክርስቲያን ዜና በጋራ በመሆን

ለተጨማሪ መረጃ፦
0911454205
0911891822

ለመመዝገብ Scan ያድርጉ አልያም ሊንኩን ተጠቅመው መመዝገብ ይችላሉ።

https://docs.google.com/forms/d/1NvZVALpBBjeOQgkv4gzSRzrVS6Ra_h47F24K1E250Z0/edit
4👍1
💍 ለተጋቡ ጥንዶች ብቻ!

ተመዝግበዋልን?

ትዳራችንን ቆም ብለን ለማጤን ጊዜው አሁን ነው። እኛ ባለትዳሮች ስለትዳራችን እና ልጆቻችን ቁጭ ብለን የምንመክርበት ልዩ ቀናት፣

🛖 የልብ ልባችንን የምንጨዋወትበት ፣ አንድነታችን የሚጠናከርበት እና ቃልኪዳናችንን የምናድስበት እድል፣
💬 ተግባቦታችንን የምንቃኝበት፣ የተሰበረ ልባችን የሚፈወስበት፣ መሰረታችን የሚጠናከርበት፣
👨‍👩‍👧 ልጆችን ለማሳደግ በዓላማ የምንታጠቅበት ፣ በአንድ ልብ ለማሳደግ የሚያስችል እሳቤ የምንሸምትበት
የቀረን ቦታ ለ4 ጥንዶች ብቻ ነው።
ዛሬውኑ ይመዝገቡ! ከጥቂቶቹ መካከል ለመሆን ይወስኑ!

ቀን፦ ከሐምሌ 5-26 ቅዳሜ ፣ ቅዳሜ ከ8:00-12:00

ቦታ:- የቀድሞው ኢምፔሪያል ውሃ ልማት አካባቢ በጨጨሆ ገባ ብሎ

ለመመዝገብ በ0911136520/0946693468 ይደውሉ!

📣 ቦታ አነስተኛ ነው— ለ4 ጥንዶች ብቻ! 
ለትዳሬ ስምረት ምንስ ብከፍልለት!

ስለትምህርቶቻችን ለማወቅ፦

https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
4👍2🔥1🙏1
#ደረሰ #ደረሰ

በክረምት መረሃ ግብር ለጋዜጠኝነት ስልጠና ፈላጊዎች (ክርስቲያኖች)

መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል።

ስልጠናውን የሚያተኩርባቸው

1. ተግባቦት (Communication)
2. ጋዜጠኝነት ( Journalism )
3. ዜና (NEWS)
4. መጣጥፍ እና ስነ ጽሁፍ (Feature Article & Literature)
5. የሚድያ ስነ ምግባር (Media Ethics)
6. ዲጂታል ሚድያ (Digital Media)
7. ፕሮዳክሽን (Production)
8. ዘጋቢ ፊልምና ቃለ መጠይቅ (Documentary and Interview)

ከሃምሌ 5 - ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም

ቦታ፡ #አዲስ አበባ #እና ሀዋሳ

(5ኪሎ መ/ኢየሱስ) (ሞቢል ሕይወት ብርሃን ቤ/ክ)

አዘጋጆች;- የደስ ደስ መልቲ ሚዲያ ፤ ቲኪቆስ ሚዲያ እና የክርስቲያን ዜና በጋራ በመሆን

ለተጨማሪ መረጃ፦
0911454205
0911891822

ለመመዝገብ Scan ያድርጉ አልያም ሊንኩን ተጠቅመው መመዝገብ ይችላሉ።

https://docs.google.com/forms/d/1NvZVALpBBjeOQgkv4gzSRzrVS6Ra_h47F24K1E250Z0/edit
1👍1🔥1
#በቁጥር 31 ሰዎች ለወንጌል አገልግሎት የደቀመዛሙርት ትምህርት ተከታትሎ ወደ አገልግሎት ደረሱ።

#ክብር ምስጋና ለሥራው ባለቤት ለኢየሱስ ክርስቶስ ይሁን ከእኔ ጋር ጌታን አመስግኑት #በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ምዕራብ ደቡብ ቀጣና ቦንጋ ዙሪያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ሕብረት የቦባ ገጫ ቃ/ሕ/ቤ/ክ በተከታታይ በቤተክርስቲያን የሚሰጠውን የአገልግሎት እና የደቀመዛሙርት ትምህርት የተማሩትን በማስመረቅ እንዲያገለግሉ በቃለ #እግዚአብሔር አስታጠቀች።

በቦባ ገጫ እናት አጥቢያ ሥር የሚገኙት ሁለቱ ተከላዎች ማለትም "የገባ ተከላ ቃ/ሕ/ቤ/ክ የድክ ተከላ ቃ/ሕ/ቤተክርስቲያን የሚገኙት የደቀመዛሙርት ትምህርት የተከታተሉት የተዘጋጀውን ሰርቲፕኬት በመውሰድ በጉባኤ ፊት ማለትም በሦስቱ ቤተክርስቲያን ስብስብ አንድነት ለማገልገል ቃል ኪዳን በመግባት ተመረቁ።

ሰዎችን ሁሉ የእውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት የማድረግ አገልግሎት ይልቁንም የሚያስፈልግበት ዘመን ይህ ነው ምክንያቱም ብዙ ነገሮች በዘመናችን ቤተክርስቲያን እየተከሰቱ ነው ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰነ-ስርዓት ወደ ገሃድ የወጣበት ዘመን ላይ ነን ስለዚህ ትውልድን በቃለ እግዚአብሔር እናስታጥቅ።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ ማስቀጠል አለብን ተልዕኮም የሚፈጸመው በመሄድ ወንጌልን በመስበክ ያመኑትን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ነውና እናስቀጥል።

“እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ማቴዎስ 28፥19-20
የክርስቶስ ወንጌል ከትውልድ ወደ ትውልድ ይቀጥላል ኢየሱስ ክርስቶስ ያድናል።

✍️ሚሽነሪ አክሊሉ ነኝ ከካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ
6👍1👌1
የምስራቅ ጉጂ መሠረተ #ክርስቶስ ኮሌጅ በታሪኩ የመጀመሪያ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚነሪ የምስራቅ ጉጂ ስነ-መለኮት ኮሌጅ ዛሬ ሰኔ 29/2017 ዓ.ም በሻኪሶ ከተማ ተማሪዎቹን አስመርቋል።

በመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የምስራቅ ጉጂ ጊዜያዊ ክልል ስር የሚገኘው ኮሌጁ በዲግሪ መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 14 ተማሪዎች ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያስመረቀው።

በምረቃ ፕሮራሙ ላይ የተገኙት በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ የክልል ካምፓሶች ተጠሪ መምህር ታደሰ በዬቻ የእግዚአብሔር ቃል ከማቅረብ ባለፈ ባደረጉት ንግግር "በድግሪ መመረቅ ማለት ከሳሎን ወደ ግቢ መውጣት ነው ሩቅ የሄዳችሁ እንዳይመስላችሁ ስለዚህ መማራችሁን ቀጥሉ" ብለዋል።

የምስራቅ ጉጂ ጊዜያዊ ክልል ዋና ጸሐፊ መጋቢ ትዕግስቱም "ተመራቂዎች የክልሉ እድገት ማሳያና የመጀመሪያዎቹ ታሪካዊ ምሩቃን በመሆናችሁ #እንኳን ደስ አላችሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ተመራቂዎችም የመጀመሪያ ተመራቂዎች በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል። በፕሮግራሙ በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቷል።

የመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ በአሁን ሰዓት 815 ተማሪዎችን በመያዝ በሀገሪቱ በሚገኙ 23 ካምፓሶች ትምህርት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ምንጭ:- Meserete Kristos Church - Head Office

ሰኔ 29/2017ዓ.ም
ሻኪሶ
👍43🔥1
"አውነት እና ፍቅር" የተሰኘው ትያትር ተመረቀ።

በትላንትናው እለት ሰኔ 29/2017 ዓ.ም በፕሮቪዥን ፈልሞች የተዘጋጀው እና "አውነት እና ፍቅር" የተሰኘው በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ዘንድ የመጀመሪያው የሆነው ትያትር በቫምዱስ ሲኒማ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቆ ለእይታ ቀርቧል።

የትያትሩ ደራሲና ደይሬክተር ሄኖክ በቀለ “በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ዘንድ እንደዚህ አይነት ስራ አልተለመደም” ያሉ ሲሆን #ይህ የመጀመሪያ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ብዙ ስራዎችን በትያትር መልኩ ለመስራት እንዳቀዱ ተናግረዋል።

#እውነት እና #ፍቅር የሚያጠነጥነው አውነትን በቀጥታ መናገርና ፍቅርን መስጠት ላይ የሚያተኩር ሆኖ በሁለት መሃል ያለውን ውዝግብ የሚያሳይ እንደሆነ ደራሲው ገልጿል።

ፕሮቪዥን ፈልሞች ላለፉት ሁለት ዓመታት በጂዶ-ክርስቲያናዊ የሥነ-ምግባር ዕሴት ላይ ታንጾ በጥበብ ዘርፍ እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ፕሮቪዥን ፊልሞች የተቋቋመው በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት አባል ከሆኑ ቤተ ዕምነት የተወጣጡ የትያትር ፣ የሚድያ #እና የፊልም ባለሙያዎች መሆኑ ተገልጿል።

ትያትሩ 55 ደቃቅ ርዝመት የለው ሲሆን በዚህ ትያትር ላይ 4 ዋና ዋና ተዋናዮችና በረካታ ሰዎች በስራው ላይ ተሳትፈዋል።

በትያትሩ ላይ ለተሳተፉት በሙሉ የእውቅና ሰርተፍኬት የተሰጣቸው ሲሆ በቀጣይም በየሳምንቱ በሻምዱስ ሲኒማ የምታይ መሆኑ ተገልጿል።

ሰኔ 30/2017ዓ.ም
#አዲስ አበባ
2👍2👌1
21ኛው የክርስቲያን ሴቶች ኮንፈረንስ በቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን ተካሄደ።

"አንቺን ለፅድቅ" በሚል በተዘጋጀው በዚህ መርሀ ግብር የፀሎት የትምህርትና የአንድነት ጊዜም ተደርጓል። ከሰኔ 24 እስከ 27 2017 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ጉባኤም ከተለያዩ ከባህር ማዶ እና ከሀገር ውስጥ የመጡ አገልጋይ እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

#ይህ የሴቶች ጉባኤ ከተጀመረ ሁለት አስርት ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ሲሆን ቀደም ሲል በሰሜን #አሜሪካ ፣ በካናዳና በአውሮፓ ሲካሄድም ቆይቷል።

አገልጋይ ሶፊያ አሰፋ እንደገለፁትም ከተለያዩ የአሜሪካ እስቴት እህቶች ተሳታፊ መሆናቸውን በመግለፅ ሁሉም በቅድስና መመላለስ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል ፓስተር ህሊና ግርማ የነበረው የአንድነት ጊዜ #መልካም መሆኑን በመግለፅ ኮንፈረንሱ እህቶች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡም ማድረጉን ገልፀዋል።

በእለቱም በኪንግደም ሳውንድ የዝማሬና የጋራ የአንድነት ጊዜ የተካሄደም ሲሆን የኢትዮጵያ ኢቫንጄሊካል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ዶክተር ትሁት አስፋው በእግዚአብሔር ቃል አገልግለዋል። በመልዕክታቸውም ሁሉም በተሰጠው ፀጋ አገልግሎቱ እንደሚቀጥልም በመግለፅ ይህም አገልግሎት ከትውልድ ትውልድ እንደሚሻገርም ገልፀዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ሁሉም አማኝ በተሰማራበት ሁሉ በትክክልኛ ክርስቲያናዊ አሰራር መስራት እና ማገልገል እንዳለባቸውም ገልፀዋል። ማንኛውም ክርስቲያን አዎንታዊ ተፅዕኖዎችን ማስተጋባት እና ማሻገር እንደሚችል እና ይህንንም ለማድረግ በቅድስና መመላለስ እንደሚገባም በትምህርቱ ወቅት ተወስቷል።

መረጃው የGMM TV Ethiopia ነው።
ሰኔ 30/2017ዓ.ም
#አዲስ አበባ
3👍3🔥1🥰1👌1
#የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰብዓዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን #አዲስ የተሾሙት የቦርድ አባላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የእውቅና መረሃ ግብር አካሄደ።

ኮሚሽኑ በመረሃ ግብሩ በቦርድ አመራርነት እንዲሁም አባል ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን በማመስገን እውቅና የመስጠት መረሃ ግብር በቤተክርስቲያኒቱ ዋና ጽፈት ቤት አካሂዷል።

በመድረኩ የኮሚሽኑ የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የቀርበ ሲሆን የቀጣይ አምስት ዓመት ስልታዊ እቅድ አሰራር በሚመለከት ከአዲሱ የቦርድ አባላት እና አመራር ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎል።

ዶ/ር ስምዖን ሄሊሶ ጨምሮ ልማት ኮሚሽኑን ላገለገሉ አካላት የእውቅና ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት ጸሎት በማድረግ ዶ/ር ተስፋዬ ያዕቆብ የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አገልግለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የቤተክርስቲያኒቱ ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላት ፤ የኮሚሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ዳንኤል ጫዕሜቦ ፤ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ተፈራ ተሎሬን ጨምሮ የቦርድ አባላት፤ ፕሮግራም ዳይሬክተሮች እና የፕሮጀክት ስራ አስተባበሪዎች ተገኝተዋል።
4👍1🔥1
እህታችን ዘማሪት ፀዳለ አየለ ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወዳገለገለችው ጌታ ሄዳለች።

#ዜና እረፍቷን ተከትሎ የሀልዎት አማኑኤል ቤተክርስቲያን ሀዘኗን ገልጻለች።

ቤተክርስቲያኒቱ በመግለጫዋ እህታችን ዘማሪት ፀዳለ አየለ በሀልዎት አማኑኤል ኀብረት ቤተክርስቲያን አባል ሆና በሀርመኒ የመዘምራን ኀብረት ውስጥ እንዲሁም በሶሎ ዝማሬ ስታገለግል የቆየች የተወደደች እህት መሆኗን በመጥቀስ ወዳገለገለችው አምላኳ ሔዳለች፤ ወደ ዘላለማዊው እረፍቷ፤ ወደ ሰማዩ ቤቷ ገብታለች ሲሉ ተናግረዋል።

ቤተክርስቲያኒቱ በመግለጫው በእህታችን በስጋ ከእኛ መለየት ብናዝንም ሀዘናችን ግን ተስፋ እንደሌላቸው አይደለም።

ከሞት ወዲያ ባለው ሕይወት ዳግመኛ እንደምንገናኝ ስለምናውቅ በሱ እንጽናናለን በማለት ለቡታጅራ ከተማ ምዕመናን መጋቢዎቿና አብራችኋት ስታገለግሉ ለነበራችሁ፣ ለሀልዎት አማኑኤል ኅብረት መዘምራን እንዲሁም ለቤተሰቦቿና ለጓደኞቿ መፅናናትን ተመኝታለች።

ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን። …….. ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ። (1 ተሰሎንቄ 4:13-18)

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በእህታችን ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለወዳጅ ዘመዶቿ ለጓደኞቿ መፅናናትን እንመኛለን።
😭8🙏42💔1
#አዲስ አመት
#አዲስ ጫማ

ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ እና ብራይት ስታር ኢትዮጵያ የ2017 ዓመተ ምህረት የክረምት ወራቶች በአዲስ ዓመት አዲስ ጫማ የተሰኘውን መርኃ ግብሩን ማጀመሩን ገለጸ፡፡

በ2016 ዓመተ ምህረት የክረምት ወራቶች በአዲስ አመት አዲስ ጫማ የተሰኘ መርኃ ግብር በማስጀመር 1,100 በላይ ለሚደርሱ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ጨምሮ ጫማ፣ የትምህርት ቤት የደንብ ልብስና የተለያዩ ግብአቶችን በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ ከሚገኙ ግለሰቦች እንዲሁም ተቋማት በማሰባሰብ ድጋፍ ማድረግ ተችሎ እንደነበር የብራይት ስታር ዳይሬክተር ቄስ ዶክተር በፍርዱ መሰረት ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዳይሬክተሩ የ2016 ዓመተ ምህረት ንቅናቄ ግቡን እንደመታ ገልፀው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡ በአዲስ አመት አዲስ ጫማ የተሰኘው መርኃ ግብር ወገኖች አሮጌ ነገራቸውን ትተው አዲስ በሆነው አመት አዳዲስ የትምህርት ግብአቶችንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን የመስጠት ልማድ ለማዳበርና ባህል ከማድረግ አንፃር የተነሳ መሆኑን ተቋሙ ገልጿል፡፡

የመስጠት ባህላችንን ለማሳደግ ታልሞ እየተሰራ የሚገኘው ንቅናቄ ከተቋሙም ባሻገር ሰዎች በአካባቢያቸው ለሚገኙ ወገኖች አዳዲስ ነገሮችን መስጠት እንዲችሉም ተጠቁሟል፡፡

በዘንድሮው2017 ዓመትም የክረምት እንቅስቃሴ እንደ አምናው ሁሉ ከአንድ ሺ አንድ መቶ በላይ ጫማዎችን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ግብአቶችን ለማሰባሰብ መታቀዱን የብራይት ስታር ዳይሬክተር ጨምረው ገልፀዋል፡፡

መረጃውን ጋዜጠኛ ጸጋህይብዛ ኢሳይያስ አደረሰን
4👍1🙏1
#ቦታ ሞልቷል፣ እንዳያመልጠን ለምትሉ 2 ጥንዶች እድል እንሰጣለን! አሁኑኑ ተመዝገቡ!

ከሀሙስ ከምሽቱ 2:00 በኋላ ምዝገባ አንቀበልም‼️

በጎጆዬ የጋብቻና የልጆች አስተዳደግ የተገኙ ባለትዳሮች ምን ያገኛሉ?

የመጀመሪያው ቅዳሜ

የጋብቻቸውን ትርጉም እና ዓላማ ያድሳሉ፣ የጋራ ራዕይ ይሰንቃሉ፣ ይቀርፃሉ፤

ሁለተኛው ቅዳሜ

እንደባልና ሚስት ከእግዚአብሔር የተቀበሉትን ማንነት በጥልቀት ያስተውላሉ፣ እርስ በርስ ስለቀደሙ ብዠታዎች ይቅር ይባባላሉ ፣ ለማክበር እና ለመተባበር ቃል ይገባባሉ፤

ሦስተኛው ቅዳሜ

ዋና ዋና ጉዳዮች ይዳሰሳሉ ፣ ፍቅር ፣ ተግባቦት ፣ ወሲብ እናም ከእነዚህም መካከል ወሳኝ ስለሆነው የተግባቦት ጥበብና ክህሎት ይቀስማሉ ፣ ይለማመዳሉ ፤

አራተኛው ቅዳሜ

እንደወላጅ ለልጆቻቸው የጋራ ራዕይን ይሰንቃሉ፣
እነዚህ ቀናት በግል የምክር አገልግሎት ይጠናቀቃሉ።

ከእነዚህ ቀናት በኋላ ፦
👉 ትዳራቸው ይታደሳል ፣
👉የጋራ ቋንቋ ያዳብራሉ፣
👉ትናንትናን በይቅርታ ይዘጋሉ፣
👉ነገን በጥበብ ፣ ማስተዋልና እውቀት ለመምራት ይታጠቃሉ፣ ይወስናሉ ፣ ቃል ይገባባሉ፤

ውድ ባለትዳሮች ፣ እናንተስ?

ዛሬውኑ ተመዝገቡ!

ቀን፣ ሐምሌ 5፣ 12፣ 19፣ 26
ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00-11:00
ቦታ፦ በቀድሞው ኢሞፔሪያል ውሃ ልማት በጨጨሆ ገባ ብሎ!
ለመመዝገብ፦ 0911136520/0946693468

ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ስራዎች ለማወቅ 👇
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
yebetesebkitiradash.org
Yebeteseb Kitir Adash
4👍3🔥1
በታንዛኒያ ከመላው #አለም የተወጣጡ ክርስቲያኖች ለ5 ቀናት ተሰብስበዋል።

ለ5ቀናት በሚቆየው ስብሰባ ክርስቲያኖች እና ቤተ ክርስቲያን በዚህ ተለዋዋጭ አለም የሚኖራቸው ሚና ላይ ጸሎት ያደርጋል፣ ውይይት ይካሄዳል፣ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ፣ ተብሎ ይጠበቃል።

መረሃ ግብሩ የሚካሄደው “Dancing in Faith – Drumming up Hope” የጉባኤው መሪ ቃል ነው።

ጉባኤውን ያዘጋጀችው የታንዛኒያ ሉተራን ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ስትሆን የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ጉባኤው በታንዛኒያ ምድር በመካሄዱ ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል፣ ለምድራችንም ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ በረከት ይሆናል ብለዋል።

የአለም ዲያቆኒያ ፌደሬሽን ጉባኤ በተባለለት በዚህ ጉባኤ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት፣ የአምልኮ፣ ባህላዊ እሴቶችን ማሳወቅ፣ የዲያቆናት አገልግሎትን በተመለከተ ውይይቶች ይኖራል ተብሏል ሲል ያስነበበው የአለም ሉተራን ፌደሬሽን ነው።

ሐምሌ 4 /2017 ዓ.ም
5👍2🔥1👌1
"አባካኙ #ልጅ" ተመረቀ።

በተወዳጇ ዘማሪት ቤተልሔም ተዘራና በባለቤቷ መንግስተ አብ ተገኝ የሚመራው የሊቪንግ ዊትነስ ሚኒስትሪ ራዕይውን በማስተዋወቅ "አባካኙ ልጅ" የተሰኘውን አጭር ፊልም ለተመልካች አቀረበ።

በትላንትናው እለት በሽራተን ሆቴል በተደረገው መረሃ ግብር የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች፣ አገልጋዮች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ወንድም መንግስተአብ ተገኝ ለጉባኤው የሊቪንግ ዊትነስ ሚኒስትሪ ራዕይን ያስተዋወቁ ሲሆን የዘማሪት ቤተልሔም ተዘራ የዝማሬ አገልግሎት የሚተርክ ዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል።

"አባካኙ ልጅ" የተሰኘው ይህ ሙዚቃዊ አጭር ፊልም ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 15 ላይ የተመሰረተው ሲሆን ፓስተር በቀለ ወልደኪዳንን እና ዘማሪ እንዳለ ወ/ጊዮርጊስ ጨምሮ የተለያዩ አንጋፋ ዘማሪዎች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ለጉባኤው በማቅረብ የእግዚአብሔርን የፍቅር ጥግ ምን ያህል እንደሆነ በመግለጽ ግንዛቤ ፈጥሯል።

#የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በጸሎት ዘማሪ ህሊና ዳዊት ዝማሬ በማቅረብ ቄስ ትግስቱ ሞገስ የእግዚአብሔርን ቃል መልዕክት በማቅረብ አገልግለዋል።

በመጨረሻም በፊልሙ ላይ ለተሳተፋ ወገኖች የሰርተፍኬት እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ምንጭ #GMM TV ETHIOPIA

ሐምሌ 4 /2017 ዓ.ም
9👍4🔥1👌1
#ነገ ይጀመራል። #ቅዳሜ ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም በ5ኪሎ መካነየሱስ 8:00 ሰዓት ይጀመራል።

በክረምት መረሃ ግብር ለጋዜጠኝነት ስልጠና ፈላጊዎች (ክርስቲያኖች) የተመዘገባችሁ በሙሉ

መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና ነገ እንደሚጀመር ልናሳዉቃችሁ እንወዳለን።

ከሃምሌ 5 - ነሃሴ 25/2017 ዓ.ም

📍 ቦታ፡ #አዲስ አበባ 5ኪሎ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን

(5ኪሎ መ/ኢየሱስ)

አዘጋጆች;- የደስ ደስ መልቲ ሚዲያ ፤ ቲኪቆስ ሚዲያ እና የክርስቲያን ዜና በጋራ በመሆን

ለተጨማሪ መረጃ፦
0911454205
0911891822

ለመመዝገብ Scan ያድርጉ አልያም ሊንኩን ተጠቅመው መመዝገብ ይችላሉ።

https://docs.google.com/forms/d/1NvZVALpBBjeOQgkv4gzSRzrVS6Ra_h47F24K1E250Z0/edit
👍51