The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በበርሊን ለተሰበሰቡ ወንጌላዊያን መሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት ምንድነው?

“አዲስ አለም አቀፍ ተልዕኮ” ያስፈልጋል ሲሉ ነው በበርሊን በተካሄደው የ2025 ወንጌላዊያን ኮንግረስ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ወንጌል ከግል ጉዳይ ይበልጣል፣ ማህበረሰብን የመቀየር አቅም አለው” ብለዋል።

ጥልቅ የመንፈሳዊ መታደስ ላይ ትኩረት ባደረገው አዲስ ተልዕኮ ባሉት እቅድ መሰረት “ዘላቂ ለውጥ ከውስጥ ይጀምራል” ብለዋል።

“ከዘር፣ ከሃይማኖት ትምህርት እና ሌሎች መከፋፈሎች ባለፈ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመመለስ” ፍቅርን እንቀበል ሲሉ ለአውሮፓዊያኑ ወንጌላዊያን መሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሙሉውን ፌስቡክ ላይ ያንብቡት
👇👇👇
https://www.facebook.com/100063892396728/posts/pfbid0V4hHKCAwLMPQ5on67caZwTLUgTBN6MQbWm17PVdSZPcKFoy4rKriYnKwwLUASb3El/?app=fbl
👍11🔥6🤷‍♂44🥰2🙏1
💍 የመጨረሻው ዝግጅት : የአጮኝነት ስልጠና💍
🔹ቀድመው ለደውሉልን 5 ጥንዶች በነፃ ስፖንሰር እናደርጋለን!
ለምዝገባ የቀረን 1 ቀን ብቻ ነው
ፈጥናችሁ ተመዝገቡ!

በቃልኪዳን የጋብቻን ጉዞ ከመጀመራችሁ ፊት በቂ ቅድመ-ዝግጅት ማድረግ ብልህነት ነው። "የመጨረሻውን ዝግጅት " ለማድረግ በዚህ የእጮኛሞች ስልጠና ተሳተፉ እና ለዘላቂና ጣፋጭ ትዳር መሰረት ለመጣል የሚረዷችሁን ግብዓቶች ሸምቱ።

📅 ቀን፦ግንቦት 30/June 7
📍 ቦታ፦ አለም ጋለሪ ገርጂ ታክሲ ተራ
💰 መመዝገቢያ Fee፦ለጥንዶች 1200፣ ለአንድ ሰዉ 650ብር ብቻ!

በነገ ህይወታችሁ ላይ ዛሬ ለመዝራት ቦታ ሳያልቅባችሁ ተመዝገቡ!

ወዳጅ ቤተሰብ! ስፖንሰር በማድረግ ለሠርጋቸው ስጦታ በመስጠት ለነገ ህይወታቸው የየድርሻችሁን ተወጡ።

አገልጋዮች ፦
👉ጌቱና ማህደር፦ የሰማይ ፋሚሊ አዘጋጆች
https://www.youtube.com/watch?v=Y6CushnHTrg

👉ሳሮን ውድነህ፦  የጋብቻ አስተማሪ እና አማካሪ
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk

ለመመዝገብ፦https://forms.gle/EKtmd52XMHF1612CA

ለበለጠ መረጃ፦ 0911136520/0911642595
3👍1
በቀል በቀለኛውን ያጠፋል።

የኤዶም የበቀል ታሪክ አሁን እንደ ሀገር እና እንደ ማህበረሰብ  እንዲሁም እንደቤተክርስቲያን ለገባንበት ቀውስ መውጫ አቅጣጫ የሚያመለክት ነው።

ትንቢተ አብድዩ ላይ ትኩረት ያደረገ ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ላለፊት 17 ዓመታት ያስተማሩት እና የሰበኩትም ታሪክ በመጽሐፍ መልክ ተሰንዶ መጣ።

"በቀል በቀለኛዉን ያጠፋዋል" ድንቅ መጽሀፍ በአድዋ መታሰቢያ ሙዝየም እንደሚመረቅ ታውቋል። ዛሬ 8:00 ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
👍63🔥1
#የእግዚአብሔር ክብር የኪዳኑ ታቦት" የሚል መጠሪያ ያለው እና በሐዋሪያው ዳንኤል መኮንን የተጻፈው መጽሐፍ ሊመረቅ ነው።

ሰኔ 2 2017ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም የሚመረቀውን መጽሐፍ አስመልክቶ በዛሬው እለት ለክርስቲያን ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው በ10 ምዕራፍ እና በ310 ገጾች የተዋቀረው #ይህ መጽሐፍ ሰኔ 2 ሰኞ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በ11:00 ሰዓት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና ጥሪ የሚደረግላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ተገልጿል።

ሐዋሪያው ዳንኤል #በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ባለፉት 55 የአገልግሎት አመታት በኦሎምፒያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ጨምሮ ፤ በጅማ ፤ በአሜሪካ እና አውሮፓ የአገልግሎት ዘመናቸው ያሳለፉት በመጽሃፉ ውስጥ በማካተት የህይወት ተሞክሮ እና ምስክርነትን በማጣመር የተዘጋጀ እንደሆነ በመግለጫው ተጠቅሷል።

#ክርስቲያን ከክብር ጋር እንዲገናኝ፤ በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ እንዲገኝ እና ናፍቆት እንዲኖረው የተጻፈ እንደሆነም የተገለጸ ሲሆን አዲሱ ትውልድ የእግዚአብሔርን ክብር ናፍቆት መሙላት ላይ የተፈለገው ተጽዕኖ እንዲያሳርፍ የተዘጋጀ እንደሆነ ተጠቅሷል።

መጽሐፉ #ሙሉ በሙሉ የሽያጩ ገቢው ለአዋሬ ወንጌል ብርሃን አ/አቀፍ ቤ/ክ ግንባታ እንደሚውልም ተገልጿል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን አቀረብንላቹ ተጨማሪ የቪዲዬ ዘገባ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

ግንቦት 28/2017 ዓ.ም

በኦቦሌሳ አዶላ
5👍2🔥2🙏1
የኢትዮጵያ ወጣት ክርስቲያን ማህበር አርቲስት ሸዋፈራው ደሳለኝን የክብር አምባሳደር አድርጎ መረጠ።

አርቲስት ሽዋፈራሁ ደሳለኝ እንዲህ አይነት ወጣቶች ላይ የሚሰራ እና ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ ከፍተኛ ፍሬ በማምጣት በጎ ተፅእኖ በመፍጠር እየተንቀሳቀሰ ካለ ተቋም ጋር በመስራቴ እኔም እድለኛ ነኝ ብሏል።
የአምባሳደርነት ስምምነቱ ለ2 አመት ይቆያል።

የኢትዬጲያ ወጣት ክርስቲያ ማህበር /E.Y.C.A  21ኛ ዓመት የወጣቶች ምስጋና በዓል ''ታሪክ ሰሪ ትውልድ" በሚል መሪ ቃል ሃምሌ 5 ቀን 2017 በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል።

ማህበሩ ያለፉትን 20 ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ከፍተኛ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ለብዙ ነፍሳቶች በክርስቶስ አምነው መዳን ምክንያት መሆኑን በመግለጫዉ ተጠቅሷል።

ከ450 ተማሪዎች በላይ የሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጆችና የሞያ ተቋማት እንዲያገኙ መደረጉ የተጠቀሰ ሲሆን በተለያዩ ማረሚያ ቤቶችና ዩኒቨርስቲዎች በመንቀሳቀስ ማህበራዊ ግዴታውን ሲወጣ ቆይቷል።

በመግለጫዉ በሃምሌ 5 በሚሊኒየም አዳራሽ፡ 2025 ''ታሪክ ሰሪ ትውልድ'' በሚል መሪ ቃል ታላቅ የምስጋና በዓል እና የወንጌል መልዕክት ፕሮግራም መዘጋጀቱ ተነግሯል።

አርቲስት ሸዋፈራሁ ይህ ጉዳይ የሁሉም ሰው በመሆኑ በከፍተኛ ችግር ያለውን ህዝባችንን መርዳት እና ትውልዳችንን በወንጌል መታደግ ስራ ላይ  ነፃ አገልግሎት በመስጠት ሁሉም ባለው ነገርና አቅም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

ማህበሩ ያለፉትን 20 ዓመታት ወጣቱን ማዕከል ያደረገ ከፍተኛ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ለብዙ ነፍሳቶች በክርስቶስ አምነው መዳን ምክንያት እንደሆነ ተነስቷል።
5👍1
"በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል" - ፓስተር ጻድቁ አብዶ

መጽሃፉ፡ የበኩር መጽሃፋቸው ሲሆን፡ መነሻ ያደረገው በመድረክ ላይ ያስተምሩ ከነበረው የትንቢተ አብድዩ መጽሃፍ የተወሰደ ነው። በቅርብ ወዳጆች ጥያቄ መሰረት በመጽሃፍነት እንዲቀመጥ ተጠይቀው እነሆ ለህትመት በቅቷል።

"መንታ ወንድማማች ስር በሰደደ ጸብ ምክኒያት አንዱ ሞተ፡ አንዱ ተሰደደ። በትውልዳቸው ጥላቻ ስር ሰደደ። ኤዶማዊያን እና እስራኤላዊያን፡ ኤሳው እና ያዕቆብ። በቂም ምክኒያት ኤዶማዊያን ዛሬ የሉም፡ እስራኤላዊያን ስር ሰደዋል።

ከዚህ ታሪክ፡ ይቅርታ እና ምህረትን እንድናደርግ መጽሃፉ ይሞግታል። የቂም እና ክፋት መንገድ ወደ ጥፋት ያደርሰናል። መጽሃፉ በእግዜብሔር ቃል ከክፋት ወደ ቀናነት እንድንመለስ የሚያስተምር ነው።

መጽሃፉ ለአብያተ ክራቲያናት፡ በቀል ይቅር የተባለ ሰው ባህሪ አይደለም። አማኞች በምህረት ያለን ነን። ስለዚህ በቀል ከክርስቲያናዊ አኗኗር ትውቃራኒ ያለ ነው። ይቅር አለማለት እራስን መውደድ እና ጨካኛነት ነው። ከአዙሪት እንዴት እንውጣ፡ የሚል መልስ ይዟል።

መጽሃፉ ሃገራዊ እና ወቅታዊ ጉዳዮቻችንን እንድንቃኝ ያበረታታል። በ150 ገጾች የተዋቀረ ነው።

እሁድ ሰኔ 8፡ 2017 ዓ.ም አድዋ መታሰቢያ አዳራሽ ይመረቃል። በእለቱ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በተገኙበት ይመረቃል። ክርስቲያኖች በስፍራው ተገኝተው አብረው እንዲመርቁ ጥሪ ቀርቧል።

በመግለጫው ስለ ርዕሱ ያብራሩት ጸሃፊው "በነብዩ አሞጽ እንደተነገረ፡ በባቢሎን ግዞት ዘመን እስራኤላዊያን በኤዶማዊያን ለመጥፋት ተቃርበው የነበረ ቢሆንም፡ በነብዩ አብድዩ አፍ ደግሞ እንዴት እንደጠፉ ያሳያል።" ብለዋል።

የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ዝርዝሩን ወደ እናንተ አደረስንላችሁ።

ግንቦት 28/2017ዓ.ም
በኦቦሌሳ አዶላ
9👍1🔥1
ቤተክርስቲያን ለቤተሰብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥታ መስራት አለባት ተባለ።

ይህ የተባለዉ የጌጃ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን የባለ ትዳሮች ቃል ኪዳን ማደስ ፕሮግራም ባደረገችበት ወቅት ነዉ።

መርሃ ግብሩ ላይ የአጥቢያ ቤተክርሲያኒቱ መስራች አባላት፣ አገልጋዮችና መሪዎች የነበሩት አቶ ማሞ ገ/መስቀል ጋሽ ሽፈራው ወልደ ሚካኤል፣ ወንጌላዊት ቀለሟ ሃይሌ፣ የወቅቱ የአጥቢያ መሪዎች፣ አገልጋዮች እና ባለትዳሮች ከትዳር አጋሮቻቸው ጋር ተገኝተዋል።

የቤተክርስቲያኒቱ የጋብቻ ማማከር አገልግሎት ለባለትዳሮችና ላልተጋቡ ወጣቶች ሥልጠናዎችን በመስጠት ተግታ እየሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

መርሃ ግብሩ ለረጅም ጊዜ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ እንደሆነ የገለጹት የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች እና የመርሃ ግብሩ ታዳሚያን ቤተክርስቲያን ለቤተሰብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥታ መስራት እንዳለባት አሳስበዋል።

የቃል ኪዳን ማደስ ሥነ-ሥርዓቱን የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መጋቢ የሆኑት መጋቢ ተስፋዬ ገመቹ “እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ኪዳኑን ያስባል፤ ከሕዝቡ ጋር ያለውም ትስስርም ከኪዳኑ ግንኙነት የሚመነጭ ነው” በማለት ከባለቤታቸው ከወ/ሮ መዓዛ መኩሪያ ጋር በመሆን ስርዓቱን መርተዋል።

በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ ከ65 አመታት በላይ በትዳር የቆዩ ጥንዶች እና በቅርቡ የተጋቡ አዳዲስ ሙሽሮች ኬክ ቆረሳ ያደረጉ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የአንድነት ጌዜ እንደነበራቸው ታውቋል፡፡

የቤተክርሲቲያኒቱ ሰብሳቢ የሆኑት ፕሮፌስር ብርሃኑ ቆጢሶ ሕዝቡን በፀሎት የባረኩ ሲሆን ዘማሪት ሃና ተክሌና ዘማሪ አድነው ዓለሙ በዝማሬ አገልግለዋል።

ጋሽ ሽፈራው ወልደ ሚካኤል በበለጠ ተስፋ፣ በበለጠ እምነትና በአንድነት በመያያዝ እግዚአብሄርን በታመነ ሕይወት ለመኖር ልትበረታቱ ያስፈልጋል በማለት የእግዚአብሄር ቃል መልዕክት አካፍለዋል።

በሮማን ከሊል
4👏3❤‍🔥1
#የእግር #ኳስ #ዜና #አይደለም

ሶስት የፈረንሳይ ሊግ ተጨዋቾች #ግብረሰዶማዊነትን #በመቃወማቸዉ ቅጣት ተጣለባቸው

የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ (ኤልኤፍፒ) የዲሲፕሊን ኮሚቴ በሶስት የፈረንሳይ ሊግ 1 ተጫዋቾች ላይ ቅጣት ጥሏል።

የሊዮኑ ተጨዋች ኒማንያ ማቲች ፣ የሌንንሱ ተጨዋች ጆናታን ግራዲት ፣ እና ለሌ ሃቭሬ የሚጫወተዉ አህመድ ሀሰን በጸረ-ግብረ ሰዶም ቀን የግብረሰዶማውያን ባንዲራ ያለበትን አርማ ባለማድረጋቸዉ "ጥላቻ" በተሰኘ ተግባራቸዉ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።

ጆናታን ግራዲት አንድ ጨዋታ ኒማንያ ማቲች እና አህመድ ሀሰን ሁለት ጨዋታዎችን እንዲቀጡ ተብሏል።

በፈረንሳይ ሊግ በተጨዋቾች እጅጌ መለያቸዉ ላይ የግብረ ሰዶማውያን መለያ አርማ ቢለጠፍም ኒማንያ ማቲች አርማዉን በፕላስተር ሸፍኖት ታይቶ ነበር። በዚህም ድርጊቱ ለሁለት ጨዋታ እንዲቀ ወስነዉበታል።

በተጨማሪም የፈረንሳይ እግር ኳስ ግብረሰዶማዉያን ላይ ሰራዋለሁ በሚለዉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ላይ እንዲሳተፍ ታዝዟል።

ዳጉ ጆርዳል እንዳስነበበው
👍10👏32🔥1
ጆሽዋ፡ በአሜሪካን ሃገር በ2021 ህይወቱ ያለፈ ታዳጊ ልጅ ነው። በለጋ እድሜው ወንጌልን ለእኩዮቹ መስበክ ጀምሮ ነበር።

አሁን ጆሽዋ ወደሚወደው ጌታ ቢሄድም፡ ቤተሰቦቹ በርሱ ስም Joshua Keep Shining የተሰኘ ፋውንዴሽን አቋቁመዋል።

ከዴንቨር ኮሎራዶ አሜሪካ የተነሳው ፋውንዴሽኑ፡ ታዳጊዎች በወንጌል እንዳያፍሩና ወንጌል እንዲሰብኩ ይሰራል። ከዚህ በተጨማሪ የማህበረሰብ አገዝ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ጆሽዋ በትንሽነቱ ወንጌል የመስበክ ልብ የነበረው ልጅ ስለነበረ፡ ምንም እንኳን ወደ ጌታ ቢሄድም የልቡን መሻት ግን በዚህ ፋውንዴሽን በኩል እዉን እናደርጋለን ሲትል እናቱ ፋሲካ ለክርስቲያን ዜና ሃሳቧን አጋርታለች።

እስካሁን ከ6 አበያተ ክርስቲያናት ጋር እየሰራ ያለ ሲሆን፡  በእነዚሁ አብያተ ክርስቲያናት የታዳጊዎች የወንጌል ስርጭት ቡድኖች ተቋቁሟል።

ወንጌላዊት አልማዝ ከካውንስሉ ተገኝተው፡ ዛሬ እንደተሰራው የወንጌል ስራ ነገ በደንብ ሂዱና ወንጌል ስበኩ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጆሽዋ ዛሬ ለጀመረው ስራ እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን ብለዋል።

በወንጌል ስርጭት ዘመቻው የተሳተፉ አብያተ ክርስቲያናት፡ ሚኒስትሪዎች እና ግለሰቦች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

በኦቦሌሳ አዶላ
9👍1
በብራዚል የወንጌል አማኞች ቁጥር ሲጨምር በአንፃሩ የካቶሊክ #እምነት ተከታዮች ቁጥር እየቀነሰ ነው።

የዓለማችን ትልቁ የሮማ ካቶሊክ መኖሪያ በሆነችው ብራዚል በ2022 የካቶሊክ ህዝብ ቁጥር እየቀነሰ ሲሆን በአንፃሩ የወንጌላውያኑ ክርስቲያኖች እና ምንም አይነት ሃይማኖት የሌላቸው #ሰዎች #ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የስታስቲክስ ኤጀንሲ ባወጣው የህዝብ ቆጠራ መረጃ ያሳያል።

ቆጠራው እንደሚያመለክተው በ2022 ብራዚል 100.2 ሚሊዮን የሮማ ካቶሊኮች አማኞች ወይም ከሀገሬው ህዝብ 56.7% የሚሆነውን #ህዝብ ድርሻ ይዟል። ይህም በ2010 ቆጠራ ከተመዘገበው 65.1 በመቶ ወይም 105.4 ሚሊዮን ያነሰ ሆኗል።

#ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ድርሻ ባለፈው ዓመት ወደ 26.9 በመቶ ከፍ ብሏል፣ በ2010 ከነበረበት 21.6 በመቶ ወይም 12 ሚሊዮን ተከታዮችን በመጨመር ወደ 47.4 ሚሊዮን ደርሷል።

ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጭማሪ ተመዝግቧል። የወንጌል አማኞች ቁጥር መጨመር በብራዚሉ ግራ ዘመም ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ አገዛዝ ላይ ችግር ሊፈጥር ይችላል። ገዢው የሰራተኞች ፓርቲ በወንጌላውያን ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሲታገል ቆይቷል።

በቅርቡ በተደረገ የሕዝብ ቆጠራ እንደሚያሳየው 45 በመቶ ካቶሊኮች የሉላ አስተዳደርን ሲቀበሉ 30 በመቶ የሚሆኑት ወንጌላውያን ብቻ መንግስትን ይደግፋሉ።

በአዲሱ የህዝብ ቆጠራ መረጃ መሰረት ሃይማኖት የለንም የሚሉ ብራዚላውያን ቁጥር ከ7.9 በመቶ ወደ 9.3 በመቶ ከፍ ማለቱን አረጋግጧል ይህም በአጠቃላይ 16.4 ሚሊዮን ህዝብ ደርሷል።

እንደ ኡምባንዳ #እና ካንዶምብል ያሉ አፍሮ ብራዚሊያውያን ሃይማኖቶችም የተከታዮች ቁጥር ከ 0.3 ወደ 1 በመቶ ማደጉን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

በስምኦን ደረጄ
ምንጭ #ዳጉ_ጆርናል
13👍8👏4🔥1🙏1
#ካወንስሉ በከተማው ለሚከናወነው የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት 17 ሚሊየን ብር አሰባሰበ።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካወንስል በስሩ ያሉ የተለያዩ ቤተ እምነቶች በከተማው ለሚከናወነው የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የኢቫንጄሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ (ETC) ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል ፕሬዝደንት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ የእንኳን ደህና መጣቸዉ ንግግር በማድረግ ኤርምያስ 29፡4 ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል በመከፈል ሁላችንም የሃገር አደራ አለብን በዚህ ስራ መሳተፋችን ለትውልድ ትልቅ ነገር ጥሎ መሄድ ነው ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

በማስቀጠልም የካውንስሉ ምክትል ፕሬዝደንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ የዚህ ፕሮግራም አላማ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑን በመግለጽ ተፈጥሮን መንከባከብና መጠበቅ የእግዚአብሔር ትዛዝ ነው። በዚህ ወስጥ ልጆችንን እና አፍሪካን የሚያኮራ ስራ ልንሰራ ይገባል።

አቶ ጥላሁን ወርቁ የወንዝ ዳር ልማት የፕሮጀክትን አላማ በመግለጽ በጸሎታቸው እና በመንከባከብ ፣በመጠበቅ ፣በማስተማር እንዲሁም በገንዘባቸው ከጎናችን እንድትቆሙ ስሉ አሳስበዋል።

በወንድም ጥላሁን ጉግሳ የገንዘብ ማሳሰቢያ ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የተሰበሰበው ገቢ 17 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር መሆን በመድረኩ ተገልጿል።
12👍2🔥1👌1
የሉተራን ወርልድ ፌደሬሽን አመራሮች #የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስን ዋና መሥሪያ ቤት ጎበኙ። 

የLWF ምክር ቤት ዛሬ በአዲስ አበባ የሚጀመር ሲሆን የLWF ምክር ቤት ስብሰባ ከመጀመሩ አስቀድም ፅ/ቤቱን ገብኝተዋል።

የምክር ቤቱ ጭብጥ "ምስክሮቼ ሁኑ" የሚል ሲሆን ከሁሉም የሉተራን ወርልድ ፌደሬሽን ክልሎች የተውጣጡ 48 የምክር ቤት አባላትን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
8👍1🔥1
"በቀል በቀለኛውን ያጠፋዋል" የፓስተር ጻድቁ አብዱ መፅሐፍ እየተመረቀ ነዉ።

የትንቢተ አብድዩ መጽሃፍ መነሻ በማድረግ የተዘጋጀዉ መፅሐፍ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ ወዳጆቻቸዉ በተገኙበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተመረቀ ነዉ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
13👍1👌1
የናይጄሪያ እርሻ ሚኒስቴር ለአገሪቱ የምግብ ዋስትና ሠራተኞቹ ጾም እና ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ

ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናን እንድታረጋግጥ ፈጣሪን ለመማጸን ፆም እና ጸሎት እንዲያደርጉ የአገሪቱ የእርሻ ሚኒስቴር ሠራተኞቹን መጠየቁን ተከትሎ ውዝግብ ተፈጥሯል።

በናይጄሪያ እርሻ ሚኒስቴር የሰው ኃይል አስተዳደር ክፍል ኃላፊ አማካኝነት ለመሥርያ ቤቱ ሠራተኞች በተሰራጫው ማስታወሻ የሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ ባልደረቦች ለተከታታይ ሦስት ሰኞዎች በሚካሄደው የተማጽኖ ፆም እና ጸሎት ላይ እንዲሳተፉ ይጠይቃል።

ይህ ዜና መውጣቱን ተከትሎ አንዳንድ ናይጄሪያውያን መንግሥታቸው በአገሪቱ እያነረ ያለውን የምግብ ዋጋ እንዲቀንስ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ በመክተት ተችተዋል።

የፆም ጸሎት ጥሪው መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ የናይጄሪያ እርሻ ሚኒስቴር ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ ማስተባበያ ሰጥቷል።

ጥሪው በአገሪቱ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍ ጸሎት የመንግሥት ይፋዊ ፖሊሲ አለመሆኑን አመልክቶ፣ ነገር ግን ጸሎቱ የሠራተኞችን ደኅንነት ለማዳበር ነው ብሏል።

ሙሉዉን BBC AMHARIC ላይ ያንብቡ
10👍3🔥1🥰1
የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ከታሪካዊ እርቅ በኋላ አዳዲስ አመራሮች መረጡ።

የጋሞ ዞን እና የአርባ ምንጭ ከተማ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በውስጥ አለመግባባቶች ለአራት ዓመታት የዘለቀውን ክፍፍል በእርቅ ተቋጭቶ አዳዲስ አመራሮችን መርጠዋል።

በታህሳስ 9, 2013 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ክልል ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ምስረታ ምክንያት በጋሞ ዞን እና በአርባምንጭ ከተማ ወ/አ/ክ የቀድሞ አመራሮች እና በዞኑ እና በከተማዉ ህብረት መሪዎች የነበረዉ አላማግባባት ለሚመከተዉ ባለድርሻ አካል ቅሬታ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ሳይፈታ መቆየቱ በወንጌል እንቅስቀሴ ላይ እና በወንድሞች ህብረት ላይ ትልቅ ጫና ፈጥሮ ቆይቶል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃድቁ አብዶ እና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጽ/ቤት ሃላፊ መጋቢ ጌትነት ለማ በጥር 15/17 አራት የእርቅ አመቻት ኮሚቴ የሰየሙ ሲሆን አመቻች ኮሚቴው በዞኑ እና በከተማዉ የነበረዉን የቀድሞን ፍቅር እና ህብረት ለመመለስ ከፍተኛ ጥራት በማድራግ ሰኔ1 እርቅ ስምምናት መደረጉ ተገልጿል።

በቀድሞ አመራሮች እጅ የነበረዉ የህብረቱ የንብረት እርክክብ ያደረገ ሲሆን የክልሉ ም/ፕሬዝደንት መጋቢ ወንድማገኝ አስፋ በመገኘት ንብረቱን የመረካካብ ሥርዓት ማስፈጸማቸው ይታወሳል።

ሰኔ 07/17 በክልሉ ፀሐፊ ዶ/ር ማርቆስ አቢሶ መሪነት የተካሄደው ምርጫ በመስራች አብያተ ክርስቲያናት መካከል እርቅን የፈጠረ አዲስ ጅማሬ እንደሆነም ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ወ/ም ቹቹ ቹርኮ የጋሞ ዞን ወ/አ/ክ/ ህብረት ሰብሳቢ እና ወ/ም ደፋርሼ ሻንካ የአርባ ምንጭ ከተማ ወ/አ/ክ/ህብረት ሰብሳቢ ተደርገው ተመርጠዋል።
4👍2🔥1