#ፍቅርን እንተክላለን #ምህረት እናደርጋለን #ሰላምን እናጭዳለን!
የመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የሰላም ግንባታ አገልግሎት በደቡብ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች በኮንሶ፣ አሌ፣ ቡርጂና ደራሼ አዋሳኝ ቀበሌዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ከሁለት አመት በላይ በአካባቢው እየሰራ ይገኛል።
በተለይ በዞኖቹ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ሰላምን ለመገንባት ለሀገር ሽማግሌዎች፤ ለሐይማኖት አባቶች፤ ለሴቶች፤ ለተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለተለያዩ የመንግስት አካላት ስልጠናዎች ሲሰጡ ቆይተዋል።
ቤተክርስቲያኒቱ በትላንትናው ዕለትም በማህበረሰቡ መካከል አብሮነትን ለማጠናከር ከኮንሶ እና አሌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያዎች ጋር በመተባበር "ፍቅርን እንተክላለን! ምህረት እናደርጋለን! ሰላምን እናጭዳለን!" በሚል መሪ-ሃሳብ በሁለቱም ዞኖች ባሉ አዋሳኝ ወረዳዎች በሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዳለች።
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ግንባታ መምሪያ ዳይሬክተር መምህር መኮንን ገመዳ ሰላም ሁለንተናዊ እንደመሆኑ መጠን ችግኝ በመትከላችን የአየር ንብረቱን ከመጠበቅ ባለፈ ሰላምን እንገነባለን ሲሉ አክለውም ይህን #ችግኝ ስንተክል የትላንትናውን ረስተን ነገን እያሰብን_ፍቅርን_የምንተክል_ሊሆን_ይገባል በማለት ለተሳታፊዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ስለ ሰላም እየሰራች መሆኑ ይታወቃል።

👍5🔥3❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#በቃን_እንመለስ
#ሀገራዊ የንስሐ ጥሪ
ሀገራዊ #ንስሐ ለሀገራዊ ፈውስ በሚል መሪ አሳብ
ለአንድ አመት በብዙ ዝግጅትና ልዮ ልዮ የንስሐ መርሃ ግብሮች ሲካሄድ የነበረው የሀገራዊ ንስሐ ሂደት ማጠቃለያ ጉባዔ ከአዲስ አበባ፣ ከክልል አብያተ ክርስቲያናት ከሃምሳ በላይ ከተሞች የሚወከሉ፣ እንዲሁም ከዲያስፖራ በሚታደሙ መሪዎች፣ አገልጋዮችና ማላጆች በአዲስ አበባ ከሰኞ ግንቦት 25 እስከ ረቡዕ ግንቦት 27 ይካሄዳል።
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ለባለድርሻ አካላት በውክልና #ንስሐ የሚገቡበት ጊዜ ይሆናል።
ቦታው በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:00 በየቀኑ ይካሄዳል።
አገልጋዮች
ዶ/ር ጆን ሙሉንዲ ከዮጋንዳ
ቄስ ዶ/ር ቶለሳ ጒዲና ከአሜሪካ
ፓስተር ዘካሪያስ በላይ ከእስራኤል
ዘማሪዎች
ዘማሪ ጌታ ያውቃልና ብሩክታዊት
ሌሎችም ያገለግላሉ።
የሀገራዊ #ንስሐ አስተባባሪ ኮሚቴ

❤13🔥2👏1
በናይጄሪያ 42 ክርስቲያኖች #ተገደሉ
በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ታራባ በተባለች ግዛት ውስጥ በሶስት መንደሮች ውስጥ ነው ግድያው የተፈጸመው። ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁ የፉላኒ ጎሳ አባላት መሆናቸው ተነግሯል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በሰሜን ናይጄሪያ ክርስቲያኖችን ብቻ ትኩረት ያደረገ ጥቃት በስፋት እየተፈጸመ ይገኛል።
ኦፕን ዶርስ ዋች ሊስት በ2025 ናይጄሪያ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር በመሆን 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጣለች። ይሁን እንጂ ክርስትና በናይጄሪያ እየተስፋፋ ይገኛል።
በ2000 ዓ.ም ከነበረበት 60 ሚሊዮን በ2020 ወደ 96ሚሊዮን አድጓል። በ2050 ወደ 155 ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ ይገመታል።

👏12💔6❤5😭4🕊3🥰1
ለክርስቲያን የሚዲያ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናዉ ወንጌል በማድረስ ሂደት የክርስቲያን የሚዲያ ባለሞያዎች ሚናን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ አዘጋጆቹ በመድረኩ ጠቅሰዋል።
በቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን የተዘጋጀዉ እና የክርስቲያን ሚዲያ ባለሞያዎችን አቅም ለማሳደግና ወንጌል በማስፋት ሂደት ድርሻቸውን እንዲወጡ ያስችላል የተባለዉ ስልጠና በኢንተርኔት ወንጌል መስራት እና የዜና ዝግጅት ከክርስቲያን አውድ አንጻር የሚል ሃሳብን ይዟል።
አለም በቴክኖሎጂ እየፈጠነች ባለችበው በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ትውልድን ለመናጠቅ እና ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለማስገባት ዘመኑ የሚጠይቀውን አውድ በመጠቀም ብዙዎችን ተደራሽ በማድረግ ታላቁ ተልዕኮን ለመወጣት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በስልጠናው ተጠቅሷል።
በስልጠናው የክርስቲያን ዜና ማሕበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎችን ጨምሮ በተለያዩ የክርስቲያን ሚዲያዎች እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች የክርስቲያን ይዘቶችን የሚሰሩ ከ60 በላይ ባለሞያዎች ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን በተቁም ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
በዮሐንስ ግርማ

❤4👏2🔥1
የተከበራችሁ ተመልካቾቻችን live ላይ ነን እየደወላችሁ ተሳተፉ ...
0997282923
0911407499
https://www.youtube.com/live/FuU0KGz6YNQ?si=XRwMY5aVV4QDnuxJ

YouTube
ርሆቦት የህይወት መንገድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን | የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም
#ልትወረስ_15_ቀን_ለቀራት_ቸርች 😭🥺 ሁላችንም የ500 ብር ቻሌንጅ በመቀላቀል ቤተክርስቲያንን እንታደግ።
የቤተክርስቲያኒቱ የሂሳብ ቁጥር ርሆቦት የህይወት መንገድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን https://gofund.me/c75b64c9
ንግድ ባንክ ፥ 1000685337391 አቢሲንያ ባንክ ፥ 220 466 655 ብርሃን ባንክ ፥ 1600420110376 አዋሽ ባንክ ፥013521542623700 ኦሮምያ ህብረት…

❤4👍1
#አስቸኳይ_የፀሎት_ጥሪ😭🙏 ሌላ ካንሰር ተገኘባት😭
( ✍️ አቤል ደመላሽ )
በጣም አሳዛኝ ነገር ተሰምቷል።
እህታችን የምስራች ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር በተዓምራት ተፈውሳ እግዚአብሔርን እያመሰገንን መቆየታችን ይታወሳል ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰ ር ተገኝቶባታል።
ከባድ ሳል ታክሎበት በፍጥነት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ ተደርጓል።
አሁንም ተስፋዋ እግዚአብሔር ነውና ጣልቃ እንዲገባላት ሁላችሁም እንድትፀልዩላት ጥሪ አናቀርባለን።
( ሁላችሁም ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ🥺) 🙏🙏🙏

😭12💔8❤2
"የወንጌል ሰባኪን ሥራ ስሩ - ወንጌልን ስበኩ አትፍሩ" ሪቨረንድ ፍራንክሊን ግርሃም
የቢሊ ግርሃም አሶሴሽን ፕሬዝደንት ፍራንክሊን ግራሃም በበርሊን የአውሮፓ የወንጌል ስርጭት ኮንግረስ ከመዘጋቱ በፊት ለተሰብሳቢዎች "የወንጌል ሰባኪን ሥራ ስሩ - ወንጌልን ስበኩ አትፍሩ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
እሳቸው ንግግራቸውን ሲቀጥሉ “አትደራደር፤ በርታ አገልግሎትህን ፈጽም፣ መከራ እንደሚኖር እናውቃለን፣ ፈተናዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን፣ አንዳንድ ግጭቶችም እንዳሉ እናውቃለን፣ ነገር #ግን እንበርታ #እና እንደሚመለስ የምናውቀውን አዳኛችንን እንስበክ ብለዋል።
ኮንግረሱ እንደተጠናቀቀ ከ1,000 ለሚበልጡ የክርስቲያን መሪዎች በመጸለይ አብረውን እንዲጸልዩ #ጥሪ በማቅረብ ወደ ትውልድ አገራቸው ሲሄዱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለሚያገኟቸው #ሁሉ በድፍረት ለማወጅ #እግዚአብሔር ኃይል እንዲሰጣቸው ጸልየዋል።

❤13👍2🔥1
ካምብሪጅ አካዳሚ ሁለተኛ ቅርንጫፉን በሐዋሳ ከፈተ
"Hawassa International School" የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ፡ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ መኩሪያ ማርሻዬ፡ የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሃፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ፡ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተ ክርስቲያናት እና ቢዝነስ መሪዎች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።
ግንባታው 8 ወራት የፈጀ ሲሆን፡ 300 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል። ትምህርት ቤቱ በሙሉ አቅሙ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስተማር ይችላል።
በቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ የተቋቋመው ካምብሪጅ አካዳሚ ኢትዮጵያ የመማር ማስተማር ካሪኩለሙን በኢንግሊዝ ሃገር መልኩ የሚሰጥ ነው።
ካምብሪጅ አካዳሚ በአዲስ አበባ ቀድሞ በከፈተው ትምህርት ቤት ተቀባይነት ማግኘቱ ይታወሳል።

❤15🥰2👍1
የ#2028 የአለም አቀፍ የአናባብቲስት አዘጋጅ #መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን #ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በየስድስት አመቱ የሚካሄደውንና በመላው አለም የሚገኙ የአናባብቲስት ቤተሰቦች የሚሳተፉበትን ጉባኤ እኤአ በ2028 በኢትዮጵያ እንድታዘጋጅ ከአመታት በፊት ተመርጣ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
ሰሞኑን በጀርመን በተካሄደው የሜኖናይት አለም አቀፍ ኮንፍረንስ 100ኛ አመት ክብረበዓል ላይ የተገኙት የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን መሪዎች የበዓሉን ታዳሚዎችና በመላው አለም የሚገኙ የአናባብቲስት ቤተሰቦች ከሶስት አመት በኋላ በኢትዮጵያ በሚደረገው ጉባኤ ላይ እንዲገኙ በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዝደንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በኩል በይፋ ግብዣ አቅርበዋል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ይህን አለም አቀፍ ጉባኤ በደማቅ ሁኔታ ለማዘጋጀት ሀገር አቀፍ የአማካሪ ኮሚቴ ሰይማ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።

❤7🔥1👏1👌1
በካዉንስሉ ፕሬዝደንት የተፃፈዉ "የመሪ ባሕሪያት መሰረታዉያን" የተሰኘዉ መፅሐፍ ተመረቀ።
በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካዉንስል ፕሬዝደንት በዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ የተፃፈዉ እና በ2 ክፍሎች እና በ4 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ200 ገፆች የተዋቀረዉ መፅሐፍ የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ፣ የፀሐፊዉ ወዳጆች እና ጥሪ የተደረገላዉ እንግዶች በተገኙበት በዘፀዓት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን በድምቀት ተመርቋል።
በመድረኩ ዶ/ር ወርቁ የመፅሐፉን ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን በንግግራቸው ዶ/ር ጣሰው መሪነት በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መጠቀሱን አንስተዉ ባለአደራነት ፤ ጥበብ እና የእግዚአብሔር ቃል የጎደለዉ መሪ ለተቋማት መውደቅ ለአመራት ክፍተት እንደሚፈጠር በመጥቀስ ይሞግታሉ ሲል አንስቷል።
ፖስተር ፃዲቁ አብዱ በበኩላቸው በመሪነት ደረጃ ላሉት ብቻ ሳይሆን ወደ መሪነት ለማደግ ለሚሄዱትም ጠቃሚ የሆነ መጽሀፍ በመሆኑ ሁሉም ሊያነቡት እንደሚገባ መክርዋል።
የመጽሀፊ አዘጋጅ ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ መፅሐፍ ቅዱሳችን እራሱ መሪነትን በየአዉዱ በመከፋፈል የሚያስቀምጥ መሆኑን በመጥቀስ ለአንድ መሪ ባሕሪ መሰራት እና የመሪዎች የበሃሪ ተግዳሮት መስተዋሉ ይህንንም ችግር ለመቀነስ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ለማበርከት መጽሀፉን እንዳዘጋጁት ተናግረዋል።
ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ ይህ 3ኛ መፅሐፋቸዉ ሲሆን ከዚህ ቀደም "የመሪ ፈተናዎች ፤ስህተቶች እና መፍትሄዎቹ" እንዲሁም "ክዋኔ የትግበራ ክህሎት" የተሰኙ ሁለት መፅሐፍትን በ2013 ዓ.ም ለንባብ ማብቃታቸዉ ይታወሳል።
በመድረኩ ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል የእግዚአብሔርን ቃል በማካፈል አቤኔዘር ለገሰ በበኩል ዝማሬ በማቅረብ አገልግለዋል።
የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መረሃ ግብሩን ተከታትለን ዝርዝሩን ወደ እናንተ አቀረብንላችሁ።

❤5👍1👏1
19 ነብሳት #ወደ #ጌታ መንግስት ተጨምረዋል።
#በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ምዕራብ ደቡብ ቀጣና ቦንጋ ዙሪያ ሕብረት በቦባ ገጫ ቃ/ሕ/ቤ/ያን #እና ከሁለቱ ተከላ ጣቢያ በጌታ አምኖ የደህንነት ትምህርት እየተማሩ የቆዩ የውሃ ጥምቀት ወስዷል።
#በክርስቶስ #ኢየሱስ አምኖ በቤተክርስቲያን የሚሰጠውን የደህንነት ትምህርት በመማር #በቁጥር 19 የሚሆኑ ሰዎች የውሃ ጥምቀት ስነ-ስርዓት ወስዷል።
መረጃውን ከስፍራው The Christian News - የክርስቲያን ዜና አደረሱን!!!

❤13👍1👏1
#አሳዛኝ #ዜና 😭😭 #ወደ #ጌታ ሄደች።
ዘማሪት የምስራች ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወደ ጌታ ሄዳለች።
እህታችን የምስራች ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር በተዓምራት ተፈውሳ እግዚአብሔርን እያመሰገንን መቆየታችን ይታወሳል ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰር ከባድ ሳል ታክሎበት በፍጥነት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ የተደረገች ቢሆንም ከደቂቃዎች በፊት ወደ ጌታ መሄዷ ታዉቋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና እግዚአብሔር ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንዲያደርግ እንመኛለን።

😭38💔12🕊1
ለመጋቢ እና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ እውቅና ተሰጣቸው።
እውቅና የሰጣቸው ተቋም የኢቫንጄሊካል ቴዎሎጂካል ኮሌጅ ሲሆን "አዎን ይሆናል" በሚል በሁለት ቋንቋዎች የተዘጋጀው የመዝሙር ስንዱቅ መጽሐፍ በተመረቀበት ወቅት ነው።
በቀድሞ የወንጌላውያን ቴዎሎጂ ኮሌጅ ተማሪ በሆነው አቶ ጥበበ አክሊል የተዘጋጀው የፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ ቁጥር 8 የመዝሙር ስንዱቅ መጽሀፍ በትላንትናው እለት በETC ተመርቋል።
በመድረኩ ይህንን መጽሐፉ ማዘጋጀት ያስፈለገበት አላማ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት አገልጋዮች ዘንድ ያለውን መንፈሳዊ ምልከታ፣ አስተምህሮና አቋም ማጥናት ለሚፈልጉ የውጪ ዜግነት ያላቸው የስነ መለኮት ተመራማሪዎች ጥቅም ላይ እንዲወል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
በትርጉም ስራው ላይም ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶን ጨምሮ 4 የተለያዩ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን አቶ ጥበበ አክሊሉ በስንዱቅ 8 የተዘመሩ 13 መዝሙሮችን በእንግሊዘኛ እና ፈረንሳይኛ በመተርጎም ለአንባብያን አቅርበዋል።
ወንድም ጥበበ አክለዉ ላለፉት 35 ዓመታት በመዝሙሮቹ ብዙ ሰለተባረኩባቸው የሌላ ሀገር ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በፈረንሳይኛና በእንግሊዝኛ ለመተርጎም ጥረት ማድረጋቸዉን አንስተዉ የተተረጎሙት መዝሙሮች በሌላ ቋንቋ መዘመር ሊያሰቸግር ይቻላል ግን የመዝሙሮቹን መልዕክቶች በማጥናት አትራፊ መሆን እንደሚችል ገልጸዋል።
መጋቢ ተስፋዬ በበኩላችው መንፈሳዊ ዝማሬ ፣በአምልኮ ፣በወንጌል ሥርጭት አማኞችን በማስተማር ረገድ የራሱ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰው በሀገራችን የተዘመሩ መዝሙሮች መጽሐፍ ቅዱሳዊና ሥነ-መለኮታዊ ይዘት ካሰተዋሉ በኋላ በዜማ እንኳን ቢቀር ቃላቱ በወጪ ሀገር ቋንቋ ቢተረጎም ለአንባቢያን እንዳች መልዕክት ሊያስተላልፋ ይችላል ብለዋል።
መፅሐፍ ለETC ሙሉ በሙሉ ተሰጥቷል።
በቤተልሔም ደረጀ

❤24👍8🥰2🔥1👏1
💍✨ የመጨረሻው ዝግጅት : የአጮኝነት ስልጠና✨💍
🔹ውስን ስፍራ፦ ለ20 ጥንዶች ብቻ!
ለምዝገባ የቀረን 3 #ቀን ብቻ ነው
ፈጥናችሁ ተመዝገቡ!
በቃልኪዳን የጋብቻን ጉዞ ከመጀመራችሁ ፊት በቂ ቅድመ-ዝግጅት ማድረግ ብልህነት ነው። "የመጨረሻውን ዝግጅት " ለማድረግ በዚህ የእጮኛሞች ስልጠና ተሳተፉ እና ለዘላቂና ጣፋጭ ትዳር መሰረት ለመጣል የሚረዷችሁን ግብዓቶች ሸምቱ።
📅 ቀን፦ግንቦት 30/June 7
📍 ቦታ፦ አለም ጋለሪ ገርጂ ታክሲ ተራ
💰 መመዝገቢያ Fee፦ለጥንዶች 1200፣ ለአንድ ሰዉ 650ብር ብቻ!
በነገ ህይወታችሁ ላይ ዛሬ ለመዝራት ቦታ ሳያልቅባችሁ ተመዝገቡ!
ወዳጅ ቤተሰብ! ስፖንሰር በማድረግ ለሠርጋቸው ስጦታ በመስጠት ለነገ ህይወታቸው የየድርሻችሁን ተወጡ።
አገልጋዮች ፦
👉ጌቱና ማህደር፦ የሰማይ ፋሚሊ አዘጋጆች
https://www.youtube.com/watch?v=Y6CushnHTrg
👉ሳሮን ውድነህ፦ የጋብቻ አስተማሪ እና አማካሪ
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
ለመመዝገብ፦https://forms.gle/EKtmd52XMHF1612CA
ለበለጠ መረጃ፦ 0911136520/0911642595

❤6👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በበርሊን ለተሰበሰቡ ወንጌላዊያን መሪዎች ያስተላለፉት መልዕክት ምንድነው?
“አዲስ አለም አቀፍ ተልዕኮ” ያስፈልጋል ሲሉ ነው በበርሊን በተካሄደው የ2025 ወንጌላዊያን ኮንግረስ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፉት።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ወንጌል ከግል ጉዳይ ይበልጣል፣ ማህበረሰብን የመቀየር አቅም አለው” ብለዋል።
ጥልቅ የመንፈሳዊ መታደስ ላይ ትኩረት ባደረገው አዲስ ተልዕኮ ባሉት እቅድ መሰረት “ዘላቂ ለውጥ ከውስጥ ይጀምራል” ብለዋል።
“ከዘር፣ ከሃይማኖት ትምህርት እና ሌሎች መከፋፈሎች ባለፈ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመመለስ” ፍቅርን እንቀበል ሲሉ ለአውሮፓዊያኑ ወንጌላዊያን መሪዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሙሉውን ፌስቡክ ላይ ያንብቡት
👇👇👇
https://www.facebook.com/100063892396728/posts/pfbid0V4hHKCAwLMPQ5on67caZwTLUgTBN6MQbWm17PVdSZPcKFoy4rKriYnKwwLUASb3El/?app=fbl

👍11🔥6🤷♂4❤4🥰2🙏1