The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የአምቦ መካነ ኢየሱስ የአምልኮ ህንጻ ተመረቀ

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አምቦ ማህረ ምዕመናን አዲስ የአምልኮ ህንፃ ተመረቀ።
ከተተከለች 50 ዓመታትን ያስቆጠረችው የአምቦ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ፡ የቤተ ክርስቲያኗ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ በተገኙበት ተመርቃለች።

ቤ/ክኗ ለወንጌላዊያን የስደት ዘመን በነበረበት 1975 ዓ.ም ጀመራ የምስራቹን ወንጌል ስታገለግል የቆየች ናት። በነዚህ ጊዜያት በርካታ ማህበረ ምዕመናንን እና የስብከት ጣቢያዎችን በመትከል ወንጌል ስታዳርስ ቆይታለች።
12👍4🔥1
#ጥንቃቄ

ከግንቦት 16 እና 17 የሚደረገው ፕሮግራም በቅድሚያ መስቀል አደባባይ ተብሎ ነበር የተሰራው ነገር ግን ቦታው በሌላ ፕሮግራም ስለ ተያዘ ወደ ሀዋሳ ኢንተርናሽናል ስታዲየም መቀየሩ ይታወቃል።

ሆኖም ቀደም ተብሎ የተሰራው የምስል ማስታወቂያ በትልልቅ መንፈሳዊ ቴሌቪዥን በEvangelical, GMM እና በሌሎችም ሚዲያዎች አሁንም ቦታው መስቀል አደባባይ ተብሎ እየተነገረ ያለው ስህተት በመሆኑ ትክክለኛው በአብያተ ክርስቲያናት የተዘጋጀው የንስሃና የምልጃ ፕሮግራም በሀዋሳ እስታዲየም መሆኑን እንዲታወቅ ለሁሉም ይነገር እና ሼር ይደረግ።

#ዛሬ ግንቦት 16 ቅዳሜ ከ9:00 ጀምሮ ሀዋሳ እስታዲየም እንገናኝ።
6🔥2👍1👏1
#የኢትዮጵያ #ሙሉ #ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የሁለት አቅመ ደካማ እማወራ ቤቶችን የማደስ ስራ አስጀመረች።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 የሁለት አቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ የማስጀመር ስራ ላይ የቤተ እምነቷ ፕሬዝዳንት መጋቢ ላኮ በዳሶ፣ ም/ት ፕሬዝዳንት መጋቢ ለወየሁ ስንሻው ተገኝተው ስራውን አስጀምረዋል።

የቤት እደሳው መርሃ ግብር በሁለት ወራት የሚጠናቀቅ መሆኑን በወቅቱ በተሰጠው መግለጫ የታወቀ ሲሆን በቤት ውስጥ የነበሩ ሰዎች ለጊዜው የማረፍያ ቦታ እንዳይቸገሩ የቤት ኪራይ የሚሆን ወጪ በቤተክርስቲያኗ መሸፈኑ ተገልጾአል።

የቤተ እምነቷ ፕሬዝደንት ባደረጉት ንግግር ቤተክርስቲያኗ እንደዚህ አይነት ማህበራዊ ሀላፊነት ማከናወን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ የተከተለና በቀጣይም በማህበራዊ እና በሀገራዊ ልማት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምስጋና እንጅሉ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ይሄን በጎ ሰናይ ተግባር በማከናወኗ ምስጋናቸውን አቅርበው በዚህ አርያነት መከተሏ ቤተክርስቲያኗ ለሌሎችም ምሳሌ የምትሆን ናት ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ዋና ጽ/ ቤት ከዚህ ቀደም በወረዳው የሚመጡትን ልማታዋና ማህበራዊ ጉዳዮች የያዙ ጥያቄዎችን በመቀበል በንቃት በመሳተፍ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ሀላፊነቷን እየተወጣች መሆኑንን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👍93
#አሁን ከሃዋሳ አለም አቀፍ እስታድየም #livestreaming

"ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ" የምልጃ እና የንሰሓ ኮንፍራንስ በሐዋሳ አለም አቀፍ እስታድየም

የሃዋሳ ከተማአቀፍ የተሃድሶ ንቅናቄ

በ Facebook እና youtube በቻናላችን ላይ በቀጥታ ስርጭት ከደቂቃዎች በኋላ ይከታተላሉ። 🙏🙏🙏
👍94🔥1
#አስደሳች #ዜና

የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ለቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲናን ጨምሮ ለ3 መሪዎች እውቅና ሰጠ።

"ኑ ወደ #እግዚአብሔር እንመለስ" በሚል የምልጃ እና የንሰሐ ኮንፍራንስ በሐዋሳ አለም አቀፍ እስታድየም እየተካሄደ ሲሆን በኮንፍራንሱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር መኩሪያ ማርሻዬ ባደረጉት ንግግር #ዛሬ በአንድነት #እና በጋራ በመስራት ሀገራችንን በላባችን እና በመሰዋዕትነት ልናሳድገት ይገባል ያሉ ሲሆን የሃይማኖት እና የብሔር ብዝሃነት ጸጋችንን በመጠቀም ሰላማችንን ለማምጣት እኛ ክርስቲያኖች #ምሳሌ በመሆን ልንኖር ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ለሃዋሳ ከተማችን መለወጥ #ወንጌል ትልቁን ድርሻ እንደሚወስድ በመጥቀስ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የከተማ አስተዳደሩ እና የሲዳማ ክልል ለ4 የወንጌላውያን መሪዎች እውቅና ሰጥቷል።

ኑሮዓቸውን በአሜሪካ ላደረጉት ለቄስ ዶ/ር ቶሎሳ ጉዲና ፤ ለኢትዮያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ለፓስተር ጻዲቁ አብዶ ፤ ለኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ እና ለሃዋሳ ሕይወት ብረሃን ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ፓስተር ጌቱ አያሌው እውቅናው እና ሽልማቱ ተሰቷቸዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ከስፍራው በ Facebook እና youtube ቻናላችን ላይ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፍን ስለሆነ እንድትከታተሉን እንጋብዛለን። https://www.youtube.com/watch?v=tHQFuhBnp5M 🙏🙏🙏
9👍3🔥1
በድል #ተጠናቀቀ #እግዚአብሔር ይመስገን!!!

በሀዋሳ #ኢንተርናሽናል ስታዲየም በግንቦት 16 እና 17 ከተማ አቀፍ የንስሃና የተሃድሶ ፕሮግራም በድል በጥሩ ውጤት ተጠናቀቀ።

“የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ #እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል፤ እናንተም እንቢ አላችሁ፥”
ኢሳይያስ 30፥15

የሲዳማ ክልል ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከየሀዋሳ ከተማ ዞን ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት እና የሲዳማ ክልል ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በጥምረት የተዘጋጀው "ኑ ወደ #እግዚአብሔር እንመለስ" በሚል የምልጃ እና የንሰሐ ኮንፍራንስ በብዙ ድምቀት ተጠናቋል።

በሐዋሳ አለም አቀፍ እስታድየም በተካሄደው ኮንፍራንስ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር መኩሪያ ማርሻዬን ጨምሮ የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የሃዋሳ ከተማ ቅዱሳን በመረሃ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ከስፍራው በ Facebook እና youtube ቻናላችን ላይ በቀጥታ ስርጭት ስናስተላልፍ የነበረ ሲሆን በስፍራው የቀጥታ ሆነው ስርጭቱን እንድናስተላልፍ የፈቀዱልን የፕሮግራሙ አስተባባሪ መሪዎች እና Amanuel Audion Video International Asfaw Ashagre ፤ Yididiya Bethelhem እና ወንድም ዳዊት ከልብ እናመሰግናለን!!!
👍82🙏2🔥1
#እኔ_እያለሁ_ቸርች_አትወረስም...

ልትወረስ 15 ቀን የቀራት ቸርች እናድን
ሁላችንም የ500 ብር ቻሌንጅ በመቀላቀል ቤተክርስቲያንን እንታደግ...
እባክዎ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ
👍141🔥1
#ዛሬ አይቀርም።

#ልትወረስ 15 ቀን ለቀራት ቤተክርስቲያን 😭🥺
ሁላችንም የ500 ብር ቻሌንጅ በመቀላቀል ቤተክርስቲያንን እንታደግ።

የቤተክርስቲያኒቱ የሂሳብ ቁጥር
ርሆቦት የህይወት መንገድ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን

ንግድ ባንክ ፥ 1000685337391
አቢሲንያ ባንክ ፥ 220 466 655
ብርሃን ባንክ ፥ 1600420110376
አዋሽ ባንክ ፥013521542623700
ኦሮምያ ህብረት ስራ ባንክ ፥ 1008100180768

ቴሌ ብር ፥ 0975836154
#ዛሬ ምሽት ለዚህች ቤተክርስቲያን በክርስቲያን ቲዩብ የፌስቡክና የዩቲዩብ ቻናል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እናደርጋለን !
👍64🔥2
ወደ 2ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በአትላንቲክ ባህር ዳርቻ ተጠመቁ

The Church of Eleven22 የተባለች ቤተ ክርስቲያን ናት በአትላንቲክ ውቂያኖስ ዳርቻ በየአመቱ የውሃ ጥምቀት የምታካሂደው።

1958 ሰዎች የተጠመቁ ሲሆን ቤተ ክርስቲያኗ፣ ይሄ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት መቀላቀላቸውን በምልክት አረጋግጠዋልብላለች።

የዘንድሮው ጥምቀት አምና ከነበረው የ1600 ሰዎች በቁጥር ከፍ ያለ መሆኑም ተነግሮለታል። የተጠመቁሰዎች ከጆርጅያ፣ ፍሎሪዳ እና ሌሎችም ግዛቶች ግዝቶች የተወጣጡ ናቸው።

የቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች ጥምቀቱ ሰዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የማፍለስ ዘመቻ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ በላይ የሚያስደስት ነገርም የለም ብለዋል።

አመታዊ የአትላንቲክ ውቂያኖስ ዳርቻ ጥምቀት መካሄድ ከጀመረ ከ10 አመት በላይ አስቆጥሯል ሲል ያስነበበው ዎርዚ ኒውስ ነው።
14👍2🔥1
#ፍቅርን እንተክላለን #ምህረት እናደርጋለን #ሰላምን እናጭዳለን!

የመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የሰላም ግንባታ አገልግሎት በደቡብ ክልል በሚገኙ አራት ዞኖች በኮንሶ፣ አሌ፣ ቡርጂና ደራሼ አዋሳኝ ቀበሌዎች መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለመፍታት ከሁለት አመት በላይ በአካባቢው እየሰራ ይገኛል።

በተለይ በዞኖቹ አዋሳኝ ቀበሌዎች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ሰላምን ለመገንባት ለሀገር ሽማግሌዎች፤ ለሐይማኖት አባቶች፤ ለሴቶች፤ ለተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ለተለያዩ የመንግስት አካላት ስልጠናዎች ሲሰጡ ቆይተዋል።

ቤተክርስቲያኒቱ በትላንትናው ዕለትም በማህበረሰቡ መካከል አብሮነትን ለማጠናከር ከኮንሶ እና አሌ ዞን ሰላምና ጸጥታ መምሪያዎች ጋር በመተባበር "ፍቅርን እንተክላለን! ምህረት እናደርጋለን! ሰላምን እናጭዳለን!" በሚል መሪ-ሃሳብ በሁለቱም ዞኖች ባሉ አዋሳኝ ወረዳዎች በሚገኙ ት/ቤቶች ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂዳለች።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ግንባታ መምሪያ ዳይሬክተር መምህር መኮንን ገመዳ ሰላም ሁለንተናዊ እንደመሆኑ መጠን ችግኝ በመትከላችን የአየር ንብረቱን ከመጠበቅ ባለፈ ሰላምን እንገነባለን ሲሉ አክለውም ይህን #ችግኝ ስንተክል የትላንትናውን ረስተን ነገን እያሰብን_ፍቅርን_የምንተክል_ሊሆን_ይገባል በማለት ለተሳታፊዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ስለ ሰላም እየሰራች መሆኑ ይታወቃል።
👍5🔥32
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#በቃን_እንመለስ
#ሀገራዊ የንስሐ ጥሪ

ሀገራዊ #ንስሐ ለሀገራዊ ፈውስ በሚል መሪ አሳብ
ለአንድ አመት በብዙ ዝግጅትና ልዮ ልዮ  የንስሐ መርሃ ግብሮች ሲካሄድ የነበረው የሀገራዊ ንስሐ ሂደት  ማጠቃለያ ጉባዔ ከአዲስ አበባ፣ ከክልል አብያተ ክርስቲያናት ከሃምሳ በላይ ከተሞች የሚወከሉ፣ እንዲሁም ከዲያስፖራ በሚታደሙ መሪዎች፣ አገልጋዮችና ማላጆች በአዲስ አበባ ከሰኞ ግንቦት 25 እስከ ረቡዕ ግንቦት 27 ይካሄዳል።

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ለባለድርሻ አካላት በውክልና #ንስሐ የሚገቡበት ጊዜ ይሆናል።

ቦታው በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:00 በየቀኑ ይካሄዳል።

አገልጋዮች
ዶ/ር ጆን ሙሉንዲ ከዮጋንዳ
ቄስ ዶ/ር ቶለሳ ጒዲና ከአሜሪካ
ፓስተር ዘካሪያስ በላይ ከእስራኤል

ዘማሪዎች
ዘማሪ ጌታ ያውቃልና ብሩክታዊት
ሌሎችም ያገለግላሉ።

የሀገራዊ #ንስሐ አስተባባሪ ኮሚቴ
13🔥2👏1
በናይጄሪያ 42 ክርስቲያኖች #ተገደሉ

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ታራባ በተባለች ግዛት ውስጥ በሶስት መንደሮች ውስጥ ነው ግድያው የተፈጸመው። ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁ የፉላኒ ጎሳ አባላት መሆናቸው ተነግሯል።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ በሰሜን ናይጄሪያ ክርስቲያኖችን ብቻ ትኩረት ያደረገ ጥቃት በስፋት እየተፈጸመ ይገኛል።

ኦፕን ዶርስ ዋች ሊስት በ2025 ናይጄሪያ ለክርስቲያኖች የማትመች ሃገር በመሆን 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጣለች። ይሁን እንጂ ክርስትና በናይጄሪያ እየተስፋፋ ይገኛል።

በ2000 ዓ.ም ከነበረበት 60 ሚሊዮን በ2020 ወደ 96ሚሊዮን አድጓል። በ2050 ወደ 155 ሚሊዮን ያድጋል ተብሎ ይገመታል።
👏12💔65😭4🕊3🥰1
ለክርስቲያን የሚዲያ ባለሞያዎች ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናዉ ወንጌል በማድረስ ሂደት የክርስቲያን የሚዲያ ባለሞያዎች ሚናን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ አዘጋጆቹ በመድረኩ ጠቅሰዋል።

በቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን የተዘጋጀዉ እና የክርስቲያን ሚዲያ ባለሞያዎችን አቅም ለማሳደግና ወንጌል በማስፋት ሂደት ድርሻቸውን እንዲወጡ ያስችላል የተባለዉ ስልጠና በኢንተርኔት ወንጌል መስራት እና የዜና ዝግጅት ከክርስቲያን አውድ አንጻር የሚል ሃሳብን ይዟል።

አለም በቴክኖሎጂ እየፈጠነች ባለችበው በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ትውልድን ለመናጠቅ እና ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለማስገባት ዘመኑ የሚጠይቀውን አውድ በመጠቀም ብዙዎችን ተደራሽ በማድረግ ታላቁ ተልዕኮን ለመወጣት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በስልጠናው ተጠቅሷል።

በስልጠናው የክርስቲያን ዜና ማሕበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎችን ጨምሮ በተለያዩ የክርስቲያን ሚዲያዎች እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች የክርስቲያን ይዘቶችን የሚሰሩ ከ60 በላይ ባለሞያዎች ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን በተቁም ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በዮሐንስ ግርማ
4👏2🔥1
#አስቸኳይ_የፀሎት_ጥሪ😭🙏 ሌላ ካንሰር ተገኘባት😭

( ✍️ አቤል ደመላሽ )

በጣም አሳዛኝ ነገር ተሰምቷል።

እህታችን የምስራች ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር በተዓምራት ተፈውሳ እግዚአብሔርን እያመሰገንን መቆየታችን ይታወሳል ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰ ር ተገኝቶባታል።

ከባድ ሳል ታክሎበት በፍጥነት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ ተደርጓል።

አሁንም ተስፋዋ እግዚአብሔር ነውና ጣልቃ እንዲገባላት ሁላችሁም እንድትፀልዩላት ጥሪ አናቀርባለን።

( ሁላችሁም ለሌሎች እንዲደርስ ሼር አድርጉ🥺) 🙏🙏🙏
😭12💔82
"የወንጌል ሰባኪን ሥራ ስሩ - ወንጌልን ስበኩ አትፍሩ" ሪቨረንድ ፍራንክሊን ግርሃም

የቢሊ ግርሃም አሶሴሽን ፕሬዝደንት ፍራንክሊን ግራሃም በበርሊን የአውሮፓ የወንጌል ስርጭት ኮንግረስ ከመዘጋቱ በፊት ለተሰብሳቢዎች "የወንጌል ሰባኪን ሥራ ስሩ - ወንጌልን ስበኩ አትፍሩ" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

እሳቸው ንግግራቸውን ሲቀጥሉ “አትደራደር፤ በርታ አገልግሎትህን ፈጽም፣ መከራ እንደሚኖር እናውቃለን፣ ፈተናዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን፣ አንዳንድ ግጭቶችም እንዳሉ እናውቃለን፣ ነገር #ግን እንበርታ #እና እንደሚመለስ የምናውቀውን አዳኛችንን እንስበክ ብለዋል።

ኮንግረሱ እንደተጠናቀቀ ከ1,000 ለሚበልጡ የክርስቲያን መሪዎች በመጸለይ አብረውን እንዲጸልዩ #ጥሪ በማቅረብ ወደ ትውልድ አገራቸው ሲሄዱ የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለሚያገኟቸው #ሁሉ በድፍረት ለማወጅ #እግዚአብሔር ኃይል እንዲሰጣቸው ጸልየዋል።

በዮሐንስ ግርማ
13👍2🔥1