የ2017 ፓስተርስ ኮንፈራንስ ተጀመረ
ከሚያዝያ 15-17 የሚቆየው አመታዊው ፓስተርስ ኮንፈራንስ በአድዋ 00 መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት አዘጋጅነት የሚካሄደው ኮንፈራንሱ ከመላ ሃገሪ የተወጣጡ ወደ 5ሺህ የሚጠጉ አገልጋዮች እና መሪዎች ለ3 ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዎችን ይወስዳሉ።
የዘንድሮው አመት ኮንፈራንስ "ክርስቲያናዊ እሴቶችን በማጎልበት የክርስቶስን መልክ የምታንጸባርቅ ቤተ፡ክርስቲያን ማነጽ በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።"
በስልጠናው
• ክርስቲያናዊ አመራር
• የወንጌል ተልዕኮ
• ሰላምና እርቅ
• የልጆች አገልግሎት
• ወጣት መሪዎች ማፍራት እና
• ግለ ሁለንተናን መንከባከብ
የሚሉ ጉዳዮች በስፋት ይነሳሉ።
በመድረኩ "99 አድቬንቸርስ በመጽሃፍ ቅዱስ ትልቅ ታሪክ ውስጥ" ህብረቱ ለልጆች ማስተማሪያ ያዘጋጀው መጽሃፍ በጸሎት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
የፓስተርስ ኮንፈራንሱ ህብረቱ ለሚያከብረው የ50 ዓመት እዮቤልዩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው።

👍14👏9❤6🔥1
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የ50ኛ የወርቅ እዮቤልዩ ክብረ በዓል በድምቀት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተከበረ ነዉ።
ባለፉት 2 ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ አመታዊው ፓስተርስ ኮንፈራንስ በዛሬዉ እለት የተጠናቀቀ ሲሆን ሕብረቱ በአሁኑ ሰዓት የምስረታ 50ኛዉን የወርቅ ኢዮቤልዩ መክፈቻ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በድምቀት ማክበር ጀምሯል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።

👍20❤6🔥1🙏1💯1
እኔ የኢየሱስ ነኝ
I BELONG TO JESUS
#Ethiopia | የሊቨርፑሉ አጥቂ ኮዲ ጋክፖ ትላንት ምሽት ክለቡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ ማንሳቱን ባረጋገጠበት ጨዋታ ጎል በማስቆጠር እኔ የኢየሱስ ነኝ" የሚል ጽሑፍ የያዘ ቲሸርት በማሳየት ወንጌልን ለዓለም ሰብኳል።
ከዚህ ቀደም ብራዚላዊው ካካ በተመሳሳይ ወንጌልን በዚህ መልክ በመስበክ የሚታወቅ ተጫዋች ነው።

❤33👍8👏3🔥2🙏2👌1
3 ቀን ቀረው!
ወላጆች ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ!
👉የት?፦ በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግቢ
👉ምን አለ?፦በእለቱ ልጆቻችንን ወደጌታ ለማምጣት እንደዚሁም እንዲፀኑ ለማገዝ የምንችልባቸውን ጥበቦችን እንካፈላለን ። ደግሞም ልጆችን ደቀመዝሙር ለማድረግና ወደዓለም ሄደው ስለኢየሱስ በቃላቸውና ምግባራቸው እንዲያወሩ ለማስታጠቅ የሚረዳንን ማስተዋል እናገኛለን።
እናንተም ኑ! ሌሎችንም ጋብዙ።
ይህ እድል ፈፅሞ እንዳያመልጣችሁ!
ለበለጠ መረጃ በ0911136520/0946693468 ደውሉልን።
ሰዓት :- ከ8:00-11:30
ቦታ:- ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቦሌ ኦሎምፒያ በቀድሞው ዴሉክስ ፈርኒቸር ገባ ብሎ
አገልጋይ:-
👉ጽጌረዳ የማነ ፣ ልጆችና ወጣቶችን ደቀመዝሙር በማድረግ ዙሪያ አሰልጣኝ ከናቪጌተርስ፤
👉አባይነህ ኃይሌ፣ ቤተሰቦችን ከደቀመዝሙር ማፍራት ተልዕኮ አንፃር አሰልጣኝ፤
ወላጆችና የልጆችና ወጣቶች አገልጋዮች ተጋብዛችኋል!

👍10❤2🔥1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ6 kilo እና FBE ካምፓስ የክርስቲያን ህብረት የቀድሞ ምሩቃን ቀን
ሚያዝያ 27 / 2017
በጌታ የተወደዳችሁ የጌታ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር የፊታችን ሚያዝያ 27 ከቀኑ 7:00 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ6 kilo እና FBE ካምፓስ የክርስቲያን ህብረት የቀድሞ ምሩቃን ቀንን አዘጋጅተን እናንተን ውድ ምሩቃኖቻችንን እየጠበቅን እንገኛለን።
ስለሆነም በዚቀን የረዳንን ጌታን አብረን እንድናመሰግን ከተያየን ከቆየናቸው ወንድም እና እህቶቻችን ጋር እንድንገናኝ እና መለስ ብለን ትዝታዎቻችንን እንድናወሳ በጌታ ፍቅር እንጋብዛችኋለን።
በዚህ ቀን አብራችዋቸው ስታገለግሉ እና ስትገለገሉ ከነበሩ ወንድም እና እህቶቻችሁ ጋር በመደዋወል እንድትገኙ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።
እስክንገናኝ እጅጉኑ ጓግተናል
መዝሙር 77
¹¹ የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤ የቀደመውን ተአምራትህን አስታወሳለሁና፤
¹² በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ።
ሰዓት ⌛️
7:00 local time
አድራሻ 📍
Assemblies of God 6k church የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ስድስት ኪሎ አጥቢያ
Location 📍
https://maps.app.goo.gl/cUL3ceMhofHErq857?g_st=atm

👍12❤4🔥1🙏1
"I Belong to Jesus" የሚል መልዕክት ያስተላለፈው ተጫዋች ሊቀጣ ነው።
ኔዘርላንዳዊው የሊቨርፑል አጥቂ ኮዲ ጋክፖ በኢንግሊዝ የእግር ኳስ አስተዳደር ያስተላለፈውን መልዕክት ተከትሎ ምርመራ እያደረገበት ነው።
ሊቨርፖል ከቶተናም ሆትስፐርስ ጋር በነበረው ጨዋታ 34 ደቂቃ ላይ ጎል ካገባ በኋላ ነው በደስታ ማለያውን አውልቆ "I Belong To Jesus" የሚል የውድጥ ቲሸርቱን ያሳየው።
በምርመራው መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እሱም ቡድኑም ይቀጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ደጋፊዎች ማህበሩ ግብረሰዶም መደገፍን አስገዳጅ አድርጎ፡ ሙስሊም ተጫዋቾች ጾም እንዲፈቱ ፈቅዶ፡ ክርስቲያን ተጫዋቾች መልዕክት እንዳያስተላልፉ መከልከሉን ተቃውመዋል።
ሊቨርፖል የ2025 ኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱን ከወዲሁ አረጋግጧል።
ዘ አትሌቲክ እንዳስነበበው

🔥7👍3😭3🕊1💔1
#መግቢያ በነፃ 8:00 ይጀምራል።
ነገ ሚያዚያ 23 ጉዞ ወደ ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ !
ለምን ? ካላችሁ የልጆች አስተዳደግ ስልጠና ለመካፈል ፣ ስንት ሰዓት? ከቀኑ 8፡00 -11፡30
"ልጆቻችንን ወደ ጌታ "
ከአማኝነት እስከ ሚሸነርነት
ልጆችን ወደጌታ ማምጣት ፣ ደቀመዝሙር ማድረግና በምግባራቸውና በቃላቸው ስለኢየሱስ እንዲያወሩ ማስታጠቅና ወደዓለም መላክ የወላጅ ኃላፊነት መሆኑን ያውቃል ?
ለዚህ የሚረዳንን ጥበብ እንሻምታለን ፣ ትጥቅ እናታጠቃለን ደግሞም ጸጋ እንከፋፈላለን!
አስልጣኝ :- በበርካታ ሀገራት በደቀመዝሙር ማፍራት ሥራ ላይ ከተሰማራው ናቪጌተርስ፦
👉 ጽጌረዳ የማነ
👉 አባይነህ ኃይሌ
አድራሻ :- ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቦሌ ኦሎምፒያ በቀድሞው ዴሉክስ ፈርኒቸር ገባ ብሎ
መግቢያ፦ በነፃ !!!
ለበለጠ መረጃ :- 0911136520 / 0946693468
አዘጋጅ :- የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk

❤7👍3🔥1
#አይቀርም
የወንጌል ማዳረስ እና የምስጋና ኮንፍረንስ
በጨንቻ ስታዲየም
ከግንቦት 13 እስከ 20 በጨንቻ እና አካባቢዋ የወንጌል ስርጭት እና የአገልጋዮች ስልጠና ይካሄዳል።
ግንቦት 16 እና 17 በጨንቻ ስታዲየም የወንጌል ማዳረስ እና የምስጋና ኮንፍረንስ ይከናወናል።
ኑ አብረውን ያምልኩ!
አዘጋጆች፡ ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ ከጨንቻ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር።

👍8❤3🔥1
#የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ።
በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል እየተካሄደ ባለዉ ጉባኤ የ2024 በጀት አመት የስራ ሪፖርት እና የ2025 እቅድ ቀርቦ ዉይይት እንደሚደረግበት የሚጠበቅ ሲሆን ጉባኤዉ የተሻሻለውን የካዉንስሉ ደንብ ተመልክቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጽሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።
በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል እየተካሄደ ባለዉ ጉባኤ የ2024 በጀት አመት የስራ ሪፖርት እና የ2025 እቅድ ቀርቦ ዉይይት እንደሚደረግበት የሚጠበቅ ሲሆን ጉባኤዉ የተሻሻለውን የካዉንስሉ ደንብ ተመልክቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጽሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።
👍5❤1👏1🙏1
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።
በጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጽሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ፤ ከሰላም ሚኒስተር ተወካይ አቶ ታዲዮስ ሲሳይን ፣ የኢትዮጵያ የመጽሀፍ ቅዱስ ማህበረ ፕሬዝደንት ሊቀ ህሩያን ይልማ ጌታሁንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጉባኤው የቦርድ አመራሮች ተገኝተዋል።
መረሃ ግብሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የካውንስሉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በአባላት መካከል ያለውን ሕብረት መጠናከሩን አንስተው ሁላችንም ለካውንስሉ መጠናከር የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሰላም በመከባበር እና በጋራ እሴቶቻችን ላይ ከሌሎች ቤተዕምነቶች ጋር በጋራ በመሆን እንሰራለን ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ናቸው።
ሊቀ ትጉሃን አክለዉ ካዉንስል የኢ/ሃ/ተቋማት ጉባኤ አባል በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ በጋራ ለሀገራችን ሰላም የተሻለ ስራን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር ፕሬዝደንት ሊቀ ሕሩሃይ ይልማ ጌታሁን በበኩላቸው ማህበሩ ከካውንስሉ ምስረታ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ እንደሆነ በማንሳት ኢትዮጵያን በወንጌል ለመሸፈን ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የሃይማኖት ተቋማት ስለሰላም በጋራ በመስራት እና በመፀለይ ሰላምን ለማፅናት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስትር ተወካይ የሆኑት አቶ ታዲዬስ ሲሳይ ናቸዉ።
በተካሄደው 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2024 የስራ ሪፖርት እና የ2025 እቅድ ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ የጸደቀ ሲሆን ጉባኤው የተሻሻለውን የካዉንስሉን ደንብ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።

❤6👍4👏2🔥1
ልክ እንደ #ዳዊት፣ እንደ #ሳሙኤል፣ እንደ #ኤርሚያስ፣ እንደ #ጤሞቴዎስ ሁሉ ልጆቻችን ዛሬ ላይ አገልጋይ እና ሚሽነሪ መሆናቸው እንዳይረሳ።
ልጆች ዛሬም አገልጋይ ናቸው በሚል ሃሳብ፣ ስልጠና ለወላጆችና የልጆች መምህራን ተሰጠ።
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ከናቪጌተርስ ኢትዮጵያ ሚኒስትሪ ጋር ነው ስልጠናውን የሰጠው።
በስልጠናው ልጆቻችንን ጥሩ ክርስቲያን ማድረግ እና ደቀ መዝሙር ማድረግ ይገባል የሚል ነው።
ልጆች ነገ ሳይሆን ዛሬ የወንጌል መልዕክተኛ ስለሆኑ ልክ እንደ ሳሙኤል፣ እንደ ዳዊት፣ ጢሞቴዎስ፣ ኤርሚያስ ያሉ በትንሽነታቸውን እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።
ይሄንንም እንዲረዱ ያግዝ ዘንድ የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ አገልጋዮች ስልጠና የሰጠው።
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ሚኒስትሪ መሪ ወ/ሮ ሳሮን ውድነህ፣ ይሄንን ሃሳብ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን ይዞ መሄድ አለበት፣ በተጨማሪም ስለ ቤተሰብ አገልግሎት በስፋት ሊሰራበት ይገባል ስትል ሃሳቧን አጋርታለች።
የስልጠናው ተሳታፊዎች ቆይታው አይን ከፋች ነው የሆነልን ሲሉ አስተያየታቸውን ለክርስቲያን ዜና አጋርተዋል።
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ በቤተሰብ ላይ የሚሰራ ሚኒስትሪ ሲሆን፣ ናቪጌተርስ ኢትዮጵያ ሚኒስትሪ ደግሞ ደቀ መዝሙር ማፍራት ላይ የሚሰራ የወንጌል አገልግሎት ሚኒስትሪ ነው።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ በመገኘት ፕሮግራሙን በመከታተል ዘገባዉን አሰናዳንላችሁ።

👍6❤2👏2🙏2❤🔥1
#በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ።
የመሠረተ ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን ከቲዲ ኤም ኤም ጋር በመተባበር በአፋር ክልል በመሬት መቀጥቀጥ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን 2,000,000 ብር ወጪ በማድረግ ለ500 አባወራዎች የምግብ ድጋፍ አደረገች።
ቤተክርስቲያኒቱ በአፋር ክልል አዋሽ አርባ አካባቢ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሁለት መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ዜጎች ድጋፉን ስታደርግ በስፍራው የተገኙት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ለተጎጂዎች እርዳታውን በሰጡበት ወቅት #እዚህ_የተገኘውን_ለእናንተ_ያለንን_ፍቅር_ለመግለጽና_በምን_ሁኔታ_ውስጥ_እንዳላችሁ_ለማየት_እንዲሁም_ይህ_ጊዜ_ያልፋል_አይዟችሁ_ለማለት_ነው_ሲሉ በጸሎታችን ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነን ብለዋል።
ተጎጂዎችም ቤተክርስቲያን ስላደረገችላቸው ድጋፍ በማመስገን ደስታቸውን ሲገልጹ ታይቷል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ወገኖቿ ተመሳሳይ ድጋፎችን ስታደርግ መቆየቷ ይታወሳል።
በተመሳሳይ ዜና የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የጸሎት ቤታቸው የፈረሰባቸውን የከሰም ቀበና መሪዎች በስፍራው በመገኘት አበረታተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዛሬው ዕለት በክልሉ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተጎዱ አካባቢዎችን ተዟዙረው በተመለከቱበት ወቅት በስፍራው ከሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች ጋር ሲወያዩ በውይይታቸውም በአካባቢው ቤተክርስቲያንን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተነጋግረዋል።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአከባቢው የእግዚአብሔር መንግስት እንዲሰፋ የምትሰጠውን የወንጌል አገልግሎት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።

👍10❤3🔥1👏1
በደቡብ #አፍሪካ የመሪዎች የአንድነት ጊዜ ተካሄደ።
በፈረንጆቹ ሜይ 6 እና 7 በኬፕ ታውን የነበረው የ2ተኛ ዙር የደቡብ አፍሪካ የመሪዎች የአንድነት ጊዜ በጥሩ መንፈስ እና በወንድማማችነት ስሜት መካሄዱን ከስፍራዉ የተላከልን ዝርዝር ያመለክታል።
መድረኩን የካውንስሉ ፕሬዝዳንት ፓስተር ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ በ“እንኳን ደህና መጣችሁ” ንግግር ያስጀመሩት ሲሆን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፓስተር ገነነ “በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ” በሚል መልዕክት አቅርበዋል።
የሴሚናሩ የመጀመሪያ ቀን ማለዳ "የወንድማማች ኅብረት" በሚል ርዕስ በፓስተር ዶ/ር ዴቪድ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን በከሰዓቱ ፕሮግራም ዓላማና ግብ ላይ ያጠነጠነ በካውንስሉ ፕሬዝዳንት በፓስተር ዶ/ር ብርሃኑ ትምህርት ቀርቧል።
ዕረቡ ማለዳ ደግሞ መሪነትን በተመለከተ በፓስተር ኤልያስ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ የፓናል ውይይት በፓስተር ገነነ አወያይነት ሐዋርያው ሳሙኤል፣ ፓስተር በየነ፣ ፓስተር ዴቪድ እና ፓስተር ጡሚሳ አማኞችን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በማድረግ ዙሪያ እና በወቅታዊ ክርስቲያናዊ ምልልስ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በሌላም በኩል በተሻለ መንገድ ለመሥራት አብዛኛውን ፕሮቪንሶች አካታች ባደረገ መልኩ 30 የሚሆኑ የቦርድ አባላትን ያካተተ 9 የሥራ አስፈጻሚ ቡድን ሰይሟል። በመሆኑም:-
1. ፓስተር ዶ/ር ብርሃኑ ታምሬ … ፕሬዚደንት
2. ፓስተር ገነነ ማስረሻ … ምክትል ፕሬዚደንት
3. ፓስተር ዴቪድ ሐለንጎ … ዋና ጸሐፊ
4. ፓስተር ብርሃኑ በቀለ … ገንዘብ ያዥ
5. ፓስተር በየነ ሎሳሶ … ሂሳብ ሹም
6. ሐዋርያው ሳሙኤል ሽራንጎ … አባል
7. ፓስተር ኤልያስ ግርማ … አባል
8. ፓስተር አባተ አበራ … አባል
9. ፓስተር ደመቀ ኃይሌ … አባል
ሆነው ተመርጠዋል።

👍7❤1🔥1
የባይተዋር ወዳጅ - ሶፊያ ሽባባዉ አዲስ መዝሙር ተባረኩበት ከረጅም ጊዜ በኋላ በድጋሜ ስላየናት ደስ ብሎናል። https://www.youtube.com/watch?v=Rp_Mls0nKgg
YouTube
የባይተዋር ወዳጅ - ሶፊያ ሽባባዉ // yebaytewar wedaj - sofia shibabaw // new song //አዲስ መዝሙር
new song አዲስ መዝሙር የባይተዋር ወዳጅ ሶፊያ ሽባባ new pro // Official Sofia Shibabaw 2023 //
subscribe and like our video for more interesting contents•
ይህን ቪዲዮ ሼር በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ ማድረግ አይርሱ።
ሰብስክራይብ ያላደረጋችሁ አዳዲስ ቪዲዮ እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ በማድረግ የደውል ምልክቱን መጫን አትርሱ።
This…

❤9🙏2🔥1👏1
የፊንፊኔ ኦሮሞ መካነ ኢየሱስ የአምልኮ ህንጻ በድምቀት ተመረቀ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ የሱስ የፊንፊኔ ኦሮሞ ማህበረ ምዕመናን ማምለኪያ ህንፃ ተመረቀ፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ የሱስ የፊንፊ ኦሮሞ ማህበረ ምዕመናን በጉለሌ ዊንጌት አከባቢ ኢቢሲ ፊት ለፊት ያስገነባችውን የአምልኮ አዳራሽ እና ሁለ ገብ ህንፃ እሁድ እለት አስመርቃለች፡፡
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች ፣ከውጭ እና ሀገር ውስጥ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ቤተ ክርስቲኑ ባለፉት 33 ዓመታት ለራሷ ድንኳን ውስጥ ተቀምጣ የስብከት ጣቢያዎችን በማስፋፋት በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የወንጌል ስርጭት ስራ በመስራት ላይምል ትገኛለች፡፡
በዚሁ መሰረት 14 ስብከት ጣቢዎችን ወደ ቤተክርስቲን በማሳደግ፣ 29 ስብከት ጣቢዎችን በመትከል ወንጌል እዲስፋፋ ትልቅ ስራ ሰርታለች፡፡
ዛሬ ላይ ቤተክርስቲያኗ በእግዚአብሔር እርዳታ ባገኘችው የራሷ ሰፊ ቦታ ላይ ያስገነባችውን የአምልኮ አዳራሽ እና ሁለ ገብ ህንፃ በማስመረቅ የወንጌል ስርጭት ስራ ይበልጥ ለማስፋፋት ተዘጋጅታለች፡፡
መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኗ መሪዎች አገኘነው

❤10👍7💔4🔥1
የወንጌል አርበኛዋ እማማ ዛናቄ በክብር ተሸኙ 🥺
በጨንቻና አካባቢዋ የመጀመሪያዋ ሴት የወንጌል አማኝ እና የወንገል አርበኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት ወ/ሮ ዛናቄ ዛሜ በትላንትናው ቀን ግንቦት 5/2017 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸዉ ይታወሳል።
የወንጌል አርበኛዋ ከዘማሪ እስራኤል ኩማ እና ከሌሎች ዘማሪያን ጋር ሆነው ሃሹ ጊዶኮና ጦሳ ና'' በሚለው የጋሞኛ ዝማሬ የቪዲዮ ክሊፕ ላይ በዝማሬ ከታዩ በኋላ በበርካቶች ዘንድ አክብሮት እና አድናቆት ተችሯቸዋል።
ወ/ሮ ዛናቀ ዛሜ በምድር ቆይታቸው በወንጌል ምክንያት መከራን ተቀብለው ለትውልድ ምሳሌ በመሆን ሲመላለሱ የነበሩ ብርቱ እናት እንደነበሩ በቅርበት የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ።በጋሞ ዞን ጨንቻና አካባቢው ወንጌልን ለትውልድ በማድረስ አንቱታን ያተረፉት እማማ ዛናቄ ዛሜ ዛሬ በቀን 6/09/2017 ዓ.ም በተወለዱበት በዶኮ መሾ ዮይራ ያጭኔ ሁለገብ ስታዲየም በመንፈሳዊ ስነስርዓት ሽኝት በድምቀት ተካሄደዋል።
ለቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን!

👍15😭11🥰4❤2🔥1👏1
በግሬስ #ክርስቲያን #ሚዲያ የተዘጋጀውን "ግሬስ ቶርናመንት" የእግር ኳስ ውድድር አስመልክቶ ጋዜጣዊ #መግለጫ በዛሬው እለት ተሰጥቷል።
'ግሬስ ቶርናመንት' ማህበረሰባችን ለስፖርት ለማንቃት #እና እርስ በእርስ ተቀራርቦ ስፖርታዊ ባህልን እንዲያዳብር ለማስለመድ የተዘጋጀ የእግር ኳስ ውድድር እንደሆነ ተገልጿል። በእግር ኳስ ጨዋታ #ውስጥ ለመያያዝና ማህበረባችን ለመጥቀም ለበጎ አላማ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህ የእግር #ኳስ ውድድር 16 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፣ በሰላምና በፍቅር ለወንጌል ምሳሌነት በሚሆን መልኩ፣ እርስ በእርስ ውድድራችን እናደርጋለን ተብሏል። እግር ኳስ ዘርፈ #ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት እናምናለን በማለት ተናግረዋል።
#ይህ ቶሮናመንት የፊታችን #ቅዳሜ የክብር እንግዶች የቤተክርስቲያን መሪዎችና አገልጋዮች በተገኙበት ግንቦት 9/2017 ከ 9:00 ጀምሮ በቡልቡላ #ሜዳ #ላይ የሚከናወን ሲሆን፣ የመክፈቻ ጨዋታው በናዝራውያን ቡድንና፣ በዘጸአት ቤተ ክርስቲያን ቡድኖች መሐል በሚደረገው ጨዋታ እንደሚጀመር ተገልጿል።

👍6❤3🔥1🥰1
“LetAfrica Go” 2025” ኮንፈራንስ ተካሄደ።
በኮንፈራንሱከ20 የአፍሪካ ሃገራት የተወጣጡ መሪዎች እና አገልጋዮች ተካፋይ ሆነዋል።
ከግንቦት1-3 አዲስ በተከፈተው የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የተካሄደው ኮንፈራንሱ “መለኮታዊ ግንኙነት - የእስራኤል
ትንቢታዊ ሃላፊነት በአፍሪካ መነቃቃትና ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።
ወንጌላዊያንመሪዎቹ ሰላም በኢየሩሳሌም እንዲሰፍን፣ በሃማስ የታገቱ እስራኤላዊያን እንዲለቀቁ እና በአፍሪካ እና እስራኤል መካከል ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖር ጸሎት አድርገዋል።
በመድረኩበኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭራሃም ንጉሴ፣ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት አስታውሰው፣
ሃገራቱ በልማት፣ ግብርና፣ መድሃኒት፣ የምግብ ደህንነት፣ ፈጠራ እና ሌሎችም ዘርፎች ላይ ይበልጥ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የ”LetAfrica Go” ንቅናቄ መስራች ዶ/ር ፓስተር አበራ ሃብቴ በአህጉሪቱ እና በውጪ ያሉ አፍሪካዊያን በሙሉ ከእስራኤል ጎን
መቆም አለባቸው ሲሉ ተናገረዋል።
LetAfrica Go ንቅናቄ የአፍሪካ ለውጥ ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ በላይ መንፈሳዊ መሆን አለበት ብሎ ያምናል። በተጨማሪ ከእስራኤል ጋር አብሮ መቆም ዋና መርሁ ነው። አመታዊ ኮንፈራንሱ በኤልሻዳይ ቲቪ ኔትወርክ መስራች ዶ/ር አበራ ሃብቴ በ2023 የተጀመረ ነው።

🔥6👍3👏2❤1
አዲሱ የካቶሊክ ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስ ቤተሰብ የሚመሰረተው በአንድ ወንድ እና አንድ ሴት ጥምረት ነው አሉ።
ሊቀ ጳጳሱ ሊዮ 14ኛ አክለውም ከማህጸን ያልወጣ እና ያረጀ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እኩል ክብር ያላቸው ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ይሄ ንግግራቸው ቤተ ክርስቲያኗ ለምትታማበት የግብረሰዶም
እና ውርጃ ጉዳዮች መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቱምቢ ያስቀመጠ ንግግር ነው ተብሏል።
የመጀመሪያው አሜሪካዊ ጳጳስ የሆኑ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ 14ኛ በቫቲካን ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በሃይማኖቶች መካከል ንግግሮችን ማዳበር ያስፈልጋል ብለዋል።
ትላንት አርብ ከዲፕሎማቲክ
ማህበረሰብ ጋር ከእሁዱ የመጀሪያዉ ሲመታቸው በፊት ባደረጉት የዝግ በር ንግግር ነው።
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱ ሊቀ ጳጵሱ ከ180 ሃገራት ጋር ግንኙነትያላትን ቫቲካን ሃገረ መንግስት መሪ በመሆናቸው የሚደረግ ግንኙነት ነው።
ሊቀ ጳጳሱ ከአውግስጢኖስ ቤተ ስርዓት የወጡ ስለሆነ ግንቦት 1 ወደ አደባባይ ሲወጡ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” ብለው ንግግራቸውን መጀመራቸው ሰላም በጵጵስናቸው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑ አመላካች ነው።
ሰላማዊ ማህበረሰብን በመገንባት ሂደት ውስጥ ለቤተሰብ ቅድሚያ በመስጠት በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት ላይ መሰረት ያደረገ ቤተሰብ መገንባትን መንግስታት ማገዝ አለባቸው ብለዋል።
ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ በጵጵስናቸው ወቅት ውርጃን እና በፈቃደኝነት ራስን ማጥፋትን የተቃወሙ ሲሆን፣ የቤተ ክርስቲያንን በሮች ለሰዶማዊያን ከፍተዋል ሲል ያስነበበው አሶሼትድ ፕረስ
ነው።

👍18👏5❤1🔥1