The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
የበዓል ስጦታ ከWSG ሚኒስትሪ

WSG የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን ምክኒያት በማድረግ ለ1ሺህ አባወራዎች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

WSG ድጋፉን ብራይት ስታር ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ከ1ሺህ ለሚበልጡ አባወራዎች የምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ያደረገው።

ድጋፉ የተደረገው የብራይት ስታር ፍሪደም ት/ቤት ተማሪ ወላጆችና የመንግስት ት/ቤት ለሚገኙ ተማሪ ወላጆች ነው ያደረገው።

የWSG ሚኒስትሪ አስተባባሪ ወ/ሮ ሃዊ በዳሳ ስጦታው ሁሉም በየቤቱ ፋሲካን በደስታ እንዲያስተላልፍ የታሰበ ነው፡ ስለዚህ እንኳን ደስ አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

WSG የከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች፡ ለጥፋት የተጋለጡና ማደሪያቸውን ጎዳና ላደረጉ ወጣቶች የመንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ WSG (Win Souls for God Evangelical Ministry) በአውሮፓ በተለይም በስዊድን ለሚገኙ ወገኖች (Mission back to Europe) በሚል ስያሜ የታረደውን በግ ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መስበነክ ላይ ይገኛል።
መረጃውን ጋዜጠኛ ጸጋይብጻህ ኢሳይያስ አደረሰን።
👏73👍1🔥1
ሲቃዩ ሊብራራ አይችልም። የመጨረሻውን ስቃይ ተሰቃየ #ሰሙነ #ሕማማት ከሆሳዕና #እስከ ትንሳኤ #እና ፕሮግራም

ከኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ #እና ለተከታታይ 8 ቀናት እየተላለፈ የሚገኝ በየቀኑ በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ .. የተለያዩ አገልጋዮች ሰሙነ ሕማማቱን እየተረኩር #ዛሬ ደርሰናል። በሚያገኙት አማራጭ ይከታተሉ።

በማሕበራዊ #ሚዲያ በThe Christian News YouTube channel ላይ ይመልከቱ። https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
👍7😭32🔥2🙏1
የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በገረሴ ከተማ አደባባይ በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከበረ።

በመዝሙርና በቃል፣ በድምቀት ተከብሯል።

ገረሴ-ውልአ

በያላችሁበት አከባቢ እንዴት እየተከበረ ነዉ ? ፎቶዎች ላኩልን 🙏🙏
👍41🔥1
የወለንጭቲ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የትንሳኤ በዓል በጋራ አከበሩ።

ዛሬ ሚያዝያ 12/08/2017 ከማለዳው 11ሰዓት ጀምሮ በፕሮግራሙ ላይ የቦሰት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ጉተማ ቢፍቱ በመገኘት #እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ስላስተላለፉልን በህብረቱ ስም አመስግነዋል።

አጠቃላይ ፕሮግራሙ ላይ በዝማሬ በቃል በወረብ አምልኮ ለሀገር በመጸለይ የተከናወነ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ ሸዋ ዞን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ሰብሳቢ ፖስተር ሰለሞን ሽፈራዉ እና የቦሰት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመገኘት እንኳን አደረሳችሁ አስተላልፈዋል::

መሪዎች ከስፍራው ላደረሳችሁን መረጃ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏
🔥41👍1
ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸዉን ታዉቋል።

ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች፡፡

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለኢትዮጵያውያን የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን መፅናናትን እንመኛለን።
👍16😭3🤔1🕊1💔1
የ2017 ፓስተርስ ኮንፈራንስ ተጀመረ

ከሚያዝያ 15-17 የሚቆየው አመታዊው ፓስተርስ ኮንፈራንስ በአድዋ 00 መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት አዘጋጅነት የሚካሄደው ኮንፈራንሱ ከመላ ሃገሪ የተወጣጡ ወደ 5ሺህ የሚጠጉ አገልጋዮች እና መሪዎች ለ3 ቀናት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዎችን ይወስዳሉ።

የዘንድሮው አመት ኮንፈራንስ "ክርስቲያናዊ እሴቶችን በማጎልበት የክርስቶስን መልክ የምታንጸባርቅ ቤተ፡ክርስቲያን ማነጽ በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።"

በስልጠናው
• ክርስቲያናዊ አመራር
• የወንጌል ተልዕኮ
• ሰላምና እርቅ
• የልጆች አገልግሎት
• ወጣት መሪዎች ማፍራት እና
• ግለ ሁለንተናን መንከባከብ

የሚሉ ጉዳዮች በስፋት ይነሳሉ።

በመድረኩ "99 አድቬንቸርስ በመጽሃፍ ቅዱስ ትልቅ ታሪክ ውስጥ" ህብረቱ ለልጆች ማስተማሪያ ያዘጋጀው መጽሃፍ በጸሎት ተመርቆ ለአገልግሎት በቅቷል።

የፓስተርስ ኮንፈራንሱ ህብረቱ ለሚያከብረው የ50 ዓመት እዮቤልዩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው።
👍14👏96🔥1
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የ50ኛ የወርቅ እዮቤልዩ ክብረ በዓል በድምቀት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተከበረ ነዉ።

ባለፉት 2 ቀናት ሲካሄድ የቆየዉ አመታዊው ፓስተርስ ኮንፈራንስ በዛሬዉ እለት የተጠናቀቀ ሲሆን ሕብረቱ በአሁኑ ሰዓት የምስረታ 50ኛዉን የወርቅ ኢዮቤልዩ መክፈቻ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች በተገኙበት በድምቀት ማክበር ጀምሯል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።
👍206🔥1🙏1💯1
እኔ የኢየሱስ ነኝ
I BELONG TO JESUS

#Ethiopia | የሊቨርፑሉ አጥቂ ኮዲ ጋክፖ ትላንት ምሽት ክለቡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ዋንጫ ማንሳቱን ባረጋገጠበት ጨዋታ ጎል በማስቆጠር እኔ የኢየሱስ ነኝ" የሚል ጽሑፍ የያዘ ቲሸርት በማሳየት ወንጌልን ለዓለም ሰብኳል።

ከዚህ ቀደም ብራዚላዊው ካካ በተመሳሳይ ወንጌልን በዚህ መልክ በመስበክ የሚታወቅ ተጫዋች ነው።
33👍8👏3🔥2🙏2👌1
3 ቀን ቀረው!

ወላጆች ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ!

👉የት?፦ በኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ግቢ 
👉ምን አለ?፦በእለቱ ልጆቻችንን ወደጌታ ለማምጣት እንደዚሁም እንዲፀኑ ለማገዝ የምንችልባቸውን ጥበቦችን እንካፈላለን ። ደግሞም ልጆችን ደቀመዝሙር ለማድረግና ወደዓለም ሄደው ስለኢየሱስ በቃላቸውና ምግባራቸው እንዲያወሩ ለማስታጠቅ የሚረዳንን ማስተዋል እናገኛለን።

እናንተም ኑ! ሌሎችንም ጋብዙ።
ይህ እድል ፈፅሞ እንዳያመልጣችሁ!

ለበለጠ መረጃ በ0911136520/0946693468 ደውሉልን።

ሰዓት :- ከ8:00-11:30
ቦታ:- ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቦሌ ኦሎምፒያ በቀድሞው ዴሉክስ ፈርኒቸር ገባ ብሎ

አገልጋይ:-

👉ጽጌረዳ የማነ ፣ ልጆችና ወጣቶችን ደቀመዝሙር በማድረግ ዙሪያ አሰልጣኝ ከናቪጌተርስ፤
👉አባይነህ ኃይሌ፣ ቤተሰቦችን ከደቀመዝሙር ማፍራት ተልዕኮ አንፃር አሰልጣኝ፤

ወላጆችና የልጆችና ወጣቶች አገልጋዮች ተጋብዛችኋል!
👍102🔥1
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ6 kilo እና FBE ካምፓስ የክርስቲያን ህብረት የቀድሞ ምሩቃን ቀን
ሚያዝያ 27 / 2017

በጌታ የተወደዳችሁ የጌታ ቤተሰቦች እንደምን ቆያችሁ ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር የፊታችን ሚያዝያ 27 ከቀኑ 7:00 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የ6 kilo እና FBE ካምፓስ የክርስቲያን ህብረት የቀድሞ ምሩቃን ቀንን አዘጋጅተን እናንተን ውድ ምሩቃኖቻችንን እየጠበቅን እንገኛለን።

ስለሆነም በዚቀን የረዳንን ጌታን አብረን እንድናመሰግን ከተያየን ከቆየናቸው ወንድም እና እህቶቻችን ጋር እንድንገናኝ እና መለስ ብለን ትዝታዎቻችንን እንድናወሳ በጌታ ፍቅር እንጋብዛችኋለን።

በዚህ ቀን አብራችዋቸው ስታገለግሉ እና ስትገለገሉ ከነበሩ ወንድም እና እህቶቻችሁ ጋር በመደዋወል እንድትገኙ በጌታ ፍቅር ተጋብዛችኋል።

እስክንገናኝ እጅጉኑ ጓግተናል

መዝሙር 77
¹¹ የእግዚአብሔርን ሥራ አስታወስሁ፤ የቀደመውን ተአምራትህን አስታወሳለሁና፤
¹² በምግባርህም ሁሉ እናገራለሁ፥ በሥራህም እጫወታለሁ።

ሰዓት ⌛️
7:00 local time

አድራሻ 📍
Assemblies of God 6k church የኢትዮጵያ ጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ስድስት ኪሎ አጥቢያ

Location 📍
https://maps.app.goo.gl/cUL3ceMhofHErq857?g_st=atm
👍124🔥1🙏1
"I Belong to Jesus" የሚል መልዕክት ያስተላለፈው ተጫዋች ሊቀጣ ነው።

ኔዘርላንዳዊው የሊቨርፑል አጥቂ ኮዲ ጋክፖ በኢንግሊዝ የእግር ኳስ አስተዳደር ያስተላለፈውን መልዕክት ተከትሎ ምርመራ እያደረገበት ነው።

ሊቨርፖል ከቶተናም ሆትስፐርስ ጋር በነበረው ጨዋታ 34 ደቂቃ ላይ ጎል ካገባ በኋላ ነው በደስታ ማለያውን አውልቆ "I Belong To Jesus" የሚል የውድጥ ቲሸርቱን ያሳየው።

በምርመራው መሰረት ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ እሱም ቡድኑም ይቀጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ደጋፊዎች ማህበሩ ግብረሰዶም መደገፍን አስገዳጅ አድርጎ፡ ሙስሊም ተጫዋቾች ጾም እንዲፈቱ ፈቅዶ፡ ክርስቲያን ተጫዋቾች መልዕክት እንዳያስተላልፉ መከልከሉን ተቃውመዋል።

ሊቨርፖል የ2025 ኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ማንሳቱን ከወዲሁ አረጋግጧል።
ዘ አትሌቲክ እንዳስነበበው
🔥7👍3😭3🕊1💔1
#መግቢያ በነፃ 8:00 ይጀምራል።

ነገ ሚያዚያ 23 ጉዞ ወደ ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ !

ለምን ? ካላችሁ የልጆች አስተዳደግ ስልጠና ለመካፈል ፣ ስንት ሰዓት? ከቀኑ 8፡00 -11፡30

"ልጆቻችንን ወደ ጌታ "
ከአማኝነት እስከ ሚሸነርነት
ልጆችን ወደጌታ ማምጣት ፣ ደቀመዝሙር ማድረግና በምግባራቸውና በቃላቸው ስለኢየሱስ እንዲያወሩ ማስታጠቅና ወደዓለም መላክ የወላጅ ኃላፊነት መሆኑን ያውቃል ?

ለዚህ የሚረዳንን ጥበብ እንሻምታለን ፣ ትጥቅ እናታጠቃለን ደግሞም ጸጋ እንከፋፈላለን!

አስልጣኝ :- በበርካታ ሀገራት በደቀመዝሙር ማፍራት ሥራ ላይ ከተሰማራው ናቪጌተርስ፦

👉 ጽጌረዳ የማነ
👉 አባይነህ ኃይሌ

አድራሻ :- ኤልሻዳይ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቦሌ ኦሎምፒያ በቀድሞው ዴሉክስ ፈርኒቸር ገባ ብሎ

መግቢያ፦ በነፃ !!!

ለበለጠ መረጃ :- 0911136520 / 0946693468

አዘጋጅ :- የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ
https://t.me/+LZGZsvB8OWA0OTFk
7👍3🔥1
#አይቀርም

የወንጌል ማዳረስ እና የምስጋና ኮንፍረንስ
በጨንቻ ስታዲየም

ከግንቦት 13 እስከ 20 በጨንቻ እና አካባቢዋ የወንጌል ስርጭት እና የአገልጋዮች ስልጠና ይካሄዳል።

ግንቦት 16 እና 17 በጨንቻ ስታዲየም የወንጌል ማዳረስ እና የምስጋና ኮንፍረንስ ይከናወናል።

ኑ አብረውን ያምልኩ!

አዘጋጆች፡ ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪስ ከጨንቻ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር።
👍83🔥1
#የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ።

በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል እየተካሄደ ባለዉ ጉባኤ የ2024 በጀት አመት የስራ ሪፖርት እና የ2025 እቅድ ቀርቦ ዉይይት እንደሚደረግበት የሚጠበቅ ሲሆን ጉባኤዉ የተሻሻለውን የካዉንስሉ ደንብ ተመልክቶ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጽሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ የምንገኝ ሲሆን ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን።
👍51👏1🙏1
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ።

በጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጽሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ፤ ከሰላም ሚኒስተር ተወካይ አቶ ታዲዮስ ሲሳይን ፣ የኢትዮጵያ የመጽሀፍ ቅዱስ ማህበረ ፕሬዝደንት ሊቀ ህሩያን ይልማ ጌታሁንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የጉባኤው የቦርድ አመራሮች ተገኝተዋል።

መረሃ ግብሩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የካውንስሉ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በአባላት መካከል ያለውን ሕብረት መጠናከሩን አንስተው ሁላችንም ለካውንስሉ መጠናከር የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በሰላም በመከባበር እና በጋራ እሴቶቻችን ላይ ከሌሎች ቤተዕምነቶች ጋር በጋራ በመሆን እንሰራለን ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ናቸው።

ሊቀ ትጉሃን አክለዉ ካዉንስል የኢ/ሃ/ተቋማት ጉባኤ አባል በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለጹ ሲሆን በቀጣይ በጋራ ለሀገራችን ሰላም የተሻለ ስራን እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መጽሀፍ ቅዱስ ማህበር ፕሬዝደንት ሊቀ ሕሩሃይ ይልማ ጌታሁን በበኩላቸው ማህበሩ ከካውንስሉ ምስረታ ጀምሮ በጋራ እየሰሩ እንደሆነ በማንሳት ኢትዮጵያን በወንጌል ለመሸፈን ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ስለሰላም በጋራ በመስራት እና በመፀለይ ሰላምን ለማፅናት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ደግሞ የሰላም ሚኒስትር ተወካይ የሆኑት አቶ ታዲዬስ ሲሳይ ናቸዉ።

በተካሄደው 4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ የ2024 የስራ ሪፖርት እና የ2025 እቅድ ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ የጸደቀ ሲሆን ጉባኤው የተሻሻለውን የካዉንስሉን ደንብ በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
6👍4👏2🔥1