The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
መካነ #ኢየሱስ #አዲስ ኮሚሽነር መረጠች።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማት #እና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አቶ ሰለሞን ሽፈራው ለቀጣይ አራት አመታት በኮሚሽነርነት እንዲያገሉ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቋል።

ወደ አገልግሎቱ የሚመጡት አቶ ሰለሞን ሽፈራ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ባጠናቀቁት ዶ/ር አበያ ዋቅወያን ምትክ ይሆናል።

አቶ ሰለሞን ኮሚሽኑን በተለያዩ ደረጃዎች ላለፉት አስርት አመታት ያገለገሉ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ የልማት አገልግሎት ፍልስፍና ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱም ለአቶ ሰለሞን አዲስ የአመራር ምዕራፍ #መልካም ምኞትዋን ገልጻለች።

ኮሚሽኑንም ወደሚቀጥለው ሁለንተናዊ የተጽኖ ምዕራፍ ለማሻገር ቤተ ክርስቲያን በአቶ ሰለሞን አመራር ላይ በፀሎት የሆነ እምነቷን አስቀምጣለች።
👍71🙏1
#አስደሳች #ዜና
ታፍነው የተወሰዱት ፓስተር ተለቀቁ

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስብከት ላይ እያሉ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት አሜሪካዊው ፓስተር በደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች ድጋፍ መለቀቃቸውን ፎክስ ዜና አስነብቧል።

ባሳለፍነው ሃሙስ በደቡብ አፍሪካ ፌሎሺፕ ባፕቲስት ቸርች ኢን ማዘርዌል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰበኩ የነበሩ ጆሽ ሱሌቫን የተባሉ አሜሪካዊ ፓስተር "አራት የታጠቁ እና ጭምብል ያጠለቁ ወንዶች ናቸው ፓስተሩን አፍነው የወሰዷቸው" ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ካፕቴን አንድሬ ቤቴጅ ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።

ፎክስ ኒውስ ከሰዓት በፊት ይዞት በወጣው ዘገባ የደቡብ አፍሪካ የምስራቅ ኬፕ ግዛት ባለስልጣናት ማክሰኞ እለት በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ታፍኖ የነበረውን አሜሪካዊ ፓስተር ማዳን መቻላቸው ገልጸዋል ሲል ዘግቧል።

የ34 ዓመቱ ፓስተር ወደ ደቡብ አፍሪካ ከቤተሰባቸው ጋር ያቀኑት በፈረንጆቹ 2018 ሲሆን፣ አላማቸውም በዦሳ ቋንቋ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ ክርስቲያን መመሥረት እንደነበር ዘገባው አክሏል።
👍137🔥1🙏1💔1
የበዓል ስጦታ ከWSG ሚኒስትሪ

WSG የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን ምክኒያት በማድረግ ለ1ሺህ አባወራዎች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

WSG ድጋፉን ብራይት ስታር ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ከ1ሺህ ለሚበልጡ አባወራዎች የምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ያደረገው።

ድጋፉ የተደረገው የብራይት ስታር ፍሪደም ት/ቤት ተማሪ ወላጆችና የመንግስት ት/ቤት ለሚገኙ ተማሪ ወላጆች ነው ያደረገው።

የWSG ሚኒስትሪ አስተባባሪ ወ/ሮ ሃዊ በዳሳ ስጦታው ሁሉም በየቤቱ ፋሲካን በደስታ እንዲያስተላልፍ የታሰበ ነው፡ ስለዚህ እንኳን ደስ አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

WSG የከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች፡ ለጥፋት የተጋለጡና ማደሪያቸውን ጎዳና ላደረጉ ወጣቶች የመንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ WSG (Win Souls for God Evangelical Ministry) በአውሮፓ በተለይም በስዊድን ለሚገኙ ወገኖች (Mission back to Europe) በሚል ስያሜ የታረደውን በግ ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መስበነክ ላይ ይገኛል።
መረጃውን ጋዜጠኛ ጸጋይብጻህ ኢሳይያስ አደረሰን።
👏73👍1🔥1
ሲቃዩ ሊብራራ አይችልም። የመጨረሻውን ስቃይ ተሰቃየ #ሰሙነ #ሕማማት ከሆሳዕና #እስከ ትንሳኤ #እና ፕሮግራም

ከኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ #እና ለተከታታይ 8 ቀናት እየተላለፈ የሚገኝ በየቀኑ በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ .. የተለያዩ አገልጋዮች ሰሙነ ሕማማቱን እየተረኩር #ዛሬ ደርሰናል። በሚያገኙት አማራጭ ይከታተሉ።

በማሕበራዊ #ሚዲያ በThe Christian News YouTube channel ላይ ይመልከቱ። https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
👍7😭32🔥2🙏1
የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በገረሴ ከተማ አደባባይ በወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት በድምቀት ተከበረ።

በመዝሙርና በቃል፣ በድምቀት ተከብሯል።

ገረሴ-ውልአ

በያላችሁበት አከባቢ እንዴት እየተከበረ ነዉ ? ፎቶዎች ላኩልን 🙏🙏
👍41🔥1
የወለንጭቲ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የትንሳኤ በዓል በጋራ አከበሩ።

ዛሬ ሚያዝያ 12/08/2017 ከማለዳው 11ሰዓት ጀምሮ በፕሮግራሙ ላይ የቦሰት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ጉተማ ቢፍቱ በመገኘት #እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ስላስተላለፉልን በህብረቱ ስም አመስግነዋል።

አጠቃላይ ፕሮግራሙ ላይ በዝማሬ በቃል በወረብ አምልኮ ለሀገር በመጸለይ የተከናወነ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የምስራቅ ሸዋ ዞን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ሰብሳቢ ፖስተር ሰለሞን ሽፈራዉ እና የቦሰት ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በመገኘት እንኳን አደረሳችሁ አስተላልፈዋል::

መሪዎች ከስፍራው ላደረሳችሁን መረጃ ከልብ እናመሰግናለን 🙏🙏
🔥41👍1
ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸዉን ታዉቋል።

ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች፡፡

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለኢትዮጵያውያን የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ምዕመናን መፅናናትን እንመኛለን።
👍16😭3🤔1🕊1💔1