The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ዋዕ ሁንደም ሞኦሃኔ
እግዚአብሔር ሁሉን ያያል

ስለዚህ ድንቅ ዘማሪ በድሩ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ 🙏🙏

መዝሙሩ የአማረኛ ትርግም (Subtitle) ስላለዉ ሁላችሁም ተባረኩበት https://youtu.be/Q2CPfbOPDeQ?si=bJuMnOh5nTW9rSCL
👍31🔥1
የህማማቱን ሳምንት በንስሃ እንቆይ ተብላችኋል!

አገራዊች የንስሃ አስተባባሪ ኮሚቴ ለ6 ቀናት የሚቆይ የንስሃ እና መመለስ የጸሎት ጥሪ አቀረበ። ኮሚቴው ቅዳሜ ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም  በሳሮማርያ ሆቴል መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ተደጋጋሚ የንስሃ እና የመመለስ ጥሪ ወደ ምድራችን እየመጣ መሆኑን ታሪካዊ ዳራ በመጥቀስ ያብራራ ሲሆን በተለይም የእውነትና የሕይወት ድምፅ አገልግሎት በኩል በመጋቢ ዘካሪያስ በላይ እግዚአብሔር ወደ ምድራችን ባመጣው ትንቢታዊ መልዕክት ትኩረት በማድረግ ለአገራዊ የንስሃ መርሃ ግብር ሲዘጋጅ መቆየቱን አንስቷል።

በአራት ምዕራፍ የንስሃ መርሃ ግብሩ የሚካሄድ ሲሆን በምዕራፍ 1 በአምስት አቅጣጫዎች ላይ ከፊታችን ሰኞ ሚያዝያ 6 ጀምሮ የህማማቱን ሳምንት ሙሉ ቅዱሳን ባሉበት አካባቢ በየአጥቢያቸው በመሰባሰብ በንስሃ ኑዛዜ እንደሚቆይ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት፦
– ሰኞ ሚያዝያ 6፦ የፅድቅ ተጠያቂነት፣
– ማክሰኞ ሚያዝያ 7፦ የህይወት ቀደም አገልግሎት ተጠያቂነት፣
– ዕሮብ ሚያዝያ 8፦ የንስሃ አገልግሎት ተጠያቂነት፣
– ሃሙስ ሚያዝያ 9፦ የእግዚአብሔር መንግስት ተጠያቂነት፣
– አርብ ሚያዝያ 10፦ የበጎ ስራ ተጠያቂነት
- ቅዳሜ ሚያዝያ 11፦ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ አገራት መካከል ስላለው ግንኙነት እንዲጸለይ አደራ ብሏል።

የንስሃ መርሃ ግብሩ በምዕራፍ 2  ከሚያዚያ 19  እስከ ግንቦት17 ለ5 ሳምንት የንስሃ ፍሬ እንዲሆን ትምህርት የሚሰጥበት እንደሚሆን ተነግሯል።

በምዕራፍ 3 ደግሞ ከግንቦት 19 እስከ 20 ቅዱሳን በያሉበት የንስሃው መዝጊያ የሚደረግ ሲሆን በምዕራፍ 4 ከግንቦት 25 – 27 በአዲስ አበባ የማጠቃለያ መርሃ ግብር እንዲሆን ታቅዷል።

ስለዚህ ሁላችሁ ቅዱሳን በዚህ አገራዊ የንስሃ መርሃ ግብር ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ ቀርቦላችኋል።
16👍7🔥1👏1
የዓመቱ ተሸላሚ #ክርስቲያን ጋዜጠኛ በመባል እውቅና ተሰጠው።

#እንኳን #ደስ አለህ 🙏🙏🙏

ከኤልሻዳይ ቴሌቪዥኝ ለተጠናቀረው ዘገባ ታምራት ሞቲ ነኝ። የሚል ድምፅ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ይሰማ ነበር።

ለክርስቲያን ሚዲያ እድገት #እና እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረገ እና እስካሁንም እየተጋ የሚገኝ እጅግ ተወዳጅ እና ሰዉ አክባሪ ወጣት ነዉ። ጋዜጠኛ እና አገልጋይ ታምራት ሞቲ

ከጋዜጠኝነቱ ባሻገር በስነፅሁፍ ስራዎቹም ይታወቃል። ለኤልሻዳይ፤ ለኢቫንጅሊካል ፤ ለGMM ቲቪ የዜና ምንጭ በመሆን አገልግሏል። እኛን ጨምሮ ዛሬ ላሉት ብዙ ታዳጊ ክርስቲያን ጋዜጠኞች አርዓያ ነው።

#አሁን ደግሞ በGMM TV "ጉብዝናዬ" የሚል ፕሮግራም እየሰራ በአገልግሎት ለሌሎች ምሳሌ የሚሆኑ አርዓያ ባለታሪኮችን እያቀረበ የጉብዝና ወራታቸውን ጌታን በማገልገል እንዴት እንዳተረፉ በማስታወስ ብዙዎችን እያገለገል ይገኛል።

አገልጋይ ፣ ጋዜጠኛ ፣ ተወናይ እና የመፅሐፍ ከታቢ ታምራት ሞቴ ከሰሞኑ በጋዜጠኞች ዘርፍ የዓመቱ ተሸላሚ በመሆን እውቅና ተቀብሏል።🏅🏆

የሳቤህ ምንጭ ዓለም አቀፍ አገልግሎት በ8 ዘርፎች በየአመቱ በሚያደርጋቸው የእውቅና መርሃ ግብር ላለፉት 12 ዓመታት በመንፈሳዊ ቴሌቪዥን የጋዜጠኝነት አገልግሎቱ እያበረከተ ላለው #መልካም አስተዋፅኦ ይገባሃል ሲል የ2017 በጋዜጠኞች ዘርፍ አሸናፊ አድርጎታል።

ደስስስስስስስስስስስስስስስስ ብሎናል! The Christian News - የክርስቲያን ዜና የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን።

አዘጋጆቹ ስላበረከቱት ሽልማት እና እውቅና ከልብ እያመሰገንን ወዳጃችን የበለጠ እየሰራ እንዲሄድ እናበረታታዋለን። 🙏🙏🙏

በድጋሜ እንኳን ደስ አለህ🙏🙏🙏
👍114🔥1
እውቅና ተሰጣቸው።

ለመጋቢ ለገሠ ጸጋዬ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም በሆሳዕና ከተማ ተዘጋጀ።

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የሆሳዕና ክልል ላለፉት 29 አመታት በፅናትና ታማኝነት ክልሉን ያገለገሉትን መጋቢ ለገሠ ጸጋዬን በመሀል ሆሣዕና መሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ከ52 በላይ በክልሉ ስር የሚገኙ የአጥቢያ መሪዎችና አገልጋዮች እንዲሁም የተለያዩ ጥሪ የተዳረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

መጋቢ ለገሠ ጸጋዬ በክልሉ አገልግሎት ሲጀምሩ የነበረው አንድ ክልል በአሁን ሰዓት ወደ ስድስት ክልሎች ሲያድግ የአጥቢያዎች ብዛት ደግሞ 112 መድረስ ችሏል።

በአካባቢው ያለው የቤተክርስቲያኒቱ አማኞች ቁጥርም ከ6900 በመነሳት በአሁን ሰዐት ከ70000 መብለጡን በመድረኩ ተገልጿል። በዚህ ሁሉ አመራር በመስጠት ላገለገሉት መጋቢ ለገሠ ጸጋዬ ቤተክርስቲያን እውቅና ሰጥታለች።

በዝግጅቱ ለመጋቢ ለገሠ ጸጋዬና ባለቤታቸው የተለያየ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን መጋቢ ለገሰም ስለሆነው ሁሉ እግዚአብሔርን በማመስገን በአገልግሎታቸው ከጎናቸው ለቆሙትና አብሮነታቸውን ላሳዪአቸው ሁሉ ምስጋና በማቅረብ ቤተክርስቲያንን ባርከዋል።
👍113🔥1
መካነ #ኢየሱስ #አዲስ ኮሚሽነር መረጠች።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማት #እና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን 21ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አቶ ሰለሞን ሽፈራው ለቀጣይ አራት አመታት በኮሚሽነርነት እንዲያገሉ በመምረጥ ጉባኤውን አጠናቋል።

ወደ አገልግሎቱ የሚመጡት አቶ ሰለሞን ሽፈራ የአገልግሎት ጊዜያቸውን ባጠናቀቁት ዶ/ር አበያ ዋቅወያን ምትክ ይሆናል።

አቶ ሰለሞን ኮሚሽኑን በተለያዩ ደረጃዎች ላለፉት አስርት አመታት ያገለገሉ ሲሆን በቤተ ክርስቲያኒቱ የልማት አገልግሎት ፍልስፍና ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱም ለአቶ ሰለሞን አዲስ የአመራር ምዕራፍ #መልካም ምኞትዋን ገልጻለች።

ኮሚሽኑንም ወደሚቀጥለው ሁለንተናዊ የተጽኖ ምዕራፍ ለማሻገር ቤተ ክርስቲያን በአቶ ሰለሞን አመራር ላይ በፀሎት የሆነ እምነቷን አስቀምጣለች።
👍71🙏1
#አስደሳች #ዜና
ታፍነው የተወሰዱት ፓስተር ተለቀቁ

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ስብከት ላይ እያሉ በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱት አሜሪካዊው ፓስተር በደቡብ አፍሪካ ፖሊሶች ድጋፍ መለቀቃቸውን ፎክስ ዜና አስነብቧል።

ባሳለፍነው ሃሙስ በደቡብ አፍሪካ ፌሎሺፕ ባፕቲስት ቸርች ኢን ማዘርዌል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየሰበኩ የነበሩ ጆሽ ሱሌቫን የተባሉ አሜሪካዊ ፓስተር "አራት የታጠቁ እና ጭምብል ያጠለቁ ወንዶች ናቸው ፓስተሩን አፍነው የወሰዷቸው" ሲሉ የፖሊስ ቃል አቀባይ ካፕቴን አንድሬ ቤቴጅ ለቢቢሲ መግለጻቸው ይታወሳል።

ፎክስ ኒውስ ከሰዓት በፊት ይዞት በወጣው ዘገባ የደቡብ አፍሪካ የምስራቅ ኬፕ ግዛት ባለስልጣናት ማክሰኞ እለት በተከፈተ የተኩስ እሩምታ ታፍኖ የነበረውን አሜሪካዊ ፓስተር ማዳን መቻላቸው ገልጸዋል ሲል ዘግቧል።

የ34 ዓመቱ ፓስተር ወደ ደቡብ አፍሪካ ከቤተሰባቸው ጋር ያቀኑት በፈረንጆቹ 2018 ሲሆን፣ አላማቸውም በዦሳ ቋንቋ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ ክርስቲያን መመሥረት እንደነበር ዘገባው አክሏል።
👍137🔥1🙏1💔1
የበዓል ስጦታ ከWSG ሚኒስትሪ

WSG የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን ምክኒያት በማድረግ ለ1ሺህ አባወራዎች የምግብ ድጋፍ አደረገ።

WSG ድጋፉን ብራይት ስታር ከተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ከ1ሺህ ለሚበልጡ አባወራዎች የምግብ እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍ ያደረገው።

ድጋፉ የተደረገው የብራይት ስታር ፍሪደም ት/ቤት ተማሪ ወላጆችና የመንግስት ት/ቤት ለሚገኙ ተማሪ ወላጆች ነው ያደረገው።

የWSG ሚኒስትሪ አስተባባሪ ወ/ሮ ሃዊ በዳሳ ስጦታው ሁሉም በየቤቱ ፋሲካን በደስታ እንዲያስተላልፍ የታሰበ ነው፡ ስለዚህ እንኳን ደስ አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

WSG የከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች፡ ለጥፋት የተጋለጡና ማደሪያቸውን ጎዳና ላደረጉ ወጣቶች የመንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ WSG (Win Souls for God Evangelical Ministry) በአውሮፓ በተለይም በስዊድን ለሚገኙ ወገኖች (Mission back to Europe) በሚል ስያሜ የታረደውን በግ ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል መስበነክ ላይ ይገኛል።
መረጃውን ጋዜጠኛ ጸጋይብጻህ ኢሳይያስ አደረሰን።
👏73👍1🔥1
ሲቃዩ ሊብራራ አይችልም። የመጨረሻውን ስቃይ ተሰቃየ #ሰሙነ #ሕማማት ከሆሳዕና #እስከ ትንሳኤ #እና ፕሮግራም

ከኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ #እና ለተከታታይ 8 ቀናት እየተላለፈ የሚገኝ በየቀኑ በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥን ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ .. የተለያዩ አገልጋዮች ሰሙነ ሕማማቱን እየተረኩር #ዛሬ ደርሰናል። በሚያገኙት አማራጭ ይከታተሉ።

በማሕበራዊ #ሚዲያ በThe Christian News YouTube channel ላይ ይመልከቱ። https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1
👍7😭32🔥2🙏1