እዚህ የመጣነው አንድ መልዕክት ለመናገር ነው። እሱም የወንጌል መልዕክት ብቻ ነው። #መስቀል አደባባይ አይቀርም። https://youtu.be/yrgyoCAaZVA
YouTube
እዚህ የመጣነው አንድ መልዕክት ለመናገር ነው። እሱም የወንጌል መልዕክት ብቻ ነው። #መስቀል አደባባይ አይቀርም።

#gospel #billy
#thechristiannews #singer #jesus #jesuschrist #መልካም በዓል #marsiltvworldwide #yonatanaklilu #abiye #ebc #fana_tv #ebs #reels
#saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopia …

❤13👍4👏2🔥1
የዛሬ 65 አመት ነው አባቴ ቢሊ ግራሃም እዚህ #አዲስ አበባ #ኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌል የሰበከው። እኔም #ዛሬ እዚህ ቆሜ መስበክ በመቻሌ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ቀናቱ መገጣጠማቸውም #የእግዚብሔር ስራ ነው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት የወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ልጅ ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።
ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወደ #ኢትዮጵያ ስመጣ ይሄ ለ11ኛ #ጊዜ ነው። በአደባባይ #ወንጌል ስሰብክ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከ117 ሺህ በላይ ሰው በመስቀል አደባባይ የምስራቹን ወንጌል ለመስበክ በመምጣቱ በጣም ተደስቻለው። ህይወታቸውን ለኢየሱስ የሰጡና ለመከተል የወሰኑ ሰዎች በመኖራቸው እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ብለዋል።
ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና። ሐዋርያት ሥራ 4፥12
እንደ #አዲስ ክርስቶስን ለመቀበል ለወሰኑ ሰዎችና እዚህ እነርሱን ለሚከታተሉ ሰዎች እንድትጸልዩ አደራ እላለሁ። #ነገ ለሚኖረው ሁለተኛ #ቀን የመለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ፕሮግራም ጸልዩ።
በዚህ ፕሮግራም በመዝሙር #እና አምልኮ ያገለገሉ በሙሉ በጣም አመሰግናችኋለው። ከ1600 በላይ ለሚሆኑና ይሄ ፕሮግራም እዉን እንዲሆን ለተጉ አብያተ ክርስቲያናት ትልቅ ምስጋና አለኝ። ወንጌሉን ለመስበክ ላላቸው ታላቅ ልብ እግዚአብሔርን አመሰግናለው።
#መስቀል አደባባይ የሚደረገው የአምልኮ ፕሮግራም #ነገ እሁድ የሚቀጥል ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በFacebook እና በYoutube በቀጥታ ስርጭት የምናስተላልፍ ስለሚሆን ከከተማ እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።

❤14👍7🔥2👏2🙏1🕊1
ቀጥታ ስርጭት ከመሰቀል አደባባይ ሊንኩን ተጠቀመው ይከታተሉ። አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን። https://www.youtube.com/watch?v=XIJRsgYEZZI
YouTube
Day 2 🔴 #ቀጥታ ስርጭት ከ#መስቀል አደባባይ #livestreaming Franklin Graham is live
🔴 #ቀጥታ ስርጭት ከ#መስቀል አደባባይ #livestreaming
ወዳችሁ እና ፈቅዳችሁ ስለምትመለከቱን ከልብ እናመሰግናለን!!! Like, Share ማድረጎን አይርሱ!!
#በ0930699543_ማንኛውንም_አይነት_የክርስቲያን_መረጃዎችን_በቴሌግራም_ለክርስቲያን_ዜና_ሚዲያ_መጠቆም_ይችላሉ
#The_Christian_News
Welcome to Our channel This is The Christian News from…

👍8❤5🔥1
ከ320 ሺህ በላይ ሰው #መስቀል አደባባይ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በመገኘቱ የተሰማኝን #ትልቅ ደስታ እገልጻለው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።
ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ የመስቀል አደባባይ የማጠቃለያ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወንጌል ሃይል አለው። #ዛሬ ንሰሃ በመግባት #ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል #ስለ ወሰኑ ሰዎች ጌታን እናመሰግናለን።
ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?”
ዮሐንስ 11፥25-26
ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ትልቅ አስተዋጾ ላደረጉ #እና ለጸለዩ ወዳጆቼ እና አብያተ ክርቲያናት በሙሉ #ትልቅ #ምስጋና አለኝ። አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ቃል እየጸናችሁ፡ የምትሰሩትን የደቀ መዝሙር ማድረግ ስራ #እግዚአብሔር ይባርክ።
ዛሬ በነበረን የዝማሪው ጊዜ በርካታ ዘማሪዎች በዝማሬ እና አምልኮ ከቀትር በኋላ እስከ ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ አገልግለዋል። መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ መርሃ ግብር ላይ ለተሳፋችሁ በሙሉ አመሰግናለሁ።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና 2ቱን ቀናት በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ ስናደርስ ቆይተናል።
አብራችሁን ስለነበራችሁ እና ስለተከታተላችሁን ስለሰጣችሁን አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።

👍28❤16🙏3🔥1
መስቀል አደባባይ ምንም አይነት የፖለቲካ ይዘት ያለው አንድም አይነት ጥያቄ አልተነሳም መልዕክትም አልተላለፈም።
አንድም ፖለቲከኛ በቦታው ተገኝቶ የፖለቲካ መልዕክቱንም ሲያስተላልፍ አልተገኘም። ለ2 ቀን በመስቀል አደባባይ የነበረው እና ሲመለክም ይሁን ሲሰበክ የነበረው ኢየሱስ ብቻ ነበር።
ኢትዮ ፎረም የተባለው ሚዲያ ስለምን እያወራ እንደሆነ አልገባንም። እጅግ ሲበዛ በወንጌላውያን አማኞች ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ግን ትንተናውን በማቆለጳጰስ ይጀምራል።
ከዛም ወንጌል ሰባኪዎችን ወደ ምድር ፈጥፍጦ ወንጌላውያንን ከሌላው ኢትዮጵያውን ነጥሎ ለመምታት ከፖለቲካው ጋር ሲደምራቸው እና አገልጋዮችንም ተላላኪ አድርጎ ይተነትናል።
ከፖለቲካ ጋር የተገናኘ የተለየ ትንታኔ አለኝ ካለ በራሱ መንገድ ይተንትነው ግን አንድን የወንጌል ሰባኪ በአደባባይ ስም እየጠቀሰ "ተላላኪ" እያለ መዝለፍ ግን እጅግ ሲበዛ ነውር እና ከጋዜጠኛ ነኝ ብሎ ከሚያስብ ሰው የማይጠበቅ እንደሆነ የዘነጋው ይመስላል።
ፍራንክሊን ግርሃም ኢትዮጵያ ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ለተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት አላቸው ኢትዮጵያ ውስጥም ላለፉት 40 ዓመታት የመልሶ ሟቋቋም ስራዎች እና የእርዳታ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል።
ፍራንክሊን ግርሃም ከ1991 ጀምሮ ሲመጡ ይህ ለ11ኛ ጊዜ እንደሆነ ይታወቃል። በሰሜን ኢትዮጵያ ሰመሪታን ፕርስ በርካታ የንጹ ውሃ ግድጓዶች እና የጠብታ ውሃ መስኖ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።
ይህንን ሁሉ አመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ አንድም ቀን ሱምን ጠርተው የማያውቁ ሚዲያዎች ዛሬ ወንጌልን ለመስበክ ሲዘጋጁ ግን በነቀፋ አፋቸውን ለመክፈት ፈጠኑ እንደ እኔ ከእንደዚህ አይነት በወንጌላውያን ጥልቅ ጥላቻ ከሰከረ ጋዜጠኛ እና ሚዲያ እራሳችሁን ጠብቁ።

👍38❤10👏4🔥2👌1🕊1
#ለማ ጎሶማ ብለሲንግ ሚኒስትሪ የምስረታ በዓሉን
አከበረ።
የምስረታ በዓሉን በአለታ ወንዶ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ያካሄደው ፕሮግራሙ በወንጌል አርበኛው ለማ ጎሶማ ልጆች አማካኝነት የተቋቋመ ነው።
ሚኒስትሪው በወንጌል አርበኞች፣ ሚሺነሪዎች እንዲሁም በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍን ማድረግ፣ ማሰልጠን እንዲሁም የወንጌል አገልጋዮችን ማሰማራትን ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡
ለ3 ቀናት በተካሄደ የምስረታ ኮንፍረንስ ፕሮፌሰር ዝናቡ ገብረ ማሪያም እና መጋቢ ታደለ ነጋሽ አገልግለዋል። ተጋባዥ ዘማሪያን በዝማሬ አገልግለዋል፡፡
ሚኒስትሪው በቀጣይ የአባቶች ባርኮት ኮንፍረንስን ጨምሮ የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚካሄዱ የሚኒስትሪው ፕሬዝደንት አቶ እስጢፋኖስ ለማ ተናግረዋል፡፡
በምስራቁ የአገራችን አካባቢዎች ሶስት የወንጌል አገልጋዮችን በመላክ ከምስረታው ምርኃ ግብር አስቀድሞ አገልግሎቱን መጀመሩን የሚኒስትሪው የውጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሚሳኤል ለማ ነግረውናል፡፡

❤5👍2🔥2🙏1
በጅማ ዞን ጋቲራ የምትባል ከተማ በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ተፈጸመ።
ሃሙስ ለሊት 9 ሰዓት፡ በጅማ ጋቲራ ከተማ የመካነ ኢየሱስ ቤ/ክ የአምልኮ ስፍራ እና የምዕመናን ቤቶች፡ እንዲሁም ምዕመናን ላይ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁ ሰዎች መሆናቸውን ቤተ ክርስቲያኗ ይፋዊ በሆነ የፌስቡክ ገጿ አሳውቃለች።
ቤተ ክርስቲያኗ የኦሮሚያ ክልል መንግስት፡ የጅማ ዞን አስተዳደር እና የጋቲራ ከተማ አስተዳደር ይሄንን ድርጊት ምርመራ አድርገው መልስ እንዲሰጡ ጠይቃለች። ምዕመናንም አጥብቀው እንዲጸልዩ አሳስባለች።

😭15🤔4👍2🙏2🕊1💔1
የተወደደው ኢንጂነር ፓ/ር ልዑለቃል ካሴ የፓ/ር ዘነበች ገሠሠ ባለቤት ወደ ሚወደው ጌታ ሄዷል።
ፈገግታ የማይለየው ፣ ትህትና መታወቂያው ፣ በስራው ትጉ፣ ለልጆቹ እጅግ መልካም አባት፣ ለጓደኞቹ የህይወት ምሳሌ እና ለትዳር አጋሩ ለፓ/ር ዘነበች ገሠሠ እውነተኛ ረዳት እና የአገልግሎቷ ብርታት የሆነው ኢንጂነር ፓ/ር ልዑለቃል ካሴ ወደ ሚወደው እና በፍጹም ንጽህና እና በማይበርድ ፍቅር ወዳገለገለው ጌታ መሄዱን ከባለቤቱ ከፓ/ር ዘነበች የሰማሁት በማለዳ ነበር።
ፓ/ር ዘነበች ከህንድ እጅግ በሚያሳዝን ቃል በእምባ :-
"ዳዲ ጥሎኝ ወደጌታ ሄደ" አለችኝ በእውነት ልቤ እጅጉን አዘነ
#ዛሬ ታላቅ ወንድማችንን ኢንጀነር ፓ/ር ልዑለቃል ካሴን አጥተናል እጅግ አዝኛለሁ።
ኢንጂነር ለህትመት የበቁ ሦስት መጽሐፎችን አበርክቶልን ወደ ሚወደው ጌታ ሄዷል።
"አክሊል" የመጀመሪያ መጽሐፉ ነው እንደፃፈልን አክሊሉን ሊቀበል ወደ ጌታ ሄዷል።
ሁለተኛ መጽሐፉ "የራዕይ መጽሐፍ እኔ እንደተረዳሁት" የሚል ነበር የተረዳውን ጽፎልን እሱ ግን ወደ ጌታው ሄዷል።
ሦስተኛው መጽሐፍ በቅርቡ ያስመረቀው "ይመለሳል" የሚል የጌታ ዳግም ምጽአት የሚተርክ ድንቅ መጽሐፍ አበርክቶልን ከእሱ ጋር ሊመለስ ቀድሞን ሄዷል።
1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።
መጽናናት ለፓ/ር ዘነበች ገሠሠ ፣ ለልጆቻቸው ፣ ለህይወት ምንጭ እየሱስ ቤ/ክ አባላት እና አገልጋዮች እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ እንዲሆን እንመኛለን። ነገ እሑድ 7:00 ሰዓት ቦሌ ኤርፖርት የሚደርሱ ሲሆን ቀብር ሰኞ መሆኑን እንገልጻለን። ፖስተር ዳኒ እንደፃፈዉ

💔16😭9👍2❤1🕊1
#ቤተክርስቲያን በመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቁ ዜጎች ድጋፍ አደረገች።
#Ethiopia | አራራ ዋቃዮ አዱኛ ቤተ ክርሰቲያን በምሥራቅ ሸዋ ዞን በፋንታሌ ወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ባስከተለዉ ጉዳት ችግር ዉስጥ ላሉ ሕብረተሰብ በ3,107,000 ብር 800 ኩንታል ዱቄት አዘጋጅታ ለህዝቡ አከፋፈለች።
የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ነቢይ መሠረት ታዬም ለሕብረተሰቡ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ድጋፉም ለ3 ሺህ 200 አባወራዎችና እማወራዎች ተከፋፍሎ ለያንዳንዳቸው 25 ኪ.ግ. ተዳርሷል።

👍23❤16👏3🔥2🤔2💯1
የአጥቢያ #ቤተክርስቲያን የቤተሰብ አገልግሎት ምን ምን መካተት ሊኖርበት ይገባል?
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ሚኒስትሪ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ አገልጋዮች ቤተሰብ ተኮር ስልጠና ሰጠ።
ስልጠናው ለሁለት ቀናት በቀነኒሳ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ተወካዮች ከስልጠናው መልስ በሚሄዱባቸ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቤተሰብ ተኮር ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተነግሯል።
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ሚኒስትሪ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳሮን ውድነህ፣ ስልጠናው አንዲት ጠንካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዴት የቤተሰብ አገልግሎት ይኖራታል፣ ምን ምን መካተት ይኖርበታል፣ አለመኖሩ ምንም ምን ችግሮችን ያመጣል በሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት መካሄዱን
ለክርስቲያን ዜና ገልጸዋል።
ዘ ክርስቲያን ኒውስ ያናገራቸው የስልጠናው ተካፋዮች እንደ አገልጋይም እንደ ባለትዳርም ብዙ የተጠቀምንበት ስልጠና ነው ብለውታል።
እዚህ የተገኘው ልምድ ወደ ቤት ተወስዶ የሚኖር ነው ሲሉ ገልጸውታል።
የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ፣ ጠንካራቤተሰብ፣ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና እና ለታላቁ ተልዕኮ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል። በመሆኑም ይላሉ ወ/ሮ ሳሮን አብያተ ክርስቲያናት ለቤተሰብ አገልግሎት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ ተገኝተን ዝርዝሩን አቀረብንላችሁ።

👍9❤2🔥1
#እሁድ የት ናቹ ? #ምክንያቴ #ብዙ ነው።
#እግዚአብሔር ሰውን ለአላማው ከፈለገው ከምን አንስቶ እንደሚጠቀምበት ፓስተር ተከስተ ጌትነት ህያው ማሳያ ነው።
የትናንቱ ቆሎ ተማሪ የዛሬው ፓስተር ተከስተ ላለፉት ሀያ አምስት አመታት በላይ በዘለቀው አገልግሎቱ ተሰምተው የማይጠገቡ፣ ተደምጠው የማይሰለቹ የዝማሬ አልበሞችን አውጥቶ ለሚሊዮኖች የመባረክ ምክንያት ሲያደርገው የተመለከተ እግዚአብሔር ይችላል እንጅ ሌላ ምን ሊል ይችላል?
የመጋቢ ተከስተ ጌትነት ዝማሬዎች የዜማ ምጥቀት፣ የግጥም ጥልቀት የብዙሀንን ልብ ለወንጌሉ ወለል አድርገው ያስከፈቱ ሚሊዮኖችን ለጌታ ፍቅር ያንበረኩኩ ሀያል የወንጌል መሳሪያዎች ሆነው ለአመታት እየተደመጡ ዘልቀዋል።
ተኬ በ80ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን አሀዱ ተብሎ የተጀመረው የዝማሬ ጉዞው በብዙ ድልና በብዙ መውደቅ መነሳት ዛሬ እዚህ ደርሶ ምክንያቴ ብዙ ነው ብለን አብረነው ጌታን ልናመልክ እንሆ ቀኑ ተቆርጧል።
መጋቢት 14 ከሰዓት በጊዮን ሆቴል እንገናኝ።
ለማመስገን ምክንያታችን ብዙ ነው።

👍28❤16🔥1🙏1
#የመሠረተ #ክርስቶስ #ቤተክርስቲያን #አዲስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሾመች።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ መጋቢት 12 እና 13፤ 2017 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛው መደበኛ ስብሰባ ለቀጣይ አራት አመታት ቤተክርስቲያኒቱን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ መጋቢ ሰብረላ ከድርን ሾሟል።
መጋቢ ሰብረላ ከደር በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ላለፋት 33 አመታት ከአጥቢያ ጀምሮ ያገለገሉ ሲሆን በተለይ ባለፈው ስድስት አመት በዋናው ቢሮ የእረኝነት አገልግሎት መምሪያ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገባቸው ይታወሳል።
የሹመት ስነስርዓቱን ያስፈጸሙት የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ለቤተክርስቲያን ሰውን የሚሰጠው #እግዚአብሔር እንደሆነ በመግለፅ አዲሱ ምክትል ፕሬዚዳንትም ከእግዚአብሔርና ከቤተክርስቲያን የተቀበሉትን አደራ በትጋት እንዲወጡ አሳስበዋል።
#መሠረተ_ክርሰቶስ_ቤተክርስቲያን!

👍11❤5🔥2🙏1👌1
7 #አገልጋዮች ታስረዋል። #ቤተክርስቲያን አሁንም ስደት እየደረሰባት ነው። ካውንስሉ
#የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች በሀገራችን የተለያዩ ቦታዎች በወንጌል አማኞች ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት እና እስር በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።
ከደቂቃዎች በፊት በተሰጠው መግለጫ በጅማ ፤ በከሰም ቀበና ፤ በጅግጅጋ እና በቦምባስ ከተማዎች በወንጌላውያን ላይ እየረሰው ያለው እስር እና እንግልት እንዲሁም ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት እንዲቆም ጠይቋል።
#ካውንስሉ በመግለጫው ይህ መግለጫ እስኪሰጥበት ደቂቃ ድረስ በጅግጅጋ እና በቦምባስ ከተማ 7 ምዕመናን በእምነታችው ምክንያት እንደታሰሩ ገለጿል።
#በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ ጋትራ ከተማ የምትገኘው ማሕበረ ምዕመናን ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ድብደባ እና የጸሎት ቤት መቃጠልን ያስታወሰው መግለጫው ምዕመናን የጸሎት ቤቱ ፈርሶባቸው አሁንም በሜዳ ላይ እያመለኩ እንደሚገኙ ጠቅሷል።
በተመሳሳይ #በአፋር ክልል በዱለቻ ወረዳ ውስጥ ባሉ የከሰም ቀበና እና በድሆ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ላይ ዝርፊያ እና ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እየተደረገ እንደሆነ በመግለጫው ተጠቅሷል።
#በሱማሌ ክልል ደግሞ በጅግጅጋ እና በቦምባስ ከተማ ውስጥ በድምሩ 7 ምዕመናን በእርስ ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ የሚመለከተው አካላት በእምነታቸው ምክንያት ለእስር የተዳረጉ ምዕመናን እንዲፈቱ ካውንስሉ ጠይቋል።
ካውንስሉ በመግለጫው የእኔ ሃይማኖት የበላይነት ሊረጋገጥ ይገባል ባዮች በአከባቢያችን ሌላ እምነት በነጻነት ሊንቀሳቀስ አይገባም በማለት ከሃይማኖት አልፈው ሰላም እና ሁከት በሚፈጥሩ አካላይ ሕጋዊ የእርምት እርምጃ በመውሰድ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተባባሰውን ሃይማኖታዊ ጥላቻ እንዲቆም የሚመለከተውን አካላት ጠይቋል።

👍18❤4🙏3🕊1😭1
#በካፋ ዴቻ የክርስቶስ #ኢየሱስ ደቀመዛሙርት የሆኑት መጽሐፍ ቅዱስን በመማር ለመድረክ አገልግሎት የበቁ በሰርተፍኬት ተመረቁ።
#በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት በምዕራብ ደቡብ ቀጣና ቦንጋ ዙሪያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያናት ሕብረት በቦባ ገጫ ቃ/ሕ/ቤያን ላለፉት 7 ወራትን የደቀመዛሙርት ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ በክብር በድል ለመድረክ አገልግሎት የመብቃት ሰርተፍኬት በምረቃ ተቀብለዋል።
#የደቀመዛሙርትን ምረቃ ስነ-ስርዓት በማስፈጸም ከቦንጋ ዙሪያ ቃ/ሕ/ቤያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የሕብረቱ መንፈሳዊ ዘረፉ ፦ወንጌላዊ መለሰ መሮ እንዲሁም የተጠሩ የአብያተክርስቲያናት ሕብረትም ተገኝቷል።
#ወንጌልን ወደ ውጭ መስበክ ወደ ውስጥ ደቀመዛሙርት በማድረግ መስራት የተሰጠን የተልዕኮአችን ዋነኛውና ቀዳሚ አደራነት ያለው አገልግሎት ነውና በያለንበት ቦታ ሁሉ ወንጌልን ላልዳኑት እየሰበክን የዳኑትን የክርስቶስ ደቀመዛሙርት በማድረግ ወንጌልን ከቀድሞም ይልቅ መስራት አለብን እግዚአብሔር እንድንሰራ በጸጋው እንዲረዳን መልዕክት አስተላልፈዋል።
መረጃውን ሚሽነሪ አክሊሉ ከካፋ ዞን አደረሰን።

👍11🔥2❤1🙏1
ለልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት የሚረዱ የመጽሐፍት ድጋፍ ከራፊኪ ፋውንዴሽን ለኢት/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ተደርጓል፡፡
መጽሐፍቶቹን የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሣ ፋውንዴሽኑ ከሚገኝበት ሞጆ ከተማ በመገኘት ከራፊኪ ፋውንዴሽን አለምአቀፍ ዳይሬክተር ካሬን ኤሊዬት እና ሌሎች የተቋሙ አህጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ አመራር ተረክበዋል፡፡
ራፊኪ ፋውንዴሽን በተለያዩ 10 የአፍሪካ ሀገራት መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፤ በትምህርት፤ በመምህራን ስልጠና፤ በወላጅ አልባ ህጻናት እና ባልቴቶች ድጋፍ የሚሰራ አህጉር አቀፍ ተቋም ሲሆን ከኢት/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ ጋር በመተባበር በተጠቀሱት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙርያ እየሰራ ይገኛል፡፡
መጽሐፍቶቹ ልጆች እና ወጣቶችን በእግዚአብሔር ቃል ቀርጾ ለማሳደግ የሚረዱ፤ ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የሚረዱ እና በልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ተቀርጾ እየተሰራ ባለው ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅ፤ ሁለንተናዊ ቤተመጻህፍትን በየማህበረምዕመናኑ ማደራጀት ለሚለው የትኩረት አቅጣጫ ጠቃሚ መሆናቸውን የመምሪያው ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሣ ገልጸው፤ ለአገልግሎቱ ለተደረገው ድጋፍ ራፊኪ ፋውንዴሽንን አመስግነዋል፡፡
የኢ/ወ/ቤ/መ/ኢ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ መጽሀፎቹን በአይራ ከተማ ለሚገኘው የቤተክርስቲያኒቱ ኦነስሞስ ነሲብ ሴሚናሪዮም እና በግምቢ ጆርጎ ሲኖዶስ ግምቢ ከተማ ለሚገኘው ለግምቢ ሁለንተናዊ ሴሚናሪ የመጽሐፍት ድጋፍ አድርጓል።
መጽፍቶቹንም ወንድማገኝ ኡዴሳ በምዕራብ ወለጋ አይራ ከተማ በመገኘት ለሴሚናሪው ፕሪንሲፓል ቄስ አለሙ ብርሃኑ እና በግምቢ ከተማ በመገኘት ለሴሚናሪው ዲን ቄስ ተስፋ ኡጁሉ በማስረከብ በሴሚናሪዎቹም ጉብኝት አድርገዋል።

❤5👍3👏3🔥1
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ታገደ።
ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።
በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል

👍31👏5❤3🔥1😭1
#ቢሾፍቱ #ስለ #ወንጌል ትጣራለች።
ላለፉት 34 ዓመታት በቢሾፍቱ ከተማ ወንጌልን የማድረስ ስራን ሲከውን የቆየው የቢሾፍቱ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት "ቢሾፍቱ ስለ ወንጌል ትጣራለች" በሚል ሃሳብ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ።
በሰጡት መግለጫ ከ100 በላይ አባላት እና አጋር አባላትን ይዞ የሚያገለግል ሕብረት መሆኑን ጠቅሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአመት 2 ጊዜ የጀማ ስብከት እና የወንጌል ስርጭት በማድረግ ወደ ጌታ መንግስት የሚጨመሩትን አዳዲስ ነብሳት ላይ ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ሕብረቱ በአሁኑ ሰዓት የሰልጠና ማዕከላትን እና ደቀመዝሙራትን እና ተተኪ ትውልዶችን ለማፍራት የበለጠ ስራዎችን ለመስራት የራሱ የሆነ ሕንጻ ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ በመግለጫው በመጥቀስ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ ያሉ ምዕመናን በሙሉ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሕብረቱን በመደገፍ ሂደት ውስጥ የማሕበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች እና ተጠቃሚዎች ንቅናቄውን በመሳተፍ አብረው እንዲያገለግሉ የክርስቲያን ሚዲያ ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ወንድም ዘሪሁን ግርማ በመግለጫው በመገኘት አሳስበዋል።
ፓስተር ጻዲቁ አብዶ በበኩላቸው ከፍተኛ የመንፈሳዊ ስራዎች ከሚሰራባቸው ሕብረቶ መካከል አንዱ የቢሾፍቱ ሕብረት መሆኑን በመጥቀስ በሕብረቱ የተገለገሉትን ጨምሮ በመላው አለም የሚገኙ ቅዱሳን የእግዚአብሔር ስራ በጋራ እንድንሰራ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለ ነገር ለማስረከብ በጋራ እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አቀርበዋል።
https://gofund.me/6378ba81
ከ ወንጌል አማኙ ጎን አብሬ በተግባር እቆማለሁ እርሶስ???
- ንግድ ባንክ- 1000011144873
- ብርሃን ባንክ- 2600180029025

👍8❤4🔥2🙏1
የቤተክርስቲያን ወለል ተደርምሶ አራት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደረሰ።
ትላንት እሁድ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጎሮ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በሚገኘዉ ቤተክርስቲያን ዉስጥ አማኞች በአምልኮ ስነ-ስርዓት ላይ እያሉ ወለሉ ተደርምሶ አራት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአምቡላንስ አገልግሎት ባለሞያዎች በአደጋዉ ቦታ ፈጥነዉ በመድረስ ተጎጂዎችን ከተደረመሰዉ ጉዳጓድ ዉስጥ በማዉጣት ለተጨማሪ ህክምና በአቅራቢዉ ወደሚገኘዉ ጎሮ ጤና ጣቢያ ማድረሳቸውን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴለቪዥን ተናግረዋል።
ለአደጋዉ ምክንያት የሆነዉም የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ ክዳኑ በመደርመሱና ቤተክርስቲያኑ በመጸዳጃ ቤት ላይ የተሰራ በመሆኑ ነዉ። ጉዳት ከደረሰባቸዉ አራት ሰዎች መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸዉ።
የአምልኮ ስፍራዎች በርካታ ሰዎች የሚታደሙት ቦታ በመሆኑ ደረጃቸዉን የጠበቁና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ያሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ መሰረታዊ በመሆኑ ለዚህም የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች የዕምነቱ ተከታዮችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ኮሚሽኑ አሳስቧል።

👍9😭3💔2🔥1🙏1
ስጦታ የተበረከተላቸውን መኪና መልሰው ለቤተክርስቲያን የሰጡት የወንጌል አባት።
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠና ነቀምት ከተማ በተካሄደ ፕሮግራም ላለፉት 55 አመታት በወለጋ በሚገኙ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አጥቢያዎች፣ ክልሎች፣ ኮሌጅና ቀጠና ላገለገሉት የወንጌል አባት መጋቢ ተፈራ ጎንፋ የምስጋናና ዕውቅና መርሃ ግብር ተከናውኗል።
መጋቢ ተፈራ ጎንፋ በወንጌል አገልግሎታቸው ብዙ ያፈሩ የአሁኑ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንትን ጨምሮ በቤተክርስቲያኒቱ ከአጥቢያ እስከ ዋናው ቢሮ በተለያዩ ኃላፊነቶች እያገለገሉ የሚገኙ አገልጋዮችን ያሳደጉ እንዲሁም ከሀያ ዘጠኝ አመት በፊት ለተመሰረተው የወለጋ መሠረተ ክርስቶስ ኮሌጅ ምስረታ እና ዕድገት የደከሙ፤ በቤተክርስያኒቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀጠና ሆኖ የተቋቋመውን የምዕራብ ኢትዮጵያ ቀጠናን ከምስረታው ጀምሮ በዋና ጸሐፊነት ያገለገሉ፤ ለመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለአካባቢው አብያተክርስቲያናት የወንጌል እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና የተጫወቱ እንዲሁም በአካባቢው ማህበረሰብ እና መንግስት በጎ ተጽዕኖ በማሳደራቸው የሚታወቁ እጅግ የተወደዱ አባት ናቸው።
የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ዋናው ቢሮ፣ የአካባቢው ሐይማኖት አባቶች፣ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ተወካዮች፣ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅት ኃላፊዎችና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በተካሄደው የእውቅና ፕሮግራም እኚህ የወንጌል አባት ባለቤታቸው በተገኙበት የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ነገር ግን በስጦታ ያገኙትን ተሽከርካሪ #እኔ አገልግሎቴን ጨርሻለሁ ከዚህ በኋላ መኪና ለእኔ ሳይሆን ለቀጠናው ነው የሚያስፈልገው በማለት በጉባኤው ፊት በምዕራብ ኢትዮጵያ ለሚካሄደው የእግዚአብሔር መንግሥት ስራ አበርክተዋል።

❤38👍8🔥2🙏2💯1