The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
52 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
1.2 #ቢሊዮን ብር ለልማት ስራ የምታውለው ቤ/ክ

የመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን ለ2025 ዓ.ም 1.2 ሚሊዮን ብር ለልማት ስራዎች ለማዋል የኮሚሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ወስኗል። በቀጣይ በጀቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ቤተ ክርስቲያኗ ወንጌልን ከመስበክ ቀጥላ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገዝ ስራዎችን ትሰራለች።
👍81🔥1👏1
በቤተ ክርስቲያን የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅም የተያዘው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ተከሳሽ አብዱራህማን ነጋ የተባለ ነዋሪነቱ ቸሃ ወረዳ አዶሼ ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማስገኘት በማሰብ ከሌላ ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክ/ከተማ ጋሶሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የዝርፊያ ወንጀል ፈጽሟል፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመዉ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6፡30 በሚሆንበት ጊዜ የፎከስ ፌሎሺፕ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የሚገለገሉበትን ቅጥር አጥር ዘሎ በመግባት ንብረትነታቸው የቤተክርስቲያኑ የሆኑ ጠቅላላ ግምታቸው በድምሩ 33,050 ብር የሆኑ እቃዎች ከንብረት ክፍል ከፍቶ በማውጣት ከቤተክርስቲያኑ አጥር ግቢ ወደ ውጪ በመወርወር ከግብረ አበሩ ጋር ሊውሰድ ሲል የአካባቢው ሰዎች ድምጽ ሰምተው መጥተው ሊይዙት ሲሉ እገድላችኋለሁ እንዳትጠጉኝ እተኩሳለሁ ብሎ ያስፈራራቸው ሲሆን በጩኸት በመጡ ሰዎች ርብርብ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በዚህም አስቦ በፈጸመው በተራ የስርቆት ወንጀል ክስ መመስረቱን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ገልጸዋል፡፡

ክሱ የቀረበለት የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ በመቀየር በወንጀል ህጉ አንቀፅ 669 ንዑፅ አንቀፅ 3 መሰረት ጥፋተኛ በማለት የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ኤልያስ ሰብለጋ ጨምረው ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡ ሲል ያስነበበው ዳጉ_ጆርናል ነው።
👍93🔥1
የካቲት 29 እና 30 ቅዳሜ እና እሁድ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው ታላቅ ድግስ አስመልክቶ ካውንስሉ መግለጫ ሰጠ።

መግለጫውን የካውንስሉ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በካውንስሉ ጽ/ቤት ሰጥተዋል።

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ፡ ከዓመት በላይ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፡ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም፡ እድገት፡ ልማት የምንጸልይበት ይሆናል። እግዚአብሔርን በዝማሬ፡ በአምልኮ፡ በቃል የምናመልክበት ትልቅ ቀን ነው ብለዋል።

በመግለጫው አውቶብሶች በሚቆሙበት ስፍራዎች በጊዜ በመገኘት ወደ መስቀል አደባባይ እንድትመጡ ይሁን። በአካባቢው ከሚኖሩ የጸጥታ አካላት ጋር ትብብር በማድረግ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ አደራ።

በነዚህ ቀናት እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ በጾም ላይ ከሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር እንዲሆን አደራ ብለዋል።

ፕሮግራሙን ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከ ኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመሆን የተዘጋጀ ነው።
👍73🔥1
#2 ቀን ቀረው

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ

ከእውቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ሬቨረንድ ፍራንልኪን ግራሃም ጋር በምድራችን የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
👍74🔥2👏1🙏1
#ተጠንቀቁ

"ብሩክ እና ወርቁ ከተባሉ አጭበርባሪዎች እንድትጠነቀቁ" ካውንስሉ

ስማቸው ከላይ የተጠቀሱ ግለሰቦች ለአብያተ ክርስቲያናት መሬት ስላገኛቹ ቅድመ ክፍያ አስገቡ በማለት ገንዘብ ሲሰበስቡ ደርሼበታለው ብለዋል።

ግለሰቦቹ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ሰራተኞች ነን እያሉ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ካውንስሉ ገልጾ፡ ቤተ እምነቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አደራ ብሏል።
👍2
የወንጌላዊ ልጅ የሆኑት ሬቨረንድ ፍራንክሊን የካቲት 29 እና 30 ለሚካሄደው "መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ"ን አስመልክቶ ለሀገር ውስጥ የመንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ #ኢትዮጵያ በመጣሁበት #ወቅት ሃገሪቱ ጦርነት #ላይ የነበረች ቢሆንም ውብ ሃገር ውብ ህዝብ እንዳላችሁ አየሁ እኔም ዛሬ ወንጌል ለማገልገል እዚህ ተገኝቻለሁ ብለዋል።

የዛሬ 65 ዓመት አባቴ በኢትዮጵያ ሰብኳል። ከዛ በኋላ ብዙ ነገር ተለዋውጧል። ነገር ግን መልዕክቱም አልተቀየረም። ዛሬም ኢየሱስ ያድናል የሚል ህያው የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በኢትዮጵያ ምድር ይሰበካል ብለዋል።

የዛሬ 65 አመት አባቴ እንደሰበከው እኔም ዛሬ አገለግላለሁ፡ ልጄ ኤድዋርድ እዚህ አለ፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለቀጣይ 65 ዓመታት ማገልገል ይቀጥላል። 1980 ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጣሁ ጀምሮ ሃገራችሁ ኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦችን አይቻለው ሲሉም ተናግረዋል።

ምናልባት ፕሬዝደንት ትራምፕ በUSAID በኩል የሚገባን ድጋፍ ዋሽንግተን ላይ ባለ ሙስና ምክኒያት አስቁመውታል። ለአጭር ጊዜ ችግር ሊገጥም እንደሚችል አምናለው። ስጋት አይግባቹ ሰማሪታን ፐርስ አገልግሎቱን ይቀጥላል። ድጋፋችን ከአሜሪካ መንግስት ሳይሆን ከእግዚአብሄር ነው ሲሉም ከሰሞኑ የአሜሪካ መንግስት በUSAID በኩል የወሰደው እርምጃንም በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቢሊ ግርሃም የዛሬ 65 አመት በንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ተጋብዘው ማገልገላቸውን አስታውሰው ልጃቸው በአሁኑ ሰዓት ለማገልገል በመምጣታቸው እንዲሁም የሚመሩት ሳማሪታን ፐርስ ለሃገራችን ያበረከቱት ትልቅ ነገር ስለሆነ እናመሰግናለን ያሉት ደግሞ የካውንስሉ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ናቸው።
👍1810🔥1
#የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባ #አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃምን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው #እንኳን ደህና መጡ ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው መሆኑን፣ ሁሌ እንደሚፀልዩና ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እንደጎበኙ መግለጻቸውን ጠቅሰዋል።

ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውን አመልክተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላሳዩት #ፍቅር እና #መልካም ምኞት አመስግነዋል።
👍1311🔥1👏1
የዛሬ 65 አመት ነው አባቴ ቢሊ ግራሃም እዚህ #አዲስ አበባ #ኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌል የሰበከው። እኔም #ዛሬ እዚህ ቆሜ መስበክ በመቻሌ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ቀናቱ መገጣጠማቸውም #የእግዚብሔር ስራ ነው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት የወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ልጅ ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።

ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወደ #ኢትዮጵያ ስመጣ ይሄ ለ11ኛ #ጊዜ ነው። በአደባባይ #ወንጌል ስሰብክ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከ117 ሺህ በላይ ሰው በመስቀል አደባባይ የምስራቹን ወንጌል ለመስበክ በመምጣቱ በጣም ተደስቻለው። ህይወታቸውን ለኢየሱስ የሰጡና ለመከተል የወሰኑ ሰዎች በመኖራቸው እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ብለዋል።

ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና። ሐዋርያት ሥራ 4፥12

እንደ #አዲስ ክርስቶስን ለመቀበል ለወሰኑ ሰዎችና እዚህ እነርሱን ለሚከታተሉ ሰዎች እንድትጸልዩ አደራ እላለሁ። #ነገ ለሚኖረው ሁለተኛ #ቀን የመለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ፕሮግራም ጸልዩ።

በዚህ ፕሮግራም በመዝሙር #እና አምልኮ ያገለገሉ በሙሉ በጣም አመሰግናችኋለው። ከ1600 በላይ ለሚሆኑና ይሄ ፕሮግራም እዉን እንዲሆን ለተጉ አብያተ ክርስቲያናት ትልቅ ምስጋና አለኝ። ወንጌሉን ለመስበክ ላላቸው ታላቅ ልብ እግዚአብሔርን አመሰግናለው።

#መስቀል አደባባይ የሚደረገው የአምልኮ ፕሮግራም #ነገ እሁድ የሚቀጥል ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በFacebook እና በYoutube በቀጥታ ስርጭት የምናስተላልፍ ስለሚሆን ከከተማ እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
14👍7🔥2👏2🙏1🕊1
ከ320 ሺህ በላይ ሰው #መስቀል አደባባይ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በመገኘቱ የተሰማኝን #ትልቅ ደስታ እገልጻለው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።

ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ የመስቀል አደባባይ የማጠቃለያ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወንጌል ሃይል አለው። #ዛሬ ንሰሃ በመግባት #ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል #ስለ ወሰኑ ሰዎች ጌታን እናመሰግናለን።

ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?”
ዮሐንስ 11፥25-26

ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ትልቅ አስተዋጾ ላደረጉ #እና ለጸለዩ ወዳጆቼ እና አብያተ ክርቲያናት በሙሉ #ትልቅ #ምስጋና አለኝ። አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ቃል እየጸናችሁ፡ የምትሰሩትን የደቀ መዝሙር ማድረግ ስራ #እግዚአብሔር ይባርክ።

ዛሬ በነበረን የዝማሪው ጊዜ በርካታ ዘማሪዎች በዝማሬ እና አምልኮ ከቀትር በኋላ እስከ ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ አገልግለዋል። መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ መርሃ ግብር ላይ ለተሳፋችሁ በሙሉ አመሰግናለሁ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና 2ቱን ቀናት በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ ስናደርስ ቆይተናል።

አብራችሁን ስለነበራችሁ እና ስለተከታተላችሁን ስለሰጣችሁን አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።
👍2816🙏3🔥1
መስቀል አደባባይ ምንም አይነት የፖለቲካ ይዘት ያለው አንድም አይነት ጥያቄ አልተነሳም መልዕክትም አልተላለፈም።

አንድም ፖለቲከኛ በቦታው ተገኝቶ የፖለቲካ መልዕክቱንም ሲያስተላልፍ አልተገኘም። ለ2 ቀን በመስቀል አደባባይ የነበረው እና ሲመለክም ይሁን ሲሰበክ የነበረው ኢየሱስ ብቻ ነበር።

ኢትዮ ፎረም የተባለው ሚዲያ ስለምን እያወራ እንደሆነ አልገባንም። እጅግ ሲበዛ በወንጌላውያን አማኞች ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ግን ትንተናውን በማቆለጳጰስ ይጀምራል።

ከዛም ወንጌል ሰባኪዎችን ወደ ምድር ፈጥፍጦ ወንጌላውያንን ከሌላው ኢትዮጵያውን ነጥሎ ለመምታት ከፖለቲካው ጋር ሲደምራቸው እና አገልጋዮችንም ተላላኪ አድርጎ ይተነትናል።

ከፖለቲካ ጋር የተገናኘ የተለየ ትንታኔ አለኝ ካለ በራሱ መንገድ ይተንትነው ግን አንድን የወንጌል ሰባኪ በአደባባይ ስም እየጠቀሰ "ተላላኪ" እያለ መዝለፍ ግን እጅግ ሲበዛ ነውር እና ከጋዜጠኛ ነኝ ብሎ ከሚያስብ ሰው የማይጠበቅ እንደሆነ የዘነጋው ይመስላል።

ፍራንክሊን ግርሃም ኢትዮጵያ ጨምሮ በርካታ የአለም ሀገራት በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ በሆኑ አደጋዎች ለተጋለጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚያደርግ ድርጅት አላቸው ኢትዮጵያ ውስጥም ላለፉት 40 ዓመታት የመልሶ ሟቋቋም ስራዎች እና የእርዳታ ስራዎች ሲሰራ ቆይቷል።

ፍራንክሊን ግርሃም ከ1991 ጀምሮ ሲመጡ ይህ ለ11ኛ ጊዜ እንደሆነ ይታወቃል። በሰሜን ኢትዮጵያ ሰመሪታን ፕርስ በርካታ የንጹ ውሃ ግድጓዶች እና የጠብታ ውሃ መስኖ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

ይህንን ሁሉ አመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ አንድም ቀን ሱምን ጠርተው የማያውቁ ሚዲያዎች ዛሬ ወንጌልን ለመስበክ ሲዘጋጁ ግን በነቀፋ አፋቸውን ለመክፈት ፈጠኑ እንደ እኔ ከእንደዚህ አይነት በወንጌላውያን ጥልቅ ጥላቻ ከሰከረ ጋዜጠኛ እና ሚዲያ እራሳችሁን ጠብቁ።
👍3810👏4🔥2👌1🕊1
#ለማ ጎሶማ ብለሲንግ ሚኒስትሪ የምስረታ በዓሉን
አከበረ።

የምስረታ በዓሉን በአለታ ወንዶ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ያካሄደው ፕሮግራሙ በወንጌል አርበኛው ለማ ጎሶማ ልጆች አማካኝነት የተቋቋመ ነው።

ሚኒስትሪው በወንጌል አርበኞች፣ ሚሺነሪዎች እንዲሁም በከፋ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍን ማድረግ፣ ማሰልጠን እንዲሁም የወንጌል አገልጋዮችን ማሰማራትን ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡

ለ3 ቀናት በተካሄደ የምስረታ ኮንፍረንስ ፕሮፌሰር ዝናቡ ገብረ ማሪያም እና መጋቢ ታደለ ነጋሽ አገልግለዋል። ተጋባዥ ዘማሪያን በዝማሬ አገልግለዋል፡፡

ሚኒስትሪው በቀጣይ የአባቶች ባርኮት ኮንፍረንስን ጨምሮ የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚካሄዱ የሚኒስትሪው ፕሬዝደንት አቶ እስጢፋኖስ ለማ ተናግረዋል፡፡
በምስራቁ የአገራችን አካባቢዎች ሶስት የወንጌል አገልጋዮችን በመላክ ከምስረታው ምርኃ ግብር አስቀድሞ አገልግሎቱን መጀመሩን የሚኒስትሪው የውጪ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሚሳኤል ለማ ነግረውናል፡፡
5👍2🔥2🙏1
በጅማ ዞን ጋቲራ የምትባል ከተማ በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ተፈጸመ።
ሃሙስ ለሊት 9 ሰዓት፡ በጅማ ጋቲራ ከተማ የመካነ ኢየሱስ ቤ/ክ የአምልኮ ስፍራ እና የምዕመናን ቤቶች፡ እንዲሁም ምዕመናን ላይ ነው ጥቃት የተፈጸመው። ጥቃት አድራሾቹ የተደራጁ ሰዎች መሆናቸውን ቤተ ክርስቲያኗ ይፋዊ በሆነ የፌስቡክ ገጿ አሳውቃለች።

ቤተ ክርስቲያኗ የኦሮሚያ ክልል መንግስት፡ የጅማ ዞን አስተዳደር እና የጋቲራ ከተማ አስተዳደር ይሄንን ድርጊት ምርመራ አድርገው መልስ እንዲሰጡ ጠይቃለች። ምዕመናንም አጥብቀው እንዲጸልዩ አሳስባለች።
😭15🤔4👍2🙏2🕊1💔1
የተወደደው ኢንጂነር ፓ/ር ልዑለቃል ካሴ የፓ/ር ዘነበች ገሠሠ ባለቤት ወደ ሚወደው ጌታ ሄዷል።

ፈገግታ የማይለየው ፣ ትህትና መታወቂያው ፣ በስራው ትጉ፣  ለልጆቹ እጅግ መልካም አባት፣ ለጓደኞቹ የህይወት ምሳሌ እና ለትዳር አጋሩ ለፓ/ር ዘነበች ገሠሠ እውነተኛ ረዳት እና የአገልግሎቷ ብርታት የሆነው ኢንጂነር  ፓ/ር ልዑለቃል ካሴ ወደ ሚወደው እና በፍጹም ንጽህና እና በማይበርድ ፍቅር ወዳገለገለው ጌታ መሄዱን ከባለቤቱ ከፓ/ር ዘነበች የሰማሁት በማለዳ ነበር።

ፓ/ር ዘነበች ከህንድ እጅግ በሚያሳዝን ቃል በእምባ :-

"ዳዲ ጥሎኝ ወደጌታ ሄደ" አለችኝ በእውነት ልቤ እጅጉን አዘነ

#ዛሬ ታላቅ ወንድማችንን ኢንጀነር ፓ/ር ልዑለቃል ካሴን  አጥተናል እጅግ አዝኛለሁ።

ኢንጂነር ለህትመት የበቁ ሦስት መጽሐፎችን አበርክቶልን ወደ ሚወደው ጌታ ሄዷል።

"አክሊል" የመጀመሪያ መጽሐፉ ነው እንደፃፈልን አክሊሉን ሊቀበል  ወደ ጌታ ሄዷል።

ሁለተኛ መጽሐፉ "የራዕይ መጽሐፍ እኔ እንደተረዳሁት" የሚል ነበር የተረዳውን ጽፎልን እሱ ግን ወደ ጌታው ሄዷል።

ሦስተኛው መጽሐፍ በቅርቡ ያስመረቀው "ይመለሳል" የሚል የጌታ ዳግም ምጽአት የሚተርክ ድንቅ መጽሐፍ አበርክቶልን ከእሱ ጋር ሊመለስ ቀድሞን ሄዷል።

1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።

መጽናናት ለፓ/ር ዘነበች ገሠሠ ፣ ለልጆቻቸው ፣ ለህይወት ምንጭ እየሱስ ቤ/ክ አባላት እና አገልጋዮች እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ እንዲሆን እንመኛለን። ነገ እሑድ 7:00 ሰዓት ቦሌ ኤርፖርት የሚደርሱ ሲሆን ቀብር ሰኞ መሆኑን እንገልጻለን። ፖስተር ዳኒ እንደፃፈዉ
💔16😭9👍21🕊1
#ቤተክርስቲያን በመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቁ ዜጎች ድጋፍ አደረገች።

#Ethiopia | አራራ ዋቃዮ አዱኛ ቤተ ክርሰቲያን በምሥራቅ ሸዋ ዞን በፋንታሌ ወረዳ የመሬት መንቀጥቀጥ ባስከተለዉ ጉዳት ችግር ዉስጥ ላሉ ሕብረተሰብ በ3,107,000 ብር 800 ኩንታል ዱቄት አዘጋጅታ ለህዝቡ አከፋፈለች።

የቤተክርስቲያኒቱ መሪ ነቢይ መሠረት ታዬም ለሕብረተሰቡ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ድጋፉም ለ3 ሺህ 200 አባወራዎችና እማወራዎች ተከፋፍሎ ለያንዳንዳቸው 25 ኪ.ግ. ተዳርሷል።
👍2316👏3🔥2🤔2💯1
የአጥቢያ #ቤተክርስቲያን የቤተሰብ አገልግሎት ምን ምን መካተት ሊኖርበት ይገባል?

የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ሚኒስትሪ ከ20 በላይ አብያተ ክርስቲያናት ለተወጣጡ አገልጋዮች ቤተሰብ ተኮር ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናው ለሁለት ቀናት በቀነኒሳ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን ተወካዮች ከስልጠናው መልስ በሚሄዱባቸ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ቤተሰብ ተኮር ስራዎችን መስራት ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ ሚኒስትሪ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳሮን ውድነህ፣ ስልጠናው አንዲት ጠንካራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እንዴት የቤተሰብ አገልግሎት ይኖራታል፣ ምን ምን መካተት ይኖርበታል፣ አለመኖሩ ምንም ምን ችግሮችን ያመጣል በሚሉ ወሳኝ ጥያቄዎች ላይ ሰፊ ውይይት መካሄዱን
ለክርስቲያን ዜና ገልጸዋል።

ዘ ክርስቲያን ኒውስ ያናገራቸው የስልጠናው ተካፋዮች እንደ አገልጋይም እንደ ባለትዳርም ብዙ የተጠቀምንበት ስልጠና ነው ብለውታል።

እዚህ የተገኘው ልምድ ወደ ቤት ተወስዶ የሚኖር ነው ሲሉ ገልጸውታል።

የቤተሰብ ቅጥር አዳሽ፣ ጠንካራቤተሰብ፣ ለቤተ ክርስቲያን ህልውና እና ለታላቁ ተልዕኮ ወሳኝ ነው ብሎ ያምናል። በመሆኑም ይላሉ ወ/ሮ ሳሮን አብያተ ክርስቲያናት ለቤተሰብ አገልግሎት ትኩረት ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራዉ ተገኝተን ዝርዝሩን አቀረብንላችሁ።
👍92🔥1
#እሁድ የት ናቹ ? #ምክንያቴ #ብዙ ነው።

#እግዚአብሔር ሰውን ለአላማው ከፈለገው ከምን አንስቶ እንደሚጠቀምበት ፓስተር ተከስተ ጌትነት ህያው ማሳያ ነው።

የትናንቱ ቆሎ ተማሪ የዛሬው ፓስተር ተከስተ ላለፉት ሀያ አምስት አመታት በላይ በዘለቀው አገልግሎቱ ተሰምተው የማይጠገቡ፣ ተደምጠው የማይሰለቹ የዝማሬ አልበሞችን አውጥቶ ለሚሊዮኖች የመባረክ ምክንያት ሲያደርገው የተመለከተ እግዚአብሔር ይችላል እንጅ ሌላ ምን ሊል ይችላል?

የመጋቢ ተከስተ ጌትነት ዝማሬዎች የዜማ ምጥቀት፣ የግጥም ጥልቀት የብዙሀንን ልብ ለወንጌሉ ወለል አድርገው ያስከፈቱ ሚሊዮኖችን ለጌታ ፍቅር ያንበረኩኩ ሀያል የወንጌል መሳሪያዎች ሆነው ለአመታት እየተደመጡ ዘልቀዋል።

ተኬ በ80ዎቹ መጨረሻ በኢትዮጵያ አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን አሀዱ ተብሎ የተጀመረው የዝማሬ ጉዞው በብዙ ድልና በብዙ መውደቅ መነሳት ዛሬ እዚህ ደርሶ ምክንያቴ ብዙ ነው ብለን አብረነው ጌታን ልናመልክ እንሆ ቀኑ ተቆርጧል።

መጋቢት 14 ከሰዓት በጊዮን ሆቴል እንገናኝ።

ለማመስገን ምክንያታችን ብዙ ነው።
👍2816🔥1🙏1