The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
53 videos
911 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#Mo'aa TV | ሞአ ቲቪ አየር ሰዓት የሸጥኩላቸው ሰዎች ያለኔ እውቅና በስሜ ገንዘብ ሲሰበስቡ ነበር አለ።

ሞአ ቲቪ በቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ በ2009 ዓ.ም የተቋቋመና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መንፈሳዊ ይዘቶችን የሚያስተላልፍ ክርስቲያን የቲቪ ጣቢያ ነው።

ድርጊቱንም በጣቢያው ስም የተደረገ ዝርፊያ ነው ብሎታል። የተወሰኑ የአየር ሰዓት የገዙ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኖች አካባቢ በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሱ ገንዘብ ሲሰብሰቡና ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ ነበር ብሏል።

ጉዳዩንም ከህግ አካላት ጋር ክትትል ላይ መሆኑን የጣቢያው ሃላፊ አቶ ኒሞና ኢታና ገልጸዋል። በመላ ሃገሪቱ እንዲሁም በአለም ዙሪያ የሚገኙ ወገኖች ከመሰል ዝርፊያዎች እንዲጠነቀቁ አደራ ብለዋል።
👍6🤔3🔥1🙏1🕊1
#የአጋር_መልዕክት

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ታላቅ ድግስ 5 ቀን ቀረው

• ፓስተርና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ
• ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
• ዘማሪት ሃና ተክሌ
በዝማሬ ያገለግሉናል

በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን የተዘጋጀ የካቲት 29ና 30 በመስቀል አደባባይ።

ሁላችሁም ተግቅብዛችኋል
👍12🔥4🙏1
#4 ቀን ቀረው

መስቀል አደባባይ ላይ እግዚዓብሔር አምላካችንን በዝማሬ፡ በጸሎት፡ በስብከት ከፍ ልናደርገው የካቲት 29 እና 30 ቀጠሮ ይዘናል።

ከሬቨረንድ ፍራንልኪን ግራሃም ጋር ታላቅ የወንጌል ስብከት ይካሄዳል።

• ዘማሪ አገኘው
• ዘማሪ ጳውሎስ
• ዘማሪ አቤኔዘር
• ዘማሪት በረከት
• ዘማሪ ጉቱ
ጋር ጌታን እናመልካለን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
10👏2👍1🔥1👌1
የሀምበሪቾ ተራራ በጸሎት ቱሪዝም መዳረሻ በመሆን በአንድ ቀን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች ለጸሎት ወደ ተራራዉ እንደሚወጡ ተነገረ።

ሀምበሪቾ ተራራ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ህገ ደንብ በመፅደቅ የሀምበሪቾ ኢኮ ቱሪዝም ስፍራ ፅህፈት ቤት በመባል ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዉጪ እራሱን ችሎ በቦርድ እንደሚመራ ተገልጿል። የ6 ወር የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሪፖርት እንደሚያሳየዉ 2 መቶ 75 ሺህ ቱሪስቶች ማዕከላዊ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ያመላክታል።
ከዚህ ዉስጥም ከ77 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቱሪስቶች የሀምበሪቾ ተራራን የጎበኙ ሲሆን በዓመት ወደ 500,000 የሚጠጉ ቱሪስቶች ተራራዉን ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዱራሜ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊና የቪዝት ከምባታ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት አቶ ሳምሶን ቶማስ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

የሀምበሪቾ ተራራን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በከፍተኛ ፕሮጀክት ተራራውን የሚያቋርጡ 777 ደረጃዎችን መገንባቱ ተገልጿል።

ተራራው በቅርብ ጊዜ ለቱሪዝም ክፍት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከ4 ና 5 አመት በፊት ትልቅ የፀሎት መዳረሻ ነበር። ከሀይኪንግ ጎን ለጎን በዓመት አንድ ጊዜ ጥር 11 ላይ ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ የወንጌል አማኞች በስፍራ ፀሎት እንደሚያደርጉ አቶ ሳምሶን ቶማስ ጨምረዉ ገልፀዋል።

ስፍራውን ለቱሪስቶች ምቹ ለማድረግ የከምባታ ዞን መንገዶች ፅህፈት ቤት በየዓመቱ መንገዶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

መንገዱን አስፋልት ለማድረግና በተራራዉ ላይ ሎጆችንና ሆቴሎች በመገንባት ምቹ ለማድረግ ፅህፈት ቤቱ እንደሚሰራ ተገልጿል። ስፍራዉን በዘላቂነት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ስራዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተሰሩ ስለመሆናቸዉም ተገልጿል።
👍125🙏1
1.2 #ቢሊዮን ብር ለልማት ስራ የምታውለው ቤ/ክ

የመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን ለ2025 ዓ.ም 1.2 ሚሊዮን ብር ለልማት ስራዎች ለማዋል የኮሚሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ወስኗል። በቀጣይ በጀቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ቤተ ክርስቲያኗ ወንጌልን ከመስበክ ቀጥላ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገዝ ስራዎችን ትሰራለች።
👍81🔥1👏1
በቤተ ክርስቲያን የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅም የተያዘው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ተከሳሽ አብዱራህማን ነጋ የተባለ ነዋሪነቱ ቸሃ ወረዳ አዶሼ ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማስገኘት በማሰብ ከሌላ ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክ/ከተማ ጋሶሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የዝርፊያ ወንጀል ፈጽሟል፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመዉ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6፡30 በሚሆንበት ጊዜ የፎከስ ፌሎሺፕ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የሚገለገሉበትን ቅጥር አጥር ዘሎ በመግባት ንብረትነታቸው የቤተክርስቲያኑ የሆኑ ጠቅላላ ግምታቸው በድምሩ 33,050 ብር የሆኑ እቃዎች ከንብረት ክፍል ከፍቶ በማውጣት ከቤተክርስቲያኑ አጥር ግቢ ወደ ውጪ በመወርወር ከግብረ አበሩ ጋር ሊውሰድ ሲል የአካባቢው ሰዎች ድምጽ ሰምተው መጥተው ሊይዙት ሲሉ እገድላችኋለሁ እንዳትጠጉኝ እተኩሳለሁ ብሎ ያስፈራራቸው ሲሆን በጩኸት በመጡ ሰዎች ርብርብ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በዚህም አስቦ በፈጸመው በተራ የስርቆት ወንጀል ክስ መመስረቱን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ገልጸዋል፡፡

ክሱ የቀረበለት የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ በመቀየር በወንጀል ህጉ አንቀፅ 669 ንዑፅ አንቀፅ 3 መሰረት ጥፋተኛ በማለት የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ኤልያስ ሰብለጋ ጨምረው ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡ ሲል ያስነበበው ዳጉ_ጆርናል ነው።
👍93🔥1
የካቲት 29 እና 30 ቅዳሜ እና እሁድ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው ታላቅ ድግስ አስመልክቶ ካውንስሉ መግለጫ ሰጠ።

መግለጫውን የካውንስሉ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በካውንስሉ ጽ/ቤት ሰጥተዋል።

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ፡ ከዓመት በላይ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፡ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም፡ እድገት፡ ልማት የምንጸልይበት ይሆናል። እግዚአብሔርን በዝማሬ፡ በአምልኮ፡ በቃል የምናመልክበት ትልቅ ቀን ነው ብለዋል።

በመግለጫው አውቶብሶች በሚቆሙበት ስፍራዎች በጊዜ በመገኘት ወደ መስቀል አደባባይ እንድትመጡ ይሁን። በአካባቢው ከሚኖሩ የጸጥታ አካላት ጋር ትብብር በማድረግ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ አደራ።

በነዚህ ቀናት እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ በጾም ላይ ከሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር እንዲሆን አደራ ብለዋል።

ፕሮግራሙን ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከ ኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመሆን የተዘጋጀ ነው።
👍73🔥1
#2 ቀን ቀረው

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ

ከእውቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ሬቨረንድ ፍራንልኪን ግራሃም ጋር በምድራችን የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
👍74🔥2👏1🙏1
#ተጠንቀቁ

"ብሩክ እና ወርቁ ከተባሉ አጭበርባሪዎች እንድትጠነቀቁ" ካውንስሉ

ስማቸው ከላይ የተጠቀሱ ግለሰቦች ለአብያተ ክርስቲያናት መሬት ስላገኛቹ ቅድመ ክፍያ አስገቡ በማለት ገንዘብ ሲሰበስቡ ደርሼበታለው ብለዋል።

ግለሰቦቹ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት አስተዳደር ሰራተኞች ነን እያሉ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ካውንስሉ ገልጾ፡ ቤተ እምነቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አደራ ብሏል።
👍2
የወንጌላዊ ልጅ የሆኑት ሬቨረንድ ፍራንክሊን የካቲት 29 እና 30 ለሚካሄደው "መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ"ን አስመልክቶ ለሀገር ውስጥ የመንግስት እና የሃይማኖት ተቋማት ሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃማ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ #ኢትዮጵያ በመጣሁበት #ወቅት ሃገሪቱ ጦርነት #ላይ የነበረች ቢሆንም ውብ ሃገር ውብ ህዝብ እንዳላችሁ አየሁ እኔም ዛሬ ወንጌል ለማገልገል እዚህ ተገኝቻለሁ ብለዋል።

የዛሬ 65 ዓመት አባቴ በኢትዮጵያ ሰብኳል። ከዛ በኋላ ብዙ ነገር ተለዋውጧል። ነገር ግን መልዕክቱም አልተቀየረም። ዛሬም ኢየሱስ ያድናል የሚል ህያው የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል በኢትዮጵያ ምድር ይሰበካል ብለዋል።

የዛሬ 65 አመት አባቴ እንደሰበከው እኔም ዛሬ አገለግላለሁ፡ ልጄ ኤድዋርድ እዚህ አለ፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለቀጣይ 65 ዓመታት ማገልገል ይቀጥላል። 1980 ለመጀመሪያ ጊዜ ከመጣሁ ጀምሮ ሃገራችሁ ኢትዮጵያ ላይ ብዙ ለውጦችን አይቻለው ሲሉም ተናግረዋል።

ምናልባት ፕሬዝደንት ትራምፕ በUSAID በኩል የሚገባን ድጋፍ ዋሽንግተን ላይ ባለ ሙስና ምክኒያት አስቁመውታል። ለአጭር ጊዜ ችግር ሊገጥም እንደሚችል አምናለው። ስጋት አይግባቹ ሰማሪታን ፐርስ አገልግሎቱን ይቀጥላል። ድጋፋችን ከአሜሪካ መንግስት ሳይሆን ከእግዚአብሄር ነው ሲሉም ከሰሞኑ የአሜሪካ መንግስት በUSAID በኩል የወሰደው እርምጃንም በተመለከተ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ቢሊ ግርሃም የዛሬ 65 አመት በንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ ተጋብዘው ማገልገላቸውን አስታውሰው ልጃቸው በአሁኑ ሰዓት ለማገልገል በመምጣታቸው እንዲሁም የሚመሩት ሳማሪታን ፐርስ ለሃገራችን ያበረከቱት ትልቅ ነገር ስለሆነ እናመሰግናለን ያሉት ደግሞ የካውንስሉ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ ናቸው።
👍1810🔥1
#የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊካል አሶሴሽን ፕሬዚዳንት ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር ተወያይተዋል።

ከንቲባ #አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃምን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው #እንኳን ደህና መጡ ማለታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፍራንክሊን ግራሃም እንደ አባታቸው ሁሉ ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያላቸው መሆኑን፣ ሁሌ እንደሚፀልዩና ላለፉት 40 ዓመታት ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ እንደጎበኙ መግለጻቸውን ጠቅሰዋል።

ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም በአዲስ አበባ ከተማ ባዩት ፈጣን ለውጥ መደነቃቸውን አመልክተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ለኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ላሳዩት #ፍቅር እና #መልካም ምኞት አመስግነዋል።
👍1311🔥1👏1
የዛሬ 65 አመት ነው አባቴ ቢሊ ግራሃም እዚህ #አዲስ አበባ #ኢትዮጵያ መጥቶ ወንጌል የሰበከው። እኔም #ዛሬ እዚህ ቆሜ መስበክ በመቻሌ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ። ቀናቱ መገጣጠማቸውም #የእግዚብሔር ስራ ነው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት የወንጌላዊ ቢሊ ግርሃም ልጅ ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።

ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወደ #ኢትዮጵያ ስመጣ ይሄ ለ11ኛ #ጊዜ ነው። በአደባባይ #ወንጌል ስሰብክ ይሄ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ከ117 ሺህ በላይ ሰው በመስቀል አደባባይ የምስራቹን ወንጌል ለመስበክ በመምጣቱ በጣም ተደስቻለው። ህይወታቸውን ለኢየሱስ የሰጡና ለመከተል የወሰኑ ሰዎች በመኖራቸው እግዚአብሔርን አመሰግነዋለው ብለዋል።

ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በስተቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና። ሐዋርያት ሥራ 4፥12

እንደ #አዲስ ክርስቶስን ለመቀበል ለወሰኑ ሰዎችና እዚህ እነርሱን ለሚከታተሉ ሰዎች እንድትጸልዩ አደራ እላለሁ። #ነገ ለሚኖረው ሁለተኛ #ቀን የመለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ፕሮግራም ጸልዩ።

በዚህ ፕሮግራም በመዝሙር #እና አምልኮ ያገለገሉ በሙሉ በጣም አመሰግናችኋለው። ከ1600 በላይ ለሚሆኑና ይሄ ፕሮግራም እዉን እንዲሆን ለተጉ አብያተ ክርስቲያናት ትልቅ ምስጋና አለኝ። ወንጌሉን ለመስበክ ላላቸው ታላቅ ልብ እግዚአብሔርን አመሰግናለው።

#መስቀል አደባባይ የሚደረገው የአምልኮ ፕሮግራም #ነገ እሁድ የሚቀጥል ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በFacebook እና በYoutube በቀጥታ ስርጭት የምናስተላልፍ ስለሚሆን ከከተማ እና ከሀገር ውጪ ያላችሁ በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
14👍7🔥2👏2🙏1🕊1
ከ320 ሺህ በላይ ሰው #መስቀል አደባባይ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በመገኘቱ የተሰማኝን #ትልቅ ደስታ እገልጻለው። ይህንን ያሉት በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ ያገለገሉት ፍራንክሊን ግርሃም ናቸው።

ፍራንክሊን ግርሃም Franklin Graham ከዛሬ የመስቀል አደባባይ የማጠቃለያ አገልግሎታቸው በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክታቸው #ወንጌል ሃይል አለው። #ዛሬ ንሰሃ በመግባት #ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል #ስለ ወሰኑ ሰዎች ጌታን እናመሰግናለን።

ኢየሱስም እንዲህ አላት፤ “ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳን በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?”
ዮሐንስ 11፥25-26

ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ትልቅ አስተዋጾ ላደረጉ #እና ለጸለዩ ወዳጆቼ እና አብያተ ክርቲያናት በሙሉ #ትልቅ #ምስጋና አለኝ። አብያተ ክርስቲያናት በእግዚአብሔር ቃል እየጸናችሁ፡ የምትሰሩትን የደቀ መዝሙር ማድረግ ስራ #እግዚአብሔር ይባርክ።

ዛሬ በነበረን የዝማሪው ጊዜ በርካታ ዘማሪዎች በዝማሬ እና አምልኮ ከቀትር በኋላ እስከ ምሽት ድረስ በጥሩ ሁኔታ አገልግለዋል። መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ መርሃ ግብር ላይ ለተሳፋችሁ በሙሉ አመሰግናለሁ።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና 2ቱን ቀናት በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ ስናደርስ ቆይተናል።

አብራችሁን ስለነበራችሁ እና ስለተከታተላችሁን ስለሰጣችሁን አስተያየት ከልብ እናመሰግናለን።
👍2816🙏3🔥1