The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
53 videos
912 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አስደሳች #ዜና

#የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ሆነ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተቋማዊ አደረጃጀቱንና ዉስጣዊ አሰራሩን እንዲሁም የአባል ቤተዕምነቶች የእርስ በእርስ ግንኙነትና በተቋሙ ላይ ያላቸዉ እይታና እርካታ አስመልክቶ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ያጸደቀ ሲሆን በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት የጉባኤውን አዲስ መተዳደሪያ ደንብ አጽድቋል።

ጉባኤዉ ከዚህ ቀደም በ7 አባል ቤተዕምነት አባልነት የነበረ ቢሆንም በአዲሱ ደንብ መሰረት 5 አባላት ብቻ እንደሚኖረዉ የተጠቀሰ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስልም አንዱ አባል ሆኗል።

በዛሬዉ እለት በፀደቀዉ ደንብ መሰረት
. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት
. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል
. የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን

በአባልነት እንደሚይዝ ደንቡ የሚጠቅስ ሲሆን ከዚህ ቀደም የጉባኤው አባል የነበሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፣ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ በካዉንስሉ እንደሚወከሉ ተጠቅሷል።

#ዛሬ ሲካሄድ በነበረው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መድረክ #የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባኤውን በጠቅላይ ጸሐፊነት ለ2ኛ ዙር እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል።
👍12🔥21👏1🕊1
#20_የበረከት_ዓመታት

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን 20ኛ አመት ክብረ በዓል እና የአዲሱ የአምልኮ ስፍራ ልታስመርቅ ነው።

ቤተክርስቲያኒቱ ቀድሞ በተከራየችበት በጎተራ የእህል ንግድ ድርጅት ግቢ ውስጥ ላለፉት 18 አመታት የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች የቆየች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ባዘጋጀላት ስፍራ የራሷን የማምለኪያ አዳራሽ ገንብታ በቀጣዩ የእግዚአብሔር መንግስት #ወንጌል በሐይል ለመስበክ ዝግጅቷን አጠናክራ ቀጥላለች።

ስለሆኑም የ 20ኛ አመት የምስጋና ኮንፈረንስና የአዳራሸ ምረቃ ፕሮግራም ከመጋቢት 1-7 ታላላቅ አገልጋዮች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አባቶች በተገኙበት ይመረቃል።

አሁን የተገነባው የማምለኪያ አዳራሽ በአሁኑ ወቅት ጐተራ ማሳለጫ ሪፍት ቫሊ ዮኒቨርስቲ አጠገብ ሲሆን፣ በእግዚአብሔር እርዳታ ላለፉት አንድ አመት ሲሰራ የቆየነውን አዳራሽ ለእግዚአብሔር ክብርና ለቅዱሳን ጥቅም እንዲሆን ተመርቆ እንደሚከፈት ተገልጿል።

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ላለፋት 20 አመታት ወንጌል የመስበክ እና የማስተማር ተልዕኮ አንግባ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች፣ የቆየች እና እያገለገለች ያለች ቤተክርስቲያን ነች።

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ኑና የረዳንን እግዚአብሔርን አብረን እናመስግን በማለት ጥሪዋን አቅርባለች።
👍114👏3🔥1
#ሰምተዋል?

👉 በአንድነት እግዚአብሔርን የምናመልክበት
👉 በፊቱ በጸሎትና ምልጃ የምንቀርብበት
👉 ታላቅ የወንጌል ስርጭት የምናካሂድበት

የካቲት 29 & 30 በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን በተዘጋጀው የመስቀል አደባባዩ ድግስ፡ አይቀርም።

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ታላቁ ድግስ ላይ እርሶም በጌታ ፍቅር ተጋብዘዋል።
15👍3🔥1👏1
#36 ወጣቶች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተቀላቅለው፡ ተጠምቀዋል!

ከአዲስ አበባ 600 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው የደቡብ ኢትዮጵያዋ አሪ ዞን ጂንካ ከተማ MKC፡ 36 ወጣቶችን በአካባቢው ባለ ወንዝ #አጥምቀናል

ወንጌል ነብሳትን እየለወጠ እየቀጠለ ነው፡ እጅግ ደስ ብሎናል አብራችሁን ደስ ይበላችሁ ብለዋል መጋቢ ደሳለኝ አበበ።
13🙏3❤‍🔥2👍2🔥1
#የታሪክ_ማስታወሻ

እውቁ የወንጌል አገልጋይ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ከ65 አመታት በፊት የምስራቹን #ወንጌል በኢትዮጵያ ምድር ሰብከው፡ ከንጉሰ ነገስት አጼ ሃይለስላሴ ዘንድ ምስጋና ተችሯቸው ነበር።

ዛሬ ደግሞ ልጃቸው ሬቭረንድ ፍራንክሊን ግራሃም  የሳቸውን #ሌጋሲ በመከተል፡ መለኮታዊ ጉባኝት ለኢትዮጵያ በሚል ታላቅ የወንጌል ስብከት ያካሂዳሉ።

የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
👍142🔥1🙏1
#እንኳን #ደስ አላችሁ!!

#የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት #ህብረት #አዲስ ያስገነባውን ህንጻ አስመረቀ።

የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ጽ/ቤት ያስገነባውን ህንጻ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ህንጻውን መርቀው የከፈቱት የከተማዋ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁዋር #እና #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት የቦርድ ሰብሳቢና የመሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ ናቸው።

የድሬዳዋ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ከተመሰረተ ከ30 አመታት በላይ ያስቆጠረ ቢሆንም የራሱ የሆነ የጽ/ቤት ህንጻ ያልነበረው ሲሆን #አሁን #ግን ከከተማ አስተዳደሩ በተረከበው #ቦታ ላይ ከትራንስፎርሜሽናል ዲሳይፕል ሜኪንግ ሚኒስትሪ (TDMM) ጋር በመተባበር አስገንብቶ ያጠናቀቀውን ህንጻ #ለእግዚአብሔር #መንግስት ክብር ለህዝቡ በረከት እንዲሆን መርቆ #ሥራ አስጀምሯል።

#ክብር#እግዚአብሔር ይሁን!!

የድሬደዋ #ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁዋር በከተማው ዉስጥ ላሉ የሃይማኖት ተቋማት ለሚሰጡት #መልካም መስተንግዶ እና የሚሰጡት አገልግሎት #እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካቸዉ።
👍21🔥21👏1
#በውኑ #ለእግዚአብሔር #የሚሳነው #ነገር #አለን?

የተከበራችሁ የማህበራዊ ሚዲያ ቤተሰቦቼ እህታችን መቅደስ መልካሙ ቸሩ ከጠፋች በ9ኛው ቀን ፣ ታግታ ከነበረችበት አዳማ አከባቢ አምልጣ ፣ አርሲ ነጌሌ አከባቢ ከደረሰች በኋላ ፣ በእጇ ይዛ የወጣችው mobile እና የእጅ ቦርሳ እንዲሁም መፅሐፍ ቅዱስ ይዛ ሲሆን ፣

ሁሉንም ቀምተዋት bible ብቻ እጇ ላይ ስለቀረ ፣ በሌላ ሰው ስልክ ወደ ቤተሰቦቿ በመደወል ፣ አርሲ መሆኗን ከነገረቻቸው በኋላ ፣ ሄደው ወደ ሀዋዛ ይዘዋት ተመልሰው ፣ እኛም ተቀብለናት ፣

የክልሉ እንዲሁም የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር በጋራ በመሆን ባደረገው ምርመራ ፣ ወጣቷ ምንም አይነት የጤና እክል እንዳልደረሰባት ተረጋግጦ ፣ ወላጆቿን ፣ ወዳጅ ዘመዶቿን በሰላም ተቀላቅላለች።

ሁላችሁም ስላደረጋችሁት ርብርብ ፈጣሪ ያክብርልኝ። 🫡🫶🙏

ቅዳሜ 22.06.017 ዓ.ም
ኤደን ለገሠ ተሰማ
👍23👏4🙏2🔥1
#6 ቀን ቀረው

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ በመስቀል አደባባይ

ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሳሶሼሽን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ታላቅ ድግስ።

የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
🔥12👍62👏2🙏2❤‍🔥1🥰1
#Mo'aa TV | ሞአ ቲቪ አየር ሰዓት የሸጥኩላቸው ሰዎች ያለኔ እውቅና በስሜ ገንዘብ ሲሰበስቡ ነበር አለ።

ሞአ ቲቪ በቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ በ2009 ዓ.ም የተቋቋመና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ መንፈሳዊ ይዘቶችን የሚያስተላልፍ ክርስቲያን የቲቪ ጣቢያ ነው።

ድርጊቱንም በጣቢያው ስም የተደረገ ዝርፊያ ነው ብሎታል። የተወሰኑ የአየር ሰዓት የገዙ ሰዎች በቤተ ክርስቲያኖች አካባቢ በተለይ በኦሮሚያ ክልል እየተንቀሳቀሱ ገንዘብ ሲሰብሰቡና ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ ነበር ብሏል።

ጉዳዩንም ከህግ አካላት ጋር ክትትል ላይ መሆኑን የጣቢያው ሃላፊ አቶ ኒሞና ኢታና ገልጸዋል። በመላ ሃገሪቱ እንዲሁም በአለም ዙሪያ የሚገኙ ወገኖች ከመሰል ዝርፊያዎች እንዲጠነቀቁ አደራ ብለዋል።
👍6🤔3🔥1🙏1🕊1
#የአጋር_መልዕክት

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ታላቅ ድግስ 5 ቀን ቀረው

• ፓስተርና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ
• ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
• ዘማሪት ሃና ተክሌ
በዝማሬ ያገለግሉናል

በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን የተዘጋጀ የካቲት 29ና 30 በመስቀል አደባባይ።

ሁላችሁም ተግቅብዛችኋል
👍12🔥4🙏1
#4 ቀን ቀረው

መስቀል አደባባይ ላይ እግዚዓብሔር አምላካችንን በዝማሬ፡ በጸሎት፡ በስብከት ከፍ ልናደርገው የካቲት 29 እና 30 ቀጠሮ ይዘናል።

ከሬቨረንድ ፍራንልኪን ግራሃም ጋር ታላቅ የወንጌል ስብከት ይካሄዳል።

• ዘማሪ አገኘው
• ዘማሪ ጳውሎስ
• ዘማሪ አቤኔዘር
• ዘማሪት በረከት
• ዘማሪ ጉቱ
ጋር ጌታን እናመልካለን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
10👏2👍1🔥1👌1
የሀምበሪቾ ተራራ በጸሎት ቱሪዝም መዳረሻ በመሆን በአንድ ቀን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች ለጸሎት ወደ ተራራዉ እንደሚወጡ ተነገረ።

ሀምበሪቾ ተራራ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በደቡብ ክልል ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ህገ ደንብ በመፅደቅ የሀምበሪቾ ኢኮ ቱሪዝም ስፍራ ፅህፈት ቤት በመባል ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዉጪ እራሱን ችሎ በቦርድ እንደሚመራ ተገልጿል። የ6 ወር የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሪፖርት እንደሚያሳየዉ 2 መቶ 75 ሺህ ቱሪስቶች ማዕከላዊ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸውን ያመላክታል።
ከዚህ ዉስጥም ከ77 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቱሪስቶች የሀምበሪቾ ተራራን የጎበኙ ሲሆን በዓመት ወደ 500,000 የሚጠጉ ቱሪስቶች ተራራዉን ይጎበኙታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የዱራሜ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊና የቪዝት ከምባታ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት አቶ ሳምሶን ቶማስ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

የሀምበሪቾ ተራራን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ በከፍተኛ ፕሮጀክት ተራራውን የሚያቋርጡ 777 ደረጃዎችን መገንባቱ ተገልጿል።

ተራራው በቅርብ ጊዜ ለቱሪዝም ክፍት መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከ4 ና 5 አመት በፊት ትልቅ የፀሎት መዳረሻ ነበር። ከሀይኪንግ ጎን ለጎን በዓመት አንድ ጊዜ ጥር 11 ላይ ወደ 60 ሺህ የሚጠጉ የወንጌል አማኞች በስፍራ ፀሎት እንደሚያደርጉ አቶ ሳምሶን ቶማስ ጨምረዉ ገልፀዋል።

ስፍራውን ለቱሪስቶች ምቹ ለማድረግ የከምባታ ዞን መንገዶች ፅህፈት ቤት በየዓመቱ መንገዶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።

መንገዱን አስፋልት ለማድረግና በተራራዉ ላይ ሎጆችንና ሆቴሎች በመገንባት ምቹ ለማድረግ ፅህፈት ቤቱ እንደሚሰራ ተገልጿል። ስፍራዉን በዘላቂነት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ ስራዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተሰሩ ስለመሆናቸዉም ተገልጿል።
👍125🙏1
1.2 #ቢሊዮን ብር ለልማት ስራ የምታውለው ቤ/ክ

የመሰረተ ክርስቶስ ቤ/ክ ልማት ኮሚሽን ለ2025 ዓ.ም 1.2 ሚሊዮን ብር ለልማት ስራዎች ለማዋል የኮሚሽኑ ስራ አመራር ቦርድ ወስኗል። በቀጣይ በጀቱ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ እንደሚጸድቅ ይጠበቃል።

ቤተ ክርስቲያኗ ወንጌልን ከመስበክ ቀጥላ ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገዝ ስራዎችን ትሰራለች።
👍81🔥1👏1
በቤተ ክርስቲያን የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅም የተያዘው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን ተከሳሽ አብዱራህማን ነጋ የተባለ ነዋሪነቱ ቸሃ ወረዳ አዶሼ ቀበሌ ሲሆን ተከሳሽ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማስገኘት በማሰብ ከሌላ ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክ/ከተማ ጋሶሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የዝርፊያ ወንጀል ፈጽሟል፡፡

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመዉ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6፡30 በሚሆንበት ጊዜ የፎከስ ፌሎሺፕ ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት የሚገለገሉበትን ቅጥር አጥር ዘሎ በመግባት ንብረትነታቸው የቤተክርስቲያኑ የሆኑ ጠቅላላ ግምታቸው በድምሩ 33,050 ብር የሆኑ እቃዎች ከንብረት ክፍል ከፍቶ በማውጣት ከቤተክርስቲያኑ አጥር ግቢ ወደ ውጪ በመወርወር ከግብረ አበሩ ጋር ሊውሰድ ሲል የአካባቢው ሰዎች ድምጽ ሰምተው መጥተው ሊይዙት ሲሉ እገድላችኋለሁ እንዳትጠጉኝ እተኩሳለሁ ብሎ ያስፈራራቸው ሲሆን በጩኸት በመጡ ሰዎች ርብርብ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

በዚህም አስቦ በፈጸመው በተራ የስርቆት ወንጀል ክስ መመስረቱን የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ኤልያስ ሰብለጋ ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ገልጸዋል፡፡

ክሱ የቀረበለት የጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረጃዎች ከመረመረ በኋላ ተከሳሽ የተከሰሰበት ድንጋጌ በመቀየር በወንጀል ህጉ አንቀፅ 669 ንዑፅ አንቀፅ 3 መሰረት ጥፋተኛ በማለት የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ኤልያስ ሰብለጋ ጨምረው ለብስራት ራድዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋል፡ ሲል ያስነበበው ዳጉ_ጆርናል ነው።
👍93🔥1
የካቲት 29 እና 30 ቅዳሜ እና እሁድ በመስቀል አደባባይ በሚካሄደው ታላቅ ድግስ አስመልክቶ ካውንስሉ መግለጫ ሰጠ።

መግለጫውን የካውንስሉ ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በካውንስሉ ጽ/ቤት ሰጥተዋል።

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ፡ ከዓመት በላይ ዝግጅት ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፡ ስለ ኢትዮጵያ ሰላም፡ እድገት፡ ልማት የምንጸልይበት ይሆናል። እግዚአብሔርን በዝማሬ፡ በአምልኮ፡ በቃል የምናመልክበት ትልቅ ቀን ነው ብለዋል።

በመግለጫው አውቶብሶች በሚቆሙበት ስፍራዎች በጊዜ በመገኘት ወደ መስቀል አደባባይ እንድትመጡ ይሁን። በአካባቢው ከሚኖሩ የጸጥታ አካላት ጋር ትብብር በማድረግ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ አደራ።

በነዚህ ቀናት እንቅስቃሴዎቻችን ሁሉ በጾም ላይ ከሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በፍቅር እንዲሆን አደራ ብለዋል።

ፕሮግራሙን ቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከ ኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጋር በመሆን የተዘጋጀ ነው።
👍73🔥1
#2 ቀን ቀረው

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ

ከእውቁ ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ልጅ ሬቨረንድ ፍራንልኪን ግራሃም ጋር በምድራችን የእግዚአብሔርን ስም እንጠራለን።

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
👍74🔥2👏1🙏1