The Christian News
5.08K subscribers
3.66K photos
53 videos
912 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
ለ20 አመት ያለ ደሞዝ ህብረተሰቡን ያገለገሉት እውቅና ተሰጣቸው።

በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጣቸው

በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን በነፃ ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ  ዕውቅና የተሰጣችው ሲሆን እነዚህም፡-

1ኛ ዶክተር ዱዌን አንደርሰን እና ባለቤታቸው ጃኪ አንደርሰን ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በፍፁም በቅንነትና በታማኝነት እና በልዩ ፍቅር ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ታካሚዎችን በማገልገላቸው፣

2ኛ- ዶክተር ማርክ ክርንስ እና ባለቤታቸው አሊሰን ካርንስ ወደ ወላይታ ሶዶ በመምጣት ላለፉት 16 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በታላቅ ትህትና በሆስፒታሉ በማገልገል፣ ሀኪሞችን በማስተማር እና በማሰልጠን ላደረጉት አስተዋጽኦ።

3ኛ ሚስተር ኬን አስሙዝና ባለቤታቸው ማርጋሪት አስሙዝ ላለፉት 20 ዓመታት የሴንት ሉክስ ቦርድ አባል በመሆንና  ከውጪ ሀገር አጋሮች ለሆስፒታሉ ልማት የሚውሉ ገንዘብ እና ቁሳቁስ በማሰባሰብ ያለምንም ክፍያ በታማኝነት በማገልገላቸው:-

በዚህም መሰረት ለመላው ኢትዮጵያዊያን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለበጎ ምግባራቸው  በክልሉ መንግስት እና በወላይታ ዞን አስተዳድር  የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።

#ዳጉ_ጆርናል
🔥167👍7🙏5👏2🥰1
ከ65 ዓመታት በኋላ ታሪክ ሊደገም ነው

አንጋፋው ወንጌላዊ #ቢሊ ግራሃም በንጉሱ ጊዜ ነው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመጀሪያ ጊዜ የጀማ ወንጌል የሰበኩት። ለዚህ ስራቸውም ከንጉሱ ዘንድ ምስጋና ተችሯቸው ነበረ።

ዛሬ በሳቸው እግር የተተካው ልጃቸው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም፣ ታላቅ የወንጌል ድግስ አዘጋጅቷል።

“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፣ የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ታላቅ የወንጌል ድግስ ይካሄዳል። ከሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር በሚኖረው የአደባባይ ድግስ፣ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል።

ፕሮግራሙን የቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከካውንስሉ ጋር በጋራ በመሆን ነው ያዘጋጀው። በፕሮግራሙ ከሃአር ውስጥ ዘማሪዎች፣ መጋቢና ዘማሪ አገኘሁ ይደግ፣ዘማሪ አቤኔዘር፣ ዘማሪ ጉቱ እና ከውጪ ሃገራት የተጋበዙ ዘማሪዎች በመድረኩ ያገለግላሉ።

ድግሱን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዚህ የጸሎት፣ የወንጌል እና የምስጋና ድግስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሬቨረንድ ፍራንክሊን የሰማሪታን ፐርስ ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ተቋሙ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተራድኦ ስራን ሲሰራ ቆይቷል።

ሙሉ መግለጫውን ዩቲዩብ ገጻችን ላይ ይከታተሉ።
https://www.youtube.com/@TheChristianNews/featured
👍157🔥2🙏1
እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር
"ለክብሩ" TO HIS GLORY
በሚል መሪ ሃሳብ
የካቲት 23 በሚሊኒየም አዳራሽ አብረን እግዚአብሔርን የምናመልክበት የመዝሙር ድግስ ይኖረናል:: ሁላችሁም በዛን ዕለት ተገኝታችሁ አብራችሁን ጌታን እንድታመልኩ በአክብሮት እንጋብዛችኃለን።
#Danielamdemichael
#apexevents
#ለክብሩ#Tohisglory
#mezemurconcert #milleniumhall
#jesus #christian #worship #legeta #protestant
🙏187👍1🔥1
በሶርያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች የወደፊት ሕይወታቸው ያሳስባቸዋል።

ይህንን ያለዉ በሶርያ የሚገኙ ክርስቲያኖችን አነጋግሬ ነዉ ሲል የዘገበዉ ዎርዚ ኒዉስ ነዉ።

እንደዘገባዉ በዲሴምበር 8 ላይ የበሽር አል አሳድ ከስልጣን መወገዱን ተከትሎ ሀገሪቱ በአዲስ መንግስት መተዳደር ከጀመረች ሰንብታለች ከአዲሱ መንግስት በኋላ በሶሪያ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ለወደፊት ህይወታቸው እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

በአሳድ ስር ያሉ ክርስቲያኖች ግድያ እና አፈና እንዲሁም በስራ ቦታ መድልዎ እና ጾታዊ ጥቃት ይደርስባቸዉ እንደነበር ያስታወሰዉ የዎርዚ ኒዉስ ዘገባ አዲሱ መንግስት አሳድን ከስልጣን አስወግዶ አዲስ የሽግግር መንግስት ሲያቋቁም በሶሪያውያን ዘንድ ሰፊ ደስታ እና የነፃነት ስሜት ነበር።

የክርስቲያን ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የሆኑት ሜይ ቢታር "ጦርነቱ አብቅቶ ሊሆን ይችላል, አሁን ግን ወደማይታወቅ ሁኔታ እየገባን ነው" ይላሉ "መምህሮቼን እና ተማሪዎቼን ለማረጋጋት እሞክራለሁ ይህ የእኔ ሚና ነው በውስጤ ግን በጣም ፈርቻለሁ ሂጃብ መልበስ ወይም መስቀሌን ማውለቅ ያለብኝ ይመስልሃል?" ሲሉም ለዘጋቢዉ ይጠይቃሉ።

"ስለ ዜግነት እና የሃይማኖት ነፃነት ይናገራሉ" "ህይወታችን እንደማይለወጥ ይነግሩናል እኛ ግን ተግባራቸውን ለማየት እየጠበቅን ነው" የሚሉት ደግሞ በአሌፖ የሚገኘው የማሮኒት መሪ ሊቀ ጳጳስ ጆሴፍ ቶብጂ ናቸዉ።

ለደህንነታቸዉ ሲባል ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ በሶሪያ የሚገኝ አንድ የክርስቲያን የካቶሊክ ግብረ ሰናይ ድርጅት የስራ ባልደረባ በበኩላቸው “ሰዎች ከምሽቱ 5 ሰዓት በኋላ ጎዳና ላይ ከመሄድ ይቆጠባሉ። ክርስቲያኑ "በእርግጥ ፍርሃቱን በጣም ይገለጻል ክርስቲያኖች መሥራት አይችሉም, ብዙዎች በቤት ውስጥ ተቀምጠዋል ሲሉ ተደምጠዋል።
👍52🔥1
“የፕሮግራሙ ማዕከል መሆን አልፈልግም!” ዘማሪት #ሊሊ (ቃልኪዳን) ጥላሁን።
“የቃል ኪዳን ፍቅር” የተሰኘው የዘማሪት ሊሊ #መጽሃፍ ይመረቃል።

ኑ የአምልኮ ኪዳናችንን እናድስ! በሚል መሪ ቃል የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተ ክርስቲያን የመዝሙር ድግስ ልታዘጋጅ ነው። ፕሮግራሙን አስመልክቶ የቤተ ክርቲያኗ መሪ መጋቢ ተስፋሁን ሙላቱ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአምልኮ ድግሱ ላይ ዘማሪት ሊሊ (ቃልኪዳን) ጥላሁን፣ ዘማሪት አዜብ ሃይሉ እና ቤተልሔም ወልዴ ያገለግላሉ።

ቅዳሜ፣ መጋቢት 6 ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ በሚኖረው የአምልኮ ፕሮግራም “የቃል ኪዳን ፍቅር” የተሰኘው የዘማሪት ሊሊ መጽሃፍ ይመረቃል።

ከመጋቢት 6 ቀድሞ ባሉት ቀናት ቤተ ክርስቲያኗ የጾም እና ጸሎት፣ የወንጌል ስርጭት፣ የእግዚዓብሔር ቃል ጥናት፣ ዲቮሽን እና ሌሎችም መርሃ ግብሮችን ማቀዷን አሳውቃለች። ቤተ ክርስቲያኗ ፕሮግራሙን ከኤልቬትዝ ኤቨንትስ እና አርት ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀችው።

መጋቢ ተስፋሁን፣ በዚህ ፕሮግራም የአምልኮ ስርዓታችን እንዲታደስ እና ከእግዚዓብሔር ጋር ያለን ግንኙነት እንዲታደስ የሚሆንበት ይሆናል ብለዋል።

ሙሉ መግለጫውን ዩቱብ ገጻችን ላይ ያገኙታል
https://www.youtube.com/@TheChristianNews
17👍1🔥1👏1🙏1🕊1💯1
#የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ም/ፕሬዝዳንትና የልማት ኮሚሽኑ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶ/ር ስሞዖን ሔሊሶ የተመራ ቡድን በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ሚደጋቶላ ወረዳ የሚሰሩ የፕሮጀክት ስራዎችን ጉብኘት አደረገ።

በጉብኝታቸው በአካባቢው እየሰራ ያለውን የፕሮጀክት አፈጻጸም አድንቀው በአከባቢው በተከሰተ #ድርቅ አደጋ ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች የፍየል፣ የምርጥ ዘር፣ የራስ አገዝ ማደራጀት፣ ጥብቅ ግብርና እና የተሰሩ የውሃ ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ እንዳለ በጉብኝታቸው ወቅት መመልከት ችለዋል፡፡

ልማት ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ የሚስተዋለውን የውሃ #እጥረት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የ350 ሜትር ጥልቀት ያለው የውሃ ጉድጓድ ለማስቆፈር የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጧል፡፡

#ይህ ፕሮጀክት ለአካባቢው ህዝብ ዘላቂ #እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር የሚያስችል ሲሆን ለማስቆፈርም ከ27 ሚሊየን ብር በላይ መመደቡ ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ስሞዖን ሔሊሶ “ይህ ከምንሰራቸው በርካታ የሰብዓዊ እርዳታ እና ልማት ስራዎች መካከል አንዱ ነው በዓመት እስከ 2 ቢሊዮን ብር በመበጀት የተለያዮ ስራዎችን በሁሉ የአገርቱ ክፍሎች እየሰራን እንደሆነ ተናግረዋል።

“እንደ ወረዳችን በጣም ከፍተኛ ችግር የሆነውን የውሃ ችግር ለመቅርፍ ልማት ኮሚሽኑ ስራ ስለ ጀመረ ከልብ እናመሰግናለን #የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን የሰበአዊ እርዳታ እና ልማት ኮሚሽን በድርቅ ለተጎዱ ህብረተሰቦች የአስቾኮይ ጊዜ እርዳታን በመስጠት ለ644 አባወራዎች በመድረሱ እና በርካታ ስራዎችን እየሰራ ስለሚገኝ ዘመን የማይሽረውን ታሪክ ሰርታችዏል ያሉት ደግሞ የሚዳጋቶላ ወረዳ ዋና አስተዳደር አብዲ ኢብራሂም ናቸው።

ዘገባውን የላከልን የሕይወት ቴሌቪዥን ነው።
👍174🔥1🙏1
#ሰርጀሪው በድል ተጠናቆ ቤቱ ገብቷል 🙏🥰 #እግዚአብሔር ይመስገን🙏

ሰርጀሪው በድል ተጠናቆ ትላንት ቤት መግባቱን አረጋግጫለሁ (አቤል ደመላሽ)

በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።

እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤
ኢሳያስ 40 : 2,3

እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8 : 28

ሐሙስ 26ተኛ አመት Anniversary ያችንን ነበር። በእለቱ በእንዲህ ሁኔታ ውስጥ ነበርኩ። በብዙ ፈተና ውስጥ እንኳ ብንሆንም እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።

ስለእኔ ሰምታችሁ በፀሎት ያገዛችሁን የቤተክርስቲያኔ ሽማግሌዎች ፓስተሮች ወንጌላዊያን የሙሉ ጊዜ አገልጋዬች እንዲሁ በሀገር ውስጥም በውጭም የምትኖሩ ቅዱሳን : በህክምናው ሙያ በብዙ ፍቅርና ትህትና ያገለገላችሁኝ ዶክተሮች ነርሶች ሌሎችም ውድ ቤተሰቦቼ  ባለቤቴና ልጆቼ እንዲሁም ውድ እህቴ ረድሻ ሁላችሁንም ሌላ ቃል ስለሌለኝ እግዚአብሔር ይባርካችሁ እላለሁ ቀዶ ጥገናው በሰላም ተጠናቋል።

አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ :: ተባረኩልኝ እውዳችኃለሁ :: 🙏🙏❤️❤️
🙏2918👍6🔥1👏1
የውጪ ሃገር ዜጋ ቄስ

መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ የውጪ ሃገር ዜጋ ቄስ አድርጋ ሾመች።

ቄስ #አንድሪያስ ቪልሪክ ይባላሉ። በአዲስ አበባ የሪዲመር ኢንተርናሽናል መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን አገልጋይ ናቸው። ቄስ አንድሪያስ በዴንማርክ ወንጌላዊት ሉተራን መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ የተላከ ሚስዮናዊ ነው።

ቤተ ክርስቲያኗ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የውጪ ሃገርቅትን ዜጎችን በኢንግሊዝኛ ቋንቋ የምታገለግል ናት። ቄስ አንድሪያስ በቤተ ክርስቲያኗ ለቃሉና ቅዱስ ሚስጥራት አገልግሎት መጋቢ ከመሆን በተጨማሪ በመካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ የስነ መለኮት መምህር ነው።

በቅስና ለማገልገል ከቤተ ክርስሪያኗ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ፡ የአዲስ አበባ ሲኖዶስ ፕሬዝደንት ቄስ ዶ/ር ጽጌ በረዳ፡ የቤተ ክርስቲያኗ ምዕመናን፡ የቄስ አንድሪያስ ቤተሰብ በተገኙበት የአገልግሎት ሃላፊነቱን ተውቀብለዋል።

መረጃውን ከቤ/ክኗ የፌስቢክ ገጽ አገኘነው።
👍197🔥1👏1🙏1
የኢንግሊዝ #ፖሊስ ድምጽ ሳያሰሙ መጸለይን ከለከለ።

በርሚንግሃም #ከተማ #ውስጥ #አንዲት #ሴት በውርጃ ክሊኒክ አቅራቢያ ድምጽ ሳታሰማ መጸለዩአን ተከትሎ ፖሊስ አካባቢውን እንድትለቅ አስገድዷታል።

ፖሊስ የምትጸልየውን ሴት በአካባቢው መገኘቷ፡ ለትንኮሳ #እና ጫና ያሳድራል በማለት ከስፍራው አባረዋታል። ኢሳቤል ቫግሃን ስፕሩስ የተባለች ክርስቲያን፡ ከዚህ ቀደምም ቢሆን ጸረ ውርጃ አቋም በማራመድ የምትታወቅ ናት።

ኢሳቤል ቫግሃን ሁኔታውን ስታስረዳ "ምንም እያደረግሽ እንዳልሆነ አውቃለው፡ ነገር ግን ከውርጃ ክሊኒኮች 150 ሜትር መራቅ አለብሽ" አለኝ ትላለች። በእምነቴ ምክንያት ተገፋሁ ስትል ለዎርዚ ኒውስ ሁኔታውን አስረድታለች።

የበርሚንግሃም ፖሊስ ይህቺኑ ሴት ከዚህ ቀደም #ሁለት #ጊዜ አስሯት ነበረ። #እኔ የጸረ ውርጃ አቋም ስላለኝ ብቻ ወንጀለኛ ተደርጌ መታይቴ ልክ አይደለም ትላለች።

በአሁኑ ወቅት በኢንግሊዝ የሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ባወጣው #መረጃ መሰረት በእነዚህ የውርጃ ማዕከላት አካባቢ መገኘት ብቻ ወንጀል ነው ይላል። የኢሳቤል ጠበቃ ጉዳዩ አስጊ ነው ይላል።

እንደ ኢሳቤል #ሁሉ እዚህ መቆም አይቻልም የምንባል ከሆነ በቅርቡ በኢንግሊዝ #መጽሃፍ ቅዱሳዊ አቋም ይዞ መገኘት ወንጀል ሊሆን ይችላል ማለት ነው ሲል ጠበቃዋ ስጋቱን ገልጿል። ኢንግሊዝ "1984" የሚለው መጽሃፍ ላይ እንደተገለጸው አይደለችም ሲል ጨምሮበታል።

ፎቶዎቹ ፋይል ናቸው።
3👍3🔥1
#ታላቅ የወንጌል ኮንፍራስ በኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በወላይታ ቀጠና ጠረቤዛ ጊቢ የተካደው ሲሆን #ይህ መርሃ ግብር በ2 አመት አንዴ የሚከናወን ነው።

የወንጌል ኮንፍራሱ በታላቅ ድምቀት የተደረገ #ሲሆን በመርሃ ግብሩ ላይ #የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት #ቤተክርስቲያን ም/ክ #ፕሬዝደንት ዶ/ር ስሞዖን ሔሊሶ፤ #የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት #ቤተክርስቲያን #ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የእግዚአብሄረን ቃል የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ስሞዖን ሙላቱ ፤ መጋቢና ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ ፤ መጋቢና ዘማሪ ታምራት ሃይሌ ፤ ጋሽ ዮሃንስ ባሰና እንዲሁም የቀጠናው ጸሃፊ መጋቢ አብርሃም ቦታ ያገለገሉ ሲሆን ዘማሪ አስፋው መሸሻ እና የጊዶ ዃየር በዝማሬ አልግለዋል።

በነበረው መርሃ ግብር ላይ #የእግዚአብሄር መገኘት በኃይል የታየ ሲሆን ከ1001 በላይ ነፍሳት ክርስቶስ እየሱስን እንደግል አዳኛቸው አድረገው ተቀብለዋል።

የቀጠናው መሪዎች የተዘጋጀ #ልዩ #የፍቅር #ስጦታ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች ፤ ለመጋቢያን እንዲሁም የወላይታ ቤተ ክርስቲያን በወንጌል እንድትሰፋ ብርቱ #ዋጋ ለከፈሉ አባቶች ተበርክቷል።
👍172🔥1🙏1
#የናይጄሪያ ሉተርና ቤ/ክ 100ኛ አመቷን አከበረች።

ከተመሰረተች 100ኛ አመቷን በማክበር ላይ የምትገኘው የናይጄሪያዋ ሉተራን ቸርች ኦፍ ክራይስ ቤ/ክ የ100 ዓመት ክ/በዓሏን በተለያዩ መርሃ ግብሮች አክብራለች።

ቤተ ክርስቲያኗ በአሁኑ ወቅት ከ2.5 ሚሊዮን አባላት ያላት ሲሆን፣ በመላው ሃገሪቱ ከ2400 በላይ አጥቢያዎች አሏት።

ቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎቷን የጀመረችው ከሱዳን ዩናይትድ ሚሽን ጋር በመሆን በ1913 ሲሆን፣ በ1925 የናይጄሪያ ሉተራን ቸርች ኦፍ ክራይስ በመባል፣ ኑማን በምትባል ከተማ አገልግሎት ጀምራለች።

የመጀመሪያዎቹ ኢንግሊዛዊያን ሚሽነሪዎች ጡብ በመስራት እና ግብርና ተሰማርተው ወንጌል ይሰብኩ እንደነበር ታሪካቸው ይናገራል።

በማህበራዊ ስራዎች፣ በጤና፣ ትምህርት፣ የወጣቶችና ሴቶች አገልግሎት፣ የልጆች አገልግሎት እና የስነ መለኮት ትምህርትን የመሳሰሉትን ስትሰራ ቆይታለች። ቤተ ክርስቲያኗ የአለም አቀፉ ሉተራን ፌደሬሽን አባል ናት።
👍42🔥1
#የአጋር_መልዕክት

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዯጵያ
🙏🙏🙏🙏🙏
የ#ቢሊ ግራሃም ልጅ ሬቭረንድ #ፍራንክሊን ግራሃም በአባታቸው እግር ተተክተው ያገለግላሉ። በመስቀል አደባባይ አሸናፊው ወንጌል ይሰበካል፡ ታሪክ ይደገማል።
🔥🔥🔥

የካቲት 29 & 30
📍መስቀል አደባባይ

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል
👍137👏2🙏2🔥1👌1🕊1
በዴሞክራቲክ ኮንጎዋ #ጎማ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት መካከል ማገልገላቸውን ቀጥለዋል።

በቅርቡ M23 አማጺ ቡድን ከሃገሪቱ መንግስት ጋር ሲያደርግ የነበረው ጦርነት፣ 2 ሚሊዮን ዜጎች የሚኖሩባትን የጎማ ከተማ መቆጣጥሩ ይታወሳል። በተጋሄደው አውዳሚ ጦርነት እስከ 3ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

በጦርነቱ ምክኒያት ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆች፣ በየጎዳናው የወዳደቁ አስክሬኖችን መመልከት፣ የአካባቢን ደህንነት የሚያስጠብቅ ፖሊስ አለመኖር፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጥ፣ የጎማ ከተማን በቀናት ውስጥ ሲኦል አድርጓታል።

በዚህ ሁሉ ሰቆቃ የጎማ ክርስቲያኖች እሁድን በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው ከማመስገን አላገዳቸውም። ከተማዋ ላይ በአመጽ ፈንታ ተስፋ ይታይባታል ተብሏል። አሁንም ቢሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎች በከተማዋና አቅራቢያዋ አሉ።

በከተማዋ ከሚደረግ የሰብዓዊ እርዳታ ይልቅ፣ ወንጌል ትልቅ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ የአካባቢዋ አገልጋዮች ተናግረዋል። በተለይ ታዳጊ ሴቶች ተደጋጋሚ በሚደፈሩበት በዚህ ክፉ፣ ቀናት ውስጥ “Bwana Asifiwe” (እግዚዓብሔር ይመስገን) የሚሉ መዝሙሮች ይዘመራሉ። ለተጎጂዎች የአካባቢው ክርስቲያኖች አስፈላጊውን ሁሉ ቁሳዊ፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ።

በጦርነት በምትናወጠው ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ጎማ ከተማ፣ ወንጌል ለህዝቡ ተስፋ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን አመጽን ስትቋቋም፣ በዚህ ምስቅልቅል ወቅት ክርስቲያኖች ክርስቶስን እያሳዩ ነው ሲል የዘገበው CDI ነው።
👍137🔥2👏1😭1
#የአጋር_መልዕክት

#መለኮታዊ_ጉብኝት_ለኢትዮጵያ

የአምልኮ፡ ጸሎትና ወንጌል ስርጭት ታላቅ ድግስ የካቲት 29 & 30 በመስቀል አደባባይ ከሬቭረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር።

#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
             👇👇👇
በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን የተዘጋጀ
👍103🔥1🕊1
#አስደሳች #ዜና

#የኢትዮጵያ #ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት #ካዉንስል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል ሆነ።

በዛሬው እለት #የኢትዮጵያ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተቋማዊ አደረጃጀቱንና ዉስጣዊ አሰራሩን እንዲሁም የአባል ቤተዕምነቶች የእርስ በእርስ ግንኙነትና በተቋሙ ላይ ያላቸዉ እይታና እርካታ አስመልክቶ የተሰራ የዳሰሳ ጥናት ያጸደቀ ሲሆን በዳሰሳ ጥናቱ መሰረት የጉባኤውን አዲስ መተዳደሪያ ደንብ አጽድቋል።

ጉባኤዉ ከዚህ ቀደም በ7 አባል ቤተዕምነት አባልነት የነበረ ቢሆንም በአዲሱ ደንብ መሰረት 5 አባላት ብቻ እንደሚኖረዉ የተጠቀሰ ሲሆን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስልም አንዱ አባል ሆኗል።

በዛሬዉ እለት በፀደቀዉ ደንብ መሰረት
. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት
. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል
. የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን

በአባልነት እንደሚይዝ ደንቡ የሚጠቅስ ሲሆን ከዚህ ቀደም የጉባኤው አባል የነበሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፣ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ በካዉንስሉ እንደሚወከሉ ተጠቅሷል።

#ዛሬ ሲካሄድ በነበረው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መድረክ #የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ጉባኤውን በጠቅላይ ጸሐፊነት ለ2ኛ ዙር እንዲመሩ በጠቅላላ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተመርጠዋል።
👍12🔥21👏1🕊1
#20_የበረከት_ዓመታት

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን 20ኛ አመት ክብረ በዓል እና የአዲሱ የአምልኮ ስፍራ ልታስመርቅ ነው።

ቤተክርስቲያኒቱ ቀድሞ በተከራየችበት በጎተራ የእህል ንግድ ድርጅት ግቢ ውስጥ ላለፉት 18 አመታት የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች የቆየች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ እግዚአብሔር ባዘጋጀላት ስፍራ የራሷን የማምለኪያ አዳራሽ ገንብታ በቀጣዩ የእግዚአብሔር መንግስት #ወንጌል በሐይል ለመስበክ ዝግጅቷን አጠናክራ ቀጥላለች።

ስለሆኑም የ 20ኛ አመት የምስጋና ኮንፈረንስና የአዳራሸ ምረቃ ፕሮግራም ከመጋቢት 1-7 ታላላቅ አገልጋዮች፣ የቤተክርስቲያን መሪዎችና አባቶች በተገኙበት ይመረቃል።

አሁን የተገነባው የማምለኪያ አዳራሽ በአሁኑ ወቅት ጐተራ ማሳለጫ ሪፍት ቫሊ ዮኒቨርስቲ አጠገብ ሲሆን፣ በእግዚአብሔር እርዳታ ላለፉት አንድ አመት ሲሰራ የቆየነውን አዳራሽ ለእግዚአብሔር ክብርና ለቅዱሳን ጥቅም እንዲሆን ተመርቆ እንደሚከፈት ተገልጿል።

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ላለፋት 20 አመታት ወንጌል የመስበክ እና የማስተማር ተልዕኮ አንግባ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከች፣ የቆየች እና እያገለገለች ያለች ቤተክርስቲያን ነች።

የሰላም ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ኑና የረዳንን እግዚአብሔርን አብረን እናመስግን በማለት ጥሪዋን አቅርባለች።
👍114👏3🔥1
#ሰምተዋል?

👉 በአንድነት እግዚአብሔርን የምናመልክበት
👉 በፊቱ በጸሎትና ምልጃ የምንቀርብበት
👉 ታላቅ የወንጌል ስርጭት የምናካሂድበት

የካቲት 29 & 30 በቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን በተዘጋጀው የመስቀል አደባባዩ ድግስ፡ አይቀርም።

መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ ታላቁ ድግስ ላይ እርሶም በጌታ ፍቅር ተጋብዘዋል።
15👍3🔥1👏1
#36 ወጣቶች ወደ እግዚአብሔር መንግስት ተቀላቅለው፡ ተጠምቀዋል!

ከአዲስ አበባ 600 ኪ.ሜ ርቃ በምትገኘው የደቡብ ኢትዮጵያዋ አሪ ዞን ጂንካ ከተማ MKC፡ 36 ወጣቶችን በአካባቢው ባለ ወንዝ #አጥምቀናል

ወንጌል ነብሳትን እየለወጠ እየቀጠለ ነው፡ እጅግ ደስ ብሎናል አብራችሁን ደስ ይበላችሁ ብለዋል መጋቢ ደሳለኝ አበበ።
13🙏3❤‍🔥2👍2🔥1