#ዊን_ሶልስ_የበዓል_ስጦታ
ብራይት እስታር ርሊፍ ኤንድ ዲቨሎፕመንት አሶሼሽንና ዊን ሶልስ ፎር ጎድ ኢቫንጄሊካል ሚኒስትሪ በጋራ ልዩ የበዓል የምገባ ፕሮግራም አዘጋጁ። የኢየሱስ ክርስቲስን ልደት በዓል ምክኒያት በማድረግ የተዘጋጀ ግብዣ ነው።
የምሳ ግብዣው በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2፣ 500 ለሚሆኑ ወገኖች ነው የምገባ መርሃ ግብሩ የተካሄደው። ዊን ሶልስ ፎ ጋድ ያለፉትን 21 ዓመታት በአዲስ አበባና በመላው ኢትዮጵያ የማህበረሰብ ድጋፍ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

👍7❤2🔥1🙏1
ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት እዉቅና ተሰጠዉ።
#የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ምስጋና አቀረበ!
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊና የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ጽ/ቤት በመገኘት ሕብረቱ ከጉባኤው ምስረታ ጀምሮ ለጉባኤው መጠናከር እና ዕድገት ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና በማቅረብ የክብር ስጦታ አበርክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ጉባኤው እንዲመሰረት እንዲሁም ከተመሰረተ በኋላ የተመሰረተበትን ዓላማ እና ተልዕኮ ጠብቆና አጠናክሮ እንዲሄድ ከማድረግ አንፃር ከፍ ያለ አስተዋጽኦ እንዳበረከት በመግለጽ፤ ላበረከተው የላቀ አስተዋፆ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም ጉባኤው የተመሰረተበትን ተልዕኮ ለመፈጸም በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ሕብረቱ የተጠናከረ ድጋፍ እና ትብብር እንዲያደርግ በአክብሮት ጠይቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝዳንት ፓስተር ፃዲቁ አብዶ በበኩላቸው ለተደረገው ምስጋናና ስጦታ ከፍያለ ምስጋና አቅርበው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የጋራ ጉባኤ እንደመሆኑ መጠን ጉባኤው ለሃገር እና ለሕዝብ ጥቅም ታሳቢ አድርጎ የሚሰራቸው ሥራዎች ይበልጥ ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል፡፡

👍15❤3🙏1
“Why Should I Listen to God” የተሰኘ መጽሃፍ ተመረቀ።
መጽሃፉን የጻፉት መጋቢ ዶ/ር #ተፈራ በላቸው ናቸው። መጽሃፉ የጸሃፊው ወዳጅ ዘመዶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የስነ ጽሁፍ ሰዎች በተገኙበት በኢገስት አዳራሽ ነው የተመረቀው።
መጽሃፉ 253 ገጾች ሲኖረው በ12 ምዕራፎች የተዋቀረ የኢንግሊዝኛ ቋንቋ መጽሃፍ ነው። መጽሃፉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች የተብራሩበት፣ ፈጣንና ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ #እግዚአብሔርን ለማወቅና ፈቃዱን ለማድረግ በግልና በኅብረት መጣር እንዳለብን የሚገልጽ፤ የራሳችንን ሕይወት እንድንመረምርና አኗኗራችንን እንደ እግዚአብሔር ቃል እንድንቃኝ የሚያደርግ መጽሐፍ ነው ተብለዋል፡፡
ጸሃፊው መጋቢ ዶ/ር ተፈራ በላቸው፣ ከ30 በላይ የተለያዩ ሳይንሳዊ የጥናት ምርምሮችን በተለያዩ ጆርናሎች ላይ በማቅረብ የሚታወቁትና የብዙ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ባለቤት ናቸው።
መጽሐፉን ለእግዚአብሔር ክብርና ለቅዱሳን መታነጽ እንዲሆን መጋቢ ኢዮብ ደምሴና መጋቢ ሳምሶን ስምዖን ጸልየው ለንባብ እንዲበቃ አድርገዋል።

👍9❤4🔥2
የቢፍቱ ቦሌ #መካነ_ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን 25ኛ አመት ክብረ በዓል።
ቤተ ክርስቲያኗ የተመሰረተችበትን 25ኛ አመት የምስጋና ክብረ በዓል #Ka’ii ibsii ወይም #ተነሺና አብሪ በሚል መሪ ቃል አክብራለች።
በክብረ በዓሉ ቤተ ክርስቲያኗ አዲስ ያስገነባችውን የአምልኮ አዳራሽ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ቤ/ክ ፕሬዝዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ፣ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ ቄስ ዶ/ር ገመቺስ ደስታ እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል።
በ25ኛ አመት ክብረ በዓሉ፣ የስዕል እና የባህል አውደ ርዕይም ተዘጋጅቷል።
ቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ያለፉትን 25 ዓመታት #የወንጌል ስራን ስትሰራ ቆይታለች።
መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኗ የፌስቡክ ገጽ አገኘነው።

👍8🔥3❤1
#ለፓስተር_ጻድቁ_የመኪና_ስጦታ_ተሰጣቸው...
ዛሬ 10/5/2017 ለፓስተር ጻድቁ ላለፉት 7 ወራት መኪና ለመግዛት የተቋቋመው ኮሚቴ ዛሬ መኪናውን ለፓስተር አስረክቧል። በሁለት ወር ለመስረከብ የተዋዋለው ሰው በውሉ መስረት ማስረከብ አለመቻሉ ና ኮሚቴውን ያጋጠመው ችግር እንድፈታ የተለያዩ አካላት ባደረጉት ተሳትፎ መፍትሔ አግኝቶ መኪናውን ተቀብለናል።
መኪናው ለማበርከት ሐዋሪያው ቶማስ ምትኩ፣ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የጽህፈት ቤት ሐላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ፣ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዚዳንት ፓስተር ለውየው፣ የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ዋና ጸሐፊ ፓስተር ታምራት፣ ኮሚቴውን ያስተባበሩት ፓስተር ግዛቸው ለታና፣ ዘሪሁን ግርማ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በቦታው ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ በበኩላቸው በዚህ ኮሚቴ ውስጥ በዋናነት የነበሩት፣ ፓስተር ግዛቸው ለታን፣ ሐዋሪያው ቶማስ ምትኩን፣ ሐዋሪያው ጆን ግርማና፣ ዘሪሁን ግርማን ያመሰገኑ ሲሆን፣ በተጨማሪም በገንዘባቸውና በተለያየ መንገድ ያገዙትን፣ ድጋፍ ያደረጉ የህግ አካላትም በሙሉ ባርከዋል። ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን።

👍32❤17🔥2🙏1
#በኢትዮጵያ ቃለ #ሕይወት ቤተክርስቲያን የወጣቶች አገልግሎት ክፍል 50ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተከበረ።
#ይህ በዓል በመላው #ኢትዮጵያ በተለያዩ መረሃ ግብሮች እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን በደቡብ ምስራቅ ሸዋ ቀጠና በኢልጌሉና በሀደሮ ከተማ ዙሪያ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ሕብረት በድምቀት ተከብሯል።
በመረሃ ግብሩ ላይ #የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተክርስቲያን ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ሰምዖን ሙላቱ በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን "ወንጌል ቅብብሎሽ ነው ይህንን አደራ እስከሚቀጥለው ትውልድ ለማስረከብ እንዲተጉ" የአደራ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ስምዖን አክለው በወንጌል ጉዳይ ሳታመቻምቹ ፤ ለጌታ በተሰጠ የደቀ መዝሙር ሕይወት በመኖር እኛ ወንጌል በመስበክ እና በመመስከር ደቀ መዛሙርት በማፍራት እንዲተጉ አደራ በማለት አሳስበዋል።
ወጣቶች "የቀደሙ አባቶች የዋጋ ውጤት ናችሁ ያሉት ደግሞ በደቡብ ምስራቅ ሸዋ ቀጠና በኢልጌሉና በሀደሮ ከተማ ዙሪያ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሕብረቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጸጋዬ ዶሌ ናቸው።
አቶ ጸጋዮ ለወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች ለሀገር እና ለቤተክርስቲያን አስፈላጊ ከመሆናቸው በላይ ቀጣይ የቤተክርስቲያን ተረካቢዎች እና ለቀጣይ ትውልድ የምታሸጋግሩ ስለሆናችሁ እስከ ቀጣዩ ሕይወት ድረስ ጽንታችሁ ቁሙ ሲሉ ወጣቶችን መክረዋል።
በክብረ በዓሉ ላይ በሃደሮ ከተማ የጽዳት መረሃ ግብር በማከናወን ለቀደምት አባቶች ስጦታ የተበረከተ ሲሆን የቡራኬ እና የጸሎት መረሃ ግብር መከናወኑን ከሕይወት ቴሌቪዥን ተመልክተን ዝርዝሩን The Christian News - የክርስቲያን ዜና አሰናዳንላችሁ።

👍6❤4🔥1
ለወንጌላዊያን_ሚድያ_ባለሙያዎች_ስልጠና
ለወንጌላዊያን ሚድያ ባለሙያዎች “Resilience in challenging day to day life” በሚል ርዕስ #ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናውን የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን የሚድያ ባለሙያዎች ማህበር ከቲኪቆስ ሚድያ ጋር በመተባበር ነው የተዘጋጀው። በስልጠናው የወንጌላዊያን ሚድያ ባለሙያዎች ከስራዎቻቸው ባለፈ በአገልግሎት እና የግል ህይወታቸው ችግሮችን መቋቋም እና የማለፍን ጥበብ የተመለከተ የሚዳስስ ነው።
የወንጌላዊያን ሚድያ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ወንድም #ዘሪሁን ግርማ እንደዚህ የሚድያ ባለሙያዎችን ሁሉን አቀፍ አቅም የሚያጎለብት ስልጠና አስፈላጊነቱን ገልጸዋል።
በስልጠናው ከ30 በላይ የሚሆኑ ከክርስቲያን እና ሴኩላር ሚድያዎች የተወጣጡ የሚድያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ስልጠናው በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤ/ክ መካነ ኢየሱስ ዋናው ጽ/ቤት የተካሄደ ሲሆን፣ ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ተፈራ በላቸው ናቸው። ዶ/ር ተፈራ በቅርቡ “Why should I listen to God” የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙና ከ30 በላይ አለም አቀፍ ጆርናሎችን አሳትመዋል።
በእለቱ ከባህርዳር እና አካባቢዋ የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት መሪዎች እና ከቡታጅራና አካባቢዋ መካነ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የመጡ አገልጋዮች በአካባቢዎቻቸው ስላሉ የወንጌል መስሪያ እድሎችና ተግዳሮቶች አብራርተዋል።

👍9❤5🔥2🙏2
#የመሪዎች ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነዉ።
በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ #ኢትዮጵያ የተዘጋጀ ዓመታዊ የመሪዎች ስልጠና በቀጠና ሁለት #ሙሉ #ወንጌል ቤተክርስቲያን እየተካሄደ ነዉ።
በመድረኩ የአመራር ግንባታ ፈርጀ ብዙ ስልቶችን በመጠቀም የሚተገበር ሲሆን በየአመቱ የሚደረገዉ የመሪዎች ስልጠና ኮንፍረንስ አንዱ እንደሆነ ተገልጿል።
ባለፉት አመታት በእነዚህ የስልጠና ኮንፍረንሶች አማካኝነት ብዙ ፍሬ መፍራቱን የሚገልፁተ ግሬት ኮሚሽን በዘንድሮ ይህ የመሪዎች ስልጠና ኮንፍረንስ "የእግዚአብሔር መንግስት ዜግነትና የወንጌል አማኝ ተልእኮ በአለም አቀፋዊና አገራዊ አዉድ (Kingdom Citizenship and Evangelism Mission in Global and National Context)" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ይገኛል።
ከሀገር ዉስጥና ከሀገር ዉጭ በተጋበዙ ክርስቲያን ምሁራን አማካኝነት ትምህርትና ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ዛሬ ከጥር 20የጀመረዉ ስልጠና እስከ ጥር 22 2017 ዓ.ም እንደሚቆይ ታዉቋል።

❤14👍6🔥2👏1
#አስደሳች #ዜና 24 #ሰው #ወደ #እግዚአብሔር መንግስት ተጨመረ።
ይህ የሆነው የወላይታ ሶዶ ዮንቨርስት የወንጌላዊያን #ክርስትያን ተማሪዎች ህብረት የወንጌል ስርጭት ቲም በደቡብ #ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በቦረዳ ወረዳ ከጥር 14-18 /6/2017ዓ.ም ለተከታታይ 4 ቀናት በነበረው የወንጌል ስርጭት ነው።
የመከሩ ጌታ በብዙዎች ልብ ላይ ስሙን የቀደሰበት ሀይለኞች እጅ የሰጡበት ጠንቋዮች ለዚህ ጌታ ልባቸውን ያንበረከኩበት ወልደ እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ ሀይል በከተማው የበራበት የውቀቱን ሽታ የገለጠበት ገጠሩ በወንጌል የታረሰበት ጊዜ እንደነበረ አዘጋጆች ለThe Christian News - የክርስቲያን ዜና በላኩልን መረጃ ገልጸዋልል።
በወንጌል ስርጭቱ በአጠቃላይ የዳነ 24 ስሆን ፤ በንስሀ የተመለሱ 3 በሚሽኑ ተስፋ የሰጡ 37
በሚሽኑ ወንጌል የሰሙ 449 ሰዎች እንደሆኑ በተላከልን ሪፖርት ተገልጿል።
በዚህ ሚሽን 80 ወጣቶች የተሳተፋ ሲሆን በተጨማሪም ይህ ስብስብ ወደ ፍት የወንጌል ስራዎችን በተለያዮ ቦታዎች ለመስራት እቅዶች እንዳላቸው ገልጸዋል።
የቡዱን መሪዎች ለማግኘት ሄኖክ +251996530002 መደወል ይችላሉ።

👍25❤15🔥6👏3🕊1
#ምን እየተፈጠረ ነው ? 2657 #ሰዎች በአንድ #አመት
ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ የሚመራት #በኢትዮጵያ የሕይወት #ብርሃን #ቤተክርስቲያን፣ በአዲስ #ክርስቲያን ላይፍ አሴምብሊይ አጥቢያ ምን እየተደረገ እንደሆነ ግልጽ ... እንዴሆን ከፈለጋችሁ በጥንቃቄ አንብባችሁ ቪዲዮውን ተመልከቱ።
#ትላንት በቤተክርስቲያኒቱ የተጀመረውን የወንጌል ስራ ለመመልከት ሄደን ነበር። በርግጥ እንባችንን ጨርሰን #እግዚአብሔርን አመስግነን ተመለስን።
#ምንም #እንኳን ቤተክርስቲያኒቱ ከተመሰረተች ጥቂት ጊዜ ቢሆናትም በ #አንድ አመት የተሰራውን የሚሽኝ ስራ ሪፖርት ስስመለክት ግን የአንድ አመት ስራ አይመስልም።
ቤተክርስቲያኒቱ በ2016 ብቻ 88 ሚሽነሪዎችን በጌታ እርዳታ ለሚሽን ስራ ለመላክ ችላለች። በዚህም 2657 ሰዎች ጌታን እንደ ግል አዳኛቸው አድርገው የተቀበሉ ሲሆን 1198 ሰዎች ደግሞ የውሃ ጥምቀት ወስደዋል።
220 አብያተክርስቲያናት መተከል የቻሉ ሲሆን ከእነዚህ መካከል በአዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ 7 ሚሽነሪዎች ተልከው ብዙዎች የምስራቹን ወንጌል እንዲሰሙ የተደረገ ሲሆን 166 ሰዎች ጌታን ሲቀበሉ 110 ሰዎች የውሃ ጥምቀት የመውሰድ እድል አግኝተዋል።
#ይህ ጅማሬ ነው። ጉዞው ገና ነው። የምስጋና 2ኛ ቀን #ዛሬ ሁላችሁም እንዳትቀሩ ምክንያቱም እናንተም #ምን እየተከናወነ እንዳለ ማረጋገጥ የምትችሉት በቦታው ስትገኙ ብቻ #ብቻ ነው።
📍 በቤተክርስቲያን በተጀመረው የወንጌል አገልግሎት #ውስጥ #ጌታ ስለሰራው ድንቅ ሥራ እርሱን ለማክበር ኑ!!!
📍በአዲስ አበባና አካባቢዋ ወንጌል ወዳልደረሰባቸው ቦታዎች የምስራቹን ወንጌል እንድናደርስ የረዳንን እግዚአብሔርን ለማመስገን እና ምስክርነቶችን ለመስማት #ኑ እና ተካፈሉ።
#ሁላችንንም #እግዚአብሔር ይርዳን!!!

❤46🔥13👍10👏3🕊3❤🔥1👌1🆒1
ኢትዮጵያ ለክርስቲያኖች አስቸጋሪ ከሆኑ ሀገራት መካከል 33ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠች።
የኦፕን ዶርስ የ2025 ለክርስትና አስቸጋሪ ናቸው የተባሉ 50 ሀገራት ዝርዝር ይፋ ሆኗል።
400 ሺህ ክርስቲያኖች እንዳሉባት የሚነገረው የኪም ጆንጉን #ሀገር ሰሜን ኮርያ የመጀመሪያውን ስፍራ ስትይዝ 170 ሺህ ክርስቲያኖች እንዳላት የሚነገረው ጆርዳን ደግሞ 50ኛ በመሆን የመጨረሻውን ስፍራ ይዛለች።
ሰሜን ኮርያ እና ጎረቤታችን ሶማሊያ ከ2023 ጀመሮ የአንደኝነትን #እና የ2ኛን ስፍራ እንደያዙ እጅግ አስቸጋሪ በሚል የነበራቸውን ስፍራ የ2025 ሪፖርትም በተመሳሳይ 1ኛ እና 2ኛ ላይ ተቀምጠዋል።
በ2024 እጅግ አስቸጋሪ ከሚባሉት 10 ሀገራት 4ኛ ስፍራ ላይ የነበረችው ጎረቤታችን ኤርትሪያ ዘንድሮ ወደ 6ኛ ደርጃ ዝቅ ስትል 8ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ሱዳን ደግሞ እጅግ አስቸጋሪ በመሆን ወደ 5ኛ ተራ ቁጥር ከፍ ብላለች።
በ2024 ዝርዝር ውስጥ የነበሩት እንደ ኢንዶኔዢያ እና ማሌዢያ የተባሉ ሀገራት በዘንድሮው ከዝርዝር ውጪ ሲሆኑ ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ ዝርዝር ውስጥ ያልነበሩት ካዛኪስታን እና ቻድ በ2025 ሪፖርት 47ኛ እና 49ኛ ስፍራን ይዘዋል።
በ2023 39ኛ ስፍራ በ2024 32ኛ ስፍራን ይዛ የነበረችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ህዝብ 4 በመቶ ብቻ ክርስቲያን ከሆነባት ዖማን ተከትላ በዘንድሮው ሪፖርት 33ኛ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች።
54 ሀገራት ያቀፈችው አሕጉራችን አፍሪካ 20ዎቹ ሀገራት በዝርዝር ውስጥ ሲካተቱ እጅግ አስቸጋሪ ከሆኑ 10 ሀገራት መካከል 5ቱ አፍሪካ አህጉር ውስጥ ያሉ እንደሆኑ ዘገባው ጠቅሷል።
ባለፈው አመት ብቻ በእምነታችው ምክንያት 4,476 ክርስቲያኖች የተገደሉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 3,100ዎቹ በናይጄሪያ ብቻ የተገደሉ ናቸዉ።
ተጨማሪ Facebook ላይ ይመልከቱ

😭23🤔7👍5🔥3💔2❤🔥1🙏1🕊1
ለ20 አመት ያለ ደሞዝ ህብረተሰቡን ያገለገሉት እውቅና ተሰጣቸው።
በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጣቸው
በክርስትያን ሆስፒታል ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ ህብረተሰቡን በነፃ ሲያገለግሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዕውቅና የተሰጣችው ሲሆን እነዚህም፡-
1ኛ ዶክተር ዱዌን አንደርሰን እና ባለቤታቸው ጃኪ አንደርሰን ላለፉት 20 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በፍፁም በቅንነትና በታማኝነት እና በልዩ ፍቅር ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ታካሚዎችን በማገልገላቸው፣
2ኛ- ዶክተር ማርክ ክርንስ እና ባለቤታቸው አሊሰን ካርንስ ወደ ወላይታ ሶዶ በመምጣት ላለፉት 16 ዓመታት ያለምንም ክፍያ በታላቅ ትህትና በሆስፒታሉ በማገልገል፣ ሀኪሞችን በማስተማር እና በማሰልጠን ላደረጉት አስተዋጽኦ።
3ኛ ሚስተር ኬን አስሙዝና ባለቤታቸው ማርጋሪት አስሙዝ ላለፉት 20 ዓመታት የሴንት ሉክስ ቦርድ አባል በመሆንና ከውጪ ሀገር አጋሮች ለሆስፒታሉ ልማት የሚውሉ ገንዘብ እና ቁሳቁስ በማሰባሰብ ያለምንም ክፍያ በታማኝነት በማገልገላቸው:-
በዚህም መሰረት ለመላው ኢትዮጵያዊያን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለበጎ ምግባራቸው በክልሉ መንግስት እና በወላይታ ዞን አስተዳድር የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል ።
#ዳጉ_ጆርናል

🔥16❤7👍7🙏5👏2🥰1
ከ65 ዓመታት በኋላ ታሪክ ሊደገም ነው
አንጋፋው ወንጌላዊ #ቢሊ ግራሃም በንጉሱ ጊዜ ነው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለመጀሪያ ጊዜ የጀማ ወንጌል የሰበኩት። ለዚህ ስራቸውም ከንጉሱ ዘንድ ምስጋና ተችሯቸው ነበረ።
ዛሬ በሳቸው እግር የተተካው ልጃቸው ሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም፣ ታላቅ የወንጌል ድግስ አዘጋጅቷል።
“መለኮታዊ ጉብኝት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፣ የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ ታላቅ የወንጌል ድግስ ይካሄዳል። ከሬቨረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ጋር በሚኖረው የአደባባይ ድግስ፣ የጸሎት፣ የወንጌል ስብከት እና የዝማሬ ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል።
ፕሮግራሙን የቢሊ ግራሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከካውንስሉ ጋር በጋራ በመሆን ነው ያዘጋጀው። በፕሮግራሙ ከሃአር ውስጥ ዘማሪዎች፣ መጋቢና ዘማሪ አገኘሁ ይደግ፣ዘማሪ አቤኔዘር፣ ዘማሪ ጉቱ እና ከውጪ ሃገራት የተጋበዙ ዘማሪዎች በመድረኩ ያገለግላሉ።
ድግሱን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠ/ጸሃፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ፣ በአዲስ አበባ ከተማ እና አቅራቢያዋ የሚገኙ ክርስቲያኖች የካቲት 29 እና 30 በመስቀል አደባባይ በመገኘት በዚህ የጸሎት፣ የወንጌል እና የምስጋና ድግስ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሬቨረንድ ፍራንክሊን የሰማሪታን ፐርስ ፕሬዝደንት ሲሆኑ፣ ተቋሙ ለረጅም አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተራድኦ ስራን ሲሰራ ቆይቷል።
ሙሉ መግለጫውን ዩቲዩብ ገጻችን ላይ ይከታተሉ።
https://www.youtube.com/@TheChristianNews/featured

👍15❤7🔥2🙏1
ተለቀቀ ዝርዝር ዘገባዉን ይመልከቱ https://youtu.be/u_VFwnGWGC0?si=WfdTeDyTFpsm1vOg
YouTube
ከ65 ዓመታት በኋላ ታሪክ ሊደገም ነው። | የቢሊ ግራሃም የወንጌል ማህበር ታላቅ የወንጌል ድግስ

#gospel
#thechristiannews #singer #jesus #jesuschrist #መልካም በዓል #marsiltvworldwide #yonatanaklilu #abiye #ebc #fana_tv #ebs #reels
#saturdayafternoonshow_ebstv #ethiopia #ethiopiantvshow …

❤7👍1🔥1