The Christian News
5.37K subscribers
3.08K photos
29 videos
730 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#አስደሳች #ዜና

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

መረሃ ግብሩን በማስመልከት በዛሬው እለት በሕብረቱ ጽ/ቤት The Christian News - የክርስቲያን ዜና መግለጫ ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መጪውን የ2016ዓ.ም ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የአንድነት ጊዜ አዘጋጅቷል።

ሕብረቱ ይህንን ያለንበትን የጻጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን ጸሎት እንዲደረግ አውጆ እንደ ነበር በመግለጫው ያስታወሱ ሲሆን ጾም እና ጸሎቱ በቀሩት ቀናትም ተጠናክረው በመላው ወንጌል አማኞች ዘንድ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም እንደሚያሄድ የገለጹት መሪዎቹ በአዲስ አበባ እና አከባቢው የሚገኙ ምዕመናን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንዲሳተፉም ጥሪ አቀርበዋል።

ተጨማሪ የቪዲዮን ዝርዝር ዘገባ ይዘን እንመለሳለን።
#ነገ #በአዲስ #አበባ #እስታዲየም
#ኑ አዲስ አመትን አብረን እንቀበል።
ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ

መስከረም 1 በአዲስ አበባ እስታዲየም የአምልኮ ፕሮግራም ይካሄዳል።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ይካሔዳል።

የጳጉሜ ወር በሙሉ ለሃገራችን ሰላም እና ለምድራችን እረፍት እንዲሆን ጸሎት ሲደረግ እንደ ነበር ይታወሳል።

#ነገ በመስከረም 1/2016ዓ.ም በአዲስ አመት የጾም ጸሎቱ ማጠቃለያ እና የጋራ የአምልኮ እና የምስጋና መረሃ ግብር በአዲስ አበባ እስታዲየም የሚደረግ ሲሆን በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው አብረን አዲስ ዓመትን እንቀበል።
የአዲስ አመትን አስመልክቶ #ልዩ ፕሮግራም በአዲስ አበባ እስታዲየም እየተካሄደ ነው።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" እየተካሄደ በሚገኘው ልዩ የበዓል #ፕሮግራም ላይ ክብርት ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የአብያተክርስቲያናት መሪዎች እና ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እየተከናወነ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻዲቁ አብዶ የእንኳን አደረሳሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ተጨማሪ ዝርዝር ይዘን እንመለሳለን...

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
"በዉጪ #ሀገር ሆናችሁ የጥላቻን #ንግግር የምትዘሩ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ አሳስባለሁ" ፖስተር ፃዲቁ አብዶ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ እስታዲየም እየተካሄደ ባለው የአዲስ አመት #ልዩ ፕሮግራም #ላይ ነው።

ፓሰተር ጻዲቁ በመልዕክታቸው 2016 #ሰላም የምንሆንበት አንዳችን ሌላውን የምናንጽበት ፤ የምንገነባበት ለሌላው ውድቀት የማንሰራበት ፤ ወጥመድ የማንዘረጋበት ፤ ድልድይ የምንገነባበት ድልድይ የምንሰራበት #ዘመን እንዲሆንልን #እግዚአብሔር በሉዓላዊነቱ ይርዳን ብለዋል።

ሰላም ለማንም #ሰው እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉት መጋቢ ጻዲቁ ከሰላም ውጪ የሚገኝ ምንም ነገር የለም ቢገኝም አይቆይም ስለዚህ ለሁላችንም ሰላም እንዲሆን እለምናለሁ።

እኛ ክርስቲያኖች እንደ አማኝ ሀገራችን ሰላም እንድትሆን እንጸልያለን ምንም #እንኳን እንድምንፈልገው ባይሆንም እግዚአብሔር በሚያውቀው በዘላለማዊ እውቀቱ #ወደ #መልካም ነገር እንደምናልፍ እናምናለን።

እኛ እንደ ሰው ድርሻ ሰላም የሚቀጥልበትን እና የምንተናነጽበትን እንፈልግ ፤ ጥላቻን ከመዝራት እንቆጠብ ፤ ጥላቻ ከልባችን ይወገድ ፤ የቂም በቀል ፍላጎት ከውስጣችን ይጥፋ።

በውጪ ሀገር ሆነው የጥላቻን አረፋ በማሕበራዊ ሚዲያ የሚደፍቁ ሰዎች #ስለ እግዚአብሔር ብለው ጥላቻቸውን ከመዝራት እንዲቆጠቡ በዚህ አጋጣሚ በዚህ ጉባኤ በይፋ መልዕክት አስተላልፋለሁ ብለዋል።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
“የሰማይ #አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

“እግዚአብሄር ታላቅ ነገር አደረገልን እኛም ደስ አለን” ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

የአዲስ አበባ #ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ እስታዲየም ተገኝተዉ ያስተላለፉት #መልዕክት #እግዚአብሔር ተግዳሮት በሚመስል መንገድ ውስጥ በርካታ ነገሮችን አሳክቶ ስራችንን ፍሬያማ አድርጎታል።

#ብዙ የምንወድቅባቸው የሚመስሉ መንገዶችን አልፈናል ዳገቶች ፤ ሸለቆዎች ነበሩ ብዙ ሰላም የሌለባቸውን ሀገሮች ታሪክ ስንመለከት እግዚአብሔር ስለ ሰጠን ሰላም እናመሰግነዋለን።

ፍጹም ስላማችን እንዲደፈርስ እርስ በእርሳችን እንዳንቀባበል እንድንበታተን ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ፈጽሞ መበታተን እንዲሆን ያልተሰራ ነገር የለም ከውስጥም ከውጪም ብዙ ጫናዎች ነበሩብን #ነገር #ግን ከእግዚአብሔር ጋር ጸንተን ቆመናል።

በእነዚህ የውጣ ውረድ መንገዶች በጸሎታችሁ አብራችሁን ለነበራችሁ በብዙ መንገድ ስትለፉ ስትደክሙ በልማት ፤ በበጎ አድራጎት ፤ በሰላም ስራዎች ያልተለያችሁን ለትውልዱ መልካሙን ዜና በመንገር ተስፋ እንዲኖረው ይልቁንሙ ከሁኔታዎች በላይ #እግዚአብሔር የሚለውን ለሃገራችን ያለውን እንዲመለከት በማድረግ ብዙ ዋጋ የከፈላችሁ እና የሰራችሁ #በሙሉ እናመሰግናችኋለን።

በአዲሱ አመትም በርካታ ውጥኖች አሉን በርትተን እንሰራለን አንሰንፍም ፤ ፈጽሞ ስንፍናን አልተማርንም በመጽሐፍ #ቅዱስ ተጽፎ ያነበብነው አባታችሁ ተግቶ ሲሰራ ነው። እኛም ልጆቹ ተግተን እንሰራለን።

በፍቅር ወንድማማችን በማስታረቅ ፤ በማቀራረብ የሰላሙን #ዜና እየተናገርን የሰላም ስራተኞች በመሆን እየታወቅን ይልቁንም ለምድራችን ብዙ ፍሬ እንዲበዛ እግዚአብሔር ለምድራችን የወደደውን ያለመከልከል መስራት እንዲችል ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ብርቱ ሰራተኞች በመሆን ለመልካም ስራ እጅ ለእጅ ተያይዘን ለምድራችን አብረን እንድንተጋ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

እያየነው ያለነው ፍሬ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሳይሆን የሚያበረታ ነው አባቶቻችን ልጆቻችን ይሰሩታል ብለው ያሳለፉትን ይህ ትውልድ እግዚአብሔር እረድቶን በራሳችን እውቀት እና ገንዘብ አባይን ገድበናል ብዙም ፍሬ አግኝተናል ይህ ቀላል አይደለም።

አንድ ላይ ሆነን ከሰራን እና ከተደጋገፍን የያዝነው ስራ በጸድቅ ከፈጸምን ይከናወንልናል ነህምያ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነስተን እንሰራለን" እንዳለው እኛ ተነስተን እንሰራለን የሰማይ አምላክም ያከናውንልናል።

#ዛሬ የጀመርነው አዲሱ አመት ለሁሉም የሃገራችን ክፍል ሞልቶ የሚፈስበት ወንድማማቾች ተጸጽተው የሚተቃቀፉበት ፤ ለምድራቸው ሰላም በጋራ የሚሰሩበት የኢትዮጵያ እሴት ደምቆ የሚታይበት ብዙ ውድቀቷን የሚፈልጉ #ኢትዮጵያን በሰላማዊነቷ በብዙ ለውጥ እና የልማት ስራዎች የሚሰራበት አመት እንደሚሆንልን እናምናለን።

#መልካም #አዲስ #አመት

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production
#እንኳን #አደረሳችሁ
#ውድ ቤተሰቦቻችን በአዲሱ አመት ተወዳጅ ፕሮግራሞች መካከል በBetachn ቤታችን Tv ተሰናድቶ በኢቫንጀሊካል ቴሌቪዥኝ የተላለፈው የተወዳጁ #ነብይ አበበ ሃ/ማርያም እና ቤተሰቦቹ ይዘንላችሁ ቀርበናል ሀሳብ አስተያየታችሁን እንድታጋሩን ግብዣችን ነው።

በድጋሜ #መልካም አዲስ አመት ፕሮግራሞችን በሙሉ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ

ክፍል 03 https://www.youtube.com/watch?v=XNtG-SFvD8Y
ክፍል 02 https://www.youtube.com/watch?v=lf2y9vTps-I
ክፍል 01 https://www.youtube.com/watch?v=Iz-3D7CkfK8
#በድል #ተጠናቋል
#እግዚአብሔር #ይመስገን 🙏🙏🙏

#በኢትዮጵያ ወንጌላውያውያን አብያተ ክርስቲያናት #ሕብረት የ2016ዓ.ም #አዲስ #ዓመት ምክንያት በማድረግ በ "አዲስ አበባ እስታዲየም" ሲካሄድ የቆየው #ልዩ የበዓል #ፕሮግራም በድል ተጠናቋል።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ

#መልካም #አዲስ#አመት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

Photo 📷 Hossana Photo & Video Production #እናመሰግናለን
#በአዲስ #አመት #ሌላ #በረከት
ከግማሽ #ሚልዮን በላይ .. በማዉጣት ለአቅመ ደካሞች ..

የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል አጥቢያ ከጉድለቷ በመቆረስ ከ550,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሶስት የአቅመ ደካሞች ቤት አስመረቁ።

በፕሮግራሙ ላይ የፌይዝ ባይብል #ኢንተርናሽናል ቸርች መሪ የሆነው ቢሾፕ ዳዊት ሞላልኝ እንዲሁም የልደታ ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤ አቶ ዘሪሁን እና የወረዳ 8 አፈጉባኤ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቀን አስረክበናል::

በዚህ በጎ ተግባር ላይ በገንዘባችሁ እና በሙያችሁ የተሳተፋችሁ የቤተክርስትያናችን አባሎች #ሁሉ #እግዚአብሔር ይባርካችሁ::

Fbi Church Miracle Chaple Mekanisa
በ2023 #ብቻ ከ1ሺህ በላይ ክርስቲያኖች ተገለዋል።

#ዓለም #አቀፍ የእርዳታ ተሟጋች ድርጅት በናይጄሪያ እስካሁን ከ1,000 በላይ ክርስቲያኖች በናይጄሪያ ታጣቂዎች መገደላቸውን ዘግቧል።

ግድያው የተፈፀመው በፉላኒ እረኞች እና በቦኮ ሃራም እና በምዕራብ አፍሪካ አሸባሪ ቡድኖች ነው ሲል አስነብቧል።

ታጣቂዎች ክርስቲያኖችን ከመግደል በተጨማሪ አማኞችን በማፈን ከድሆች የገጠር ማህበረሰቦች አቅም በላይ ገንዘብ ይጠይቃሉ ሲል ገልጿል።

በቅርብ ጊዜ የፉላኒ ታጣቂዎች በፈረንጆቹ ኦገስት 21 ቀን በባቺ ከተማ ሰባት ክርስቲያኖችን ጠልፈው ጠላፊዎቹ 2,600 ዶላር ካሳ እየጠየቁ ነው ይህም ለተጠለፉት ክርስቲያኖች ቤተሰቦች ብዙ ገንዘብ ነው። ገንዘቡ ካልተከፈለ ደግሞ አጋቾቹ እስረኞችን እንደሚገድሉ ዘገባው አክሏል።

በ2023 ክርስቲያኖች ከሚሰደዱባቸው 50 አገሮች ውስጥ ናይጄሪያን 6ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የክርስቲያን ተሟጋች ድርጅት በድረ-ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ ገልጿል።
#መምህሩ...
የመዝሙር ድግስ ከዘማሪ በረከት ተስፋዬ ጋር
ጥቅምት 4 በሚሊኒየም አዳራሽ
#አባባ #ሴባ #ዋባሎ #ከዚህ #አለም #ድካም #አረፉ!

አባባ በ1901ዓ.ም በወላይታ ዞን ኦፋ ወረዳ ሳዶዬ ቀበሌ የተወለዱ ሲሆን በ1952 ዓ.ም ከተወለዱበት ከኦፋ ወረዳ ወንጌልን ለማገልገል ወደ ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ ማንአራ ቀበሌ አቀኑ።

በተያዘም ከጤፓ ቀበሌ ጀምሮ በጨራቼ አድርጎ እስከ ጫው ካሬ ገበረ ማህበር ድረስ በቁጥር 13 የቃለህይወት ቤቴክርስቲያንን የመሠረቱና የተከሉ እኔን ጨምሮ በርካቶች ወንድሞቼና እህቶቼ ወደዚህ ዓለም እንዲንመጣ በረከት የሆኑ ታላቅ የእምነት አባት እና የሥጋ አያቴን በሞት ማጣት ምነኛ የሚያሳዝን ብሆንም ወዳገለገሉ ጌታ መሄዳቸው ከባድ መታደል ነው።

አባባ በበጉ ሠርግ በዳግም ምጻት እንገናኝ ቻው መልካም እረፍት።

Taway lo"uwan da!!
ልጃቸዉ
"የዘላለም ፈጣሪ"
የመዝሙር ኮንሰርት
መስከረም 20/2016 ከሰዓት 10:30
በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
ሁላችሁም ተጋብዛችኃል!!!
#አሳዛኝ_ዜና_እረፍት 😭

ልብ ይሰብራል 😭

#Ethiopia | ሆሳዕና እጅግ በጣም ጥልቅ ሀዘን ዉስጥ ናት።

ዛሬ ከሆሣዕና ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ላይ እያሉ ሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመኪና አደጋ የሆሣዕና ከተማ እናት ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን መሪ እና አገልጋይ የሆኑ ዮናስ ዱባለ እና አብረውት ከነበሩት ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ህይወታቸው አልፏል።

በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የሶዶ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሶዶ ወረዳ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ፍሰት ቁጥጥር ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን አማረ ታከለ እንዳሉት በዛሬው እለት ከጠዋቱ 12:00 ሰአት ላይ የህዝብ ማመላለሻ FSR የሰሌዳ ቁጥር ደቡብ 13955 የሆነ 49 ሰዎችን ጭኖ ከአዲስ አበባ እየመጣ ከሆስአና ወደ አዲስ አበባ የሚሄድ የሰሌዳ ቁጥሩ B-20669 ላንድ ክሮዘር መኪና ጋር በሶዶ ወረዳ አናቲ ቀበሌ በመጋጨት የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 4ሰዎች ከባድ ጉዳት እንደደረሰ ገልፀዋል፡፡

ዋና ሳጅን ጨምረው እንዳብራሩት አደጋው የተከሰተበት ሰአት የአየር ንብረቱ ጭጋጋማ በመሆኑ እንዲሁም አደጋ የደረሰበት አካባቢ መንገዱ ብልሽት ያለበት በመሆኑ በየጊዜው አደጋ እንደሚደርስና በተደጋጋሚ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት የሚቀጥፍና ከፍተኛ የንብረት ውድመት የሚያስከትል በመሆኑ አሽከርካሪዎች ከፍጥነት በላይ ባለማሽከርከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የዘገበው የሶዶ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ለቤተሰቡ ለቤተክርስቲያን ምዕመን ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን 🙏🙏 😭😭😭😭
የዘላለም ፈጠሪ የዝማሬ ኮንሰርት ከሃና ተክሌ ጋር
የፊታችን መስከረም 20 በምስራቅ መሰረተክርስቶስ ቤተክርስቲያን....
#እንኳን #ደስ #አሎት 🙏🙏

#በኢትዮጵያ #ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉት #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ እዉቅና ተሰጣቸው።

መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን 92ኛው ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ በቢሾፍቱ ከተማ በቤተክርስቲያኗ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህም ጉባኤ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወንጌልን በቃልና በኑሮ ምሳሌ በመሆን ያገለገሉ ቀደምት አባቶች #የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት መጋቢ ጻድቁ አብዶን ጨምሮ የመሠረተ ክርስቶስና የሌሎች ቤተዕምነት አገልጋዮች ዕውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ካዎንስል ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጄ ጀምበሩን ጨምሮ የተለያዩ የቤተዕምነት መሪዎች ተገኝተዋል።

በጉባኤ ላይ በተለይ መልኩ አስከ ዛሬ እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል እውነት በመስበካቸው በመልካም ምሣሌነታቸው ከተመሰከረላቸው መካከል ለአሁኑ 10 ከሌሎች ቤተዕምነቶች 11 ደግሞ ከመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 21 አገልጋዮች በጉባኤ ፊት እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የእውቅና መርሃግብር ወደፊት በስፋት እንደሚቀጥል የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሣለኝ አበበ ገልፀዋል።