The Christian News
5.09K subscribers
3.66K photos
51 videos
910 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#በሰላም #ተጠናቋል

ከ3000 በላይ የቤተ-እምነት መሪዎች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ዓለም አቀፍ አስተማሪዎች እና የወንጌል ሠራተኞች የታደሙበት "የመጋቢያን ኮንፍራንስ" በሚሊኒየም አዳራሽ ተጠናቀቀ።

“እርቅ፣ መንፈሳዊ ተሃድሶና መነቃቃት ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የመሪዎች ኮንፍራን የተጠናቀቀ ሲሆን The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን በጉባኤው የነበረውን ድባብ በተመለከተ መሪዎችን አናግረን መረጃዎችን ይዘን ምሽት ላይ የምንመለስ ይሆናል።

ጉባኤዉ የአቋም መግለጫ ያዉጣ ሲሆን መሉ መግለጫዉን በyoutube ቻናላችን ይዘን እንመለሳለን።
👍72👏2
የኬንያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አስራት ለቤተክስርቲያን የማይሰጡ ሰራተኞች ላይ ክትትል እንደሚያደርጉ አስታወቁ

በኬንያ የናንዲ ግዛት ገዥ አዲስ የተሾሙ ስራ አስፈፃሚዎች 10 በመቶ ገቢያቸውን ለቤተክርስትያ እንዲሰጥ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸዉን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የናንዲ ግዛት አስተዳዳሪ እስጢፋኖስ ሳንግ መመሪያው ያስፈለገው አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከመሪዎች እና ከግዛቲቱ መንግስት ድጋፍ ስለሚያስፈልጋቸው ነው ብለዋል።

በዴይሊ ኔሽን ድህረ ገጽ ዘገባ መሰረት "በመጨረሻ የስራ ዘመኔ የምሾማቸዉ ዋና የስራ ኃላፊዎች በተለየ መንገድ መስራት እና ለህብረተሰቡ ማገልገል አለባቸው" ሲል ተናግረዋል።ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን ያሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መሪዎች በተገኙበት በተካሄደው የባለሥልጣናቱ ቃለ መሃላ ወቅት ነው።

ገዥው የአስራት ትእዛዙን እንዴት ለማስፈጸም እንዳቀዱ ባይታወቅም አስራት በማይሰጡ  የመንግስት ሰራተኞችን የስም ዝርዝር ከሀይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።አሥራት ለቤተ ክርስቲያን የመስጠት ልማድ የክርስትና የጥንት አካል ቢሆንም የግዴታ መሆን አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ እርስ በእርሱ የሚጋጩ አስተያየቶች ተሰንዝረዋል፡፡

በኬንያ ያሉ ገዥዎች እና የስራ አስፈፃሚ ሰራተኞቻቸው ለትምህርት ቤቶች፣ ለመንገዶች እና ለሆስፒታሎች የታሰበ የህዝብ ገንዘብ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር ያደርጋሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
👏63👍1
የምጽአት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል በሚል የሰጉ 100 የዩጋንዳ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አምባሳደር መለሰ አለም ተናገሩ

የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ ዓለም በዛሬው እለት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዋና ዋና የውጭ ዲፕሎማሲ ተግባራት ላይ መግለጫና ማብራሪያ  ሰጥዋል።

በመግለጫው ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የምጽአት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል በሚል የሰጉ ከሴራሬ እና ኩሚ ከሚባሉ ቦታዎች ወደ 100 የሚጠጉ ዜጎች  በድንበር በኩል ወደ ኢትዪጵያ የገቡ መሆኑን ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል።

እነዚሁ ምፅዓት የሰጉ የኡጋንዳ ዜጎች በኛንጋቶም መስፈራቸውን ተናግረዋል።

ከምስራቃዊ ዩጋንዳ ተነስተው በድንበር በኩል ሰላም እና መረጋጋት ለማግኘት ኢትዮጵያ መጥተዋል ዝርዝር ጉዳይ በቀጣይ ይገልፃል ሲሉ ቃል አቀባይ አክለዋል ተናግረዋል። 
👍72
#አዲስ #ዜና
#መረጃ #vatican #VaticanNews

ፖፕ ፍራንሲስ ሆስፒታል ገቡ።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመተንፈሻ አካላት የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ገቡ።

ፖፕ ፍራንሲስ ከመተንፈሻ አካላት ህመም ጋር በተያያዘ ለጥቂት ቀናት ሮም በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉም ቫቲካን አስታውቋል።

የ86 ዓመቱ አባ ፍራንሲስ በቅርብ ቀናት ውስጥ የመተንፈስ ችግር እንደገጠማቸው ነገር ግን በኮቪድ-19 አልተያዙም ሲል መግለጫው አክሏል።

“ለተወሰኑ ቀናት ተገቢ የሆስፒታል ህክምና ያስፈልጋቸዋልም” ብሏል የቫቲካን መግለጫ።

“ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደረሷቸው በርካታ መልዕክቶች ልባቸው የተነካ ሲሆን እየተደረገላቸው ላለው ጸሎትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል” ሲልም አክሏል።

ረቡዕ ጥዋት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሳምንታዊውን የጸሎት ፕሮግራም መርተው የነበረ ሲሆን በወቅቱም በጥሩ መንፈስ ላይ ነበሩ ተብሏል። ነገር ግን ወደ ተሽከርካሪያቸው ሲገቡ በእርዳታ የገቡ ሲሆን ተዳክመው ታይተዋል።

ቫቲካን መጀመሪያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በየጊዜው ለሚያደርጉት ምርመራ ወደ ሆስፒታል ማቅናታቸውን አሳውቆ የነበረ ቢሆንም አባ ፍራንሲስ የቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሰረዛቸውን ተከትሎ የጣሊያን ሚዲያዎች መታመማቸውን ዘግበዋል።

የህመማቸው ዜና ከወጣ በኋላ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አባ ፍራንሲስ እንዲያገግሙ ሕዝቡ በጸሎት እንዲያግዝ ጠይቀዋል።

በአሜሪካ መሪነት ሁለተኛው የሮማ ካቶሊክ እምነት ተከታይ የሆኑት ፕሬዚዳንት ባይደን፣ አባ ፍራንሲስ በዓለም ካሉ ሰዎች “እንደ እየሱስ ክርስቶስ የመሰሉ” ሲሉም ገልጸዋቸዋል።

#BBC News Amharic
3👍2
ታይላንድ 63 ጥገኝነት የሚጠይቁ ቻይናውያን ክርስቲያኖችን አሰረች።

በትላንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋሉት ክርስቲያኖች ቻይና ውስጥ ባለው የሃይማኖት ገደብ ምክንያት በ2019 ቻይናን ለቀው የወጡ እንደሆነም ታውቋል።
4👍4
#አዲስ #መረጃ

የያቤሎ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን #ድንቅ ስራ ስርታለች።

ከደንቬር ቤተክርስቲያን እና ከኒዩወርክ ቤተክርስቲያን ከያቤሎ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉት ለቦረና ሕዝብ የተደረገ በያቤሎ እና በኤልወዬ ወረዳ ድጋፍ ተደርጓል።
👏7👍43
#ዛሬ #እሁድ ነዉ።

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ... 🏠 🚶‍♀️🚶‍♂️🏃‍♀️🏃‍♂️
👍138
#አዲስ
#መረጃ

"አሜሪካ በስደት ውስጥ ከሚገኙ የህንድ ክርስቲያኖች ጋር መቆም አለባት"

ለአለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳም ብራውንባክ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በተለይም ዩኤስ በተለይ በህንድ ስደት ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን መንግስት እንዲጠብቃቸው በመጫን ከጎናቸው እንዲቆም አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

ብራውንባክ ከ2018 እስከ 2021 በዩኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የአለም አቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ቢሮን መርተዋል። ከዚህ በፊት ከ2011 እስከ 2018 ድረስ የካንሳስ 46ኛው ገዥ (ሪፐብሊክ) ሆኖ አገልግሏል።
ብራውንባክ በህንድ ክርስቲያኖች ላይ የማያቋርጥ ስደት የሚያሳዩ አስደንጋጭ ማስረጃዎች ቢኖሩም እነሱን ለመርዳት የተኬደው መንገድ በጣም ትንሽ መሆኑን ይገልጻል።

“በህንድ እና በአብዛኛዎቹ ደቡብ እስያ የሚኖሩ አናሳ ሃይማኖተኞች ስጋት ላይ ናቸው። ቻትስጋርህ ለህንድ ክርስቲያኖች ሁለተኛው በጣም አደገኛ ክልል ሆኖ ተቀምጧል።

የተፈናቀሉ ክርስቲያኖች በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ። የአካባቢ መንግስት ውጤታማ ምላሽ መስጠት አልቻለም።

ዩናይትድ ስቴትስ በሁሉም የደቡብ እስያ መንግስታት ላይ አናሳ ሀይማኖቶች እንዲጠብቁ ጫና ለማድረግ ሁሉንም የዲፕሎማሲ መሳሪያ መጠቀም አለባት ብለዋል።
5🔥1
#አዲስ
#መረጃ
#35_ዓመታት
#የምህረት እና የባርኮት አመታት

የሰሜን አዲስ አበባ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን የ35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሏን በድምቀት አከበረች።

ቤተክርስቲያኗ የተመሰረተችበትን 35ኛ አመት ባከበረችበት ወቅት በቤተክርስቲያኗ መመስረት ወቅት የነበሩ የእምነት አባቶች ያሰለፉትን የህይወት ምስክርነት መከራ እና እንግልት ተወስቷል።

ለአምልኮ መሰብሰብ በማይፈቀድበት በዚያ ወቅት ግለሰቦች ቤታቸውን በመስጠት ባለቸው ነገር ሁሉ ህይወታቸውን ሳይቀር ከፍለው ቤተክርስቲያንዋን እዚህ በማድረሳቸው አድናቆት ተሰጥቷቸዋል፡፡

አሁን ያሉ የቤተክርስቲያኗ አገልጋዮች አጥቢያ ቤተክርስቲያኗ የዛሬ 35 አመት ልትደርስበት የሚገባት የአገልግሎት ጥራት እና ደረጃን የያዘ የጋራ ሰነድ የተዘጋጀ ሲሆን ሰነዱም በጠርሙስ ተደርጎ የመሰረት ድንጋይ ተዘጋጅቶለት የቤተክርስቲያኒቷ አገልጋዮችና ወጣት ታዳጊዎች በተገኙበት የማስቀመጥ በርሀ ግብር ተደርጓል፡፡

ከቤተክርስቲያንዋ አባቶች ጀምሮ እስከ ወጣቶች ድረስ በየዕደሜ ተከተል የመጽሐፍ ቅዱስ ቅብብሎሽ መረሃግብርም ተካሄዷል፡፡

የአጥቢያ ቤተክርስቲያኗ ዋና ሰብሳቢ አቶ ታፈሰ በመልዕክታቸው ትላንትን የረሳ ትውልድ ነገ መድረስ አይችልም ፕሮግራሙም የተዘጋጀበት አላማም ይህንኑ ለማሰብ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዘላለም ደረጄ እና የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ የሆኑት ሻሮን ደምሴ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
3👍3