The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ኬንያ_እየፀለየች_ነው

ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ " የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል " በማለት ከቀናት በፊት በመላው ኬንያ #ጸሎት_እንዲደረግ አውጀዋል።

''ጎረቤት ሀገር ኬንያ በትምህር ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችውን " የተመሳሳይ ጾታ " አጀንዳ ላይ ዘመቻ ጀምራለች።

የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ ፥
ሚንስትሩ በት/ ቤቶች ውስጥ " የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን " ለማስቀረት በኬንያ ኢቫንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።

በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው #መማሪያ እና #አጋዥ_መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህር ሚንስትሩ እየተነገረ ነው።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ‘ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል' ማለታቸዉ ይታወሳል።

ቀዳማዊ እመቤት ሬቸል ሩቶ “አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ” ማለታቸዉን ከሰሞኑ በዜናችን ማስነበባችን ይታወሳል።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት #በኬንያ ሕጋዊ አይደለም።
👍7
#አሁን
#ቀጥታ
#ሚሊኒየም_አዳራሽ

ከ3000 በላይ የቤተ-እምነት መሪዎች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ዓለም አቀፍ አስተማሪዎች እና የወንጌል ሠራተኞች የታደሙበት "የመጋቢያን ኮንፍራንስ" በሚሊኒየም አዳራሽ ተጀምሯል።

“እርቅ፣ መንፈሳዊ ተሃድሶና መነቃቃት ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት” በሚል መሪ ቃል መካሄድ የጀመረው ኮንፍረንስ እስከ አርብ የሚቆይ ይሆናል።

ዝርዝር መረጃዎችን እየተከታተልን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።
6
#ግብረ_ሰዶምን_እንቃወማለን
#ሕብረቱ

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረትና በግሬት ኮሚሽን የተዘጋጀውና ዛሬ የጀመረውና ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቆየውና በሚሊኒየም አዳራሽ እየተደረገ ባለው 'የመሪዎች ስልጠና' ላይ መጋቢ ጻድቁ አብዶ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ የኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ፕሬዚዳንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ ከዚህ በዚህ በኃላ አትኩረን የምንሰራባቸው ያሉትን ጉዳዮች አጽንኦት ሰተው ተናግረዋል።

፨ ግብረ ሰዶምን እንቃወማለን
፨ የትምህርት ስህተቶችን
፨ የልምምድ ችግሮችን
፨ በዘርና በሐይማኖት መሐል የሚደረግን ግጭቶች መሐል ጣልቃ ገብነትን
፨ ያለ አግባብ የሆነ በወንጌላውያን ላይ የሚደረግ ጫና እንቃወማለን ብለዋል።

ምንጭ @Christian ዜማ tube
17
#አዲስ
#ፓስተር_ጻዲቁ ምንድነው_ያሉት?
#አቋም የተያዘባቸው 6 ነጥቦችስ ምን ምን ናቸው?

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረትና በግሬት ኮሚሽን ሚኒስትሪ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ከሶሰት ሺህ በላይ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

#የሕብረቱ ፕሬዝደንት ፓስተር ጻዲቁ አብዱ ዛሬ በነበረው የመክፈቻ መሰናዶ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዋናነት 6 ነጥቦች ላይ ትኩረት እንዲደረግ እና #አቋም እንዲያዝ አጽንዖት እንዲሰጠው አሳስበዋል።

እነዚህ ስድስት ነጥቦች ምን ምን ናቸው?

1. እንደ ወንጌላውያን #ጥላቻን እና ቂም በቀልን ለግጭት የሚዳርጉ ድርጊቶችን እና ሰዎችን ከየትኛውም ወገን ይሁን ለጥላቻ የሚቀሰቅሱ #ለቂም በቀል የሚያነሳሱ ግጭቶች በተለያየ ምክንያት በሰዎች መካከል እንዲነሱ የሚያደርጉ ሰዎችን #እምቢ ማለት እና ልንቃወም ይገባል።

2. በእኛ ወንጌላውያን ስም እይተጠሩ እና #ወንጌላውያን ናቸው ተብሎ እየታሰቡ ነገር ግን ከወንጌላውያን አስተምሮ በእጅጉ የራቁ #የሃሰት #ትምህርት የሚያስተምሩትን ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ያላቸውን ፤ እጅግ የተበላሸ የሞራል #ሕይወት የሚኖሩትን ሰዎች የማንቀበል መሆኑን በይፋ የምንናገርበት እና የምናሳውቅበት ጊዜ ነው።

3. የኢትዮጵያን ሕዝብ #በብሔር እና #በሃይማኖት ለማጋጨት የሚደረገው ሙከራ መቃወም ይገባናል። እምነታቸውም ይሁን ብሔራቸው ከኛ ለተለዩ ሰዎች "ባልንጀራሕን እንደ ራስህ ውደድ" በሚለው መርህ እንዲሁም "ሰዎች እንዲያደርጉላቸሁ የምትወዱትን እናንተም ለሌሎች እንዲሁ አድርጉላቸው። በሚለው ወርቃማ ሕግ እየተመራን ለሰዎች ሁሉ መልካምን እናድርግ። ጥላቻን በፍቅር እናሸንፍ። ለክፉ #መልካም በመመለስ የሚረግሙንን በመመረቅ የጌታችንን ምሳሌ እንከተል።

4. በእምነታችን እና በማንነታችን ምክንያት የሚደረግብንን ማንኛውም #መድሎ እና #ጫና #መቃወም አለብን። ወንጌላውያን ዛሬም በተለያዩ ቦታዎች በተለይም የወንጌላውያን አማኞች ቁጥር በሚያንስባቸው አከባቢዎች እጅግ የከፋ መድሎ እንደሚደረግብን እናውቃለን። ሀገራችን የሁላችንም ሀገር ስለሆነች እንደ ዜጋ ለሃገራችን ሰላም እና ልማት መስራት ይጠበቅብናል። የሌሎች #እምነት ያለ አግባብ #ሲደፈር ዝም አለማለት የራሳችንንም #በሕግ አግባብ ማስጠበቅ ይገባናል።

5. በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የነበረው የእርስ በዕርስ #ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ስለተቋጨ እና #ሕዝቡ እፎይታ ስላገኘ አከባቢውም ከጦርነት ስላረፈ ታላቅ ደስታ ተሰምቶናል። ይህ ሰላም ጸንቶ እንዲቆይ እንዲሁም ግጭት ባለባቸው ሌሎች የሃገራችን ክፍሎች ሰላም እንዲሰፍን እኛ ወንጌላውያን እጅግ አብልጠን ልንጸልይ እና ለሰላም የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል።

6. (አጽንዖት የሚፈልግ #ጉዳይ) #ግብረ_ሰዶም ሰበዓዊም ዲሞክርራሲያዊም መብት አይደለም። #ግብረ_ሰዶም_ሐጢያት_ነው። ግብረ ሰዶም ምንም ከፍቅር ጋር ግንኙነት የለውም። በግብረ ሰዶም ችግር ስለወደቀ ሰው አዝናለሁ። ከዚህ አስከፊ ከሆነ ሐጢያት እንዲወጣ እጸልይለታለሁ። ነገር ግን ሃጢያቱን ልምምዱን የእግዚአብሔር ቃል እጅግ የሚያወግዘው የከፋ #ሐጢያት ስለሆነ #እቃወማለሁ

ዛሬ በሰበዓዊ ስም የዲሞክራሲ መብት ነው ተብሎ ግብረሶዶማዊነትን በተለያየ መንገድ #በአፍሪካ በተለይም ከ97% በላይ ሃይማኖተኛ በሆንን ሀገር ላይ በተለያየ መንገድ ለመጫን አዕምኖዕችን ለዚህ ዝግጁ የሚደረገውን ግፊት በሙሉ እኛ እንደ #ወንጌላውያን አንቀበል። እንቃወመዋለን።

ግብረ ሰዶም በመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ የከፋ ሐጢያት እና የሐጢያት ምሳሌ ነው። ሰዶም እና ጎመራ ተቃጥለው የጠፉት በዚህ ሃጢያት ምክንያት ነው።

እግዚአብሔር ሰዎችን በመልኩ ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው። ጾታዬን ለማወቅ እንድሜዬ 18 መድረስ የለበትም። ስወለድ እና እግዚአብሔር ሲፈጥረኝ ማን እንደሆንኩኝ አውቃለሁ።

ጾታችሁን የምታውቁት ስታድጉ ነው የሚለው አደገኛ አስተምሮ ስለሆነ ዝም ብለን አናልፍም። ግብረ ሰዶም ሰበዓዊነት ሳይሆን ሰበዓዊነትን ወደ አውሬነት የሚለውጥ ስበዓዊነትን የሚያሳንስ ሴጣናዊ የሚያደርግ ሐጢያት ነው።

በየትኛውም #ሐጢያት ላይ ግልጽ #አቋም መውሰድ እንዳለብን ሁሉ በተለይ በግብረሰዶም ላይ አፋችንን ዘግተን የምንቀመጥበት አይደለም። ስለዚህ ለሰዎቹ እናዝናለን ከዚህ ጉድጓድ እና አዝቅት ውስጥ እንዲወጡ በፍቅር እንጸልይላቸዋልን ፤ እናለቅሳለን። ነገር ግን ሐጢያቱ ሐጢያት ነው።

መጋቢ ጻዲቁ አብዶ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዝደንት
👍109
እዋዳን ልራመታ ኢየሱስ አቴቴ
እዎሮር ቆጡኮክ ኬሴኔ ሀንጨቴቴ (2X)

ገለተ ኡዋሙላ ልራንችኔ እሱም ፎቃ
ፎቃ ገትስት ብክናጋለታ ቡቃ ዮኮ ዮኮ

ዮኮ ዮኮ ዮኮ ኢየሱስና
እገለታ ኤጣ እሆና (2X)

ገለታ ዮሞ
ዘማሪ ደግነት አስፈው

https://www.youtube.com/watch?v=xQp0tvY3bOc
🔥1
#ቤተክርስቲያን ተዘረፈች

በፓስተር አማረ ሀጎስ የምትመራው "ግሬስ ላይፍ ኮሚዩኒቱ ቤተክርስቲያን" ተዘረፈች።

ቤተክርስቲያኒቱ ትጠቀምባቸው የነበሩ ከ40 በላይ የመገልገያ ቁሳቁሶች የተዘረፉ ሲሆን በዚህ ዝርፊያ ቀዳሚ ተጠርጣሪ እና የድርጊቱ አስተባባሪ በጥበቃ ስራ ላይ የነበረው ሰው እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህ ዘፊያ ለሚዲያ የሚያገለግሉ ካሜራዎችን ጨምሮ የሙዚቃ መሳሪያዎች ኪቦርድ ፤ ማይክ ፤ ሚክሰር ፤ ጀነሬተር ፤ እስፒከሮች እና ድራም ይገኙበታል።

6.5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ንብረት መዘረፉን የቤተክርስቲያኒቱን መሪዎች ዋቢ አድርጎ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ ዘግቧል።

በዘገባው እንደተመለከትነው ከሆነ የቤተክርስቲያኒቱ ጥበቃ በተቀናጀ ሁኔታ እቃዎቹን ዘርፎ መሰወሩ ተገልጿል።

ዘገባውን በምስል ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=EQLwcb3pwWc

ምንጭ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
👍4
#አስደሳች #ዜና
#ቤተክርስቲያን #ሚሲዮናዊ ላከች።
ከታቦር ተራራ - ጋና አክራ

ሐዋሳ ታቦር መካነ ኢየሱስ ከእናት መካነ ኢየሱስ ወጥታ ማኅበረ ምእመን ከሆነች ገና ሁለት አስርትን እያስቆጠረች ብትሆንም እየሰራችው ያለችው ሥራ ግን የ200 ዓመታት ታሪክ ያላት ነው የሚመስለው።

ወንጌል ለዓለም ሁሉ ለማድረስ በታላቅ ግለትና ቅናት በመንቀሳቀስ በመላው ኢትዮጵያ በሰሜን፣ በደቡብ፣ በምዕራብና በምስራቅ ከ70 በላይ የወንጌል መልእክተኞችን በማሰማራት አርአያ የሆነች ማኅበረ ምእመን ናት።

የአገር ውስጡን እንዲህ እየስራችም ወንጌልን በዓለም ለማድረስ ሃላፊነቱ የኔ ነው በማለት በጥር 7 ቀን 2015 ዓ.ም በጉባኤ ፊት በጸሎት የሸኘችው ሚስዮናዊ ሳሙኤል ሐይሶ ዛሬ ማለዳ ወደ ጋና አክራ አቅንቷል።
👍4🔥3
#አስደሳች #ዜና
ታዳጊ ሊዲያ_እንድትፈታ ተወሰነ

ከሰሞኑ በሃላባ በእስር ላይ የነበረችው ታዳጊ ሊዲያ አበራ ከደቂቃዎች በፊት በዋለው ችሎት በ30ሺህ ብር ዋስ እንድትፈታ ተወስኗል።

ችሎቱ በትላንትና እለት ወደ ዛሬ የዞረ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ፍርድ ቤቱ ጠበቆች ሳይገኙ አላነብም በማለት ወደ ከሰዓት 9:00 ሰዓት ዞሮ የነበረ ሲሆን ምንም እንኳን ጠበቆቹ በስፍራው ባይገኙም ፍርድ ቤቱ ታዳጊዋ በ30ሺህ ብር ዋስ እንድትፈታ ውሳኔ አሳልፏል ሲል Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ ዘግቧል።

ምንም እንኳን ታዳጊዋ በዋስ እንድትፈታ ውሳኔ ቢተላለፍም አሁንም በአከባቢው በክርስቲያኖች ላይ ስጋት እንዳለ አክሎ ዘገባው አስታውሷል።
9👍2
" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " - ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ

የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች በአፍሪካ አገራት ላይ በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

ሙሴቬኒ ይህን ያሉት አገራቸው የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በተመለከተ አዲስ ሕግ እያረቀቀች ባለችበት ወቅት ነው።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ወንጀል በሆነባት ኡጋንዳ እየተረቀቀ ያለው ሕግ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ የበለጠ ጠንካራ ቅጣት የሚጥል ነው።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ትናንት ሐሙስ መጋቢት 07/2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ፓርላማ ቀርበው ይህን ብለዋል ፦

" ምዕራባውያን እንግዳ የሆነ ባህል (የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት) እንድንፈቅድ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ።

ምዕራባውያን የራሳቸውን አሰራር በሌሎች ላይ ለመጫን የሚያባክኑትን ጊዜ ማቆም አለባቸው።

አውሮፓውያኑ የአጎት እና የአክስት ልጅ ጋር ትዳር ይመሰርታሉ እዚህ [ኡጋንዳ] የአንድ ጎሳ አባልን ማግባት ነውር ነው።

እነሱ የቅርብ ዘመድ እንዳያገቡ ማዕቀብ እንጣል ? ይህ የእኛ ሥራ አይደለም። "

ፕሬዜዳንት ሙሴቬኒ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን አፈንጋጭ ብለው የገለጿቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ብዙ ምክክር መደረግ አለበት ብለዋል።

ኡጋንዳ አሁን ላይ እያረቀቀች ባለችው ሕግ መሠረት በተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ውስጥ ያለ ወይም እራሱን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አፍቃሪ ብሎ የሚገልጽ ሰው እስከ 10 ዓመታት የእስር ጊዜን እንዲያሳልፍ ያዛል።

የኡጋንዳ መንግሥት በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የውጭ አገራት መንግሥታት ተቋማት እና ምዕራባውያን ኤጀንሲዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን እያስተዋወቁ ነው በማለት ይከሳል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
9🔥2👍1