ጕዳዩ፦ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የተነገረውን የተሳሳተ አገላለጽ እንዲታረም ስለመጠየቅ
የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በተለያዩ ግለ ሰቦች የተጻፉና ለሕዝብ ይጠቅማሉ የተባሉ መጽሐፎችን በመገምገም ጸሐፊዎችንና አንባቢዎች በጥሩ አመለካከት እንዲታነጹ በማድረግ የተቀደሰ ስራ የሚሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ በርቱ ማለት እንፈልጋለን።
በዚሁ የመጽሐፍ ክበብ በጥር ወር ላይ፣ “የተከዳ እውነት” በሚል በቀረበውና በመጋቢ ስሜ ታደሰ የተጻፈ መጽሐፍ ግምገማ ላይ የተገኙት የመጽሐፉ ጸሐፊ “መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊ ቤተክርስቲያን ነች” በማለት በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይወክላትን የራሳቸውን እይታ የቤተክርስቲያኗ እምነትና ልምምድ አድርገው ተናግረዋል።
የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን እኛ ካልቪን ነን ወይም አርሚን ነን ብላ አስተምራ አታውቅም። ከሁለቱም ጎራ ባትሆንም አመጣጧ ከአናባፕቲስት ስትሆን ሰዎች ለመዳን ክርስቶስ ኢየሱስን ማመን እንዳለባቸው/እንደሚጠበቅባቸው/፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሁሉም ሰው እንጂ ለተወሰኑ ምርጦች ብቻ እንዳልሆነ፣ ሰው የተሰጠውን በወንጌል የማመን ዕድል ሊጠቀም ወይም ላይጠቀም እንደሚችል፣ ሰው የተዘጋጀለትን የዘላለም ክብር ለማግኘት መጽናት እንደሚገባው የእግዚአብሔርም ጸጋ ለዚህ እንደሚረዳው ታምናለች ታስተምራለች።
ስለዚህ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊት ነች የሚለው የተሳሳተ ፍረጃ በቀረበበት የሕንጸት መድረክ ላይ የተሳሳተ ገለጻ እንደሆነ ታውቆ ማስተካከያ እንዲደረግ እየጠየቅን የትምህርትና ስልጠና መምሪያ በቅርበት እንዲከታተል ግልባጭ ተደርጎለታል።

👍4
ኬንያ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ዘመቻ ጀመረች።
ኬንያ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችው የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳ ላይ ዘመቻ ጀመረች።
የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።
ሚንስትሩ በትምህር ቤቶች ውስጥ ‘የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን’ ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።
በኬንያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው መማሪያ እና አጋዥ መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህርት ሚንስትሩ ገልጸዋል።
ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል በማለት በመላው ኬንያ ጸሎት እንዲደረግ ካወጁ ከቀናት በኋላ ነው።
የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ‘ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል' ብለዋል።
“አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ” ብለዋል ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ።
አንዳንድ የተመሳሳይ ጾታ ደጋፊዎች ግን ይህ የመንግሥት እርምጃ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ ተመሳሳይ ጾታ የተሳሳተ ግንዛቤ አንዲሰርጽ ያደርጋል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በኬንያ ሕጋዊ አይደለም። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው ታይተዋል።

👍7👏1
የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘዋል ስለተባሉት ሰዎች የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ ሰጠ።
የዓለም ፍፃሜ ተቃርቧል በሚል ፍራቻ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመንደራቸው ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የኡጋንዳ ፖሊስ ከሰሞኑ አስታውቆ ጉዳዩንም እየመረመረ መሆኑን ገልጾ ነበር።ኡጋንዳዊያኑ "የክርስቶስ ሐዋሪያዎች" የተሰኘ እምነት ተከታዮች የዓለም ፍጻሜ በቅርቡ የሚጀምረው ከአካባቢያቸው መሆኑን በማመን ንብረታቸውን በመሸጥ ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ያሉት ከየካቲት ጀምሮ እንደሆነ የኡጋንዳ ፖሊስ ተናግሯል ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም በሳምንታዊ መግለጫቸው ከሰሞኑ ከ100 በላይ ኡጋንዳዊያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል ፣መድህን የሚገኘውም በኢትዮጵያ ነው በሚል ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ስለተባሉት የሀይማኖት ሰዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ዜናውን እንደሰሙት የተናገሩት አምባሳደር መለስ "በተባለው ልክ ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም፣ ከወትሮው የተለየ ቁጥር ያላቸው ኡጋንዳዊያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም" ብለዋል።

👍2🔥1
#የፓስተሮች ኮንፍረንስ ሊካሔድ ነዉ።
በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አዘጋጅነት ከ3000 በላይ የቤተ ዕምነት መሪዎች የሚሳተፊበት ፓስተርስ ኮንፍረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሔድ ነዉ።
በዚህ የመጋቢያን ኮንፍራንስ ከ3000 በላይ የቤተ-እምነት መሪዎች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ዓለም አቀፍ አስተማሪዎች እና የወንጌል ሠራተኞች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ አገር አቀፍ ኮንፍራንስ፣ “እርቅ፣ መንፈሳዊ ተሃድሶና መነቃቃት ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት” በተሰኘ መሪ አሳብ፣
ሁለንተናዊ ክርስቲያናዊ አመራር፤
የወንጌል መልዕክትና መልዕክተኛው፤
ሰላምና እርቅ፤ ከተማ አቀፍ የወንጌል አገልግሎት፤ የባህላዊ እምነት ተግዳሮትን መመከት፤ የተሰኙ ንዑሳን ርዕሶች ትኩረት የሚደረግባቸው እንደሆነም ታዉቋል።
ጉዳዩን አስመልክቶ የሕብረቱ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የመሪዎቹ ኮንፍረንስ ከመጋቢት 6-8 ቀን /2015 ዓ.ም የሚካሔድ ሲሆን ከ2:30 - 11:00 የመሪዎች ኮንፍረንስ ከ11:30 - 2:00 ሰዓት ልዩ ኮንፍረንስ ለሁሉም ለወንጌል አማኞች በሙሉ የሚከወን ይሆናል።
ሙሉ መግለጫዉን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://youtu.be/vQ80ZKds3_w
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ፣ ከታች 👇 በሚገኙ ስልክ ቁጥሮች በመገልገል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
09-95-99-56-77
09-95-99-56-67
09-95-99-57-06
09-95-99-57-07
09-26-76-82-81
09-11-43-14-43

👍4❤2
#አሳዛኝ #ዜና
መቼም ይሄንን ዜና ስንሰማ ልንደነግጥ እንደሚገባ ግልፅ ነዉ። ምክንያትም በሰዉ እና በእግዚአብሔር ፊት ቃልኪዳን ተገባብተዉ መልሰዉ ሲለያዩ የሚፈጠረዉ ... የአደባባይ ሚስጥር ነዉ።
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ የተመዘገበው የፍቺ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ተቀራራቢ ሲሆን፤ በ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 623 የፍቺ ምዝገባዎች መደረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በአዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 16 ሺህ 35 ፍቺዎች እንደተካሄዱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።
ትዳር በበርካታ ምክንያቶች ሊፈርስ እንደሚችል ጥናቶች የሚያመለክቱ ሲሆን ለአብነትም የኢኮኖሚ ድቀት፣ ቅናት እና አለመተማመን ወዘተ ይጠቀሳሉ።
እንግዲህ #የቤተክርስቲያን እና የመሪዎች የቤት ስራ ጨምሯል።

#ፍትህ
#የሀላባዋ_ታዳጊ_ሊዲያ_ጉዳይ
#ኢየሱስ
በቀን 22/06/2015 እንደማንኛውም ጊዜ ሊዲያ ት/ቤት ለመማር ክፍሏ ተገኝታለች።አንዲት ሙስሊም ተማሪ በክፍሏ ትወድቃለች። ወድቃም ኢየሱስ ጌታ ነው ትላለች።
ይኼኔ ነው ተማሪዋን ከነለበሰችው ዩኒፎርም ያለ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት መጥሪያ አፋፍሶ ወደ ሀላባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዷታል፤''ልጄን'' እያለ ሊጠይቃት የሄደውን አባቷንም ያስሩታል።ከዛ አባቷን ይፈቱታል።
ከተያዘችበት 5 ቀን በኋላ በ5ኛው ቀን 27/06/2015 ፍ/ቤት ያቀርቧታል፣"ድግምት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በመስራት ወንጀል ጠርጥረናታል የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን" በማለታቸው 11 ቀን ተፈቅዶላቸው የ14 ዓመት ታዳጊዋን ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ሃላባ ማረሚያ ተቋም ውስዷት እየማቀቀች ትገኛለች።
በምርመራ ወቅት በንቅሳት ድግምት አሰርተሻል በሚል እርቃኗን አስቀርቶ እንደፈተሿት እና ሊነገር የማይችል የመብት እና የስነልቦና ጥቃት እንደደረሰባት ሊዲያ ትናግራለች።
#ወንጌል ወንጀል አይደለም!!!
#ፍትህ_ለሊዲያ
በታዳጊዋ ዙሪያ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ እና ሌሎች ማሕበራዊ ሚዲያዎች ለምታደርጉት ጥረት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነዉ።
#share #ShareThisPost

🔥12❤2👍1
#ወደ_ጌታ_እቅፍ_ተሰበሰበ
ተወዳጁ #ዘማሪ ወደ ቤተ ክርስቲያን ዝግጅት ሲያመራ በድንገተኛ አደጋ #ህይወቱ አለፈ።
ዘማሪ ፊሌ ኤልያስ ለአገልግሎት ተጋብዞ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ዛሬ ማለዳ ከማርሳቢት-ሞያሌ አውራ ጎዳና ላይ ከጠዋቱ 4 ሰአት በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።
የተወዳጁ ዘማሪ ቤተሰቦች እና ወጃጆቹ ሞቱን መቀበል ቢያቅታቸዉም "በአምልኮህ እና በምስጋና መዝሙሮችህ በሰዎች ህይወት ላይ ተፅእኖ በመፍጠር እንደዚህ አይነት መልካም ህይወት ኖረክ ትልቅ ውርስ ትተሃል። በማለት ገልፀዉታል።
ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
የዮሐንስ ወንጌል 11 : 25
እንደሚል The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ መፅናናትን ይመኛል።

❤1
#እግዚአብሔር ይመስገን ቦረና ዝናብ ጥሎዋል 🙏
በቦረና ዝናብ ያዘነበ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ክብር ለንጉሱ❗️Yeesoon Gooftaa❗️
አሁንም ፀሎቱ እና ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥል።

🥰5
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ኪሪል ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ባላት ቤተክርስቲያን ላይ የምትፈጥረውን ተጽእኖ እንድታቆም ጠየቁ፡፡
የኬቭ መንግስት የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከተመሰረተችበትና ረዥም ዘመናት ካስቆጠረው ገዳም ለቃ እንድትወጣ ያዘዘው አርብ እለት እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚህም ከጥቅምት ወር ጀምሮ የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት በዩክሬን አብያተ ክርስቲያናት ላይ በየጊዜው ፍተሻ ሲያደርግ መቆየቱ፣ በጳጳሳቱ እና የገንዘብ ድጋፍ በሚያደርጉ ላይ ማዕቀብ መጣሉ እንዲሁም በደርዘን በሚቆጠሩ ቀሳውስት ላይ የወንጀል ክስ መክፈቱን ነው ሬውተርስ የዘገበው።
የዩክሬን ባህል ሚኒስቴር ፤ የዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እስከ መጋቢት 29 ባለው ጊዜ ውስጥ 980 አመታት ካስቆጠረው የኪቭ-ፔቸርስክ ላቭራ ገዳም ግቢ መልቀቅ አለባት ሲል አሳስቧል፡፡
የሩሲያው ፓትሪያርክ የዩክሬን መንግስት ውሳኔን ተቃውሞውታል፡፡
ኪሪል የዩክሬን ምዕመናን መብት እና ነጻነት በገሃድ እየተጣሰ መሆኑ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።
ፓትሪያርኩ የተወሰደሰውን እርምጃ በመቃውም የካቶሊኩ አባ ፍራንሲስን እና ሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ዩክሬን ከድርጊቷ እንድትቆጠብ እንዲያሳምኑ ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
“ገዳሙን በኃይል መዝጋት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩክሬን አማኞች መብት መጣስ ነው” ያሉት ፓትሪያርኩ፤ የሃይማኖት መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ድርጊቱን ለማስቆም የተቻላቸውን እንዲደርጉ ማሳሰባቸውም በቤተክርስቲያኗ ድረ ገፅ ላይ የወጣው መግለጫ አትቷል።
ቤተክርስቲያኗ ከሞስኮ ፓትርያርክ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ ማለቷም አይዘነጋም።

በፓስተሮቻቸው #ጸሎት ተአምራትን ለማግኘት #ዕዳ ውስጥ የሚዘፈቁ ምዕመናን።
“ከሐሰተኛ #ነብያት ተጠንቀቁ” እንደሚለው መጽሃፉ፣ በኬንያ በርካቶች ፓስተሮች እንዲጸልዩላቸው ለመጠየቅ ዕዳ ውስጥ መዘፈቃቸው ተነግሯል።
ኤቫርሊን ኦኬሎ አንድ ፓስተር እንዲጸልይላት ለመክፈል ዕዳ ውስጥ ገብታለች።
በመቶዎች የሚቆጠር ዶላር ዕዳ እንዳለባት ስትናገር እያነባች ነው።
ነዋሪነቷ በኬንያዋ መዲና ናይሮቢ፣ ዋነኛው የድሆች መኖሪያ መንደር ኪቤራ ነው።
ኤቫርሊን በአሁኑ ወቅት አራት ልጆቿን መመገብ ተስኗታል።
ለወራት ያህል ምንም ገንዘብ እንደሌላት ለቢቢሲ ተናግራለች።
በአንድ ወቅት ነው ጸሎቱ ሕይወት ስለሚያሻሽለው ፓስተር የሰማችው።
አገኘችው፣ ፓስተሩም 15 ሺህ የኬንያ ሽልንግ (115 ዶላር) እንድታመጣ ጠየቃት።
ይህ የገንዘብ ስጦታ “የዘር መስዋዕት” በመባል ይታወቃል።
ተዓምር ለሚያደርጉ የሃይማኖት መሪዎች የሚበረከት የገንዘብ መዋጮ ነው።
ኤቫርሊን ገንዘቡን ከጓደኛዋ ተበደረች።
ጓደኛዋም ለእሷ ስትል ብድር ወስዳ ነው የሰጠቻት።
የዚህ ፓስተር ጸሎት በጣም ኃይለኛም ስለሆነ በሳምንት ውስጥ ገንዘቧ እንደሚመለስም ተነግሯታል።
የተባለው ተአምር አልደረሰም። እንዲያውም ይባስ ብሎ ጓደኛዋ የተበደረችውን ገንዘብ በጊዜ ባለመክፈሏ ወለዱ ጨመረ።
በአሁኑ ወቅት ኤቫርሊን ከ300 ዶላር በላይ ብድር አለባት። እንዴት እንደምትከፍለው ግን አታውቅም።
ጓደኛዋም አታናግራትም፤ ሥራም የላትም።
“በጣም ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ስለሆንኩ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጫለሁ” ትላለች።
ለማንኛውም ይህ ዘገባ BBC News Amharic ነው ሙሉውን ገብታችሁ አንብቡት። https://www.bbc.com/amharic/articles/c89e7dv8zvvo

BBC News አማርኛ
በፓስተሮቻቸው ጸሎት ተአምራትን ለማግኘት ዕዳ ውስጥ የሚዘፈቁ ምዕመናን
በርካታ ምዕመናን ላሉባቸው የተለያዩ ችግሮች ተአምራዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት ፊታቸውን ወደ ዕምነት ቤቶቻቸው ያዞላራሉ። በተለይ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስ ባጋጠመበት በዚህ ዘመን በርካቶች ከችግር ለመውጣት አማራጮችን ይፈልጋሉ። በዚህም ሳቢያ ሥራ ለማግኘት እና ኑሮን ለማሻሻል የሚያስችሉ ተአምራቶችን ለማግኘት የገንዘብ ስጦታ ለማበርከት ሲሉ በርካቶች ለዕዳ እየተዳረጉ ነው።