The Christian News
5.08K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ምንድነው እየሆነ ያለው?

በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #asbury ዮንቨርስቲ ምን እየሆነ እንዳለ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

በከተማዋ ከሚገኙት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በዚህ ድንቅ ሪቫይቫል ውስጥ እየተካፈሉ ነው። ለ40 ደቂቃ ወደ ጸሎት የገቡት ወጣቶች ዛሬ ቀናትን ተሻግረዋል።

#አምልኮ ለአፍታ ሳይቋረጥ ሳምንት ተሻግሯል። ብዙዎች ከተለያዩ ከተሞች ወደስፍራው እየጎረፉ ነው። እውነት ነው በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት አስበሪ ዮንቨርስቲ ታላቅ #ሪቫይቫል ተነስቷል።

እንደሚል በኬንታኪ ስቴት በሚገኘው ዩኒቨርሲት ተማሪዎች በየሴሚስቴሩ በግቢው ውስጥ በሚገኘው የማመለኪያ አዳራሽ ለጸሎት የተወሰኑ ቀናት መገኘት ይኖርባቸዋል።

ባሳለፍነው ረቡዕ ላይ ለአምልኮ በተሰበሰቡበት ኳየሮች አምልኮ መምራት ይጀምራሉ። ይሁንና ጥቂት ደቂቃዎች እንደሚፈጅ የተጠበቀው አምልኮ ሳይቋረጥ ለሰዓታት ይቀጥላል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ይህንን የሰሙ ወገኖች ከየስቴቱ በስፍራው ይሰበሰባሉ ዛሬ ሳምንቱን ተሻግሯል።

በአንድ ወቅት ወንድማችን ተስፋዬ ሮበሌ ሪቫይቫል ምንድን ነው? ሲል ካሰፈራቸው ነጥቦች ሶስቱን እናስነብባችሁ።

1. "የሪቫይቫል" ቀዳማይ ግብ የሕይወት ለውጥና የነፍሳት ድነት እንጂ፣ ልሳንና ተኣምር አይደለም!

2. የጸጋ ስጦታዎችም ቀዳማይ ግብ፣ እውነተኛ የሕይወት ተሐድሶና የሰዎች ድነት (ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸውና ጌታቸው መቀበላቸው) ነው!

3. "ሪቫይቫል" ነገን እውን ይሆናል ብለን የምንጠብቀው ክሥተት ሳይሆን፣ ዛሬን የምንተገብረውና የምንኖረው ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው! እውነተኛ የሕይወት ለውጥና የነፍሳት ድነት ባለበት ቦታ ሁሉ "ሪቫይቫል" አለ:: ይህ በሌለበትም ቦታ "ሪቫይቫል" የለም!

ሲል አስፍሮ ነበር። ሪቫይቫል ምንድነው በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን።
1
#በሊቢያ ስድስት የግብፅ #ክርስቲያኖች ታፍነው ተወሰዱ።

ስድስቱ ሰዎች ለስራ ወደ ሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ተጉዘዋል እንደነበር ምንጮች ተናግረዋል። ነገር ግን ከኤርፖርት ወደ ስራ ቦታቸው ሲጓዙ በህገ ወጥ ኬላ ላይ መቆማቸው ታውቋል። ሊቢያዊው ሾፌራቸው ወዲያው የተፈታ ሲሆን ነገር ግን ክርስቲያኖቹ ወዳልታወቀ ቦታ ተዛውረዋል ሲሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ምንጮች ተናግረዋል።

ድርጊቱን በቅርበት የተከታተለው ግብፃዊው ጋዜጠኛ ናደር ሹክሪ፣ ታጋቾቹ በአንድ ምርኮ 15,000 የሊቢያ ዲናር (3,100 ዶላር) ክፍያ እንደሚፈልጉ ሰምቻለው ሲል ጽፏል።

ናድር ሹክሪ ቤተሰቦቻቸው ቤታቸውን ሳይሸጡ እነዚህን ክፍያዎች መክፈል እንደማይችሉ ተናግራለች። የግብፅ ፕሬዝዳንት እና መንግስት ጣልቃ እንዲገቡ አሳስበዋል።

አክሎም በየቀኑ ድብደባ እንደሚደርስባቸው እና በጣም ትንሽ ምግብ እንደሚያገኙም ተናግሯል።
ለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጸሎት ከተፈቀደ በኋላ የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን መሪ ተወገዙ።

የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን ለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ጸሎት እንዲደረግ ድጋፍ ከሰጠች በኋላ ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ የአንግሊካን መሪዎች የቤተ ክርስቲያኗ መሪ ጀስቲን ዌልቢ መሪያችን አይደሉም አሉ።

በመላው ዓለም የሚገኙት እና 42 አባላት ካሉት የአንግሊካን ኅብረት አባላት መካከል አሥሩን የሚወክሉት ሊቀ ጳጳሳት፤ ጀስቲን ዌልቢ ከአሁን በኋላ “የዓለም አቀፉ ኅብረት መሪ” አድርገን አንመለከታቸውም ብለዋል።

ሊቀ ጳጳሳቱ ጨምረውም የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን “እናት ቤተ-ክርስቲያን” ከመሆን “ውድቅ” ተደርጋለች ብለዋል።

42 አንግሊካን አብያተ ክርስቲያናትን ያቀፈው ዓለም አቀፉ የአንግሊካን ኅብረት እአአ 1867 በእንግሊዝ አገር ከተመሠረተ ጀምሮ የካንተበሪ ሊቀ ጳጳሳት የኅብረቱ መንፈሳዊ መሪ ኃላፊነትን ሲወስዱ ቆይተዋል።

ይህንን ሃሳብ የተቃወሙት 10 ሊቃነ ጳጳሳት እና በአሜሪካ እና ብራዚል የሚገኙ ሁለት ተገንጣይ አብያተ ክርስቲያናት የደቡብ ሱዳን፣ የቺሊ፣ የኢንዲያን ኦሽን፣ የኮንጎ፣ የሚያንማር፣ የባንግላዴሽ፣ የኡጋንዳ፣ የሱዳን፣ የአሌክሳንደሪያ እና የሜላኔሲያ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። እነዚህ አብያተ ክርስቲያናት በተለይ በእሲያ እና በአፍሪካ ብዙ ተከታዮች ያሏቸው ናቸው።

ተቃውሟቸውን ያሰሙት ሊቃነ ጳጳሳት ባወጡት መግለጫ ላይ የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን በጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ጸንተው ከሚገኙት የኅብረቱ አባላት ለመለየት ወስናለች ብለዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም ቤተ-ክርስቲያኗ በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ላይ ያላት አቋም አልተቀየረም እንዲሁም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ማድረግ አልተፈቀደም።
👍3
ጕዳዩ፦ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን የተነገረውን የተሳሳተ አገላለጽ እንዲታረም ስለመጠየቅ

የሕንጸት የመጽሐፍ ክበብ በተለያዩ ግለ ሰቦች የተጻፉና ለሕዝብ ይጠቅማሉ የተባሉ መጽሐፎችን በመገምገም ጸሐፊዎችንና አንባቢዎች በጥሩ አመለካከት እንዲታነጹ በማድረግ የተቀደሰ ስራ የሚሰራ እንደሆነ ይታወቃል። ለዚህ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ በርቱ ማለት እንፈልጋለን።

በዚሁ የመጽሐፍ ክበብ በጥር ወር ላይ፣ “የተከዳ እውነት” በሚል በቀረበውና በመጋቢ ስሜ ታደሰ የተጻፈ መጽሐፍ ግምገማ ላይ የተገኙት የመጽሐፉ ጸሐፊ “መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊ ቤተክርስቲያን ነች” በማለት በምንም ዓይነት ሁኔታ የማይወክላትን የራሳቸውን እይታ የቤተክርስቲያኗ እምነትና ልምምድ አድርገው ተናግረዋል።

የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አንድም ቀን እኛ ካልቪን ነን ወይም አርሚን ነን ብላ አስተምራ አታውቅም። ከሁለቱም ጎራ ባትሆንም አመጣጧ ከአናባፕቲስት ስትሆን ሰዎች ለመዳን ክርስቶስ ኢየሱስን ማመን እንዳለባቸው/እንደሚጠበቅባቸው/፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለሁሉም ሰው እንጂ ለተወሰኑ ምርጦች ብቻ እንዳልሆነ፣ ሰው የተሰጠውን በወንጌል የማመን ዕድል ሊጠቀም ወይም ላይጠቀም እንደሚችል፣ ሰው የተዘጋጀለትን የዘላለም ክብር ለማግኘት መጽናት እንደሚገባው የእግዚአብሔርም ጸጋ ለዚህ እንደሚረዳው ታምናለች ታስተምራለች።

ስለዚህ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ካልቪናዊት ነች የሚለው የተሳሳተ ፍረጃ በቀረበበት የሕንጸት መድረክ ላይ የተሳሳተ ገለጻ እንደሆነ ታውቆ ማስተካከያ እንዲደረግ እየጠየቅን የትምህርትና ስልጠና መምሪያ በቅርበት እንዲከታተል ግልባጭ ተደርጎለታል።
👍4
ኬንያ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ዘመቻ ጀመረች።

ኬንያ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተንሰራፍቷል ያለችው የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳ ላይ ዘመቻ ጀመረች።

የኬንያ የትምህርት ሚንስትር ኢዚኬል ማቾጉ በኬንያ ትምህር ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች አጀንዳ ሰርጎ ገብቷል ሲሉ ለአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።

ሚንስትሩ በትምህር ቤቶች ውስጥ ‘የተመሳሳይ ጾታ አጀንዳን’ ለማስቀረት በኬንያ አንጀሊካን ቤተ-ክርስቲያን የሚመሩ ጉዳዩን የሚከታተሉ ሰዎች ይሾማሉ ብለዋል።

በኬንያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚከታተል ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው መማሪያ እና አጋዥ መጽሐፍትን መከለሰን ሊያካትት እንደሚችል ትምህርት ሚንስትሩ ገልጸዋል።

ይህ የኬንያ ትምህርት ሚንስቴር እቅድ የተሰማው ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት አደጋ ፈጥሯል በማለት በመላው ኬንያ ጸሎት እንዲደረግ ካወጁ ከቀናት በኋላ ነው።

የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ‘ቤተሰብ በሚባለው ተቋም ላይ አደጋ ደቅኗል' ብለዋል።

“አባት፣ እናት እና ልጆች ያሉበትን የቤተሰብ ተቋም ማጠናከር እንፈልጋለን። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በመጽሐፍ ቅዱስም ሆነ በአፍሪካውያን ዘንድ ተቀባይነት የለውም። የቤተሰብ እሴቶችን እንጠብቅ” ብለዋል ቀዳማዊት እመቤት ሬቸል ሩቶ።

አንዳንድ የተመሳሳይ ጾታ ደጋፊዎች ግን ይህ የመንግሥት እርምጃ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለ ተመሳሳይ ጾታ የተሳሳተ ግንዛቤ አንዲሰርጽ ያደርጋል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በኬንያ ሕጋዊ አይደለም። የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ አመለካከቶች ባለፉት ቀናት ጠንከር ብለው ታይተዋል።
👍7👏1
የዓለም ፍጻሜ ደርሷል በሚል ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘዋል ስለተባሉት ሰዎች የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መልስ ሰጠ።
የዓለም ፍፃሜ ተቃርቧል በሚል ፍራቻ በኡጋንዳ ምስራቃዊ ክፍል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመንደራቸው ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን የኡጋንዳ ፖሊስ ከሰሞኑ አስታውቆ ጉዳዩንም እየመረመረ መሆኑን ገልጾ ነበር።ኡጋንዳዊያኑ "የክርስቶስ ሐዋሪያዎች" የተሰኘ  እምነት ተከታዮች የዓለም ፍጻሜ በቅርቡ የሚጀምረው ከአካባቢያቸው መሆኑን በማመን ንብረታቸውን በመሸጥ ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ያሉት ከየካቲት ጀምሮ እንደሆነ የኡጋንዳ ፖሊስ ተናግሯል ተብሏል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አምባሳደር መለስ አለም በሳምንታዊ መግለጫቸው ከሰሞኑ ከ100 በላይ ኡጋንዳዊያን የዓለም ፍጻሜ ደርሷል ፣መድህን የሚገኘውም በኢትዮጵያ ነው በሚል ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ስለተባሉት የሀይማኖት ሰዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
ዜናውን እንደሰሙት የተናገሩት አምባሳደር መለስ "በተባለው ልክ ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም፣ ከወትሮው የተለየ ቁጥር ያላቸው ኡጋንዳዊያን ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውን የሚያሳይ ነገር የለም" ብለዋል።
👍2🔥1
#የፓስተሮች ኮንፍረንስ ሊካሔድ ነዉ።

በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት አዘጋጅነት ከ3000 በላይ የቤተ ዕምነት መሪዎች የሚሳተፊበት ፓስተርስ ኮንፍረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ሊካሔድ ነዉ።

በዚህ የመጋቢያን ኮንፍራንስ ከ3000 በላይ የቤተ-እምነት መሪዎች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ዓለም አቀፍ አስተማሪዎች እና የወንጌል ሠራተኞች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሚሊኒየም አዳራሽ በሚካሄደው በዚህ አገር አቀፍ ኮንፍራንስ፣ “እርቅ፣ መንፈሳዊ ተሃድሶና መነቃቃት ለኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት” በተሰኘ መሪ አሳብ፣
ሁለንተናዊ ክርስቲያናዊ አመራር፤
የወንጌል መልዕክትና መልዕክተኛው፤
ሰላምና እርቅ፤ ከተማ አቀፍ የወንጌል አገልግሎት፤ የባህላዊ እምነት ተግዳሮትን መመከት፤ የተሰኙ ንዑሳን ርዕሶች ትኩረት የሚደረግባቸው እንደሆነም ታዉቋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የሕብረቱ ፕሬዝዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የመሪዎቹ ኮንፍረንስ ከመጋቢት 6-8 ቀን /2015 ዓ.ም የሚካሔድ ሲሆን ከ2:30 - 11:00 የመሪዎች ኮንፍረንስ ከ11:30 - 2:00 ሰዓት ልዩ ኮንፍረንስ ለሁሉም ለወንጌል አማኞች በሙሉ የሚከወን ይሆናል።

ሙሉ መግለጫዉን ለመመልከት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://youtu.be/vQ80ZKds3_w

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለግዎ፣ ከታች 👇 በሚገኙ ስልክ ቁጥሮች በመገልገል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

09-95-99-56-77
09-95-99-56-67
09-95-99-57-06

09-95-99-57-07
09-26-76-82-81
09-11-43-14-43
👍42
#አሳዛኝ #ዜና

መቼም ይሄንን ዜና ስንሰማ ልንደነግጥ እንደሚገባ ግልፅ ነዉ። ምክንያትም በሰዉ እና በእግዚአብሔር ፊት ቃልኪዳን ተገባብተዉ መልሰዉ ሲለያዩ የሚፈጠረዉ ... የአደባባይ ሚስጥር ነዉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 6 ወራት 1ሺህ342 ፍቺዎች እና 14ሺህ 136 ጋብቻዎች መመዝገባቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ዘንድሮ በ6 ወራት ብቻ የተመዘገበው የፍቺ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ተቀራራቢ ሲሆን፤ በ2014 በጀት ዓመት 1 ሺህ 623 የፍቺ ምዝገባዎች መደረጋቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።

በአዲስ አበባ ከ2012 እስከ 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ 16 ሺህ 35 ፍቺዎች እንደተካሄዱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል።

ትዳር በበርካታ ምክንያቶች ሊፈርስ እንደሚችል ጥናቶች የሚያመለክቱ ሲሆን ለአብነትም የኢኮኖሚ ድቀት፣ ቅናት እና አለመተማመን ወዘተ ይጠቀሳሉ።

እንግዲህ #የቤተክርስቲያን እና የመሪዎች የቤት ስራ ጨምሯል።
#ፍትህ
#የሀላባዋ_ታዳጊ_ሊዲያ_ጉዳይ
#ኢየሱስ

በቀን 22/06/2015 እንደማንኛውም ጊዜ ሊዲያ ት/ቤት ለመማር ክፍሏ ተገኝታለች።አንዲት ሙስሊም ተማሪ በክፍሏ ትወድቃለች። ወድቃም ኢየሱስ ጌታ ነው ትላለች።

ይኼኔ ነው ተማሪዋን ከነለበሰችው ዩኒፎርም ያለ ፖሊስ እና ፍርድ ቤት መጥሪያ አፋፍሶ ወደ ሀላባ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ይወስዷታል፤''ልጄን'' እያለ ሊጠይቃት የሄደውን አባቷንም ያስሩታል።ከዛ አባቷን ይፈቱታል።

ከተያዘችበት 5 ቀን በኋላ በ5ኛው ቀን 27/06/2015 ፍ/ቤት ያቀርቧታል፣"ድግምት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ በመስራት ወንጀል ጠርጥረናታል የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን" በማለታቸው 11 ቀን ተፈቅዶላቸው የ14 ዓመት ታዳጊዋን ከፖሊስ ጣቢያ ወደ ሃላባ ማረሚያ ተቋም ውስዷት እየማቀቀች ትገኛለች።

በምርመራ ወቅት በንቅሳት ድግምት አሰርተሻል በሚል እርቃኗን አስቀርቶ እንደፈተሿት እና ሊነገር የማይችል የመብት እና የስነልቦና ጥቃት እንደደረሰባት ሊዲያ ትናግራለች።

#ወንጌል ወንጀል አይደለም!!!
#ፍትህ_ለሊዲያ

በታዳጊዋ ዙሪያ Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ እና ሌሎች ማሕበራዊ ሚዲያዎች ለምታደርጉት ጥረት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነዉ።

#share #ShareThisPost
🔥122👍1
#ወደ_ጌታ_እቅፍ_ተሰበሰበ

ተወዳጁ #ዘማሪ ወደ ቤተ ክርስቲያን ዝግጅት ሲያመራ በድንገተኛ አደጋ #ህይወቱ አለፈ።

ዘማሪ ፊሌ ኤልያስ ለአገልግሎት ተጋብዞ እየተጓዘ በነበረበት ወቅት ዛሬ ማለዳ ከማርሳቢት-ሞያሌ አውራ ጎዳና ላይ ከጠዋቱ 4 ሰአት በደረሰበት የመኪና አደጋ ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

የተወዳጁ ዘማሪ ቤተሰቦች እና ወጃጆቹ ሞቱን መቀበል ቢያቅታቸዉም "በአምልኮህ እና በምስጋና መዝሙሮችህ በሰዎች ህይወት ላይ ተፅእኖ በመፍጠር እንደዚህ አይነት መልካም ህይወት ኖረክ ትልቅ ውርስ ትተሃል። በማለት ገልፀዉታል።

ኢየሱስም። ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤
የዮሐንስ ወንጌል 11 : 25

እንደሚል The Christian News - የክርስቲያን ዜና ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ መፅናናትን ይመኛል።
1