The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#እናመሰግናለን

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በYoutube ቻናል 40,000 ቤተስቦች ደርሰናል ታማኝ #የክርስቲያን መረጃዎች ምንጭ አድርጋችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።

በቀጣይ እጅግ በርካታ ስራዎች በጋራ እንደምንሰራ በማመን አሁንም አብሮነታችሁ ይቀጥል እንላለን። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰቦቻችን ቁጥር #50ሺህ ደርሶ ለምስጋና በድጋሜ እንደምንገናኝ እናምናለን።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A
#ልጃቸውን አየር ማረፊያ ውስጥ ጥለው የሄዱት ጥንዶች

ልጅን ያለ ትኬት በረራ ማድረግ እንደማይችል የተነገራቸው ጥንዶች በእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ የመግቢያ መሥሪያ ቤት ሕፃኑን ጥለው መሄዳቸው ተሰምቷል።

ወላጆቹ ከ እስራኤል ቴል አቪቭ ወደ ቤልጂየም ብራስልስ እየተጓዙ ነበር በረራቸውን ለማየት ማክሰኞ ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ደረሱ

የእስራኤሉ አየር ማረፊያ ባለስልጣን ለሲኤንኤን በሰጠው መግለጫ ቤተሰቦቹ ለበረራ ዘግይተው ተርሚናል 1 መድረሳቸውን እና ወላጆች ልጃቸው የበረራ ትኬት እንደሌላቸው ሲረዱ መግቢያው ተዘግቷል ብሏል።

የእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ ባለስልጣን "ጥንዶች የጨቅላ መቀመጫውን ከልጁ ጋር ትተው እና ተርሚናል 1 ላይ ወደሚገኘው የደህንነት ፍተሻ ሮጡ" ሲል የእስራኤል አየር ማረፊያ ባለስልጣን ተናግሯል።

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ራያኔር ሁኔታው ለአካባቢው ፖሊስ መተላለፉን ለ CNN ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ፖሊስ በደረሰበት ጊዜ ጉዳዩ እልባት አግኝቶ ህፃኑ ከወላጆቹ ጋር እንደነበረ እና ምንም ተጨማሪ ምርመራ እንደማይደረግ ተናግረዋል ።

እንደ Ryanair ድረ-ገጽ ከሆነ "በኦንላይን ቦታ ማስያዝ ሂደት ውስጥ ህፃናት በበረራ ቦታ ማስያዝ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ" በድረ-ገጹ ላይ ለአንድ ህፃን በአዋቂዎች ጭን ላይ ለመቀመጥ የእያንዳንዱ የአንድ መንገድ በረራ ዋጋ 25 ዩሮ (27 ዶላር) እንደሆነ ይገልጻል።
#አስቸኳይ
#ሕብረቱ #አስቸኳይ መግለጫ እየሰጠ ነዉ።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ መግለጫ እየሰጠ ነዉ።

#ሕብረቱ በመግለጫዉ በሃገራችን በተለያዩ ጊዜያት ለፈሰሰው ደም ንሰሃ ልንገባ ይገባል ብሏል።

#በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረዉን ጉዳይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ወንጌላዊያን በፀሎት እንዲቆዩ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

ሙሉ መግለጫውን ከደቂቃዎች በኋላ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://youtu.be/Jh06dRDzYRc
#ህብረቱ አስቸኳይ መግለጫ ሰጠ #በአስቸኳይ ጾም ጽሎት ይጀምር # እርስ በራሳችን እንታረቅ #በአሁኑ ሰዓት አስቸኳይ ጾም ጽሎት ታውጇል።

https://youtu.be/TnuNfE_4cjY
#አስቸኳይ ጾም ጽሎት ታውጇል።
#ህብረቱሕብረቱ አስቸኳይ ጾም እና ጸሎት አውጇል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት
መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ገነት ቤተርስቲያን
የኢትዮጵያ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በጋራ በመሆን አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ለሁሉም ወንጌላውያን አማኞች አውጀዋል።

የጾም እና ጸሎት መረሃ ግብሩ ከየካቲት 9-12/2015 ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ታውቋል።

ሙሉ የመግለጫውን ሃሳብ The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ስለተከታተልነው እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል።

"እግዚአብሔር ሆይ ተስፋ ባደረግንህ በእኛ ላይ ምህረትህ ትሁን"
መዝ 33:22

እኛ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮ አደጋና በሰው ሰራሽ ጦርነት ምክንያት ተክለን ነቅለናል ፣ ገንብተን አፍርሰናል ከሁሉ በላይ ደግሞ በማንነትና በሀሳብ ልዩነቶች ምክንያት ምትክ የማይገኝለትን የሰው ልጅ ህይወት ፣ በየትውልዱ እየተገበረ እዚህ ደርሰናል።

በዚህ ምክንያት ፣ አለመተማመንና አለመደማመጥ ስር ከመስደዱ የተነሳ ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት አስቸጋሪ ሆኖብናል።

በሌላ በኩል በሀገራችን ለተከሰቱት በደሎች ተጠያቂና ጥፋተኛ በመፈለግ እራሳችንን ከችግሩ ነፃ ለማድረግ ስንጥር እንታያለን። ነገር ግን እውነታው ሲፈተሽ በማድረግ ወይም ባለማድረግ ፣ በመናገር ወይም ባለመናገር ፣ በመሆን ወይንም ባለመሆን ሁላችንም በድለናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎን ተገኝተናል።

ስለሆነም ከካቲት 9-12/2015 ዓ.ም በንስሃና ምልጃ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሃገራችንና ለህዝባችን ምህረትን ለመለመን በአገር ውስጥና በመላው አለም የምንገኝ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት አባላት እንዲሁም እዚህ የተገኙት አራቱ ቤተዕምነቶች በጋራ የነገሩ ክብደት አሳስቦን ይህንን ጥሪ አስተላልፈናል።

ህብረቱ በመግለጫው ይህ ሀገር አቀፍ የምልጃ እና የንሰሃ የጸሎት ጥሪ 3 የፀሎት አርዕስቶችን የያዘ እንደሆነም ጠቅሷል።

1. ስለ ፈሰሰው የንጹሃን ደም የእግዚአብሔርን ምህረትን መለመን

2. በጭንቀት ላይ ላሉ አረጋውያን፣ ወላጅ አጥ የሆኑ ህጻናትን፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር በቃችሁ ብሎ እንዲያሳርፋቸው ምህረትን መለመን።

3. ለሃይማኖት እና ለሃገር መሪዎች ጥበብና ማስተዋል እንዲሰጣቸውና ፣ለሚመሩት ህዝባቸው የተሻለውን ፈጥነው የሚወስኑበትን ማስተዋል እንዲበዛላቸው መለመን።

መግለጫውን የሰጡት የሕብረቱ ፕሬዝደንት በመግለጫቸው እንዳስታወሱት ሕብረቱ ከዚህ ቀደም አሁን በተፈጠረው ጉዳይ "ከመጸለይ ባሻገር ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት እንድትቆጠቡ በአደራ ጭምር እንጠይቃለን" ማለታቸውን አስታውሰው አሁንም ከጸሎት የሚበልጥ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

የህብረቱ ፕሬዝደንት አክለው እስካሁን ካሳለፍነው ነገር አንጻር እግዚአብሔር በቃ እንዲለን በእውነተኛ ቅን ልቦና ልመናን እና ምልጃን እንድናቀርብ ይሁን ብለዋል።

በዚህ ልመናን ምልጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ወንጌላውያን እና በመላው አለም የሚገኙ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ሕብረት አባላታቶች በሙሉ እንዲካፈሉ ጥሪ ቀርቧል።

የመግለጫውን ሙሉ ቪዲዮ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=TnuNfE_4cjY&t=170s
የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅቶች በቱርክ እና ሶሪያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈጠረው አደጋ አፋጣኝ ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በሬክተር ስኬል 7.8 በተመዘገው የመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን ከ15ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ሲያጡ ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የጉዳት ሰለባ ሆኗል።

የክርስቲያን በጎ አድራጎት ድርጅቶች በሶሪያ እና በቱርክ በደረሰው አደጋ የእርዳታ ስራን እየሰሩ እንደሆነ ክርስቲያን ፖስት በፊት ገጹ አስነብቧል።

እንደ ሳማሪቲያን ያሉ ክርስቲያናዊ ድርጅት ወደ 75 የሚሆኑ ስራተኞቻቸው ወደ አከባቢው አሰማርተዋል። ድርጅቱ በሰጠው ማስታወቂያ ላይ እንደገለጸው አስፈላጊ የሆኑ እቃዎችን ወደ ቱርክ በማጓጓዝ ላይ እንደሆነ ጠቅሷል።

"የእኛ ምላሽ እያደገ ሲሄድ ተጨማሪ የአደጋ እርዳታ ባለሙያዎችን እና አቅርቦቶችን ወደ ክልሉ እናሰማራለን" ሁላችሁም ባላችሁበት በጽሎት አግዟቸው ሲል የሳምሪታን ሃላፊዎች ተናግሯል።

ዜናዎችን በቪዲዮ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ https://www.youtube.com/watch?v=TnuNfE_4cjY&t=542s
1👍1
በናይጄሪያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጠመንጃ ታጥቀው የሰበኩት ፓስተር መነጋገሪያ ሆኑ።

ናይጄሪያዊው ፓስተር እሁድ ዕለት ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ታጥቀው ስበከት ላይ መገኘታቸው በምዕመናኑ ዘንድ ግራ መጋባትን ሲፈጥሩ በአገሪቱ ውስጥ መነጋገሪያ ሆነዋል።

በአቡጃ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ‘ሐውስ ኦን ዘ ሮክ’ የተባለው ቤተከርስቲያን ሰባኪ የሆኑት ኡቼ አይግቤ፣ ትናንት እሁድ ለስበከት ወደ መድረክ የወጡት ኤኬ47 የተባለው ጠመንጃ አንግበው ነበር።

በርካታ ምዕመን በታደመበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ ፓስተሩ ጠመንጃ ታጥቀው ወደ መድረኩ ሲወጡ በርካቶች ግራ ተጋብተው የነበረ ሲሆን፣ ይህንን የሚያሳየው ቪዲዮም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ታይቷል።

ፓስተሩ በትምህርታቸው ወቅት ጠመንጃ መታጠቃቸውን የምእመናኑን “ልብ ከሐሰተኛ መምህራን ከመጠበቅ” እና “እምነት ያለ ሥራ ምንም መሆኑን” ለማሳየት ተጠቅመውበታል ተብሏል።

“አንዳንዶች ችግር ይገጥመዋል ብለው እየጠበቁ ነው። እኔም ተዘጋጅቼ ነው የመጣሁት” በማለት ጠመንጃቸውን እያሳዩ መድረክ ላይ ቀልድ ጣል አድርገዋል።

ፓስተሩ ከምእመኑ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ስለሚሰበስቡ ሰባኪያን በማንሳት “ከእንዲህ አይነቶች እራሳችንን ለመጠበቅ መታጠቅ አለብን” በማለት ጠመንጃቸውን ለምሳሌው ተጠቅመውበታል።

በዚህም ሳቢያ የፓስተር ኡቼ አይግቤ ድርጊትን የሚያሳየው ቪዲዮ በስፋት ከመሰራጨቱ ባሻገር በመላው ናይጄሪያ መነጋገሪያ ሆኗል።

የሰባኪውን ጠመንጃ ታጥቆ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣትን በተመለከተ ፓስተሩ ሲሰብኩበት የነበረው ቤተክርስቲያ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጥያቄ ቢቀርብለትም ምላሽ አልሰጠም።
👍1
#ሕብረት ያወጀው የንስሃና ምልጃ ጽሎት ዛሬ ተጀምሯል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከየካቲት 9-12/2015 ዓ.ም እንዲቆይ ያወጀው የንስሃና ምልጃ ጽሎት በትላንትናው እለት በሕብረቱ ጽ/ቤት ያስጀመረ ሲሆን በመላው ሀገሪቱ እና ከሀገር ውጪ ደግሞ ከዛሬ የሚጀምር ይሆናል።

"እግዚአብሔር ሆይ ተስፋ ባደረግንህ በእኛ ላይ ምህረትህ ትሁን"
በሚል መዝ 33:22 መሪ ቃል በማድረግ የተጀመረው የንስሃና ምልጃ ጽሎት

1. ስለ ፈሰሰው የንጹሃን ደም የእግዚአብሔርን ምህረትን መለመን
2. በጭንቀት ላይ ላሉ አረጋውያን፣ ወላጅ አጥ የሆኑ ህጻናትን፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር በቃችሁ ብሎ እንዲያሳርፋቸው ምህረትን መለመን።
3. ለሃይማኖት እና ለሃገር መሪዎች ጥበብና ማስተዋል እንዲሰጣቸውና ፣ለሚመሩት ህዝባቸው የተሻለውን ፈጥነው የሚወስኑበትን ማስተዋል እንዲበዛላቸው መለመን።

ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ የሚያተኩር ይሆናል።
1
#ድንቅ ተዓምር ነው።
#አስደሳች አለቀ በተባለ ነገር ላይ ህይወት ይቀጥላል።

ምንም እንኳን የቱርክ ርዕደ መሬት (የመሬት መንቀጥቀጥ) ከ20,000 በላይ የሚሆን የሰዎን ህይወት ቢቀጥፍም ዛሬም ድረስ በተዓምር ስለተረፉ ሰዎች መስማት ብዙዎችን ከሃዘናቸው እያጽናናቸው ነው።

ዛሬ የተሰማው ዜና ደግሞ እናትና ልጅን ጨምሮ 5 ሰዎች በፍርስራሽ ውስጥ ከ9 ቀናት በኋላ በህይወት መገኘታቸውን የሚገልጽ ነው።

ከዘጠኝ ቀናት በፊት ከተከሰተው ርዕደ መሬት በኋላ ከተማዋን በማጽዳት ላይ የነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች የ42 እና የ74 ዓመት አዛውንቶችን ጨምሮ 5 ሰዎችን ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት አግኝተዋቸዋል።

የዳርካ ከተማ ከንቲባ ሙዛፈር ቢያክ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ያጋሩት ቪዲዮ የነፍስ አድን ሰራተኞች የ74 ዓመቷ ሴሚሊክ ኬኪትስን እያበረታቱ ወደ አምቡላንስ ሲጭኗቸው አሳይቷል።

በሌላ በኩል የ42 ዓመቷ ሜሊክ ኢማንጉሉን ነፍስ አድን ሰራተኞች በህይወት ሲያገኟቸው አድናቆታቸውን እንደገለጹላቸው የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በርዕደ መሬቱ ክፉኛ በተጎዳችው ሌላኛዋና አንታይካ በተባለችው ከተማ አንዲት እናት ከፍርስራሽ ውስጥ ከሁለት ልጆቿ ጋር በህይወት ተገኝታለች።

አለቀ በተባለ ነገር ላይ የአንዳንዶች ታሪክ ዛሬም ቀጥሏል።
እንደ #ኢየሱስ 40 ቀን እጾማለው ያለው #ፓስተር ሞተ

እንደ #ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም የሞከረው ሞዛምቢካዊ #ፓስተር ሕይወቱ አለፈ።

ፍራንሲስ ባራጃህ የተባለው ፓስተር ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀናት በመጾም ያደረገውን ምሳሌ ለመድገም ባደረገው ሙከራ ነው ለሕልፈት የተዳረገው።

ፓስተሩ በሞዛምቢክ ማዕከላዊ ግዛት ማኒሺያ ውስጥ የምትገኘው ሳንታ ትሪንዳድ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መሥራች ሲሆን ከጾሙ ጋር በተያያዘ ሕይወቱ ማለፉ ረቡዕ ዕለት ተረጋግጧል።

ፓስተር ፍራንሲስ ባራጃህ በጾሙ ምክንያት ክፉኛ በተዳከመበት ጊዜ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም ሕይወቱን ለማትረፍ ሳይቻል መቅረቱ ተዘግቧል።

ፓስተሩ ጾሙን ለ40 ቀናት ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ከ25 ቀናት ጾም በኋላ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ክብደቱ ቀንሶ ለመቆምም ሆነ ለመራመድ ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር።

ይህም ሆኖ ግለሰቡ በጾሙ የቀጠለ ሲሆን፣ ከቀናት በኋላ ግን በዘመዶቹ እና በቤተክርስቲያኗ አባላት ውትወታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል።

ነገር ግን በጾሙ ምክንያት ክፉኛ በመጎዳቱ የተነሳ ሐኪሞች ጤናውን ለመመለስ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ለህልፈት ተዳርጓል።

ፓስተር ፍራንሲስ ባራጃህ ጾሙን ከጀመረ በኋላ በታየበት ከፍተኛ አካላዊ ለውጥ የተነሳ የቤተክርስቲያኗ አባላት እና በዙሪያው ያሉ ሰዎች ሕልፈቱ ብዙም አላስደነቃቸውም።

ፍራንሲስ ባራጃህ በጾሙ ወቅት ከፍተኛ የክብደት መቀነስ እና የሰውነት አቋሙም ተቀይሮ እንደነበር ተነግሯል።

BBC News Amharic
👍1
የኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተክርስቲያን ቢሾፍቱ ደብረዘይት አጥቢያ የድምፅ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ስለወደሙባት የእናንተን ቅዱሳንን እገዛ ትሻለች።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ ደብረ ዘይት ቅርንጫፍ
1000011507698
#ብርሃን ባንክ
2602750022834
#አቢሲኒያ ባንክ
83161717
#ኦሮሚያ ኮፕሬቲቭ
1017100056104
#ለበለጠ መረጃ፦ +251912299228
0114335375
#ምንድነው እየሆነ ያለው?

በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት ውስጥ በሚገኝ #asbury ዮንቨርስቲ ምን እየሆነ እንዳለ ብዙዎችን ግራ አጋብቷል።

በከተማዋ ከሚገኙት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በዚህ ድንቅ ሪቫይቫል ውስጥ እየተካፈሉ ነው። ለ40 ደቂቃ ወደ ጸሎት የገቡት ወጣቶች ዛሬ ቀናትን ተሻግረዋል።

#አምልኮ ለአፍታ ሳይቋረጥ ሳምንት ተሻግሯል። ብዙዎች ከተለያዩ ከተሞች ወደስፍራው እየጎረፉ ነው። እውነት ነው በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት አስበሪ ዮንቨርስቲ ታላቅ #ሪቫይቫል ተነስቷል።

እንደሚል በኬንታኪ ስቴት በሚገኘው ዩኒቨርሲት ተማሪዎች በየሴሚስቴሩ በግቢው ውስጥ በሚገኘው የማመለኪያ አዳራሽ ለጸሎት የተወሰኑ ቀናት መገኘት ይኖርባቸዋል።

ባሳለፍነው ረቡዕ ላይ ለአምልኮ በተሰበሰቡበት ኳየሮች አምልኮ መምራት ይጀምራሉ። ይሁንና ጥቂት ደቂቃዎች እንደሚፈጅ የተጠበቀው አምልኮ ሳይቋረጥ ለሰዓታት ይቀጥላል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ይህንን የሰሙ ወገኖች ከየስቴቱ በስፍራው ይሰበሰባሉ ዛሬ ሳምንቱን ተሻግሯል።

በአንድ ወቅት ወንድማችን ተስፋዬ ሮበሌ ሪቫይቫል ምንድን ነው? ሲል ካሰፈራቸው ነጥቦች ሶስቱን እናስነብባችሁ።

1. "የሪቫይቫል" ቀዳማይ ግብ የሕይወት ለውጥና የነፍሳት ድነት እንጂ፣ ልሳንና ተኣምር አይደለም!

2. የጸጋ ስጦታዎችም ቀዳማይ ግብ፣ እውነተኛ የሕይወት ተሐድሶና የሰዎች ድነት (ሰዎች ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸውና ጌታቸው መቀበላቸው) ነው!

3. "ሪቫይቫል" ነገን እውን ይሆናል ብለን የምንጠብቀው ክሥተት ሳይሆን፣ ዛሬን የምንተገብረውና የምንኖረው ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው! እውነተኛ የሕይወት ለውጥና የነፍሳት ድነት ባለበት ቦታ ሁሉ "ሪቫይቫል" አለ:: ይህ በሌለበትም ቦታ "ሪቫይቫል" የለም!

ሲል አስፍሮ ነበር። ሪቫይቫል ምንድነው በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን።
1