The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የ5_ዓመቱ_ህጻን_ሰባኪ

አነጋጋሪው እና ብዙዎች በየአቅጣጫው የአድናቆት መልዕክት እየላኩለት የሚገኘው ህጻኑ ሰባኪ እየተባለ የሚጠራው ታዳጊ ከሰሞኑ አንድ ሾው ላይ ቀርቦ ሲሰብ እና ሲዘምር ተስተውሏል።

ይህ ታዳጊ ሙሉ ስሙ ሉቃስ ቲልማን ይባላል። ነዋሪነቱ ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር በሚንቺንግሃም ሲሆን 4 ወንድሞችም አሉት።

ታዲያ ይህ ህጻን ከሰሞኑ በታዋቂዋ ጄኒፌር ሀድሰንስ ቴሌቪዥኝ ሾው ላይ ቀርቦ ሲሰብክ እና ተወዳጁን "Take Me to the Water" የተሰኘውን ዝማሬ ዘምሯል።

በዝግጅቱ ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምትወደው ጥቅስ የትኛው ነው ተብሎ ተጠይቆ ዮሐንስ 3:16 እንደሆነ ተናግሯል።

ታዳጊው ከሰሞኑ በፈረንጆቹ Dec 29 የራሱን የመጫወቻ አሻንጉሊት ሲያጠምቅ የሚያሳይ ቪዲዮ በእናቱ አማካኝነት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ከተለቀቀ በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካችን እና ተወዳጅነትን አግኝቶ ስንብቷል።

ታዲያ ዝናን ያገኘው ታዳጊ በታዋቂው የቴሌቪዥን ሾው ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር በመጋበዝ ተወዳጅ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

በቃለ መጠይቁ ከ2 ዓመቱ ጀመሮ አባቱን አጥምቀኝ እያለ ይጠይቅ እንደነበረም ተናግሯል። አባቱ ሰባኪ ሲሆን ባለፉት 20 አመታት 20 ሚሊዮን ሰዎችን የሰበከ እንደሆነ ጠቅሶ ታዳጊው ልጁ ግን በአንድ ሾው 20 ሚሊዮኖችን እንደደረሰ ተናግሯል።

@CBN
በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት የቄስ ትምህርት መደበኛዉን የትምህርት ስርዓት በመተካት አስተዋጽዖ ያደርግ እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ምክኒያት በተለይ በትግራይ ክልል ዜጎች ማግኘት የነበረባቸዉን መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማግኘት ተቸግረው ቆይተዋል። አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች የትምህርት ፣ የጤና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዉ የነበረ ቢሆንም በተለይ በትምህርት ዘርፉ ላይ ህጻናት ማግኘት የነበረባቸዉን እዉቀት ሳያገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

ኮቪድ - 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተበትና ይህንኑ ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ለሶስት አመታት ገደማ ተቋርጧል በተባለዉ መደበኛ ትምህርት ፤ ህጻናት እዉቀት ካለማግኘታቸዉ በተጨማሪ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ከሚገኙ የእድሜ እኩዮቻቸዉ ወደ ኋላ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል።አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የሰጡን የክልሉ ነዋሪች እንደገለጹት ፤ ጦርነቱ አይሎ በነበረባቸዉ ወቅት የቄስ ትምህርት ተቋርጦ የነበረዉን መደበኛ ትምህርት በመተካት እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ሲማሩ ቆይተዋል።

በተለይ እድሜያቸዉ ለጦርነት ያልደረሱና  ከሰባት እስከ አስራ አምስት አመት የሆኑ ህጻናት ትምህርቱን በስፋት ሲከታተሉ ነበር። በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀዉ ዓመታትን ያስቆጠሩ እንደመሆናቸዉ የስነልቦና ጫና ይታይባቸዋል ብለዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዉ ገለጻ " ህጻናት ከትምህርት ይልቅ ስለ ብረት እና ጦርነት ያወራሉ" ሲሉ ተናግረዋል። አክለዉ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ወደ መኖሪያ ቀዬአቸዉ መመለስ ያልቻሉ በርካታ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ብለዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
#ጸሎት #ብቻ

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት፣ ኅብረቶች፥ ቤተ እምነቶችና ምዕመናም በሙሉ፤

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የተከሰተውን ሁኔታ/ ችግር አስመልክቶ ከመጸለይ ባሻገር ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት እንድትቆጠቡ በአደራ ጭምር እንጠይቃለን።

በክርስቶስ ፍቅር
መጋቢ ጻድቁ አብዶ
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዝደንት

Christian ዜማ Tube
ከደቂቃዎች በኋላ #ሰበር ዜና ይጠብቁን!!!
ዘማሪ ሳሚ አበበ ሙሉ በሙሉ ከቤተክርስቲያን ተሰናብቷል።

ዉድ የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ዛሬ የሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን በዘማሪ ሳሚ አበበ ላይ የሰጠችዉ የመጨረሻ መግለጫ ቢሆንም እዚህ ከመደረሱ አስቀድሞ ላለፉት 6 ወራት በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ተገልጿል።

ምንም እንኳን ዜናዉ አሳዛኝ ቢሆንም ቤተክርስቲያን ይህ እንዳይፈጠር በርካታ ስራዎችን ብትሰራም አልተሳካም።

ነገር ግን ምንም እንኳን ቤተክርስቲያን ከዘማሪዉ ጋር ያላት ግንኙነት ቢቋረጥም ባለቤቱን እና ልጁን ግን ሙሉ ሃላፊነት በመዉሰድ አስፈላጊውን እገዛ እንደምታደርግላቸዉ በመግለጫው ተጠቅሷል።

ላለፉት 6 ወራት ዘማሪው የፅሞና ጊዜ ወስዶ ልጁን እና ቤተሰቡን እየተንከባከበ በንሰሃ እንዲመለስ ቤተክርስቲያን እና መሪዎች ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ዘማሪው ፍቃደኛ ባለመሆኑ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል።

ይልቁንም ባለቤቱ ከቤት እንዳበረረችዉ እና ቤተክርስቲያን ድጋፍ እያደረገችልኝ አይደለም በሚል ቤተክርስቲያንን ከሷል።

ሙሉ ዝርዝር መረጃዉን

በቪዲዬ መመልከት ትችላላችሁ። https://youtu.be/AilX6O9IC24
ለክርስትና እጅግ አስቸጋሪ የሆኑ ሃገራት ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ። በሪፖርቱ መሰረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ50 ሀገራት መካከል 39ኛ ስፍራን ይዛለች።

በየአመቱ ለክርስትና አስቸጋሪ የሆኑ ሀገራትን ስም ዝርዝር ይፋ የሚያደርገው ኦፕን ዶርስ የተሰኘ ተቋም በቅርቡ የያዝነውን የፈረንጆቹ 2023ዓ.ም ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ይፋ እንዳደረገው ሪፖርት ከሆነ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2022 ከ5,600 በላይ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት እንደተገደሉ የጠቀመ ሲሆን ከ2,100 በላይ ቤተክርስቲያኖች ደግሞ በደረሰባቸው ጥቃት ከፊሉ ሲወድሞ ከፊሎ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

ከ124,000 በላይ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ከቤታቸው በኃይል የተፈናቀሉ ሲሆን ወደ 15,000 የሚጠጉት ደግሞ ስደተኞች እንደሆኑ አስነብቧል።

በዘንድሮው አመት ሪፖርት ሰሜን ኮርያ ለክርስትና እጅግ አስቸጋሪ በመባል በ1ኛ ስፍራ ስትቀመጥ ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ በ2ኛ ደረጃ እጅግ አስቸጋሪ በመባል ተቀምጣለች።

የመን ፤ ጎረቤት ሀገር ኤርትራ እና ሊቢያ ከ3 እስከ 5ኛ ስፍራን ይዘዋል። ባሳለፍነው አመት የ1ኛ ስፍራን ይዛ የነበረችው አፍጋኒስታን ከፍተኛ መሻሻልን በማሳየት በ9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ናይጄሪያ ፤ ፓኪስታን ፤ ኢራን ፤ አፍጋኒስታን እና ጎረቤት ሀገር ሱዳን ከስድስኛ እስከ አስረኛ ደረጃን በመያዝ ለክርስትና እጅግ አስቸጋሪ ሀገራት ተርታን እየመሩ ተቀምጠዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘንድሮው አመት 39ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን ከ2022 ሪፖርት 1 ደረጃን ብቻ አሻሽላለች።

በ2022 3ኛ 6ኛ እና 13ኛ ስፍራ የነበሩት የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ሶማሊያ ኤርትራ እና ሱራን በዘንድሮው አመት 2ኛ 4ኛ እና 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
#ቤተክርስቲያን_ምንም ግንኙነት የላትም

ቤተ-ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ ዓመታት ከክርስቶስ የተቀበለችውን የወንጌል ተልዕኮ ተቀዳሚ ተግባሯ በማድረግ ቃለ-እግዚአብሔርን በማስተማር ትውልድን የክርስቶስ ደቀ-መዝሙር የማድረግ ሥራ በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ብሎም ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ ሀገራት ህጋዊ ተቋም ሆና በመመዝገብ በትጋት ስትሰራ ቆይታለች፡፡

ይሄንኑ ተልዕኮ ለማስፈጸም አገልግሎቱን በምንሰጥባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለሥራችን እንደየአመቺነቱና አስፈላጊነቱ የተለያዩ ንብረቶችን እና ቁሶችን የተለያየ እምነትና አመለካከት ካላቸው ግለሰቦች ብሎም ድርጅቶች በግዢም ሆነ በኪራይ ስንጠቀም ቆይተናል፣ እየተጠቀምን እንገኛለን፤ ወደፊትም ይህ እየሆነ ይቀጥላል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘውንና ንብረትነቱ የአባ ገብረ-እግዚአብሔር ታደለ የሆነ ቤት ህጋዊ በሆነ መንገድ በፌደራል የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት ውል በመፈራረም ተከራይተን በመገልገል ላይ እንገኛለን፡፡

ለዚህም የኪራይ አገልግሎት ክፍያዎችን ህጋዊ በሆነ የገንዘብ ተቋም አማካኝነት በውል በታሰረው የጊዜ ገደብ ልዩነት ለግለሰቡ ስንከፍል ቆይተናል፤ ንብረታቸውን እስከምንገለገልበትም ጊዜም ድረስ የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈላችንን እንቀጥላለን፡፡

ቤተ-ክርስቲያናችንም ከግለሰቡ ጋር ከአከራይና ተከራይነት ውጪ ምንም ዓይነት ግንኙነት የላትም፡፡

ነገር ግን እውነታው ይሄ ሆኖ ሳለ ከዚህ በእጅጉ ባፈነገጠ መልኩ ለኚሁ ግለሰብ ከቤተ-ክርስቲያናችን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የቤት ኪራይ ገንዘብ ገቢ ያደረግበትን የባንክ ደረሰኝ በማያያዝና የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት በማህበራዊ ድረ-ገጾች ህዝብን ግራ የማጋባትና ጥላቻ የመዝራት ሙከራዎች እየተደረገ ነው።
#እናመሰግናለን

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በYoutube ቻናል 40,000 ቤተስቦች ደርሰናል ታማኝ #የክርስቲያን መረጃዎች ምንጭ አድርጋችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።

በቀጣይ እጅግ በርካታ ስራዎች በጋራ እንደምንሰራ በማመን አሁንም አብሮነታችሁ ይቀጥል እንላለን። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የቤተሰቦቻችን ቁጥር #50ሺህ ደርሶ ለምስጋና በድጋሜ እንደምንገናኝ እናምናለን።

https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A
#ልጃቸውን አየር ማረፊያ ውስጥ ጥለው የሄዱት ጥንዶች

ልጅን ያለ ትኬት በረራ ማድረግ እንደማይችል የተነገራቸው ጥንዶች በእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ የመግቢያ መሥሪያ ቤት ሕፃኑን ጥለው መሄዳቸው ተሰምቷል።

ወላጆቹ ከ እስራኤል ቴል አቪቭ ወደ ቤልጂየም ብራስልስ እየተጓዙ ነበር በረራቸውን ለማየት ማክሰኞ ቤን ጉሪዮን አየር ማረፊያ ደረሱ

የእስራኤሉ አየር ማረፊያ ባለስልጣን ለሲኤንኤን በሰጠው መግለጫ ቤተሰቦቹ ለበረራ ዘግይተው ተርሚናል 1 መድረሳቸውን እና ወላጆች ልጃቸው የበረራ ትኬት እንደሌላቸው ሲረዱ መግቢያው ተዘግቷል ብሏል።

የእስራኤል አውሮፕላን ማረፊያ ባለስልጣን "ጥንዶች የጨቅላ መቀመጫውን ከልጁ ጋር ትተው እና ተርሚናል 1 ላይ ወደሚገኘው የደህንነት ፍተሻ ሮጡ" ሲል የእስራኤል አየር ማረፊያ ባለስልጣን ተናግሯል።

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ራያኔር ሁኔታው ለአካባቢው ፖሊስ መተላለፉን ለ CNN ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ፖሊስ በደረሰበት ጊዜ ጉዳዩ እልባት አግኝቶ ህፃኑ ከወላጆቹ ጋር እንደነበረ እና ምንም ተጨማሪ ምርመራ እንደማይደረግ ተናግረዋል ።

እንደ Ryanair ድረ-ገጽ ከሆነ "በኦንላይን ቦታ ማስያዝ ሂደት ውስጥ ህፃናት በበረራ ቦታ ማስያዝ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ" በድረ-ገጹ ላይ ለአንድ ህፃን በአዋቂዎች ጭን ላይ ለመቀመጥ የእያንዳንዱ የአንድ መንገድ በረራ ዋጋ 25 ዩሮ (27 ዶላር) እንደሆነ ይገልጻል።
#አስቸኳይ
#ሕብረቱ #አስቸኳይ መግለጫ እየሰጠ ነዉ።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት አስቸኳይ መግለጫ እየሰጠ ነዉ።

#ሕብረቱ በመግለጫዉ በሃገራችን በተለያዩ ጊዜያት ለፈሰሰው ደም ንሰሃ ልንገባ ይገባል ብሏል።

#በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረዉን ጉዳይ አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ወንጌላዊያን በፀሎት እንዲቆዩ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል።

ሙሉ መግለጫውን ከደቂቃዎች በኋላ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://youtu.be/Jh06dRDzYRc
#ህብረቱ አስቸኳይ መግለጫ ሰጠ #በአስቸኳይ ጾም ጽሎት ይጀምር # እርስ በራሳችን እንታረቅ #በአሁኑ ሰዓት አስቸኳይ ጾም ጽሎት ታውጇል።

https://youtu.be/TnuNfE_4cjY
#አስቸኳይ ጾም ጽሎት ታውጇል።
#ህብረቱሕብረቱ አስቸኳይ ጾም እና ጸሎት አውጇል።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት
መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ገነት ቤተርስቲያን
የኢትዮጵያ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን
የኢትዮጵያ ሕይወት ብርሃን ቤተክርስቲያን በጋራ በመሆን አስቸኳይ የጾም እና ጸሎት ለሁሉም ወንጌላውያን አማኞች አውጀዋል።

የጾም እና ጸሎት መረሃ ግብሩ ከየካቲት 9-12/2015 ዓ.ም የሚቆይ እንደሆነም ታውቋል።

ሙሉ የመግለጫውን ሃሳብ The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን ስለተከታተልነው እንደሚከተለው ይዘንላችሁ ቀርበናል።

"እግዚአብሔር ሆይ ተስፋ ባደረግንህ በእኛ ላይ ምህረትህ ትሁን"
መዝ 33:22

እኛ ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮ አደጋና በሰው ሰራሽ ጦርነት ምክንያት ተክለን ነቅለናል ፣ ገንብተን አፍርሰናል ከሁሉ በላይ ደግሞ በማንነትና በሀሳብ ልዩነቶች ምክንያት ምትክ የማይገኝለትን የሰው ልጅ ህይወት ፣ በየትውልዱ እየተገበረ እዚህ ደርሰናል።

በዚህ ምክንያት ፣ አለመተማመንና አለመደማመጥ ስር ከመስደዱ የተነሳ ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት አስቸጋሪ ሆኖብናል።

በሌላ በኩል በሀገራችን ለተከሰቱት በደሎች ተጠያቂና ጥፋተኛ በመፈለግ እራሳችንን ከችግሩ ነፃ ለማድረግ ስንጥር እንታያለን። ነገር ግን እውነታው ሲፈተሽ በማድረግ ወይም ባለማድረግ ፣ በመናገር ወይም ባለመናገር ፣ በመሆን ወይንም ባለመሆን ሁላችንም በድለናል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎን ተገኝተናል።

ስለሆነም ከካቲት 9-12/2015 ዓ.ም በንስሃና ምልጃ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለሃገራችንና ለህዝባችን ምህረትን ለመለመን በአገር ውስጥና በመላው አለም የምንገኝ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት አባላት እንዲሁም እዚህ የተገኙት አራቱ ቤተዕምነቶች በጋራ የነገሩ ክብደት አሳስቦን ይህንን ጥሪ አስተላልፈናል።

ህብረቱ በመግለጫው ይህ ሀገር አቀፍ የምልጃ እና የንሰሃ የጸሎት ጥሪ 3 የፀሎት አርዕስቶችን የያዘ እንደሆነም ጠቅሷል።

1. ስለ ፈሰሰው የንጹሃን ደም የእግዚአብሔርን ምህረትን መለመን

2. በጭንቀት ላይ ላሉ አረጋውያን፣ ወላጅ አጥ የሆኑ ህጻናትን፣ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር በቃችሁ ብሎ እንዲያሳርፋቸው ምህረትን መለመን።

3. ለሃይማኖት እና ለሃገር መሪዎች ጥበብና ማስተዋል እንዲሰጣቸውና ፣ለሚመሩት ህዝባቸው የተሻለውን ፈጥነው የሚወስኑበትን ማስተዋል እንዲበዛላቸው መለመን።

መግለጫውን የሰጡት የሕብረቱ ፕሬዝደንት በመግለጫቸው እንዳስታወሱት ሕብረቱ ከዚህ ቀደም አሁን በተፈጠረው ጉዳይ "ከመጸለይ ባሻገር ምንም አይነት አስተያየት ከመስጠት እንድትቆጠቡ በአደራ ጭምር እንጠይቃለን" ማለታቸውን አስታውሰው አሁንም ከጸሎት የሚበልጥ ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

የህብረቱ ፕሬዝደንት አክለው እስካሁን ካሳለፍነው ነገር አንጻር እግዚአብሔር በቃ እንዲለን በእውነተኛ ቅን ልቦና ልመናን እና ምልጃን እንድናቀርብ ይሁን ብለዋል።

በዚህ ልመናን ምልጃ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ወንጌላውያን እና በመላው አለም የሚገኙ የወንጌላውያን አብያተክርስቲያን ሕብረት አባላታቶች በሙሉ እንዲካፈሉ ጥሪ ቀርቧል።

የመግለጫውን ሙሉ ቪዲዮ ለማግኘት ሊንኩን ይጠቀሙ። https://www.youtube.com/watch?v=TnuNfE_4cjY&t=170s