The Christian News
5.08K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሀልዎት

የሀልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከ ሦስት መቶ በላይ 7ተኛ ዙር ካልቸር የተማሩ አባላቶችን አስመርቃለች።

የምረቃ ስነስርአቱ በቢሾፍቱ ከተማ ጆርጋ ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በደማቅ ስነስርአት ተካሂዷል።

በዕለቱ የዝማሬ የትምህርት እንዲሁም የቃልኪዳን ፕሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ለቤተክርስቲያኒቷ መሪዎች እና አገልጋዮች ከተመራቂዎች ስጦታዎች ተበርክተዋል።

ተመራቂዎች በአንድነት ማዕድ በመጋራት እና በመካከላቸዉ ከተገኙ የጫወታ አዘጋጅ ድርጅት አስተባባሪዎች ጋር በተለያዩ ጨዎታዎች እና ዉድድሮች አሳልፈዎል።
#እንኳን #አደረሳችሁ !!!

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብረሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

The Christian News - የክርስቲያን ዜና የጥምቀት በዓልን በ #ዱራሜ ከተማ ተገኝተን እጅግ የሚያምረዉን ስነስርዓት እየተከታተልን ነዉ።

በድጋሜ #እንኳን #አደረሳችሁ !!!
የቦረና እና አካባቢው ሲኖዶስ ምስረታ ተከናወነ።

የኢ/ወ/ቤ/መካነ ኢየሱስ 21ኛ የቤተክርስቲያኒቱ ዓቢይ ጉባኤ እንዲመሰረቱ ከተወሰኑ ሲኖዶሶች አንዱ የሆነው የቦረና እና አካባቢው ሲኖዶስ የምስረታ ጉባኤ እና ኮንፈረንስ ከጥር 04-07: 2015ዓ.ም በያቤሎ ከተማ ተካሂዷል።

በተደረገው የሲኖዶሱ ምስረታ ጉባኤም የሲኖዶሱ መሪዎች ምርጫ የተደረገ ሲሆን:

1. ቄስ ጋልጋሎ ቃሬ- የሲኖዶሱ ፕረዚዳንት:
2. ቄስ ጋልጋሎ ዳዳቻ: ምክትል ፕረዚዳንት:
3. አቶ ተከተል ንጋቱ አቃቤ ንዋይ በመሆን ተመርጠዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኀብረት ከአጋር አባላቱ ጋር በዓመት ሁለት ጊዜ ሊያደርግ ካቀደው ስብሰባ የመጀመሪያውን አካሄደ፡፡

ሁለት መቶ የሚጠጉ አጋር አባላት በተገኙበት በዚህ ስብስባ የኅብረቱ ኘሬዚዳንት ፓ/ር ፃድቁ አብዶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እንዴት መኖር እደሚገባ የሚያስገነዝብና የሚያሳስብ መልእክት ያቀረቡ ሲሆን፣የኅብረቱ ሚሽንና ቲዎሎጂ መምሪያ ዳይሬክተር ፓ/ር ደረጀ ታፈሰ፣ ኅብረቱ ከአጋር ቤተ እምነቶች ጋር በዓመት ሁለት ጊዜ ሊያካሂድ ካቀደው ስብሰባ ይህ አንደኛው መሆኑን ጠቅሰው፣ መተያየትና አብሮ በጋራ መጸለይ የክርስቶስን አካል ይበልጥ የሚያስተሳስርና አንዱ ለሌላው እንዲያስብ የሚያበረታታ በመሆኑ እንዲህ ዓይነቱን መተያየት ደጋግሞ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

ኅብረቱ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር እስከ 2030 የአስር ዓመት የአገልግሎት ፍኖተ ካርታ ቀርጾ በተግባር ላይ እያዋለ መሆኑን የገለጡት ፓ/ር ደረጀ በሦስት ዐበይት ነጥቦች ማለትም፣ በተሃድሶ፣ በመንፈሳዊ መነቃቃት እንዲሁም በእርቅና ሰላም ጉዳዮች ላይ ትኩረት የተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ያለንበት መንፈሳዊ ዐውድ ተሃድሶ ጠሪ መሆኑን፣ መንፈሳዊ መነቃቃትም በእጅጉ እንደሚያስፈልግ፣ ከመቼውም ጊዜ ይልቅም በሰላምና እርቅ ዙሪያ አብዝቶ መጸለይና አብዝቶ መሥራት ከእያንዳንዱ ምዕመን እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሰብሳቢዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተነሱና ምላሽ ከተሰጠባቸው በኋላ ከዚህ ቀደም ሲያገለግሉ በነበሩ ኮሚቴዎች ምትክ አዲስ ምርጫ ተካሂዷል
1. ፓ/ር ወርቅነህ አላሮ
2. ፓ/ር ካሱ ቱሉ
3. ፓ/ር ብዙአየሁ መኮንን
4. እ/ት ፀዳሽ ተፈራ
5. ፓ/ር ፀጋዬ ተንኮሉ የአጋር ቤተእምነቶችን በኮሚቴነት እንዲያገለግሉ ተመርጠው፣ ስብሰባው በጸሎት ተጠናቋል።
1
ሂንዱዎች በህንድ ውስጥ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት አደረሱ። በጥቃቱ በርካቶች ቆስለዋል።

የሂንዱ አክራሪ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ከ1,000 የሚበልጡ መንደሮች በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት በመሰንዘር በህንድ ወደብ አልባ በሆነችው ቻቲስጋርህ ግዛት ናራያንፑር አውራጃ ውስጥ ጥቃት ማድረሳችውን ዘገባዎች አመልክተዋል።

“ሃይማኖት ተለውጧል” በሚል ክስ ከቀረበ በኋላ ህዝቡ ከእንጨትና ከብረት ዘንግ ታጥቆ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሕንፃ መግባቱን የገለጹት እማኞች፣ ሕንጻውንና ቤተ ክርስቲያኑ ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

ጥር 2 ቀን የተፈጠረውን ግርግር ለማስቆም ሲሞክሩ የወረዳውን ዋና አስተዳዳሪን ጨምሮ በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል።

ክርስቲያኖች በአካባቢው ላሉት አማኞች እና ሌሎች “በክርስቶስ ላይ ስላላቸው መድልዎ” ጸሎት ጠይቀዋል።

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW
#የ5_ዓመቱ_ህጻን_ሰባኪ

አነጋጋሪው እና ብዙዎች በየአቅጣጫው የአድናቆት መልዕክት እየላኩለት የሚገኘው ህጻኑ ሰባኪ እየተባለ የሚጠራው ታዳጊ ከሰሞኑ አንድ ሾው ላይ ቀርቦ ሲሰብ እና ሲዘምር ተስተውሏል።

ይህ ታዳጊ ሙሉ ስሙ ሉቃስ ቲልማን ይባላል። ነዋሪነቱ ደግሞ ከቤተሰቦቹ ጋር በሚንቺንግሃም ሲሆን 4 ወንድሞችም አሉት።

ታዲያ ይህ ህጻን ከሰሞኑ በታዋቂዋ ጄኒፌር ሀድሰንስ ቴሌቪዥኝ ሾው ላይ ቀርቦ ሲሰብክ እና ተወዳጁን "Take Me to the Water" የተሰኘውን ዝማሬ ዘምሯል።

በዝግጅቱ ላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ የምትወደው ጥቅስ የትኛው ነው ተብሎ ተጠይቆ ዮሐንስ 3:16 እንደሆነ ተናግሯል።

ታዳጊው ከሰሞኑ በፈረንጆቹ Dec 29 የራሱን የመጫወቻ አሻንጉሊት ሲያጠምቅ የሚያሳይ ቪዲዮ በእናቱ አማካኝነት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ከተለቀቀ በኋላ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተመልካችን እና ተወዳጅነትን አግኝቶ ስንብቷል።

ታዲያ ዝናን ያገኘው ታዳጊ በታዋቂው የቴሌቪዥን ሾው ላይ ከቤተሰቦቹ ጋር በመጋበዝ ተወዳጅ ቃለ መጠይቅ አድርጓል።

በቃለ መጠይቁ ከ2 ዓመቱ ጀመሮ አባቱን አጥምቀኝ እያለ ይጠይቅ እንደነበረም ተናግሯል። አባቱ ሰባኪ ሲሆን ባለፉት 20 አመታት 20 ሚሊዮን ሰዎችን የሰበከ እንደሆነ ጠቅሶ ታዳጊው ልጁ ግን በአንድ ሾው 20 ሚሊዮኖችን እንደደረሰ ተናግሯል።

@CBN
በትግራይ ክልል በጦርነቱ ወቅት የቄስ ትምህርት መደበኛዉን የትምህርት ስርዓት በመተካት አስተዋጽዖ ያደርግ እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በነበረው ጦርነት ምክኒያት በተለይ በትግራይ ክልል ዜጎች ማግኘት የነበረባቸዉን መሰረታዊ አገልግሎቶች ለማግኘት ተቸግረው ቆይተዋል። አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች የትምህርት ፣ የጤና እና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዉ የነበረ ቢሆንም በተለይ በትምህርት ዘርፉ ላይ ህጻናት ማግኘት የነበረባቸዉን እዉቀት ሳያገኙ ቀርተዋል ብለዋል።

ኮቪድ - 19 በኢትዮጵያ ከተከሰተበትና ይህንኑ ተከትሎ ከተቀሰቀሰው ጦርነት ወዲህ ለሶስት አመታት ገደማ ተቋርጧል በተባለዉ መደበኛ ትምህርት ፤ ህጻናት እዉቀት ካለማግኘታቸዉ በተጨማሪ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ከሚገኙ የእድሜ እኩዮቻቸዉ ወደ ኋላ እንዲቀሩ አድርጓቸዋል።አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የሰጡን የክልሉ ነዋሪች እንደገለጹት ፤ ጦርነቱ አይሎ በነበረባቸዉ ወቅት የቄስ ትምህርት ተቋርጦ የነበረዉን መደበኛ ትምህርት በመተካት እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ሲማሩ ቆይተዋል።

በተለይ እድሜያቸዉ ለጦርነት ያልደረሱና  ከሰባት እስከ አስራ አምስት አመት የሆኑ ህጻናት ትምህርቱን በስፋት ሲከታተሉ ነበር። በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀዉ ዓመታትን ያስቆጠሩ እንደመሆናቸዉ የስነልቦና ጫና ይታይባቸዋል ብለዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዉ ገለጻ " ህጻናት ከትምህርት ይልቅ ስለ ብረት እና ጦርነት ያወራሉ" ሲሉ ተናግረዋል። አክለዉ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ወደ መኖሪያ ቀዬአቸዉ መመለስ ያልቻሉ በርካታ ተፈናቃዮች ይገኛሉ ብለዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል