#አስደሳች #ዜና
#ሕብረቱ በከተማችን እና በሌሎች ከተሞች የሚያደርገዉን መልካም ተግባር አለማድነቅ አይቻልም።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የ2015 ዓ.ም የጌታችንና የመድኅኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል መታሰቢያን አስመልቶ ለተለያዩ ሰዎች ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም አድርጓል።
በዚህ ማዕድ የማጋራት ፕሮግራም፥ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ አራት ለሚገኙ 600 አባወራዎች ዘይት፥ዱቄት፥ፓስታና ማኮሮኒ የተከፋፈለ ሲሆን፥ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ለሚገኙ 100 አባወራዎች ደግሞ ለበዓል መዋያ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ አበርክቷል።
በስፍራው ተገኝተው ስጦታውን ያበረከቱት የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓ/ር ጻድቁ አብዶ፥ ድሆችን ማሰብ ተገቢና እግዚአብሔር የሚወደው መልካም ተግባር እንደሆነ አስታውሰው፥ ኅብረቱም እንዲህ ዓይነቱን ርዳታ በተደጋጋሚ እንዳደረገ፥ ይህን ተግባሩን ለወደፊት እንደሚቀጥል ገልጠው፥ በዓሉ የደስታ እንዲሆንም ምኞታቸውን ገልጠዋል።
Christian ዜማ Tube

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ለታማኙ_አገልጋይ_ቤት_እንስራ!!
በአገልግሎቱ ያልተባረከ ወይም በአገልግሎት ያልተጠቀመ በዝማሬው ያልተጽናና፣ ያልተባረከ የወንጌል አማኝ የለም። 8 ሙሉ አልበሞችና ከተለያዩ ዘማሪያን ጋር የተለያዩ ኮሌክሽኖችን ሰርቷል ላለፉት 35 አመታትም በዝማሬ አገልግሏል መጋቢ አገኘሁ ይደግ!!
በውጭ አገርና እዚህም አገር ውስጥ ባሉ ጥቂት ወዳጆቹ ተነሳሽነት 'ይህ የእግዚአብሔር ሰው ብዙ አመታት አገልግሏል ስለዚህም መኖሪያ ቤት የለውምና ቅዱሳን ተባብረን ቤት እንስራለት' ብለን ይህን ሐሳብ አመንጭተን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን። በአገራችን ሰው ተቸግሯል ታሟል ሲባል ብዙዎቻችን እንሯሯጣለን ያ ጥሩ ነው እጅግም አስፈላጊ ነው ነገር ግን ያገለገሉን ሰዎች ተቸግረዋል ሳይባል ለሚገባቸው እንዲህ ተባብረን በተለያዩ ክፍተቶቻቸው መቆምም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው። መጋቢ አገኘሁ እንዲህ ሆኛለሁ እንዲህ አድርጉልኝ ሳይል በኪራይ መኖሩን አይተን ይህን ቤት ለእርሱ የመስራህ እቅድ ይዘን መተናል። በውጪና በአገር ውስጥም ይህን የሚከታተሉ የመጋቢ አገኘሁ በቅርበት የሚያውቁ በኮሚቴ ደረጃ ጉዳዩን በመከታተል ላይ ናቸው።
በአገር ውስጥ ያላችሁ የተለያዩ ለዚህ አላማ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች የተዘጋጁ ሲሆን በአሜሪካ እና በካናዳ ላላችሁም ጎ ፈንድ ሚ (Gofund me) ተከፍቷል። ሁላችንም በመስጠት የሚገኝን በረከት እንድንካፈል ይህ አጋጣሚ ተዘጋጅቶልና በልባችን እንደሞላ ካለን በደስታ እናካፍል። እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
የጎ ፈንድ ሚና የባንክ አካውንቶቹ፦
https://gofund.me/bb1feb54
1000504436563 CBE
1011135483703 Brhan Bank
01347096661701 Awash Bank
ገነት በርሄ
አማረ በሻህ

#የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች ቄስ ሆነ።
ለማንቸስተር ዩናይትድ፣ ኖርዊች ሲቲ፣ ካርዲፍ ሲቲ የተጫወተው ፊል ሙልራይን እግር ኳስን እርግፍ አድርጎ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሆኗል።
ፊል ሙልራይን ይባላል ከ1999 ጀመሮ ከ150 በላይ ጨዋታዎችን አድርጓል።
ከ600 ሺህ ፓውንድ በላይ ደመወዝ ያገኝ የነበረው ተጫዋች፥ የፍቅር አጋሩን ካጣ በኋላ የእግር ኳስ ህይወቱ ደስታን እንዳልስጠው ነው የሚገልጸው።
እናም በሰሜን አየርላንዷ መዲና ቤልፋስት ወደሚገኘው ኪዩን ዩኒቨርሲቲ በመግባት ፍልስፍናን ለሁለት አመት አጠና።
ሙልራይን ዩኒቨርሲቲ ከመግባቱ በፊት የኖርዊች ተጫዋች እያለ ሃብትና ዝናው ደስታን ሊሰጡት እንዳልቻሉ ነው ለኖርዊች ክለብ ድረገጽ የተናገረው።
“ሁሉ ነገር እያለኝ በወጣትነት እድሜዬ እንዴት ደስታ ራቀኝ ስል እጠይቅ ነበር” የሚለው ተጫዋቹ፥ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ወደ እግር ኳስ አልተመለሰም።
ከእግር ኳስ ያላገኘውን ደስታ ወደ እምነቱ በመጠጋት ለማሳካት ወደ ካቶሊክ ቤተክርስቲያናት ደጋግሞ መመላለስን ተያያዘው።
በዚህም መንፈሳዊ እረፍትና ደስታን እያገኘ መምጣቱን የሚናገረው ተጫዋቹ በ2017ም በኮርክ ከተማ የምትገኘው የካቶሊክ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቄስ ሆኖ ለማገልገል ቅስና ተቀብሏል።
እግር ኳስን እርግፍ አድርጎ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ለመሆን አመታት ወስደውብኛል የሚለው የቀድሞው ኮከብ ፊል ሙልራይን፥ የእግር ኳስ ከፍ እና ዝቅ በመንፈሳዊው አለም የለም ባይ ነው። በወጣትነቱ ጫማ ያስቀለው መንፈሳዊ አገልግሎትም እረፍትና ደስታን እንደሰጠው ተናግሯል።
Al Ain Amharic አል ዐይን አማርኛ

#ሀልዎት
የሀልዎት አማኑኤል ህብረት ቤተክርስቲያን ከ ሦስት መቶ በላይ 7ተኛ ዙር ካልቸር የተማሩ አባላቶችን አስመርቃለች።
የምረቃ ስነስርአቱ በቢሾፍቱ ከተማ ጆርጋ ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በደማቅ ስነስርአት ተካሂዷል።
በዕለቱ የዝማሬ የትምህርት እንዲሁም የቃልኪዳን ፕሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን ለቤተክርስቲያኒቷ መሪዎች እና አገልጋዮች ከተመራቂዎች ስጦታዎች ተበርክተዋል።
ተመራቂዎች በአንድነት ማዕድ በመጋራት እና በመካከላቸዉ ከተገኙ የጫወታ አዘጋጅ ድርጅት አስተባባሪዎች ጋር በተለያዩ ጨዎታዎች እና ዉድድሮች አሳልፈዎል።

የቦረና እና አካባቢው ሲኖዶስ ምስረታ ተከናወነ።
የኢ/ወ/ቤ/መካነ ኢየሱስ 21ኛ የቤተክርስቲያኒቱ ዓቢይ ጉባኤ እንዲመሰረቱ ከተወሰኑ ሲኖዶሶች አንዱ የሆነው የቦረና እና አካባቢው ሲኖዶስ የምስረታ ጉባኤ እና ኮንፈረንስ ከጥር 04-07: 2015ዓ.ም በያቤሎ ከተማ ተካሂዷል።
በተደረገው የሲኖዶሱ ምስረታ ጉባኤም የሲኖዶሱ መሪዎች ምርጫ የተደረገ ሲሆን:
1. ቄስ ጋልጋሎ ቃሬ- የሲኖዶሱ ፕረዚዳንት:
2. ቄስ ጋልጋሎ ዳዳቻ: ምክትል ፕረዚዳንት:
3. አቶ ተከተል ንጋቱ አቃቤ ንዋይ በመሆን ተመርጠዋል።