The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የክርስቲያኖች_ስደት_ሊጨመር_ይችላል
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በፈረንጆቹ 2023 በአለም ዙሪያ የክርስቲያኖች ስደት ሊጨምር እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

"በቅርብ ዓመታት ውስጥ ስደት እየጨመረ መጥቷል። 2023 ያንን አዝማሚያ የሚቀጥል ይመስላል" ሲሉ አንድ የክርስቲያን አገልግሎት መሪ አስጠንቅቀዋል።

ሪሊዝ ኢንተርናሽናል የስደት ጉዳዮች ተከታታይ ድርጅት በጥናቱ በናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ኢራን ያለው ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት አማኞች ያለውን ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል ብሏል።

በናይጄሪያ በፉላኒ ታጣቂዎች የተገደሉት የክርስቲያኖች ቁጥር ከ6,000 በላይ ሲሆን ቦኩሃራም ጨምሮ የሚያደርሰው ጥቃት ጉዳቱን ከፍ እንደሚያደርግ አሳስቧል።

በተመሳሳይ በህንድ ክርስትያኖች ላይ በሂንዱ ብሔርተኞች እየተጠቁ ሲሆን ፀረ ለውጥ ሕጎችም በተለያዩ ግዛቶች እየተሰራጩ ሲሆን ይህም ብሄራዊ ህግ ሊተገበር የጊዜ ጉዳይ ነው ወደሚል ስጋት እንደሚያመራ እንደሆነ ተገልጿል።

የሪሌዝ ኢንተርናሽናል አጋር እንዳለው በኢራን በዚህ አመት በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት “በእርግጥ ተስፋ የቆረጡ የሌላ ዕምነት ተከታዮች ክርስቲያን እየሆኑ ነው” በዚህም ምክንያት ስደት ሊጨምር እንደሚችል ጥርጥር የለውም።
#እንኳን #ደስ #አላችሁ
#አገልጋይ #ዮናታን_አክሊሉ እና #ዶኢ እንኳን ደስ አላችሁ

#ሜላላ_ዮናታን አክሊሉ እቺን ምድር ተቀላቅላለች።
#ደስታችን_ወደር የለውም

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ስም እንኳን ደስ አላችሁ።
#አባቶች እየተወያዩ ነው።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙርያ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምንወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ጋር እየመከሩ ነው።

አባቶቹ በዋናነት በሀገራችን ሰላም እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል የነበረው የቀደመ አብሮ በጋራ የመኖር እሴታችንን ጠብቆ ከመሄድ አንጻር መከናወን ስለሚገባው ጉዳዮች እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተዕምነቶች መካከል የተከሰቱትን ፉክክር እና ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ አባቶች ውይይት እያደረጉ እንደሆነ የሃይማኖት ተቋማት በማህበራዊ ገጻቸው መጠሳቸው ይታወሳል።

የዛሬው ውይይትም የዚህ አንዱ ማሳያ ሲሆን አባቶች በውይይታቸው የደረሱበትን ውጤት በቀጣይ ተከታትለን ወደ እናንተ የምናቀርብ ይሆናል።
#በይቅርታ_ተጠናቋል

በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እየተካሄደ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

የጋራ ውይይት ጉባኤዉ ኦርቶዶስሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ ቤተ ክርስቲያንም ይቅርታውን በመቀበል ውይይቱን ተጠናቋል።

ወደፊትም  ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል ።
#ልደቱ -- #የለውጥ አብነቱ

የዚህ ምድር ቋጥኝ የደም ግብር ምሱ ነው፤ ድንጋዩ ሁሉ፥ አፈሩ ሁሉ ሲቀለብ የኖረው የአዳምን ልጆች የደም ዥረት ነው። የዓለማችን ቋሚ መልክ ጠብ ነው።

ከዚያች የገነት ደጅ ጠብና ሽሽት በኋላ ሰብአውያን ግጭትና ቁርሾ፥ሁካታና ቱማታ መታወቂያችን ሆኗል። የሰማይ መላእክት አፍ አድጧቸው ቢናገሩ ምን ይሉን ይሆን?

"ውይ ! እነዚያ ሁከተኞች፥ እኒያ የሰላም ባይተዋሮች፥እኒያ የጠብ ዐርበኞች፥ ወርቅ ሲሰጧቸው ጠጠር የሚወረውሩ ሞገደኞች"ሳይሉን አይቀርም።

እኔ የሰው ልጅ የምጣላው ባጣ፥ ዐናቴ ላይ ከበቀለው ጉተና ጋር፥ጉልበቴ ላይ ከፈረጠመው ሎሚ ጋር፥ከራሴውም ጋር ቢሆን ጠብ ማብቀሌ አይቀርም።

ቢርበኝ፥ ብጠግብም መዝናኛዬ ጠብ ነው። ታላላቅ መንግሥታት ፥ታናናሽ መንግሥታት ፥ የተማሩ ሕዝቦች፥ ማይማን ብሔረ ሰቦች፥ ሁሉም የሠለጠኑት ጠብ በመለኰስና ልኵሱን በማፋፋም ነው።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት የሰላም ልደት ነው።
"ስሙም ድንቅ መካር ፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል"....."ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፥ሰላምም በምድር".....ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጦር በተሰበቀበት፥ የፈረስ ኮቴ በጎደፈረው ምድር ላይ የሰላም ባንዲራ ተከለ።

ሃሌሉያ! መጀመሪያ ከአባቱ ጋር፥አያይዞም ከራሳችን፥ ከሰው ሁሉ ጋርም አስታረቀን። እርሱ የሰላም መንገድ ጠቋሚ ብቻ አይደለም፤ የሰላም ሰባኪም ብቻ አይደለም።" እርሱ ሰላማችን ነው።" በሰው ጥበብ ና ጉልበት የማይበቅል ሰላም ምንጭ ሆኖ ኢየሱስ ተወለደልን።

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሰን።

"መስተአየት"ገጽ 133/4

@ጋሽ ንጉሴ ቡልቻ
#የማርሲል_ቴሌቪዥን የ YouTube ቻናል ተዘግቷል።

ከ500 ሺህ በላይ ተከታዬች የነበረዉ የማር-ሲል ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሙሉ በሙሉ ከቁጥጥር ዉጪ እንደሆነ ታወቋል።

ይህ የተፈጠረዉ ባሳለፍነው ሰኞ ቢሆንም ተቋሙ ቻናሉን ለማስመለስ ከፍተኛ ረብረብ ሲያደርግ ቆይቶ ለጊዜው ከቁጥጥር ዉጪ መሆኑን በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው (Facebook) ላይ አሳዉቀዋል።

የተቋሙ የቀደመ ቻናላቸዉን በድጋሜ ማስተካከል እስከሚቻል ድረስ አዲስ በከፈትነው የዩቲዩብ አካውንታችን የተለያዩ ትምህርቶችን መዝሙሮችን አና ጸሎቶችን ማግኘት ይችላሉ።

https://www.youtube.com/channel/UC77n0Y0J-4ZDpZiFz8qQwvQ

ማር-ሲል ቴሌቨዥንን ምርጫችሁ ስላደረጋችሁ እናመሰግናለን!!
#አስደሳች_ዜና

የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ የሆነውን ሚሽነሪ ወደ ናይጄሪያ ላከች።

ቤተክርስቲያኒቱ በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ሃያ ሁለት ሙሉ ወንጌል አጥቢያ አባል የሆነውን ዶክተር ዮሐንስን የላከች ሲሆን በእለቱም የቤተ እምነቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ላኮ በያሶን ጨምሮ ምክትል ፕሬዚዳንትና የቤተ እምነቱ የግሎባል ሚሽን ቦርድ አባላት እንዲሁም የአጥቢያዋ አባላት በተገኙበት ጸሎት ተደርጎ ከቤተሰቡ ጋር ሽኝት ተደርጎለታል።

ይህ በቤተክርስቲያኒቱ የተደረገዉ ተግባር ጅማሬ እንደሆነ እና ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ ወንጌል ወዳልደረሰባቸዉ አከባቢዎች ሚስዬናዉያንን ለመላክ እየተሰራ እንደሆነም ተገልጿል።

በእለቱ የነበረዉን መረሀ ግብር ቤተክርስቲያን ወደ ዋናው ስራዋ እየተመለሰች እንደሆነ ማሳያ ነዉ ሲሉ ገልፀዉታል።

ከ150 ሺህ በላይ ሕዝብ በየቀኑ ጌታን እንደግል አዳኛቸው አድርገው ሳይቀበሉ እንደሚሞቱ ጥናቶች ያሳያሉ።

በ2022 ሪፖርት መሰረት ናይጄሪያ ለክርስትና አስቸጋሪ ከሚባሉ 50 ሀገራት መካከል እጅግ አስቸጋሪ በመባል በ7ኛ ስፍራ ትገኛልች።