The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#ሊቀ_ጳጳሱ_አርፈዋል

ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ኤሜራተስ ቤኔዲክት 16ኛ ባደረባቸው ሕመም በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቫቲካን ይፋ አድርጋለች።

የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ፣ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ክፉኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ገልጸው ምእመኑ እንዲጸልያላቸው ጠይቀው ነበር።
#እንኳን ደስ አለሽ

ተወዳጇ ዘማሪት ሀና ተክሌ በድጋሜ በThe Christian News - የክርስቲያን ዜና ስም እንኳን ደስ አለሽ።

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW
#የወንጌላውያን ቁጥር ጨምሯል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በፈረንሳይ የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ቁጥር ማደጉን ቀጥሏል።

የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ብሔራዊ ምክር ቤት (ሲኤንኤፍ) ያወጣው አዲስ አኃዛዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ለእያንዳንዱ 25,000 ነዋሪዎች አንድ ቤተ ክርስቲያን አለ።

ከአምስት ዓመታት በፊት ለ29,000 ነዋሪዎች አንድ ቤተ ክርስቲያን የነበረች ሲሆን በፈረንጆቹ በ2017 2,521 የነበረው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር ዛሬ ከ2,700 በላይ ደርሷል።

እንደ ሲኤንኤፍ ዘገባ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ከ800 በላይወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዳሉ ሲናገር ይህም ከ1970 ጀምሮ ከፍተኛ ጭማሪ ነው ተብሏል።

የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን (ፈረንሳይ) በ(530) ቁጥር ትልቁን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ድርሻ ይይዛል በመቀጠልም ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት በ(308) ቁጥር ቀሪውን ይይዛሉ።

በ2017፣ በመላው ፈረንሳይ እና በባህር ማዶ ግዛቶች 650,000 ወንጌላውያን ነበሩ። ዛሬ ይህ አሃዝ 745,000 ደርሷል።

እንደ ሲኤንኤፍ ዘገባ ከሆነ ቁጥሩ ከ1950 ጀምሮ በፈረንሳይ ወንጌላውያን በ15 እጥፍ ጭማሪ አሳይቷል።
ከCAC Ethiopia TV አዲስ አስደሳች ዜና እየመጣ ነው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ዝርዝሩን ይጠብቁ...
"ድመት ተፈወሰ እያሉ ሚድያ መውጣት ትክክል አይደለም።" ፓ/ር ቢንያም ዋሌ
****************************
"የኢትዮዽያ ህዝብ በዚህ ዘመን እንደተጨነቀ በዚህ ዘመን እንደተቸገረ መቼም እንዲህ ሆኗል ብዮ አላስብም::በአባቶች ዘመን ይሰራ የነበረው መንፈስ የምድሪቱን አየርዋን እንስሶችን እየፈወሰ ቢሆን ኖሮ የሰው ልጅ እንዲህ በጭንቅ ውስጥ ባልኖረ?ድመትዋን የፈወሰ ዘይት የምድራችንን ቀንበር ቢሰብር ለምስጋና ይሆናል:: ይህንን ቀልድ የመቀበል ስብዕና የለኝም።

ወንድምን መሸሸግ መልካም ነው::ነገር ግን ለህዝብ የሚተላለፍን ነገር መምረጥ አስፈላጊ ነው::ትክክል ያልሆነ ነገር ትክክል አይደለም መባሉ ለእርማት ይጠቅማል::"

ፓ/ር ቢንያም ድመት ፈወስን እያለ ሚድያ ላይ ለወጣው ነብይ ሄኖክ ግርማ ጂፒስ JPS ቲቪ የሠጠው ሚላሽ ሁላችንንም የሚያስማማ ይመስለኛል።
#ይቅርታ 🙏 #ሰሞኑን_በለቀኩት_የድመት_ቪዲዮ_ዙሪያ 🐈
👉 #ነብይ ሔኖክ ግርማ ይህን ብሏል...

ሰሞኑን በዩትዩብ ቻናላችን ስለተለቀቀው የድመትዋ ምስክርነት ጌታ የሰራው ድንቅ ስራ ቢሆንም የእህታችንም ደስታ ደስ ብሎን ደግሞም “ጻድቅ ሰው ለእንስሳቱ ይራራል፤ ክፉዎች ራሩ ቢባል እንኳ ዞሮ ዞሮ ሥራቸው ጭካኔ ነው።

"ምሳሌ 12 : 10 በሚለው የአምላካችን ቃል ክፋ ስላልሆን እንጂ ለጌታም ምንም ከመምጣቱ በፊት እድሜያችንን ለሰጠንለት ወንጌል ክብርና ፍቅር አጥተን አይደለም::

ቢሆንም በዚህ ምክንያት ያሳዘንነውን ሁሉ ይቅርታ እንጠይቃለን!
JPS TV WORLDWIDE

"እኔ ግን እጅግ በጣም የሚገርመኝ የመሪዎቹ ሳይሆን የምዕመናኑ ነው። አንዳንድ መሪዎች ጥፋታቸውን አምነው እንዲህ ይቅርታ ሲጠይቁ ምዕመናን ግን ዛሬም ባሉበት ናቸው። ይመቻቸው" (የግል ሃሳብ)
#የክርስቲያኖች_ስደት_ሊጨመር_ይችላል
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በፈረንጆቹ 2023 በአለም ዙሪያ የክርስቲያኖች ስደት ሊጨምር እንደሚችል አንድ ጥናት አመለከተ።

"በቅርብ ዓመታት ውስጥ ስደት እየጨመረ መጥቷል። 2023 ያንን አዝማሚያ የሚቀጥል ይመስላል" ሲሉ አንድ የክርስቲያን አገልግሎት መሪ አስጠንቅቀዋል።

ሪሊዝ ኢንተርናሽናል የስደት ጉዳዮች ተከታታይ ድርጅት በጥናቱ በናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ኢራን ያለው ሁኔታ ከሌሎች ሀገራት አማኞች ያለውን ሁኔታ አጉልቶ ያሳያል ብሏል።

በናይጄሪያ በፉላኒ ታጣቂዎች የተገደሉት የክርስቲያኖች ቁጥር ከ6,000 በላይ ሲሆን ቦኩሃራም ጨምሮ የሚያደርሰው ጥቃት ጉዳቱን ከፍ እንደሚያደርግ አሳስቧል።

በተመሳሳይ በህንድ ክርስትያኖች ላይ በሂንዱ ብሔርተኞች እየተጠቁ ሲሆን ፀረ ለውጥ ሕጎችም በተለያዩ ግዛቶች እየተሰራጩ ሲሆን ይህም ብሄራዊ ህግ ሊተገበር የጊዜ ጉዳይ ነው ወደሚል ስጋት እንደሚያመራ እንደሆነ ተገልጿል።

የሪሌዝ ኢንተርናሽናል አጋር እንዳለው በኢራን በዚህ አመት በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት “በእርግጥ ተስፋ የቆረጡ የሌላ ዕምነት ተከታዮች ክርስቲያን እየሆኑ ነው” በዚህም ምክንያት ስደት ሊጨምር እንደሚችል ጥርጥር የለውም።
#እንኳን #ደስ #አላችሁ
#አገልጋይ #ዮናታን_አክሊሉ እና #ዶኢ እንኳን ደስ አላችሁ

#ሜላላ_ዮናታን አክሊሉ እቺን ምድር ተቀላቅላለች።
#ደስታችን_ወደር የለውም

The Christian News - የክርስቲያን ዜና ስም እንኳን ደስ አላችሁ።
#አባቶች እየተወያዩ ነው።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙርያ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱምንወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖትን በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ጋር እየመከሩ ነው።

አባቶቹ በዋናነት በሀገራችን ሰላም እና በሃይማኖት ተቋማት መካከል የነበረው የቀደመ አብሮ በጋራ የመኖር እሴታችንን ጠብቆ ከመሄድ አንጻር መከናወን ስለሚገባው ጉዳዮች እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተዕምነቶች መካከል የተከሰቱትን ፉክክር እና ተገቢ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ አባቶች ውይይት እያደረጉ እንደሆነ የሃይማኖት ተቋማት በማህበራዊ ገጻቸው መጠሳቸው ይታወሳል።

የዛሬው ውይይትም የዚህ አንዱ ማሳያ ሲሆን አባቶች በውይይታቸው የደረሱበትን ውጤት በቀጣይ ተከታትለን ወደ እናንተ የምናቀርብ ይሆናል።