The Christian News
5.09K subscribers
3.65K photos
50 videos
908 links
ይህ The Christian News ነዉ። ከመላዉ አለም ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስትያን ዜናዎች ይቀርቡበታል ከወደዱት ይቀላቀሉት።

@TCNEW
Download Telegram
#የክርስቲያን_ሚዲያዎች_ጉባኤ

የእስራኤል 6ኛው የክርስቲያን ሚዲያ ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተካሄዷል።

በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ከ28 ሀገራት የተወጣጡ 150 የሚደርሱ
ከፍተኛ የክርስቲያን የዜና ስራ አስፈፃሚዎችን እና በአለም ዙሪያ ያሉ ታዋቂ የክርስቲያን ሚዲያዎች መስራቾች እና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የሚዲያ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።

ለአራት ቀናት የሚቆየው የመሪዎች ጉባኤ ከክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር የበለጠ ትብብር ለመፍጠር እና ከእስራኤል ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2017 የተጀመረው ይህ ጉባኤ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ተሰብሳቢዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥት ትልቅ የድንጋይ መዋቅር የዳዊትን ከተማ ጎብኝተዋል።

የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ኃላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ከኢትዮጵያ እንደተሳተፉ ታውቋል።

በነገራችን ላይ በሀገራችን ቁጥራቸው 40 የሚደርሱ የመንፈሳዊ (ወንጌላውያን ክርስቲያን) ሚዲያዎች ቢኖሩም አንድም በጉባኤው ላይ መገኘት የሚያስችል አቋማ ያለቸው ሚዲያ ስለመኖራቸው የሚታወቅ ነገር የለም።

ይህ የሚዲያ ጋጋታ እንጂ የተሻለ ሚዲያ እንደሌለን እና ይህንን ለመፍጠር ትልቅ የቤት ስራ እንዳለብን የሚያሳይ ነው።
እስራኤል ዳንሳ ነኝ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ከ100 ሺሕ ብር በላይ የተቀበለዉ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

እስራኤል ዳንሳ ነኝ በሚል የሀይማኖት ሽፋን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ከቤንች ሸኮ፣ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እና ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ነዋሪ ከሆኑት ግለሰቦች ከ100 ሺሕ ብር በላይ የተቀበለዉ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ግለሰቡ የግል ተበዳይን ማንነት በማጥናትና ስልክ በመደወል ራሱን የፀሎት ሰዉ በማስመሰል ልጅህ በቅርብ ቀን ወደ ካናዳ እንድትሄድ ፀሎት አድርጌያለሁ የተጀመረውን ህንፃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ አድርጉልኝ በማለት፤ በመጀመሪያ ዙር 30 ሺሕ ብር በባንክ ቁጥሩ ከግል ተበዳይ ገቢ ማስደረጉ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከሌሎች አራት ሰዎች ማንነትና የስራ ቦታን ጥናት በማድረግ ስልክ በመደወል የሃይማኖት መሪ እስራኤል ዳንሳ ነኝ በማለትና የተለያዩትን የተሳሰቱ ምልዕክቶችን  ለሰዎች በማስተላለፍ 109 ሺሕ 500 ብር የማታላል ወንጀል ሲፈፅም ከህብረተሰቡ በደረሰው  ጥቆማ መሠረት በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የቤንቺ ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ የታክቲክ ምርመራ ባለሞያ ሳጅን ደመላሽ አስፋዉ ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የማታለል ወንጀል የተፈፀመባቸው ግለሰቦች መረጃውን በፍጥነት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ክስ እንዲመሰርቱ ጥሪ ያቀረበው ፖሊስ፤ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

#አዲስ_ማለዳ
#ሊለቀቅ_ነዉ

የተወዳጁ ዘማሪ ግርማ አዴቦን "ጆሪን ጋጋቡክስዮ" ነጠላ ዝማሬ ነገ ይለቀቃል።

ተወዳጆቹ ዘማሪ ተስፋዬ ግርማ እና ዘማሪት የምስራች አብረሃም የተሳተፉበት ዝማሬ ወደ እናንተ ሊደርስ ነዉ።

ነገ አርብ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በሆሳዕና ፕሮዳክሽን ዮቲዮብ ቻናል ይጠብቁ።

ሊንኩን በመንካት ቻናሉን Subscribe በማድረግ ተደምጠዉ የማይጠገቡ ዝማሬዎችን ይከታተሉ። https://youtu.be/_AqGaf1Doa8
#ሕብረቱ_አስቸኳይ_መግለጫ_እየሰጠ_ነዉ
#በዮናታን_አክሊሉ ጉዳይ መግለጫ እየተሰጡ ነወ።

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከሰሞኑ በአንዳንድ በቤተዕምነት መሪዎች መካከል የነበረዉን ዉዝግብ አስመልክቶ ቦርዱ የደረሰበትን ዉሳኔ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነዉ።

ጋዜጣዊ መግለጫዉን የሕብረቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ እና የሕብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ሰንበቶ በሼ በጋራ እየሰጡ ይገኛል።

መሪዎቹ በመግለጫቸው ከሰሞኑ የተፈጠረዉ ጉዳይ ወደ ከፍተኛ አመራሮች ድረስ ስለተጓዘ በጉዳዩ ዙሪያ የሕብረቱን አቋም እና የቦርዱን ወሳኔ ልናሳዉቅ ተገደናል ብለዋል።

በሕብረቱ ዉስጥ የሚገኙ አባል ቤተዕምነቶች ከአካሔድ ዉጪ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ እንደ መሪዎች እንገስፃለን ነገር ግን ጠቅልሎ ሁሉንም ወንጌላውያን አላግባብ ቃላትን መናገር ተገቢ አይደለም ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዉስጥ በጋራ ለመስራት ስንስማማ እንደዚህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ በጋራ ለመነጋገር እንደሆነ የጠቆሙት መሪዎች በወቅቱ ሌሎቹ መሪዎች ተነጋግረው ቀሩ በሚል የተላለፈው መልዕክት የተሳሳተ እንደሆነ ተናግረዋል።

The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መግለጫውን እየተከታተልን ሲሆን ዝርዝር ሙሉ መግለጫውን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።
#ሊቀ_ጳጳሱ_አርፈዋል

ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ኤሜራተስ ቤኔዲክት 16ኛ ባደረባቸው ሕመም በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቫቲካን ይፋ አድርጋለች።

የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ፣ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ክፉኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ገልጸው ምእመኑ እንዲጸልያላቸው ጠይቀው ነበር።
#እንኳን ደስ አለሽ

ተወዳጇ ዘማሪት ሀና ተክሌ በድጋሜ በThe Christian News - የክርስቲያን ዜና ስም እንኳን ደስ አለሽ።

አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/TCNEW
#የወንጌላውያን ቁጥር ጨምሯል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና

በፈረንሳይ የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ቁጥር ማደጉን ቀጥሏል።

የወንጌላውያን ክርስቲያኖች ብሔራዊ ምክር ቤት (ሲኤንኤፍ) ያወጣው አዲስ አኃዛዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ለእያንዳንዱ 25,000 ነዋሪዎች አንድ ቤተ ክርስቲያን አለ።

ከአምስት ዓመታት በፊት ለ29,000 ነዋሪዎች አንድ ቤተ ክርስቲያን የነበረች ሲሆን በፈረንጆቹ በ2017 2,521 የነበረው የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር ዛሬ ከ2,700 በላይ ደርሷል።

እንደ ሲኤንኤፍ ዘገባ ከሆነ በአሁኑ ሰዓት ከ800 በላይወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት እንዳሉ ሲናገር ይህም ከ1970 ጀምሮ ከፍተኛ ጭማሪ ነው ተብሏል።

የጉባኤ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን (ፈረንሳይ) በ(530) ቁጥር ትልቁን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ድርሻ ይይዛል በመቀጠልም ገለልተኛ አብያተ ክርስቲያናት በ(308) ቁጥር ቀሪውን ይይዛሉ።

በ2017፣ በመላው ፈረንሳይ እና በባህር ማዶ ግዛቶች 650,000 ወንጌላውያን ነበሩ። ዛሬ ይህ አሃዝ 745,000 ደርሷል።

እንደ ሲኤንኤፍ ዘገባ ከሆነ ቁጥሩ ከ1950 ጀምሮ በፈረንሳይ ወንጌላውያን በ15 እጥፍ ጭማሪ አሳይቷል።
ከCAC Ethiopia TV አዲስ አስደሳች ዜና እየመጣ ነው። ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ዝርዝሩን ይጠብቁ...